8 days ago
የቀብር አስፈጻሚው የፈፀመው አስደንጋጭ ወንጀል
*35 አስክሬኖች ሳይቀበሩ በተቋሙ ህንፃ ውስጥ ተከማችተው ተኝተዋል።
#ethiopia | የቀብር አስፈጻሚ ድርጅት ባለቤት የሆኑት የ48 ዓመቱ ሮበርት ቡሽ የሟቾችን አስክሬን ክብር ባለው መልኩ ባለማሳረፍ እና ሌሎች 68 ወንጀሎች በመፈፀም ጥፋተኛ ተብለዋል።
ግለሰቡ የተሳሳተ የሟች አመድ ለቤተሰቦች በመስጠት ማታለል በመፈጸምና ከበጎ አድራጎት ድርጅቶች ገንዘብ በመቀበል ወንጀል ጥፋተኛ መሆናቸውን አምነዋል ሲል ፍ/ቤት ገልጿል።
ድርጊቱ ለዓመታት የተፈጸመ ሲሆን ግለሰቡ ለገንዘብ ጥቅም ሲል በከፍተኛ ሀዘን ላይ የነበሩ ቤተሰቦችን እምነት አላግባብ በመጠቀም የማይጠገን በደል ፈጽሟል ሲል ፖሊስ ገልጿል።
35 አስክሬኖች ሳይቀበሩ በተቋሙ ህንፃ ውስጥ ተከማችተው ተኝተዋል።
ለበርካታ ዓመታት የሟች ቤተሰቦች የተቃጠለው አስክሬን አመድ ነው ተብሎ የተሰጣቸው አመድ የሌላ ሰው እንደነበር ወይም ተደባልቆ የተሰጠ እንደነበር ተደርሶበታል።
ግለሰቡ የፈፀመውን ነገር የሰሙ የሟች ቤተሰቦች እንደተናገሩት የአባታችንን የቀብር ሥነ ሥርዓት ፈጽመን አመዱን ተቀብለናል ብለን በምናስብበት ወቅት አስክሬኑ አሁንም በተቋሙ ህንፃ ውስጥ ይገኛል መባላችን በቃላት ልንገልጸው የማንችለው ድንጋጤ ፈጥሮብናል ብለዋል።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#ethiopia #getutemesgen #getunews #england #funeraldirector #police #court

12 days ago
120 ስልክ ሿሿ ያደረገው ግለሰብ….
በኡጋንዳ በቀን 120 ስልኮችን የሰረቀው ግለሰብ ከስልኮቹ ጋር የተያዘ ሲሆን፣ «ስልኮቻችሁ የተሰረቁባችሁ ሰዎች ወደ ኡጋንዳ ፖሊስ ጣቢያ እየመጣችሁ ተቀበሉ» ተብሏል።
የሚገርመው ነገር፣ ስልኮቹ የስክሪን ምስላቸው (Screen saver) እንኳን ሳይቀየር እንደነበረው ነው ያሉት።
ያ ማለት የተሰረቀባቸው ሰዎች በስክሪናቸው ላይ ያደረጉት ምስል የራሳቸው ከሆነ በቀላሉ ስልካቸውን ማግኘት ይችላሉ ማለት ነው።
ስለዚህ ለክፉም ለደጉም የስልካችሁን Screen Saver የራሳችሁን አድርጉት።
ህዝቡም ወደ ፖሊስ ጣቢያ እየተመመ ነው።
Via Uganda Police
Seledadotio

18 days ago
ነገ በአዲስ አበባ ሰላማዊ ሰልፍ ይደረጋል። ሰልፉ ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስዱ መንገዶች ለተሽከርካሪ ዝግ እንደሚሆኑ የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አስታወቀ።
በትግራይ ክልል እየተባባሰ የመጣውን ቀውስ ለመቃወምና ለማስቆም እንዲሁም ለፌደራል መንግስትና ዓለም አቀፍ ማህበረሰብ ለማሳወቅ ''አፈሳ ይቁም ሰላም ይስፈን'' በሚል መሪ ቃል ሐምሌ 11 ቀን 2018 ዓ/ም ከጥዋቱ 12:00 ሰዓት ጀምሮ በመስቀል አደባባይ ሰላማዊ ሰልፉ ይደረጋል።
ሰልፉ ተጀምሮ እስከ ሚጠናቀቅበት ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስዱ መንገዶች ለተሽከርካሪ ዝግ ይሆናሉ።
በዝህም መሰረት:-
# ከመገናኛ በ22 አደባባይ ወደ መስቀል አደባባይ ቅ/ዑራኤል አደባባይ
# በቦሌ መንገድ ወደ መስቀል አደባባ ኦሎምፒያ አደባባይ
# ከጎተራ ወደ መስቀል አደባባይ ለከባድ ተሽከርካሪ አጎና ሲኒማ መስቀለኛ ለቀላል ተሽከርካሪ ጥላሁን አደባባይ
# ከሜክሲኮ አደባባይ ወደ መስቀል ለገሀር መብራት
# ከለገሀር ቴሌ ማቋረጫ ወደ ስታዲዮም ለገሀር ቴሌ ማቋረጫ
# ከአራት ኪሎ ወደ መሰቀል አደባባይ ብሔራዊ ቤተ-መንግስት
# ከካሳንቺስ በመቅረዝ ሆስፒታል ወደ መስቀል አደባባይ መቅረዝ ሆስፒታል አጠገብ
# ከአምባሳደር ቴአትር ወደ መሰቀል አደባባይ ሐራምቤ መብራት የሚወስዱ መንገዶች ከንጋቱ 11:00 ሰዓት ጀምሮ ፕሮግራሙ እስከሚጠናቀቅ መንገዶቹ ለተሽከርካሪ ዝግ ይሆናሉ።
ከዛሬ ሐምሌ 10 ቀን 2018 ዓ/ም ጀምሮ በመስቀል አደባባይና በዙሪያው ባሉ መንገዶች ከምሽቱ 12፡00 ሰዓት ጀምሮ ተሽከርካሪ ለአጭርም ሆነ ረዥም ሠዓት ማቆም የተከለከለ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አስታውቋል።
Addis Ababa police

19 days ago
ተሽከርካሪው በፀጥታ አካላት ተይዟል በሚል ምክንያት ለስራ የተሰጠውን ሲኖ ትራክ መኪና ለመሸጥ ሲያስማማ የነበረ ግለሰብ እና ግብራበሮቹ በቁጥጥር ስር ዋሉ።
የወንጀል ድርጊቱ የተፈፀመው በአቃቂ ክ/ከተማ ወረዳ 9 ኮዬ አደባባይ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ነው።
የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 3- 92267 ኢት የሆነ ሲኖ ትራክ ሹፌር የሆነው ብዙአየሁ ምላ ተሽከርካሪው በፖሊስ ይፈለጋል ተብሎ እንደተወሰደ ለባለንብረቱ ይናገራል።ባለንብረቱ ጉዳዮን ለአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ዋና ፖሊስ መምሪያ ያሳውቃሉ።ፖሊስ ባሰባሰበው መረጃ ተሽከርካሪው በፖሊስ እንዳልተያዘ ማረጋገጡን ተከትሎ ክትትሉን ይቀጥላል።
የአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ዋና ፖሊስ መምሪያ ክትትል ሲያደርግ የቆየ ሲሆን ከህብረተሰቡ በተገኘ መረጃ ተሽከርካሪው ገላን ኮንዶሚኒየም አካባቢ ተገኝቷል። አሽከርካሪው አበበ ወርቁ ከተባለው ረዳቱ እና ቢኒያም እሸቱ ከተባለው ግለሰብ ጋር በመተባበር መኪናውን ለመሸጥ ሲያስማሙ ሶስቱ ተጠርጣሪዎች በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተጣራባቸው እንደሚገኝ ተጠቁሟል።
የተሽከርካሪ ባለንብረቶች አሽከርካሪ ሲቀጥሩ በተያዥ በመቅጠር መሰል ወንጀሎችን ሊከላከሉ እና የተሽከርካሪውን ውሎ ሊከታተሉ እንደሚገባ የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ መልዕክቱን አስተላልፏል።

21 days ago
የግድያ ወንጀል የፈጸሙ 11 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ።
ሰኔ 28 ቀን 2018 ዓ/ም በግምት ከለሊቱ 7:00 ሠዓት በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 ልዩ ቦታው ቡልቡላ አቦ መሻገሪያ ድልድይ እየተባለ ከሚጠራው አካባቢ ነው የግድያ ወንጀሉ የተፈፀመው።
በወቅቱ ማንነቱ ያልታወቀ ግለሠብ ከሳሪስ አቦ ወደ ኮዬ መሄጃ በሚገኝ መንገድ ድልድይ ስር ደረቱ ላይ በስለት ተወግቶ ህይወቱ አልፎ ተገኘ።
የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ የሰው መግደል ምርመራ፣ የክትትልና ኦፕሬሽን ቡድኑ በመቀናጀት የሟችን ማንነት ለማወቅ እና ወንጀል ፈፃሚዎችን ለመለየት ባደረገው ጥረት ወንጀሉ በተፈፀመ 48 ሠዓት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ የሟችን ማንነትና እና ወንጀሉን ፈፅመዋል ያላቸውን እንዳለ ተሰማ፣ ኤርሚያስ አሰፋ፣ ያብስራ እንዳለ፣ ዘካሪያስ ለማ፣ ናትናኤል ግርማ፣ ተመስገን ተስፋዬ፣ ብሩክ ኤርሚያስ፣ ኢዮብ ጌታቸው፣ ላምሮት አረጋኸኝ፣ ኤልሻዳይ ዳዊት እና ኤዶሚያስ ወንድወሰን የተባሉ ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን ገልጿል።
ፖሊስ በተያዙት ተጠርጣሪዎች ላይ ባደረገው ምርመራ ሟች ዘይኑ ፈድሉ በመንገድ እየተጓዘ ባለበት ወቅት አንገቱን በመያዝና ደረቱን በጩቤ በመውጋት ህይወቱ እንዲያልፍ በማድረግ ይዞት የነበረውን ሳምሰንግ ስልክ ወስደዋል።
የሟችን አስክሬን ኤርሚያስ አሠፋ በተባለው ግለሠብ የሠሌዳ ቁጥር ኮድ 3-B 83677 አ/አ ቪትስ ኮምፓክት ተሽከርካሪ ኮፈን ውስጥ በመክተት ሌሎቹ ተጠርጣሪዎች ደግሞ ኮድ 3-71724 አ/አ በሆነ ቪትስ ተሽከርካሪ በመሆን ተከታትለው በመሄድ የሟችን አስክሬን ድልድይ ስር ጥለውት መሄዳቸውን በምርመራ ወቅት ገልጸዋል።
ተጠርጣሪዎቹ ወንጀሉን በፈጸሙ 48 ሠዓት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ በፖሊስ እንደተያዙ እና በራሳቸው ፍላጎት ወንጀሉን እንዴት እንደፈፀሙ መርተው ማሳየታቸውን ከምርመራ ክፍሉ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
ፖሊስ በተጠርጣሪዎቹ ላይ ባደረገው ምርመራ የማስፋት ስራ ለወንጀሉ መፈፀሚያ የሚጠቀሙበት 2 ጩቤ፣ 3 ሽጉጥ መያዙን የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ ገልፆ በተጠርጣሪዎቹ ላይ ምርመራው እንደቀጠለ ገልጿል።
የሟች ዘይኑ ፈድሉ ቤተሰቦች በበኩላቸው በወንድማቸው ህልፈት እጅጉን ማዘናቸውን ገልጸው ፖሊስ በአጭር ጊዜ ውስጥ ወንጀል ፈፃሚዎቹን በቁጥጥር ስር በማዋሉ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

Sponsored by
Surafel
24 days ago
የነገው የጎዳና ሩጫ ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ ለተሽከርካሪ ዝግ የሚሆኑ መንገዶች
***************
ነገ ሐምሌ 5 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ አስተባባሪነት የ5 ኪሎ ሜትር ሩጫ የጎዳና ሩጫ ይደረጋል።
ውድድሩ መነሻውን ከመስቀል አደባባይ በማድረግ በገሀር፣ ሜክሲኮ አደባባይ፣ ዋቢ ሸበሌ ሆቴል፣ ብሔራዊ ቴአትር፣ ኢትዮጵያ ሆቴል፣ ንግድ ባንክ፣ ጋንዲ ሆስፒታል እና ጊዮን ሆቴል አቋርጦ በመስቀል አደባባይ ፍጻሜውን ያገኛል።
በመሆኑም ነገ እሁድ ከንጋቱ 11:30 - ሰዓት ጀምሮ ውድድሩ እስከሚጠናቀቅ፦
• ከኦሎምፒያ አደባባይ ወደ መስቀል አደባባይ (ኦሎምፒያ አደባባይ ላይ)
• ከጥላሁን አደባባይ ወደ ሳንጆሴፍ መብራት (ጥላሁን አደባባይ ላይ) ለከባድ ተሽከርካሪ (አጎና ሲኒማ ላይ)
• ከAU መብራት ወደ ሜክሲኮ አደባባይ (ጥይት ቤት መስቀለኛ ላይ)
• ከፓርላማ መብራት ወደ ኮንሰን መታጠፊያ (ፓርላማ መብራት ላይ)
• ከኮንሰን መታጠፊያ ወደ ገብርኤል (ኮንሰን መታጠፊያ ላይ)
• ከጥይት ቤት ወደ ገብርኤል በጀርባው (ጥይት ቤት መታጠፊያ ላይ)
• ከሴቶች አደባባይ ወደ ካዛንቺስ (ሴቶች አደባባይ ላይ)
• ከሴቶች አደባባይ ወደ ካዛንቺስ ቶታል (ሴቶች አደባባይ ላይ)
• ከ22 አደባባይ ወይም ዘሪሁን ህንፃ ወደ ዑራኤል አደባባይ (ዘሪሁን ህንፃ መስቀለኛ ላይ)
• ከጋዜቦ አደባባይ ወደ ደንበል (ጋዜቦ አደባባይ ላይ)
• ከቂርቆስ ቤ/ክርስቲያን መስቀለኛ ወደ ለገሃር መብራት (ቂርቆስ ቤ/ክርሰቲያን ነርክ ተራ ላይ)
• ከላንድ ማርክ ሆስፒታል መታጠፊያ ገነት ሆቴል ወይም ወደ ገነት መብራት (ላንድ ማርክ ሆስፒታል መስቀለኛ ላይ)
• ከጠማማ ፎቅ ወደ ሜክሲኮ አደባባይ (ጠማማ ፎቅ መስቀለኛ ላይ)
• ከኤዩ መብራት ወደ ሜክሲኮ አደባባይ (ሜክሲኮ ጥይት ፋብሪካ መስቀለኛ ላይ)
• ከከፍተኛ ፍ/ቤት አደባባይ ወደ ሜክሲኮ አደባባይ (ከፍተኛ ፍ/ቤት አደባባይ ላይ)
• ከሠንጋ ተራ 40/60 ወደ ሠንጋ ተራ መብራት (ሠንጋ ተራ 40/60 መታጠፊያ ላይ)
• ከጎማ ቁጠባ መብራት ወደ ብ/ቲያትር (ጎማ ቁጠባ መብራት ላይ)
• ከሜትሮሎጂ መታጠፊያ ወደ ፖስታ ቤት መብራት (ሜትሮዎሎጂ መታጠፊያ ላይ)
• ከጥቁር አንበሳ ሼል ወደ ኢምግሬሽን (ጥቁር አንበሳ ሼል ላይ)
• ከጎላ ሚካኤል መስቀለኛ ወደ ኢሚግሬሽን (ጎላ ሚካኤል መስቀለኛ ላይ)
• ከአገር አስተዳደር መብራት ወደ ብሔራዊ ቲያትር (አገር አስተዳደር መብራት ላይ)
• ከንግድ ማተሚያ ወደ ኦርማ ጋራዥ (ንግድ ማተሚያ መስቀለኛ ላይ) መንገዶች ለተሽከርካሪ ዝግ እንደሚሆኑ የአዲስ አበባ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አስታውቋል።
በተጨማሪም በተገለፁት መስመሮች ላይ መኪና ለአጭርም ይሁን ለረጅም ጊዜ ማቆም የተከለከለ መሆኑን ዋና ጠቅላይ መምሪያው አስታውቋል።
ሕዝቡ ለጸጥታው ሥራ እያደረገ ላለው ቀና ትብብር ምስጋናውን አቅርቦ፤ አሽከርካሪዎች የትራፊክ መጨናነቅ እንዳያጋጥማቸው አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ መልዕክት አስተላልፏል።
#ethiopia #addisababa #police #streetrace #ebc

26 days ago
የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ በመምሰል የማታለል (በተለምዶ ሿሿ) ተብሎ የሚጠራውን ወንጀል ሲፈፅሙ የነበሩ 9 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ።
ተጠርጣሪዎቹ የወንጀል ድርጊቱን የፈፀሙት ሰኔ 28 ቀን 2018 ዓ/ም ከጥዋቱ 1:40 በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ልዩ ቦታው ሪቼ ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ ነው።
የግል ተበዳይ ከአጎና ወደ እስታዲየም ለመሄድ በማሰብ ኮድ 3-83620 ኦሮ ነጭ ሚኒባስ ተሽከርካሪ በማስቆም ትገባለች። ተጠርጣሪዎችም የግለሰቧን ወደ ተሽከርካሪው መግባት ተከትለው በማዋከብ እና ትኩረቷን በማሳጣት ይዛው ከነበረው ቦርሳ ውስጥ 32 ሺ ብር ግምት ያለው ሳምሰንግ ስልክ ሰርቀው ጥለዋት ይሄዳሉ።
ይህን የተመለከቱ የትራፊክ ፖሊሶች ተሽከርካሪውን በማስቆም እና ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር የማዋል ስራ ሰርተዋል።
ተጠርጣሪዎቹ ከተያዙ በኋላ በተሽከርካሪው ውስጥ በተደረገ ፍተሻ 7 ስልኮች መገኘታቸውን የቂርቆስ ክ/ከተማ ፖሊስ ዋና መምሪያ አስታውቋል።
ከተጠርጣሪዎቹ መካከል ነፍሰ ጡር መኖሯ የተገለጸ ሲሆን የቀን ውሎ አበል በመክፈል እና ተሽከርካሪ በመከራየት ወንጀሉን የሚፈፅሙ ግለሰቦች እንዳሉ ህብረተሰቡ ተገንዝቦ ትራንስፖርት ሲጠቀም ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባም የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አስታውቋል።

የተሽከርካሪ ሠሌዳ የሰረቀው ግለሰብ በእስራት ተቀጣ፡፡
ቃኛቸው ታመነ የተባለው ተከሳሽ የተሽከርካሪ ሠሌዳ ሲሰርቅ በቁጥጥር ስር የዋለው ሰኔ 13 ቀን 2018 ዓ/ም ከጠዋቱ 1:30 በየካ ክ/ከተማ ወረዳ 7 ፓኪስታን ኤምባሲ አካባቢ ነው፡፡
ተከሳሹ በተጠቀሰው አካባቢ ከሚገኝ የተሽከርካሪ ማቆሚያ ቆሞ ከነበረ የሠሌዳ ቁጥር ኮድ 3B- 70-5-38 A/A የሆነ ዊሊንግ ተሽከርካሪ ላይ የፓርኪንግ ሰራተኞች ያለመኖራቸውን በማየት ሰሌዳውን ፈትቶ ሊሰወር ሲል በአካባቢው ህብረተሰብና በፖሊስ በቁጥጥር ስር መዋሉን በየካ ክፍለ ከተማ ፖሊስ ዋና መምሪያ የአድዋ አካባቢ ፖሊስ መምሪያ አስታውቋል።
ፖሊስ ተከሳሹን በቁጥጥር ስር በማዋል ባደረገው ምርመራ የማስፋት ተግባር ተከሳሹ ከቦሌ ክ/ከተማ ሌላ ተጨማሪ የተሽከርካሪ ሰሌዳ ሰርቆ እንደሸጠ መርቶ አሳይቷል። በምሪቱም የተሰረቀ ሰሌዳ በመግዛት የተጠረጠረውን ግለሰብ በቁጥጥር ስር በማዋል የሌላ ተሽከርካሪ የፊት እና የኋላ ታርጋ የተገኘ በመሆኑ ተጠርጣሪውንም ለቦሌ ክ/ከተማ ፖሊስ ዋና መምሪያ ማስተላለፉን የአድዋ ፖሊስ መምሪያ አስታውቋል።
በተከሳሹ ላይ ምርመራ ተጣርቶ መዝገቡ ለአቃቤ ህግ ተልኮም በፈጣን ችሎት ታይቷል። ጉዳዩን የተመለከተው በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የካ ምድብ 1ኛ ወንጀል ችሎት ሰኔ 25 ቀን 2018 ዓ/ም በዋለው ችሎት በ 1 ዓመት ከ6 ወር እስራት እንዲቀጣ ወስኖበታል፡፡
አሽከርካሪዎች እና የፓርኪንግ ሰራተኞች መሰል ወንጀል እንዳያጋጥም አስፈላጊውን ጥንቃቄ ሊያደርጉ እንደሚገባም የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ መልዕክቱን አስተላልፏል።

29 days ago
የሺሻ ማስጨሻ እቃዎችና 75 ኪሎ ግራም የሚመዘን አደንዛዥ እፅ ተወገደ፡፡
በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 ጭንቻ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በተከናወነው የማስወገድ ሂደት በተለያዩ ጊዜያት በተደረጉ የኦፕሬሽን ተግባራት በኤግዚቢትነት የተያዙ የተለያዩ አደንዛዥ ዕፆች፣ የሺሻ እቃዎች እንዲሁም ለጤና ጠንቅ የሆኑ ጊዜያቸው ያለፈባቸው፣ አልባሳት፣ የፅዳት ዕቃዎችና ልዩ ልዩ ቁሳቁሶች መወገዳቸውን የአራዳ ክ/ከተማ ፖሊስ ዋና መምሪያ አስታወቀ፡፡
በቦታው የአራዳ ክፍለ ከተማ ፖሊስ ዋና መምሪያ የወንጀል ምርመራ መምሪያ ኃላፊ ኮማንደር ጌታነህ በቀለ፣ የክ/ከተማው ሠላምና ፀጥታ አስተዳደር ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ድሪባ ዶጃ፣ የደንብ ማስከበር አባላት፣ በየደረጃው የሚገኙ የፖሊስ አመራሮችና አባላት እንዲሁም የኃይማኖት አባቶችና የአካባቢው ነዋሪዎች ተገኝተዋል፡፡
የክ/ከተማው ፖሊስ ዋና መምሪያ የወንጀል ምርመራ መምሪያ ኃላፊ ኮማንደር ጌታነህ በቀለ በዋና መምሪያው እና በ6ቱ መምሪያዎች ከ2006 ዓ/ም ጀምሮ በኤግዚቢትነት የተያዘ 75 ኪሎ ግራም አደንዛዥ እፅ፣ 250 የሺሻ እቃዎች፣ ጊዜያቸው ያለፈባቸው 425 እሽግ ሳይንታዘር፣ 480 እሽግ ፈሳሽ ሳሙና፣ 3658 ጠርሙስ ተመሳስሎ የተሰራ የአልኮል መጠጦች እንዲሁም የተለያዩ አልባሳት መወገዳቸውን በመግለፅ በቀጣይም ፖሊስ ከሚመለከታቸው ባለ ድርሻ አካላት ጋር በመሆን የህብረተሰቡን ደህንነት የሚጎዳ ማንኛውንም ነገር ለመከላከል ከምን ጊዜውም በላይ እንደሚሰራ ተናግረዋል፡፡
የክ/ከተማው ሠላምና ፀጥታ አስተዳደር ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ድሪባ ዶጃ እንደተናገሩት የተወገዱት አደንዛዥ እፆች ትውልዱን የሚያበላሹ እና ወጣቱ ወንጀል እንዲፈፅም መንስኤ መሆናቸውን በመግለፅ የግል ጥቅማቸውን በማሰብ ለህብረተሰቡ ጤና ጠንቅ የሆኑና ጊዜያቸው ያለፈባቸውን የንፅህና መጠበቂያ ቁሳቁሶች ፖሊስ እና ባለ ድርሻ አካላት ተከታትለው በቁጥጥር ስር በማዋል ማስወገዱን ገልፀው ስራውን በጋራ አጠናክረው እንደሚቀጥሉም ጠቁመዋል።
ያነጋገርናቸው የኃይማኖት አባቶች በበኩላቸው የተወገዱት ኤግዚቢቶች በህብረተሰቡ ላይ የሚያስከትሉት ጉዳትና በተለይ በወጣቱ ላይ የሚያሳድሩት የጤና እና የስነ ልቦና ቀውስ ቀላል የሚባል እንዳልሆነ ገልጸዋል፡፡ ፖሊስ በሰራው ስራ መደሰታቸውን በመጠቆም የበኩላቸውን ድርሻ እንደሚወጡም ተናግረዋል።

2 months ago
የጠቅላይ ሚኒስትሩ እንግዶች ምን ገጠማቸው?
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ያጋሩት የቴክኖሎጂንና የፖሊስን ቅንጅት የሚያሳይ አስገራሚ ታሪክ
******************
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአፍሪካ ቀዳሚ የሆነውን የተቀናጀ የዲጂታል አገልግሎት መተግበሪያ መርቀው ሥራ ሲያስጀምሩ ባደረጉት ንግግር የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ከቦሌ እስከ ዋናው መሥሪያ ቤት የCCTV ካሜራ ተጠቅሞ ወንጀለኞችን እንዴት ተከታትሎ በቁጥጥር ስር እንዳዋለ አንድ አስገራሚ ታሪክ አጋርተዋል።
ከትናንት በስቲያ የተፈጠረ አጋጣሚ ነው። የጠቅላይ ሚኒስትሩ እንግዶች አዲስ አበባ መጡ። ለሥራ የመጡ የውጭ ዜጎች ናቸው። ኢትዮጵያን ሲያዩ የመጀመሪያቸው ነበር።
ቀን ላይ ከተማዋን ተዘዋወሩ ጎበኙ። የሪቨርሳይድ ከተማ ኮሪደርም የጉብኝቱ አካል ነበር። በሀገራችን ውበት እጅግ ተማረኩ። "እንዴት የምታምር ሀገር ናት!" በማለት አደነቁ።
ምሽት ላይ አየር ለመቀበል ከሀያት ሆቴል ወጥተው በእግራቸው መንቀሳቀስ ጀመሩ። በዚህ መሀል ያልታሰበ ነገር ተፈጠረ። ሁለት ሦስት ሰዎች ድንገት ወደ እነሱ በመጠጋት የእንግዶቹን ሞባይል ነጥቀው ተሰወሩ። ሰዓቱ ማታ 4 ሰዓት ገደማ ነበር።
ቀኑን ሙሉ ሲያደንቁ የዋሉት እንግዶች አዘኑ። ማታ 4 ሰዓት ከ10 ላይ ለአዲስ አበባ ፖሊስ ስልክ ተደዎሎ የተፈተረው ነገር ተነገራቸው።
ከዚያ በኋላ የሆነው ግን ተዓምር ነበር። አምስት ሰዓታት ብቻ አለፉ። ሌሊት 9 ሰዓት ላይ የአዲስ አበባ ፖሊስ የእንግዶቹን በር አንኳኳ። የተሰረቀውን ሞባይል ይዘው ከተፍ አሉ።
እንግዶቹ ማመን አቃታቸው። "የመንገዱን ንጽሕና፣ ኮሪደሩንና ዛፉን ስናደንቅ ውለናል" አሉ። "ይህን ተዓምር ግን ፈጽሞ አልጠበቅንም!" በማለት ተገረሙ።
አክለውም፣ "ገንዘብ ተደራድረን ከፍለን እንኳን እቃችንን እናገኛለን ብለን አላሰብንም። ፖሊስ በነፃ በራችንን አንኳኩቶ ያመጣል ብለን አልገመትንም" በማለት ታላቅ ደስታቸውን ገለጹ።
ይህንን የሰሙት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደኋላ መለስ ብለው ታሪኩን በማስታወስ፤ "ያኔ ካሜራ ለመትከል መሟገታችንና ተለምኖም ቢሆን መሠራቱ እንኳን ሆነ፤ እነሆ ዛሬ ያደረግነው ጥረት ፍሬ አፍርቶ መልሶ ከፈለን" በማለት ስሜታቸውን ገልጸዋል።
ጊዜው ከሁለት ዓመት በፊት ነበር። ከቦሌ እስከ ፌዴራል ፖሊስ ዋና መሥሪያ ቤት የደህንነት ካሜራ እንዲዘረጋ ጥያቄ ቀረበ። ፌዴራል ፖሊስ ክፍያ መክፈል አልችልም አለ። ሆኖም ፕሮጀክቱ በነፃ እንዲሠራ ተወሰነ። ይህንን ለማሳካት ለወራት የፈጀ ፍትግያ ነበረ። ድካሙ ግን ከንቱ አልነበረም።
Ethiopian Broadcasting Corporation Ethiopian Federal Police #ኢትዮጵያ #ፖሊስ

የቅሚያ ወንጀል የፈፀመው ተከሳሽ በፅኑ እስራት ተቀጣ።
ተከሳሽ ዋአልኤ ዋርዳ የቅሚያ ወንጀሉን የፈፀመው በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 ካራ ቆሬ አካባቢ ነው።
የግል ተበዳይ በግምት ከምሽቱ 1፡30 ሰዓት ገደማ ከስራ ወደ መኖሪያ ቤታቸው በሚጓዙበት ወቅት ተከሳሹ ከኃላቸው በመምጣት የግል ተበዳይ ይዘውት የነበረውን የእጅ ቦርሳ ቀምቶ ለማምለጥ ሲሞክር በፖሊስ አባላትና በአካባቢ ጥበቃዎች ትብብር እጅ ከፈንጅ መያዙን በኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ ፖሊስ ዋና መምሪያ የካራ ቆሬ አካባቢ ፖሊስ መምሪያ አስታውቋል።
ተከሳሹ በቁጥጥር ስር በዋለበት ወቅትም በቦርሳው ውስጥ የነበረውን ስማርት ሞባይልና 8 ሺህ 550 ብር በአጠቃላይ 23 ሺህ 700 ብር የሚገመት ንብረት በማስመለስ አስፈላጊው ምርመራ ከተጣራበት በኃላ አቃቤ ህግ ክስ እንደመሰረተበት ፖሊስ ገልጿል።
የተከሳሽ ዋአልኤ ዋርዳን ጉዳይ የተመለከተው የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ኮልፌ ቀራንዮ ምድብ ፈጣን የወንጀል ችሎት ጥፋተኝነቱን በሰው ማስረጃ ካረጋገጠ በኋላ ተከሳሹን ያስተምራል ሌሎች ወንጀል ፈፃሚዎችን ያስጠነቅቃል በማለት በፈፀመው የቅሚያ ወንጀል በ2 አመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ውሳኔ አስተላልፎበታል።
ማንም ሰው ወንጀል ፈፅሞ ከህግ እንደማያመልጥና የህግ የበላይነት እንደሚረጋገጥ የገለፀው የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ ህብረተሰቡ ወንጀል እንዳይፈፀምበት ተገቢውን ጥንቃቄ በማድረግ እንደ ከዚህ ቀደሙ ለፀጥታ አካላት እየሰጠ ያለውን ትብብር አጠናክሮ እንዲቀጥልም ጥሪውን አቅርቧል።

ከሁለት ተሽከርካሪዎች ላይ ስፖኪዮ የገነጠለው ተከሳሽ በእስራት ተቀጣ፡፡
የወንጀል ድርጊቱ የተፈፀመው ግንቦት 18 ቀን 2018 ዓ/ም በአራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 9 ልዩ ቦታው ድል በር ሆቴል አካባቢ ከቀኑ 7፡30 ነው፡፡
ተከሳሽ አብዱልሀኪም ፈድሉ የተባለ በተጠቀሰው ቦታ ቆመው ከነበሩ ሁለት ተሽከርካሪዎች ላይ የዋጋ ግምታቸው 58 ሺህ የሚያወጣ ሁለት ስፖኪዮዎችን በመንቀል ሊያመልጥ ሲል በወቅቱ በአካባቢው በስራ ላይ በነበሩ የፖሊስ አባላት በቁጥጥር ስር ሊውል ችሏል፡፡
ተከሳሹ በቁጥጥር ስር ከዋለም በኋላ በአራዳ ክ/ከተማ ፖሊስ ዋና መምሪያ የአራት ኪሎ ፖሊስ መምሪያ ተገቢውን የሰውና የሰነድ ማስረጃ በማጠናቀርና መዝገቡን በማደራጀት ለዐ/ህግ አቅርቧል፡፡
የወንጀል ምርመራ መዝገቡን ሲከታተል የቆየው በፌደራሉ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ 3ኛ ወንጀል ችሎት ግንቦት 27 ቀን 2018 ዓ/ም ውሎው ተከሳሽን ያስተምራል፣ ሌሎች ወንጀል ፈፃሚዎችን ያስጠነቅቃል ሲል በ2 ዓመት ከ9 ወር እስራት እንዲቀጣ ወስኖበታል፡፡
ህብረተሰቡ ወንጀል ፈፃሚዎችን በቁጥጥር ስር በማዋል ጭምር ወንጀል ጠል መሆኑን እያስመስከረ መምጣቱ የሚያስመሰግን መሆኑን የገለፀው የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ መሰል ድርጊቶች ሲያጋጥሙም በአቅራቢያ ለሚገኝ ፖሊስ ማሳወቅ እንደሚገባም መልዕክቱን አስተላልፏል፡፡

ከ33 ሚሊየን ብር በላይ ዋጋ ግምት ያለው የሞተር ዘይት የሰረቁ ግለሰቦች ላይ ክስ ተመሰረተባቸው።
የወንጀል ድርጊቱ የተፈፀመው በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ወረዳ 5 ካዲስኮ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ነው።
ናሽናል ኦይል ኢትዮጵያ አክሲዮን ማህበር ወይም ኖክ የዋጋ ግምታቸው 3መቶ ሚሊዮን ብር የሚያወጡ 200 በርሜል የሞተር ዘይት ለዊ ቢዩልድ ኮይሻ ኤሌክትሪክ ኃይል ፕሮጀክት የትራንስፖርት አገልግሎት እንዲሰጡት ከአንድ ግለሰብ ጋር ከስምምነት ላይ ይደርሳል።
በስምምነቱ መሰረት አሽከርካሪው መንጃ ፍቃድ እና ሊብሬ አቅርቦ እንዲሁም የተሽከርካሪውን ሰሌዳ አስመዝግቦ የሞተር ዘይቱ ቢጫንም ጭነቱ ኮይሻ እንዳልደረሰ ኖክ ያረጋግጣል። ጉዳዩንም ለአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ፖሊስ ዋና መምሪያ ሪፖርት ያደርጋል።
ግለሠቡ ያቀረበው ሊብሬ እና መንጃ ፈቃድ ሀሰተኛ እንደሆነ እንዲሁም ጠፍቷል ተብሎ የተመዘገበ የሌላ ተሽከርካሪ ሰሌዳን አሽከርካሪው መጠቀሙን ፖሊስ ባደረገው ምርመራ አረጋግጧል።
የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ፖሊስ ዋና መምሪያ ባደረገው ብርቱ ክትትል አሽከርካሪውን ከኖክ ጋር ያገናኘውን ግለሰብ እና ከወንጀል ድርጊቱ ጋር ተሳትፎ ያላቸውን አብዱልሠላም ወራኪ፣ አብዱራህማን ሀሰን፣ መሀመድ ቢላል፣ ደረጄ በቀለ፣ አብዱልሀፊዝ አብዱልሽኩር፣ ነጃ ካሚል የተባሉት ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር በማዋል ንብረቱን ማስመለስ ችሏል።
ኤግዚቢቶቹ በሸገር ከተማ አሸዋ ሜዳ እና በቢሾፍቱ ከተማ እንደተገኙ ዋና ፖሊስ መምሪያው ገልጿል።
ፖሊስ በወንጀሉ ጠርጥሮ በቁጥጥር ስር ካዋላቸው ተጠርጣሪዎች ውስጥ ነጃ ካሚል የተባለው ከዚህ ቀደም በግድያና በዘረፋ ወንጀሎች ተጠርጥሮ በአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ በወንጀል ምርመራ ምክትል ዋና ጠቅላይ መምሪያ ሲፈለግ እንደነበር ታውቋል።
ግለሰቡ በፖሊስ ላለመያዝ ሲሞክር ያሽከረክር በነበረው የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 3 17262 አማ መኪና ለማምለጥ ሲሞክር ጎማው በጥይት ተመቶ ተይዟል።
ተጠርጣሪው በወቅቱ መረጃ ለማጥፋት ሲል በእጁ ይዞት የነበረውን ውድ ዋጋ ያለውን ሞባይል ስልክ መስበሩ አደገኛ ወንጀል ፈጻሚ መሆኑን እንደሚያሳይ ፖሊስ አረጋግጧል።
የአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ፖሊስ ዋና መምሪያ ምርመራውን በማጠናቀቅ በአቃቤ ህግ በኩል በወንጀል ፈጻሚዎቹ ላይ ክስ እንዲመሰረት አድርጓል።
ዋና ፖሊስ መምሪያው ንብረቱን በህግ አግባብ ለናሽናል ኦይል ኢትዮጵያ አክሲዮን ማህበር አስረክቧል።
በርክክቡ ወቅት የኖክ ስራ አስኪያጅ አቶ በኩሪያ ጌታቸው በሰጡት አስተያየት እንደገለፁት ድርጅታቸው የመጡለትን ሰነዶች በተገቢው ሁኔታ ትክክለኛ ሰነድ መሆናቸውን ማረጋገጥ ሲኖርባቸው ሳያረጋግጡ ንብረቱን ለአሽከርካሪው መስጠቱ ክፍተት መሆኑን በመግለፅ በቀጣይ ስህተቱ እንዳይደገም ጥንቃቄ እንደሚደረግ ተናግረዋል።

በቡድን በመደራጀትና ጨለማን ተገን በማድረግ የመሰረተ ልማት አውታሮች ላይ የስርቆት ወንጀል የፈፀሙ 5 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ።
የወንጀል ድርጊቱ የተፈፀመው በልደታ ክ/ከተማ ወረዳ 6 ራሺያ ካምፕ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ነው።
ተጠርጣሪዎቹ ጨለማን እንደምቹ አጋጣሚ በመጠቀም ከሌሊቱ 7 ሠዓት አካባቢ ለቴሌኮም አገልግሎት የሚውል ከመሬት ስር የተዘረጋ ኬብል በተለያዩ መቁረጫዎች በመቆራረጥ ይዘው ከአካባቢው ሊሰወሩ ሲሞክሩ በስራ ላይ በነበሩ የፖሊስ አባላትና የአካባቢ ጥበቃዎች ትብብር ከነ ኤግዚቢቱ በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተጣራባቸው መሆኑን በልደታ ክ/ከተማ ፖሊስ ዋና መምሪያ የመከኒሳ አካባቢ ፖሊስ መምሪያ ገልጿል።
ፖሊስ በተጠርጣሪዎቹ ላይ ተገቢውን ምርመራ የማስፋት ተግባር እያከናወነ መሆኑን ገልጾ በቀጣይ ክስ እንደሚያስመሠርትም ጠቁሟል።
በመሰረተ ልማት ላይ የሚፈፀሙ ወንጀሎች ሀገርን ለከፍተኛ ኪሳራ የሚዳርግ ተግባር በመሆኑ ህብረተሰቡ መሰል የወንጀል ድርጊቶችን ሲመለከት እንደተለመደው በአካባቢው ለሚገኝ የጸጥታ ኃይል ጥቆማ መስጠት እንዳለበት የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ መልእክቱን አስተላልፏል።

በታክሲ መያዣ ተርሚናል ከኪስ ውስጥ ሞባይል የሰረቀው ተጠርጣሪ ፈጣን ችሎት ቀርቦ በእስራት ተቀጣ፡፡
የወንጀል ድርጊቱ የተፈፀመው ግንቦት 26 ቀን 2018 ዓ/ም በአራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 9 ልዩ ቦታው ቅድስት ሥላሴ የመገናኛ ታክሲ መያዣ ቦታ ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ነው፡፡
መትክል ሀብቱ የተባለው ተከሳሽ በተጠቀሰው ቦታ ላይ የታክሲ ትራንስፖርት አገልግሎት በመጠቀም ላይ ከነበሩ ግለሰብ ኪስ ውስጥ በመግባት የዋጋ ግምቱ 28 ሺህ ብር የሚያወጣ ሳምሰንግ ሞባይል ስልክ ሲሰርቅ በአካባቢው በነበሩ ትራንስፖርት ተጠቃሚዎችና በፖሊስ አባላት በቁጥጥር ስር ሊውል ችሏል፡፡
ተከሳሹ በቁጥጥር ስር ከዋለ በኋላ በአራዳ ክ/ከተማ ፖሊስ ዋና መምሪያ የአራት ኪሎ ፖሊስ መምሪያ ተገቢውን የሰውና የሰነድ ማስረጃ በማጠናቀርና መዝገቡን በማደራጀት ለዐ/ህግ አቅርቧል፡፡
የወንጀል ምርመራ መዝገቡን ሲከታተል የቆየው በፌደራሉ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ 3ኛ ወንጀል ፈጣን ችሎት ሰኔ 2 ቀን 2018 ዓ/ም ውሎው ተከሳሽን ያስተምራል፣ ሌሎች ወንጀል ፈፃሚዎችን ያስጠነቅቃል ሲል በ1 ዓመት ከ4 ወር እስራት እንዲቀጣ ወስኖበታል፡፡
ህብረተሰቡ ወንጀል ፈፃሚዎችን በቁጥጥር ስር በማዋል ጭምር ወንጀል ጠል መሆኑን እያስመስከረ መምጣቱ የሚያስመሰግን መሆኑን የገለፀው የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ መሰል ድርጊቶች ሲያጋጥሙም በአቅራቢያ ለሚገኝ ፖሊስ ማሳወቅ እንደሚገባም መልዕክቱን አስተላልፏል፡፡
Addis Ababa police
የወንጀል ድርጊቱ የተፈፀመው ግንቦት 26 ቀን 2018 ዓ/ም በአራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 9 ልዩ ቦታው ቅድስት ሥላሴ የመገናኛ ታክሲ መያዣ ቦታ ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ነው፡፡
መትክል ሀብቱ የተባለው ተከሳሽ በተጠቀሰው ቦታ ላይ የታክሲ ትራንስፖርት አገልግሎት በመጠቀም ላይ ከነበሩ ግለሰብ ኪስ ውስጥ በመግባት የዋጋ ግምቱ 28 ሺህ ብር የሚያወጣ ሳምሰንግ ሞባይል ስልክ ሲሰርቅ በአካባቢው በነበሩ ትራንስፖርት ተጠቃሚዎችና በፖሊስ አባላት በቁጥጥር ስር ሊውል ችሏል፡፡
ተከሳሹ በቁጥጥር ስር ከዋለ በኋላ በአራዳ ክ/ከተማ ፖሊስ ዋና መምሪያ የአራት ኪሎ ፖሊስ መምሪያ ተገቢውን የሰውና የሰነድ ማስረጃ በማጠናቀርና መዝገቡን በማደራጀት ለዐ/ህግ አቅርቧል፡፡
የወንጀል ምርመራ መዝገቡን ሲከታተል የቆየው በፌደራሉ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ 3ኛ ወንጀል ፈጣን ችሎት ሰኔ 2 ቀን 2018 ዓ/ም ውሎው ተከሳሽን ያስተምራል፣ ሌሎች ወንጀል ፈፃሚዎችን ያስጠነቅቃል ሲል በ1 ዓመት ከ4 ወር እስራት እንዲቀጣ ወስኖበታል፡፡
ህብረተሰቡ ወንጀል ፈፃሚዎችን በቁጥጥር ስር በማዋል ጭምር ወንጀል ጠል መሆኑን እያስመስከረ መምጣቱ የሚያስመሰግን መሆኑን የገለፀው የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ መሰል ድርጊቶች ሲያጋጥሙም በአቅራቢያ ለሚገኝ ፖሊስ ማሳወቅ እንደሚገባም መልዕክቱን አስተላልፏል፡፡
Addis Ababa police
2 months ago
የትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪ በመምሰል የሿሿ ወንጀልና የሞባይል ስርቆት የፈጸሙ 7 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ።
ተጠርጣሪዎቹ የወንጀል ድርጊቱን የፈጸሙት በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 6 ልዩ ቦታው ሳሪስ አቦ የትራፊክ መብራት አካባቢ ነው።
ተጠርጣሪዎቹ የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ 3 A 02122 ኦሮ በሆነ ሚኒባስ ተሽከርካሪ የትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪና ተጠቃሚ በመምሰል አዲሱ መኮንንና ኢሳያስ ደገፋ የተባሉ የግል ተበዳዮችን በመጫን ጥቂት እንደተጓዙ ኪሳቸው ውስጥ የነበረውን የሞባይል ስልክ እና ገንዘብ ለመውሰድ ሲሞክሩ የግል ተበዳዮች ወንጀሉን ለመከላከል በሚሞክሩበት ወቅት ገፍትረዋቸው በፍጥነት በመጓዝ ላይ ሳሉ ከሌላ ተሽከርካሪ ጋር በመጋጨት ቆመዋል።
በወቅቱ ድርጊቱን በተመለከተው የአካባቢው ህብረተሰብና በትራፊክ ፖሊስ አማካኝነት በተሽከርካሪው ውስጥ የነበሩ ትዕግስት ጌታቸው፣ ገነት ደሳለኝ፣ ሜላት ጌታቸው፣ እየሩሳሌም ጌታነህና መአዛ ማሞ የተባሉ ተጠርጣሪዎችን ከ6 የተለያዩ ስማርት ሞባይል ስልኮችና 11 ሚሞሪ ካርዶች ጋር ሊያዙ መቻላቸውን በወንጀል ምርመራ ም/ዋና ጠቅላይ መምሪያ የልዩ ልዩ እና የተደራጁ ወንጀሎች ምርመራ መምሪያ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
በተያዙ ተጠርጣሪዎች ላይ ተገቢው ምርመራ የማስፋት ተግባር እየተከናወነ ሲሆን ሌሎች ያልተያዙ ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር ለማዋልም ከፍተኛ ክትትል እየተደረገ መሆኑን ፖሊስ ገልጿል።
ተጠርጣሪዎቹ በተለያዩ ክፍለ ከተሞች እየተንቀሳቀሱ ወንጀሉን የሚፈፅሙ በመሆናቸው በእነዚህ ተጠርጣሪዎች ወንጀል የተፈጸመባቸው አዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ በመቅረብ ስልኮቻቸውን መረከብ እንደሚችሉ ተገልጿል።
በተያያዘም በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 ልዩ ቦታው ቡልቡላ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ፖሊስ ከህብረተሰቡ በደረሰው ጥቆማ የሞባይል ስርቆት ወንጀሉ ይፈጽማሉ የተባሉ ሀብታሙ ዮሃንስ እና አንተነህ ዮሃንስን በቁጥጥር ስር በማዋል ባደረገው ምርመራ 4 ስማርት የሞባይል ስልኮችን ሊይዝ ችሏል።
በተመሳሳይ በእነዚህ ተጠርጣሪዎችም የሞባይል ስልክ የተወሰደባቸው የግል ተበዳዮች ካሉም በአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ በመምጣት ስልኮቻቸውን በመለየት መረከብ እንደሚችሉም ፖሊስ አስታውቋል።

(ዘ-ሐበሻ ዜና) የዱባይ ፖሊስ ስለታማ መሳሪያዎችን በመጠቀም አደገኛ በሆነ የርስበርስ ግጭት ውስጥ የተሳተፉ ወጣቶችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን አስታውቋል። በተጨማሪም ይህንን የድብድብ ክስተት በቪዲዮ ቀርጾ በማህበራዊ ሚዲያ ያሰራጨ ሌላ ግለሰብም በፖሊስ ተይዟል። ፖሊስ ለካሊጅ ታይምስ እንደገለጸው፣ በሁሉም ተጠርጣሪዎች ላይ አስፈላጊው ህጋዊ እርምጃ የተወሰደ ሲሆን፣ ጉዳያቸው ለሚመለከተው የፍትህ አካል ተላልፏል።
የጸጥታ አካላቱ የህዝብን ደህንነት ለማስጠበቅ ያላቸውን ቁርጠኝነት በድጋሚ በማረጋገጥ፣ ማንኛውም የህብረተሰብ ክፍል አጠራጣሪ ወይም ህገወጥ ድርጊቶችን ሲመለከት በዱባይ ፖሊስ የስማርት ስልክ መተግበሪያ ላይ በሚገኘው የ“Police Eye” አገልግሎት በኩል ወይም በቀጥታ ወደ 999 የስልክ መስመር በመደወል ጥቆማ እንዲሰጥ አሳስበዋል።
የ“Police Eye” አገልግሎት ነዋሪዎች ማንነታቸው በሚስጥር ተጠብቆ ጥቆማዎችን እንዲሰጡ ያስችላቸዋል። ተጠቃሚዎች ፎቶዎችን፣ ቪዲዮዎችን ወይም የድምጽ መልዕክቶችን ከጥቆማቸው ጋር አያይዘው እንዲሁም የቦታውን አድራሻ ገልጸው መላክ ይችላሉ። ይህ አገልግሎት እንደ ረብሻ፣ ድብድብ፣ ከዕፅ እና መጠጥ ጋር የተያያዙ ወንጀሎችን እንዲሁም ሌሎች ህገወጥ ድርጊቶችን ሪፖርት ለማድረግ ያገለግላል።
በመጨረሻም ፖሊስ ጥብቅ ማሳሰቢያ አስተላልፏል።
የህብረተሰብ ክፍሎች እንዲህ ያሉ ህገወጥ ድርጊቶችን በቪዲዮ ቢቀርጹ እንኳ በቀጥታ ለጸጥታ አካላት ከመላክ ባለፈ፣ በምንም አይነት ሁኔታ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ መለጠፍም ሆነ ማሰራጨት በጥብቅ የተከለከለ መሆኑን አስጠንቅቋል።
ዱባይ ያላችሁ ጥንቃቄ አድርጉ።

የውጭ ሀገር ዜጎችን በመያዣነት ይዘው ገንዘብ የጠየቁ ወንጀል ፈፃሚዎች በቁጥጥር ስር ማዋሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አስታወቀ።
በኢትዮጵያ የስሪላንካ ኤምባሲ ተወካይ ግንቦት 15 ቀን 2018 ዓ/ም ለስራ ወደ ኢትዮጵያ የመጡ ሦስት የስሪላንካ ዜጎቹ እንደተሰወሩ እና ሲሪላንካ ከሚገኙ ቤተሰቦቻቸው ተደውሎ እያንዳንዳቸው 30ሺ ዶላር እንዲከፍሉ መጠየቃቸውን ግንቦት 18 ቀን 2018 ዓ/ም ለቦሌ ክፍለ ከተማ ፖሊስ ዋና መምሪያ ሪፖርት አደረጉ።
በአዲስ አበባ ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ምክትል ዋና ጠቅላይ መምሪያ ወንጀል ፈፃሚዎቹን በቁጥጥር ስር ለማዋል የክትትልና የምርመራ ቡድን በማዋቀር ወደ ስራ ገብቷል።
ፖሊስ ከሌሎች የፀጥታ ጉዳይ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመቀናጀት በቴክኖሎጂ በመታገዝ ባሰባሰበው መረጃ ሦስቱ ግለሰቦች በሰሌዳ ቁጥር ኮድ 2C- 40461 አ/አ በሆነች ሱዚኪ ዲዛየር መኪና ከኤርፖርት ተሳፍረው መሄዳቸው አረጋግጧል።
የክትትል ቡድኑ አባላት አሽከርካሪውን ጨምሮ ሁለት ኢትዮጵያውያንን እና አራት የፓኪስታን ዜግነት ያላቸውን ስድስት ወንጀል ፈፃሚዎች በቁጥጥር ስር ማዋል ችሏል፡፡
ወንጀል ፈፃሚዎቹ ሦስቱን የሲሪላንካ ዜጎች በሻሸመኔ ከተማ ወረዳ ቡቄ ቀበሌ 4 ልዩ ቦታው ደራርቱ ሆቴል ጀርባ አንድ መኖሪያ ቤት ውስጥ አንድ ክፍል ውስጥ ዘግተውባቸው እንደተገኙ የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አስታውቆ ምርመራውን አጠናክሮ መቀጠሉን ገልጿል።
ወንጀል ፈፃሚዎቹን በቁጥጥር ስር ለማዋል በተሰራው ስራ የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት፣ የፌደራል ፖሊስ፣ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር፣ በኦሮሚያ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ የሻሸመኔ ከተማ ፖሊስ መምሪያ እንዲሁም የአዳማ ፈጣን መንገድ ኢንተርፕራይዝ ከፍተኛ ድጋፍ ማድረጋቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ ገልጾ ለተቋማቱ ምስጋናውን አቅርቧል፡፡

ነገ ዝግ የሚሆኑ መንገዶች
ነገ መስቀል አደባባይ በሚደረገው የህዝብ ንቅናቄ ፕሮግራምን ምክንያት የተወሰኑ መንገዶች ለተሽከርካሪ ዝግ እንደሚሆኑ የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አስታወቀ፡፡
በርካታ ህዝብ የሚታደምበት የህዝብ ንቅናቄ በመስቀል አደባባይ ይደረጋል፡፡- በመሆኑም ፕሮግሙ ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ፦
ከመገናኛ በባንቢስ ሱፐር ማርኬት ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ኡራኤል አደባባይ
ከጎተራ ወደ መስቀል አደባባይ ጥላሁን አደባባይ ወይም መሾለኪያ ለከባድ ተሽከርካረዎች አጎና ሲኒማ
ከሜክሲኮ ወደ መስቀል አደባባይ ለገሃር መብራት
ከንግድ ባንክ ወደ አዲስ አበባ ስቴዲዩም ቴሌ መ/ቤት
ከፒያሳ በአምባሳደር ቴአትር ወደ መስቀል አደባባይ ሀራምቤ ሆቴል
ከአራት ኪሎ ወደ መስቀል አደባባይ ብሔራዊ ቤተ መንግስት
ከሜክሲኮ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው ለገሃር መብራት
በቦሌ መንገድ ወደ መስቀል አደባባይ ኦሎፒምያ ወይም ደንበል አደባባ ጋር ከለሊቱ 10 ሰዓት ጀምሮ ፕሮግራሙ እስከሚጠናቀቅ ለተሽከርካሪ ዝግ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አስታውቋል።
መረጃ ከተላለፈበት ጊዜ ጀምሮ በተጠቀሱ አካባቢ ለአጭርም ሆነ ለእረጅም ጊዜ ተሽከርከካሪ አቆሞ መሄድ የተከለከለ መሆኑን ዋና መምሪያው ገልጾ መሰል ፕሮግሞች በሚዘጋጁበት ወቅት ሆነ በሌሎች የፀጥታ ስራዎች ህዝቡ እያደረገ ላለው ቀና ትብብር የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ ምስጋናውን እያቀረበ አሽከርካሪዎች የትራፊክ መጨናነቅ እዳያጋጥማቸው አመራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ ፖሊስ መልእክቱን አስተላልፏል፡፡

ከአንድ መኖሪያ ቤት በአጥር ዘሎ በመግባት ብስክሌት የሰረቀው ተከሳሽ በፅኑ እስራት ተቀጣ።
ፈረጃ ዳኛቸው የተባለው ተከሳሽ የስርቆት ወንጀሉን የፈፀመው በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 አካባቢ ከሚገኝ አንድ መኖሪያ ቤት ውስጥ ነው።
ግለሰቡ ከለሊቱ በግምት 8፡00 ሰዓት ገደማ ከግል ተበዳይ መኖሪያ ቤት ግቢ በአጥር ላይ ዘሎ በመግባት ተቀምጠው ከነበሩ ብስክሌቶች ውስጥ 45 ሺህ ብር የሚያወጣን አንድ ብስክሌት ሰርቆ ለመውጣት ሲሞክር በግቢው አጥር ላይ ተገጥሞ የነበረ አላርም ድምፅ ማሰማቱን ተከትሎ የግል ተበዳይም የይድረሱልኝ ጥሪ በማሰማታቸው አካባቢው ላይ በነበሩ የፖሊስ አባላትና የቅጥር ጥበቃዎች ትብብር እጅ ከፈንጅ ተይዞ ንብረታቸው መመለሱን በኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ ፖሊስ ዋና መምሪያ የአውጉስታ ፖሊስ ጣቢያ አስታውቋል፡፡
በተከሳሽ ፈረጃ ዳኛቸው ላይ አስፈላጊውን ምርመራ በማጣራት መዝገቡን ለአቃቤ ህግ በመላክ ክስ እንደተመሰረተበት ያስታወቀው ፖሊስ ጣቢያው የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ኮልፌ ቀራንዮ ምድብ 3ኛ ወንጀል ችሎትም ፈረጃ ዳኛቸውን ጥፋተኝነቱን በሰው ማስረጃ በማረጋገጥ ተከሳሽን ያስተምራል ሌሎችን ያስጠነቅቃል ሲል ግንቦት 14 ቀን 2018 ዓ/ም በዋለው ፈጣን ችሎት በ5 አመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ውሳኔ እንዳስተላለፈበት ፖሊስ አስታውቋል፡፡
ጨለማን ተገን አድርገው ወንጀል የሚፈፅሙ ግለሰቦች ቀን ቀን ጥናት አድርገው በመሆኑ ህብረተሰቡ በየአካባቢው ላይ የማያውቁት ፀጉር ልውጥ ሰው አጠራጣሪ እንቅስቃሴ ሲያሳይ ለፖሊስ ማሳወቅ እንደሚገባ ያሳሰበው የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ መሰል ወንጀልን ለመከላከል የአካባቢ ቅጥር ጥበቃ ከመቅጠር ጀምሮ ህብረተሰቡ ለንብረቱ ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለበትም መልዕክት ተላልፏል፡፡

የተሽከርካሪ መስኮት በመስበር የስርቆት ወንጀል የፈጸመ ተከሳሽ በ7 ዓመት ከ9 ወር እስራት እንዲቀጣ ተወሰነበት፡፡
እንዳልካቸው ጣሰው የተባለው ተከሳሽ የወንጀል ድርጊቱን የፈፀመው መጋቢት 29 ቀን 2018 ዓ/ም ከቀኑ 7:00 ሠዓት በየካ ክ/ከተማ ወረዳ 1 ጨፌ ኳስ ሜዳ ከሚባል ስፍራ ነው፡፡
ተከሳሹ በተጠቀሰው ዕለትና ቦታ ንብረትነቱ የቅዱስ ጊዮርጊስ እግር ኳስ ክለብ የሆነውን የሠሌዳ ቁጥር ኮድ 2A-40-5-29 አ/አ ዶልፊን ተሽከርካሪ መንገድ ዳር ባቆሙበት ወቅት የተሽከርካሪያቸውን መስኮት በመስበር 4 የተለያዩ ሞዴል ያላቸውን ስማርት ሞባይል ስልኮችን ሰርቆ ይሰወራል።
የግል ተበዳዮች የወንጀሉን መፈፀም በየካ ክ/ከተማ ፖሊስ ዋና መምሪያ ለፈረንሳይ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ በማሳወቃቸው ፖሊስ ተጠርጣሪውን አፈላልጎ በመያዝ ባከናወነው የወንጀል ምርመራ ተግባር አራቱን ስልኮች በ25 ሺ ብር በመሸጥ በአካውንቱ እንዳስላከ በማረጋገጥ ብሩን በኤግዚቢትነት በመያዝ የምርመራ መዝገቡን ለአቃቤ ህግ በማቅረብ ክስ እንዲመሰረትም አድርጓል፡፡
የክስ ሂደቱን ሲከታተል የቆየው በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የካ ምድብ አንደኛ ወንጀል ችሎት ተከሳሽ እንዳልካቸው ጣሰው በፈፀመው የወንጀል ድርጊት ጥፋተኛ መሆኑን በማረጋገጡ በ7 ዓመት ከ9 ወር እስራት እንዲቀጣ ወስኖበታል።
ተሽከርካሪን ደህንነቱ ባልተጠበቀ ቦታ ማቆም ለመሰል ወንጀል ተጋላጭ የሚያደርግ መሆኑን ያስታወቀው የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አሽከርካሪዎች የወንጀል ሰለባ ከመሆናቸው በፊት ተገቢውን ጥንቃቄ ሊያደርጉ እንደሚገባም መልዕክቱን አስተላልፏል፡፡

በከባድ የሰው መግደል ወንጀል ሲፈለጉ የነበሩ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ፡፡
ዮናታን ከድር፣ ደረሰ ኃይሉና አብደላ በድር የተባሉት ተጠርጣሪዎች የወንጀል ድርጊቱን የፈፀሙት ሚያዝያ 16 ቀን 2018 ዓ/ም በን/ስ/ላፍቶ ክ/ከተማ ወረዳ 14 ልዩ ቦታው አዲስ አበባ ፉሪ ኮንዶሚኒየም አካባቢ ነው፡፡
ተጠርጣሪዎቹ ሟች ኪሩቤል ከበደ የተባለውን ስራ አለ በሚል በስልክ በመጥራት አንገቱን አንቀው ህይወቱ እንዲያልፍ አድርገዋል፡፡
አስከሬኑንም በፕላስተርና በላስቲክ በጠቅለል በልብስ መያዣ ሻንጣ ውስጥ በመክተት የሟችን የሠሌዳ ቁጥር ኮድ 3 አ/አ 50945 D4D ፒካፕ ተሽከርካሪ በመያዝ ሚያዝያ 17 ቀን 2018 ዓ/ም ከምሽቱ 3፡00 ሠዓት አካባቢ ለዕይታ ተጋላጭ በማይሆኑበት ቆጣሪ ኮንዶሚኒየም አካባቢ አስከሬኑን ጥለው ከአካባቢው ተሰውረዋል፡፡
ተጠርጣሪዎቹ ከሟች ላይ የወሰዱትን ሳምሰንግ አልትራ 21 ተንቀሳቃሽ ስልክና ተሽከርካሪውን ይዘው ወደ ሳሪስ በመጓዝ ብሔረ ፅጌ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የተሽከርካሪው ሞተር በመጥፋቱና በማስቸገሩ በአካባቢው በሚገኝ የመኪና ማሳደሪያ ቦታ በማቆም የሟችን ስልክ በመሸጥ ራሳቸውን ደብቀዋል፡፡
የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ የወንጀል ምርመራ ምክትል ዋና ጠቅላይ መምሪያ የምርመራና የክትትል ቡድኑ የወንጀል ድርጊቱ መፈፀም መረጃ ከደረሰው በኋላ 24/7 ያላሰለሰ ብርቱ ክትትል ሲያደርግ ቆይቷል፡፡
የምርመራና የክትትል ቡድኑ ከሟች ጋር ተያያዥነት ሊኖራቸው ይችላል ባላቸው መረጃዎች ላይ ሰፊ ጥናትና ክትትል በማድረግ ተጠርጣሪዎቹን የመለየት እንዲሁም ከአድካሚ ክትትል በኋላ በቁጥጥር ስር የማዋል ተግሩንም በድንቅ ብቃት ፈጽሟል፡፡
በዚህ የግድያ ወንጀል የክትትል ስራ ውስጥ የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት፣ የኦሮሚያ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ፣ የደቡብ ኢትዮጵያ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ እንዲሁም ህብረተሰቡ ላደረገው ድጋፍ የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ ምስጋናውን ያቀርባል፡፡

በተሽከርካሪ በመንቀሳቀስ የባልትና ዕቃ የሚገዙ በመምሰል ሞባይል ስልክ ስርቆት ሲፈፅሙ የነበሩ 3 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ፡፡
ተጠርጣሪዎች መቅደስ ተስፋዬ፣ ያሬድ ሙሉጌታ እና ኤፍሬም አብርሀሌ የተባሉ ሲሆን የወንጀል ድርጊቱን የፈፀሙት ግንቦት 10 ቀን 2018 ዓ/ም በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 አርባ ዘጠኝ ሎሚ ከለር የጋራ መኖሪያ ቤቶች አካባቢ ነው።
ተጠርጣሪዎቹ የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 2A 73615 አ/አ የሆነ ቪትስ ተሽከርካሪ በመጠቀም በክፍለ ከተማው የተለያዩ ቦታዎች በመንቀሳቀስ ባልትና መሸጫ ቤቶችና ብቻቸውን የሚንቀሳቀሱ ሰዎችን በመከታተል ሞባይል ስልኮችን በመቀማትና በመስረቅ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ መሆናቸው በምርመራ ተረጋግጧል፡፡
ተጠርጣሪዎቹ እንደለመዱት ግንቦት 10 ቀን 2018 ዓ/ም በክፍለ ከተማው ወረዳ 5 አርባ ዘጠኝ ሎሚ ከለር የጋራ መኖሪያ ቤቶች አካባቢ ከሚገኝ ባልትና መሸጫ ሱቅ በመሄድ የዋጋ ግምቱ 45000 ሺህ ብር የሚሆን ሞባይል ስልክ ሰርቀው በተሽከርካሪያቸው ሊያመልጡ ሲሉ በአካባቢው በነበሩ የወንጀል መከላከል የፖሊስ አባላትና በህብረተሰቡ ትብብር በቁጥጥር ስር ሊውሉ ችለዋል።
ፖሊስ ተጠርጣሪዎቹን በቁጥጥር ስር ካዋለ በኋላ በተሽከርካሪው ውስጥ ባደረገው ፍተሻ የተለያየ ሞዴል ያላቸው 4 ሞባይል ስልኮች የተገኙ ሲሆን በግለሰቦቹ ወንጀል የተፈጸመባቸው ዜጎች ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ በአካል በመቅረብ ንብረታቸውን መምረጥና መረጃ መስጠት እንደሚችሉ ተገልጿል፡፡
የወንጀል አፈፃፀም ከጊዜ ወደ ጊዜ መልኩን እየቀየረ በመሆኑ ህብረተሰቡ ተገቢውን ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለበት ያሳሰበው የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ መሰል ድርጊቶች ሲያጋጥሙም በአፋጣኝ ለፖሊስ መረጃ መስጠት እንደሚገባም መልዕክት ተላልፏል፡፡

ከሚሰሩበት ድርጅት ውስጥ ከ1ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመቱ ካሜራዎችን የሰረቁ ተከሳሾች በ7 ዓመት ከ6 ወር እስራት እንዲቀጡ ተወሰነባቸው፡፡
ተከሳሾች ዘሪሁን አበበ እና ሄኖክ አማረ ወንጀሉን የፈፀሙት ሚያዝያ 27 ቀን 2018 ዓ/ም በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 09 ልዩ ቦታው አራት ኪሎ ቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርስቲ ህንፃ ላይ ከሚገኝ አንድ የፊልም ስራዎች ኮሌጅ ነው፡፡
ተከሳሾች በኮሌጁ ውስጥ በጥበቃ ሠራተኝነትና በህንፃ እድሳት ስራ ተቀጥረው የሚሰሩ ሲሆኑ የቢሮውን ቁልፍ በማስቀረፅ ሰው ያለመኖሩን እንደመልካም አጋጣሚ በመጠቀም ጠቅላላ ግምታቸው ከ1ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጡ 2 ቪድዮ ካሜራዎች፣ 2 የካሜራ ባትሪ፣ 1 የካሜራ ቻርጀር እንዲሁም 2 ኒክ ማይክ በመስረቅ ወንጀላቸውን ለመደበቅና ከውጭ ሌባ ገብቶ የሰረቀ ለማስመሰል ጣሪያውን በመቅደድ ወንጀሉን ፈፅመዋል፡፡
የግል ተበዳይ አልኣዛር ጥላሁን በድርጅታቸው የቤት ሰብሮ ወንጀል ከተፈፀመባቸው በኋላ 4 ኪሎ ፖሊስ ጣቢያ በማመልከታቸው ፖሊስ ጠንካራ ምርመራና እና ክትትል በማድረግ ተከሳሾቹን በቁጥጥር ስር በማዋል ንብረቶቹን እንዲመለስ በማድረግ በዐ/ህግ ክስ እንዲመሰረትም አድርጓል፡፡
የምርመራ መዝገቡን ሲከታተል የቆየው የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ አምስተኛ ወንጀል ችሎት ግንቦት 10 ቀን 2018 ዓ/ም በዋለው ችሎት ዘሪሁን አበበ እና ሄኖክ አማረ እያንዳንዳቸው በ7 ዓመት ከ6 ወር ፅኑ እስራት እንዲቀጡ ውሳኔ አስተላልፎባቸዋል፡፡
የትኛውም ተቋምም ሆነ ግለሰብ የሰራተኛ ቅጥር በሚፈፅምበት ወቅት ጥንቃቄ በማድረግ ተቀጣሪዎች ያሏቸውን መረጃዎች እና ዋስትና በተገቢው ሁኔታ በማረጋገጥ መሰል ወንጀሎች ለመፈፀም ዕድል እንዳይኖራቸው ማድረግ ይኖርበታል ሲል የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ መልዕክቱን ያስተላልፋል፡፡

3 months ago
በተቀጠረች በ3ኛው ሳምንት ከ200 መቶ ሺ ብር በላይ የሚገመት ንብረት የሰረቀች የቤት ሰራተኛ በእስራት ተቀጣች።
ተከሳሽ ምስጋና ሙሉጌታ የስርቆት ወንጀሉን የፈፀመችው በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11 ልዩ ቦታው ካራ ቆሬ መብራት ኃይል ጀርባ ከሚገኝ አንድ መኖሪያ ቤት ውስጥ ነው።
ግለሰቧ በቤት ሰራተኝነት ተቀጥራ ስትሰራ ከነበረችበት መኖሪያ ቤት ውስጥ ለ ሦስት ሳምንታት ስትሰራ ቆይታለች፡፡
አሰሪዎቿ ወደ ስራ በሄዱበት አጋጣሚ ግምታቸው 267ሺህ 340 ብር የሚያወጡ የተለያዩ የአዋቂና የህፃናት አልባሳትን፣ ታብሌት ስልክ፣ የጆሮና የጣት የወርቅ ጌጣጌጥ፣ የብር ሃብል፣ የእጅ ሰዓትና 3 ሺህ 500 ብር ሠርቃ ትሰወራለች፡፡
ተከሳሿ በወቅቱ ስትቀጠር በቂ ተያዥ ባታቀርብም ፖሊስ ባደረገው ክትትል ግለሰቧ ከነበረችበት ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ጠምባሮ ልዩ ወረዳ ከእነ ንብረቱ እንተያዘች በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ የካራ አካበቢ ፖሊስ ጣቢያ አስታውቋል።
ፖሊስ በግለሰቧ ላይ አስፈላጊውን ምርመራ በማጣራት አቃቤ ህግ ክስ መስርቶባት ጉዳዩን የተመለከተው የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ኮልፌ ቀራንዮ ምድብ የወንጀል ችሎት ተከሳሽ ምስጋና ሙሉጌታ ጥፈተኛነቷን በማረጋገጡ በ5 አመት ፅኑ እስራት እንድትቀጣ ወስኗል፡፡
ህብረተሰቡ የቤት ሰራተኛ ሲቀጥር በቂ ተያዥና ማንነታቸውን የሚገልጽ መታወቂያ ያላቸው መሆኑን ማረጋገጥ እንዳለባቸው እና ወንጀል ተፈፅሞ ሲገኝም በወቅቱ ለፖሊስ ማሳወቅ እንደሚገባም መልዕክቱን አስተላልፏል።

ከ405 ሚሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ ዕቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ
የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ፣ የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽንና ሌሎች የጸጥታ አካላት ጋር በተቀናጀ መልኩ ከኅብረተሰቡ የተገኘን ጥቆማ መነሻ በማድረግ ባከናወኑት ኦፕሬሽን 405.4 ሚሊዮን ብር ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የገቢና የወጪ የኮንትሮባንድ ዕቃዎች በተለያዩ የሀገራችን አካባቢዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገልጿል።
ከሚያዚያ 29 እስከ ግንቦት 5 ቀን 2018 ዓ.ም በተካሄደው ክትትል 353.6 ሚሊዮን ብር የሚያወጡ የገቢ እንዲሁም 51.8 ሚሊዮን ብር ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የወጪ የኮንትሮባንድ ዕቃዎች የተያዙ ሲሆን በጅግጅጋ፣ በአዋሽ፣ በሞያሌ እና በሌሎችም የጉምሩክ መቆጣጠሪያ ቅርንጫፎች በተከናወነ የተጠናከረ ኦፕሬሽን በቁጥጥር ስር ከዋሉት የኮንትሮባንድ ዕቃዎች መካከል፤ አዳዲስና ልባሽ ጨርቆች፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ የግብርና ምርቶች፣ የተሽከርካሪ መለዋወጫዎች፣ የመዋቢያ ዕቃዎች፣ ጫት፣ አደንዛዥ ዕጾች፣ መድኃኒቶች፣ ማዕድናት፣ ነዳጅ፣ የቁም እንስሳትና የተለያዩ የውጭ ሀገራት ገንዘቦች እንደሚገኙበት የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን በማኅበራዊ ሚዲያ ገጹ ላይ ያጋራው መረጃ ያመላክታል።
የኮንትሮባንድ ዕቃዎቹ በጸጥታ አካላትና በጉምሩክ ኮሚሽን ባለሙያዎች የተቀናጀ ጥረት በፍተሻ፣ በጥቆማና በበረራ ኦፕሬሽኖች የተያዙ ሲሆን በሕገ-ወጥ ድርጊቱ ላይ የተሳተፉ 10 ተጠርጣሪዎችና ዕቃዎቹን ሲያዘዋውሩ የነበሩ ሰባት ተሽከርካሪዎች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተካሄደባቸው እንደሚገኝ ተጠቅሷል።
የኮንትሮባንድና ሕገ-ወጥ ንግድ የአፈጻጸም ስልት በየጊዜው ተለዋዋጭ በመሆኑ ድርጊቱን ለመግታትና በሀገር ላይ የሚያሳድረውን ዘርፈ ብዙ ጉዳት ለመከላከል ኅብረተሰቡ ለጸጥታ አካላት እያደረገ ያለውን ሁለንተናዊ ድጋፍ አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ ቀርቧል።
Ethiopian Federal Police

ህፃን በማገት ከቤተሰቡ ገንዘብ የጠየቁ ተከሳሾች በፅኑ እስራት ተቀጡ
የ6 ዓመት ህፃን በማገት ከቤተሰቡ ገንዘብ ሲጠይቁ የነበሩ ተከሳሾች በ12 እና በ9 ዓመት ፅኑ እስራት መቀጣታቸውን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፖሊስ አስታውቋል።
አንደኛ ተከሳሽ እንዳሻው በቀለ እና ሁለተኛ ተከሳሽ ጌቱ ገረመው የተባሉ ተከሳሾች የ6 ዓመቱን ህፃን ብሩክ ወልደኪዳን በዲላ ከተማ በማገትና ወደ ሲዳማ ክልል በመውሰድ ደብቀውት እንደነበር የተገለጸ ሲሆን ህፃኑን ለመልቀቅም ከቤተሰቦቹ ጋር በገንዘብ ሲደራደሩ እንደነበር በፖሊስ የምርመራ መዝገብ ተመላክቷል። የክልሉ ፖሊስ ከአጋር የፀጥታ አካላትና ከህብረተሰቡ ጋር በመቀናጀት ባደረገው ተከታታይ ክትትል ሁለቱንም አጋቾች በቁጥጥር ስር በማዋል፣ ታጋች ህፃኑን በሰላም ለወላጆቹ ማስረከብ ችሏል።
የክልሉ ፖሊስ በተጠርጣሪዎቹ ላይ ምርመራውን አጣርቶ መዝገቡን ለአቃቤ ህግ የላከ ሲሆን አቃቤ ህግም በመሰረተው ክስ መሰረት ጉዳዩን ሲመለከት የቆየው የዲላ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት 1ኛ እና 2ኛ ተከሳሽ በፈጸሙት ወንጀል ጥፋተኛ ሆነው በመገኘታቸው በ12 እና በ9 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጡ ውሳኔ አስተላልፎባቸዋል።
ፖሊስ መሰል ኢ-ሰብአዊ ድርጊቶችን በመከላከል ረገድ ከህብረተሰቡ ጋር ያለውን ቅንጅት አጠናክሮ እንደሚቀጥል በመግለጽ ወላጆች ለልጆቻቸው ደህንነት አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉና አጠራጣሪ ድርጊቶች ሲገጥሙም ለፀጥታ አካላት ጥቆማ እንዲሰጡ አሳስቧል።
Ethiopian Federal police

የንግድ ባንክ ሰራተኛዋን በአሰቃቂ ሁኔታ ገድሎ የተሰወረው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለ
#ethiopia | በሰንዳፋ በኬ ከተማ ነዋሪ እና በአሌልቱ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ ሰራተኛ የነበሩትን ወይዘሮ አዳነች ኩምሳን ህይወት ካለፈው ታህሳስ ወር ጀምሮ በአሰቃቂ ሁኔታ በመቅጠፍ ሲፈለግ የነበረው ተጠርጣሪ ፀጋዬ አሳልፈው በደብረ ብርሃን ከተማ ተያዘ።
ግለሰቡ ግድያውን የፈጸመው ታህሳስ 6 ቀን 2018 ዓ.ም ምሽት ላይ ከሟች ጋር በሆቴል ውስጥ ምግብ ሲመገቡ በተፈጠረ አለመግባባት መሆኑ ተገልጿል።
ሟች ተጠርጣሪውን ትታ በመሄዷ ምክንያት ተከትሏት በመሄድ መኪና ውስጥ ካስገባት በኋላ ጎማጣ ተብሎ በሚጠራው ስፍራ በሽጉጥ በመተኮስ ህይወቷ እንዲያልፍ ማድረጉ በፖሊስ የምርመራ መዝገብ ተመልክቷል።
ወንጀሉን ከፈጸመ በኋላ አስክሬኗን ጥሎ በመሰወሩ የሟች አካል በዱር አራዊት ተበልቶ ጭንቅላቷ ብቻ ሊገኝ ችሏል።
ተጠርጣሪው ግድያውን የፈጸመበትን መኪና እና መሳሪያ አሌልቱ ከተማ ውስጥ ጥሎ የተሰወረ ቢሆንም ፖሊስ በመኪናው ውስጥ ባገኘው የደም ዱካ እና በሽጉጡ አማካኝነት ክትትል ሲያደርግ ቆይቷል።
የፌዴራል ፖሊስ ከብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት እና ከሌሎች የፀጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት ባደረገው ኦፕሬሽን ግለሰቡን በቁጥጥር ስር ለማዋል ተችሏል።
ተጠርጣሪው በደብረ ብርሃን፣ በከሚሴ፣ በሸዋ ሮቢትና በአጣዬ ከተሞች ውስጥ የተለያዩ የሐሰት መታወቂያዎችን በመጠቀም እንደ ሰላማዊ ሰው ሲንቀሳቀስ እንደነበር ተደርሶበታል።
ፖሊስ በአሁኑ ወቅት በተጠርጣሪው ላይ ጥብቅ ምርመራ እያደረገ የሚገኝ ሲሆን ወንጀል ፈጽሞ ከህግ ማምለጥ እንደማይቻል አስታውቋል።
ለተጠርጣሪው መያዝ ትብብር ላደረጉ አካላትም ምስጋና ቀርቧል።
#justice #police #crime #federalpolice #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኛዋን በአሰቃቂ ሁኔታ በመግደል የተሰወረው ተጠርጣሪ በቁጥጥር ሥር ዋለ
የሰንዳፋ በኬ ከተማ ነዋሪ እና የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አሌልቱ ቅርንጫፍ ሠራተኛ የሆነችውን ወ/ሮ አዳነች ኩምሳ ታህሳስ 6 ቀን 2018 ዓ.ም በአሰቃቂ ሁኔታ በመግደል የተሰወረው ፀጋዬ አሳልፈው ጎንጤ የተባለው ተጠርጣሪ በደብረ ብርሃን ከተማ በቁጥጥር ሥር ውሏል።
ሟች እና ተጠርጣሪ ታህሳስ 6 ቀን 2018 ዓ.ም በምሽት በሆቴል ውስጥ ምግብ ሲመገቡ በመካከላቸው አለመግባት በመፈጠሩ ሟች ተጠርጣሪውን ጥላ በመሄዷ ተከትሏት ወደ መኪና ውስጥ ካስገባት በኋላ ''ጎማጣ" ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በሽጉጥ ትኩሶ ገድሏት ጥሎ በመጥፋቱ የሟች አስክሬን በዱር አራዊት ተበልቶ ጭንቅላቷ ብቻ መገኘቱን የፖሊስ የምርመራ መዝገብ ያመላክታል።
ተጠርጣሪው ወንጀሉን የፈጸመበትን መኪና እና ሽጉጥ በአሌልቱ ከተማ ጥሎ መሰወሩን የደረሰበት ፖሊስ በመኪናው ውስጥ የደም ዱካ እና ሽጉጡን እንደ ማስረጃ በመጠቀም ግለሰቡን በቁጥጥር ሥር ለማዋል ክትትል ሲያደርግ ቆይቷል።
የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ከብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት እና ከሌሎች የፀጥታና ደህንነት ኃይሎች እንዲሁም ከሰንዳፋ በኬ ከተማ አስተዳደር ጋር በመቀናጀት ባደረገው ከፍተኛ ክትትል ተጠርጣሪው የተለያዩ ሐሰተኛ መታወቂያዎችን በማውጣት በደብረ ብርሃን፣ በከሚሴ፣ በሸዋ ሮቢትና በአጣዬ ከተሞች ውስጥ ሰላማዊ ሰው መስሎ ሲንቀሳቀስ በቁጥጥር ሥር ሊያውል ችሏል።
ፖሊስ በተጠርጣሪው ላይ ምርመራውን አጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን ማንኛውንም ወንጀል ፈጽሞ ከፖሊስ ለመሰወር የሚሞክር ወንጀለኛ ከሕግ ማምለጥ እንደማይችል ገልጿል። ተጠርጣሪውን በቁጥጥር ሥር ለማዋል በተደረገው ጠንካራ ክትትል ትብብር ላደረጉ ኣካላት በሙሉ ምስጋናውን አቅርቧል።

Comments