3 months ago
የብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደሥላሴ መታሰቢያ ሐውልት በኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ ተመረቀ
#ethiopia | በኢትዮጵያ ዘመናዊ ታሪክ፣ በዲፕሎማሲ፣ በሥነ ጽሑፍና በሕዝብ አገልግሎት ዘርፍ የማይረሳ አሻራ ያሳረፉትን ብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደሥላሴን ለመዘከር የተገነባው የመታሰቢያ ሐውልት ሐምሌ 9 ቀን 2018 ዓ.ም. በኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ ቅጥር ግቢ በይፋ ተመርቋል።
በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ ላይ የቤተሰብ አባላት፣ የአካዳሚው አመራሮች፣ ምሁራንና የተለያዩ የክብር እንግዶች ተገኝተዋል።
የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ ፕሬዝዳንት ፕሮፌሰር በላይ ካሳ እንደገለጹት፣ ብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደሥላሴ ከ24 በላይ መጻሕፍትን በመጻፍ ለኢትዮጵያ ዘመናዊ ሥነ ጽሑፍ መሠረት ከጣሉ ሊቃውንት አንዱ ሲሆኑ፣ በዲፕሎማሲ፣ በባንክ ሥርዓት፣ በቴአትር፣ በቀይ መስቀል ማኅበር እና በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዘርፎችም የላቀ አስተዋጽኦ አበርክተዋል።
በተጨማሪም ኢትዮጵያ በሊግ ኦፍ ኔሽንስ አባልነት እንድትቀላቀል በተደረገው ዲፕሎማሲያዊ ጥረት ጉልህ ሚና የተጫወቱ ሲሆን፣ ከአምባሳደርነት እስከ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትርነት ሀገራቸውን በታማኝነት ማገልገላቸው ተጠቅሷል።
አካዳሚው ታሪካዊ መኖሪያ ቤታቸውን በቅርስነት በመጠበቅ ዋና መሥሪያ ቤት አድርጎ እየተጠቀመበት ሲሆን፣ የግል ሰነዶቻቸውን፣ ፎቶግራፎችን፣ መጻሕፍቶችንና ሌሎች ቅርሶችን የያዘ ቋሚ ሙዚየምም ለጎብኚዎች ክፍት አድርጓል።
ሐውልቱ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የእይታ ጥበብ ባለሙያ ሠዓሊ ኢዮብ ኪታባ እና በቡድናቸው የተቀረጸ ሲሆን፣ ለሥራው መሳካት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላበረከቱት የብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደሥላሴ የልጅ ልጅ ልጅ ወይዘሮ ገነት ኅሩይ የእውቅና ሰርተፍኬት ተበርክቶላቸዋል።
ይህ የመታሰቢያ ሐውልት የብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደሥላሴን ታሪካዊ አስተዋጽኦ ለቀጣዩ ትውልድ በማስተላለፍ ረገድ ከፍተኛ ፋይዳ እንደሚኖረው ተገልጿል።
#ethiopia #scienceacademy #blatengetahruy #history #heritage #getutemesgen #ጌጡተመስገን

Comments