በእስልምና ላይ የጥላቻ ንግግር ያሰራጨው ግለሰብ በእስራት ተቀጣ
#fastmereja I በፌስቡክ ገጹ ላይ የእስልምና ሃይማኖትን ክብር የሚነኩ ምስሎችንና የጥላቻ ንግግሮችን ሲያሰራጭ የነበረው ደሳለኝ በቀለ ጃላታ የተባለ ተከሳሽ፣ በ8 ወር እስራት እንዲቀጣ ተወሰነበት።
ተከሳሹ በየካቲት ወር 2018 ዓ.ም በግል የፌስቡክ ገጹ ላይ የእስልምና ሃይማኖት የሆኑትን ቆብና ጀለቢያ የለበሰ፣ ነገር ግን አካላዊ ቅርጹ የተዛባ (እጅና እግሩ የተገላቢጦሽ የሆነ) ምስል በመልቀቅ "የእስልምና ሃይማኖት ያለበትን ሁኔታ በምስል ስንገልጽ" የሚል ጽሁፍ አጅቦታል። በተጨማሪም "እግዚአብሔር ሆይ! ይህን የጠመመ ሰው አቅናው" የሚሉ መልዕክቶችን አብሮ ሲያሰራጭ እንደነበር የሳቺ ወረዳ አቃቤ ህግ ክስ መስርቶበታል።
ተከሳሹ ድርጊቱን መፈጸሙን አምኖ፣ "ድርጊቱን የፈጸምኩት አብዱልቃሲም የተባለ ሰው የኔን ሃይማኖት (ክርስትናን) ዝቅ አድርጎ በመጻፉ በንዴት ተገፋፍቼ ነው" በማለት ስህተቱን አምኗል።
ፍርድ ቤቱ ተከሳሹ የጥላቻ ንግግርና የሀሰተኛ መረጃ ስርጭትን ለመቆጣጠር የወጣውን አዋጅ መጣሱን አረጋግጧል።
በኦሮሚያ ክልል ኢሉ አባቦር ዞን የሳቺ ወረዳ ፍርድ ቤት ተከሳሹ ጥፋተኛ መሆኑን አምኖ ቀደምት የወንጀል ሪከርድ የሌለበት መሆኑን እንደ ማቅለያ በመያዝ፣ ሌሎች መሰል ድርጊት ከሚፈጽሙ ሰዎች እንዲማሩበት በሚል የ8 ወር ቀላል እስራት እንዲቀጣ እንደወሰነበት ፋስት መረጃ ሰምቷል።
#ችሎት

5 months ago