2ኛው የኢትዮጵያ የቡና ባህል ቀን ፌስቲቫል በአድዋ ድል መታሰቢያ ይካሄዳል!
📅 የካቲት 10 ቀን 2018 ዓ.ም
📍 አዲስ አበባ
ዋርካ ኮፊ ኃ/የተ/የግ/ማህበር "የቡና ባህላችን ለሀገራዊ አንድነታችንና ለኢኮኖሚ እድገታችን" በሚል መሪ ቃል 2ኛውን የኢትዮጵያ የቡና ባህል ቀን ፌስቲቫል የፊታችን የካቲት 14 ቀን 2018 ዓ.ም በአድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም በድምቀት እንደሚከበር ተገለፀ።
ይህ ፌስቲቫል ዝም ብሎ የቡና መጠጫ ፕሮግራም ብቻ ሳይሆን የሀገር ኩራት የሆነውን የቡና ባህላችንን በዓለም አቀፉ የቅርስ ተቋም (UNESCO) እንዲመዘገብ የሚደረግበት ትልቅ ሀገራዊ ንቅናቄ መሆን ተገልጿል።
በእለቱ የአስራ አንዱም ክልሎች ውብ የቡና ባህል አልባሳት እና የቁሳቁስ አውደ-ርዕይ፣በእናቶቻችን እጅ የሚፈሉ ጣፋጭ ቡናዎችና የባህል የቡና ቁርሶች፣የስዕል ኤግዚቢሽን፣ የእደ ጥበብ ስራዎች ባዛርና ልዩ ልዩ ጌሞች እንዲሁም ስለ ቡና ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ከባለሙያዎች ጋር የፓናል ዉይይት እንደሚኖር ነዉ የተገለፀዉ።
በእለቱም ከ2500-3000 የከተማዋ ነዋሪዎችና የዉጭ ሀገር ጎብኚዎች ይሳተፋሉ ተብሎ ይጠበቃል።
በፌስቲቫሉ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች፣ የክልል ተወካዮች፣ ዲፕሎማቶች፣ በአዲስ አበባ የሚገኙ የኤምባሲ አምባሳደሮች፣ የቅርስ ጥበቃ ባለሙያዎች እንዲሁም የቡና ላኪዎችና ተመራማሪዎች ይገኛሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ተገልጿል።
እንዲሁም በዛሬዉ መርሀ-ግብር ዋርካ ኮፊ ኃ/የተ/የግ/ማ እና የኢትዮጵያ ኤክስፖርት ማርኬት (EEM) በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸዉን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርመዋል።
#fastmereja | #ፋስት_መረጃ
----------------------------
ፈጣን • ታማኝ • ተደራሽ
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ቤተሰብ ይሁኑ፦
🔘 ቴሌግራም፦ https://t.me/fastmereja

6 months ago