2 months ago
u1320u1245u120bu12ed u121au1292u1235u1275u122d u12d0u1262u12ed u12a0u1215u1218u12f5 (u12f6/u122d) u12e8u130eu1260u1299u1275 u12e8u12f0u1234 u130eu122b u12e8u1218u1235u1296 u1355u122eu1300u12adu1275
#ethiopia #pmabiyahmed #irrigation #borenadevelopment #waterinfrastructure ","delight_ranges":[],"image_ranges":[],"inline_style_ranges":[],"aggregated_ranges":[],"ranges":[{"entity":{"__typename":"Hashtag","__isEntity":"Hashtag","url":"https://www.facebook.com/h...
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የጎበኙት የደሴ ጎራ የመስኖ ፕሮጀክት
#ethiopia #pmabiyahmed #irrigation #borenadevelopment #waterinfrastructure
3 months ago
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኅብረተሰቡን የንፁህ መጠጥ ውኃ ተጠቃሚ የሚያደርጉ ፕሮጀክቶች ተጠናቀቁ
*****************
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በአምስት ከተሞች የሚገኙ ከ180 ሺህ በላይ የኅብረተሰብ ክፍሎችን የንፁህ መጠጥ ውኃ ተጠቃሚ የሚያደርጉ ግዙፍ የውኃ ፕሮጀክቶች ተጠናቀው ለአገልግሎት ክፍት እየሆኑ ነው።
በክልሉ በ1.2 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ የተገነቡና ከአምስት በላይ ከተሞችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ የንፁህ መጠጥ ውኃ ፕሮጀክቶች ምረቃ ዛሬም ቀጥሎ ውሏል።
የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደ እና የውኃና ኢነርጂ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር አስፋው ዲንጋሞ በተገኙበት፣ በዛሬው ዕለት በወላይታ ዞን ሆቢቻ ወረዳ የተገነባው የብዝሃ ቀበሌ ንፁህ መጠጥ ውኃ ፕሮጀክት ተመርቆ አገልግሎት መስጠት ጀምሯል፡፡
ይህ ፕሮጀክት ብቻውን ከ150 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተደረገበት ሲሆን፣ ከ31 ሺህ በላይ የሚሆኑ የአካባቢውን ነዋሪዎች የንፁህ መጠጥ ውኃ ችግር ይቀርፋል ተብሎ ይጠበቃል።
ሰሞኑን የተመረቁትን ጨምሮ በክልሉ ግንባታቸው በተከታታይ እየተመረቁ የሚገኙት እነዚህ ፕሮጀክቶች በአጠቃላይ ከ180 ሺህ በላይ የኅብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ናቸው።
ፕሮጀክቶቹ በጌዴኦ ዞን የጨለለቅቱ ከተማ፣ በወላይታ ዞን የሆቢቻ ወረዳ ብዝሀ-ቀበሌ፣ በጋሞ ዞን የዘፍነ ከተማ፣ በደቡብ ኦሞ ዞን የቀያፈር ከተማ እና በኮሬ ዞን የኬሌ ከተማ የሚገኙ ናቸው።
በትናንትናው ዕለት በጌዴኦ ዞን ጨለለቅቱ ከተማ የምረቃ መርሐ ግብር የተካሄደ ሲሆን፣ ዛሬ በወላይታ ዞን ሆቢቻ ወረዳም ተካሂዷል፡፡ በቀጣይም በሌሎች ቀሪ ከተሞች የምረቃ ሥነ-ሥርዓቱ እንደሚካሄድ ታውቋል።
እነዚህ የንፁህ መጠጥ ውኃና ሳኒቴሽን ፕሮጀክቶች "የአፍሪካ ቀንድ ዘላቂ የከርሰ ምድር ውሃ ፕሮጀክት" አካል ሲሆኑ፣ ግንባታቸውም በፌዴራል፣ በክልልና በዞን መንግሥት እንዲሁም ከአጋር ድርጅቶች ጋር በመተባበር የተከናወነ ነው።
ፕሮጀክቶቹ ተጠናቀው ለአገልግሎት መብቃታቸው በክልሉ በተለይም በገጠር እና በከፊል የከተማ አካባቢዎች የነበረውን የንፁህ መጠጥ ውኃ እጥረት በከፍተኛ ሁኔታ እንደሚቀንሰው በምረቃው ወቅት ተገልጿል።
በትዕግስቱ ቡቼ
#ethiopia #southethiopia #waterinfrastructure #development #cleanwater #ethiopianbroadcastingcorporation

Comments