Logo
SeledaPost
ቶታል ነዳጅ ማደያ ኢትዮጵያን ለቆ ሊወጣ ነው፡፡

በኢትዮጵያ ውስጥ ከ75 አመታት በላይ በነዳጅ ችርቻሮ ንግድ ላይ ተሰማርቶ የቆየው ቶታል ኢነርጂስ ከኢትዮጵያ ለመውጣት ማቀዱ ተገለፀ፡፡

በመላው ኢትዮጵያ ወደ120 ያህል ማደያዎች ያሉት ይህ ተቋም ንብረቱን በሙሉ ለኦላ ኢነርጂ ወይንም ለቀድሞው ኦይልሊቢያ በሽያጭ ለማስተላለፍ እንቅስቃሴ እያደረገ መሆኑ ተዘግቧል፡፡

አፍሪካ ቢዝነስ ባቀረበው ዘገባ ሁለቱ ድርጅቶች በሽያጩ ዙሪያ ስምምነት ላይ መድረሳቸውን ገልፆ በምን ያህል ዋጋ ግብይቱ እንደተከናወነ ያለው ነገር የለም፡፡

ቶታል ኢነርጂስ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከብራዚል፣ ፓኪስታንና አንዳንድ የአውሮፓ አገራት የነዳጅ ማደያዎቹን ሸጦ የወጣ ሲሆን ይህ እርምጃውም የዚህ አካል እንደሚሆን ተገምቷል፡፡

Seledadotio
Seledadotio
2 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.