1 month ago
አውስትራሊያ 1 - 1 ግብፅ :- የመደበኛ ሰዓት ውጤት
*************************
በአውስትራሊያ እና በግብፅ መካከል የተደረገው የጥሎ ማለፍ ጨዋታ መደበኛው የ90 ደቂቃ ክፍለ ጊዜ በ 1 ለ 1 አቻ ውጤት ተጠናቅቋል።
በመጀመሪያው አጋማሽ በ13ኛው ደቂቃ ላይ በኢማም አሹር ግብ መሪ የነበረችው ግብፅ፣ በ55ኛው ደቂቃ ላይ ሞሀመድ ሀኒ በራሱ መረብ ላይ ባስቆጠራት ግብ አውስትራሊያ አቻ መሆን ችላለች።
በጨዋታው በመደበኛው ሰዓት አሸናፊ ባለመገኘቱ፣ ወደ ጭማሪ 30 ደቂቃ አምርቷል።
#worldcup #australia #egypt #football #ebc #fifa2026

ስፔን ኦስትሪያን 3 ለ 0 በማሸነፍ 16ቱን ተቀላቀለች
*******************
በ23ኛው የዓለም ዋንጫ የጥሎ ማለፍ ጨዋታ ስፔን ኦስትሪያን 3 ለ 0 በመርታት ወደ 16ቱ ጥሎ ማለፍ ተሸጋግራለች።
ስፔንን ለድል ያበቋትን ሦስት ግቦች ሚኬል ኦያርዛባል በ36ኛው እና በ89ኛው ደቂቃ ላይ ሲያስቆጥር፤ ቀሪዋን አንድ ግብ ፔድሮ ፖሮ በ66ኛው ደቂቃ ላይ አስቆጥሯል።
ስፔን በቀጣይ ዙር ጨዋታዋ ከፖርቹጋል እና ክሮሺያ አሸናፊ ጋር የምትገናኝ ይሆናል።
#worldcup #spain #austria #sports #ebc #fifa2026

እንግሊዝ ዲሞክራቲክ ኮንጎን 2 ለ 1 በማሸነፍ 16ቱን ተቀላቀለች
**************************
በ23ኛው የዓለም ዋንጫ የጥሎ ማለፍ ጨዋታ እንግሊዝ ዲሞክራቲክ ኮንጎን 2 ለ 1 በመርታት ወደ 16ቱ ጥሎ ማለፍ ተሸጋግራለች።
እንግሊዝን ለድል ያበቋትን ሁለት ግቦች ሃሪ ኬን በ75ኛው እና በ86ኛው ደቂቃ ላይ ሲያስቆጥር፤ ለዲሞክራቲክ ኮንጎ ብሪያን ሲፔንጋ በ7ኛው ደቂቃ ላይ ብቸኛ ግብ አስቆጥሯል።
እንግሊዝ በቀጣይ ዙር ጨዋታዋ ከሜክሲኮ ጋር የምትገናኝ ይሆናል።
#worldcup #england #drcongo #sports #ebc #fifa2026

3 months ago
ኢራንን በጣልያን ለመተካት እየታሰበ ነወ ተባለ
#ethiopia | በ2026ቱ የዓለም ዋንጫ ዋዜማ፣ የእግር ኳሱን ዓለም የሚያነጋግር አዲስ ውዝግብ ተነስቷል። የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ መልዕክተኛ የሆኑት ፓኦሎ ዛምፖሊ፣ ፊፋ ኢራንን ከውድድሩ ውጪ አድርጎ በምትኳ ጣልያንን እንዲያስገባ መጠየቃቸው ታውቋል።
ምንም እንኳን የጣልያን ብሔራዊ ቡድን በሜዳ ላይ በነበረው የማጣሪያ ጨዋታ ለ2026ቱ የዓለም ዋንጫ ማለፍ ባይችልም፣ ዛምፖሊ ግን ፊፋ በኢራን ላይ የቅጣት እርምጃ እንዲወስድና ለጣልያን ድንገተኛ ዕድል እንዲሰጥ ጥሪ አቅርበዋል። ጥያቄው በዲፕሎማሲያዊ ጫናዎች የታጀበ እንደሆነ ቢገለጽም፣ በስፖርቱ ማህበረሰብ ዘንድ ግን ግርምትን ፈጥሯል።
ለጣልያን ደጋፊዎች ይህ ትልቅ ተስፋ የሚሰጥ ቢመስልም፣ የፊፋው ፕሬዝዳንት ጂያኒ ኢንፋንቲኖ ግን ከሳምንት በፊት በሰጡት ማረጋገጫ ኢራን በውድድሩ ላይ እንደምትሳተፍ በይፋ መናገራቸው ይታወሳል።
ፊፋ እስካሁን ድረስ በፖለቲካዊ ምክንያቶች ቡድኖችን ከመተካት ይልቅ በሜዳ ላይ ለተመዘገበ ውጤት ቅድሚያ እንደሚሰጥ ይታወቃል።
ኢራን በፖለቲካዊ ምክንያቶች እንድትታገድና ጣልያን እንድትተካ የቀረበ ጥያቄ።
ቡድኑ በማጣሪያው ወድቆ የነበረ ቢሆንም፣ አሁን ግን በደብዳቤ የመግባት ዕድል እየተፈለገለት ነው።
ፕሬዝዳንት ኢንፋንቲኖ የኢራንን ተሳትፎ አስቀድመው አረጋግጠዋል።
ይህ ያልተጠበቀ ዲፕሎማሲያዊ ጫና በፊፋ ውሳኔ ላይ ለውጥ ያመጣ ይሆን ወይስ ኢራን በለመደችው መልኩ ጉዞዋን ትቀጥላለች? የሚለው ጉዳይ የብዙዎች መጠባበቂያ ሆኗል። ሆኖም የኳስ ወዳጆች እንደሚሉት "የሜዳ ውጤት በደብዳቤ አይቀየርም"።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን) #getutemesgen #getu #nbc
#fifa2026 #worldcup #italy #iran #gianniinfantino #footballnews #trumpenvoy #worldcupupdate #sportnews

Comments