በአለም አቀፍ ደረጃ ሲፈለግ የነበረው አደገኛ የሰው አዘዋዋሪ በቁጥጥር ስር ዋለ
#ethiopia | በኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ እና በዓለም አቀፉ የጸጥታ መረጃ ትብብር (ROCK) በተደረገ የተቀናጀ ኦፕሬሽን፣ ለዓመታት ሲፈለግ የነበረው አደገኛ የሰው አዘዋዋሪ ይትባረክ ዳዊት (ክብሮም) በትግራይ ክልል ሽረ ከተማ በቁጥጥር ስር ውሏል።
ይህ ግለሰብ በስዊድን፣ ሱዳን፣ ጅቡቲ እና ኬንያ ጨምሮ በተለያዩ ሀገራት ክብሮም፣ ሙኒር፣ አድሀኖም እና አህመድ የተባሉ የሀሰት ስሞችን በመጠቀም ወንጀሉን ሲያስፋፋ የቆየ ሲሆን፣ ከእርሱ ጋር ዘጠኝ ግብረ-አበሮቹም አብረው ተይዘዋል።
ከ2010 ዓ.ም ጀምሮ ከኢትዮጵያ፣ ሱዳን፣ ኤርትራ፣ ጅቡቲ፣ ኬንያ እና ሶማሊያ የተወጣጡ ከ3,000 በላይ ወጣቶችን ለከፍተኛ ስቃይ ዳርጓል።
በህገ-ወጥ ዝውውሩ ምክንያት የ100 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ፣ በ50 ሴቶች ላይ ደግሞ የአስገድዶ መድፈር ወንጀል ተፈጽሟል።
ወንጀለኞቹ ተጎጂዎችን ሊቢያ ውስጥ በሚገኙ 5 መጋዘኖች በማገትና ቤተሰቦችን በማስፈራራት ከ3 ቢሊዮን ብር በላይ ሲያንቀሳቅሱ እንደነበር ተደርሶበታል።
የፌደራል ፖሊስ የምርመራ መዝገቡን ለማጠናከር በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገራት (ሊቢያ፣ ቤልጂየም፣ ካናዳ እና እንግሊዝን ጨምሮ) ከሚገኙ 100 በላይ ምስክሮች ቃል ተቀብሏል። በአሁኑ ወቅት የተጠርጣሪዎቹ የባንክ ሂሳብና ንብረት የታገደ ሲሆን፣ መዝገቡ ለዓቃቤ ሕግ መላኩ ተገልጿል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ethiopia #federalpolice #humantrafficking #justice #shire #internationalcrime #news #update

2 months ago