9 hours ago
(ዘ-ሐበሻ ዜና) የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን ባለፉት 22 ቀናት በስልታዊ ቡድን ደረጃ ሲያካሂድ የቆየውን የምክክር ሂደት ቢያጠናቅቅም፣ ሂደቱ ግን በከባድ የገለልተኝነት ጥያቄዎች፣ በፖለቲካ ጣልቃ ገብነት እና በተሳታፊዎች አድማ የታጀበ እንደነበር በዋዜማ ራድዮ ተጋልጧል። ለተጨማሪ ሦስት ቀናት በተራዘመው በዚህ የምክክር ምዕራፍ፣ የኮሚሽኑን ተአማኒነት እና የሂደቱን ነጻነት ፈተና ውስጥ የጣሉ በርካታ ክስተቶች ተስተውለዋል።
የምክክር ሂደቱን ነጻነት ጥያቄ ምልክት ውስጥ ከከተቱት ዋነኛ ጉዳዮች አንዱ በአወያዮች እና ቃለ-ጉባኤ ያዦች ላይ የቀረበው "ለአንድ ወገን የማድላት" ከባድ ቅሬታ ነው። ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ ይህንኑ ቅሬታ ማመናቸው የችግሩን ስፋት ያሳያል። ከዚህም ባሻገር፣ የምክክር መድረኩ የሃሳብ መንሸራሸሪያ ከመሆን ይልቅ፣ ተሳታፊዎች በብሔር፣ በሃይማኖት እና በፓርቲ ማንነት ተደራጅተው የቡድን ፍላጎታቸውን በኃይል የሚያንጸባርቁበት የትግል አውድማ እየመሰለ መምጣቱ ታዝቧል። ኮሚሽኑ ይህንን አደገኛ የቡድን (Factional) እንቅስቃሴ ለማስቆም እስካሁን የወሰደው እርምጃ አለመኖሩ ሂደቱ የተሳሳተ አቅጣጫ እንዳይዝ ስጋት ፈጥሯል።
በተለይም "የሀገር ግንባታ" እና "የአዲስ አበባ ከተማ ሕጋዊ ቁመና" በሚሉት አጀንዳዎች ላይ የተደረጉት ውይይቶች የምክክር መድረኩን ጫፍ ያረገገጡ ነበሩ። የኮሚሽኑ አባል ዶ/ር አምባዬ ኦጋቶ እንዳረጋገጡት፣ በብሔራዊ ቋንቋ እና በአዲስ አበባ ጉዳይ ላይ በተነሳው ከባድ የሃሳብ ልዩነት የተነሳ ተመካካሪዎች ለሁለት ጊዜያት ያህል "አድማ" እስከመምታት እና ሂደቱን እስከማቋረጥ ደርሰዋል። ይህ ሁኔታ በዋና ዋና ሀገራዊ አጀንዳዎች ላይ ያለውን ጥልቅ ስምጥ የሚያሳይ ነው።
የምክክር ኮሚሽኑን ነጻነት እጅግ አደጋ ላይ ከጣሉት ጉዳዮች መካከል የገዢው ብልጽግና ፓርቲ በሂደቱ ላይ እያደረገ ያለው ቀጥተኛ ጣልቃ ገብነት ይጠቀሳል። ፓርቲው በምክክሩ ላይ የሚሳተፉ አባላቱን ከዋናው መድረክ ውጭ በተለያዩ አዳራሾች (በለሚ ኩራ እና ሲቪል ሰርቪስ) በመሰብሰብ የጋራ አቋም እንዲይዙ አቅጣጫ መስጠቱ፣ ምክክሩን የፓርቲው አጀንዳ ማስፈጸሚያ እያደረገው ነው የሚል ጠንካራ ትችት አስነስቷል። በተለይም "አዲስ አበባ የኦሮሚያ አካል ትሁን" የሚል የተለየ ሀሳብ ያንጸባረቁ የኦሮሚያ ክልል አመራሮችን "አቋማችሁን አስተካክሉ" በማለት ፓርቲው ማስጠንቀቁ፣ መድረኩ የነጻ ሀሳብ መፍለቂያ መሆኑን ጥያቄ ውስጥ ከቶታል።
በሌላ በኩል የምክክር ሂደቱ ግልጽነት በጎደለው አሰራር መተብተቡ ተጋልጧል። የመጀመሪያዎቹን የጥቃቅን እና ንዑስ ቡድን ምክክሮች ያላለፉ አዳዲስ ግለሰቦች፣ በኮሚሽነሮች ግላዊ ፍቃድ ብቻ ወደ ስልታዊ ቡድኑ "በፓራሹት" እየገቡ መሆኑ ተሰምቷል። በተጨማሪም፣ በመጀመሪያ ካልተወያዩበት አጀንዳ በመነሳት፣ መታወቂያቸውን እያስቀየሩ ወደ ሌላ አጀንዳ የተዛወሩ ተሳታፊዎች መኖራቸው፣ የምክረ-ሀሳብ አሰባሰቡን እና የድምጽ አሰጣጡን ታማኝነት በእጅጉ ያጎድፈዋል።
ከሐምሌ 30 ቀን ጀምሮ ለሦስት ቀናት ይካሄዳል የተባለው የርዕሰ ጉዳይ ተመካካሪ ቡድኖች የውሳኔ አሰጣጥ ምዕራፍ፣ ከላይ በተዘረዘሩት የፖለቲካ ጫናዎች፣ የአሰራር ግድፈቶች እና የሃሳብ መከፋፈሎች ምክንያት ከተቀመጠለት ጊዜ በላይ ሊወስድ እንደሚችልና ከባድ ውዝግብ ሊገጥመው እንደሚችል ከወዲሁ ተገምቷል።

24 hours ago
በፋብሪካ የሚመረቱ አልኮሎችና ትንባሆ ላይ የኤክሳይዝ ታክስ መጣል የምርቶቹን ዋጋ አንዲጨምር በማድረጉ የምርቶቹ የተጠቃሚዎች ቁጥር መቀነሱን ጥናት አሳየ፡፡
በሌላ በኩል ግን ጠጅ ፣ ጠላ ፣ አረቄ የመሳሰሉት ምርቶች ተጠቃሚያቸው መብዛቱን በጥናቱ ግኝት ተጠቅሷል፡፡
ጥናቱን ያጠናው በጤናው መስክ ጥናትና ምርምሮችን የሚያካሂደው ፍኖት የተሰኘ ድርጅት ነው ።
ድርጅቱ ይህን ጥናት ይፋ ያደረገው ከስድስት ዓመት በፊት በአልኮል እና በትንባሆ ላይ የተጣለው ኤክሳይዝ ታክስ ምን ውጤት እንዳመጣ በአማራ፣ኦሮሚያና በአዲስ አበባ ላይ ያካሄደው ዳሰሳዊ ጥናት ነው ።
በአልኮልና በትንባሆ ምርቶች ላይ የተጣለው ኤክሳይዝ ታክስ የተጠቃሚዎችን ቁጥር ከ10 እስከ 20 በመቶ እንዲቀንስ አድርጓል ሲሉ በፍኖት አሶሼት የሄልዝ ኬር ፋይናንሲንግ ባለሙያና አማካሪ የሆኑት ፕሮፌሰር አስማማው አጥናፉ የጥናቱን ውጤት ጠቅሰው ነግረውናል፡፡
በሌላ በኩል መንግስት የሚያገኘው ገቢ እንዲያድግ ማስቻሉንም በጥናቱ አረጋግጠናል ይላሉ።
የፍኖት አሶሼት መስራች አባል እና የፍኖት ፕሮጀክት ዳይሬክተር ዶ/ር ፅኑኤል ግርማ በበኩላቸው
እንደ ትንባሆ እና ሲጋራ ምርቶች በህገወጥ መንገድ አሁንም እየገቡ መሆኑን ነግረውናል።
በፍኖት አሶሼት የፋይናንሲንግ ም/ ዳይሬክተር ዶ/ር ግርማ ደዬ በፋብሪካዎች የማይመረቱ፣ የአልኮል መጠናቸውም በማይታወቁ እንደ ጠላ፣ ጠጅ እና አረቄ ያሉ መጠጦች በሰዎች ጤና ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ እያመጡ ነው ብለዋል ።
በሌላ በኩል በህገወጥ የሚገቡ ምርቶችን መቆጣጠር እንደሚገባም ጠቁመዋል ።
Via Sheger Fm

1 day ago
መዝሙረ ሄላም ላይ የተደረገ አጭር ኂሳዊ ንባብ
ከቢኒያም አቡራ
#ethiopia | አዳም ረታ ታሪክን ከነገሥታት፣ ከመሪዎች፣ ማኅበረሰቡ ባበጀው ድልድል ውስጥ ‹ላዕላይ› ከሚባሉት ደረጃዎች አንጻር አያስመለክተንም። ታሪካዊ ከሚባሉ አጋጣሚዎች ውስጥ የተዘነጉትን ጥቃቅን የታሪክ ኹነተ-ደቂቅ (micro-events) ይመርጣል። ይወስዳል መንገድ ላይ … “ቀዳዳ” በተሰኘው ታሪክ ላይ ፍንዳታውን ከሚሞት ዘመድ፣ ከሚደነግጥ ለማኝ፣ ከሚሰነጠቅ የወፍ እንቁላል፣ ከሚፈስ የእናት ወተት ጋር Micro-Macro Connection በመፍጠር የትልቁ ቀዳዳ መፈጠርን ከሚጢጢዬ ሽንቁሮች ጋር ያስተሳስርልናል። እንዲህ ያሉ የኒው ሂስቶሪሲዝም ባሕሪያትን ከዚህ ቀደም ባሳተማቸው መጻሕፍቱ ውስጥ በተለያየ መጠን እናገኛለን።
Adam Reta አዳም ረታ "መዝሙረ ሄላም" በተሰኘው በዐዲሱ መጽሐፉ ላይም በኢትዮጵያ ታሪካዊ-ፖለቲካዊ አጋጣሚ ውስጥ እንደ ዐውራ የሚታዩትን የእድገት በኅብረት ዘመቻን እንደነ-አሮን፣ እንደነቃል … ባሉ ገጸባሕርያት በኩል፣ የሰባ ሰባቱን ድርቅ በሄላም ጡት በኩል፣ “ጥላሁን ለምን ለምን ሞተ” እየተባለ ኢዮቤልዩ ቤተመንግሥት ጋር የተደረገውን ሰላማዊ ሰልፍ በሡልጣን በኩል፣ የከተማ መሬት ዐዋጅን በተለያዩ ግለሰቦች በኩል … እናያለን። በዚህም የታሪክን ትልቅ ካርታ ለመረዳት የተረሱና የጠለሉ ታሪኮችን ይመረምራል። ስለዚህ ነቁጣዊ ማኅበራዊ ክስተቶችን ወደ ታሪክ ምኩራብ በማምጣት ከትልቁ የታሪክ ምሥል ጎን ያስተያያል። ይህ ደግሞ የኒው ሂስቶሪሲዝም ኹነኛ ማጠንጠኛ ነው።
ልክ “ይወስዳል መንገድ ያመጣል መንገድ …” በተሰኘው መጽሐፉ ውስጥ ባለው “የመንግሥቱ ጊዜ” በሚለው ድርሰት ውስጥ፣ ትልቁን “የታኅሣሥ ግርግር”ን እንደ መቼት አምጥቶ የተጻፈውና የተተኮረው ግን ኹነተ-ደቂቅ (micro-events) ላይ ነው። ስለግርማሜ ንዋይ፣ ስለኮሌኔል ወርቅነህ ገበየሁ፣ ሰለጄነራል ሙልጌታ ቡሊ አይደለም የሚያትተው። ስለአንድ ብላቴና ከእንቅልፍ መነሳት፣ ስለገበጣ ጨዋታ፣ ቤተክርስቲያን ውስጥ ሕፃናትን አሰብስቦ ‹ኪራላይሶን› የሚያስብል ካሕን፣ ስለመንደር ውስጥ ሐሜቶች፣ ስለግለሰቦች ፍርሃት፣ በአጋጣሚ ስላየው አስደናቂ አሞራ … ያወጋል። የታሪክ አጋጣሚ አምጥቶ በታሪክ ውስጥ ግለሰቦች ላይ ስለሚረብበው የታሪክ መንፈስ ያትታል። ልክ እንደዚሁ መዝሙረ ሄላም ላይም ጽሑፉ ታሪክን አያብራራም፤ ነገር ግን ታሪክ እንዴት በሰው ልብ ውስጥ እንደሚኖር ያሳያል። በዚህ ኹነተ-ደቂቅ (micro-event) ምክንያት በዘመኑ ላይ ያገነገነውን ባሕላዊ እምነትን፣ የሥልጣን መዋቅርን፣ የወል ግንዛቤን አጨንቁረን እንድንመለከት ያስችለናል።
ከመንግሥት ሼልፍ ላይ ሳይኾን ከግለሰብ ጀርባ ላይ የተወሰደው የአዳም የአጻጻፍ መንገድ ከኒው ሂስቶሪስዝም ጽንሰ-ሐሳቦች ጋር በአንድ መም ላይ የሚሄዱ ናቸው። መዝሙረ ሄላም የተሰኘው ዐዲሱ የአዳም ረታ መጽሐፍ የኒው ሂስቶሪሲዝም ባሕርያትን ይጋራል። አንዳንድ ነገሮችን በዓይን መመልከት ባይቻልም በግብሩ (ቁስ ላይ በሚያደርገው ግፊት) ግን ይታወቃል። በመዝሙረ ሄላም መጽሐፍ ውስጥም አንዳንድ ነገሮችን በቀጥታ ማየት ባንችልም ቅሉ እነርሱን የሚያሳይልንን ነገሮች ግን እንቃኛለን። ዘማች ወጣት ተማሪዎችን እናያለን፤ መንግሥትን፣ ሕግንና ኃይልን ግን በቀጥታ አንመለከትም። የተማከለ ኃይል አናይም ግን የገጸባሕርያቱ የፍርሃት ምንጭ ከተማከለ ኃይል ጋር የተያያዘ ቀጭን መስመር መኖሩን እናያለን። መንግሥትም ቢኾን በቀጥታ አይገባም፤ ነገር ግን ፍርሃት እንደ ሥርዓት ዘዋሪ (system driver) ይኾናል። እንደ ሚሸል ፉኮ አገላለጽ ኃይል ከተማከለ ሥርዓት የሚመነጭ ሳይኾን በየትኛውም ቦታና ጊዜ በፍርሃት፣ በልማድ፣ በንግግር … ሊከሰት የሚችል ሂደት አይደል?
መዝሙረ ሄላም ላይ ታሪክ እንደ “circulation of social energy” ቀርቧል። መዝሙረ ሄላም ላይ መረጃ ከመንግሥት አይመጣም፤ ከግለሰብ እንጂ። የከተማ መሬት ዐዋጅም ኾነ የተማሪዎች ዘመቻ በገጸባሕርያቱ ወሬ ውስጥ ነው የሚንቀረቀበው። ይህ የመረጃ ሥርዓት ኃይል ማን እንዳለው ማን እንደሌለው ያሳያል። እንግዲህ ይህ በፉኮኛ micro-power መኾኑ ነው። በመዝሙረ ሄላም ላይ ታሪክ እንደ ወሬ እንጂ እንደ ሰነድ አይቀርብም።
ወሬ የፍርሃት ቤንዚን ነው … ፍርሃት ደግሞ በዝምታ መሸበብን ይፈጥራል … የዝምታ አፈ-ሙቅ ደግሞ ኃይለኛው እንዳይታይ ያደርጋል … የተደራጀው ኃይል ጥፋትን ሊያደርስ ባሰበ ቁጥር የወሬ ቤንዚን ይጨምራል። ሰዎች በዕቅብተ-ንግግር ራሳቸውን ሲሸብቡ ደርዝ ያለው ሙግት ይኮሰምናል፣ ንግግር ሲጠፋ ያልታወቀ አደጋ ይከሰታል፣ ፍርሃትም ይጨምራል። ያልታወቀ አደጋ ደግሞ ከታወቀ አካል ይመጣል። ስለዚህ ጥንስሱ የሚጀምረው ከወሬ እንደኾነ ያስመለክተናል። አዳም በመዝሙረ ሄላም ላይ ታሪክን እንደ “circulation of social energy” ሲያቀርብ ፕሬዝዳንት፣ ጀነራል፣ ፕሮፌሰር የኾኑ ታሪክ ከላዕላይ ያስቀመጣቸው ሰዎች አያስፈልጉትም። በአንጻሩ ሄላም ለማን እንደሳመችው ተደርጎ ብርሃኔ ያስወራው ወሬ፣ የሄላም አባት ወታደር በመኾኑ ምክንያት በካሱ፣ በሄኖክ እናት የተነዛው ወሬ እና ሄላም ከሄኖክ ጋር የተቆራረጠችበት መንገድ እንዲሁም የሄላምን የጡት ወተት በተመለከተ የተነዛው ወሬን ይጠቀማል።
መዝሙረ ሄላምን ከድኅረ-ቅኝ-አገዛዝ የኂስ መንገድ አንጻር እንመልከተው።
እውን ቅኝ-ግዛት ተረት ኾኖ ቀርቷል? በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚ፣ በሥነልቦና ረገድ የቅኝ አገዛዝ ዳናው ሙሉ ለሙሉ ጠፍቷል? አዳም በመዝሙረ ሄላም ጽሑፍ ውስጥ ከቅኝ-ግዛት በተወረሰ መዋቅር ምክንያት የተሰናከለን ሕይወት ሊያስመለክተን ይኾን?
“ከተሞች ከቅኝ ግዛት በኋላ ሁለት ዓይነት መልክ ይኖራቸዋል፤ ለጥቂቱ የተድላ፣ ለተቀረው ደግሞ የአሳር መንደር ይኾናሉ” ይላል ፍራንዝ ፋኖን። በመዝሙረ ሄላም ላይ እና “የቢሾፍቱ ልጆች ጥላሞት” የተሰኘው ድርሰት ላይም ይህንን ነው የምንመለከተው። “ይወስዳል መንገድ ያመጣል መንገድ …” በተሰኘው መጽሐፉ ውስጥ ካሉ ጽሑፎች መካከል “የቢሾፍቱ ልጆች ጥላ ሞት” አንዱ ነው። የቢሾፍቱ ልጆች ሆቴሉን ያዩታል፤ ግን አይገቡበትም። ሆቴሉ የሀገራቸው መሬት ላይ ነው፤ እነርሱ ግን ከሆቴሉ ውጭ ናቸው። መናፈሻው ውስጥ አንዲት የፈረንጅ ልጅ ጠግባ ለልጆቹ እንደ ውሻ ዳቦ ትወረውርላቸዋለች። አፈር ላይ የወደቀን ዳቦ አራግፈው ይመገባሉ። በገዛ ሐይቃቸው ዳር ላይ ናቸው፤ ሌሎች ግን በጀልባ እየተንሸራሸሩ ይንፈላሰሳሉ። ለፈረንጆቹ ያደረው ሞገስ የላንድሮቨር ተፈናጣጭ ኾኗል። ሌሎቹ ግን ከመኪናው ውጪ ናቸው። ሞገስ እንደ እነርሱ ሕጻን ቢኾንም ለፈረንጅ በማሸርገዱ የትምህርት ቤቱ ባለቤት ሲመስል ሌሎች ልጆች ግን በገዛ መምህራቸው ይብጠለጠላሉ። የቢሾፍቱ ልጆች፣ ነጻ በተባለች ሀገር እየኖሩ በቅኝ ግዛት ጥላ ይተዳደራሉ። የቢሾፍቱ ልጆች በገዛ መንደራቸው አካሉ በማይታይ የቅኝ ግዛት እጅ ይገፋሉ። ሞገስ አይናገርም፤ የሚናገርለት አለ። ልክ የቢሾፍቱ ልጆች ላይ በአንድ ከተማ ውስጥ ሁለት የከተማ ምሥል እንደምናገኘው ሁሉ “የስንብት ቀለማት” ላይም በአዲስ አበባ ውስጥ ሁለት የከተማ ምሥል እንመለከታለን። እንደ ዘድሬክ፣ ሳተርን፣ ከተስፋዬ ወደ አሸናፊ የተቀየሩ የድሎት ምሥሎች እና የእነምትክ ጉልት፣ የእትየ እልልታ የጉርሻ መሸጫ መስኮት ያሉ የእጦት ሥዕል እናገኛለን። መዝሙረ ሄላም ላይም እንዲህ ያለ በአንድ ከተማ ላይ የሁለት ምሥሎች አደባባይ እጀግ ብዙ ቦታ ይገኛል።
በሌላኛው የድኅረ-ቅኝ-ግዛት ኂስ (postcolonial criticism) መዝሙረ ሄላምን ስንመለከት መጀመሪያ ላይ “ፈረንጅ ሲያደንቀኝና ሲገረምብኝ የሰሙ የአገሬ ደነዞች በየተራ “ካላስ የኔ ጎሳ ናት” … እያሉ መሻማት ጀመሩ ትላለች - ሄላም። በኋላ ደግሞ በተነዛባት አጓጉል ወሬ … የሄላምን ጡት ንቀው፣ አንጓጥጠው፣ አባረዋት ሲያበቁ የፈረንጅ የዱቄት ወተትን ይመርጣሉ። ይህ በባሕላዊ ማንነትና በዘመናዊነት መካከል የሚዋልል ማኅበረሰብን ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ የድኅረ-ቅኝ-ግዛት አካል ነው። በሌሎቹ የአዳም ሥራዎች ውስጥ ድኅረ-ቅኝ-ግዛት አተያይ በቋንቋና በኪነ-ጥበብ ምርጫ ውስጥ እንዴት እንደሚንፀባረቅ ያሳያል። በመዝሙረ ሄላም ላይ ደግሞ ምዕራባዊው ዓለም ለአገር በቀል መፍትኼ-ሥራይ የሚሰጠው ዋጋ ዝቅተኛ መኾኑንና የኢኮኖሚ ብዝበዛው አሁንም በረቂቅ መንገድ መቀጠሉን ያሳያል። እዚህ ላይ ሥዕለማርያም የተባለችዋን ገጸባሕርይ እና በውጭ ሀገራት የተነዙ ወሬዎችን ስንጨማምር ደግሞ የበለጠ ብዙ ለማለት ያስችላል።
መዝሙረ ሄላም ላይ እጅግ ብዙ ማኅበረሰባዊ ኂስ እናገኛለን። ለአብነት ያህል አንድ ሁለቱን እንቃኝ።
“መዝሙረ ሄላም” ላይ ማኅበረሰቡ በችላ-ባይነት አልያም በኾን ተብሎነት ልጆቹን ምን ያህል ተጠቂ እንዳደረጋቸው የሚያሳይ መልክ ተንጸባርቆበታል ማለት ይቻላል። ጋሽ ክብካብና ዘመናይ ኾን ብለው ቴዲና ሄላም ላይ የሚያደርሱትን፣ ተክለማርያም የወላጁን(የዘሪቱን) ችላ-ባይነት ለአብነት ማቅረብ ይቻላል። ማኅበረሰቡ ልጆችን “የነገ ተስፋዎች” ይላል፤ ነገር ግን ዛሬያቸው ላይ አይሠራም።
ማኅበረሰብ የመማጸኛ ከተማዎችን ወደ ተጨማሪ ግፍ መሥሪያ ቦታዎች እንደሚቀይር በአዳም መጻሕፍት ላይ በብዛት እንመለከታለን። “ይወስዳል መንገድ …” ላይ … “ቀዳዳ” በተሰኘው ታሪክ ላይ ማርታ ለደበበ በምትሰጠው ፍቅር ሳቢያ የሚሠራበትን ግፍ የምታስረሳ ብትኾንም ማኅበረሰቡ ግን ተጨማሪ ግፍ የሚሠራበት መሣሪያ ኾናለች። የስንብት ቀለማት ላይ ምኒልክ ከዚያ ሁሉ እስርና እንግልት በኋላ፣ “በፊያሜታ አርፋለሁ” ብሎ ቤቷ ሲሄድ ተጨማሪ ሕመም በጆሮው በኩል ጭንቅላቱ ላይ ይሻጥበታል። መዝሙረ ሄላም ላይም፣ ሄላም “ሙዚቃዬን ከሕዝብ ጆሮ ያደርስልኛል … ያሳርፈኛል …” ብላ የተመካችበት ምናሴ እንጦሮጦስ ይጨምራታል። ማኅበረሰባችን የመስቀል ተ ሠላጢን ግብር እንዳለው፣ ከላይ አሳልሞ ከታች በአንካሴው ጉድጓድ እንደሚምስ ያሳያል። ይህም የመልእክትን ወጭት ሰብሮ የወጣ ጥበባዊ አጻጻፍ ነው። በፈጣጣው የቀረበ የትችት ኮሶ አይደለም። ድንቅ ነው!
መዝሙረ ሄላም ላይ ከምናገኛቸው ዋና ዋና ገጸባሕርያት የተወሰኑት (አሮን፣ ቃል፣ ምናሴ፣ ሄላም) ላይ መጠነኛ ቅኝት እናድርግ።
auto-fiction ዓይነት አጻጻፍ ባለው የአሮን አተራረክ ውስጥ አሮን “system observer” መኾኑን እንገነዘባለን። ሥርዓቱን ያያል፣ ዘማቹን ያስተውላል፣ ቃለጉባኤ ይይዛል፣ ችግሩን ይመለከታል፣ ይጽፋል። አሮን የተገፋ ታሪክ ድምፅ ነው፤ ንቃት አለው፣ ግን የታሪክ ሂደትን የሚቀይር ኃይል የለውም፤ ስለዚህም ያ ሁሉ የጻፈውን ጽሑፍን ያጣል። የንቃት ችግር የለበትም፤ የማኅበራዊ ንቃት ድምፅነቱን ከዘመነ አባት ጋር ባደረገው ውይይት ውስጥ ተመልክተናል። ግን ደግሞ ይህ ብቻውን የቆመ ነጠላ ነገር ነው፤ ምክንያቱም ማኅበራዊ ተሳትፎ የለበትም። ቃል የተሰኘችው ገጸባሕርይም እንደ አሮን ናት፤ ንቃት ያላት፣ system observer ናት። ማኅበራዊ ንቃት ማኅበራዊ እንቅስቃሴ ካላገዘው ግንጥል ጌጥ ነው። ቃልና አሮን ንቃት አላቸው፤ ግን ንቃታቸውን ተግባር አላገዘውም፤ ንቃቱን የሚተገብር አደረጃጀት የላቸውም። ስለዚህ ዕጣ-ፈንታቸው ውድቀት ይኾናል። በኢትዮጵያ ውስጥ የተንሰራፋውን ይህን የድግግሞሽ አዙሪት መዝሙረ ሄላም ላይ ደራሲ አዳም ረታ በሰላ ብዕር አስቀምጧል።
የደራሲና የአርታኢ ትስስር በተንጸባረቀበት በሄላም አተራረክ ውስጥ ምናሴ የተሰኘ ገጸባሕርይ እናገኛለን። ምናሴ የ-false collective consciousness ትእምርት ነው። ምናሴዎች ለሥልጣን ይሠራሉ፣ ራሳቸውን እንደ ነጻ ያስባሉ፤ ነገር ግን የሥርዓቱ የመጠቀሚያ መሣሪያ (system functionary) ናቸው። ምናሴዎች የኦልቪቴዎች ጥይት ናቸው። ምናሴዎች የሔላምዎች ስኬት ሳይኾን የገዛ ጥቅማቸውን የሚያስቀድሙ የማኅበረሰቡ አካል ናቸው። ምናሴ በሌላ መነጽር ብናየው የመንግሥት ቢሮክራት የመካከለኛው መደብ ውክል ነው። ሀገሩ ከንጉሣዊ ሥርዓት ወደ ወታደራዊ ሥርዓት ቢቀየርም፤ ከወታደራዊ ሥርዓት ወደ ሌላ ሥርዓት ቢለወጥም ምናሴያውያን ግን አይቀየሩም። ሥርዓት ይቀየራል - ምናሴያውያን አይቀየሩም፣ ትእዛዝ ይፈጽማሉ፣ ይከድራሉ። ይህ በኢትዮጵያ ፖለቲካል-ታሪክ ውስጥ የተደጋገመ፣ ግን ደግሞ ያልተስተዋለ እውነት ነው።
ሄላም የወታደር ልጅ ናት፤ እንዲያሳድጋት በአደራ የተሰጠው ቤተሰብ የሚበድላት። የሷ ዓይነት ዕጣ ከደረሰው እንደ ወንድሟ ከምታየው ቴዲ ከሚባል ልጅ ጋር ታድጋለች። መጀመሪያ የሚልዮን፣ የኋላ ኋላ የምናሴ ፍቅረኛ የምትኾን ድምፀ-መረዋ ሴት ናት። ሁሉ ነገሯን ባጣችበት ወቅት ጡቷ ተአምር ያመርታል።
በመዝሙረ ሄላም ላይ የሄላም የጡት ወተት የአንዳች ነገር ውክል ይመስለኛል። ሻዕቢያ ለታጋይ ወጣቶች ማሳደጊያ ፈልጓት ሊሰርቃት መፈለጉ በቀላሉ የሚዘለል ነገር ነው? ወተት እና ጡት በመጀመሪያ እይታ የሕፃናት ትዝታ፣ የእናትነት ምሥል፣ የእምነት እና የጾታ መነሳሳት የተዋሃዱበትም አይደል? ወተት ሕይወት ነው? የመጀመሪያ ምግብ፣ ከእናት ወደ ልጅ የሚፈስም አይደል? በክርስቲያናዊ ምልክት ንጹሕነትን አይወክልም? ወተት ከ“ቅዱስ” ወደ “ሥጋዊ” የሚያስተላልፍ ድልድይ ነው ማለት እንችል ይኾን? የሄላምን ጡት የጠባ ታማሚ ልጅ እንዴት ጤናማ ሊኾን ቻለ? የምን ትእምርት ነው? ሄላም ከብዙ ወንድ ጋር የወጣች እንደመኾኗ ለዚህ ሰናይ ግብር ለምን የሷ ጡት ተመረጠ?
ሌላው፣ መዝሙረ ሄላም ላይ ኦልቬቲን እናገኛታለን። ኦልቬቲ የግራጫ ቃጭልዋ። መዝገቡ ንፋስ መውጫ ሳለ፣ ባልንጀራው ኤልያስ የብልግና ሀሁ ሊያስተምረው እፊቱ ያቆማት ቀይ ሰሌዳ ነበረች ኦልቬቲ። መዝሙረ ሄላም ላይ ምናሴን እና ቤተሰቡን የምታሾር ዐውራ ገጸባሕርይ ኾና ትከሰታለች። መዝሙረ ሄላም እና ግራጫ ቃጭሎች በጋለሞታይቱ በኦልቬቲ ብቻ ሳይኾን በዘመነ እንድርያስ እና በመዝገቡ ዱባለም ይገናኛሉ። ነጋ ዳቦ ጋጋሪውም በ-typological space መዝሙረ ሄላም ላይ እናገኘዋለን።
መዝሙረ ሄላምን ከህላዌነት (Existentialism) አንጻር እንመልከተው። ሄላም ትርጉም በማይሰጥ ዓለም ውስጥ እንዴት እንደምትኖር እናነባለን። የሀገሯ ዳር ድንበር እንዳይነካ አባት ብታዋጣም አሳዳጊዎቿ ግን የወላጅን ፍቅር አዋጥተው አይለግሷትም። ወርቅ አበድራ ጠጠር ትነፈጋለች። ዕቃ ለማገዝ ቤቷ ድረስ ለመጣው ሚልዮን ልቧን ትሰጣለች። ሀና የሸነቆረችውን ክፍተት ለሞላችበት ውለታዋ ክፍያ ይኾን ዘንድ ሚልዮን ለሄላም የወለፈንዴ ቡጢ ያሳርፍባታል። ለሕይወት ትርጉም ለመስጠት ባስ ውስጥ ካገኘችው ሄኖክ ጋር ብትሞክርም የበለጠ የሕይወት ትርጉም ይዛባባታል። የወታደር ልጅ መኾኗ ሄላምነቷን በዜሮ ያባዘዋል። የመጨረሻው ስንብትም ከሄኖክ ጓደኛ አፎት በሚወጣ ሰይፍ መቀላት ይኾናል። ከሄኖክ ጓደኛ ጀርባ የሚውለበለበው ባንዲራ ደግሞ የሄኖክ ሸሚዝ መኾኑ ደግሞ ቁስሉን እንደ አቡሰዲቅ ያደርገዋል። ለሕይወቷ ትልቅ ትርጉም ያለውን የሙዚቃ ሥራዋን፣ “ትርጉም ወዳለው
ነገር ይቀይርልኛል” ብላ በምትተማመንበት በምናሴ ትነጠቃለች። ተአምር በሚያስብለው በጡት ወተት ምክንያት ለሕይወቷ ትርጉም ለመስጠት ትታትራለች። የጡት ወተቷን ምርምር በማድረግ ለትልቅ ዓለምአቀፍ በጎ ተፅዕኖ ታደርጋለች ተብላ የተቆጠረችው ሥዕለማርያም የዓለም አቀፍ መሳለቂያና ትችት ምንጭ ትኾንባታለች። ይህ ሁሉ ትርጉም የሌለው ድግግሞሽ ነው። ይህ ደግሞ በሳርተር የተገለጸውን “existence without essence”-ን ያሳያል።
የህላዌነት መሠረታዊ ሐሳብ ነጻነት ነው፤ ግን ነጻነት ፍርሃትን ይወልዳል። ሄላም ለአሮን ፍቅሯን መናገር ትችላለች፤ ነገር ግን ዝምታን መርጣለች። የግራጫው መዝገቡ፣ የእንጀራ እናቱ የምታደርስበትን በደል እንደሚያውቀው ሁሉ ሄላምም ክብካብና ዘበናይ የሚያደርሱባትን አድሎ ታውቃለች፤ ግን ለረዥም ጊዜ ዝም ብላለች። ሄላም፣ ሙዚቃዋን ካጣች በኋላ ወደ ባንዱ ሄዳ መጋፈጥ ትችላለች፤ ነገር ግን አትሄድም … ይህ በሳርተርኛ bad faith ነው።
የሄላም ምርጫ ዝምታ ኾነ እንጂ ደካማ ናት ማለት አይደለም። “አልተናገርኩም ማለት አላውቀውም ማለት አይደለም” የሚል ዝምታ ነው ያላት። በሌላ ጎኑ ደግሞ ዝምታዋ፣ የለመደችውን ግፍ ከማታውቀው ዐዲስ ግፍ የመምረጥ ኹኔታ ነው። ዐዳዲስ ግፎችን ለመሸሽ በዝምታ አላዋቂነት ዛጎል ውስጥ የመደበቅ ብቃት ነው። የለመደችውን ግፍ የመከላከል አቅም ስላላት ባለመደችው ግፍ እንዳያጠፏት ሠግታ በውስጣዊ ንቃተ ሕሊና የዘየደችው ብልሃት ሊኾን ይችላል። ዝምታዋ የመቆየቷ ምሥጢር ነው። ደበበ ቀዝቃዛ ገለልተኛ ነኝ የሚለው ሰው ለመኖር ሲል ሳይታወቀው ስሜቱን የሚቆጣጠርበት መንገድን ለማስታወስ ነው።
“የስንብት ቀለማት” ገጸባሕርይ የኾነው ዮሴፍም ብዙ ነገር ያውቃል፤ ግን ዝም ይላል … ፊያሜታ ቂል መስሏት ትዘባርቃለች … እሱ ግን “አልተናገርኩም ማለት አላውቀውም ማለት አይደለም” የሚል የዝምታ መልስ ይመልስላታል። እሷ ግን ዝምታው አይገባትም። የ“ቀዳዳ”ው ደበበ እና “የስንብት …” ዮሴፍ ቀዳዳውን አይሞሉትም፤ እያዩት ይኖራሉ። ዶነሮች ጥሩ ፈንድ ሲለቁ ፊያሜታ ፕሮጀክቱን ለአሳምነው ትሰጠውና ዮሴፍን “ምን ዶነሮች እኮ ጠፉ ትለዋለች” … ዝም ይላል፤ ይታዘባል።
ቃል መሣሪያ ነበር፤ በዘመነ ደበበ፣ በዘመነ ዮሴፍ፣ በዘመነ ሄላም እና በዘመነ መዝገቡ ዱባለ ግን ቃል አደገኛ ኾኗል፤ ዝምታ ኹነኛ መጠጊያ ነው … ይህ ከደርግ በኋላ የተፈጠረ “traumatized literary silence” ማሳያ ነው። ስለኾነም ተራኪዎቹ (ደበበ፣ መዝገቡ፣ ዮሴፍ እና ሄላም) ለምን ዝም አሉ ሳይኾን "ዝምታን የሚያመነጭ ሥርዓት ምን ይኾን?" ብለን እንድንጠይቅ ያደርጋል። ግለሰብ ዝም ሲል፤ ሕዝብ በጸጥታ ይዋጣል፤ የዚያኔ የተማከለው ኃይል አፍ ያወጣል።
የአዳምን ዐዲሱን መጽሐፍ "በንባብ ይለቅ" ብለን መርቀናል።
ቢኒያም አቡራ
ሐምሌ 25 / 2018 ዓ.ም

3 days ago
እኔ ውሸታም ወይም አታላይ አይደለሁም!
#ethiopia | የካምብሪጅ ዩኒቨርሲቲ የሶሺዮሎጂ ትምህርት ክፍል መምህር የሆኑት ፕሮፌሰር ጄሰን አርደይ የሌሎች ምሁራን ጽሑፎች ያለ አግባብ ተጠቅመዋል በሚል ክስ ቀረበባቸው።
ክሱ በዋናነት የተነሳው በፈረንጆቹ 2015 ባዘጋጁት የመመረቂያ ጽሑፏቸው ላይ ሲሆን በዚህ ጽሁፋቸው የምሁራን ጥናቶች በቀጥታ ያለ ምንጭ ተጠቅመዋል የሚል ነው።
ፕሮፌሰሩም በፒኤችዲ ቴሲሳቸው እና ባሳተሟቸው አካዳሚያዊ ጥናቶች ላይ የቀረበባቸውን የጽሑፍ ስርቆት ክስ አስተባብለዋል።
ፕሮፌሰሩ በጥናቶቻቸው ላይ ጥቂት የአሰራር እና የቴክኒክ ስህተቶች መከሰታቸውን አምነው እኔ ግን ውሸታም ወይም አታላይ አይደለሁም ሲሉ ራሳቸውን ተከላክለዋል።
በቀደሙት ሥራዎቼ ላይ የቴክኒክና የምንጭ አጠቃቀም ስህተቶች መኖራቸውን እቀበላለሁ ለሰራኋቸው ስህተቶችም ኃላፊነቱን እወስዳለሁ ብለዋል።
ነገር ግን አካዳሚያዊ ማጭበርበር ወይም የፁሁፍ ስርቆት ፈፅመሀል የሚለው ውንጀላ ፍፁም ከእውነት የራቀና ተቀባይነት የሌለው ነው ሲሉ ተናግረዋል።
የካምብሪጅ ዩኒቨርሲቲ በበኩሉ በሰጠው መግለጫ የቀረቡት አቤቱታዎች ላይ ጥልቅ ምርመራ መደረጉንና ፕሮፌሰሩ ምንም የፈፀሙት ስህተት የለም ብሏል።
ዩኒቨርሲቲው ውንጀላውን የፕሮፌሰሩን ስም ለማጠልሸት ሆን ተብሎ የተደረገ ነው ሲል ገልጾታል።
በተጨማሪም በርካታ ምሁራንና የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች ለፕሮፌሰሩ ድጋፋቸውን ሰጥተዋል።
ክሱ በጥቁር ምሁራን ስኬት ላይ ያተኮረ ፖለቲካዊና ርዕዮተ ዓለማዊ ጫና እንደሆነ ተናግረዋል።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#ethiopia #getutemesgen #getunews #england #cambridgeuniversity #professor

“ታሪክ በትዝታ ላይ የተጫነ ሸክም አይደለም-የነፍስ መገለጥ እንጂ”
ጋዜጠኛ ዮናስ አየለ እንደጻፈው
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ከአሚኮ ጋር ያደረጉትን ቃለምልልስ አዳምጬ እንደጨረስኩ በቃለ ምልልሱ በርዕሰ ጉዳይ ደረጃ ጎልተው ከወጡ ዋና ዋና ጭብጦች መካከል አንዱ ነገረ ታሪክ እንደሆነ ተሰምቶኛል፡፡ ታሪክ-የሀገር ውስጥና የውጭ፤ የሩቅና የቅርብ ዘመን! ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቃለ ምልልሳቸው ያንጸባረቁትን ሚዛናዊና አምክኖአዊ የታሪክ እይታና ድምዳሜያቸውን አለማድነቅ ንፉግነት ነው፡፡ የአሥራ ዘጠነኛው ክፍለ ዘመን እንግሊዛዊ የታሪክ ጸሐፊና ፖለቲከኛ ሎርድ አክተን “History is not a burden on the memory but an illumination of the soul” ብሎ ሲጽፍ “ታሪክ የነፍስ መገለጥ እንጂ በትዝታ ላይ የተጫነ ሸክም አይደለም” ማለቱ ነበር፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቃለ ምልልሳቸው ያነሷቸው የታሪክ አንኳር ጉዳዮች እስከዛሬ ድረስ በሀገራችን የታሪክ አጻጻፍ(Historiography) እና በሕዝባዊ ትርክቶቻችን(በሚዲያዎችን ጭምር) በሚገባቸው ልክ ያልተወሱ፤ ቢወሱም ፈራ ተባ እየተባሉ የሚጠቀሱ፤ አለፍሲልም ባልተገባ የፖለቲካ እይታ ደንቃራ ተደርገው የተወሰዱ የታሪክ ግርዶሽ(eclipse of the history) ሆነው የኖሩ ስብራቶቻችን ነበሩ፡፡ ከነዚህ ቁልፍ ጉዳዮች መካከል ዋነኛዎቹ አንዱ የሕዝቦች ትስስር እና መስተጋብር ታሪክ ሲሆን ሌላኛው በአገረ መንግስት ምሥረታ ውስጥ የሸዋ ጂኦ-ስትራቴጂካዊ ሚናን የተመለከቱት ናቸው፡፡
በመጀመሪያ የአማራና የኦሮሞ ሕዝቦች በኩታ ገጠም ቀዬዎቻቸው እና የታሪክ እድል በፈጠረላቸው የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚና የባህል አጋጣሚዎች እንደሌሎች ማህበረሰቦች ሁሉ መጋባት መዋለዳቸው፤መተሳሰር መዋሀዳቸው ሀቅ የመሆኑን ያህል የታሪክ ጥናት እና የትርክቶቻችን ማጠንጠኛ አለመሆናቸው ይታወቃል፡፡ ከዚህ በባሰ ሁኔታ ደግሞ በነገሥታቱ መካከል የነበረው የፖለቲካ ጋብቻና የመሪዎቻችን ማህበራዊ መሠረት ጉዳይ ነውር እስኪመስል በእውነታው ልክ ሳይጠናና፣ሳይነገርለት ዘመናት አልፈዋል ፡፡ በሌላ በኩል በሸዋና አካባቢው ለረዥም ዘመን የኖሩ ሕዝቦች በአገረ መንግሥት ግንባታ ሂደት የተጫወቱት ሚናና የሚጋሩት ቀደምት የሥልጣኔ ባለቤትነት (ታሪክ ሰሪነት-Agency) ግጥምጥሞሽ በሀገር መሪ ደረጃ መወሳታቸው እጅግ ጉልህ ፋይዳ ያለው ጉዳይ ነው ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቃለ ምልልሳቸው ያነሷቸው የታሪክ እውነታዎች ያለጥርጥር ታሪካችንንና የታሪክ ምልከታችንን ደጋግመን መመርምር እንዳለብን የሚያስገነዝቡና የወገንተኝነት ጥያቄ በሚነሳባቸው ሃይማኖታዊ የታሪክ ምንጮች እንኳን የተቀመጡ ገሃድ እውነታዎች ናቸው፡፡ መመርመር ለሚፈልግ አጥኚ እነዚህ የታሪክ እውነታዎች በየነገሥታቱ ዜና መዋዕሎች (የዐጼ አምደ ጽዮን፣ ዐጼ ሱስንዮስ፣የዐጼ ገላውዲዮስ፣ የዐጼ ሠርጸ ድንግል ወዘተ)፤ የሃይማኖት ሰነዶች፣ የታሪከ ነገሥት ቅጂዎች፣ ወደ ኢትዮጵያ መጥተው የነበሩ አውሮፓውያን ተጓዦችና ጸሐፊያን (ፍራንስስኮ አልቫሬዝ፣ ፔድሮ ፔዝ፣ ማኑኤል አልሜዳ፣ ጄሮኒሞ ሎቦ፣ ጀምስ ብሩስ፣ ኮንቲ ሮሲኒ ወዘተ ) መዝግበው በተውልን ሰነዶች ሰፍረው የምናገኛቸው፤ ከትውልድ ወደ ትውልድ ሲተላለፉ የኖሩ ቱባ መረጃዎች ናቸው፡፡
ፍራንሲስኮ አልቫሬዝ የተወልን የጽሑፍ ሰነድና ሌሎች ሀገርኛ የቃል መረጃ ምንጮች ዐፄ ልብነድንግል(1498-1532 ዓ.ም.) እንደ መሪ የአማራና የኦሮሞ ብቻ ሳይሆን ምናልባትም የሌሎች ሕዝቦችም ማህበራዊ ዳራ የነበራቸው ንጉሠ ነገሥት እንደሆኑ የሚያስረዱ ሲሆን አልቫሬዝ የንጉሱ የእናት ወንድም የነበሩት አጎታቸው ዶሪ ባህረ ነጋሽ ኦሮሞ እንደነበሩና ባህረ ነጋሽ ዶሪ ሲሞቱ ሥልጣኑ በቀጥታ ወደልጃቸው ቡሎ መሸጋገሩን ጭምር በአይኑ ያየውን ጽፏል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በትኩረት መታየት የሚገባው ጉዳይ ስለዐጼ ልብነ ድንግል የጦር አዛዦች የተነገሩ የቃል መረጃዎች ናቸወ፡፡ ከእነዚህ መካከል የንጉሠ ነገሥቱ ሠራዊት የቦረንትቻ ባሕል ያውቅ እንደነበር በተክለጻዲቅ መኩሪያ መጻፉና ከዐጼ ልብነድንግል የጦር አዛዦች አንዱ የነበረው ቱሉ ደገልሀን በመራው ከኢማም አሕመድ ጋር የተካሄደ ጦርነት የዐጼው ጦር ሲያፈገፍግ ንጉሠ ነገሥቱ “ሁሉም ቢፈራ ቱሉ እንዴት ፈራ? ” ማለታቸው ስለሠራዊታቸው ሥብጥር የሚነግረን ነገር አለ፡፡
ኦቶማን ቱርኮችን እና የዘመኑ ተላላኪዎቻቸውን ለመዋጋት የንጉሠ ነገሥቱ ሠራዊት አንድ አካል ሆነው እስከ ኤርትራ ድረስ ዘምተው ስለነበሩ የኦሮሞ ተዋጊዎች ተጋድሎ የዐጼ ሠርጸድንግል(1542-1590 ዓ.ም.) ዜና መዋእል በግልጽ አስፍሯል፡፡ እነዚህ የኦሮሞና የሌሎች ሕዝቦች ተወላጅ ወታደሮች ትግራይ እንጢጮ አካባቢ ያካሄዱትን አውደ ውጊያ ዜና መዋዕሉ ይተርካል፡፡ ለመንግሥታቸውና ለሀገራቸው እስከባሕር ጠረፍ ድረስ ዘምተው ዋጋ መክፈላቸውም ተመዝግቧል፡፡ የዐጼ ሱስንዮስ(1607-1632 ዓ.ም.) ዜና መዋእል እና በዘመኑ ኢትዮጵያ መጥተው የነበሩ የአውሮፓ(የፖርቱጋል) ተጓዦች የጻፏቸው የመረጃ ምንጮች ንጉሠ ነገሥቱ ግንደበረት፣ሐምቦና አካባቢው ቤታቸው እንደነበር፤ አጎታቸው ለማሞ እንደሚባል፣ ወላጅ እናታቸው(ሐመልማል ወርቅ) የአዛዥ ኩሎ ልጅ የነበረች፤ የዚሁ የሐመልማል ወርቅ ጎሳ ተወላጅ የሆነ ቡኮ የተባለ ኦሮሞና ሠራዊቱ ለአባይ ቅርብ የሆነች ምዕራብ ሸዋ ላይ ዐጼ ሱስንዮስ ሲያገኙት የነበረውን ደስታና የፍቅሩን ጽናት ዜና መዋዕሉ ሳይሰስት ጽፎታል፡፡ ዐጼ ፋሲል(ከ1632 እስከ 1667 ዓ.ም.) አባቱ ሱስንዮስ እናቱ የወሎ ቃሉ ሰው(እቴጌ ሥልጣን ሞገሳ የሚል ስም የተሰጣት) እንደሆነች የታሪክ ምንጮች ያስረዱናል፡፡ በ1620ዎቹ ዓመታት ጀምሮ በኢትዮጵያ ይኖር የነበረው ፖርቱጋላዊ ቄስ ጄሮኒሞ ሎቦ ስለዐጼ ፋሲል እናትና ኦሮሞ ዘመዶቻቸው በአይን ምስክርነት የሚያውቀውን ጽፏል፡፡ የእቴጌ ሥልጣን ሞገሳ አያት ስለብዝሀ ሃይማኖት አስፈላጊነት የነበራቸውን ግልጽ ፖሊሲ ጭምር ሎቦ ዘግቦታል፡፡ የዐጼ በካፋ(1721-1730 ዓ.ም.) እና የዐጼ ኢዮአስ(1747-1761 ዓ.ም.) ጎንደር መቼም ለሕዝቦች ውህደትና ትስስር ጥሩ ማሳያ ነበረች፡፡ የየጁ ኦሮሞ ገዢ የነበረው የአሚቶ ሴት ልጅ ዝነኛዋ ውቢት ልጇ ዐጼ አዮአስ ነበር፡፡ ኢዮአስ ከኦሮሞ አጎቱ ከደጃች ሉቦ ጋር ሥልጣኑን በጎንደር እንዴት እንዳጸና፤ የቤተ መንግሥቱም የሥራ ቋንቋ አፋን ኦሮሞ እንደነበረ የንጉሠ ነገሥቱ ዜና መዋዕልና በጀምስ ብሩስ ቅጽ ሁለት መጽሀፍ የተመዘገቡ የታሪክ መረጃዎች ያስረዱናል፡፡
መነሻውን ወሎ በማድረግ ጎንደር ጸንቶ የኖረው የየጁ ሥርወ መንግሥት(ወረ ሼኮች) መሥራቾች የመርሳው አባ ጌትዬ፣ የልጃቸው ጓንጉል አባ ሴሩ እንዲሁም የልጅ ልጃቸው የራስ አሊ ጓንጉል(አሊ ትልቁ) ታሪክ በኢዮአስ ዜና መዋዕል፣ በጀምስ ብሩስ መጽሐፍና በሌሎች በርካታ ሰነዶች ታሪካቸው ተዘግቧል፡፡ በኋላ ላይ በሽፈራው በቀለ(ፕሮፌሰር) እና ሞላ ትኩዬ የቀረቡ ጥልቅ ጥናቶች ይህን እውነት በዝርዝር ያስረዱናል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቃለ ምልልሳቸው እንደጠቀሱት የእነዚህ መሪዎች የፖለቲካ ጋብቻ ታሪክ የሚያሳየን በሄዱበት አገር ሁሉ የሕዝቦች ትሥሥር እና የፖለቲካ ጋብቻ የኖረ ታሪካችን እና የጉልበታችን ምንጭ እንደነበረ ነው፡፡ በዳግማዊ ዐጼ ቴዎድሮስ ዘመን የተጻፉ የታሪክ ሰነዶች የወሎዋ ገዢ ወርቂቱ ወዳጆ(የማመዶች ሥርወ መንግሥት መሪ የኢማም አሊ አባ ቡላ ባለቤት) ንጉሥ ምኒልክ ከመቅደላ እስር ቤት እንዲያመልጡ ያደረጉ፤ አጃቢ ሠራዊት አሰማርተው ምኒልክን እስከሸዋ የሸኙ እንደነበሩ በዋናነት ከጸሓፌ ትእዛዝ ገብረ ሥላሴ ታሪከ ዘመን ዘ ዳግማዊ ምኒልክ ዜና መዋዕል እና በመቅደላ አምባ እስር ላይ የነበሩ አውሮፓውያን ከጻፏቸው መረጃዎች እንረዳለን፡፡
ሥልጣኔዎቻችን ሁሉ ተደምረን ያሳካናቸው እንደሆነ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቃለ ምልልሳቸው አንስተዋል፡፡ የዐድዋ ዘመቻና ድሉ ለዚህ አንዱ ማሳያ እንደሆነ ተጨባጭ የታሪክ ምንጮች ያስረዱናል፡፡ በ1888 ዓ.ም. ለዓድዋ ዘመቻ ከመላው ኢትዮጵያ የተመመው ሠረዊት ወፍላ ላይ የነበረው ሠልፍ የንጉሠ ነገሥቱ ዜና መዋዕል እንኳን እንዲህ ይገልጸዋል፡፡ “የመኳንንቱ የጦር መሣሪያ፣ወርቁ፣ ጣፋ፣ ብሩ፣ ሙጣው፣ ጫሜው፣ ሎሚታውና ኩፊታው፣ ከሌቻው፣ ወርቅ ለምዱ እንደጸሐይ ሲያበራ ዋለ፡፡” እንደጸሐይ የበራውን ሕብረ ባሕልና ሕብረ ማንነት ትርክቶቻችን በልኩ አጉልተው ያውቃሉ?
ሸዋና አካባቢው(ወሎን ጨምሮ) እንደ አንድ ጂዞ ስትራቴጂ ሥፍራ የሕዝቦች ውህደትና ትስስር መሠረት ሆኖት የመልክዓ ምድር መገኛው ለግብርና እና ለውጭ ንግድ የተመቸ በመሆኑ በኢትዮጵያ አገረ መንግሥት ግንባታ ታሪክ ውስጥ ቁልፍ ቦታ ይዞ መኖሩን ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቃለ ምልልሳቸው መግቢያ አስታውሰውናል፡፡ ሸዋና አካባቢው ከመንግሥታት ምስረታ ጋር በተገናኘ ከዘጠነኛው አንስቶ እስካሁን ያለው ረዥም የታሪክ ጉዞ በርግጥም ሊነገር፣ ሊተነተን የአደባባይ ትርክት አካል ሊደረግ የሚገባው እውነት ነው፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከሸዋ ሡልጣኔት ምስረታ( እ.አ..አ.896 ዓ.ም.) እስከ ዓድዋ ድል(1888 ዓ.ም.) ሥላወሷቸው የአርጎባ(የወላስማ/ወሊ አስማ ሥርወ መንግሥት)፣ የአማራ(ሰለሞናዊ ሥርወ መንግሥት)፣ ኦሮሞ(ቱለማው በተለይ)፣ወርጂ፣ ጉራጌ፣ ጋፋት፣ ወዘተ ሕዝቦች ትስስርም ይሁን የፖለቲካ ጋብቻ የተመለከተ ታሪክ ከበቂ በላይ የታሪክ ማስረጃ ምንጮች ቢኖሩንም በታሪክ ግርዶሹ ምክንያት የወል ትርክት አካል መሆን አልቻለም፡፡
ኤንሪኮ ቼሩሊ ከሐረር አግኝቶ ያሳተመው በአረብኛ የተጻፈው የሸዋ ሡልጣኔት ዜና መዋዕል እንደሚያመለክተው ሡልጣኔቱን እ.አ.አ. በ896/7 የመሰረቱት የማህዙሚ ጎሳ አባላት ናቸው፡፡ መንግሥታቸውም ከ9ኛው እስከ 13ኛው ክፍለ ዘመን ድረስ በተከታታይ በገዙ አሥራ አራት ሱልጣኖች እንደጸና የታሪክ መረጃ ምንጮች ያመለክታሉ፡፡ የሸዋ ሙስሊም ሡልጣኔቱ መቀመጫ ከተማ ከአዲስ አበባ በስተሰሜን ምሥራቅ 70 ኪሎ ሜትር ላይ የምትገኝ ወለላ የተባለች ሥፍራ እንደነበረች የጆርጅ ደብሊው ቢ ሀንቲንግፎርድ(1989) ጥናት ያመለክታል፡፡ የማህዙሚ ሥርወ መንግሥት ከመጨረሻዎቹ መሪዎች አንዱ የነበረው ሡልጣን ድልመራህ ወርጂዎች የይኖሩበት በነበረው አካባቢ በ1270ዎቹ በነበረ የርስ በርስ ጦርነት ድል ሳይቀናው ሲቀር ሕይወቱን ለማትረፍ ዐጼ(የአማራ ገዥ?) እንደሄደ ይህው የአረብኛ ዜና መዋእል ያስረዳል፡፡ የማህዙሚዎች የሸዋ ሡልጣኔት የተተካው በዋናነት የአርጎባዎች አገር በሆነው ይፋት(ዊፋት) ላይ በወላስማዎች ነበር፡፡ ወላስማዎች ከአጎራባቾቻው ጋር እየተጋቡ፣ እየተስማሙም እየተጋጩም የይፋት ሡልጣኔትን ከ13ኛው እስከ 15ኛው ክፍለ ዘመን ከሸዋ እስከ ምሥራቃዊ የኢትዮጵያ ጠረፍ እንዳስተዳደሩ ስፍር ቁጥር የሌለው የሰነድ( የኢብን ካልዱን ተማሪ የነበረው አል ማቅሪዚ ጽሑፍ- ኪታብ አል ኢልማም)፣ የአርኪዮሎጂና የቃል መረጃ ምንጮች አሉ፡፡
መነሻውን ሰሜን ሸዋ እና ደቡብ ወሎ ያደረገው የክርስቲያኑ ሰሎሞናዊ ሥርወ መንግሥት በአካባቢው ያሉ ሕዝቦች ተዋህደው ከ13ኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ በጋራ የመሠረቱት እንደሆነ አያጠያይቅም፡፡ አማራዎች፤ አርጎባዎች፣ ወርጂዎች፣ ጋፋቶች፣ ጉራጌዎች እና ኦሮሞዎች፣ አፋሮች፣ ሐረሪዎች ወዘተ በዚህ የሸዋ መንግሥታት የተጽዕኖ ምህዳር(Orbit) ውስጥ እንደሚገኙ ዜና መዋእሎች፣ የሃይማኖት ሰነዶች፣ የአርኪዮሎጂ ማስረጃዎች ከትውልድ ወደ ትውልድ ሲተላለፉ የኖሩ የቃል መረጃ ምንጮች ያመለክታሉ፡፡ ለምሳሌ ታደሠ ታምራት(ፕሮፌሠር) ከ13ኛው እስከ 16ኛው ክፍለ ዘመን የቤተ ክርስቲያንና መንግሥትን ግንኙነት ታሪክ ባጠኑበት መጽሐፋቸው የገላንና ያያ ሰዎች ሸዋ ውስጥ በ13ኛው ክፍለ ዘመን በኦዳ ዛፍ (ኮቢል የሚባል ዋርካ) ሥር ሃይማኖታዊ ሥርዓት ይፈጽሙ እንደነበር ገድለ አቡነ ቀውስጦስን ጠቅሰው ጽፈዋል(ገጽ 184)፡፡ ሸዋ የባለ ብዙ ማንነት ሕዝቦች ሀገር ከመሆኗ ባሻገር በ16ኛው ክፍለ ዘመን የተከናወኑ ዐበይት ጉዳዮች ላይ መረጃ የተወልን መነኩሴው አባ ባህሪይ እንደገለጸው “ሸዋ የመንግሥት ሀገር ነች” (ገጽ 130)፡፡ በየዘመናቱ ከሸዋ የተነሱ የፖለቲካ ኃይሎች፣ ፈረሰኛ ሠራዊታቸውን ይዘው በሰሜን እስከ ኤርትራ(በዐጼ ሠርጸ ድንግል ዘመን- የኤርትራዋ ባሬንቱ የዚህ የታሪክ ሂደት ውርስ አይደለችም ማለት አይቻልም፡፡) በምሥራቅ እስከ ዘይላ(ከዐጼ አምደጽዮን እስከ ገላውዲዮስ ዘመን)፣ በምዕራብ እስከ ሱዳን ፋዞግሊ(ዐጼ ሱስንዮስ ዘመን) በደቡብ እስከ ሞያሌ ተንቀሳቅሰው በአገረ መንግሥት ግንባታ ሂደት ውስጥ ቁልፍ ሚና ተጫተዋል፡፡
እነዚህ የሸዋ እና አካባቢው ሕዝቦችና ገዢዎች ትልቁን ንቅናቄያቸውን ያደረጉት ግን በ19ኛው ክፍለ ዘመን እንደሆነ ይታወቃል፡፡ ዐጼ ምኒልክና ራስ ጎበና ዳጬ የቱለማ ኦሮሞ፤ የሸዋ አማራ እና የሌሎችም ውህድ የሆነ ጦራቸውን አዝምተው ወሎ ወግተው ወረኢሉን የመንሥታቸው መቀመጫ ያደረጉት አርሲ፣ወለጋ፣ከሐረር ከመዝመታቸው በፊት ነበር፡፡ የመጫ ኦሮሞ ተወላጁን የጎጃሙን ንጉስ ተክለሃይማኖት(አዳል ተሰማ) በቱለማው መሪ ራስ ጎበና ዳጪ እምባቦ ላይ ያስገበሩት የጂኦ ፖለቲካዊ እና የሕዝቦች ትስስር እድሎች ጉልበት ፈጥሮላቸው፤ ኃይል አጎናጽፏቸው እንጂ በአጋጣሚ አይደለም፡፡ በርግጥ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የፖለቲካችን ደንቃራነት የፈጠረውን የታሪክ ግርዶሽ ያሸነፉ ፋና ወጊ ጥናቾች መውጣት ጀምረዋል፡፡ አንዱ “Invisible Actors: The Oromo and the Creation of Modern Ethiopia(1855-1913)” በሚል ርዕስ በብሪያን ጀምስ ዬትስ(2002) በኤሊኖይስ ዩኒቨርሲቲ ከተጠናው እጅግ ጠቃሚ የዶክትሬት ዲግሪ ማሟያ ጥናት ሲሆን ሌላው የደቻሳ አበበ(ዶ/ር) ጎበና ወታደራዊና ፖለቲካዊ ሕይወት ነው፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቃለ ምልልሳቸው የዘመናዊት ኢትዮጵያን እውን መሆን ያለ ምኒልክና ያለ ጎበና እንደማይታሰብ ሲጠቅሱ ይህንን እውነታ ማጉላታቸው ይመስለኛል፡፡
የሕዝቦች ትስስርና የፖለቲካ ጋብቻ በአማራና በኦሮሞ ሕዝብ መስተጋብር ብቻ የታጠረ አልነበረም-ሊሆንም አይችልም፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ ባህልና ሥልጣኔ መጋመዱ ረቂቅ ነው፡፡ ከጥንታዊ አክሱም ዘመን ጀምሮ በዝነኞቹ የአክሱም መቃብር ሀውልቶች እና በላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት ላይ ከምናገኛቸው የኪነ ሕንጻ ትእምርቶች(Symbols) መካከል የውሸት በሮች (False Doors) እና የውሸት መስኮቶች(False windows) የሙታን መንፈስ(ኤከራ) መመላለሻ እንደሆኑ በጥናት የተረጋገጠ ነው (ቢትራይስ ፕሌይን Annales d'Éthiopie 1965) ፡፡ ይህ የኤከራዎች መመላለስና የመነጋገር ባህል እና እምነት ከደቡባዊ ግብጽ አንስቶ እስከ ሰሜን ኬንያ ድረስ በሚኖሩ የኩሽ ሕዝቦች በሰፊው የሚታወቅ ረዥም ዘመን ያስቆጠረ ልምምድ ነው፡፡
ሌላው በልኩ ያልተጠና እና በትርክቶቻችን ውስጥ ትኩረት ያልተሰጠው በሕዝቦች መካከል ያለ ሥልጣኔ ትስስር ታሪክ የእያንዳዱን የዛግዌ ነገሥታት የሥልጣን ዘመናትን የተመለከተ ነው፡፡ ከታሪክ ነገሥት፣ ከልዩ ልዩ ዜና መዋዕሎች፣ ከፖርቱጋል ተጓዦች(ፓኤዝና አልሜዳ) ከብሪቲሽ ሙዝየም እንዲሁም ከኮንቲ ሮሲኒ የተገኙት ምንጮች የሚረጋግጡት የሁሉም የዛግዌ ዐጼዎች( ከአንድ ሁለቱ በስተቀር) የሥልጣን ዘመን 40፤40 ዓመታት ነበር፡፡ ይህ ጉዳይ በኦሮሞ የገዳ ሥርዓት የአንድ ትውልድ የሥልጣን ዑደት ጋር አንድ አይነት የሆነው በአጋጣሚ ነው ወይስ ዛግዌዎች እና ኦሮሞዎች የኩሽ ሕዝቦች በመሆናቸው ቀዳሚ ከሆነው የጋራ ሥልጣኔያቸው የሚቀዳ የአስተዳደር ሥርዓት ነው? እነዚህስ ሀቆች የወል ትርክቶቻችን መመሆን አለመቻላቸው በፖለቲካ ደንቃራነት የተፈጠረ የታሪክ ግርዶሽ(eclipse of history) እንጂ ሌላ ምን ሊባል ይችላል? በላሊበላ አብያተ ክርስቲያናትና እና በሸዋ በሚገኘው የአዳዲ ማርያም ቤተ ክርስቲያን ኪነሕንጻ መካከል ያለው ፍጹም ተመሳሳይነት ምንጩ ምንድነው? ሊጠና፣ ሊነገር ልንማርበት ይገባል፡፡
በርግጥም ታሪካችን ትዝታችን ላይ የተጫነ ሸክም ሳይሆን የነፍስ መገለጥ ነው የሚያሰኘው የሕዝቦች ትሥሥር፣ ውህደት የሥልጣኔ መጋራትና መወራረስ ታሪክ መታወቁ መንፈስን ሃርነት ማውጣቱ ይመስለኛል፡፡

6 days ago
የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ የCGIAR የመጀመሪያው የቦርድ ሊቀመንበር ሆነው ተሾሙ
#ethiopia | የቀድሞ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ቦሼ በዓለም አቀፍ የግብርና ምርምር ትብብር ተቋም CGIAR አዲስ የተዋቀረው የቦርድ የመጀመሪያ ሊቀመንበር ሆነው መሾማቸውን ተቋሙ በይፋ አስታውቋል። ሹመታቸው ከነሐሴ 1 ቀን 2026 ጀምሮ በይፋ ተግባራዊ ይሆናል።
እንደ CGIAR መግለጫ፣ አዲሱ ቦርድ የተቋሙን የዓለም አቀፍ የግብርና ምርምር ሥራዎች በማስተባበር በምግብ ዋስትና፣ በግብርና ምርታማነት፣ በአየር ንብረት ለውጥን የመቋቋም አቅም እና በተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ዙሪያ የሚከናወኑ ስትራቴጂያዊ ውሳኔዎችን ይመራል።
ሹመቱ የተካሄደው ለወራት የዘለቀ የምልመላና የእጩ ምርጫ ሂደት ተጠናቆ ሲሆን፣ ኃይለማርያም ደሳለኝ በግብርና ፖሊሲ፣ በአህጉራዊ እና ዓለም አቀፍ ትብብር፣ እንዲሁም በሳይንስን መሠረት ባደረገ የልማት አመራር ያላቸው ልምድ ለሹመታቸው ዋና ምክንያት መሆኑን ተቋሙ ገልጿል።
የCGIAR ጊዜያዊ የቦርድ ሊቀመንበር ፕሮፌሰር ሮኤል መርክስ በሰጡት መግለጫ፣ ኃይለማርያም በሳይንስ ላይ የተመሰረተ የግብርና ልማትን ለማራመድ ያላቸው ልምድና አመራር ለተቋሙ ትልቅ እሴት እንደሚያመጣ ገልጸዋል።
ኃይለማርያም ደሳለኝ ከ2019 ጀምሮ የAGRA (Alliance for a Green Revolution in Africa) ቦርድ ሊቀመንበር በመሆን ሲያገለግሉ የቆዩ ሲሆን፣ በተጨማሪም የTradeMark Africa ቦርድን ጨምሮ በበርካታ ዓለም አቀፍ ተቋማት የአመራር ሚና እየተወጡ ይገኛሉ።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)

የ5 ዓመቱ የትምህርት ሪፎርም፦ ምን ተሰራ? ምን ተለወጠ?
#ethiopia | በኢትዮጵያ ባለፉት አምስት ዓመታት የተካሄደው የትምህርት ሪፎርም በሥርዓተ ትምህርት፣ በመሠረተ ልማት፣ በትምህርት ጥራት እና በዲጂታል አገልግሎት ዘርፎች ጉልህ ለውጦችን ማስመዝገቡን የትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ገልጸዋል።
ፕሮፌሰር ብርሃኑ እንደገለጹት፣ በዚህ ጊዜ ውስጥ የትምህርት ጥራትን የሚያሻሽል አዲስ ሥርዓተ ትምህርት ተተግብሯል፤ ደረጃቸውን የጠበቁ ትምህርት ቤቶች ተገንብተዋል፤ በተለይ ተሰጥኦ ያላቸውን ተማሪዎች ለማብቃት የሚያገለግሉ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤቶችም ተቋቁመዋል።
በመሠረታዊ ትምህርት ዘርፍ የመማሪያ መጻሕፍትን "አንድ ተማሪ አንድ መጽሐፍ" (1፡1) በሚል መርህ ለተማሪዎች ማዳረስ መቻሉ ተጠቅሷል።
እንዲሁም የተማሪዎች የምገባ መርሃ ግብር ሽፋን በስፋት መጨመሩ የትምህርት ተሳትፎን እና የተማሪዎችን የመማር አቅም ለማጠናከር አስተዋፅኦ እንዳበረከተ ተገልጿል።
ከትምህርት ጥራት ጋር በተያያዘ የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ከኩረጃ ነፃ እንዲሆን የበይነ መረብ (Online) ፈተና ሥርዓትን ማስፋፋት ከተሳኩ ለውጦች አንዱ መሆኑን ሚኒስትሩ አስታውቀዋል።
ይህም የፈተናዎችን ተዓማኒነት ለማሳደግ እና የትምህርት ሥርዓቱን ተጠያቂነት ለማጠናከር እንደረዳ ተገልጿል።
በከፍተኛ ትምህርት ዘርፍም የዩኒቨርሲቲዎች አስተዳደር በብቃት ላይ የተመሠረተ እንዲሆን ሥርዓት መዘርጋቱ፣ የዩኒቨርሲቲ ቦርዶችና አመራሮች ከአካባቢያዊ ተፅዕኖ ውጪ በብቃት እንዲመረጡ መደረጉ እና ተቋማት በተልዕኳቸውና በልዩ ተልእኳቸው መሠረት እንዲመሩ መደረጉ ተጠቅሷል።
በተጨማሪም 9 ዩኒቨርሲቲዎች ወደ ራስ ገዝ አስተዳደር ለመሸጋገር በሂደት ላይ መሆናቸው የተገለጸ ሲሆን፣ ይህ የተቋማቱን ተጠያቂነት፣ ውጤታማነት እና የውሳኔ አሰጣጥ ብቃት እንደሚያሳድግ ተጠቁሟል።
የትምህርት ሚኒስቴሩ በዲጂታል ሽግግር ረገድም 22 የሶፍትዌር ሥርዓቶችን በራሱ አቅም በማበልጸግ የአገልግሎት አሰጣጡን ማዘመንና ማቀላጠፍ መቻሉን ገልጿል።
ይህም በመረጃ አያያዝ፣ በተማሪዎች እና በመምህራን መረጃ ሥርዓት፣ እንዲሁም በአስተዳደራዊ ሥራዎች ቅልጥፍናን ለማሳደግ አስችሏል።
ሚኒስቴሩ በመጪዎቹ ዓመታትም የተጀመሩትን የትምህርት ጥራት ማሻሻያ ሥራዎች ይበልጥ በማጠናከር፣ ተደራሽነትን በማስፋት፣ ዲጂታል ቴክኖሎጂን በማጠናከር እና የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን ውጤታማነት በማሳደግ ላይ ትኩረት እንደሚያደርግ አረጋግጧል።

7 days ago
የ18 አመቱ ፕሮፌሰር
በ18 አመቱ የፕሮፌሰርነት ማዕረግ ያገኘው ናታን ቶማስ የ300 አመት ታሪክ ቀየረ
#ethiopia | ለ300 ዓመታት በላይ ተይዞ የቆየውን የጊነስ ቡክ ሪከርድስ ታሪክ የ18 አመቱ ናታን ቶማስ በእጅ አስገብቷል።
ናታን ቶማስ ይህንን ድንቅ ስኬት መጎናጸፍ የቻለው እ.ኤ.አ በ1717 በ19 ዓመታቸው ፕሮፌሰር በመሆን ለ306 ዓመታት ያህል ሪከርዱን ይዘው የቆዩትን ስኮትላንዳዊውን የማቲማቲክስ ሊቅ ኮሊን ማክላውሪን በመበለጥ አዲሱ ባለታሪክ ለመሆን ችሏል።

ገና በ10 ዓመቱ በማያሚ የኮሌጅ ትምህርቱን የጀመረ ሲሆን በ14 ዓመቱ ደግሞ ወደ ፍሎሪዳ ኢንተርናሽናል ዩኒቨርስቲ በመዛወር ከፍተኛ ትምህርቱን ተከታትሏል።
የናታን ኢዚህ ደረጃ የመድረሱ ዋናው ምክንያት ወላጆቹ እንደሆኑ ይናገራል።
የናታን እናትና አባት ህዳዊ ሲሆኑ ሁለቱም በኢንጂነሪግ ትምህርት የተመረቁ ናቸው።
እሱም በዚህ የትምህርት ዘርፍ የመመረቁም ምክንያት የወላጆቹ ተጽዕኖ እንደሆነ ነው የተናገረው።
አብዛኞቹ የናታን እኩዮች የዩኒቨርሲቲ ትምህርት ለመጀመር በሚዘጋጁበት እድሜ ላይ ናታን በ18 ዓመቱ በኤሌክትሪካል ኢንጂነሪንግ የመጀመሪያ እና የሁለተኛ ዲግሪውን በከፍተኛ ማዕረግ አጠናቋል።
ናታን ቶማስ ሲናገር እንዳህ ይላል እድሜ እዚጋ ቦታ የለውም የሚል።
ትኩረቴ ስራዬን በአግባቡ መስራትና ተማሪዎችን በምችለው መንገድ ሁሉ መርዳት ነው አሁን ፍላጎቴ ሲል ተናግሯል።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#ethiopia #getutemesgen #getunews #professor #guinnessworldrecords #nathanthomas

Sponsored by
Surafel
8 days ago
በትግራይ ክልል የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና በወረቀት እየተሰጠ ነው
#ethiopia | በትግራይ ክልል ለሚገኙ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች የሚሰጠው የሀገር አቀፍ ማጠናቀቂያ ፈተና በወረቀት በአዲስ አበባ፣ በመቐለ እና በአክሱም ዩኒቨርሲቲዎች በተዘጋጁ ማዕከላት እየተሰጠ መሆኑ ተገልጿል።
የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ፕሮፌሰር ክንደያ ገብረሕይወት በአዲስ አበባ የሚገኘውን የፈተና ማዕከል ጎብኝተው፣ መንግሥት ባደረገው ዝግጅት መሰረት የትግራይ ተማሪዎች በተለያዩ ማዕከላት ፈተናቸውን በሰላም መጀመራቸውን ገልጸዋል።
እንደ ሚኒስትር ዴኤታው ገለጻ፣ በአክሱም፣ በመቐለና በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲዎች ከ15 ሺህ በላይ ተማሪዎች በወረቀት የሚሰጠውን ፈተና እየወሰዱ ሲሆን፣ በክልሉ በሚገኙ አራት ዩኒቨርሲቲዎች በበይነ መረብ (ኦንላይን) የተሰጠው ፈተናም በተሳካ ሁኔታ መጠናቀቁን አስታውቀዋል።
ፕሮፌሰር ክንደያ በሁሉም የፈተና ማዕከላት የሚፈተኑ ተማሪዎች በመረጋጋት ፈተናቸውን እንዲወስዱ በመመኘት፣ መልካም ውጤት እንዲያስመዘግቡ ምኞታቸውን ገልጸዋል።
በሌላ በኩል የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ተፈራ ፈይሳ፣ ፈተናው መጀመሩ የክልሉ ወጣቶች ትምህርታቸውን በመቀጠል የወደፊት ዕድላቸውን እንዲያሻሽሉ ጠቃሚ እንደሆነ ገልጸዋል። እንዲሁም ተማሪዎች ያለምንም እንግልትና ስጋት ፈተናቸውን እንዲወስዱ የፀጥታ አካላትና የፈተና አስተባባሪዎች የተቀናጀ ድጋፍ እያደረጉ መሆኑን ጠቁመዋል።
በዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ከ30 ሺህ በላይ የትግራይ ክልል ተማሪዎች በወረቀትና በበይነ መረብ በአዲስ አበባ፣ በመቐለ እና በአክሱም ዩኒቨርሲቲዎች ፈተናቸውን እየወሰዱ መሆኑ ተገልጿል።

9 days ago
በሆነ በዘመን የቀረውን እኔን የመለሰ አልበም!
የአህመድ ተሸመ (ዲንቢ) “ጊዜ አይሄድም”!
ተስፋዬ እሸቱ (ረ/ፕሮፌሰር)
#ethiopia | መቸም የአህመድ ተሾመ (ዲንቢ) ድንቅ የዜማ ደራሲነት ሰብዕና ለድርድር የሚቀርብ አይደለም፡፡ ለራሱ የሠራቸውን ዘግየት እናድርግና ለሌሎች የሙያ አጋሮቹ ሠርቶላቸው በብዙኋን አድማጮች ዘንድ ሰፊ ተቀባይነትን ያገኙትን የዜማ ድርሰቶቹን እንዘርዝር ብንል ጊዜም ሥፍራም አይበቃንም፡፡
እንደው ከግምታችን በላይ ስለሆነው ስለዲንቢ የላቀ የዜማ ደራሲነት ሰብዕና መሠረታዊ ግንዛቤ ሊያስጨብጠን ቢችል ግን ጥቂቱን ብቻ ከዚህ እንደሚከተለው እዘረዝርላችኋለሁ፡—
ለአሊ ቢራና ሄለን በርሄ - “ሲያዴ”፤ ለፀሀዬ ዮሐንስ - “ማን ልበልሽ”፤ ለማዲንጎ አፈወርቅ - “ላላተርፍ”፤ ለብዙአየሁ ደምሴ - “የህልሜ ንግስት”፤ ለዘቢባ ግርማ - “ገራገር”፤ ለኢሳያስ ታምራት - “እያዳነ ያማል”፤ ለታረቀኝ ሙሉ - “ስሚያቸው”፤ ለሚኪያስ ቸርነት - “ግርማ ሞገሴ”፤ ለሃይማኖት ግርማ - “ከዚራ ቁ-2”፤ ለግርማ ተፈራ - “ልዩ”፤ ለሀመልማል አባተ - “ሀሴት”፤ እና የመሳሰሉቱን የአህመድ ዲንቢን የዜማ ፈጠራዎች ከብዙ በጥቂቱ ማስታወስ ይቻላል፡፡
አንዳንድ ሙዚቃዎች ለጆሮ ብቻ አይሰሩም፤ ለስሜት ይደርሳሉ፤ ዛሬ ተሰርተው ግን ትዝታችንን ይመልሱልናል፡፡
አንዳንድ ዜማዎች፣ በውስጣችን የተከረቸሙ የጊዜ በሮችን ያንኳኳሉ፤ ይከፍታሉምም፡፡ በሮቹ ሲከፈቱ ደግሞ የተዘነጉ ፊቶች፣ የተለየናቸው ጓደኞች፣ የተራመድንባቸውን ጎዳናዎች… ብቻ ምኑ ቅጡ ትላንታችንን እንደ መጽሀፍ ይገልጡልናል፡፡ በሆነ ዘመን የቀረውን ማንነታችንን እንደገና ይመልሱልናል።
አህመድ ተሾመ (ዲንቢ) ከ14 ዓመታት በኋላ በአዲስ አልበሙ ሲመለስ፣ እኔ የሰማሁት የአዳዲስ ዜማዎች ስብስብን አይደለም። አንድ በሆነ ዘመን የነበረ የዜማ ሰዋሰውና በዚሁ ዜማ ምክንያት የተሰፋ፣ የምናፍቀውን ዘመን የመለሰልኝ ያህል ነው የተሰማኝ፡፡
ያ የኔ ዘመን የምለው “ዘጠናዎቹ”ን ነው፡፡
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪ ሆኜ የገባሁት በ1997 ዓ.ም. ነው። አይ፣ ተማሪነት! እንዴት ያለ ጣፋጭ፣ እንዴት ያለ የማይደገም ዘመን ነበር! ያ ዘመን ለእኔ የወጣትነት ወርቃማ ጠዋት ነበር። ዓለምን እንደ አዲስ ማየት የጀመርኩበት፤ ከተማዋን፣ ሕይወትን፣ ፍቅርን፣ ሐሳብንና ነፃነትን ለመጀመሪያ ጊዜ በሙሉ ልብ ያጣጣምኩበት ዘመን ነበር።
ያ ዘመን ከጓደኞቸ ጋር እንደፈለግን የኖርንበት ዘመን ነበር። በአደባባይ የተከራከርንበት፣ አለምን የጠየቅንበት፣ መንግሥትን ለመጀመሪያ ጊዜ የተቃወምንበት፣ ነፃነትን ያየንበት፣ ዜማን ያጣጣምንበት ወቅት ነበር። ያ ዘመን “ዘጠናዎቹ” ነበር፡፡
ያንን ዘመን ሁሌም እናፍቀዋለሁ፤ ምናልባትም የምናፍቀው ዘመኑን ራሱን አይደለም፤ በዚያ ዘመን ውስጥ የነበርነውን እሱን፣ እሷን፣እኔን፣እኛን ነው። እንደገና እንዲመጣም እመኛለሁ።
ማርሴል ፕሩስት የተባለ ፈረንሳያዊ የልብ ወለድ ጸሀፊና ሀያሲ ጥልቅ የሆነን ትዝታ አስበን ለማስታወስ በምናደርገው ጥረት አይመለስም፤ ነገር ግን የስሜት ሕዋሳችን በሚነካ አንድ ድንገተኛ ልምድ ሊቀሰቀስ ይችላል ይላል፡፡ ሙዚቃም ከእነዚህ የትዝታ ቀስቃሾች መካከል እጅግ ኃይለኛው ሳይሆን አይቀርም።
በዚህ ረገድ እንደ አህመድ ተሾመ ጥንቅቅ ተደርጎ የተሰራ ዜማ የተረሳ ግን ተደበቀ ስሜትን ይቀሰቅሳል፤ የጠፋ የሚመስለውን የዜማ ስልተ ምት ይመልሳል፤ በዘመን ጥላ ሥር ተደብቆ የኖረ ማንነት እንደገና ያነቃቃል።
በ1990ዎቹ የኢትዮጵያ ሙዚቃ የራሱ የሆነ የዜማ ሰዋሰው፣ ቀለምና የአወራረድ ለዛ ነበረው። ያ ዘመን ለእኔ ሙዚቃን ከመስማት ወደ ማዳመጥ የተሸጋገርኩበት ጊዜ ነው። ስለዚህ የዚያ ዘመን ዜማዎች በጆሮዬ ብቻ ተደምጠው አልቀሩም፤ በማንነቴ ውስጥ ህያው ናቸው።
እኔ የሙዚቃ ባለሙያ አይደለሁም፤ ሙዚቃን ግን በልቤ አዳምጠዋለሁ። በእኔ የዜማ አረዳድ፣ የዚያ ዘመን የዜማ አሠራሮች በቀላሉ የሚደገሙ አይደሉም። ምክንያቱም ዜማው የተፈጠረው በድምፅ ብቻ ሳይሆን፣ በዘመኑ መንፈስም ጭምር ነው። ከዚያ በኋላ የመጡት ዘመናት የራሳቸውን የሙዚቃ ቋንቋ ፈጥረዋል።
ያው ዘመን ሲለወጥ የዜማ ሰዋሰውም የሚለወጥ ይመስለኛል፡፡ ይህም የሥነ ጥበብ ተፈጥሯዊ ሂደት ነው፤ ዋናው ጉዳይ ግን በ1990ዎቹና ከዚያ በኋላ በመጡት ዜማዎች መካከል የተቋረጠ ነገር ያለ ይመስለኛል፡፡ መቆራረጡ ለሙዚቃ ባለሙያዎች ትልቅ የጥናት ርዕስ የሚሆንም ነው፡፡
ታዲያ የአህመድ ተሾመ አዲስ አልበም፣ የ1990ዎቹን የዜማ መንፈስ አገኘሁበት፤ የቀድሞውን በቀጥታ ሳይደግም፣ ያንን ለዛ በአዲስ ስልተ ምት የቀነበበ ዜማ ሆኖ አዳመጥኩት። ጉዳዩን ሳይንቲፊካሊ መግለጽ ባልችልም ልቤ ግን አልበሙ በዚያን ጊዜና በዛሬው የሙዚቃ ዘመን መካከል የተዘረጋ የዜማ ድልድይ እንደሆነ ይነግረኛል።
በአጠቃላይ ለእኔ፣ የአህመድ ተሾመ (ዲንቢ) ጊዜ አይሄድም አዲስ አልበም የአዳዲስ ዜማዎች ስብስብ ብቻ አይደለም። ካለፈ ጊዜና ትዝታ ጋር የተደረገ ውይይት ነው፤ ትናንትን ከዛሬ ጋር ያስታረቀ የዜማ ድልድይ ነው፤ በዘጠናዎቹ የቀረውን እኔን የመለሰ አልበም ነው። ይመችሽ ዲንቢ!!
ካላመናችሁኝ ደግሞ ከአዲስ አልበሙ መካከል "ጊዜ አይሄድም"፣"አይሽና"፣ "ይረፍዳል" እና "ህልም ነው" አድመጣችሁ ፍረዱኝ፤ ካጠፋሁ እኔ ሳልሆን ዲንቢ ይቀጣል፡፡

12 days ago
u121du12adu12adu1229 u1208u12a0u1295u12f5 u12c8u1308u1295 u12ebu12f0u120b u12a0u12edu12f0u1208u121d
************
u121du12adu12adu1229 u1260u134du1275u1210u12cau1290u1275 u12a5u1293 u1260u12a5u12a9u120du1290u1275 u1218u122du1205 u120bu12ed u1270u1218u1235u122du1276 u12a5u12e8u1270u12abu1214u12f0 u1290u12cd u1355u122eu134cu1230u122d u1218u1235u134du1295 u12a0u122du12d3u12eb
u27a1 https://youtube.com/live/V...
#ebcdotstream #nationaldialogue #peacefulpolitics #dialogueforpeace ","delight_ranges":[],"image_ranges":[],"inline_style_ranges":[],"aggregated_ranges":[],"ranges":[{"entity":{"__typename":"ExternalUrl","__isEntity":"ExternalUrl","url":"https://l.facebook.com/l.p...
ምክክሩ ለአንድ ወገን ያደላ አይደለም
************
ምክክሩ በፍትሐዊነት እና በእኩልነት መርህ ላይ ተመስርቶ እየተካሔደ ነው ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ
➡ https://youtube.com/live/V...
#ebcdotstream #nationaldialogue #peacefulpolitics #dialogueforpeace
12 days ago
u1200u1308u122bu12ca u121du12adu12adu1229 u12e8u121au1230u122bu12cd u1208u12a2u1275u12eeu1335u12eb u1265u127b u1290u12cd
****************
u12e8u12a2u1275u12eeu1335u12eb u1200u1308u122bu12ca u121du12adu12adu122d u12e8u121bu1295u121d u1323u120du1243 u1308u1265u1290u1275 u12e8u1208u1260u1275u121d u12e8u121au1230u122bu12cdu121d u1208u12a2u1275u12eeu1335u12ebu12cdu12ebu1295 u1265u127b u1290u12cd u1355u122eu134cu1230u122d u1218u1235u134du1295 u12a0u122du12d3u12eb
u27a1 https://youtube.com/live/V...
#ebcdotstream #nationaldialogue #peacefulpolitics #dialogueforpeace ","delight_ranges":[],"image_ranges":[],"inline_style_ranges":[],"aggregated_ranges":[],"ranges":[{"entity":{"__typename":"ExternalUrl","__isEntity":"ExternalUrl","url":"https://l.facebook.com/l.p...
ሀገራዊ ምክክሩ የሚሰራው ለኢትዮጵያ ብቻ ነው
****************
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር የማንም ጣልቃ ገብነት የለበትም የሚሰራውም ለኢትዮጵያውያን ብቻ ነው ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ
➡ https://youtube.com/live/V...
#ebcdotstream #nationaldialogue #peacefulpolitics #dialogueforpeace
12 days ago
ጽናት
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ታሪካዊ የለውጥ ጉዞ
1947-2017
#ethiopia | የዶ/ር አሥራት ዓፀደወይን Asrat Atsedeweyn መጽሐፍ በጎንደር ከተማ እየተመረቀ ነው።
ይህ መጽሐፍ መታሰቢያነቱ ስጎንደር ዩኒቨርሲቲ ርስታቸወነ ስሰጡ 59 የጎንደር አርሶ አደሮች፧ እንዲሁም በተለያዩ ዘመናት በአመራርነት፤ በባለሙያነት፤ በሠራተኛነትና በአጋርነት አገልግለው ተቋሙን አሁን ላስበት ታላቅ ደረጃ ኣደረሱ ሞስንነ ባለውለታዎች በሙሉ ይሁን፡፡
***
ከመጽሐፉ ጀርባ (blurb)
ጎንደር የኒቨርሲቲ ኢትዮጵያ ካፈራቻቸው ዩኒቨርሲቲዎች በአንጋፋነት ተርታ የሚመደብ ነው:: በቅርቡም ሰባኛ ዓመቱንና የዩኒቨርሲቲው አስኳል የሆነውን ሆስፒታሉን መቶኛ ዓመት በደማቅ ሁኔታ መዘከሩ ይታወሳል። በዚህ የታሪክ አጋጣሚ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት የሆነው ዶ/ር አሥራት ዓፀደወይን እነሆ የዩኒቨርሲቲውን ታሪካዊ ጉዞ እርሱ ራሱ በተለያዩ የኃላፊነት እርከኖች ካከናወናቸው ተግባራት ጋር አዛምዶ የሚዘግብ፣ በጠንካራ መረጃ ላይ የተዋቀረ መጽሐፍ አቅርቦልናል።
በዚህም የዩኒቨርሲቲ ቆይታቸውን ከግለ ታሪካቸው ጋር አሰናስለው ለንባብ ያበቁትን የቀደምት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንቶችን ፈለግ ተከትሏል ማለት ይቻላል። የተቋሙ ታሪካዊ ጉዞ በስኬት የታጀበውን ያህል አያሌ ፈተዎችና ተግዳሮቶችም የተጋረጡበት ነበር። የመጽሐፉ ትልቁ ፋይዳም እነዚህን ስኬቶችና ተግዳሮቶች ነቅሶ በማውጣት ሰፊ ግንዛቤ መስጠቱ ላይ ነው:: በተለይም በደራሲው አመራር የተከናወኑትን P70/100 ዝክረ በዓል ዘርፈ ብዙ ዝግጅቶችና ክንዋኔዎች በዝርዝር ያትታል፤ ዘላቂ እርባናቸውንም ይጠቁማል። በመጨረሻም ከዩኒቨርሲቲ አመራር ተሞክሮው የቀሰማቸውን ትምህርቶች በተመሳሳይ ተቋም ግንባታ ላይ ላሉ ያካፍላል።
ባሕሩ ዘውዴ፣ የታሪክ ኤሜሪተስ ፕሮፌሰር አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ
***
የስኬታማ ተቋማትና የአገር ግንባታ በትውልዶች ቅብብሎሽ፣ በቁርጠኝነትና በመሪዎች እቅድ ላይይመረኮዛል። ዶ/ር አሥራት ዓፀደወይን በዚህ መጽሐፋቸው የጎንደር ዩኒቨርሲቲን የ7ዐ ዓመታት ጉዞ፣ በየዘመናቱ የነበሩ መሪዎችንና ባለድርሻ አካላትን አበርክቶ፣ እንዲሁም የራሳቸውን የኃላፊነት ዘመን ፈተናና ስኬት በጥልቀት አቅርበዋል። በከፍተኛ ትምህርት አመራርነት በነበረኝ የረጅም ጊዜ ኃላፊነት ተቋሙንም ሆነ ደራሲውን በቅርብ እንደማወቄ መጠን፤ ይህ መጽሐፍ ከተጨባጩ ዓለም የተገኘ ጥልቅ እውቀት የሚሰጥ፣ ለመሰል ተቋማት መሪዎችና ተመራማሪዎች ታላቅ ማስተማሪያና ማጣቀሻ እንደሚሆን ሙሉ እምነት አለኝ።
ሳሙኤል ክፍሌ (ዶ/ር)፣ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ኘሬዚደንት
***
ጎንደር ዩኒቨርሲቲ በፈተናዎች ውስጥ ያለፈ ታላቅ ዓለም አቀፍ ተቋም ቢሆንም፣ የነበረው የታሪክ ምዝገባ ግን በቂ አልነበረም:: የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶ/ር አሥራት ዓፀደወይን “ጽናት” በተሰኘው መጽሐፋቸው ይህንን የታሪክ ክፍተት ለመሙላት ሞክረዋል። መጽሐፉ፣ ተቋሙ በፈተናዎች ውስጥ አልፎ ለዛሬው ስኬት እንዲበቃ አሻራቸውን ያሳረፉ የቀድሞ ከፍተኛ አመራሮችን እውቅና ይሰጣል። በተጨማሪም፣ ዶ/ር አሥራት ላለፉት ስምንት ዓመታት በኘሬዚዳንትነት ሲያገለግሉ ያጋጠሟቸውን ከባድ ፈተናዎች እንዴት በብቃት እንደተወጧቸውና የዩኒቨርሲቲውን ስኬት እንዴት ማስቀጠል እንደቻሉ ያሳያል። ይህም ለተቋሙ ቀጣይ ጤናማ የአመራር ሽግግርና ለተተኪ አመራሮች ትልቅ ስንቅ የሚሆን ነው።
ዶ/ር ደሳለኝ መንገሻ፣ በኦሃዮ ስቴት ግሎባል ዋን ሄልዝ የኢትዮጵያ ዳይሬክተር እና የቀድሞ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት
እንኳን ደስ አለህ!

14 days ago
4 ሺህ ተመካካሪዎች በነፃነትና በመተማመን እየተወያዩ ነው
- ፕሮፌሰር መሥፍን አርአያ
#ethiopia | የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መሥፍን አርአያ የሀገራዊ ምክክር ጉባኤው በሰላማዊ፣ በነፃ እና በመተማመን መንፈስ እየተካሄደ መሆኑን በዕለታዊ የመገናኛ ብዙኃን መግለጫቸው ገልጸዋል።
እንደ ዋና ኮሚሽነሩ ገለጻ፣ ከ4 ሺህ በላይ ተመካካሪዎች ከ10 እስከ 50 አባላት ባሉ ንዑሳን የውይይት ቡድኖች ተከፋፍለው ሀሳባቸውን በነፃነት እየተለዋወጡ ሲሆን፣ በቀጣይ 250 አባላት ወዳሉ ትላልቅ ስብስቦች በመሸጋገር ውይይታቸውን እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል።
ተሳታፊዎች ያለምንም ፍርሃትና ገደብ ሀሳባቸውን እየገለጹ እንደሆነ የጠቀሱት ፕሮፌሰር መሥፍን፣ በመድረኩ ላይ በሚያቀርቡት ማንኛውም ሀሳብ ምክንያት በሌላ አካል ተጠያቂ እንዳይሆኑ ኮሚሽኑ ሙሉ ኃላፊነትና ከለላ መስጠቱን አስረድተዋል።
በሀገረ መንግሥት ግንባታ፣ በታሪክ፣ በማንነት፣ በፌዴራሊዝም እና በግጭት አፈታት ዙሪያ ጥልቅ ዕውቀት ያላቸው ምሁራን ለተሳታፊዎች ገለጻ እያደረጉ እንደሆነ ገልጸው፣ በ500 አባላት በስምንት ቡድኖች የተደራጁ ተሳታፊዎችም ከምሁራኑ ጋር ሰፊ ውይይት እያካሄዱ መሆኑን አመልክተዋል።
በተጨማሪም በማኅበራዊ ሚዲያ የሚሰራጩ ያልተረጋገጡ መረጃዎችን ሕዝቡና የመገናኛ ብዙኃን በጥንቃቄ እንዲመለከቱ ጥሪ አቅርበው፣ ዜጎች በየዕለቱ የሚወጡትን የኮሚሽኑ ኦፊሴላዊ መረጃዎች እንዲከታተሉ አሳስበዋል።
#ኢትዮጵያ

17 days ago
የ4 ሺህ ድምፆች ውክልና፡- ሀገራዊ ምክክሩ የኢትዮጵያን የፖለቲካ ባህል ሲያድስ
*********************
የጥይት ቋንቋን በሰለጠነ የጠረጴዛ ዙሪያ ውይይት የጦር ሜዳ ጀግንነትን ደግሞ በሐሳብ ልዕልና ለመተካት የሚያስችለው አዲስ የታሪክ ምዕራፍ በኢትዮጵያ ተከፍቷል።
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን 4 ሺህ ተመካካሪዎች ያካተተውን ሰፊ የምክክር መድረክ በአዲስ አበባ በይፋ መጀመሩን ተከትሎ፣ ይህ ታሪካዊ ክስተት ሀገራችን ከጦርነት አዙሪት ወጥታ ወደ ዘላቂ ሰላምና የሀገር ግንባታ የምትሸጋገርበት ወሳኝ ምዕራፍ መሆኑ ተመላክቷል።
በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ በማኅበረሰቡ ዘንድ እንደ ገዳ እና የሽምግልና ሥርዓቶች ያሉ የዳበረ የውይይትና የችግር አፈታት ባህል ቢኖርም፣ የፖለቲካው ማኅበረሰብ ግን ከዚህ እሴት ባለመቅዳቱ "አሸናፊ ወደ ቤተመንግሥት፣ ተሸናፊ ወደ ግዞት" የሚል አጥፊ የፖለቲካ ባህል ስር ሰዶ ቆይቷል።
ይሁንና አሁን የተጀመረው ሀገራዊ ምክክር ይህንን የተዛባ የፖለቲካ ትርክት በማረም ብሔራዊ መግባባትን ለመፍጠር ትልቅ ተስፋ የተጣለበት ሂደት ነው።
በጉዳዩ ዙሪያ ሙያዊ ትንታኔያቸውን የሰጡት የማኅበራዊ ሳይንስ መምህርና ተመራማሪው ረዳት ፕሮፌሰር ጌትነት ተሾመ ኢትዮጵያ ጠንካራ የመንግሥት ምስረታ ታሪክ ያላት ሀገር ብትሆንም፣ በውስጣዊ ክፍፍሎች እና የውጭ ኃይሎች የጂኦ-ፖለቲካ ፍላጎት ምክንያት በሚፈለገው ልክ ማደግ አለመቻሏን ይገልጻሉ።
ይሁንና በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያ በኢኮኖሚ፣ በከተማ ልማት እና በዲፕሎማሲ እያስመዘገበች ያለችውን አበረታች ዕድገት ለማስቀጠል፣ ሀገራዊ ምክክሩ ወቅታዊ እና ወሳኝ መድኃኒት መሆኑን አስምረውበታል።
በየትኛውም የዓለም ክፍል ጦርነት ትርፍ አምጥቶ እንደማያውቅና ይልቁንም አምራች ኃይልን እና ሀገራዊ ኢኮኖሚን እንደሚያወድም ያነሱት ምሁሩ፣ የፖለቲካ ልሂቃን፣ የሚዲያ አካላት እና የሃይማኖት አባቶች አጀንዳዎቻቸውን ኦዲት በማድረግ ለትውልድ የሚሻገር ሀገር ለመገንባት በጋራ ሊቆሙ ይገባል ብለዋል፡፡
በየትኛውም ስሌት የምክክር መድረኩን መጀመር በራሱ ለኢትዮጵያ አንድነት፣ ሰላም እና ልማት ለሚሹ ኃይሎች ታላቅ ድል ተደርጎ ይወሰዳል፡፡
ኢትዮጵያ በርካታ ዓለም አቀፍ ጫናዎችን ተቋቁማ ታላቁን የሕዳሴ ግድብን ጨምሮ የተለያዩ ሀገራዊ ስኬቶችን ማስመዝገብ የቻለች ሲሆን፣ አሁን ደግሞ ዋነኛው የትኩረት አቅጣጫ መሆን ያለበት ዘላቂ የሀገር ግንባታ ነው።
ሀገረ-መንግሥት የመመስረቱ ሂደት ቀደም ብሎ ቢጠናቀቅም በእኩልነትና በመተባበር ላይ የተመሰረተ ጠንካራ ማኅበረሰባዊ አንድነትን ለመፍጠር መመካከር የግድ ይላል።
ባለፈው ታሪክ ውስጥ የተፈጠሩ ቁርሾዎችንና ህመሞችን በዛሬው ዘመን የሰብአዊ መብት መነጽር ከመመዘን ይልቅ፣ ያለፈውን እንደ መማሪያ በመውሰድ ለጋራ የወደፊት ራዕይ በጋራ መሥራት ያስፈልጋል፡፡
በዚህ ዘመን እውነተኛ ጀግንነት የሚለካው በጦር ሜዳ ሳይሆን፣ በጠረጴዛ ዙሪያ በሚደረግ የሰለጠነ ድርድር መሆኑንም ብዙዎች ይስማሙበታል፡፡
ባለፉት አራት ዓመታት ሰፊ የቅድመ-ዝግጅት ሥራዎችን ሲያከናውን የቆየው ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን፣ ከ1 ሺህ 200 በላይ ወረዳዎችን በማዳረስና የኅብረተሰቡን አንገብጋቢ አጀንዳዎች በማሰባሰብ የሁሉንም ድምፅ ያካተተ ዴሞክራሲያዊ ሂደት እያስኬደ ይገኛል።
መላው ማኅበረሰብ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ እየተሳተፈበት የሚገኘው ይህ መድረክ፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) "ሁለት ዓመት ከመዋጋት፣ 20 ዓመት መወያየት ይሻላል" በማለት ያስቀመጡትን መርህ በተግባር የሚተረጉም ነው።
በመሆኑም፣ ይህ በሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን በአንድ አዳራሽ የተሰባሰቡበት ታሪካዊ የምክክር መድረክ፣ ዜጎች ልዩነቶቻቸውን በሰለጠነ መንገድ በማንሸራሸር ለነገዋ ኢትዮጵያ ጠንካራ መሰረት የሚጥሉበት ወርቃማ እድል ነው፡፡
በበረከት ሽመልስ
#ethiopia #ethiopianbroadcastingcorporation #nationaldialogue #nationbuilding #ebcdotstream

18 days ago
ትምህርት ሚኒስቴር በዩኒቨርሲቲዎች አዲስ የአመራር ሹመት መምሪያ ይፈ አደረገ‼️
ትምህርት ሚኒስቴር በመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውስጥ የሚሾሙ ፕሬዝዳንቶችና ምክትል ፕሬዝዳንቶች አሰያየምን የሚገዛ አዲስ መመሪያ ይፋ አድርጓል።
መመሪያው በብቃትና በውድድር ላይ የተመሰረተ አሰራርን ለማስፈን ያለመ ሲሆን፣የዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት የአንድ ጊዜ የስራ ዘመን 6 ዓመት እና የምክትል ፕሬዝዳንቶች 4 ዓመት መሆኑ ተነግሯል።
በማንኛውም የመንግስት ዩኒቨርሲቲ በተከታታይ ሁለት ጊዜ በፕሬዝዳንትነት ያገለገለ አመራር በድጋሚ መወዳደር እንደማይችልም ተገልጿል።
ለፕሬዝዳንትነት የሚወዳደሩ ወንድ እጩዎች ቢያንስ የረዳት ፕሮፌሰርነትና ከዚያ በላይ ማዕረግ ሊኖራቸው የሚገባ ሲሆን፣ቢያንስ 2 ዓመት በፕሬዝዳንትነት ወይም 3 ዓመት በምክትል ፕሬዝዳንትነት/ዲንነት ያገለገሉ መሆን እንደለባቸው ገልጿል።
አመራሩ በየ 3 ወሩ በቦርዱ የሚገመገም መሆኑ እና ። ውጤቱ በሁለት ተከታታይ የስድስት ወር ግምገማዎች ከ60% በታች ከሆነ፣ በጤና እክል ወይም በዲሲፕሊን ጉድለት ከሃላፊነቱ እንዲነሳ ለሚኒስቴሩ ሀሳብ ይቀርባል ተብሏል።
በምልመላና ምርጫ ሂደቱ ላይ ቅሬታ ያለው ተወዳዳሪ፣ ውጤቱ በይፋ በተገለጠ በ10 ቀናት ውስጥ ለዩኒቨርሲቲው ቦርድ ቅሬታውን ማቅረብ እንደሚችል አረጋግጧል።
Seledadotio

20 days ago
የብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደሥላሴ መታሰቢያ ሐውልት በኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ ተመረቀ
#ethiopia | በኢትዮጵያ ዘመናዊ ታሪክ፣ በዲፕሎማሲ፣ በሥነ ጽሑፍና በሕዝብ አገልግሎት ዘርፍ የማይረሳ አሻራ ያሳረፉትን ብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደሥላሴን ለመዘከር የተገነባው የመታሰቢያ ሐውልት ሐምሌ 9 ቀን 2018 ዓ.ም. በኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ ቅጥር ግቢ በይፋ ተመርቋል።
በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ ላይ የቤተሰብ አባላት፣ የአካዳሚው አመራሮች፣ ምሁራንና የተለያዩ የክብር እንግዶች ተገኝተዋል።
የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ ፕሬዝዳንት ፕሮፌሰር በላይ ካሳ እንደገለጹት፣ ብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደሥላሴ ከ24 በላይ መጻሕፍትን በመጻፍ ለኢትዮጵያ ዘመናዊ ሥነ ጽሑፍ መሠረት ከጣሉ ሊቃውንት አንዱ ሲሆኑ፣ በዲፕሎማሲ፣ በባንክ ሥርዓት፣ በቴአትር፣ በቀይ መስቀል ማኅበር እና በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዘርፎችም የላቀ አስተዋጽኦ አበርክተዋል።
በተጨማሪም ኢትዮጵያ በሊግ ኦፍ ኔሽንስ አባልነት እንድትቀላቀል በተደረገው ዲፕሎማሲያዊ ጥረት ጉልህ ሚና የተጫወቱ ሲሆን፣ ከአምባሳደርነት እስከ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትርነት ሀገራቸውን በታማኝነት ማገልገላቸው ተጠቅሷል።
አካዳሚው ታሪካዊ መኖሪያ ቤታቸውን በቅርስነት በመጠበቅ ዋና መሥሪያ ቤት አድርጎ እየተጠቀመበት ሲሆን፣ የግል ሰነዶቻቸውን፣ ፎቶግራፎችን፣ መጻሕፍቶችንና ሌሎች ቅርሶችን የያዘ ቋሚ ሙዚየምም ለጎብኚዎች ክፍት አድርጓል።
ሐውልቱ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የእይታ ጥበብ ባለሙያ ሠዓሊ ኢዮብ ኪታባ እና በቡድናቸው የተቀረጸ ሲሆን፣ ለሥራው መሳካት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላበረከቱት የብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደሥላሴ የልጅ ልጅ ልጅ ወይዘሮ ገነት ኅሩይ የእውቅና ሰርተፍኬት ተበርክቶላቸዋል።
ይህ የመታሰቢያ ሐውልት የብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደሥላሴን ታሪካዊ አስተዋጽኦ ለቀጣዩ ትውልድ በማስተላለፍ ረገድ ከፍተኛ ፋይዳ እንደሚኖረው ተገልጿል።
#ethiopia #scienceacademy #blatengetahruy #history #heritage #getutemesgen #ጌጡተመስገን

21 days ago
የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት 100ኛ ዓመቱን አከበረ
#ethiopia | የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት (EPHI) "የአንድ ክፍለ ዘመን ጥረት ለተሻለ የሕብረተሰብ ጤና" በሚል መሪ ቃል ታሪካዊ የ100ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን ዛሬ በከፍተኛ ድምቀት አክብሯል።
ይህ መቶ ዓመታትን የተሻገረው ክብረ በዓል ተቋሙ ላለፉት አሥርት ዓመታት የሀገሪቱን የጤና ደህንነት ለመጠበቅ ያደረገውን ዘርፈ ብዙ ጉዞ የዘከረ ሲሆን፣ በቀጣይም የጤና ሥርዓቱን ወደ ላቀ ምዕራፍ ለማሸጋገር አዲስ ቃል ኪዳን የተገባበት መድረክ ሆኗል።
በበዓሉ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ክቡር ታዬ አፅቀስላሴ ጠንካራ የሕብረተሰብ ጤና ተቋማት የሀገር ደህንነትና ልማት መሠረቶች መሆናቸውን በመግለጽ፣ መንግሥት ተቋሙን ይበልጥ ለማጠናከር ቅድሚያ ሰጥቶ እንደሚሠራ አረጋግጠዋል።
ፕሬዚዳንቱ አክለውም ተቋሙ ከጊዜው ጋር እንዲራመድ የዲጂታል ቴክኖሎጂንና የሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) አጠቃቀምን ማሳደግ እንደሚገባው አሳስበዋል።
በተመሳሳይ መልኩ የጤና ሚኒስትሯ ክብርት ዶክተር መቅደስ ዳባ ተቋሙ ላለፉት 100 ዓመታት በበሽታ ቅኝት፣ በላቦራቶሪ አገልግሎትና በምርምር ዘርፍ ያበረከተውን ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያወሱ ሲሆን፣ አዳዲስ ወረርሽኞችንና የአየር ንብረት ለውጥ ያመጣቸውን የጤና ተግዳሮቶች ለመመከት ጠንካራ ተቋማዊ ትብብር እንደሚያስፈልግ በአፅንኦት ገልጸዋል።
የዓለም ጤና ድርጅት (WHO) በኢትዮጵያ ተወካይ ፕሮፌሰር ፍራንሲስ ካስሎ በበኩላቸው ኢንስቲትዩቱ በአፍሪካ እጅግ ጠንካራ ከሆኑ የልህቀት ማዕከላት አንዱ መሆኑን ጠቅሰው፣ ተቋሙን የዓለም ጤና ድርጅት የትብብር ማዕከል ለማድረግ እንቅስቃሴ መጀመሩን ይፋ አድርገዋል።
የአፍሪካ የበሽታ መከላከያና መቆጣጠሪያ ማዕከል (Africa CDC) ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ጄን ካሴያም በበኩላቸው የወደፊቱ የሕብረተሰብ ጤና ያለ ሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) የማይታሰብ መሆኑን ጠቁመው፣ ኢትዮጵያ በዚህ ረገድ እያደረገች ያለችው ጥረት ለጤናው ዘርፍ ስኬት ትልቅ አቅም እንደሚፈጥር ገልጸዋል።
የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር መሳይ ኃይሉ ተቋሙ ያለፉትን ስኬቶች መሠረት በማድረግ በቀጣዩ መቶ ዓመታት የሀገሪቱን የሳይንስና የጤና ሉዓላዊነት በተሟላ ሁኔታ ለማረጋገጥ በቁርጠኝነት እንደሚሠራ ቃል ገብተዋል።
በበዓሉ ማጠቃለያ ላይም ላለፉት ዓመታት ተቋሙን በምርምርና በአመራርነት ያገለገሉ ባለውለታዎች ከፕሬዚዳንት ታዬ አፅቀስላሴ እጅ የእውቅና ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።
ጌትነት ተመስገን
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ
#healthsovereignty #publichealthethiopia
#aiinhealthcare #ethiopia
#ephi #ministryofhealthethiopia

22 days ago
የ"ሸገሩ"፣ "የእነሆ መቆያው" እሸቴ አሰፋ!
#ethiopia | ባለፈው ሳምንት "እነሆ መቆያ" የተሰኘ መጽሐፉን ለንባብ ያበቃው፣ አንጋፋውና ስመ-ጥሩ ጋዜጠኛ እሸቴ አሰፋ (እሸቴ ከጃንሜዳ) ሐምሌ 19 ቀን 1953 ዓ.ም በሰሜን ሸዋ መንዝና ግሼ አውራጃ ተወለደ።
የአንደኛ ደረጃ ትምህርቱን በተወለደበት አካባቢ ራቤል የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ያጠናቀቀ ሲሆን፣ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን ደግሞ በመሐል ሜዳ፣ በሆለታና በአቃቂ ተማሪ ቤቶች ተከታትሏል።
ገና በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እያለ በሚኒ-ሚዲያ በመሳተፍ የጋዜጠኝነት ፍቅሩን ያሳየው እሸቴ፣ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በቋንቋና ሥነ-ጽሑፍ የመጀመሪያ ዲግሪውን አግኝቷል።
ለመጀመሪያ ጊዜ ጽሑፉ የታተመለት በአዲስ ዘመን ጋዜጣ "አድማስ" አምድ ላይ ነበር ይላል - ለዚህ ጽሑፍ ዋነኛ ምንጭ አድርገን የተጠቀምነው የ"ተወዳጅ ሚዲያ" መረጃ።
በተለይም "የካቲት" መጽሔት ላይ እንደ ጳውሎስ ኞኞ፣ ስብሐት ገብረእግዚአብሔር፣ ብርሃኑ ዘርይሁን፣ ወጋየሁ ንጋቱ፣ ይድነቃቸው ተሰማና ፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ ያሉ ታላላቅ ሰዎችን ታሪክ በጥናት አስደግፎ በማቅረብ የአንባቢን ልብ መግዛት ችሏል።
በተለያዩ ዘርፎች ብዙ ውለታ የዋሉ ታላላቅ የሀገራችንን ሰብዕናዎችንም 'ቃለ-መጠይቅ' (Interview) አድርጓል።
በዚህ የጋዜጠኝነት ጉዞው ውስጥ የአጻጻፍና የጋዜጠኝነት ሙያዊ ዕውቀት የሰጡትንና እንደ መምህር የሚያያቸውን የመጽሔቷን ዋና አዘጋጅ አቶ ጸጋዬ ኃይሉ ተፈራን ምንጊዜም በታላቅ አክብሮት ያስታውሳል።
በአንድ ጊዜ በበርካታ ሚዲያዎች ላይ የመሥራት ልዩ ታታሪነት የነበረው እሸቴ፣ ከ1978 ዓ.ም ጀምሮ ለአምስት ዓመታት ያህል በለገዳዲ ሬዲዮ "የእሁድ ለአንዳፍታ" ፕሮግራም ላይ "እሸቴ ከጃንሜዳ" በሚል ስያሜ የገጠሪቱን ኢትዮጵያ ባህልና ውሎ የሚያሳዩ ማራኪ የሥነ-ቃል ስብስቦችን በራሱ አንደበት እያነበበ ለአድማጭ ያቀርብ ነበር።
በተያያዥነትም ከ1979 ዓ.ም ጀምሮ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን በፍሪላንስ ጋዜጠኛነት በመቀጠር፣ በተለይ ታሪካዊና ተፈጥሯዊ አካባቢዎች ላይ ያተኮሩ የተለያዩ ባለ አንድ ሰዓት ዘጋቢ ፊልሞችን (ዶክመንተሪዎችን) አዘጋጅቷል።
ከእነዚህም መካከል ስለ ጣና ሐይቅ አድባራት የሠራውና አዲስ አበባ 100ኛ ዓመቷን ስታከብር ያቀረበው ባለ አንድ ሰዓት ተኩል ልዩ ፕሮግራም ተጠቃሽ ናቸው።
በ1987 ዓ.ም "ሪፖርተር" ጋዜጣ ሲመሠረት ከዋና መሥራቾቹ አንዱ የነበረ ሲሆን፣ ከ1989 ዓ.ም ጀምሮ ደግሞ የ"ሪፖርተር" ጋዜጣና መጽሔት ምክትል ዋና አዘጋጅና ዋና አዘጋጅ በመሆን ሙያዊና እውነተኛ መረጃ ላይ የተመሠረተ ጋዜጠኝነት እንዲሰፍን ከፍተኛ አስተዋጽኦ አበርክቷል።
ላለፉት አስራ አምስት ዓመታት ደግሞ በሸገር 102.1 ኤፍ ኤም ሬዲዮ በቅዳሜው "እነሆ መቆያ" መሰናዶው የዓለም መሪዎችን፣ ታዋቂ ሰዎችንና ታላላቅ የስለላ ተቋማትን፣ ታሪካዊ ክስተቶችን እና ሌሎችንም ጉዳዮች በበቂ ንባብና ማስረጃ አደራጅቶ በማቅረብ ከፍተኛ ተወዳጅነትን አትርፏል።
በአሁኑ ወቅትም በሸገር fm 102.1 ሬዲዮ ጣቢያ በዋና አዘጋጅነት እያገለገለ ይገኛል። ጋዜጠኛ እሸቴ አሰፋ ባለትዳርና የሁለት ልጆች አባት ነው።
ስለራሱ በአንደበቱ ከማውራት ይልቅ በሥራው መናገርን የሚመርጠው ይህ በሳል ጋዜጠኛ፣ ባለፉት ሠላሳ ዓመታት በሀገሪቱ ሚዲያ ታሪክ ውስጥ የራሱን የማይረሳ ደማቅ አሻራ አስቀምጧል። እናመሰግናለን፤ እሼ!
#ወይ_አዲስ_አበባ_on_Sheger_fm_102 .1 #sheger_fm_102 .1 #zefenenazemen #jafarbooks #radio #አዲስ_አበባ

23 days ago
በሕዝባዊ የባለቤትነት መንፈስ የተሰናዳው ታሪካዊ ጉባኤ
********************
ላለፍት አራት ዓመታት ከቅድመ ዝግጅት ምዕራፍ ጀምሮ ሰፊና አሳታፊ ሥራዎችን ሲያከናውን የቆየው የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በ8 የተለዩ አጀንዳዎች ላይ ለመምከር የመጨረሻ የዝግጅት ምዕራፉን አጠናቆ ዋዜማ ላይ ይገኛል።
የምክክር ሂደቱ አካታች፣ አሳታፊ እና ተዓማኒ እንዲሆን በተደረገው ከፍተኛ ጥረት በውጭ ሀገር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንም በሂደቱ ንቁ ተሳትፎ እንዲያደርጉ መደረጉ፣ ከተለያዩ አቅጣጫዎች የሚነሱ ወሳኝ ጥያቄዎችን በተሟላ መንገድ ለመመለስ ትልቅ ዕድል የሚፈጥር ነው፡፡
ነገ በአዲስ አበባ በይፋ ለሚጀመረው ለዚሁ ታላቅ የሀገራዊ ምክክር ጉባኤ ከመላው ኢትዮጵያ የተወከሉ 4 ሺህ የሕብረተሰብ ክፍሎች (ተመካካሪዎች) በአሁኑ ወቅት አዲስ አበባ የገቡ ሲሆን፣ በኮሚሽኑ ቅጥር ግቢ ውስጥም ደማቅና ታሪካዊ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።
ይህንን ታላቅ ምዕራፍ አስመልክተው የኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ ባስተላለፉት መልዕክት፤ ተመካካሪዎቹ ከማንኛውም ስሜታዊነት በፀዳ መልኩ፣ ኢትዮጵያን ብቻ ማዕከል አድርገው በመወያየት የዘላቂ ሰላምን መንገድ እንደሚያቀኑ ታላቅ ተስፋ እንዳላቸው ገልጸዋል።
በዚህ ታሪካዊ ጉባኤ ላይ ልሂቃን በሂደቱ ውስጥ ለሚነሱ ውስብስብ ጉዳዮች ታሪካዊ አመጣጥና የታዩ ክስተቶችን በጥናትና ምርምር አስደግፈው በማቅረብ፣ ተመካካሪዎች ወደ ጋራ መረዳትና ወደ ዘላቂ መፍትሔ እንዲያመሩ የማገዝ ታላቅ ኃላፊነት እንዳለባቸውም ተመልክቷል።
ነገ በሚከናወነው በዚህ ታላቅ ጉባኤ ላይ የሀገር ውበት የሆነው “አንተ ትብስ፣ አንቺ ትብሽ” የመባባል ኩሩ እሴትና የኢትዮጵያውያን ሕብረ-ቀለማት ደምቀው የሚታዩበት ይሆናል። ከሀገሪቱ ልዩ ልዩ ማዕዘናት የተውጣጡ ወገኖች ልዩነቶቻቸውን ወደ ጎን ትተው፣ ያለ ምንም የውጭ ጣልቃ ገብነት ለጋራ ዕጣ ፈንታቸው በአንድነት ለመምከር በከፍተኛ ጉጉት ላይ ይገኛሉ።
ለረጅም ዘመናት የኢትዮጵያ የፖለቲካ እና የማኅበራዊ ውጥረቶች መፍትሔ ከውጭ ሲጠበቅ የቆየበት አሮጌ አዝማሚያ ተቀይሮ፣ ዛሬ የችግሮቹ ባለቤቶች የሆኑት ኢትዮጵያውያን ራሳቸው መፍትሔ ፍለጋ በአንድ ጠረጴዛ ዙሪያ መሰየማቸው ትልቅ ብሔራዊ ስኬት ነው።
መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ለሂደቱ የሰጠው ከፍተኛ ትኩረት እና ያሳየው የባለቤትነት መንፈስ እጅግ የሚያበረታታ ሲሆን፣ ታሪክ የማይረሳው ሀገራዊ ኃላፊነትም እየተወጣ ይገኛል። ይህ ታሪካዊ ጉባኤ የአንድ ወገን አሸናፊነት ሳይሆን፣ የኢትዮጵያና የሕዝቦቿ የጋራ ድል የሚረጋገጥበት፣ ለቀጣዩ ትውልድ ደግሞ የሰላም ውርስ የሚተውበት ደማቅ አሻራ ሆኖ በታሪክ ማህደር ላይ ይመዘገባል።
በብሌን ደምበሎ
#ebc #ethiopia #nationaldialogue #nationalconsensus #inclusiveethiopia

25 days ago
እስከአሁን የተቸገርንባቸውን ሁሉ ለመፍታት ኢትዮጵያውያን በምክክር ሊፈቱ በጠረንጴዛ ዙሪያ ተቀምጠው ይመካከራሉ:- ፕሮፌሰር መስፍን ዓርአያ ያስተላለፉት መልእክት
Ethiopian Broadcasting Corporation
Sponsored by
Surafel
26 days ago
(ዘ-ሐበሻ ዜና) በቴህራን የሚገኘው የተግባራዊ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ፕሮፌሰር የሆኑት ሞስታፋ ኾሽቼሽም ለአልጀዚራ እንደተናገሩት በቀድሞው ጠቅላይ መሪ አሊ ኻሜኒ ላይ የተፈጸመውን ግድያ ተከትሎ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ኢራናውያን የበቀል እርምጃ እንዲወሰድ አጥብቀው እየጠየቁ ይገኛሉ። ፕሮፌሰሩ ይህን ያሉት የቀድሞው መሪ የሽኝት ስነ-ስርዓት ከመካሄዱ በፊትም ህዝቡ ቁጣውን ሲገልጽ እንደነበር በማስታወስ ነው።
አዲሱ ጠቅላይ መሪ ሞጅታባ ኻሜኒ የአባታቸውን ግድያ ለመበቀል የገቡትን ቃል በተመለከተ ፕሮፌሰሩ ሲያብራሩ፣ ኢራናውያን በየምሽቱ አደባባይ በመውጣት እያሰሙ ያሉት ድምጽ እያደገ ለመጣው የህዝብ የበቀል ጥያቄ ትክክለኛ ምላሽ መሆኑን ገልጸዋል።
"አሜሪካውያን የኢራንን መሪ እና ከፍተኛ ጄኔራሎች መግደላቸው ትክክል ነው፣ ኢራናውያንም ይህን አምነው ዝም ብለው መቀመጥ አለባቸው የሚል ማንም ሰው በዓለም ላይ ይኖራል ብዬ አላምንም" ያሉት ኾሽቼሽም፣ አሜሪካውያን ለፈጸሙት ጥቃት ተገቢውን ዋጋ ካልከፈሉ፣ በአደባባይ እያስጠነቀቁ እንዳሉት አዲሱንም ጠቅላይ መሪ ከመግደል ወደኋላ እንደማይሉ ስጋታቸውን አስቀምጠዋል።
አሜሪካውያን ከኢራን ጋር ለሚደረግ ለማንኛውም ዓይነት ስምምነት ታማኝ ሆነው ስለማያውቁ፣ በቀጣይ ቀናት በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለው ግጭት እና ወታደራዊ ውጥረት መባባሱ ፈጽሞ የማይቀር ጉዳይ መሆኑን ምሁሩ አክለው አስጠንቅቀዋል።

ኢትዮጵያውያን ለመነጋገርና ለመደማመጥ በአንድነት መሰባሰባቸው ትልቅ ምዕራፍ ነው!
- ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ
#ethiopia | የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ከሐምሌ 8 ቀን 2018 ዓ.ም. ጀምሮ ለሚያካሂደው ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ በመዘጋጀት፣ ለተሳታፊ ተመካካሪዎች የቅድመ ምክክር ገለጻ በአድዋ ድል መታሰቢያ እየሰጠ ነው።
የኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ በመክፈቻ ንግግራቸው፣ ኢትዮጵያውያን ስለ ሀገራቸው ሰላም፣ ሀገር ግንባታ፣ ሰብዓዊ መብት፣ ማኅበራዊ ጉዳዮችና ሌሎች ወሳኝ ጉዳዮች ለመነጋገርና ለመደማመጥ በአንድነት መሰባሰባቸው በኢትዮጵያ ታሪክ ትልቅ ምዕራፍ መሆኑን ገልጸዋል።
ፕሮፌሰር መስፍን አክለውም፣ ሀገሪቱ በአንድነትና በመተባበር ነፃነቷን እንዳስጠበቀች ሁሉ፣ ዛሬም በረጅም የመንግሥት ግንባታ ሂደት የተፈጠሩ አለመግባባቶችንና ቁርሾዎችን በውይይት ለመፍታት መሰባሰቧ ከችግሮች ለመውጣት ያለውን ፅኑ ቁርጠኝነት የሚያሳይ መሆኑን ጠቁመዋል።
በዛሬው መርሃ ግብር ኮሚሽኑ ምክክሩ በሚመራበት ስልት፣ ተሳታፊዎች በሚኖራቸው ሚና እና በምክክሩ መርሆዎች ዙሪያ ሰፊ ገለጻ ሰጥቷል። በዚህም አካታችነት፣ አሳታፊነት፣ ትብብር፣ እኩልነት፣ መልካም ግንኙነት ግንባታ፣ የጋራ አስተሳሰብን ማጎልበት እና ሰፊ ስምምነትን መፈለግ እንደ መሠረታዊ እሴቶች ቀርበዋል።
በተጨማሪም የምክክር ሂደቶች፣ የቡድን አደረጃጀት፣ የጊዜ ሰሌዳ እና የተሳታፊዎች ኃላፊነት ዙሪያ ዝርዝር ማብራሪያ የተሰጠ ሲሆን፣ ይህ መድረክ ወደ ሀገራዊ መግባባት ለመድረስ የሚደረገውን ሂደት በይፋ ያስጀመረ መሆኑ ተገልጿል።
#ethiopia #nationaldialogue #nationalconsensus

ኮሚሽኑ ለተመካካሪዎች ገለጻ እየሰጠ ነው
#fastmereja | የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ከሐምሌ 8 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ለሚካሄደው ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ ዝግጅቱን አጠናክሮ በመቀጠል፣ ለተመካካሪዎች የቅድመ ምክክር ገለጻ መስጠት ጀምሯል።
በጉባኤው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መሥፍን አርአያ፣ ኢትዮጵያ ለታላቁ የአፍሪካ ነፃነት ተምሳሌት መሆኗን አስታውሰዋል። ተመካካሪዎች የአድዋን መንፈስ በመያዝ፣ ይህንን የጋራ የሀገር ፍቅር ስሜት ወደ ገንቢ የሀገር ግንባታ እና የመግባባት ሂደቶች እንዲቀይሩ ጥሪ አቅርበዋል። በሚቀጥሉት ሦስት ቀናት የሚቆየው ይህ ገለጻ፣ ተመካካሪዎች በሂደቱ ዙሪያ ጥልቅ ግንዛቤ እንዲጨብጡ በማድረግ ምክክሩን በስኬት ለመወጣት ወሳኝ መሆኑን ዋና ኮሚሽነሩ አሳስበዋል።
በገለጻው ወቅት የሀገራዊ ምክክር ጉባኤው ዓላማ፣ ተመካካሪዎች ሊኖራቸው የሚገባው ሚናና ኃላፊነት፣ እንዲሁም የውይይቱ ሥነ ምግባር እና የአሠራር ሥርዓት በዝርዝር እየቀረበ ይገኛል። ይህ ቅድመ ዝግጅት፣ ከሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች የተወጣጡት ተመካካሪዎች በጉባኤው ላይ ውጤታማ እና የተሳለጠ ተሳትፎ እንዲያደርጉ ለማስቻል የታለመ መሆኑ ተመላክቷል።

28 days ago
🎉 መልካም ልደት! 🎉
ለረዳት ፕሮፌሰር ተስፋዬ እሸቱ
#ethiopia | በኢትዮጵያ የትያትር ጥበብ፣ የከፍተኛ ትምህርት እና የባህል ልማት ዘርፍ ለዓመታት ያበረከቱትን ከፍተኛ አስተዋጽኦ በአክብሮት እያሰብን፣ ዛሬ የልደት ቀንዎን በደስታ እናከብራለን።
እንደ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የትያትር መምህር እና የባህል ማዕከል ዋና ዳይሬክተር፣ ለሥነ-ጥበብ እና ለትውልድ ግንባታ የሰጡት አስተዋጽኦ የሚደነቅ ነው።
መጪዎቹ ዓመታት በጤና፣ በሰላም፣ በደስታ እና በተጨማሪ ስኬቶች የተሞሉ ይሁኑልዎ። እግዚአብሔር ዕድሜና ጤና አብዝቶ ይስጥዎ፤ ለሀገርዎና ለሙያዎ የሚያበረክቱት አስተዋጽኦም ይበልጥ ይጎልብት።
"እያንዳንዱ ልደት አዲስ ምዕራፍ፣ አዲስ ተስፋ እና አዲስ ዕድል ይዞ ይመጣል። ዕድሜዎ በጤና፣ በሰላምና በበረከት ይሞላ!" 🎂🎉
🎂 መልካም ልደት ለረዳት ፕሮፌሰር ተስፋዬ እሸቱ! 🎉
#happybirthday #tesfayeeshetu #addisababauniversity #theatre #culture #getu

በአዲስ አበባ ሲካሄድ የቆየው የአፍሪካ የሕክምና ትምህርት ጉባኤ በስኬት ተጠናቀቀ
#ethiopia | በአፍሪካ አህጉር የሕክምና ትምህርትን ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር ያለመውና ለሦስት ቀናት በአዲስ አበባ ከተማ ሲካሄድ የቆየው የ"MedEDAfrica 2026" ዓለም አቀፍ ጉባኤ በስኬት ተጠናቋል።
በጉባኤው ማጠቃለያ ሥነ-ሥርዓት ላይ ንግግር ያደረጉት የጤና ሚኒስትር ዲኤታዋ ወይዘሮ ሳህረላ አብዱላሂ መድረኩ ለኢትዮጵያ የጤና ዘርፍ ጠቃሚ እይታዎችንና የፖሊሲ ምክረ-ሃሳቦችን ተገኝቶባቸዋል።
በተጨማሪም ሀገሪቱ በሕክምና ትምህርትና በጤናው ዘርፍ ልማት ያሏትን መልካም ተሞክሮዎች ለሌሎች ሀገራት ያካፈለችበት መልካም አጋጣሚ መሆኑን ጠቁመዋል።
ኢትዮጵያ የጤና ባለሙያዎችን አቅም ለማጠናከርና የሥልጠና ጥራትን ለማሻሻል በርካታ ሥራዎችን እየሠራች መሆኑን ያነሱት ሚኒስትር ዲኤታዋ በሬዚደንሲ መርሃ-ግብሮቿ አማካኝነት የጎረቤት ሀገራትን የሕክምና ተማሪዎች በማሠልጠን ለቀጣናው የጤና ልማት የበኩሏን ድጋፍ እያበረከተች እንደምትገኝም አክለው ገልጸዋል።
በሌላ በኩል የ"MedEDAfrica" ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር ሊዮኔል ግሪን-ቶምፕሰን ኢትዮጵያ ለጉባኤው መሳካት ላደረገችው የላቀ አስተዋጽኦ አድናቆታቸውን ችረዋል።
ይህ ታላቅ መድረክ በመላው አፍሪካ ጠንካራና የማይበገሩ የጤና ሥርዓቶችን ለመገንባት የሚያስችሉ ስልታዊ ውይይቶች የተካሄዱበት መሆኑንም አጉልተው አሳይተዋል።
በማጠቃለያ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ በዘርፉ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላበረከቱ መምህራን፣ የጤና ባለሙያዎችና ባለድርሻ አካላት የዕውቅናና የምስጋና መርሃ-ግብር ተከናውኗል።
ከጉባኤው ማጠናቀቂያ በኋላም የጉባኤው ተሳታፊዎች የአድዋ ሙዚየምን ጨምሮ በአዲስ አበባ ከተማ በስፋት እየተተገበሩ ያሉ የወንዝ ዳርቻና የኮሪደር ልማት ፕሮጀክቶችን ጎብኝተዋል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu

29 days ago
"ሁላችንም መሣሪያ አስቀምጠን በአንድነት አሸናፊ የምንሆንበት ዕድል ተፈጥሯል" - ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ
***********************
እየተከናወነ ያለው ሀገራዊ የምክክር ሂደት ያለ ምንም የጦር መሣሪያና ጠመንጃ፣ ወገኖች በሐሳብ ብቻ እየተነጋገሩና እየተደማመጡ ሁሉም አሸናፊ የሚሆኑበት ታሪካዊ መድረክ እንደሚሆን የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ ገለጹ።
ኮሚሽነሩ ከኢቲቪ ዜና ጋር ባደረጉት ቆይታ፤ ሂደቱ ለሀገሪቱ የዲሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ጠንካራ መሠረት የሚጥል መሆኑን ጠቁመው፣ በሂደቱ ስኬታማነት ላይ ሙሉ እምነትና እርግጠኝነት እንዳላቸው ተናግረዋል።
ሐምሌ 8 በሚጀመረው ታሪካዊ ጉባኤ የሚመካከሩ ተሳታፊዎች ከየወረዳው፣ ከክልሎች፣ ከፌደራል እንዲሁም ከተለያዩ የዓለም ሀገራት የተወከሉ የኢትዮጵያውያን እንግዶች በአሁኑ ወቅት ወደ ዋና ከተማዋ አዲስ አበባ መግባት መጀመራቸውን ዋና ኮሚሽነሩ ጠቁመዋል።
እንግዶቹን በፐብሊክ ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ፣ በቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ እንዲሁም በተለያዩ ሆቴሎች የመቀበልና የማስተናገድ ሥራ በጥሩ ሁኔታ እየተከናወነ እንደሚገኝ አንስተዋል።
ይህ ጉባኤ አርሶ አደሮች፣ አርብቶ አደሮች፣ አካል ጉዳተኞች፣ ሴቶችና ወጣቶችን ጨምሮ ከ4,000 በላይ የኅብረተሰብ ክፍሎች በጥምረት የሚሳተፉበት በመሆኑ እጅግ ሁሉን አቀፍና አካታች ያደርገዋል ብለዋል።
ታላቁ ጉባኤ ሐምሌ 8 ቀን 2018 ዓ.ም ከመጀመሩ በፊት በርካታ የቅድመ-ዝግጅት ሥራዎች እንደሚከናወኑም ገልጸዋል። ተሳታፊዎቹ በኮንቬንሽን ሴንተርና በዓድዋ ድል መታሰቢያ አዳራሾች በሚኖራቸው ቆይታ የሥነ-ምግባር ደንቦችን እንዲረዱ፣ የምክክር ሂደቱን ዝርዝር መመሪያዎች እንዲገነዘቡ እና ከአማካካሪዎች ጋር የቅድመ-ውይይት ትውውቅና ዝግጅት እንዲያከናውኑ እንደሚደረግ ዋና ኮሚሽነሩ አብራርተዋል።
ባለፉት ሦስት ዓመታት ከመላው የሀገሪቱ ሕዝብ የተሰበሰቡ ከሁለት ሺህ በላይ አጀንዳዎች መኖራቸውን ያስታወሱት ፕሮፌሰር መስፍን፤ ከእነዚህ ውስጥ መሠረታዊና ሀገራዊ ፋይዳ ያላቸው ስምንት ትልልቅ አጀንዳዎች በጥልቀት ተለይተው ለግምገማ ቀርበው መፅደቃቸውን ጠቁመዋል።
ተመካካሪዎቹ በ8 የተለያዩ ቦታዎች በየ500 ቡድን በመሆን በእነዚህ በጸደቁት አጀንዳዎች ላይ በሰፊው እንደሚመክሩም ተናግረዋል።
ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ አክለውም፤ የምክክር ሂደት ጊዜና ትዕግሥት የሚወስድ መሆኑን የኢትዮጵያ ሕዝብ በጥብቅ ሊገነዘበው እንደሚገባ አሳስበው፤ ሂደቱ ሁሉንም ዜጋ ባሳተፈና ስልጣኔ በተሞላበት መንገድ መላው ኢትዮጵያውያንን አሸናፊ እንደሚያደርግ ያላቸውን ፅኑ እምነት ገልጸዋል።
በመሀመድ ፊጣሞ
#ebc #nationaldialogue #inclusiveethiopia #dialogueforpeace #nationalconsultation

“ሂሳብ ከባድ ነው” የሚለውን ትርክት የሚሰብረው የኢትዮጵያውያን አሻራ እና ማቲማቲክስ 2.0
******************
አስቡት... ሂሳብ በፈተና ወረቀት ላይ ብቻ ተሰርቶ የሚያበቃ የትምህርት ዓይነት ሳይሆን፣ የዓለማችንን እጣ ፈንታ የሚወስን፣ የቴክኖሎጂ እና የስልጣኔ ሁሉ የልብ ትርታ ነው።
ዛሬ ላይ የሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI)፣ ዳታ ሳይንስ፣ የህክምና እና የህዋ ምርምር ያለ ሂሳብ ቀመር አንድም እርምጃ ወደፊት መራመድ አይችሉም።
በየዓመቱ ሀምሌ 1 የሚከበረው የዓለም የማቲማቲክስ 2.0 ቀን ይህንኑ እውነታ የሚያስታውሰን ነው። ይህ ቀን የባህላዊ ሂሳብ ፅንሰ ሀሳቦች ከዘመናዊ ስልታዊ ቀመሮች፣ ከኮዲንግ እና ከዳታ ሳይንስ ጋር ተቀናጅተው ዓለምን እንዴት እየቀየሯት እንደሆነ በጉልህ የምናስብበት ዕለት ነው።
ታዲያ በዚህ ዓለም አቀፍ የዕውቀት መድረክ ላይ የኢትዮጵያውያን አሻራ ምን ይመስላል? የኢትዮጵያ ስም በዓለም አቀፍ የሂሳብ ውድድሮች እና በምርምር መድረኮች ላይ ደማቅ ሆኖ ተጽፏል። ለዚህም በአሜሪካ ሳቫና ስቴት ዩኒቨርሲቲ የሂሳብ ፕሮፌሰር የሆኑት ሙላቱ ለማ (ዶ/ር) ትልቅ ማሳያ ናቸው።
ፕሮፌሰሩ በአውሮፓውያኑ 2011 "የሙላቱ ቁጥሮች" የተሰኘውን የሂሳብ ቀመር በማስተዋወቅ የተለያዩ ዓለም አቀፍ ሽልማቶችን አግኝተዋል።
በሌላ በኩል ከኮርኔል ዩኒቨርሲቲ በኮምፒውተር ሳይንስ የዶክትሬት ዲግሪ በመቀበል የመጀመሪያዋ ጥቁር ሴት የሆነችው ወጣቷ ተመራማሪ ረድኤት አበበ በኮምፒውተር ሳይንስ እና ሂሳብ ላበረከተችው አስተዋጽኦ የዓለምን ትኩረት መሳብ ችላለች።
የኢትዮጵያ ከሂሳብ ጋር ያላት ትስስር የዛሬ ብቻ ሳይሆን የሺህ ዓመታት ታሪክ ያለው ነው። የራሳችን የግዕዝ የቁጥር ሥርዓት ባለቤት ከመሆናችን ባሻገር፤ የአክሱም ሀውልቶች የሕንፃ ስነ ጥበብ፣ የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት አስደናቂ ምህንድስና፣ እንዲሁም የቅዱስ ያሬድ የዜማ ሥርዓት ከጀርባቸው እጅግ ጥልቅ የሆነ የጂኦሜትሪና የሂሳብ እውቀት እንደነበራቸው ታሪካችን በግልጽ ይመሰክራል።
በዘመናዊው የትምህርት ሥርዓታችን ሂሳብ ወደ ሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ እና ምህንድስና የሚያስገባን ዋነኛ በር ነው። አሁንም ድረስ ሂሳብን እንደ "አስፈሪ" እና "ከባድ" ትምህርት አድርጎ የማየት ክፍተት ቢኖርም፣ የኮዲንግ፣ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ስልጠናዎች እና የሂሳብ ክለቦች ይህንን አመለካከት በመቀየር ረገድ ትልቅ ተስፋ እየፈጠሩ ነው።
ሂሳብ የሀገር ግንባታ፣ የኢኮኖሚ ዕድገት እና የቴክኖሎጂ ሽግግር ቁልፍ መሆኑን ተገንዝበን ታዳጊዎቻችንን በሂሳብ ትምህርት ይበልጥ ልናበረታታቸው ይገባል።
በልዩ እሸቱ

30 days ago
(ዘ-ሐበሻ ዜና) ለበርካታ ትውልዶች በሚቺጋኑ ካላማዙ ኮሌጅ ከኢኮኖሚክስ መምህርነትም የዘለለ አሻራ ያሳረፉት ፕሮፌሰር ኤሜሪተስ አህመድ ሁሴን የህይወት ጉዟቸውን የሚያወሳ አዲስ መጽሐፍ አሳትመዋል። ፕሮፌሰሩ በኮሌጁ የትምህርት ክፍሉ ኃላፊ፣ የአካባቢ ጥበቃ ትምህርት መስራች፣ እንዲሁም የኮሌጁ ከፍተኛ የማስተማር ክብር የሆነው የፍሎረንስ ጄ. ሉካሴ ሽልማት ተሸላሚ በመሆን ትልቅ ታሪክ ሰርተዋል። ሆኖም ከተማሪዎቻቸው አዕምሮ የማይጠፋው ማዕረጋቸው ሳይሆን፣ ለተማሪዎቻቸው ስኬት የነበራቸው ልባዊ ፍላጎት፣ ያበረከቱት የላቀ የምክር አገልግሎት እና ደግነታቸው ነው።
አሁን ደግሞ "ዘ ዴሴ ኪድ" (The Dessie Kid) በተሰኘው አዲሱ ማስታወሻቸው፣ ከኢትዮጵያ ደሴ ከተማ የልጅነት ጊዜያቸው አንስቶ አህጉራትን እስካቋረጠው የአካዳሚክ የህይወት ጉዟቸው ድረስ ያለውን ታሪክ ወደኋላ መለስ ብለው ዳስሰውታል። መጽሐፉ ፕሮፌሰሩ በጃፓን ዋሴዳ ዩኒቨርሲቲ፣ በዚምባብዌ አፍሪካ ዩኒቨርሲቲ፣ እንዲሁም በቦትስዋና ዩኒቨርሲቲ ያሳለፉትን ጊዜያት ጨምሮ፣ ስለ ጽናት፣ ምስጋና፣ ቤተሰብ እና ህይወታቸውን ስለቀረጹ ሰዎች ጥልቅ የሆነ ግላዊ ምልከታን የያዘ ነው።
ፕሮፌሰሩ ይህንን ማስታወሻ ለመጻፍ ስላነሳሳቸው ምክንያት ሲገልጹ፣ ዓለማዊ ትምህርት ገና ባልተስፋፋበት ወቅት፣ መደበኛ ትምህርት ከሌላቸው ቤተሰቦች የተገኘ አንድ ልጅ እንዴት በአሜሪካ የአካዳሚክ ዓለም ውስጥ ስኬታማ ሊሆን እንደቻለ ለመረዳት መሆኑን ይናገራሉ። በተለይም የመንግስት ትምህርት ቤቶች የክርስትና ትምህርት ተጽዕኖ አለባቸው ተብሎ በሚታሰብበት ማህበረሰብ ውስጥ አድገው ይህንን ደረጃ ላይ መድረሳቸው ታሪካቸውን ልዩ ያደርገዋል።
ጸሃፊው አክለውም ታሪካቸው የተለመደውን የስደተኞች ህይወት የሚያስተጋባ ቢሆንም፣ መጽሐፉን የጻፉት የግል ስኬታቸውን ለማክበር አለመሆኑን ያብራራሉ። ይልቁንም፣ ማንም ሰው ብቻውን ስኬት ላይ እንደማይደርስ በማመን፣ ህይወታቸው በተለያዩ አጋጣሚዎች፣ እንዲሁም በትክክለኛው ጊዜ በደረሱላቸው ሰዎች እና ተቋማት ደግነት የተቀረጸ መሆኑን ለማሳየት ነው። መጽሐፉ በዋናነት የተጻፈው ቤተሰቦቻቸው ታሪካቸውን እንዲያውቁ፣ እንዲሁም በጉዟቸው ላይ ለረዷቸው መምህራን፣ ጓደኞች እና ተማሪዎች ምስጋና ለማቅረብ ነው።
በካላማዙ ኮሌጅ ያሳለፉት 34 ዓመታት በሙያ ህይወታቸው ውስጥ ትልቅ ስፍራ እንዳለው የሚያወሱት ፕሮፌሰሩ፣ ኮሌጁ ሙያዊ ክህሎታቸውን ከማሳደግ ባሻገር ማንነታቸውን ሙሉ በሙሉ የተቀበለ እና ያከበረ የመጀመሪያው ተቋም እንደነበር ይመሰክራሉ። ኮሌጁ ከነጭ-ተኮር ተቋምነት ወደ አካታች እና ብዝሃነት ወዳለው ማህበረሰብ ሲቀየር በዓይናቸው ማየታቸውም በህይወታቸው ትልቅ ስፍራ ከሚሰጡት ክስተቶች አንዱ ነው።
ጡረታ ከወጡ በኋላ ጊዜያቸውን ከልጅ ልጆቻቸው ጋር በማሳለፍ በማንበብ እና ከህይወት አጋራቸው ጋር በመጓዝ ላይ የሚገኙት ፕሮፌሰር አህመድ፣ ይህን መጽሐፍ ለማጠናቀቅ ወደ ስድስት ዓመታት ገደማ እንደፈጀባቸው ገልጸዋል። የህትመት እና የስርጭት ሂደቱንም የጥራት ደረጃውን ለመጠበቅ ሲሉ ሙሉ በሙሉ በራሳቸው ወጪ እንዳከናወኑት ጠቁመው፣ አንባቢያን መጽሐፉን ለዚሁ ዓላማ ከተዘጋጀው ድረ-ገጽ ላይ ማግኘት እንደሚችሉ አስታውቀዋል።

Comments