4 months ago
"ዴሞክራሲ ገዳይ ነው፤ አፍሪካውያን ሊረሱት ይገባል" — የቡርኪና ፋሶው መሪ ኢብራሂም ትራኦሬ
#ethiopia | የቡርኪና ፋሶው ወታደራዊ መሪ ካፒቴን ኢብራሂም ትራኦሬ፣ የምዕራባውያን የዴሞክራሲ ሥርዓት በአፍሪካ ምድር ላይ "ደም መፋሰስን" እንጂ እድገትን አላመጣም ሲሉ በፅኑ ተቃወሙ። መሪው ባደረጉት የቴሌቪዥን ቆይታ፣ የሀገሪቱ ሕዝብ ስለ ዴሞክራሲ ያለውን ሃሳብ "መዘንጋት" እንዳለበትና ሥርዓቱ ለአህጉሪቱ የማይበጅ "ባዕድ መጫወቻ" መሆኑን ገልጸዋል።
"ዴሞክራሲ ወይስ ጥፋት?"
ትራኦሬ በንግግራቸው ምዕራባውያን ዴሞክራሲን ለማስፈን ጣልቃ በገቡባቸው ሀገራት ሁሉ ውጤቱ ውድመት መሆኑን ጠቅሰዋል። ለዚህም እንደ አብነት ያነሱት ሊቢያን ነው።
"በሙአመር ጋዳፊ ዘመን ሕዝቡ ነፃ ትምህርት፣ ሕክምናና መኖሪያ ቤት ያገኝ ነበር፤ ምዕራባውያን ጣልቃ ገብተው ጋዳፊን ከገደሉ በኋላ ግን ሊቢያ በማብቂያ የሌለው ትርምስ ውስጥ ትገኛለች" ሲሉ የሥርዓቱን "ገዳይነት" አስረድተዋል።
መሪው በአፍሪካ ፖለቲከኞች ላይ ያላቸውን ዕይታም አልሸሸጉም። "እውነተኛ ፖለቲከኛ የሚባለው ውሸታም፣ አድርባይና በአፈ-ጮሌነት ሕዝብን የሚያታልል ነው" ያሉ ሲሆን፣ የፖለቲካ ፓርቲዎችም ለሀገር አንድነት እንቅፋትና "ከፋፋይ" በመሆናቸው በሀገራቸው እንዳይታገዱ ማድረጋቸውን ተከላክለዋል።
ከምዕራባውያን ኮፒ-ፔስት (Copy-paste) አሰራር ወጥቶ የራስን መንገድ መከተል እንደሚገባ የገለጹት ትራኦሬ፣ የሚከተሉትን ነጥቦች እንደ መፍትሄ አስቀምጠዋል፦
ከታች የሚነሳና በባሕላዊ መሪዎች የሚታገዝ አዲስ ሥርዓት መገንባት።
በቀን 6 ወይም 8 ሰዓት በመሥራት ብቻ ሀገርን ማሳደግ እንደማይቻልና አፍሪካውያን የሥራ ባህላቸውን መቀየር እንዳለባቸው አሳስበዋል።
ከምዕራባውያን ዕርዳታ መላቀቅና በኢኮኖሚም ሆነ በወታደራዊ መስክ ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ።
ካፒቴን ትራኦሬ በሐምሌ 2024 ምርጫ እንደሚያካሂዱ መጀመሪያ ላይ ቃል ገብተው የነበረ ቢሆንም፣ የሥልጣን ዘመናቸውን ለተጨማሪ 5 ዓመታት ማራዘማቸው ይታወሳል። ይህ የዴሞክራሲ "አይበጀንም" ንግግራቸውም በሥልጣን ላይ ለቆዩባቸው ዓመታት እንደ ርዕዮተ-ዓለማዊ መከራከሪያ እየቀረበ ይገኛል።
በአጠቃላይ የ38 ዓመቱ ወጣት መሪ መልእክት ግልጽ ነው፦ "የእኛ መንገድ አብዮታዊ ነው፤ የማንንም ፈለግ አንከተልም!"
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ibrahimtraore #burkinafaso #africapolitics #democracy #sovereignty #panafricanism #westafrica #politicalshift

Comments