4 months ago
አሰልጣኝ አሊዮ ሲሴ ከሊቢያ ብሔራዊ ቡድን ጋር መለያየታቸውን ገለጹ
#ethiopia | የቀድሞው የሴኔጋል ብሔራዊ ቡድን ስኬታማ አሰልጣኝ አሊዮ ሲሴ፣ በሊቢያ ብሔራዊ ቡድን የነበራቸውን የአንድ ዓመት ቆይታ በይፋ ማጠናቀቃቸው ታውቋል።
ባለፉት 12 ወራት የሊቢያን "የሜዲትራኒያን ፈረሰኞች" ሲመሩ የቆዩት ሲሴ፣ ቡድኑን በአስር ጨዋታዎች ላይ መርተዋል።
አሊዮ ሲሴ ከሊቢያ ጋር መለያየታቸውን ተከትሎ፣ ስማቸው ከሌላኛው የአፍሪካ ግዙፍ ተገዳዳሪ ጋና (ጥቁር ከዋክብት) ጋር በስፋት እየተያያዘ ይገኛል።
ሲሴ ሴኔጋልን ለረጅም ዓመታት በመምራትና የአፍሪካ ዋንጫን በማንሳት የነበራቸው ልምድ፣ ለጋና ብሔራዊ ቡድን ትልቅ ግብዓት ሊሆን ይችላል ተብሎ ይጠበቃል።
አሊዮ ሲሴ በተለይ በሴኔጋል ብሔራዊ ቡድን ለ9 ዓመታት በቆዩበት ወቅት ለሀገራቸው የመጀመሪያውን የአፍሪካ ዋንጫ በማምጣት ትልቅ ታሪክ የሰሩ ድንቅ አሰልጣኝ መሆናቸው ይታወሳል።
አሁን ደግሞ አዲስ ፈተና ፍለጋ ወደ ጋና የሚያደርጉት ጉዞ እውን ይሆን እንደሆን ወደፊት የሚታይ ይሆናል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #alioucisse #libyafootball #ghanablackstars #africanfootball #soccernews #senegal #footballcoach

Comments