“ሂሳብ ከባድ ነው” የሚለውን ትርክት የሚሰብረው የኢትዮጵያውያን አሻራ እና ማቲማቲክስ 2.0
******************
አስቡት... ሂሳብ በፈተና ወረቀት ላይ ብቻ ተሰርቶ የሚያበቃ የትምህርት ዓይነት ሳይሆን፣ የዓለማችንን እጣ ፈንታ የሚወስን፣ የቴክኖሎጂ እና የስልጣኔ ሁሉ የልብ ትርታ ነው።
ዛሬ ላይ የሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI)፣ ዳታ ሳይንስ፣ የህክምና እና የህዋ ምርምር ያለ ሂሳብ ቀመር አንድም እርምጃ ወደፊት መራመድ አይችሉም።
በየዓመቱ ሀምሌ 1 የሚከበረው የዓለም የማቲማቲክስ 2.0 ቀን ይህንኑ እውነታ የሚያስታውሰን ነው። ይህ ቀን የባህላዊ ሂሳብ ፅንሰ ሀሳቦች ከዘመናዊ ስልታዊ ቀመሮች፣ ከኮዲንግ እና ከዳታ ሳይንስ ጋር ተቀናጅተው ዓለምን እንዴት እየቀየሯት እንደሆነ በጉልህ የምናስብበት ዕለት ነው።
ታዲያ በዚህ ዓለም አቀፍ የዕውቀት መድረክ ላይ የኢትዮጵያውያን አሻራ ምን ይመስላል? የኢትዮጵያ ስም በዓለም አቀፍ የሂሳብ ውድድሮች እና በምርምር መድረኮች ላይ ደማቅ ሆኖ ተጽፏል። ለዚህም በአሜሪካ ሳቫና ስቴት ዩኒቨርሲቲ የሂሳብ ፕሮፌሰር የሆኑት ሙላቱ ለማ (ዶ/ር) ትልቅ ማሳያ ናቸው።
ፕሮፌሰሩ በአውሮፓውያኑ 2011 "የሙላቱ ቁጥሮች" የተሰኘውን የሂሳብ ቀመር በማስተዋወቅ የተለያዩ ዓለም አቀፍ ሽልማቶችን አግኝተዋል።
በሌላ በኩል ከኮርኔል ዩኒቨርሲቲ በኮምፒውተር ሳይንስ የዶክትሬት ዲግሪ በመቀበል የመጀመሪያዋ ጥቁር ሴት የሆነችው ወጣቷ ተመራማሪ ረድኤት አበበ በኮምፒውተር ሳይንስ እና ሂሳብ ላበረከተችው አስተዋጽኦ የዓለምን ትኩረት መሳብ ችላለች።
የኢትዮጵያ ከሂሳብ ጋር ያላት ትስስር የዛሬ ብቻ ሳይሆን የሺህ ዓመታት ታሪክ ያለው ነው። የራሳችን የግዕዝ የቁጥር ሥርዓት ባለቤት ከመሆናችን ባሻገር፤ የአክሱም ሀውልቶች የሕንፃ ስነ ጥበብ፣ የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት አስደናቂ ምህንድስና፣ እንዲሁም የቅዱስ ያሬድ የዜማ ሥርዓት ከጀርባቸው እጅግ ጥልቅ የሆነ የጂኦሜትሪና የሂሳብ እውቀት እንደነበራቸው ታሪካችን በግልጽ ይመሰክራል።
በዘመናዊው የትምህርት ሥርዓታችን ሂሳብ ወደ ሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ እና ምህንድስና የሚያስገባን ዋነኛ በር ነው። አሁንም ድረስ ሂሳብን እንደ "አስፈሪ" እና "ከባድ" ትምህርት አድርጎ የማየት ክፍተት ቢኖርም፣ የኮዲንግ፣ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ስልጠናዎች እና የሂሳብ ክለቦች ይህንን አመለካከት በመቀየር ረገድ ትልቅ ተስፋ እየፈጠሩ ነው።
ሂሳብ የሀገር ግንባታ፣ የኢኮኖሚ ዕድገት እና የቴክኖሎጂ ሽግግር ቁልፍ መሆኑን ተገንዝበን ታዳጊዎቻችንን በሂሳብ ትምህርት ይበልጥ ልናበረታታቸው ይገባል።
በልዩ እሸቱ

29 days ago