በትራፊክ አደጋ ጉዳት ደርሶባት የነበረችው ህፃን ሔርማ ስንታየሁ ህይወቷ አለፈ
#fastmereja I በተባበሩት አደባባይ አካባቢ በደረሰ የትራፊክ አደጋ ምክንያት በፅኑ ቆስላ በህክምና ስትረዳ የቆየችው ህፃን ሔርማ ስንታየሁ (እኩቹ) በዛሬው እለት ህይወቷ ማለፉ ተረጋገጠ። የህፃኗ ስርዓተ ቀብር ዛሬ ሚያዝያ 1 ቀን 2018 ዓ.ም በሰዓሊተ ምህረት ማርያም ካቴድራል ተፈጽሟል።
መጋቢት 23 ቀን 2018 ዓ.ም በደረሰው በዚሁ የትራፊክ አደጋ፣ የአንድ ሰው ህይወት ወዲያውኑ ማለፉንና ሶስት ሰዎች ደግሞ ከባድ ጉዳት ደርሶባቸው እንደነበር ፖሊስ መግለጹ ይታወሳል። ህፃን ሔርማ በደረሰባት ከባድ ጉዳት ላለፉት ቀናት በህክምና ስትረዳ ብትቆይም፣ ጥረቱ ሳይሳካ ቀርቶ ዛሬ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይታለች።
"ፋስት መረጃ" ለቤተሰቦቿ እና ለወዳጅ ዘመዶቿ መጽናናትን ይመኛል።

4 months ago