Logo
SeledaPost
ግብፅ እና ኢትዮጵያ ሳይስማሙ ቀሩ

በኢትዮጵያ አዘጋጅነት ለአራት ቀናት በአዲስ አበባ ሲካሄድ የቆየው 22ኛው የምስራቅ አፍሪካ የኃይል ትስስር የሚኒስትሮች ምክር ቤት እና 37ኛው የአስተባባሪ ኮሚቴ አስቸኳይ ልዩ ጉባዔ ዛሬ ተጠናቋል።

ጉባዔው ያስፈለገው ግብፅና ሊቢያ ጨምሮ 13 አባል ሀገራት ያሉት ትስስሩ የመበታተን አደጋ የተጋረጠበት በመሆኑ ነው፡፡

አባል ሀገራቱን ከመበታተን ለመታደግ የህግ ማዕቀፎችን በማሻሻልና ማጠናከር ማስፈለጉን የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ኢንጂነር ሀብታሙ ኢተፋ ገልጸዋል።

በጉባዔው አዲስ የሚመሰረተው የኤሌክትሪክ ኃይል የገበያ ማዕከል ዋና መቀመጫን ለመወሰን ውይይት ተደርጓል፡፡

በዚህ አጀንዳ ኢትዮጵያ ከድርጅቱ አባል ሀገራት ብቸኛ የኃይል አቅራቢ እንደመሆኗ ለአራት ቀናት በዘለቀው የትስስሩ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ስብሰባ ከፍተኛ ሙግት ማካሄዱ ተገልጿል፡፡

በተለይም ከግብፅ ጋር  የገበያ ማዕከሉ ኢትዮጵያ መሆን አለበት በሚለው ሃሳብ ከፍተኛ ሙግት መደረጉን ኢንጂነር ሃብታሙ ገልፀዋል።

በዚሁ ጉዳይ የግብፅ ተወካዮች ማዕከሉ ወደ ካይሮ ካልሆነ በሚል የያዙት አቋም ከኢትዮጵያ ጋር ከመግባባት ሳይደርሱበት ጉባዔው ተጠናቋል።

Seledadotio
Seledadotio
26 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.