9 days ago
የቀብር አስፈጻሚው የፈፀመው አስደንጋጭ ወንጀል
*35 አስክሬኖች ሳይቀበሩ በተቋሙ ህንፃ ውስጥ ተከማችተው ተኝተዋል።
#ethiopia | የቀብር አስፈጻሚ ድርጅት ባለቤት የሆኑት የ48 ዓመቱ ሮበርት ቡሽ የሟቾችን አስክሬን ክብር ባለው መልኩ ባለማሳረፍ እና ሌሎች 68 ወንጀሎች በመፈፀም ጥፋተኛ ተብለዋል።
ግለሰቡ የተሳሳተ የሟች አመድ ለቤተሰቦች በመስጠት ማታለል በመፈጸምና ከበጎ አድራጎት ድርጅቶች ገንዘብ በመቀበል ወንጀል ጥፋተኛ መሆናቸውን አምነዋል ሲል ፍ/ቤት ገልጿል።
ድርጊቱ ለዓመታት የተፈጸመ ሲሆን ግለሰቡ ለገንዘብ ጥቅም ሲል በከፍተኛ ሀዘን ላይ የነበሩ ቤተሰቦችን እምነት አላግባብ በመጠቀም የማይጠገን በደል ፈጽሟል ሲል ፖሊስ ገልጿል።
35 አስክሬኖች ሳይቀበሩ በተቋሙ ህንፃ ውስጥ ተከማችተው ተኝተዋል።
ለበርካታ ዓመታት የሟች ቤተሰቦች የተቃጠለው አስክሬን አመድ ነው ተብሎ የተሰጣቸው አመድ የሌላ ሰው እንደነበር ወይም ተደባልቆ የተሰጠ እንደነበር ተደርሶበታል።
ግለሰቡ የፈፀመውን ነገር የሰሙ የሟች ቤተሰቦች እንደተናገሩት የአባታችንን የቀብር ሥነ ሥርዓት ፈጽመን አመዱን ተቀብለናል ብለን በምናስብበት ወቅት አስክሬኑ አሁንም በተቋሙ ህንፃ ውስጥ ይገኛል መባላችን በቃላት ልንገልጸው የማንችለው ድንጋጤ ፈጥሮብናል ብለዋል።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#ethiopia #getutemesgen #getunews #england #funeraldirector #police #court

Comments