ኤስ ኦ ኤስ የህጻናት መንደሮች በኢትዮጵያ በ2.8 ቢሊዮን ብር ፕሮጀክቶችን ይፋ አደረገ
---------------------------------------
📅 የካቲት 12 ቀን 2018 ዓ.ም
📍 አዲስ አበባ
ኤስ ኦ ኤስ የህጻናት መንደሮች በኢትዮጵያ በስዊዘርላንድ መንግስት ድጋፍ የሚተገበሩና ከ2.8 ቢሊዮን ብር በላይ በጀት የተመደበላቸው ስድስት ፕሮጀክቶችን በዛሬው ዕለት በይፋ አስጀምሯል።
በሲዳማ ክልል (አለታወንዶ እና ይርጋለም) እንዲሁም በኦሮሚያ ክልል (ያቤሎ) የሚተገበሩ ስድስት አዳዲስ የቤተሰብ እና የማህበረሰብ ማጠናከሪያ ፕሮጀክቶች ይፋ ሆነዋል።
ቀደም ሲል በሐረር፣ በጅጅጋ እና በጎዴ ሲተገበሩ የነበሩ ሶስት ፕሮጀክቶችም በዚሁ በጀት ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተገልጿል።
ከእነዚህ በተጨማሪ በሶማሌ ክልል (ቀብሪ ደሃር) እና በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል (ሆሳዕና) ላይ ከ251 ሚሊዮን ብር በላይ በጀት የተመደበላቸው ተመሳሳይ ፕሮጀክቶች እየተተገበሩ ይገኛሉ ተብሏል።
ፕሮጀክቶቹ በሚቀጥሉት ከሶስት እስከ አራት ዓመታት ውስጥ ተግባራዊ የሚሆኑ ሲሆን፣ በአጠቃላይ ከ420,000 በላይ ዜጎችን ተጠቃሚ ያደርጋሉ።
ዋና ዓላማውም ለህጻናትና ወጣቶች ሁለንተናዊ እድገት ምቹ የሆነ አካባቢ መፍጠር፣ ቤተሰቦችን በኢኮኖሚ ማጠናከር እና የህጻናት ጥበቃ ስርዓቶችን ማጎልበት እንደሆነ ተነግሯል።
የኤስ ኦ ኤስ የህጻናት መንደሮች የኢትዮጵያ እና የደቡብ ሱዳን ብሄራዊ ዳይሬክተር አቶ ሳህለማርያም አበበ እንደገለጹት፤ ድርጅቱ ቤተሰብንና ማህበረሰብን ማጠናከር፣ እንዲሁም የህጻናትና ወጣቶችን ደህንነት ማረጋገጥ አማራጭ የሌለው ግዴታ መሆኑን አምኖ እንደሚሰራ አረጋግጠዋል።
በስካይላይት ሆቴል በተካሄደው የፕሮጀክቶቹ ማስጀመሪያ ስነ-ሥርዓት ላይ ከፍተኛ የመንግስት ኃላፊዎች፣ የክልል ተወካዮች፣ የኤምባሲ ዲፕሎማቶች እና የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ተገኝቷል።
#fastmereja | #ፋስት_መረጃ

4 months ago