4 months ago
ዘመኑን የዋጀው ፌዴራል ፖሊስ፤ ከሀገራዊ ሪፎርም እስከ ድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎች መከላከል ስኬት
***************
የሀገራችንን ታሪክና ልዕልና የሚመጥን ዘመናዊ የፖሊስ ተቋም ለመገንባት የተጀመረው ሀገራዊ ሪፎርም፣ የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስን ወንጀልን አስቀድሞ የመከላከል ቁመና ወደ ላቀ ደረጃ አሸጋግሮታል።
የፌዴራል ፖሊስ ጠቅላይ አዛዥ ኮሚሽነር ጄኔራል ደመላሽ ገብረሚካኤል እንደገለጹት፤ ተቋሙ የሀገራዊ ለውጡን ተከትሎ ባካሄደው ጥልቅ የሪፎርም ትግበራ አሁን ላይ ዘመኑን የዋጀና ውጤታማ ተግባራትን የሚያከናውን ጠንካራ አቅም መገንባት ችሏል።
ይህ አዲስ ተቋማዊ ቁመናም ፖሊስ ከተለዋዋጭ ሁነቶች እና ከዲጂታሉ ዓለም ፈጣን ዕድገት ጋር እኩል እንዲጓዝ ትልቅ አቅም የፈጠረለት ሲሆን፣ በተለይም በዓለም አቀፍና ድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎችን በመከላከል ረገድ በርካታ ስኬታማ ተግባራትን ለማስመዝገብ እንዳስቻለው ተናግረዋል።
ተቋሙ በስኬት ከተወጣቸው ተልዕኮዎች መካከል በየአቅጣጫው መረባቸውን ዘርግተው በሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር ላይ ተሰማርተው የነበሩ በርካታ ተጠርጣሪዎችን ከነመሪዎቻቸው እጅ ከፍንጅ በመያዝ ለሕግ ማቅረቡ ዋነኛው መሆኑን ኮሚሽነሩ አንስተዋል።
መሰል የደህንነት ስጋቶች በስፋት የሚከሰቱባቸውን ቀጣናዎች በመለየት ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑን ያመለከቱት ኮሚሽነር ጄኔራል ደመላሽ፤ የብዙ ዜጎችን ሕይወት እየቀጠፈ በሚገኘው በዚህ ሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር ላይ ፖሊስ በቁርጠኝነት ያከናወነው ተግባር በተለያዩ ዓለም አቀፍ ተቋማት ዘንድ ከፍተኛ አድናቆትና ዕውቅና የተቸረው መሆኑን አብራርተዋል።
በዚህም የተነሳ ተቋሙ ከኢትዮጵያ አልፎ በዓለም አቀፍ ወንጀሎች ቁጥጥር ዙሪያ አይተኬ ሚናውን እየተወጣ እንደሚገኝ ነው ያመላከቱት።
የወንጀል ድርጊቶች ከጊዜ ወደ ጊዜ እየረቀቁና በቴክኖሎጂ የታገዙ እየሆኑ ቢመጡም፣ ፌዴራል ፖሊስ በዛው ልክ ዘመናዊ ቴክኖሎጂንና ስልታዊ አደረጃጀትን በመጠቀም አቅሙን በከፍተኛ ደረጃ እያጠናከረ እንደሚገኝ መግለጻቸውን የፌዴራል ፖሊስ መረጃ ያመላክታል።
በዘርፉ ከሚሰሩ ዓለም አቀፍ ተቋማት ጋር በቅንጅትና በጋራ መሥራት መቻሉ የተቋሙን ተጽዕኖ፣ ተአማኒነትና ተደራሽነት ይበልጥ ከፍ እንዳደረገው የገለጹት ኮሚሽነር ጄኔራሉ፤ ወደፊትም ዘመኑን በዋጀ መንገድ የሕግ የበላይነትን የማስከበር፣ የዜጎችን ደህንነት የማረጋገጥና የሀገርን ሰላም ዘላቂ የማድረግ ስልታዊ ተልዕኮው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቀዋል።
#federalpolice #ethiopia #institutionalreform #bordersecurity #ethiopianbroadcastingcorporation

5 months ago
ፌደራል ፖሊስ ምስራቅ ፈጥኖ ደራሽ ማዕከል በድሬዳዋ ከተማ ተመረቀ
*************
በምስራቅ ኢትዮጵያ ያለውን የሰላምና ደህንነት ስራ ይበልጥ ለማጠናከር የሚያግዘው የፌደራል ፖሊስ ምስራቅ ፈጥኖ ደራሽ ማዕከል በፌደራል ፖሊስ ጠቅላይ አዛዥ ኮሚሽነር ጄነራል ደመላሽ ገብረሚካኤል ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት ሆኗል።
ለተለያዩ የፀጥታና የደህንነት ሥራ እንቅስቃሴዎች ምቹ ተደርጎ በሁለት ዓመት ጊዜ ውስጥ ተገንብቶ የተጠናቀቀው ይህ ማዕከል የፖሊስ አባላት ማዘዣ ጣቢያዎችን፣ ዶርሚተሪዎችን፣ ዘመናዊ ቢሮዎችን፣ የእንግዳ ማረፊያዎችን እና የጤና ማዕከልን ያካተተ ነው።
በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ ላይ ንግግር ያደረጉት ኮሚሽነር ጄነራል ደመላሽ ገብረሚካኤል ድሬዳዋን ጨምሮ አካባቢው የታላቋ ኢትዮጵያ ዋነኛ የወጪ ገቢ ንግድ እና የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ የሚስተናገድበት ስትራቴጂካዊ ቀጣና መሆኑን ገልጸዋል።
በመሆኑም የማዕከሉ በዚህ ሥፍራ መገንባት አሸባሪዎችን እና ፀረ-ሰላም ኃይሎችን ቀድሞ በመቆጣጠር ሰላምና ደህንነትን በአስተማማኝ ሁኔታ ለማረጋገጥ እንዲሁም በምስራቁ የሀገራችን ክፍል ነጻ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ እንዲሰፍን ለማድረግ ወሳኝ መሆኑን አስገንዝበዋል።
ጠቅላይ አዛዡ አክለውም፣ ማዕከሉ የወንጀል ምርመራ ኃይልን ለማጠናከርና የተሰጡ ተልዕኮዎችን በብቃት ለመፈጸም የሚኖረው ፋይዳ የጎላ መሆኑን ጠቅሰዋል።
የፌደራል ፖሊስ በሁሉም የሀገራችን ማዕዘናት ላይ መሰል ዘመናዊ ማዕከሎችን በመገንባት ለሰላም መረጋገጥ በቁርጠኝነት እንደሚሰራ አጽንኦትም ሰጥተዋል።
በምረቃ መርሐ ግብሩ ላይ የተገኙት የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ከድር ጁሀር በበኩላቸው፣ የሀገር ሰላምና ደህንነት እንዲረጋገጥ እንዲሁም ዜጎች በነፃነት ወጥተው እንዲገቡ የፌደራል ፖሊስን ጨምሮ የሌሎች የፀጥታ አካላት ሚና ከፍተኛ እና የሚደነቅ መሆኑን ተናግረዋል።
ከንቲባ ከድር ጁሀር አዲስ የተገነባው የፈጥኖ ደራሽ ማዕከል ከድሬዳዋ ከተማ ባለፈ አጠቃላይ ለምስራቁ የሀገራችን ክፍል ደህንነት መረጋገጥና ለህዝቡ አስተማማኝ ከለላ ለመስጠት ያለው ፋይዳ እጅግ የጎላ እንደሆነ ገልጸዋል።
በቴዎድሮስ ታደሰ
#diredawa #federalpolice #peaceandsecurity #ethiopia #ethiopianbroadcastingcorporation

የንግድ ባንክ ሰራተኛዋን በአሰቃቂ ሁኔታ ገድሎ የተሰወረው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለ
#ethiopia | በሰንዳፋ በኬ ከተማ ነዋሪ እና በአሌልቱ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ ሰራተኛ የነበሩትን ወይዘሮ አዳነች ኩምሳን ህይወት ካለፈው ታህሳስ ወር ጀምሮ በአሰቃቂ ሁኔታ በመቅጠፍ ሲፈለግ የነበረው ተጠርጣሪ ፀጋዬ አሳልፈው በደብረ ብርሃን ከተማ ተያዘ።
ግለሰቡ ግድያውን የፈጸመው ታህሳስ 6 ቀን 2018 ዓ.ም ምሽት ላይ ከሟች ጋር በሆቴል ውስጥ ምግብ ሲመገቡ በተፈጠረ አለመግባባት መሆኑ ተገልጿል።
ሟች ተጠርጣሪውን ትታ በመሄዷ ምክንያት ተከትሏት በመሄድ መኪና ውስጥ ካስገባት በኋላ ጎማጣ ተብሎ በሚጠራው ስፍራ በሽጉጥ በመተኮስ ህይወቷ እንዲያልፍ ማድረጉ በፖሊስ የምርመራ መዝገብ ተመልክቷል።
ወንጀሉን ከፈጸመ በኋላ አስክሬኗን ጥሎ በመሰወሩ የሟች አካል በዱር አራዊት ተበልቶ ጭንቅላቷ ብቻ ሊገኝ ችሏል።
ተጠርጣሪው ግድያውን የፈጸመበትን መኪና እና መሳሪያ አሌልቱ ከተማ ውስጥ ጥሎ የተሰወረ ቢሆንም ፖሊስ በመኪናው ውስጥ ባገኘው የደም ዱካ እና በሽጉጡ አማካኝነት ክትትል ሲያደርግ ቆይቷል።
የፌዴራል ፖሊስ ከብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት እና ከሌሎች የፀጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት ባደረገው ኦፕሬሽን ግለሰቡን በቁጥጥር ስር ለማዋል ተችሏል።
ተጠርጣሪው በደብረ ብርሃን፣ በከሚሴ፣ በሸዋ ሮቢትና በአጣዬ ከተሞች ውስጥ የተለያዩ የሐሰት መታወቂያዎችን በመጠቀም እንደ ሰላማዊ ሰው ሲንቀሳቀስ እንደነበር ተደርሶበታል።
ፖሊስ በአሁኑ ወቅት በተጠርጣሪው ላይ ጥብቅ ምርመራ እያደረገ የሚገኝ ሲሆን ወንጀል ፈጽሞ ከህግ ማምለጥ እንደማይቻል አስታውቋል።
ለተጠርጣሪው መያዝ ትብብር ላደረጉ አካላትም ምስጋና ቀርቧል።
#justice #police #crime #federalpolice #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

6 months ago
በአለም አቀፍ ደረጃ ሲፈለግ የነበረው አደገኛ የሰው አዘዋዋሪ በቁጥጥር ስር ዋለ
#ethiopia | በኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ እና በዓለም አቀፉ የጸጥታ መረጃ ትብብር (ROCK) በተደረገ የተቀናጀ ኦፕሬሽን፣ ለዓመታት ሲፈለግ የነበረው አደገኛ የሰው አዘዋዋሪ ይትባረክ ዳዊት (ክብሮም) በትግራይ ክልል ሽረ ከተማ በቁጥጥር ስር ውሏል።
ይህ ግለሰብ በስዊድን፣ ሱዳን፣ ጅቡቲ እና ኬንያ ጨምሮ በተለያዩ ሀገራት ክብሮም፣ ሙኒር፣ አድሀኖም እና አህመድ የተባሉ የሀሰት ስሞችን በመጠቀም ወንጀሉን ሲያስፋፋ የቆየ ሲሆን፣ ከእርሱ ጋር ዘጠኝ ግብረ-አበሮቹም አብረው ተይዘዋል።
ከ2010 ዓ.ም ጀምሮ ከኢትዮጵያ፣ ሱዳን፣ ኤርትራ፣ ጅቡቲ፣ ኬንያ እና ሶማሊያ የተወጣጡ ከ3,000 በላይ ወጣቶችን ለከፍተኛ ስቃይ ዳርጓል።
በህገ-ወጥ ዝውውሩ ምክንያት የ100 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ፣ በ50 ሴቶች ላይ ደግሞ የአስገድዶ መድፈር ወንጀል ተፈጽሟል።
ወንጀለኞቹ ተጎጂዎችን ሊቢያ ውስጥ በሚገኙ 5 መጋዘኖች በማገትና ቤተሰቦችን በማስፈራራት ከ3 ቢሊዮን ብር በላይ ሲያንቀሳቅሱ እንደነበር ተደርሶበታል።
የፌደራል ፖሊስ የምርመራ መዝገቡን ለማጠናከር በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገራት (ሊቢያ፣ ቤልጂየም፣ ካናዳ እና እንግሊዝን ጨምሮ) ከሚገኙ 100 በላይ ምስክሮች ቃል ተቀብሏል። በአሁኑ ወቅት የተጠርጣሪዎቹ የባንክ ሂሳብና ንብረት የታገደ ሲሆን፣ መዝገቡ ለዓቃቤ ሕግ መላኩ ተገልጿል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ethiopia #federalpolice #humantrafficking #justice #shire #internationalcrime #news #update

Sponsored by
Surafel
8 months ago
የፌደራል ፖሊስ ለግማሽ ክፍለ ዘመን የተጠቀመበትን የታርጋ ስርዓት በዲጂታል ሊተካ ነው
#ethiopia | የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ላለፉት 50 ዓመታት ሲጠቀምበት የቆየውን የተሽከርካሪ ሰሌዳ (ታርጋ) በመቀየር፣ በቴክኖሎጂ የተደገፈ አዲስ አሰራር ይፋ ማድረጉን አስታወቀ። ተቋሙ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ መሰረት፣ ይህ ለውጥ የቀድሞውን ወጥነት የጎደለው አሰራር በማስቀረት ዘመናዊ የክትትል ስርዓት ለመዘርጋት ያለመ ነው።
ለምን ለውጥ አስፈለገ?
የፌደራል ፖሊስ የሎጂስቲክ መምሪያ ዋና መምሪያ ኃላፊ ረዳት ኮሚሽነር እሸቱ ፊጣ እንደገለጹት፣ ነባሩ የታርጋ ስርዓት፦
* ቀለምና ቁጥርን ብቻ የያዘ በመሆኑ ለሐሰተኛ (ፎርጅድ) ስራዎች የተጋለጠ ነበር።
* ወጥ የሆነ ቁጥጥር ለማድረግ ምቹ አልነበረም።
የአዲሱ ታርጋ ልዩ መለያዎች
አዲሱ የታርጋ ስርዓት ከድሮው በተለየ መልኩ
የሚከተሉትን ይዟል፦
* የተቋሙ ሎጎ፡ የፌደራል ፖሊስን መለያ ምልክት አካቷል።
* ሚስጥራዊ ባር ኮድ፡ የደህንነት መጠበቂያና ሚስጥራዊ መለያ ያለው በመሆኑ ፎርጅድ ማድረግ አይቻልም።
* ዲጂታላይዜሽን፡ የ"ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030" እቅድን ለማሳካት እንደ አንድ ትልቅ ስኬት ተወስዷል።
ትግበራው መቼ ይጀምራል?
በዓይነቱ የመጀመሪያ የሆነው ይህ ዘመናዊ የታርጋ ለውጥ ጥር 28 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በይፋ ስራ ላይ እንደሚውል ተቋሙ አረጋግጧል። ይህም አሰራር አገልግሎቱን ፈጣን፣ ግልጽና ተጠያቂነት የሰፈነበት ያደርገዋል ተብሎ ይጠበቃል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #amn #ኢትዮጵያ #ፌደራልፖሊስ #ቴክኖሎጂ #ዲጂታልኢትዮጵያ #የታርጋለውጥ #ethiopia #federalpolice

Comments