20 days ago
የተፈሪ መኮንን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ያዘጋጀው ታላቅ የሥራ ትስስር (Job Fair) ተካሄደ
#fastmereja I የተፈሪ መኮንን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ በ2018 ዓ.ም ስልጠናቸውን ያጠናቀቁ ምሩቃንን እና ሌሎች የቴክኒክና ሙያ ሰልጣኞችን በቀጥታ ከቀጣሪ ድርጅቶች ጋር ለማገናኘት ያለመ የመጀመሪያው የሥራ ትስስር (Job Fair) ዛሬ ሐምሌ 09 ቀን 2018 ዓ.ም. በታላቅ ድምቀት አካሂዷል።
የተፈሪ መኮንን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ዋና ዲን አቶ ተሾመ ፌይሳ ዋክቶሌ ለፋስት መረጃ በሰጡት ቃል እንደገለጹት፤ ይህ የሥራ አውደሪ የተዘጋጀው ቀጣሪ ኢንዱስትሪዎችንና ሥራ ፈላጊ ሰልጣኞችን በአንድ መድረክ በማገናኘት፣ ሁለቱም ወገኖች ተፈላጊ ሰራተኛና የሥራ ዕድል ፍለጋ የሚያባክኑትን ጊዜና እንግልት ለመቀነስ ታስቦ የተዘጋጀ ነው። ኮሌጁ ይህንን መድረክ በተቋም ደረጃ ሲያዘጋጅ ለመጀመሪያ ጊዜ ሲሆን፣ ከዚህ ቀደም በሌሎች መንግስታዊ ባልሆኑ ድርጅቶችና አማካሪዎች አማካኝነት ይዘጋጅ የነበረውን መርሃ ግብር ተቋሙ በባለቤትነት ተረክቦ ከተማ አቀፍ በሆነ መልኩ ማዘጋጀቱን አስረድተዋል።
በአውደሪው ላይ የኮሌጁ 967 መደበኛና የአጭር ጊዜ ሰልጣኞች ብቻ ሳይሆኑ፣ በአዲስ አበባ የሚገኙ 14ቱም ኮሌጆች ሰልጣኞቻቸውን ይዘው እንዲገኙ ጥሪ ተላልፎላቸዋል። ሰልጣኞቹ ከቀጣሪዎች ጋር ከመገናኘታቸው አስቀድሞ የሲቪ (CV) አጻጻፍ፣ የቃለ መጠይቅ ዝግጅት፣ አለባበስ እና የስራ ፈጠራ አስተሳሰብን በሚመለከት ሰፊ የአቅም ግንባታ ስልጠና ተሰጥቷቸዋል። ይህ ዝግጅት ምሩቃኑ በራስ የመተማመን ስሜት ኖሯቸው ወደ ሥራው ዓለም እንዲቀላቀሉ ትልቅ እገዛ እንደሚያደርግላቸው ታምኖበታል።
በዕለቱ በተካሄደው የሥራ አውደሪ ላይ ከሆቴል፣ ከኮንስትራክሽን፣ ከማኑፋክቸሪንግ፣ ከዘመናዊው የፈጠራ ግሪን ቴክኖሎጂ እና ከኢንፎርሜሽን ኮሙዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ (ICT) ዘርፎች የተውጣጡ ከ35 በላይ ኢንዱስትሪዎች ተገኝተው የቅጥር ሂደቶችን ሲያከናውኑ ውለዋል። ከተለመደው የቅጥር ሁኔታ በተጨማሪ በኮሌጁ በቴክኖሎጂ (ICT) ዘርፍ የተደራጁና የሰው ሰራሽ አስተዋጽኦ (AI) መተግበሪያዎችን በመጠቀም ድረ-ገጾችንና የተለያዩ የፈጠራ ስራዎችን የሚሰሩ ወጣት ስራ ፈጣሪዎች የራሳቸውን ማሳያ ጥግ ይዘው ስራዎቻቸውን ለእይታ አቅርበዋል።
ለአንድ ቀን ብቻ የሚቆየው ይህ የሥራ አውደሪ መርሃ ግብር፣ በቀጣይም በየዓመቱ ከምረቃ ሥነ-ሥርዓት አስቀድሞ በቋሚነትና በስፋት የሚዘጋጅ ዓመታዊ መርሃ ግብር ሆኖ እንደሚቀጥል ዋና ዲኑ አቶ ተሾመ ፌይሳ ጨምረው ገልጸዋል።
#ኹነት

21 days ago
መንገደኞችን መልካም መንገድ በማለት ውሃ እና ቆሎ የሚሰጡት ሃላባዎች
#fastmereja | መነሻቸውን ወላይታ ሶዶ አድርገው መድረሻቸውን አዲስ አበባ ላደረጉ አሽከርካሪዎችና ተጓዦች በሃላባ ዞን ዌራ ዲጆ ወረዳ የክብር አቀባበልና የውሃና ቆሎ ግብዣ እየተደረገላቸው ነው። ተጓዦቹ አዲሱን አማራጭ መንገድ መጠቀም መጀመራቸውን ተከትሎ የአካባቢው ማህበረሰብ የአቀባበል መርሃግብሩን አዘጋጅቷል።
አሽከርካሪዎችና ተጓዦች ከአዲስ አበባ ወደ ሃላባ፣ ወላይታና አካባቢው ለማቅናት የነበረውን ረጅም መንገድ በማሳጠር በሃላባ ዞን ዌራ ዲጆ ወረዳ በኩል ያለውን የኮረኮንች (ፒስታ) መንገድ መጠቀም ጀምረዋል። ይህ አዲስ መንገድ ምንም እንኳን አስፓልት ባይኖረውም፣ በአሁኑ ወቅት እጅግ አጭር በመሆኑ ተመራጭ ሆኗል። ተጓዦቹ በዚሁ የፒስታ መንገድ አልፈው በስልጤ ዞን ሚቶ ወረዳ ከሚገኘው አስፓልት መንገድ ጋር በመቀላቀል ወደ አዲስ አበባ የሚያደርጉትን ጉዞ በስኬት እያካሄዱ ነው።
ይህንን አዲስ ጉዞ ምክንያት በማድረግ ሰላም ወዳዱ የሃላባ ማህበረሰብ ለአሽከርካሪዎችና ለተሳፋሪዎች "እንኳን በደህና መጣችሁ፣ ቀጣይ መንገዳችሁ የሰላም ይሁን" በማለት ሞቅ ያለ አቀባበል አድርጎላቸዋል። የአካባቢው ነዋሪዎች ይህ መንገድ ምንጊዜም ሰላማዊና ምቹ መሆኑን በመግለጽ የውሃና የቆሎ ግብዣ በማቅረብ ላይ ይገኛሉ።
ይህንን በስፍራው የተከናወነውን ህዝባዊ መስተንግዶና አዲስ የጉዞ መረጃ ለ"ፋስት መረጃ" ያደረሰን ናሙስ አባባ ነው።

25 days ago
"በአቅም ምክንያት ቤተሰቦቼ ባለመገኘታቸው ከፍቶኛል" የዋንጫ ተሸላሚ ተመራቂ
#fastmereja I ተማሪ ማስተዋል ካሳዉ በደቡብ ጎንደር ዞን ደብረታቦር ከተማ አካባቢ ተወልዳ እንዳደገች ትናገራለች። የመጀመሪያ ደረጃና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርቷንም ደብረታቦር አካባቢ እንደተማረች መረጃዎችን ያጋራችን ሲሆን በትምህርቷ ወቅትም ቤተሰቦቿ አቅም የሌላቸዉ በመሆኑ በርካታ ዉጣ ዉረዶችን ፣ፈተናዎችን ለማሳለፍ ተገዳለች።
የ12ኛ ክፍል ከአጠናቀቀች በኋላ የሪሚዲያል ትምህርቷን ለመከታተል ወደ ጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ ብታመራም ዉጤቷ 49.5 በመሆኑ በ0.5% ዉጤት ሳይመጣላት ቀርቷል።
ዉጤት በመቅረቱ ተስፋ ያልቆረጠችዉ ተማሪ ማስተዋል ካሳዉ ወደ ቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ግልገል በለስ ከተማ በማቅናት በለስ ፓራዳይዝ ኮሌጅ በዲፕሎማ መርሃግብር በፋርማሲ ትምህርት ክፍል በግል ለመማር ትመዘገባለች።
ወደ በረሃ ገነቷ ግልገል በለስ ከተማ ለትምህርት ከሄደች በኋላም ቤተሰቦቿ የፋይናንስ አቅም የሌላቸዉ በመሆኑ ህይወት ዉጣ ዉረድ እንደሆነባት ትገልፃለች።
ትምህርቷን ለማጠናቀቅ የትምህርት፣ የዶርም እንዲሁም የእለት ጉርስ ለማግኜት ከትምህርቷ ጎን ለጎን የቀን ስራ በመስራት ራሷን እያስተዳደረች ትምህርቷን በከፍተኛ ዉጤት ለማጠናቀቅ በቅታለች።
ተማሪ ማስተዋል ካሳሁን የቀን ሰራተኛ በመሆን ለተከታታይ ዓመታት ጊዜዋን እየገፋች የነበረ ሲሆን ዛሬ ሐምሌ 4 ቀን 2018 ዓ.ም (26 A+ እና 16A ) 4.00 በማምጣት የ2 ሜዳልያና የዋንጫ ተሸላሚ ለመሆን በቅታለች።
የዋንጫና የሜዳልያ ባለቤቷ ተማሪ ማስተዋል ካሳሁን ቤተሰቦቿ አቅም የሌላቸዉ በመሆኑ እሷን ለማስመረቅ የመጣ አንድም ቤተሰብ ግን የሌለ በመሆኑ በጣም እንደከፋትም ትናገራለች።
የበረሃ ሰዉ እጅግ ደግ በመሆኑ አከራዮቿና ጎረቤቶቿ ደስታዋን ለመካፈል በምረቃ ፕሮግራሙ የተገኙ መሆኑን ለመታዘብ ችለናል።
በመጨረሻም በለስ ፓራዳይዝ ኮሌጅ ግልገል በለስ ካምፓስ የቀን ሰራተኛዋ ብርቱና ጀግናዋን ባለ ዋንጫና ሜዳልያ ባለቤቷን ተማሪ ማስተዋል ካሳሁንን በቋሚ ቅጥር እንደፈፀመላት የሚያሳይ የቅጥር ደብዳቤ ዋንጫዉን ስታነሳ በኮሌጁ አካዳሚክ ኮሚሽን በኩል በይፋ የቅጥር ደብዳቤዉ ተሰጥቷታል።
መረጃውን የፋስት መረጃ አጋር ምሳሌ ሚዲያ ከስፍራው አድርሶናል።

26 days ago
አትሌት ገንዘቤ ዲባባ ወደ ሪል እስቴት ዘርፍ ተቀላቀለች።
#fastmereja I አትሌት ገንዘቤ ዲባባ በስፖርት ዓለም ባካበተችው ስኬት ታግዛ፣ በኢትዮጵያ እያደገ ባለው የሪል እስቴት ንግድ ዘርፍ አዲስ ኢንቨስትመንት መጀመሯን የፋስት መረጃ ሰምቷል።
#ቢዝነስ

1 month ago
መርጌታ ነን በማለት 827 ሺህ ብር ያጭበረበሩት ወንድማማቾች በቁጥጥር ሥር ዋሉ
#fastmereja I ሰኔ 28 ቀን 2018 ዓ.ም.
በምስራቅ ጎጃም ዞን ሉማሜ ከተማ "መርጌታ ስመኘው የባህል መድኃኒት" በሚል የሐሰት ስም በመጠቀም፣ ከአንድ የአርባ ምንጭ ከተማ ነዋሪ ላይ 827 ሺህ ብር ያጭበረበሩ ስመኝ አባትነህ እና ያዛቸው አባትነህ የተባሉ ወንድማማቾች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን የከተማዋ ፖሊስ አስታወቀ።
የሉማሜ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽህፈት ቤት አዛዥ ኢንስፔክተር በድሉ መልሰው እንደገለጹት፣ አካሉ መለሰ የተባለው ተበዳይ በቡና ንግድ ሥራ ላይ የተሰማራ ሲሆን፣ ቡና ያስረከበው ደንበኛ ገንዘቡን ሊመልስለት ባለመቻሉ ለችግር ተዳርጎ ነበር። ተጠርጣሪዎቹ ወንድማማቾች ይህንን አጋጣሚ በመጠቀምና የሐሰት ሰነድ በማዘጋጀት "መርጌታ ነን፤ ያልተመለሰልህን ገንዘብ በባህል መድኃኒትና በጸሎት እናስመልሳለን" በሚል ማታለል የጠቀሱትን ከፍተኛ ገንዘብ ተቀብለዋል።
ፖሊስ በተጠርጣሪዎቹ ላይ ባደረገው ተከታታይ ክትትል በቁጥጥር ሥር ያዋላቸው ሲሆን፣ የተጭበረበረው 827 ሺህ ብር በከተማ አስተዳደሩ ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ጽህፈት ቤት በጊዜያዊነት በኤግዚቢትነት እንዲቀመጥ ተደርጓል። በአሁኑ ወቅት በአጭበርባሪዎቹ ላይ ሕጋዊና ተገቢው ቅጣት እንዲያገኙ የምርመራ መዝገብ ተደራጅቶ በትኩረት እየተሠራ ይገኛል።
በሉማሜ ከተማ ተመሳሳይ የማጭበርበር ወንጀሎች እየተደጋገሙ ሲሆን፣ ከዚህ ቀደም 625 ሺህ ብር በሐሰት ያጭበረበረ ሌላ ግለሰብ በ2 ዓመት ከ9 ወር ፅኑ እስራት መቀጣቱ ይታወሳል። ማኅበረሰቡ በተለይም በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ የሚለጠፉ መሰል የተጋነኑና የሐሰት ማስታወቂያዎችን በመለየት ራሱን ከትልቅ የገንዘብ ኪሳራና ማጭበርበር እንዲጠብቅ ፖሊስና የፋስት መረጃ ዝግጅት ክፍል መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
#ችሎት

2 months ago
Sponsored by
Surafel
2 months ago
"ሰላም ፋስት መረጃዎች ይህ ምስል እና ቪዲዮ በርካቶች "የአርሲ ኦርቶዶክሶች" ተብሎ እየተሰራጨ ይገኛል ነገሩ ግን አርሲ አይደለም በአማራ ክልል ማኖ ቀጨኔ ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያ የአከባቢው ገበሬ አዲስ ላሰራው ቤተክርስቲያን በከተማ የተሰሩ የቤተክርስቲያን ንዋይተ ቅድሳትን ይዞ ወደ አዲሱ ቤተ ክርስቲያን ሲሄድ የሚያሳይ ምስል ነው።
በቪዲዮ ላይ የሚያውቁን የከተማ ሰዎች እየደወሉ ምን ሆናችሁ ነው? በማለት እየተጨነቁ ስለሆነ እኛ ጋር ሰላም መሆናችን የሚዘዋወረው ፎቶ እና ቪዲዮ ለአዲሱ ቤተክርስቲያን መሆኑን አሳውቁልን። በአርሲ የተፈጸመውን ተግባር ሙሉ በሙሉ እናወግዛለን።"

ዛሬ የዌብሳይት ዲዛይነሮች ቀን ነው። ዓለማችን ወደ ዲጅታል እየተቀየረች ባለችበት በዚህ ወቅት ድርጅታችሁ እና ቢዝነሳናችሁ መዘመን ግድ ነው።
ሱራፌል ተፈሪ ይባል በጣም ጎበዝ የሆነ የዌብሳይት ዲዛይነር ነው። የፋስት መረጃን ጨምሮ በርካታ ሚዲያዎችን ድረ ገጽ ዲዛይን የሰራው ይህ ጎበዝ ወጣት ነው። "Yene IT solution" የተሰኘ ተቋሙ ምርጥ ምርጥ ድረ ገጾችን ከAI ጋር አስተሳስሮ ይሰራል።
ሱራፌልን ለማግኘት
+25193333-2325
itsolutionyenevibe.com

3 months ago
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ባለውለታ የአትሌት የብርጓል መለሰ ድንገተኛ እረፍት
#fastmereja I በተለያዩ ዓለም አቀፍ የጎዳና ላይ ውድድሮች የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ ከፍ ስታደርግ የቆየችው ዝነኛው አትሌት የብርጓል መለሰ፣ ለመጪው የካናዳው ኦታዋ ማራቶን ዝግጅት ላይ እያለች ዛሬ ጠዋት በድንገት ህይወቷ አልፏል። የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በጀግናዋ አትሌት ድንገተኛ ህልፈት የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን ገልጿል።
አትሌት የብርጓል መለሰ በስፖርታዊ ጨዋታዋ ለአፍሪካ እና ለዓለም አቀፍ መድረኮች አዲስ አልነበረችም። እ.ኤ.አ በ2015 በኮንጎ ብራዛቪል በተካሄደው የመላው አፍሪካ ጨዋታዎች በግማሽ ማራቶን የነሐስ ሜዳሊያ በማሸነፍ ሀገሯን አስከብራለች። በታዋቂው የቺካጎ ማራቶን የብር ሜዳሊያ ባለቤት ከመሆኗም ባሻገር፣ በሻንጋይ፣ ፕራግ እና ሂውስተን ማራቶኖች ላይ የድል አክሊልን ተቀዳጅታለች። በተጨማሪም በፓሪስ ግማሽ ማራቶን ለሁለት ጊዜያት እና በሊዝበን ግማሽ ማራቶን አሸናፊ በመሆን ስሟ በደመቀ ሁኔታ የሚነሳ ብርቱ አትሌት ነበረች።
ለተሳትፎ በዝግጅት ላይ በነበረችበት ወቅት የተሰማው ይህ አስደንጋጭ ዜና በመላው ስፖርት አፍቃሪ ዘንድ ታላቅ ሀዘንን ፈጥሯል። የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ለአትሌቷ ቤተሰቦች፣ ወዳጆች እና ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ መፅናናትን ተመኝቷል።
የ"ፋስት መረጃ" ዝግጅት ክፍልም በጀግናዋ አትሌት ህልፈተ ህይወት የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን እየገለፀ ለቤተሰቦቿ መፅናናትን ይመኛል።

ዲኬ ሆልዲንግስ የሀገር ውስጥ ምርትን በማሳደግ የውጭ ምንዛሬን እያዳነ መሆኑን ገለጸ
#fastmereja I በአራተኛው ዙር "የኢትዮጵያ ታምርት" ኤክስፖ ላይ የተሳተፈው ዲኬ ሆልዲንግስ (DK Holdings)፣ ትራክተሮችንና የግብርና መሣሪያዎችን ጨምሮ ልዩ ልዩ የኢንዱስትሪ ምርቶችን በሀገር ውስጥ በማምረት የውጭ ምርትን በከፍተኛ ደረጃ መተካት መቻሉን አስታወቀ። ኩባንያው በአሁኑ ወቅት ምርቶቹን እስከ 70 በመቶ የሚደርስ የሀገር ውስጥ ግብዓት በመጠቀም እያመረተ ይገኛል።
የኩባንያው ተወካይ አቶ ታረቀኝ ይልማ ለፋስት መረጃ እንደገለጹት፣ ድርጅቱ በግብርናው ዘርፍ ያለውን የቴክኖሎጂ ክፍተት ለመሙላት ሚዛን አማን ላይ ግዙፍ የትራክተር ማምረቻ ፋብሪካ እየገነባ ነው። ከትራክተር ባሻገር እንደ ማረሻ፣ መከትከቻ፣ የበቆሎ መፈልፈያ እና መውቂያ ያሉ የግብርና መሣሪያዎችን በሀገር ውስጥ ባለሙያዎችና ማሽነሪዎች እያመረተ ለገበሬው እያቀረበ ይገኛል።
ኩባንያው የኤሌክትሪክ ፍጆታን የሚቆጥቡና የክልሎችን ባህላዊ እሴት የሚያንፀባርቁ "ስማርት ፖሎችን" (ዘመናዊ የጎዳና መብራት ምሶሶዎች) በማምረት በጎንደር፣ በሚዛንና በቢሾፍቱ ከተሞች ተግባራዊ አድርጓል።
ቀደም ሲል 100 ፐርሰንት ከውጭ ይገቡ የነበሩ ትራንስፎርመሮችን የሀገሪቱን የጥራት ደረጃ በጠበቀ መልኩ በሀገር ውስጥ እያመረተ ነው። ለከተማ ውበትና ለጽዳት አገልግሎት የሚውሉ የቆሻሻ ማጠራቀሚያ ጋንዳዎችን በስፋት እያቀረበ ይገኛል።
ዲኬ ሆልዲንግስ እነዚህን ምርቶች በሀገር ውስጥ ማምረቱ በከፍተኛ ዶላር ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በመተካት ረገድ ትልቅ እገዛ እያደረገ መሆኑንና በቀጣይም የኢንዱስትሪ ማሽኖችን የመገጣጠም እና የመተከል ስራዎችን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቋል።

በአሶሳ ዞን በደረሰ የባስ መገልበጥ አደጋ የ6 ሰዎች ሕይወት አለፈ
#fastmereja I በአሶሳ ዞን በመንጌ ወረዳ በደረሰ አስከፊ የትራፊክ አደጋ የ6 ሰዎች ሕይወት ወዲያውኑ ሲያልፍ፣ በ24 ተሳፋሪዎች ላይ ደግሞ ከባድና ቀላል የአካል ጉዳት ደረሰ።
አደጋው የደረሰው ዛሬ ሚያዝያ 23 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡30 ገደማ ሲሆን፣ መነሻውን በሆሞሻ ወረዳ ፆሬ 6ኛ ካምፕ መገንጠያ አድርጎ ወደ ሽርቆሌ ወረዳ ይጓዝ የነበረ የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 3 - 01220 ቤ.ጉ የሆነ የሕዝብ ማመላለሻ ባስ በመንጌ ወረዳ "አቧራ ቀበሌ" ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ቁልቁለት ላይ ሲደርስ ተገልብጧል።
እንደ አሶሳ ዞን ፖሊስ መምሪያ መረጃ ከሆነ፣ የአደጋው መንስኤ በዝርዝር እየተጣራ ቢሆንም በቅድመ ምርመራ ግን ተሽከርካሪው ከልክ በላይ ጭነት ጭኖ ይጓዝ እንደነበር ታውቋል። ጉዳት የደረሰባቸው ተሳፋሪዎች ወደ ሕክምና ተቋማት ተወስደው እርዳታ እየተደረገላቸው ይገኛል።
ፖሊስ አሽከርካሪዎች የትራፊክ ሕግን በማክበርና የጭነት ልክን በመጠበቅ የዜጎችን ሕይወት እንዲታደጉ ጥሪ አቅርቧል። የ"ፋስት መረጃ" ዝግጅት ክፍል በአደጋው ሕይወታቸውን ላጡ ወገኖች ቤተሰቦች መጽናናትን ይመኛል።

4 months ago
አንጋፋው የጤና ባለሙያ ላይ የተፈጸመው ድብደባ
#fastmereja I በባሌ ዞን ሮቤ ከተማ መናኸሪያ ውስጥ የ35 ዓመታት የሥራ ልምድ ያላቸው አንጋፋ የጤና ባለሙያ የደረሰባቸው የመንጋ ድብደባ ህዝቡን አስቆጥቷል። ግለሰቡ ለረጅም ዓመታት በጤናው ዘርፍ ሀገራቸውን ሲያገለግሉ የቆዩና በአሁኑ ወቅት የጡረታ ሰነዶቻቸውን እያስተካከሉ የሚገኙ አባት መሆናቸው ታውቋል።
ተጎጂው አቶ ዋቆ ከዲር ይባላሉ። ግለሰቡ በጤናው ዘርፍ ለ35 ዓመታት ያህል በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ማለትም በቄለም ወለጋ ሆስፒታል፣ በጎባ ሆስፒታል፣ በጊኒር ሆስፒታል፣ በራይቱ ጤና ጣቢያ ሲያገለግሉ የቆዩ ባለሙያ ናቸው።
አቶ ዋቆ አገልግሎታቸውን አጠናቅቀው የጡረታ መብታቸውን ለማስከበር ሰነዶቻቸውን በማደራጀት ላይ በነበሩበት ወቅት፣ በሮቤ ከተማ መነኸሪያ ውስጥ ማንነታቸው ባልታወቁ ግለሰቦች አማካኝነት (ቪዲዮ በፋስት መረጃ ቴሌግራም ላይ አለ) ድብደባ ተፈጽሞባቸዋል።
እንደ ቤተሰብ አባላትና የቅርብ ወዳጆቻቸው ገለጻ፣ አቶ ዋቆ በ2009 ዓ.ም ከሶማሌ ክልል ጋር በነበረው የድንበር ግጭት ወቅት ዛሬ ደጋፊ ሊሆኑ የሚችሉ ልጆቻቸውን በሞት ያጡ አባት ናቸው። ይህን መሰል በሀገር ባለውለታ ላይ የተፈጸመ ግፍ በማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ዘንድ ከፍተኛ ቅሬታን ፈጥሯል።
ቪዲዮ 📍https://t.me/fastmereja

በትራፊክ አደጋ ጉዳት ደርሶባት የነበረችው ህፃን ሔርማ ስንታየሁ ህይወቷ አለፈ
#fastmereja I በተባበሩት አደባባይ አካባቢ በደረሰ የትራፊክ አደጋ ምክንያት በፅኑ ቆስላ በህክምና ስትረዳ የቆየችው ህፃን ሔርማ ስንታየሁ (እኩቹ) በዛሬው እለት ህይወቷ ማለፉ ተረጋገጠ። የህፃኗ ስርዓተ ቀብር ዛሬ ሚያዝያ 1 ቀን 2018 ዓ.ም በሰዓሊተ ምህረት ማርያም ካቴድራል ተፈጽሟል።
መጋቢት 23 ቀን 2018 ዓ.ም በደረሰው በዚሁ የትራፊክ አደጋ፣ የአንድ ሰው ህይወት ወዲያውኑ ማለፉንና ሶስት ሰዎች ደግሞ ከባድ ጉዳት ደርሶባቸው እንደነበር ፖሊስ መግለጹ ይታወሳል። ህፃን ሔርማ በደረሰባት ከባድ ጉዳት ላለፉት ቀናት በህክምና ስትረዳ ብትቆይም፣ ጥረቱ ሳይሳካ ቀርቶ ዛሬ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይታለች።
"ፋስት መረጃ" ለቤተሰቦቿ እና ለወዳጅ ዘመዶቿ መጽናናትን ይመኛል።

ሰብአዊነት በማደያ ሰልፍ
#fastmereja I በቀናት የነዳጅ ጥበቃ ሰልፍ ለተሰላቹ ሹፌሮች "ሲርለና" የተባለ በጎ አድራጎት ድርጅት ምግብና መጠጥ በማቅረብ አጋርነቱን አሳየ። ድርጅቱ በነዳጅ ማደያዎች አካባቢ ሌሊትና ቀን ለሚሰቃዩ አሽከርካሪዎች የሞራል ስንቅ ሆኗል።
ባለፉት ቀናት በነዳጅ እጥረት ምክንያት በርካታ አሽከርካሪዎች መኪናቸውን በማደያዎች ሰልፍ ላይ አቁመው አስቸጋሪ ሁኔታዎችን እያለፉ ይገኛሉ። ይህንን የተመለከተው ሲርለና በጎ አድራጎት ድርጅት፣ አባላቱን በማሰማራት ምግብ፣ ንጹህ የመጠጥ ውሃ፣ ቡና እና ሻይ በማቅረብ ሹፌሮችን "አይዟችሁ" ብሏል።
ይህ በጎ ተግባር በሹፌሮች ዘንድ ትልቅ ደስታን የፈጠረ ሲሆን፣ "በዚህ አስቸጋሪ ወቅት እንዲህ ያለ አጋርነት ማየት ትልቅ የሞራል ጥንካሬ ይሰጠናል" ሲሉ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። ድርጅቱ ያከናወነው ይህ ተግባር በችግር ወቅት መረዳዳትን የሚያሳይ እና "ይበል" የሚያሰኝ አርአያነት ያለው ስራ ሆኖ ተመዝግቧል። የ"ፋስት መረጃ" ዝግጅት ክፍልም እንዲህ ያሉ በጎ አድራጊዎችን ማበረታታት ለህብረተሰቡ አጋርነት ወሳኝ መሆኑን ያምናል።

5 months ago
ሚሊዮን ድሪባ ይባላል ልክ የዛሬ አመት በአዲስ አበባ ጡት ማስያዣ በማድረግ በአዲስ አበባ ጎዳናዎች እየቀረጸ በቲክቶክ በሚለቃቸው ቪዲዮዎች በአዲስ አበባ ፖሊስ ተይዞ ክስ እንደተመሰረተበት በፋስት መረጃ ተዘግቦ ነበር።
ከስህተቱ ያልተማረው ወጣት ሚሊዮን ድሪባ ከሀገር በመውጣት በስደት ኑሮውን የጀመረ ቢሆንም በቲክቶክ የሚለቀውን ቪዲዮ ግን አላቆመም ነበር በተለይ በእስልምና እና በኦርቶዶክስ እምነት ላይ በሚያስተላልፋቸው የጥላቻ ንግግሮች እና ድርጊቶች በርካቶችን ሲያስቆጣ ነበር። የእስልምና እምነት ተከታዮች ባደረጉት ክትትል የሚኖርበት አድራሻ በማግኘት በኬኒያ ይዘው ለፖሊስ አሳልፈው በመስጠት በስደት በሚኖርበት ሀገር ክስ መስርተውበታል።
ሚሊዮን በተያዘበት ወቅት በማልቀስ ይቅርታ እጠይቃለሁ ተውኝ በማለት ቢያለቅስም ለፖሊስ አሳልፈው ሰጥተውታል።
ቪዲዮን በቴሌግራም ገጻችን ያገኙታል
📌 https://t.me/fastmereja

የሜትር ታክሲ ድርጅቶች "የቴክኖሎጂ አውታር ወይንስ የገንዘብ መሰብሰቢያ?" ከአሽከርካሪዎች የቀረበ ከባድ ወቀሳ
በፋስት መረጃ ሪፖርተር #fastmereja I በኢትዮጵያ የትራንስፖርት ዘርፍ ውስጥ አብዮት የፈጠሩት የሜትር ታክሲ ድርጅቶች፣ በአሁኑ ወቅት በአሽከርካሪዎችና በባለንብረቶች ዘንድ "ቸልተኞች" የሚል ስያሜ እየተሰጣቸው ነው። ድርጅቶቹ ከእያንዳንዱ ጉዞ ኮሚሽን ከመሰብሰብ ባለፈ፣ አሽከርካሪው በየመንገዱ ለሚገጥሙት መዋቅራዊ ችግሮች ድምጽ ለመሆን ፍቃደኛ አይደሉም የሚሉ ቅሬታዎች በዝርዝር እየቀረቡ ነው።
📍የመቆሚያና የመጫኛ ቦታ እጥረት
አሽከርካሪዎች ከሚያነሱት ዋነኛ ችግር አንዱ ተሳፋሪ ለመጫንና ለማውረድ፣ እንዲሁም ትዕዛዝ እስኪመጣ ቆመው የሚጠብቁበት ቦታ አለመኖሩ ነው።
ድርጅቶቹ በሺዎች የሚቆጠሩ መኪኖችን ወደ ስራ ቢያሰማሩም፣ እነዚህ መኪኖች የት ቆመው ትዕዛዝ እንደሚጠብቁ ከአስተዳደሩ ጋር ተነጋግረው መፍትሄ አላመጡም።
ተሳፋሪ ለመጫን ለአፍታ የቆመ አሽከርካሪ በትራፊክ ፖሊሶች "ህገ-ወጥ ማቆም" ተብሎ ለከፍተኛ ቅጣት ይዳረጋል። ድርጅቶቹ ግን ይህንን የአሰራር ችግር ለመፍታት ከመንግስት ጋር ድርድር ሲያደርጉ አይታዩም።
📍የበዙ ቅጣቶችና የአሽከርካሪው መከላከል አቅም ማጣት
በአሁኑ ወቅት የትራፊክ ቅጣቶች ከመጠን በላይ መጨመራቸው ይታወቃል። አሽከርካሪዎች እንደሚሉት፦
"ተሳፋሪው በፈለገበት ቦታ ቁም ይላል፤ እምቢ ካልን መጥፎ ደረጃ (Rating) ይሰጡናል። ከቆምን ደግሞ ፖሊስ ይቀጣናል።"
ድርጅቶቹ አሽከርካሪዎቻቸው በስራ ላይ እያሉ ለሚገጥማቸው አድሏዊ ቅጣት የህግ ከለላ ወይም ድምጽ የመሆን ዝንባሌ የላቸውም።
📍"የሚቆጥረው አይቆጥርም" የቴክኖሎጂ ስህተቶችና የታሪፍ ኢ-ፍትሃዊነት
ሌላው አሳሳቢ ቅሬታ በድርጅቶቹ መተግበሪያ (App) ላይ የሚታየው የርቀትና የዋጋ ስሌት አለመጣጣም ነው።
መተግበሪያዎቹ ብዙ ጊዜ የሚሰላው በኪሎሜትር እንጂ በትራፊክ መጨናነቅ ውስጥ ለሚባክነው ጊዜ እና ርቀት ተገቢውን ክፍያ አያካትቱም።
"አፕሊኬሽኑ የሚቆጥረው ርቀትና መኪናው በትክክል የሄደበት ርቀት አይጣጣምም፤ በዚህም የተነሳ አሽከርካሪው የሚገባውን ክፍያ አያገኝም" ሲሉ ቅሬታቸውን ይገልጻሉ።
📍የታክስ ጫና እና የኮሚሽን ግትርነት
የነዳጅ ዋጋ በየጊዜው ቢጨምርም፣ ድርጅቶቹ የሚወስዱት የኮሚሽን መቶኛ ግን ዝቅ እንዲል አይደረግም።
ባለንብረቶች እንደሚሉት ድርጅቶቹ ከመንግስት ጋር ተነጋግረው ለአሽከርካሪዎች የነዳጅ ድጎማ ወይም የቀለለ የታክስ ስርዓት እንዲዘረጋ ግፊት ማድረግ ሲገባቸው፣ ትኩረታቸው ኮሚሽን መሰብሰብ ላይ ብቻ ሆኗል።
📍ማጠቃለያ
አሽከርካሪዎችና ባለንብረቶች ድርጅቶቹን "ፕላትፎርሙን ብቻ ዘርግቶ ገንዘብ መሰብሰብ እንጂ ለአሽከርካሪው መብትና ለስራው ምቹ ሁኔታ መፈጠር ግድ የማይላቸው ከሆነ፣ ዘርፉ ወደ ቀውስ ሊያመራ ይችላል" ሲሉ የዘርፉ ተዋንያን ያስጠነቅቃሉ።

"እንኳን ለ130ኛው የአድዋ ድል በዓል በሰላም አደረሳችሁ! አድዋ የኢትዮጵያውያን የአንድነት ማህተም፣ የጥቁር ህዝቦች የነፃነት ፋና ነው። አባቶቻችንና እናቶቻችን በደማቸው የጻፉት ታሪክ ዛሬም ለእኛ ኩራታችን ነው! ድል ለኢትዮጵያ!"
ፋስት መረጃ
ፋስት መረጃ
5 months ago
በእስልምና ላይ የጥላቻ ንግግር ያሰራጨው ግለሰብ በእስራት ተቀጣ
#fastmereja I በፌስቡክ ገጹ ላይ የእስልምና ሃይማኖትን ክብር የሚነኩ ምስሎችንና የጥላቻ ንግግሮችን ሲያሰራጭ የነበረው ደሳለኝ በቀለ ጃላታ የተባለ ተከሳሽ፣ በ8 ወር እስራት እንዲቀጣ ተወሰነበት።
ተከሳሹ በየካቲት ወር 2018 ዓ.ም በግል የፌስቡክ ገጹ ላይ የእስልምና ሃይማኖት የሆኑትን ቆብና ጀለቢያ የለበሰ፣ ነገር ግን አካላዊ ቅርጹ የተዛባ (እጅና እግሩ የተገላቢጦሽ የሆነ) ምስል በመልቀቅ "የእስልምና ሃይማኖት ያለበትን ሁኔታ በምስል ስንገልጽ" የሚል ጽሁፍ አጅቦታል። በተጨማሪም "እግዚአብሔር ሆይ! ይህን የጠመመ ሰው አቅናው" የሚሉ መልዕክቶችን አብሮ ሲያሰራጭ እንደነበር የሳቺ ወረዳ አቃቤ ህግ ክስ መስርቶበታል።
ተከሳሹ ድርጊቱን መፈጸሙን አምኖ፣ "ድርጊቱን የፈጸምኩት አብዱልቃሲም የተባለ ሰው የኔን ሃይማኖት (ክርስትናን) ዝቅ አድርጎ በመጻፉ በንዴት ተገፋፍቼ ነው" በማለት ስህተቱን አምኗል።
ፍርድ ቤቱ ተከሳሹ የጥላቻ ንግግርና የሀሰተኛ መረጃ ስርጭትን ለመቆጣጠር የወጣውን አዋጅ መጣሱን አረጋግጧል።
በኦሮሚያ ክልል ኢሉ አባቦር ዞን የሳቺ ወረዳ ፍርድ ቤት ተከሳሹ ጥፋተኛ መሆኑን አምኖ ቀደምት የወንጀል ሪከርድ የሌለበት መሆኑን እንደ ማቅለያ በመያዝ፣ ሌሎች መሰል ድርጊት ከሚፈጽሙ ሰዎች እንዲማሩበት በሚል የ8 ወር ቀላል እስራት እንዲቀጣ እንደወሰነበት ፋስት መረጃ ሰምቷል።

የማህበራዊ ሚዲያ ተፅዕኖ ፈጣሪው መንሱር ጀማል ወደ ኢትዮጵያ ተመልሻለሁ አለ።
ባለፉት ወራት ኑሮውን በምዕራብ አፍሪካዊቷ ሀገር ቡርኪናፋሶ አድርጎ የቆየው ታዋቂው የማህበራዊ ሚዲያ ተፅዕኖ ፈጣሪ መንሱር ጀማል፣ ዛሬ ረቡዕ የካቲት 18 ቀን 2018 ዓ.ም ወደ ኢትዮጵያ መመለሱን አስታውቋል።
መንሱር ጀማል ወደ አዲስ አበባ መግባቱን ለፋስት መረጃ አረጋግጧል። በቡርኪና ፋሶ በቆየባቸው ጊዜያት በተለያዩ የቢዝነስ ጉዳዮች እያስጨረሰ እንደቆየ ተናግሯል።

6 months ago
አዋሽ ኢንሹራንስ እና የኢትዮጵያ አየር መንገድ አዲስ የጉዞ ጤና ኢንሹራንስ አገልግሎት ጀመሩ
📅 የካቲት 12 ቀን 2018 ዓ.ም
📍 አዲስ አበባ
አዋሽ ኢንሹራንስ ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ጋር በመተባበር መንገደኞች በጉዟቸው ወቅት ለሚያጋጥሟቸው ያልተጠበቁ የጤና እክሎች ዋስትና የሚሰጥ ዘመናዊ የጉዞ ጤና ኢንሹራንስ አገልግሎት በይፋ ማስጀመሩን አስታወቀ።
መንገደኞች የአየር መንገዱን የሞባይል መተግበሪያ (Mobile App) በመጠቀም ብቻ አገልግሎቱን በቀላሉ ማግኘት ይችላሉ ተብሏል።
በጉዞ ወቅት ለሚከሰቱ ድንገተኛ የጤና እክሎች እና ሌሎች ተያያዥ ችግሮች አስተማማኝ የኢንሹራንስ ሽፋን ይሰጣል።
የሁለቱን ግዙፍ ተቋማት ስትራቴጂካዊ ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር እና የደንበኞችን ምቾት ለማረጋገጥ ያለመ እንደሆነ ተነግሯል።
አዋሽ ኢንሹራንስ እስከ ታህሳስ 2025 (እ.ኤ.አ) ድረስ አጠቃላይ ሀብቱ ከ13 ቢሊዮን ብር በላይ መድረሱን ገልጿል።
#fastmereja | #ፋስት_መረጃ #ቢዝነስ መረጃ

ኤስ ኦ ኤስ የህጻናት መንደሮች በኢትዮጵያ በ2.8 ቢሊዮን ብር ፕሮጀክቶችን ይፋ አደረገ
---------------------------------------
📅 የካቲት 12 ቀን 2018 ዓ.ም
📍 አዲስ አበባ
ኤስ ኦ ኤስ የህጻናት መንደሮች በኢትዮጵያ በስዊዘርላንድ መንግስት ድጋፍ የሚተገበሩና ከ2.8 ቢሊዮን ብር በላይ በጀት የተመደበላቸው ስድስት ፕሮጀክቶችን በዛሬው ዕለት በይፋ አስጀምሯል።
በሲዳማ ክልል (አለታወንዶ እና ይርጋለም) እንዲሁም በኦሮሚያ ክልል (ያቤሎ) የሚተገበሩ ስድስት አዳዲስ የቤተሰብ እና የማህበረሰብ ማጠናከሪያ ፕሮጀክቶች ይፋ ሆነዋል።
ቀደም ሲል በሐረር፣ በጅጅጋ እና በጎዴ ሲተገበሩ የነበሩ ሶስት ፕሮጀክቶችም በዚሁ በጀት ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተገልጿል።
ከእነዚህ በተጨማሪ በሶማሌ ክልል (ቀብሪ ደሃር) እና በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል (ሆሳዕና) ላይ ከ251 ሚሊዮን ብር በላይ በጀት የተመደበላቸው ተመሳሳይ ፕሮጀክቶች እየተተገበሩ ይገኛሉ ተብሏል።
ፕሮጀክቶቹ በሚቀጥሉት ከሶስት እስከ አራት ዓመታት ውስጥ ተግባራዊ የሚሆኑ ሲሆን፣ በአጠቃላይ ከ420,000 በላይ ዜጎችን ተጠቃሚ ያደርጋሉ።
ዋና ዓላማውም ለህጻናትና ወጣቶች ሁለንተናዊ እድገት ምቹ የሆነ አካባቢ መፍጠር፣ ቤተሰቦችን በኢኮኖሚ ማጠናከር እና የህጻናት ጥበቃ ስርዓቶችን ማጎልበት እንደሆነ ተነግሯል።
የኤስ ኦ ኤስ የህጻናት መንደሮች የኢትዮጵያ እና የደቡብ ሱዳን ብሄራዊ ዳይሬክተር አቶ ሳህለማርያም አበበ እንደገለጹት፤ ድርጅቱ ቤተሰብንና ማህበረሰብን ማጠናከር፣ እንዲሁም የህጻናትና ወጣቶችን ደህንነት ማረጋገጥ አማራጭ የሌለው ግዴታ መሆኑን አምኖ እንደሚሰራ አረጋግጠዋል።
በስካይላይት ሆቴል በተካሄደው የፕሮጀክቶቹ ማስጀመሪያ ስነ-ሥርዓት ላይ ከፍተኛ የመንግስት ኃላፊዎች፣ የክልል ተወካዮች፣ የኤምባሲ ዲፕሎማቶች እና የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ተገኝቷል።
#fastmereja | #ፋስት_መረጃ

"በስሜት ተገፋፍቶ መናገር ቡድኑን ይጎዳል" ሚኬል አርቴታ
#fastmereja | ሚኬል አርቴታ ነጥብ ከጣሉ በኋላ ስላለው ስሜትና ቀጣይ እርምጃዎች የሚከተለውን ብሏል፦ "አሁን ስሜት ውስጥ በሆንንበት ሰዓት ቡድኑን ሊጎዱ የሚችሉ ነገሮችን መናገር በጣም ቀላል ነው። ሁሉም ተጫዋች የተቻለውን ለማድረግ እንደሚጥር ጥርጥር የለውም፤ ስለዚህ በዚህ ሰዓት የተሳሳተ ንግግር ማድረግ ሊወሰድ የሚችል መጥፎ ውሳኔ ነው" ብሏል።
"ዛሬ በሚፈለገው ደረጃም ሆነ ፉክክር ውስጥ አልነበርንም። በዚህ የሊግ ደረጃ ደግሞ ከሚፈለገው የብቃት ደረጃ በታች ከሆንክ የሚመጣውን ውጤት መቀበል አለብህ" ሲል ገልጿል።
"በሊጉ አሁን ያለንበት ደረጃ ላይ መገኘትን ደስ የሚል የሚያደርገው እንዲህ ያሉ የፈተና ጊዜያትን ማለፍ ነው። በፕሪምየር ሊግ ወደ የትኛውም ሜዳ ሄደህ ያለ ምንም ፈተናና መከራ ታሸንፋለህ ብለህ ካሰብክ፣ ያ ከእውነታው የራቀ ነው" ሲል አክሏል።
#ፋስት_መረጃ #ስፖርት

2ኛው የኢትዮጵያ የቡና ባህል ቀን ፌስቲቫል በአድዋ ድል መታሰቢያ ይካሄዳል!
📅 የካቲት 10 ቀን 2018 ዓ.ም
📍 አዲስ አበባ
ዋርካ ኮፊ ኃ/የተ/የግ/ማህበር "የቡና ባህላችን ለሀገራዊ አንድነታችንና ለኢኮኖሚ እድገታችን" በሚል መሪ ቃል 2ኛውን የኢትዮጵያ የቡና ባህል ቀን ፌስቲቫል የፊታችን የካቲት 14 ቀን 2018 ዓ.ም በአድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም በድምቀት እንደሚከበር ተገለፀ።
ይህ ፌስቲቫል ዝም ብሎ የቡና መጠጫ ፕሮግራም ብቻ ሳይሆን የሀገር ኩራት የሆነውን የቡና ባህላችንን በዓለም አቀፉ የቅርስ ተቋም (UNESCO) እንዲመዘገብ የሚደረግበት ትልቅ ሀገራዊ ንቅናቄ መሆን ተገልጿል።
በእለቱ የአስራ አንዱም ክልሎች ውብ የቡና ባህል አልባሳት እና የቁሳቁስ አውደ-ርዕይ፣በእናቶቻችን እጅ የሚፈሉ ጣፋጭ ቡናዎችና የባህል የቡና ቁርሶች፣የስዕል ኤግዚቢሽን፣ የእደ ጥበብ ስራዎች ባዛርና ልዩ ልዩ ጌሞች እንዲሁም ስለ ቡና ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ከባለሙያዎች ጋር የፓናል ዉይይት እንደሚኖር ነዉ የተገለፀዉ።
በእለቱም ከ2500-3000 የከተማዋ ነዋሪዎችና የዉጭ ሀገር ጎብኚዎች ይሳተፋሉ ተብሎ ይጠበቃል።
በፌስቲቫሉ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች፣ የክልል ተወካዮች፣ ዲፕሎማቶች፣ በአዲስ አበባ የሚገኙ የኤምባሲ አምባሳደሮች፣ የቅርስ ጥበቃ ባለሙያዎች እንዲሁም የቡና ላኪዎችና ተመራማሪዎች ይገኛሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ተገልጿል።
እንዲሁም በዛሬዉ መርሀ-ግብር ዋርካ ኮፊ ኃ/የተ/የግ/ማ እና የኢትዮጵያ ኤክስፖርት ማርኬት (EEM) በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸዉን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርመዋል።
#fastmereja | #ፋስት_መረጃ
----------------------------
ፈጣን • ታማኝ • ተደራሽ
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ቤተሰብ ይሁኑ፦
🔘 ቴሌግራም፦ https://t.me/fastmereja

🧧 祝大家 2026 马年快乐!🧧
全球数十亿人正在欢庆中国农历新年。速报 向在埃塞俄比亚生活的中国同胞、合作伙伴及所有朋友致以最亲切的节日问候。
根据中国传统历法,2026 年是马年。马象征着力量、速度、活力与成功。正如奔腾的骏马,我们祝愿大家在新的一年里勇往直前,事业腾飞!
🧧 እንኳን ለ2026 የቻይና የፈረስ ዓመት በሰላም አደረሳችሁ! 🐎
#fastmereja
በቢሊዮኖች የሚቆጠሩ የዓለማችን ሕዝቦች የሚያከብሩት የቻይና አዲስ ዓመት (Lunar New Year) ዛሬ በደመቀ ሁኔታ እየተከበረ ይገኛል። ፋስት መረጃ በኢትዮጵያ ለሚኖሩ የቻይናውያን ማህበረሰብ፣ ለሥራ ባልደረቦቻቸውና ለወዳጆቻቸው በሙሉ ልባዊ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክቱን ያስተላልፋል።
እንደ ቻይናውያን የዘመን አቆጣጠር 2026 የፈረስ ዓመት ነው። በቻይና ባህል ፈረስ የጥንካሬ፣ የፍጥነት፣ የነፃነት እና የድል ተምሳሌት ተደርጎ ይታመናል። ልክ እንደ ሚጋልብ ፈረስ፣ አዲሱ ዓመት ለሁላችንም ወደፊት የምንገሰግስበትና ስኬትን የምናጭድበት እንዲሆን እንመኛለን።

ህወሓት የኢትዮጵያ መንግስት "ለሌላ ዙር ደማዊ ጦርነት እየተዘጋጀ ነው" ሲል ከሰሰ
#fastmereja I ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ባወጣው ሳምንታዊ መግለጫ፣ የኢትዮጵያ መንግስት በፕሪቶርያው የሰላም ስምምነት መሰረት ወደ ድርድር ከመግባት ይልቅ መጠነ-ሰፊ ወታደራዊ ዝግጅት በማድረግ ወደ አዲስ ጦርነት እያመራ መሆኑን አስታወቀ። ፋስት መረጃ ከመግለጫው እንደተመለከተው፣ ድርጅቱ ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የጦርነት ደመናውን ለመግታት በአስቸኳይ ጣልቃ እንዲገባ ጥሪ አቅርቧል።
ህወሓት በመግለጫው እንዳመለከተው፣ የኢትዮጵያ መንግስት በአሁኑ ወቅት ግዙፍ የጦር መሳሪያና የሰራዊት ክምችት ወደ ትግራይ አቅጣጫ እያስጠጋ ይገኛል። ይህ እንቅስቃሴ "ሌላ ዙር ደማዊ ጦርነት ለመክፈት የታለመ ነው" ሲል ድርጅቱ የገለጸ ሲሆን፣ ባለፈው ሳምንት በሰላማዊ ሰዎችና በሰራዊቱ ላይ የተፈጸሙ የአየርና የምድር ጥቃቶች ለዚህ ማሳያ መሆናቸውን ጠቁሟል።
ድርጅቱ በመግለጫው ካሰፈራቸው ዋና ዋና ነጥቦች መካከል የኢትዮጵያ መንግስት ባደራጃቸው ታጣቂዎች አማካኝነት 40 በመቶ የሚሆነውን የትግራይ ህገ-መንግስታዊ መሬት ወሮ በመያዙ፣ ህዝቡ በመጠለያ ጣቢያዎች ውስጥ ለሞትና ለስቃይ መዳረጉን ገልጿል።
ህወሓት ለሰላም ቅድሚያ በመስጠት ልዩነቶች በውይይት እንዲፈቱ ጥረት ሲያደርግ መቆየቱንና አሁንም ፍላጎቱ ወደ ጦርነት መግባት ሳይሆን የፕሪቶርያው ስምምነት ወደ ዘላቂ ሰላም እንዲሸጋገር መሆኑን ገልጿል።
ማህበረሰቡ እስካሁን ለቀረቡ የሰላም ጥሪዎች "ጆሮ ዳባ ልበስ" ማለቱን የጠቀሰው መግለጫው፤ ሰሞኑን በተባበሩት መንግስታት፣ በአፍሪካ ህብረትና በአሜሪካ በኩል የወጡ መግለጫዎች ጥሩ ጅምር ቢሆኑም፣ አሁን ካለው ስጋት አንጻር ግን "ተጨባጭ እርምጃ" እንደሚያስፈልግ አሳስቧል።
በመጨረሻም ህወሓት፣ የኢትዮጵያ መንግስት ወታደራዊ ዝግጅቱን በአስቸኳይ አቁሞ ወደ ሰላማዊ ድርድር እንዲመለስ ሲል በመግለጫው ገልጿል።

አረቄ ቤት እና ቢንጎ ቤት እንዲዘጋ ህዝቡ ጠየቀ
l በሲዳማ ክልል ሆኮ ወረዳ የግርጃ ከተማ ወጣቶች የአረቄ መጠጥና የቢንጎ ቁማር ቤቶች የብዙ ወንድሞቻችን ህይወት ችግር ውስጥ ከቷል ብዙ ወንድሞቻችን በሞትም አጥተናል ስለዚህ በከተማችን ውስጥ የምገኙ አረቄ ቤቶችንና የቢንጎ ቁማር ቤቶች ይዘጉልን በማለት ድምፃቸውን አሰምቷል።
መረጃውን የፋስት መረጃ ነዉ
seledadotio

FastMereja.com l በሲዳማ ክልል ሆኮ ወረዳ የግርጃ ከተማ ወጣቶች የአረቄ መጠጥና የቢንጎ ቁማር ቤቶች የብዙ ወንድሞቻችን ህይወት ችግር ውስጥ ከቷል ብዙ ወንድሞቻችን በሞትም አጥተናል ስለዚህ በከተማችን ውስጥ የምገኙ አረቄ ቤቶችንና የቢንጎ ቁማር ቤቶች ይዘጉልን በማለት ድምፃቸውን አሰምቷል።
ፍሬዘር ግማ መረጃውን ለፋስት መረጃ ያደረሰው

መንታ ወንድማማቾችን በአንድ ጊዜ የምታፈቅረው ወጣት አነጋጋሪ ሆናለች
#fastmereja I በታይላንድ አንዲት ወጣት ሁለት ተመሳሳይ መንታ ወንድማማቾችን በአንድ ጊዜ በማፍቀርና በአንድ ጣራ ሥር አብራቸው በመኖር ላይ መሆኗን ይፋ ማድረጓ በዓለም አቀፍ ደረጃ የማኅበራዊ ሚዲያ መነጋገሪያ ሆኗል። ኦዲቲ ሴንተራል የተባለው የዜና ምንጭ እንደዘገበውና ፋስት መረጃ እንደተመለከተው፣ የ24 ዓመቷ ኖንግ ፋህ ይህን ያልተለመደ የፍቅር ግንኙነት የጀመረችው ሲንግ እና ሱዌ ከተባሉ መንታ ወንድማማቾች ጋር በአንድ ምግብ ቤት ውስጥ ከተዋወቁ በኋላ ነው።
መጀመሪያ ላይ ከሁለቱ አንዱን እንድትመርጥ በጓደኞቿ ግፊት ይደረግባት የነበረ ቢሆንም፣ እሷ ግን ለሁለቱም እኩል ፍቅር እንዳላት ተረድታለች። ፋስት መረጃ ከኦዲቲ ሴንተራል ዘገባ እንደተረዳው፣ ወንድማማቾቹም ሁኔታውን በጸጋ በመቀበል ሦስቱም በአንድ ቤት ውስጥ በፍቅር ለመኖር መስማማታቸውን ገልጸዋል።
ይህ ግንኙነት ከፍቅር ባለፈ በጋራ የገንዘብ አያያዝም የታጀበ ነው። ወንድማማቾቹ በግብርና ሥራ የሚተዳደሩ ሲሆን፣ ፋህ ደግሞ የቤቱን ፋይናንስና የሁለቱንም ወንድማማቾች የባንክ ሂሳብ በበላይነት ታስተዳድራለች። ወጣቷ በመካከላቸው ምንም ዓይነት የቅናት መንፈስ እንደሌለና ሦስቱም በአንድ ትልቅ አልጋ ላይ አብረው እንደሚተኙ ለሚዲያዎች በግልጽ ተናግራለች።
ምንም እንኳ ጉዳዩ በማኅበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ዘንድ የሥነ-ምግባር ክርክር ቢያስነሳም፣ የወጣቷና የወንድማማቾቹ ቤተሰቦች ግንኙነታቸውን አውቀውና ተቀብለው አብረው እንዲኖሩ ፈቅደውላቸዋል። በታይላንድ ሚዲያዎች ከፍተኛ ሽፋን ያገኘው ይህ ታሪክ፣ በሰዎች ዘንድ "የዘመኑ አስገራሚ የፍቅር ታሪክ" በሚል እየተነገረ ይገኛል።

የአዲስ አበባ የሜትር ታክሲዎች፦ በታክስና በገቢ መሃል የቆመው "የመቆሚያ" ፈተና
#fastmereja I በኢትዮጵያ ዋና ከተማ አዲስ አበባ፣ የትራንስፖርት ዘርፉን ለማዘመንና ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት ታስቦ ወደ ሥራ የገቡት የሜትር ታክሲዎች፣ በአሁኑ ወቅት ከከፍተኛ የመቆሚያ ቦታ እጥረት ጋር እየታገሉ ይገኛሉ። የፋስት መረጃ ዘጋቢ እንደዘገበው፤ አገልግሎት ሰጪዎቹ መንግሥት የሚፈልግባቸውን ግብርና ልዩ ልዩ ክፍያዎች በአግባቡ ቢወጡም፣ በምላሹ ግን በከተማዋ የንግድ ማዕከላትና ሰው በሚበዛባቸው አካባቢዎች በነፃነት ቆመው ተሳፋሪ የሚጠብቁበት ቦታ በማጣታቸው ለከፍተኛ እንግልት ተዳርገዋል።
1. የችግሩ ምንጭና መገለጫዎች
የሜትር ታክሲዎች እንደ ታክሲ (ሰማያዊና ነጭ) በተወሰነ መስመር ብቻ የሚመላለሱ ሳይሆኑ፣ ጥሪ በሚደረግላቸው ቦታ ሁሉ ተገኝተው አገልግሎት የሚሰጡ ናቸው። ሆኖም የሚከተሉት ችግሮች ተግዳሮት ሆነውባቸዋል፦
የማቆሚያ ቦታዎች እጥረት፦ በከተማዋ ሰፊ የግንባታ ስራዎችና የመንገድ ማስፋፊያዎች በሚካሄዱባቸው አካባቢዎች ለሜትር ታክሲዎች የሚሆን የተለየ ማቆሚያ አልተዘጋጀም።
ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ያለው ግጭት፦ አሽከርካሪዎች ተሳፋሪ ለመጠበቅ መንገድ ዳር ሲቆሙ በየትራፊክ ፖሊሶችና በመንገድ ደህንነት ተቆጣጣሪዎች ለከፍተኛ ቅጣትና ለሰሌዳ መፈታት ይጋለጣሉ።
ከሆቴሎችና የንግድ ማዕከላት ጋር ያለው አለመግባባት፦ ትልልቅ ሆቴሎችና የገበያ አዳራሾች ለራሳቸው ደንበኞች ብቻ ቦታውን ስለሚይዙ፣ የሜትር ታክሲዎች በነዚህ ቦታዎች አካባቢ መጠጋት እንኳን እንደማይችሉ ይገልጻሉ።
2. የአሽከርካሪዎች ብሶት
ብዙዎቹ አሽከርካሪዎች እንደሚገልጹት፣ ስራው አትራፊ የሚሆነው ሰው ባለበት አካባቢ ቆሞ በመጠበቅ እንጂ ዝም ብሎ ከተማዋን በማሽከርከር (Cruising) አይደለም። "ነዳጅ እየተወደደ ባለበት ሁኔታ ደንበኛ ፍለጋ ከተማዋን ማዞር ኪሳራ ነው" ይላሉ።
ዘጋቢያችን ያነጋገራቸውና ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ አንድ አሽከርካሪ እንደሚከተለው ብለዋል፦
"እኛ የንግድ ፈቃድ አውጥተን፣ ግብር እየከፈልን የምንሰራ ነን። ነገር ግን ቆመን ተሳፋሪ የምንጠብቅበት ቦታ ስለሌለን፣ በየደቂቃው ከትራፊክ ፖሊሶች ጋር እንጋጫለን። መቆሚያ ማጣት ማለት ለእኛ ሥራ ማጣት ማለት ነው።"
3. የኢኮኖሚና የማህበራዊ ተፅዕኖው
ይህ ችግር በአሽከርካሪዎች ላይ ብቻ ሳይሆን በከተማዋ ኢኮኖሚ ላይም ተፅዕኖ አለው፦
የአገልግሎት ጥራት መውረድ፦ ታክሲዎች ራቅ ያሉ ቦታዎች ላይ ለመቆም በመገደዳቸው፣ ደንበኞች ጥሪ ሲያደርጉ ታክሲው እስኪመጣ ረጅም ጊዜ እንዲጠብቁ ያደርጋቸዋል።
የነዳጅ ብክነትና የትራፊክ መጨናነቅ፦ ቋሚ መቆሚያ የሌላቸው ታክሲዎች ደንበኛ ፍለጋ መንገዶችን እያጨናነቁ ለመዞር ይገደዳሉ፣ ይህም ከፍተኛ የነዳጅ ብክነትን ያስከትላል።
የገቢ መቀነስ፦ አሽከርካሪዎች አብዛኛውን ጊዜያቸውን ለቅጣት ስለሚያሳልፉ፣ ያገኙት ገቢ ለቤት ኪራይና ለቤተሰብ ማስተዳደሪያ ሳይበቃቸው ይቀራል።
4. መፍትሔ የሚሹ ነጥቦች
አገልግሎት ሰጪዎቹና የዘርፉ ባለሙያዎች የሚከተሉትን የመፍትሔ ሃሳቦች ያነሳሉ፦
ተለይተው የታወቁ ማቆሚያዎች (Dedicated Zones)፦ በከተማዋ ዋና ዋና የንግድ አካባቢዎችና በሆቴሎች አቅራቢያ ለሜትር ታክሲዎች ብቻ የሚውሉ የመቆሚያ ቦታዎች መመደብ።
የዲጂታል መተግበሪያዎችንና መቆሚያዎችን ማቀናጀት፦ ቴክኖሎጂን በመጠቀም አሽከርካሪዎች በአቅራቢያቸው ወዳለ ክፍት ማቆሚያ የሚመሩበትን አሰራር መዘርጋት።
ከባለድርሻ አካላት ጋር መነጋገር፦ የትራንስፖርት ቢሮ፣ የትራፊክ ማኔጅመንት እና የሜትር ታክሲ የሚሰጡ ድርጅቶች በጋራ በመቀመጥ የአሰራር መመሪያዎችን ማሻሻል።
ማጠቃለያ
የአዲስ አበባ ሜትር ታክሲዎች የከተማዋን ገጽታ ከመቀየር ባለፈ ለብዙ ሺህ ወጣቶች የሥራ ዕድል የፈጠሩ ናቸው። በመሆኑም እነዚህ ግብር ከፋይ ዜጎች በሥራቸው ላይ የሚገጥማቸውን የመቆሚያ ቦታ ችግር መፍታት፣ የከተማዋን የትራንስፖርት ሥርዓት ከማዘመን ባለፈ ፍትሃዊ የሥራ አካባቢን ለመፍጠር ወሳኝ እርምጃ መሆኑን ዘጋቢያችን ዘገባውን ያጠናቅቃል።

ስለ ማስተር አብነት ከበደ የጤና ሁኔታና እየተሰራጩ ስላሉ የሀሰት መረጃዎች የተሰጠ ማብራሪያ
#fastmereja I በአሁኑ ወቅት በህክምና ላይ የሚገኙት ታዋቂው የማህበራዊ ሚዲያ በጎ ፣ድራጊ ማስተር አብነት ከበደን ስም በመጠቀም፣ የተሳሳቱ መረጃዎችና የማጭበርበር ድርጊቶች እየተፈጸሙ መሆኑ ተገለጸ። ማስተር አብነት ለፋስት መረጃ በላከው ልዩ መግለጫ፣ ህዝብ ከእነዚህ መሰል ድርጊቶች ራሱን እንዲጠብቅ አሳስቧል።
የማጭበርበር ሙከራዎችና የAI ቴክኖሎጂ ስጋት
ማስተር አብነት በህክምና ላይ መሆኑን ተገን በማድረግ፣ በተለያዩ የሀሰት (Fake) አካውንቶች እና በሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ቴክኖሎጂ ተቀናብረው የሚወጡ ምስሎች፣ ጽሁፎችና ተንቀሳቃሽ ምስሎች በስፋት እየተሰራጩ መሆኑ ተረጋግጧል።
ከዚህም ባለፈ አጭበርባሪዎች በውስጥ መስመር (Inbox) የድምጽና የጽሁፍ መልዕክቶችን በመላክ፣ “ለህክምና ድጋፍ” በሚል ስም የደጋግ ሰዎችን ገንዘብ ለመዝረፍ ሙከራ እያደረጉ መሆኑን መግለጫው አመልክቷል።
መግለጫው በግልጽ እንደሚያስረዳው፦
📌 ለማስተር አብነት ከበደ ህክምና የሚውል ምንም ዓይነት የገንዘብ ማሰባሰብ ስራ እየተከናወነ አይደለም።
📌 በማንኛውም መንገድ በስሙ የሚጠየቅ የገንዘብ ድጋፍ ሙሉ በሙሉ ሀሰተኛ እና ለማጭበርበር የታለመ ነው።
በማስተር አብነት ስም የተከፈቱ በርካታ የሀሰት ገጾች ቢኖሩም፣ ተከታዮች መረጃ እንዲቀበሉ የተፈቀደላቸው በሚከተሉት ትክክለኛ ገጾቹ ብቻ መሆኑ ታውቋል፦
Facebook: ከ1.9 ሚሊዮን በላይ ተከታዮች ያሉት ገጽ።
TikTok: ከ5.7 ሚሊዮን በላይ ተከታዮች ያሉት ገጽ።
በመጨረሻም፣ ህዝባችን እና የሚዲያ ተከታዮች ካልተረጋገጡና ከተቀናበሩ የሀሰት መረጃዎች ራሳቸውን እንዲጠብቁ፣ እንዲሁም መረጃዎችን ከታመኑ ምንጮች ብቻ እንዲከታተሉ ጥብቅ መልዕክት ተላልፏል።

Comments