Logo
FastMereja
ኮሚሽኑ ለተመካካሪዎች ገለጻ እየሰጠ ነው

​#fastmereja | የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ከሐምሌ 8 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ለሚካሄደው ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ ዝግጅቱን አጠናክሮ በመቀጠል፣ ለተመካካሪዎች የቅድመ ምክክር ገለጻ መስጠት ጀምሯል።

​በጉባኤው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መሥፍን አርአያ፣ ኢትዮጵያ ለታላቁ የአፍሪካ ነፃነት ተምሳሌት መሆኗን አስታውሰዋል። ተመካካሪዎች የአድዋን መንፈስ በመያዝ፣ ይህንን የጋራ የሀገር ፍቅር ስሜት ወደ ገንቢ የሀገር ግንባታ እና የመግባባት ሂደቶች እንዲቀይሩ ጥሪ አቅርበዋል። በሚቀጥሉት ሦስት ቀናት የሚቆየው ይህ ገለጻ፣ ተመካካሪዎች በሂደቱ ዙሪያ ጥልቅ ግንዛቤ እንዲጨብጡ በማድረግ ምክክሩን በስኬት ለመወጣት ወሳኝ መሆኑን ዋና ኮሚሽነሩ አሳስበዋል።

​በገለጻው ወቅት የሀገራዊ ምክክር ጉባኤው ዓላማ፣ ተመካካሪዎች ሊኖራቸው የሚገባው ሚናና ኃላፊነት፣ እንዲሁም የውይይቱ ሥነ ምግባር እና የአሠራር ሥርዓት በዝርዝር እየቀረበ ይገኛል። ይህ ቅድመ ዝግጅት፣ ከሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች የተወጣጡት ተመካካሪዎች በጉባኤው ላይ ውጤታማ እና የተሳለጠ ተሳትፎ እንዲያደርጉ ለማስቻል የታለመ መሆኑ ተመላክቷል።

29 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.