6 days ago
ቬንዙዌላ በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ የወንጀል መጠን የሚፈጸምባት ሀገር ተባለች።
#ethiopia | የረቀቁና የተደራጁ ወንጀሎች በብዛት ከሚፈጸምባቸው ሀገራት ቬንዙዌላ አንዷ ስትሆን በትጥቅ የተደገፈ ዝርፊያ ግድያ እና እገታ በብዛት ይበዛበታል ተብሏል።
መረጃው እንደጠቆመው ከፍተኛ የወንጀል መጠን የሚመዘገብባቸው አገራት በዋናነት በኢኮኖሚ አለመረጋጋት በፖለቲካዊ ውጥረት እና በቡድን ሁከቶች የሚታወቁ ናቸው።
ፓፓዋ ጊኒ ከፍተኛ የወንጀል መጠን ከሚፈፀምባቸው ሀገራት መካከል በሁለተኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠች ሲሆን ከከተሜነት መስፋፋት እና ሥራ አጥነት ባስከተለው ማኅበራዊ ውጥረት ምክንያት ከፍተኛ የወንጀል መጠን የሚመዘገብባት ሀገር ሆናለች።
ደቡብ አፍሪካ ከአለም ሶስተኛ ከአፍሪካ በቀዳሚነት ከፍተኛ የወንጀል መጠን የሚፈጸምባት ሀገር ተብላለች።
በጥናቱ መሠረት በሀገሪቱ የጦር መሣሪያ በቀላሉ መገኘቱ የኢኮኖሚ አለመመጣጠን እና የጎዳና ላይ ጥቃቶች መስፋፋታቸው ለወንጀሉ መጨመር በምክንያትነት ተጠቅሰዋል።
ከደቡብ አፍሪካ በመቀጠል ናይጄርያ በህገ-ወጥ እገታዎችና በሳይበር ወንጀሎች ሁለተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች።
እንዲሁም ሶማሊያ እና ሊቢያ በፖለቲካዊ አለመረጋጋትና በታጠቁ ቡድኖች እንቅስቃሴ ምክንያት ከአህጉሩ ከፍተኛ የወንጀል ስጋት ካለባቸው ሀገራት መካከል ሶስተኛና አረተኛ ደረጃን ይዘዋል።።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#ethiopia #getutemesgen #getunews #reviewindex #venezuela #southafrica

Comments