14 days ago
የአፋር ሕዝብ የህልውና ትግል እና የአሰብ እውነታ
***************
ከዳህላክ እና ምጽዋ ጀምሮ እስከ ታጁራ ድረስ ከአንድ ሺህ ኪሎሜትር በላይ በተዘረጋው የቀይ ባሕር ጠረፍ ላይ በመሃል ሌላ ማኅበረሰብ ሳይኖር ብቸኛ ነዋሪ የሆነው የአፋር ሕዝብ፣ ከእናት ሀገሩ ኢትዮጵያ እና ከተፈጥሮ መኖሪያ ምድሩ የተነጠለው በፍላጎቱ አልነበረም።
ይህ ሰፊ የባሕር ጠረፍ የሕዝቡ ተፈጥሯዊ መተንፈሻ እና የህልውናው መሠረት ቢሆንም፣ በፖለቲካዊ ሤራ ከባሕሩ እና ከወንድሞቹ እንዲገነጠል መደረጉን ኢቢሲ በጉዳዩ ዙሪያ ያሰናዳው ዘጋቢ ፊልም ይገልጻል።
በወቅቱ የአፋር ሕዝብ መሪ የነበሩት ሱልጣን አሊሚራህ ሀንፈሬ በጊዜው የተደረገውን አፋርን ለሁለት ቆርጦ የመገንጠል ድርጊት አጥብቀው ተቃውመውት ነበር።
ሱልጣኑ የኤርትራ ሕዝብ የራሱን ዕድል በራሱ የመወሰን መብት አለው በሚል የአፋርን ሕዝብ ለሁለት በከፈለው የኤርትራ ሪፈረንደም ላይ የአፋር ሕዝብ ጥያቄ እንዳለው ጠቅሰው፣ "አፋር ከኢትዮጵያ ጋር ነው የሚገናኘው" በማለት በግልጽ ሞግተዋል።
የአፋር ቋንቋ ባህልና ታሪክ ጥናትና ምርምር ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ሀቢብ መሐመድ እንደሚሉት፣ ሱልጣን አሊሚራህ ሀንፈሬ በወቅቱ አፋርን ለሁለት ከፍሎ የመገንጠልን ድርጊት በጽኑ ተቃውመዋል።
የአፋሮች መኖሪያ የሆነው የአሰብ አካባቢ እንዳይለማ እና እንዲራቆት መደረጉን የሚጠቅሱት ሀቢብ መሐመድ፣ ይህ የተደረገው አፋር ኢትዮጵያዊነቱን ስለሚያውቅ አንድ ቀን መመለሱ አይቀርም ብለው ስለሚፈሩ እንደሆነ ይናገራሉ።
የቀድሞ የአሰብ ከተማ ምክትል ከንቲባ አሊ ኢሳ መሐመድ፣ ሱልጣኑ "ዴሞክራሲ ከሆነ ኤርትራ ላለው የአፋር ሕዝብ ለምን የመምረጥ ዕድል አይሰጠውም?" ብለው ሲናገሩ፤ አቶ ኢሳይያስ አፈወርቂ ስብሰባውን ረግጠው ወጥተው እንደነበር ያስታውሳሉ።
ይህ የዴሞክራሲ ጥያቄ ምላሽ በማጣቱ ሱልጣኑ ሀገር ለቅቀው እንዲወጡ ተገደዱ፤ አፋርም ሳይወድ በግድ ተከፈለ።
ኤርትራ ነጻ ሀገር ከሆነች በኋላ በቀይ ባሕር አፋሮች ላይ የደረሰው ሰቆቃ ዋነኛ ዓላማ ሕዝቡን ከተፈጥሮ ምድሩ ማላቀቅ እንደነበር አስተያየት ሰጪዎቹ ይናገራሉ።
አቶ ሀቢብ መሐመድ እንዳብራሩት፣ ኢሳይያስ አፈወርቂ ሥልጣን ከያዙ በኋላ የነበራቸው ድብቅ አጀንዳ አፋርን ከቀይ ባሕር ጠረፍ ሙሉ በሙሉ ማጽዳት ነበር።
የተፈለገው መሬቱ እንጂ ሕዝቡ ባለመሆኑ ማፈናቀል፣ ግድያ እና ንብረት መውረስ ስልታዊ በሆነ መንገድ ተፈጽሟል።
ከማፈናቀል ባለፈ ወጣቶችን ከ12ኛ ክፍል በኋላ ወደ ሳዋ ወታደራዊ ካምፕ በግድ በመውሰድ፣ ባህላቸውን እንዲረሱ የማድረግ የማንነት ማጥፋት ወንጀል ተፈጽሟል።
የአፋር ቀይ ባሕር ዴሞክራሲያዊ ድርጅት ሊቀመንበር ኢብራሂም ሀሩን እንደሚሉት፣ ሳዋ የባህል እና የቋንቋ መጥፊያ ሲሆን፤ ሕዝቡ ሀገሩን ለቅቆ እንዲሄድ፣ የቀረው ደግሞ ቋንቋ እና ባህሉን እንዲተው ተገድዷል።
አሊ ኢሳ መሐመድ በበኩላቸው እንዳሉት፣ በአካባቢው የነበረው የአፋር ሕዝብ ተፈጥሯዊ የዓሣ ማጥመድ ሥራ በማፊያዎች እና በሕገወጥ መረቦች እንዲወድም ተደርጓል።
ዓሣ የሚኖርበትን እና ኮራል ያለበትን አካባቢ ጠራርጎ በሚወስድ መረብ ባሕሩ እንዲቀየር ከመደረጉም በላይ፣ ማፊያዎች ሚሊዮን ዶላሮች እየተቀበሉ መርዛማ ቆሻሻዎችን ባሕሩ ውስጥ እንዲጥሉ ተደርጓል።
አፋሮች በተፈጥሮ ሀብታቸው እንዳይሠሩ መከልከላቸው እና ያለ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ ለእስር መዳረጋቸውም የዚሁ ግፍ አካል ነው።
የቀድሞው የአሰብ ምክትል ከንቲባ ለ13 ዓመታት ያለ ፍርድ መታሰራቸውን ገልጸው፣ ጉዳያቸው ለባህላዊው የአፋር ፍርድ (መድዓ) እንዳይቀርብ መከልከሉም የሕዝቡን ሕግ እና ባህል ለማጥፋት እንደሆነ አብራርተዋል።
የቀድሞው የሀገር መከላከያ ሠራዊት ኤታማዦር ሹም ሌ/ጄኔራል ጻድቃን ገ/ተንሣይ እንዳብራሩት፣ የባህላዊው አውሳ ሱልጣኔት ሃይማኖታዊ፣ ባህላዊ እና ፖለቲካዊ ማዕከል ኢትዮጵያ ውስጥ ነው።
ምንም እንኳን አርቲፊሻል ድንበሮች ተሰምረው ሕዝቡን ከባሕሩ ቢያርቁትም፣ የአፋር ሕዝብ ማዕከል ምንጊዜም ኢትዮጵያ መሆኗን ጄኔራል ጻድቃን አረጋግጠዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ይህን እውነት ሲያጠናክሩ፣ የኤርትራም ሆነ የጅቡቲ አፋሮች በውክልና መጥተው ባህላዊ መሪያቸውን የሚመርጡት አሳይታ ላይ መሆኑን ጠቅሰው፣ የአውሳ ሱልጣኔት ማዕከሉ ኢትዮጵያ ውስጥ መሆኑን አስምረውበታል።
ከሰላሳ ዓመታት ዝምታ በኋላ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የአሰብን ጉዳይ ማንሳታቸው በአፋር ሕዝብ ዘንድ የፈጠረውን ወደር የለሽ ደስታ በተመለከተ ሀቢብ መሐመድ ሲገልጹ፣ "የአፋር ስሜቱ ገንፍሎ ወጥቷል፤ ከልክ በላይም ተደስቷል" ብለዋል።
ጥያቄያችን የዴሞክራሲ አይደለም የሚሉት የቀይ ባሕር አፋር ዴሞክራሲያዊ ድርጅት ሊቀመንበር ኢብራሂም ሀሩን፣ ምክንያቱንም ሲያስረዱ "የአፋር ሕዝብ ይኖራል ወይስ አይኖርም?" የሚል የሕልውና ትግል ውስጥ በመገባቱ እንደሆነ ጠቅሰዋል።
የተነጠቀውን ጠረፍ በመመለስ የአፋርን አንድነት ማረጋገጥ፣ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነትን ማስፈን እንዲሁም ታሪክን ከመደለዝ መታደግ የአፋር ሕዝብ አንገብጋቢ ጥያቄ መሆኑን ሊቀመንበሩ ያብራራሉ።
የቀይ ባሕር ወደ ኢትዮጵያ መመለስ ከማንም በላይ ጥቅሙ የአፋር ሕዝብ መሆኑን የጠቀሱት ሀቢብ መሐመድ፣ ባሕሩ ወደ ባለቤቱ እንዲመለስ አፋር አስፈላጊውን መስዋዕትነት ለመክፈል ዝግጁ መሆኑን ተናግረዋል።
በለሚ ታደሰ
#ethiopia #afar #seaaccess #seaport #redsea #assab #hornofafrica #ebc

1 month ago
ቅዱስ ዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ ከክፉ ነገር ሁሉ ይከልለን፤ ምለሰጃው እና ረድኤቱም አይለየን🙏
የተወለደው በገሊላ አውራጀ በቤተ ሳይዳ ነው፣ አባቱ ዘብዴዎስ ይባላል ገና በወጣትነቱ ዘመን ከወንድሙ ከያዕቆብ ጋር ለሐዋርያነት ከተጠራበት ጊዜ ጀምሮ የጌታውን እግር ተከትሎ አድጓል ቅዱስ ዮሐንስ፡፡ ወልደ ዘብዴዎስ፣ ወልደ ነጎድጓድ፣ ነባቤ መለኮት /ታኦሎጎስ/፣ ቁጽረ ገጽ በመባል ይታወቃል። ወንጌላዊው ቅዱስ ዩሐንስ ከ12ቱ ሐዋርያት አንዱ ሲሆን የመጀመሪያው ወጣት የመጨረሻው ሽማግሌ ሐዋርያ እሱ ነበር፡፡ የጌታ ደቀ መዝሙር ከመሆኑ በፊት የመጥምቀ መለኮት የቅዱስ ዮሐንስ ደቀ መዝሙር ከነበሩት አንዱ ነው፡፡ ለጌታችን ባሳየው ልዩ ቀረቤታና ፍቅር ምክንያት “ፍቁረ እግዚእ” የሚል ስያሜ አግኝቷል፡፡ ፍቅሩንና ታማኝነቱንም ጌታ በተሰቀለ ጊዜ “እሱን ያገኘ ያገኘኛል” ብሎ ሳይፈራ ከመስቀሉ ስር በመዋል አስመስክሮአል፡፡
በዩሐንስ 19÷26 እንደተጻፈው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ላይ ሳለ በመጨረሻዋ ሰዓት ቅዱስ ዮሐንስን ሲያየው እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን “እነኋት እናትህ ታጽናናህ” ብሎ ሰጥቶታል፡፡ እኛንም እመቤታችሁ እናታችሁ ቅድስት ድንግል ማርያም ናትና ታጽናናችሁ፣ ተስፋ አለኝታ ትሁናችሁ ማለቱ ነው፡፡ እርሷንም “እነሆ ልጅሽ፣ ይርዳሽ ያጽናናሽ” ብሎ ለእኛ ለክርስቲያኖችም በቅዱስ ዮሐንስ አማካኝነት ለእመቤታችን መስጠቱን እናያለን፡፡ እመቤታችን በቤተ ዮሐንስ እንደኖረች ሁሉ በልበ ምእመናንም አድራ በሃይማኖት የምታጸና፣ ምግባረ ሃይማኖትን፣ ሕገ ትሩፋትን የምታሰራ፣ ከልጅዋ ከወዳጅዋ ከመድኃኔዓለም ክርስቶስ ድኀነተ ስጋንና ድኀነተ ነፍስን፣ በረከተ ስጋንና በረከተ ነፍስን የምታሰጠን መሆንዋን ነው፡፡
ቅዱስ ዮሐንስ እንደ ጌታው ቃል እመቤታችንን ወደ ቤቱ ይዟት ሄደ ከእርሱ ጋርም አስራ አምስት ዓመት ተቀምጣለች፡፡ ሐዋርያው የጌታ ትንሣኤ በተነገረ ጊዜ ቅዱስ ጴጥሮስን ቀድሞ ከመቃብረ ክርስቶስ እንዲገኝ ያደረገው የፍቅሩ ጽናት ነበር፡፡ የቅዱስ ዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ የድንግልና ሕይወትም ረቂቁን ምስጢረ መለኮት ለማየት አስችሎታል፡፡ ምስጢረ ሥጋዌን አስተካክሎ አደላድሎ በመጻፍ አምልቶ አስፍቶ አስተምሯል፡፡ የፍቅረ እግዚአብሔርንና የፍቅረ ቢጽን ጠቃሚነት በስፋት ጽፏል፡፡ ሰማያትን ሰንጥቆ የሚበር ንስር፣ ልዑለ ስብከት፣ ምሥጢራትን የሚያይ ወንጌላዊ ዮሐንስ፣ ነገሩ ሁሉ በምስጢረ መለኮት የተቀመመ ነው፡፡ ገዳማውያንም ቅዱሳንን አብነት አድርገው ስለ ክርስቶስ ፍቅር ዓለምን ንቀው ይመንናሉና ገዳማቸውን እንደግፍ በዓታቸውን እናጸና፡፡
ድጋፍ ለማድረግ፦ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም
ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391
ወይም
አቢሲኒያ ባንክ
141029444
የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444

ያልተዘመረለት ጀግና!
* በኢትዮጵያ 30 ትምህርት ቤት አስገንብቷል
***
የአቶ አዲስ ገሠሠ አጭር የሕይወት ታሪክ
#ethiopia | አቶ አዲስ ገሰሰ ከአባታቸው ከግራዝማች ገሰሰ መንገሻ እና ከእናታቸው ከወይዘሮ አስናቀች መልሴ ጥር 8 ቀን 1945 ዓ.ም. በቀድሞው ኢሊባቦር ጠቅላይ ግዛት ጎሬ ከተማ ተወለዱ፡፡
እስከ 9ነኛ ክፍል በጎሬ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ት/ቤት ከተማሩ በኋላ፤ የ10ኛ ክፍል ትምህርታቸውን አዲስ አበባ በዳግማዊ ምንሊክ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተምረው፤ ወደ ጅማ በመሄድ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በሚያዝያ 27 2ተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተከታትለዋል፡፡
አቶ አዲሱ ገሰሰ በህይወታቸው ትልቅ ቦታ የሚሰጡትና “ ስብዕናዬን በዲሲፕሊን ገንብቶታል” የሚሉትን የኢትዮጵያ አየር ኃይልን በ1961 ዓ.ም. በመቀላቀል ከወታደራዊ ስልጠና ጋር በበረራ ቴክኒሻንነት ተመርቀዋል፡፡
በሙያቸው አንድ ዓመት ካገለገሉ በኋላ፤ በ1964 ዓ.ም. ነፃ የትምህርት እድል በማግኘታቸው ወደ አሜሪካ ሀገር ሺካጎ ከተማ በማቅናት በራንቱል ኤርፎርስ ቤዝ፤ እና በቴክሳስ ላክላንድ ኤርፎርስ ቤዝ ትምህርታቸውን አጠናቀው ተመርቀዋል፡፡
አቶ አዲስ ገሰሰ በወጣትነት ዘመናቸው ያን ጊዜ ሉፕ ኮሌጅ በሚባለው ሃሮልድ ዋሺንግተን ዩኒቨርሲቲ የሜካኒካል ኢንጅነሪንግ ትምህርታቸውን ተከታትለዋል፡፡ በመቀጠልም በኖርዝ ኢስተርን ኢሊኖይ ዩኒቨርሲቲ በማኔጅመንት ትምህርታቸውን አጠናቀዋል፡፡
አቶ አዲስ ገሰሰ ወንድሞቻቸውን ሙሉጌታ ገሰሰን፤ ዘለቀ ገሰሰንና ጓደኞቻቸውን እነ መላኩ ረታን ወደ ሺካጎ ካመጡ በኋላ ዳሎል ባንድን መስርተዋል፡፡ አቶ አዲስ ገሰሰ በሚማሩበት ኖርዝ ኢስተርን ኢሊኖይ ዩኒቨርሲቲ የጥቁር ታሪክ ወር /Black History Month/ በሚል መጠሪያ በየዓመቱ የካቲት ወር ላይ በተለያየ መዘክር በሚከበር በዓል ላይ፤ ዳሎል ባንድ ሙዚቃ እንዲያቀርብ በማስቻል የሙዚቃ ማኔጅመንት የህይወት ጉዟቸውን ሀ ብለው ጀመሩ፡፡
በመቀጠልም ዳሎል ባንድን ይዘው በዋሺንግተን፤ በሎስ አንጀለስ እና በመላው አሜሪካ ለመጀመሪያ ጊዜ ለኢትዮጵያውያን-በኢትዮጵያ ባንድ የሙዚቃ ኮንሰርት በማቅረብ ፈር ቀዳጅ እና ውጤታማ ስራ ሰርተዋል፡፡
አቶ አዲስ ገሰሰ ሙዚቃን ማኔጅ በማድረግ ጉዟቸው የእውቁን የሬጌ ሙዚቃ ንጉስ የቦብ ማርሌን ቤተሰብ ሃብትና ንብረቱን በማስተዳደር ብቻ ሳይሆን፤ የቦብን ልጆች በስነ ምግባር ኮትኮቶ ለማሳደግ ከአሜሪካ ኒውዮርክ -ጃማይካ ኪንግስተን እየተመላለሱ በትጋትና በታማኝነት ኃላፊነታቸውን ተወጥተዋል፡፡
በዚያን ጊዜም ዘመን አይሽሬውን የቦብ ማርሌይ “ሌጀንድ አልበም" እንዲሰራ ባቀረቡት ንድፈ-ሃሳብ መሰረት ከአይላንድ ሪከርዲንግ ጋር በመፈራረም ውጤማ ስራ ሰርተዋል፡፡
አቶ አዲስ ገሰሰ በቦብ ማርሌይ ቤተሰቦች የተዘጋጁትንና ከምድር ዳር እስከ ምድር ዳር ድረስ የተደረጉትን ዓለም አቀፍ የሬጌ ሙዚቃ ኮንሰርቶች ሃሳብ ከመጠንሰስ ጀምሮ ለሃያ ሁለት ዓመታት ያክል ስራውን በሃላፊነት መርተዋል፡፡ አስተዳድረዋል፡፡
በዚሁ የአስተዳደር ዘመናቸው በዘረጉት መንገድ እስካሁን ድረስ በየዓመቱ የሚደረገውን ዓለም አቀፍ የሬጌ ሙዚቃ ፌስቲቫል በማይናወጥ መሰረት ላይ አፅንተዋል፡፡
አቶ አዲስ ገሰሰ ዚጊ ማርሌይን ከጃማይካ… የነዘለቀን ገሰሰን ዳሎል ባንድ ደግሞ ከሺካጎ ወደኒዮርክ በማምጣት ካጣመሩ በኋላ ፤ ከሲግማ ስቱዲዮ እና ከቨርጂኒያ ሪከርድስ ጋር ውል በመፈራረም በአሜሪካ ምድር ቁጥር አንድ ተደማጭ የነበረውን ኮንሺየስ ፓርቲ አልበም እንዲለቀቅ አድርገዋል፡፡
በአልበሙ ከተካተቱት ስራዎች መካከል ቱሞሮ ፒውፕል የተሰኘው ሙዚቃ በዓለም ላይ እጅግ ከመወደዱ የተነሳ ብዙዎች እንደ ብሔራዊ መዝሙር ያዜሙት ነበር፡፡
በአቶ አዲስ ገሰሰ ማናጀርነት በተመራው በዚሁ የሙዚቃ አልበም ዚጊ ማርሌይ የአሜሪካንን ትልቁን ግራሚ አዋርድ ሽልማት ሲያገኝ፤ የኢትዮጵያው ዳሎል ባንድ ደግሞ ለመጀመሪያ ጊዜ እንደ ባንድ የግራሚ ሽልማት እንዲወስድ በማስቻል ታሪክ የማይረሳውን ስራ ሰርተዋል፡፡
ለሀገራቸው ኢትዮጵያ የተለየ ፍቅር የነበራቸው አቶ አዲስ ገሰሰ ከወንድማቸው ከአርቲስት ዘለቀ ገሰሰ ጋር በመሆን የቦብ ማርሊ 60ኛ ዓመት የልደት በዓሉን ለመዘከር የሚዘጋጀውን “አፍሪካ ዩናይት” ዓለም አቀፍ የሙዚቃ ዝግጅት ኢትዮጵያን መዳረሻ በማድረግና አንድ አመት የፈጀ የዘመቻ /ካምፔይን/ በመስራት ፤ በ1997 ዓ.ም. መስቀል አደባባይ የተካሄደውን የሙዚቃ ፌስቲቫል ስኬታማ እንዲሆን አስችለዋል፡፡ በዚሁ ፌስቲቫል ላይ የቀድሞውን ጠቅላይ ሚኒስትር ጨምሮ ሪታ ማርሌይና አምስቱ የቦብ ልጆች ተገኝተዋል፡፡
ይኸው ፌስቲቫል በፈጠረው መልካም አጋጣሚም ሀገራችንን በዓለም ዙሪያ ለማስተዋወቅ፤ የቱሪስት መዳረሻ ለማድረግና ኢንቨስመንት ለመሳብ በማለም ከ50 በላይ ዓለም አቀፍ ሚዲያዎችን ጋብዘው የራሳቸውን የዜግነት ድርሻ ተወጥተዋል፡፡
አቶ አዲስ ገሰሰ በሙዚቃ ማኔጅመንት የሕይወት ጉዟቸው ያካበቱትን እውቀትና ልምድ ተጠቅመው ተሰጥዎ ያላቸውን ልጆች በመቃኘት ሀገራቸውን በሙዚቃው ኢንደስትሪ ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪ ለማድረግ ትልቅ ህልም ነበራቸው፡፡ ለዚህም ቴዎድሮስ ካሳሁን /ቴዲ አፍሮን/ከመጀመሪያው አልበሙ ጀምሮ ማኔጅመንቱን በመያዝ ፤ እንዲሁም እጅጋየው ሽባባው /ጂጂን/ ከአጋራቸው ፓልም ሪከርዲንግ ጋር በመሆን ተወዳጅ የሆነ አልበሟን እንድተሰራ ያደረጉት አስተዋፅኦ የሚጠቀስ ነው፡፡
ይሄም ብቻ ሳይሆን ጃኖ ባንድን በመመስረት ለልጆቹ ውጤታማነት አቶ አዲስ ገሰሰ የአንበሳውን ድርሻ ይወስዳሉ፡፡ አቶ አዲስ “ጃናናይት” የተባለ ተሰጥዎ ያላቸውን ሴቶች የያዘ ባንድ መስርተው ስኬታማ ለማድረግ ያደረጉት ጥረትም የሚወሳ ነው፡፡
በሙዚቃ ኢንዱስትሪው- እጅግ ገዝፈው፤ በተለያየ የአድናቆት ቃል የሚጠሩት አቶ አዲስ ገሰሰ ከሀገራችን ውጪ እንደ ዚጊ ማርሌ፤ ስቴፈን ማርሌ፤ ሎረን ሂል፣ ፊል ኮሊንስ፣ ኧርዝ ዊንድ ኤንድ ፋየር እና ሌሎችንም በርካታ የሙዚቃ ከዋክብትን በማግኘትና በማስተዳደር በዓለም አቀፍ ደረጃ የብዙ ታላላቅ የሙዚቃ ሰዎች ስራን መስመር አሲዘዋል።
አቶ አዲስ ገሰሰ መደበኛ መኖሪያቸውን ወደ ኢትዮጵያ ካዞሩ በኋላ በሆቴሊንግ ዘርፍ በመሰማራት ላየንስ ዴን ሆቴልን፤ በማእድን ዘርፍም ዩኒቨርሳል ማይኒንግን፤ በግብርና መስክ አድሶጌት ኩባንያን በማቋቋም ለሀገራቸው እድገት ቀን ከሌት ያለእረፍት ሰርተዋል፡፡
አቶ አዲስ ገሰሰ በሙዚቃ ማኔጅመንትና በኢንቨስትመንት ስራቸው ብቻ ሳይሆን በበጎ አድራጎታቸውም አርአያነት ያለው ተግባር ፈፅመዋል፡፡ በግል ከደገፏቸው ግለሰቦች በተጨማሪ በሀገራችን በተለያዩ ወቅቶች በተፈጠሩ ሰብአዊ ችግሮች ቀድመው በመድረስ ያደረጉት አስተዋፅኦ የሚጠቀስ ነው፡፡
በዋናነትም ከወንድማቸው ዘለቀ ገሰሰ ጋር በመሆን በተለያዩ ገጠራማ አካባቢዎች 30 ትምህርት ቤቶችን አሰርተዋል፡፡
አቶ አዲስ ስለእነኚሁ በተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች ስላሰሯቸው 30 ትምህርት ቤቶች ሲናገሩ “ተስፋ ሳልቆርጥ በፅናት የታገልኩበት በጎ ተግባር በመሆኑ ያስደስተኛል” ይሉ ነበር፡፡
ቤተ-ክርስቲያን በጠራቻቸው ጊዜ ሁሉ እየተገኙም በመላው ኢትዮጵያ አዳዲስ ቤተክርስቲያኖችን በማሰራት ፤ የተጎዱ ገዳማትንና ቤተክርስቲያኖችን በማደስ ፤ የተዘጉ ቤተክርስቲያኖችን በማስከፈት፤ የቤተክርስቲያኖችን ንዋየ ቅዱሳን በማሟላትና የካህናት ደሞዝን በመክፈል እስከ ህይወት ፍፃሜያቸው ድረስ ድምፃቸውን አጥፍተው አገልግለዋል፡፡
አቶ አዲሱ ገሰሰ በማህበራዊ ህይወታቸው ቀልድ አዋቂ፤ ተጫዋች እና በቀላሉ ከሰዎች ጋር ተግባብተው የመኖር ፀጋ የነበራቸው ሲሆን ከሁሉም ግን ሰው አካባሪ እና ስነ-ምግባር ያለው ቀረቤታቸው ተወዳጅና በሰው ልብ አይረሴ አድርጓቸዋል፡፡
አቶ አዲስ ገሰሰ ከወ/ሮ ሶስና ሽፈራው ጋር በነበራቸው የፀና ትዳር አንድ ወንድና አንዲት ሴት ልጅ አፍርተዋል፡፡
አቶ አዲስ ገሰሰ ባደረባቸው ህመም በህክምና ሲረዱ ቆይተው ፤ በአሜሪካ ሀገር ኒውጄርሲ ሰኔ 9 ቀን 2018 ዓ.ም. ከዚህ ዓለም ድካም አርፈዋል፡፡
የቀብር ሥነ ስርዓቱ ዛሬ፣ ሰኔ 20 ቀን 2018ዓ.ም በ6:00 ሰዓት በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ተፈጽሟል።
አቶ አዲስ ገሰሰን ከአጠገቡ ሳትለዩ ላስታመማችሁትና ለጠየቃችሁት ወዳጅ ዘመዶች ልዑል እግዚአብሔር ብድራችሁን ይከፈላችሁ፡፡
የአቶ አዲስ ገሰሰን ነፍስ ልዑል እግዚአብሔር በአፀደ ገነት ከደጋጎቹ አብርሃም ይስሐቅ እና ያቆብ ጎን ያሳርፍልን፡፡
ለቤተሰቡ፤ ለወዳጆቹ፤ ለዘመዶቹ፤ ለሙያ አጋሮቹ፤ ለአድናቂዎቹ ሁሉ መፅናናቱን ይስጣቸው፡፡

አገር አቀፍ ፈተና እና የሴቶች #የወርአበባ ንፅህና መጠበቂያ
በወር አበባ ምክንያት #ሴት ተማሪ መሸማቀቅ የለባትም!
#ethiopia | እንደሚታወቀው የሰኔ ወር የ 6ኛ; የ 8 ኛ እና የ 12 ኛ ክፍሎች የአገር አቀፍ እና ክልላዊ ፈተናዎች የሚሰጥበት ወቅት ነው።
ከሰኔ ወርም ቀደም ተብሎ የመንግስትና የግል ት/ቤቶች እና የትምህርት ሚኒስቴር; ቢሮዎችና ፅ/ቤቶች ተማሪዎች በጥሩ ውጤት ፈተናዎቹን እንዲያልፉ በትጋት ተማሪዎቻቸውን ያዘጋጃሉ።
የፈተና ቁሳቁሶች; ጥያቄዎች; የመፈተኛ ት/ቤቶች; ፈታኝ መምህራን እና ሌሎችንም ቀድመው ለማዘጋጀት የሚደረገው ርብርብ የሚደነቅ ነው። ለወላጆችም/ለቤተሰቦችም ልጆቻችንን ለፈተናዎቹ በአግባቡ እንድናዘጋጅ ተደጋጋሚ መልእክቶችና ማስጠንቀቂያዎች ይላኩልናል።
በተለይ ፈተናዎቹ ቀናቸው እየቀረበ ሲመጣ ተማሪዎች ለፈተና ሲመጡ ይዘው መምጣት ያለባቸው እና ይዘው ለመምጣት የሚከለከሉ ቁሳቁሶች ለተማሪዎቹም ተደጋግሞ ይነገራቸዋል ለእኛም ለወላጆች/ቤተሰቦች ማስጠንቀቂያ ይላክልናል።
ተማሪዎቹ በፈተና ቦታው ይዘው መምጣት የሚፈቀድላቸው :-
1)እርሳስ ; ላጲስ; መቅረጫ
2)የት/ቤት መታወቂያ እና admission card #ብቻ ነው።
አንድ ትልቅ ነገር ግን ተረስቷል #ሞዴስ !
እንደ አገር ትልቅ ዝግጅት የምናደርግለት አገር አቀፍ ፈተና ላይ ሴት ተማሪዎች በፈተና ወቅት #የወር አበባ ላይ ከሆኑ የንፅህና መጠበቂያ #ሞዴስ እንደሚያስፈልጋቸው መዘንጋት ማለት የፈተናው ዝግጅት; ሂደት እና አፈፃፀም #በስርአተ -ፆታ እይታ እንዳልተቃኘ ማሳያ ነው።
እንኳን ፈተና ተጨምሮበት ይቅርና ወር አበባ ሴት ታዳጊዎች ላይ ከባድ የአካል #ህመም ; #የሆርሞን መዛባት እና #የስነልቦና ጫና ያሳድርባቸዋል።
ስለዚህ የወር አበባ + ፈተና የትምህርት ዘርፉ እና ት/ቤቶች ለሴት ተማሪዎች የተለየ ትኩረት እንዲሰጡ ግድ የሚላቸው ጉዳይ ነው።
ፈተና እየተፈተኑ ድንገት የወር አበባቸው የሚመጣባቸው እና የወር አበባ የሚበዛባቸው /heavy flow period / ሴት ተማሪዎች ቶሎ #ምዴስ መቀየር ወይም መጠቀም ሰላለባቸው በፈተና ወቅት ሞዴስ ይዘው እንዲገቡ ባልተፈቀደበት ሁኔታ ሴት ተማሪዎቹ ከአሁን አሁን ልብሴ ተበላሸ ብለው #ሲሳቀቁ ለፈተናው የሚሰጡት #ትኩረት ይጎዳል ።በዚህም የተነሳ ውጤታቸው ላይ #አሉታዊ ተፅእኖ ያመጣል።
ታዲያ የፈተናው ጣቢያዎች ለሴት ተማሪዎች በመፈተኛ ክፍሎች ውስጥ የድንገተኛ ግዜ #ሞዴስ /emergency sanitary pad / ሊያስቀምጡ ይገባል። አለበለዚያ ፈተናው ለሴት ተማሪዎች #ኢፍትሀዊ ይሆናል።
አንዲትም #ሴት ተማሪ #በተፈጥሮ ምክንያት #ከወንድ ተማሪዎች ወደኋላ መቅረት የለባትም!
የህግ ባለሙያ ሜሮን አራጋው

Sponsored by
Surafel
2 months ago
የሀዘን መግለጫ
#ethiopia | ዓለም አቀፍ እውቅናን የነበረቻው እውቁ የሙዚቃ ማናጀር አቶ አዲሱ ገሰሰ ባደረባቸው ህመም በአሜሪካ ሀገር በህክምና ሲረዱ ቆይተው በ73 ዓመታቸው ሰኔ 09 ቀን 2018 ዓ.ም. ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል፡፡
በሙዚቃ ኢንዱስትሪው "የነፍስ አባት" (Godfather) በመባል የሚታወቁት አቶ አዲሱ ገሰሰ የህይወት ፔንዱለም ወደ ሙዚቃ ማናጀርነት ከማዞሯ በፊት በዲሲፕሊን አንፆኛል በሚሉት ዝነኛው የኢትዮጵያ አየር ኃይል በግራንድ ቴክኒሳንነት ለአንድ አመት እንዳገለገሉ የትምህርት እድል በማግኘታቸው ወደ አሜሪካ ሺካጎ በማቅናት ራንቱል ኤርፎርስ ቤዝ እና ቴክሳስ ላክላንድ ኤርፎርስ ቤዝ ትምህርታቸውን ተከታትለው ተመርቀዋል፡፡
በመቀጠልም ሃሮልድ ዋሺንግተን ዩኒቨርሲቲ በዛን ስያሜው ሉፕ ኮሌጅ በሚባለው ሜካኒካል ኢንጅነሪንግ ትምህርታቸውን ተከታትለዋል፡፡ ኖርዝ ኢስተርን ኢሊኖይስ ዩኒቨርሲቲ በማኔጅመንት ትምህርታቸውን አጠናቀዋል፡፡
አቶ አዲሱ ገሰሰ ይማሩበት በነበረው ኖርዝ ኢስተርን ኢሊኖይስ ዩኒቨርሲቲ የጥቁር ታሪክ ወር /Black History Month/ ተብሎ በየዓመቱ የካቲት ወር ላይ በተለያየ መዘክር ወንሞቻቸው ዘለቀ ገሰሰ፤ ሙሉጌታ ገሰሰ፤ እና ጓደኞቻቸውን እነ መላኩ ረታ በዳሎል ባንድ ሙዚቃ እንዲያቀርቡ በማስቻል የማናጅመንቱን ስራ በመስራት የሙዚቃ ህይወት ጉዟቸውን ሀ ብለው ጀመሩ፡፡
በዋሺንግተን፤ በሎስ አንጀለስ በአሜሪካ መድር በኢትዮጵያን ለኢትዪጵያን የመጀመሪያውን የሙዚቃ መድረክ በዳሎል ባንድ ውጤታማ ስራ መስራት ችለዋል፡፡
አቶ አዲሱ ገሰሰ የማርሌን ቤተሰብ ከነሃብት ንብረቱ በሚያስተዳድሩበት ጊዜ ዘመን አይሽሬውን ኤክሶደስ ሌጀንድ አልበም ከአይስ ላንድ ሪከርዲንግ ጋር እነዲሰራ ማድረግ የቻሉ ሲሆን አቶ አዲሱ ገሰሰ በማርሌ ቤተሰቦች በሚዘጋጀው አለም አቀፍ የሬጌ ሙዚቃ መድረክ ከምድር ዳር እስከ ምድር ዳር ድረስ ለተደረጉት የሙዚቃ መድረኮች የሙዚቃ ጉዞ ሃሳቡን ከመጠንሰስ ጀምሮ ከሁለት አስር ዐመታት በላይ ስራውን በማኔጅመንትነት በመምራት እና በማስተዳደር የዘረጉት መንገድ እስካሁን ድረስ በየዓመቱ የሚደረግን ዓለም አቀፍ የሬጌ ሙዚቃ ፌስቲቫል የማይናወፅ የማእዘን ድንጋይ ተክለዋል፡፡
በየሀገሩ እና ሙዚቃ በተደረገበት መድረክ ሁሉ አቶ አዲስ ፕሮግራሙን የሚያስጀምሩት አባታችን ሆይ በሚለው ቡራኬና ፀሎት በመሆኑ ፌስቲቫሉን የተለየ ድባብ መፍጠራቸውም የሚዘነጋ አይደለም፡፡
አቶ አዲሱ ገሰሰ ዚጊን ከጃማይካ የነዘለቀን ዳሎል ባንድ ከሺካጎ ወደኒዮርክ በማምጣት ካጣመሩ በኋላ ከሲግማ ስቱዲዮ ጋር፤ እና ከቨርጂኒያ ሪከርድስ ጋር ውል በማድረግ በአሜሪካ ምድር ቁጥር አንድ አልበም የሆነውን ኮንሺየስ ፓርቲ ማኔጅ በማድረግ ዚጊ ማርሌ የሜሪካንን ትልቁን ግራሚ አዋርድ ሽልማት ሲያገኝ፤ የኢትዮጵያ ዳሎል ባንድ ደግሞ ለመጀመሪያ ጊዜ እንደ ባንድ የግራሚ ሽልማቱን እንዲወስዱ በማስቻል ታሪክ የማይረሳው ስራ ሰርተው አልፈዋል፡፡
ለሀገራቸው ኢትዮጵያ የተለየ ፍቅር የነበራቸው አቶ አዲሱ ገሰሰ ከወንድማቸው አርቲስት ዘለቀ ገሰሰ ጋር በመሆን የቦብ ማርሊ 60 ዓመት የልደት በዓሉን ምክንያት በማድረግ የሚዘጋጀውን ዓለም አቀፍ የሙዚቃ ዝግጅት ኢትዮጵያን መዳረሻ በማድረግ አንድ አመት የፈጀ የዘመቻ /ካምፔይን/ በመስራት በ1997 ዓ.ም. መስቀል አደባባይ የተካሄደውን የሙዚቃ ፌስቲቫል ስኬታማ እንዲሆን በማስቻል መልካም አጋጣሚ በመፍጠር፤ ሀገራችንን በዓለም ዙሪያ ለማስተዋወቅ፤ የቱሪስት መዳረሻ ለማድረግ፤ እና ኢንቨስመንት ለመሳብ በማለም ዓለም አቀፍ የሆኑ ከ50 በላይ ሚዲያዎችን በመጋብዝ ድርሻቸውን ተወጥተዋል፡፡
አቶ አዲሱ ገሰሰ በሙዚቃ ማኔጅመንት የሕይወት ጉዟቸው ያካበቱትን እውቀትና ልምድ በመላ ተጠቅመው ተሰጥዎ ያላቸውን ልጆች በመቃኘት ሀገራቸውን በሙዚቃው ኢንደስትሪ ዓለም አቀፍ ተወዳዳዳሪ ለማድረግ ትልቅ ህልም ነበራቸው፡፡ በዚህም እጅጋየው ሽባባውን /ጂጂ/ ከአጋራቸው ፓልም ሪከርዲንግ ጋር በመሆን ተወዳጅ የሆነ አልበሟን እንድተሰራ ያደረጉ ሲሆን፤ ቴዎድሮስ ካሳሁን /ቴዲ አፍሮ/ በሚሰራው ሙዚቃም ማኔጅምቱን በመያዝ ያበረከቱት አስተዋፅኦ የሚጠቀስ ነው፡፡
ይሄም ብቻ ሳይሆን ጃኖ ባንድን በመመስረት እና ለፍሬ እንዲበቁ የአቶ አዲስ ገሰሰ ድጋፍ የአንበሳውን ድርሻ የሚይዝ ተግባር ነበር፡፡ አቶ አዲስ ጃናናይት የተባለ ተሰጥዎ ያላቸውን ሴቶች የያዘም ባንድ መስርተው ለመጓዝ ያደረጉትንም ጥረት የሚወሳ ነው፡፡ በሙዚቃ ኢንዱስትሪው "የነፍስ አባት" (Godfather) በመባል የሚታወቁ አቶ አዲሱ ገሰሰ ከሀገራችን ውጪ እንደ ዚጊ ማርሌ፤ ስቴፈን ማርሌ፤ ሎሪን ሂል፣ ፊል ኮሊንስ፣ አርዝ ዊንድ ኤንድ ፋየር (Earth, Wind, & Fire) እና ሌሎችንም በርካታ የሙዚቃ ከዋክብትን በማግኘትና በማስተዳደር በዓለም አቀፍ ደረጃ የብዙዎችን የሙዚቃ ስራ መስመር አሲዘዋል።
አቶ አዲሱ ገሰሰ በሙዚቃ ማኔጅመንት ስራቸው ብቻ ሳይሆን በበጎ ስራ ተግባራቸው የተወደደ አርአያነት ያለው ተግባር ፈፅመዋል፡፡ ከነዚህም መሃከል በግል ከደገፏቸው ግለሰቦች በተጨማሪ በሀገራችን በተለያያ ጊዜ የተፈጠሩ ሰብአዊ ችግሮችን ለመድረስ ያደረጉት አስተዋፅኦ የሚጠቀስ ሲሆን በዋናነት ከወንድማቸው ዘለቀ ገሰሰ ጋር በመሆን በተለያዩ ገጠረማ አካባቢዎች 30 ትምህርት ቤቶችን በማሰራት ያደረጉት በጎ ተግባር በታሪክ የሚወሳ አርአያነት ያለው ተግባር ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
አቶ አዲሱ ገሰሰ መደበኛ መኖሪያቸውን ወደ ኢትዮጵያ ካዞሩ በኋላ በሆቴሊንግ ዘርፍ በመሰማራት ላየንስ ዴን ሆቴልን፤ በማእድን ዘርፍ ዩኒቨርሳል ማይኒንግን፤ በግብርና መስክ አድሶጌት ኩባንያን በማቋቋም የራሳቸውን ጡብ ለማስቀመጥ ቀን ከሌት ያለእረፍት ጥረዋል፡፡
አቶ አዲሱ ገሰሰ በማህበራዊ ህይወታቸው ቀልድ አዋቂ፤ ተጫዋች እና በቀላሉ ከሰዎች ጋር ተግባብተው የመኖር ፀጋ የነበራቸው ሲሆን ከሁሉም ግን ሰው አካባሪ እና ስነ ምግባር ያለው ቀረቤታቸው ተወዳጅ እና በሰው ልብ አይረሴ አድርጓቸዋል፡፡
አቶ አዲሱ ገሰሰ ከወ/ሮ ሶስና ሽፈራው ጋር በነበረው የፀና ትዳር አንድ ወንድ እና አንድ ሴት ለማፍራት ችለዋል፡፡
የአቶ አዲሱ ገሰሰ የአስክሪን ሽኝትና ስርዓተ ቀብር አፈጻጸም ስንነስርዓት በቅርቡ እናሳውቃለን ፡፡

3 months ago
ከቤተ-መንግሥት ወደ ስብከት መድረክ
የአቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ የሽግግር እንቆቅልሽ
የአንድ አገር መሪ ከስልጣን ሲወርድ የሚመርጠው መንገድ የራሱን የነበረውን ማንነት የወደፊት እጣ ፈንታውን እና የህዝቡን የታሪክ ትውስታ ይወሰናል። በኢትዮጵያ የቅርብ ጊዜ የፖለቲካ ታሪክ ውስጥ አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ የስልጣን መልቀቂያ በማስገባት የመጀመሪያው መሪ በመሆን ታሪክ ሰርተዋል።
ያ ውሳኔ በወቅቱ ለነበረው ህዝባዊ አመፅና ውጥረት የተወሰነ መተንፈሻ የሰጠ በጎ እርምጃ ተደርጎ ቢወሰድም ከስልጣን በኋላ የመረጡት የሕይወት መስመር ግን በብዙዎች ዘንድ ጥያቄና ትዝብትን እያስከተለ ይገኛል።
በተለይም በቅርብ ጊዜያት በመድረኮች ላይ እንደ ወንጌል ሰባኪና የሃይማኖት መምህር ሆነው መታየታቸው ፖለቲካው በፈጠረው ቁስል ላይ የወንጌል ፈውስ ወይስ የታሪክ ሽሽት? የሚል ጠንከር ያለ ክርክር አስነስቷል።
አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ አገሪቱን በጠቅላይ ሚኒስትርነት የመሩባቸው ዓመታት (ከ2005 እስከ 2010 ዓ.ም) በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ከፍተኛ ህዝባዊ ተቃውሞ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች የዜጎች መፈናቀልና የብዙ ወጣቶች ህይወት የጠፋባቸው ከባድ ዓመታት ነበሩ። ምንም እንኳን ውሳኔዎች በጋራና በፓርቲ (ኢህአዴግ) መዋቅር ይሰጡ የነበረ ቢሆንም እርሳቸው የአገሪቱ የመጨረሻው የሥልጣን ማማና የጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ እንደመሆናቸው መጠን በዚያ ዘመን ለደረሰው መከራና የደም መፋሰስ ቀጥተኛ የታሪክና የሞራል ተጠያቂነት አለባቸው።
ህዝብ በበደልና በደምና በደመ ነፍስ የታለፉ ቁስሎችን በቀላሉ አይረሳም። በጥይት የተመቱ ወጣቶች፣ የታሰሩ ጋዜጠኞችና ፖለቲከኞች፣ የተፈናቀሉ ማህበረሰቦች ትውስታ ዛሬም ትኩስ ነው። ስለሆነም ያንን ሁሉ መከራ ያስተናገደ ህዝብ በወቅቱ የነበረው መሪ በአንዴ መጽሐፍ ቅዱስ ይዞ በመድረክ ላይ ሲሰብክ ሲያይ መገረሙ መጠራጠሩና መቆጣቱ ሰብአዊና አመክንዮአዊ ምላሽ ነው።
በክርስትና እምነት (በተለይም አቶ ኃይለማርያም በሚከተሉት የሃዋርያት እምነት መሠረት) ማንኛውም ሰው በማንኛውም ጊዜ ንስሐ ገብቶ ወደ እግዚአብሔር የመመለስና የማገልገል መብት አለው። ይሁን እንጂ የወንጌል መሠረታዊ አስተምህሮ ከእግዚአብሔር ጋር መታረቅን ብቻ ሳይሆን ከበደሉት ሰውና ማህበረሰብ ጋር መታረቅንም ይጨምራል።
"እንግዲህ መባህን በመሠዊያው ላይ ብታቀርብ፥ በዚያም ወንድምህ አንዳች በአንተ ላይ እንዳለው ብታስብ በዚያ በመሠዊያው ፊት መባህን ትተህ ሂድ አስቀድመህም ከወንድምህ ጋር ታረቅ ከዚያም መጥተህ መባህን አቅርብ።" (ማቴዎስ 5:23-24)
የአቶ ኃይለማርያም ወደ ወንጌል አገልግሎት መግባት ትልቅ ጥያቄ የሚነሳበት እዚህ ጋ ነው። በመሪነታቸው ዘመን ለተፈጠሩት ስህተቶች፣ ለጠፋው ሕይወትና ለፈሰሰው ደም የኢትዮጵያን ህዝብ በይፋ፣ በግልጽና በስም ጠርተው ይቅርታ ጠይቀዋል ወይ? ጥፋቱን አምኖ ንስሐ መግባት፣ የተበደሉትን መካስና ይቅርታ መለመን የወንጌል ስብከት መነሻ እንጂ መድረሻ ሊሆን አይገባም ነበር?
እነዚህ ጥያቄዎች ሳይመለሱ በቀጥታ ወደ መድረክ ወጥቶ መስበክ ለብዙዎች ታሪኬ ተረስቶልኛል ከሚል ግምት ወይም የህዝብን ቁስል ካለማክበር የመነጨ ሊያስመስለው ይችላል።
በሌላ በኩል የአቶ ኃይለማርያምን ወገን የሚከላከሉ ሰዎች እርሳቸውም ቢሆኑ የራሳቸው የህሊና ጉዞ እንዳላቸው ይከራከራሉ። ስልጣን በገዛ ፈቃድ መልቀቅ ራሱ በአገሪቱ ፖለቲካ ውስጥ ትልቅ የመጸጸትና ለውጥ የመሻት መግለጫ እንደነበር የሃይማኖት አገልግሎታቸውም የዚሁ የውስጥ ለውጥና ሰላምን የመፈለግ ጉዞ አካል ሊሆን እንደሚችል ይገምታሉ።
በተጨማሪምከፖለቲካው ዓለም ሙሉ በሙሉ ርቀው በግል ሕይወታቸውና እምነታቸው ላይ ማተኮራቸው መብታቸው እንደሆነ ይነገራል።
ነገር ግን ግለሰቡ ተራ ዜጋ ሳይሆኑ የአገር መሪ ነበሩ።
የአገር መሪ የህዝብ ሃብት ነው ታሪኩም፣ ውሳኔውም፣ ከስልጣን በኋላ የሚያደርገው እንቅስቃሴም ሁሉ በህዝብ መነጽር መቃኘቱ አይቀሬ ነው።
የአቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ የወንጌል ሰባኪነት ጉዞ በኢትዮጵያ ህዝብ ዘንድ አሁንም የተደበላለቀ ስሜት ይፈጥራል። በአንድ በኩል የሰው ልጅ መለወጥና ወደ እምነቱ መመለስ የሚደገፍ ቢሆንም በሌላ በኩል ግን ያለ ይፋዊ ይቅርታና የፖለቲካ ተጠያቂነት ወደ መንፈሳዊ መድረክ መሻገር የህዝብን ቁስል የሚነካ ሆኖ ተገኝቷል።
እውነተኛ የወንጌል አገልግሎት የሚጀምረው ከእውነትና ከፍትህ ነው። አቶ ኃይለማርያም ካለፈው ታሪካቸው ጋር በግልጽ ተጋፍጠው ለደረሰው ጥፋት የድርሻቸውን ሃላፊነት ወስደው ለኢትዮጵያ ህዝብ ይቅርታን እስካላወረዱ ድረስ ስብከታቸው ምንም ያህል ጥራዝ ቢኖረው በብዙሃኑ ዘንድ ካለፈው ታሪክ የመሸሻ ጥላ ተደርጎ መታሰቡ አይቀሬ ነው።
ታሪክ አይረሳም የህዝብ እምባም ዝም ብሎ አይታለፍም።
Via Henock Megerssa

ተቆጣሽኝ በሚል ምክንያት አክስቱን የገደለው ግለሰብ የሞት ቅጣት ውሳኔ ተላለፈበት።
***
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 19 ቀን 2018 ዓ/ም (አዲስ ፖሊስ)፦ በለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 6 ክልል ልዩ ቦታው ኢካ ሳይት ብሎክ 705 የቤት ቁጥር 59 ውስጥ መስከረም 27 ቀን 2017 ዓ/ም ከምሽቱ 4 ሠዓት ነው ወንጀሉ የተፈፀመው።
በአካባቢው ላይ የሟች ማንነት የማይታወቅና የተወሰነ የሰው ቅሪት አካል በመገኘቱ ከአካባቢው ነዋሪዎች ለፖሊስ ጥቆማ ይደርሳል። ፖሊስም የደረሰውን ጥቆማ መነሻ በማድረግ የሟችን ማንነት ለመለየት እና የወንጀል ፈፃሚውን ማንነት ለመለየት በተደረገው ጥረት በሠዓታት ውስጥ ሟችን መለየት እና በወንጀሉ የተጠረጠረውን ግለሰብ በቁጥጥር ስር ሊያውል መቻሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ የወንጀልና ትራፊክ አደጋ ምርመራ ም/ጠቅላይ መምሪያ ገልጿል።
ፖሊስም በተከሳሽ ሻምበል ሙሉጌታ ላይ በተደረገ ምርመራ ሟች ወርቅነሽ ኃይሌ የተባለችው የ36 ዓመት ጎልማሳ ስትሆን በጉምሩክ አስተላላፊነት የስራ መስክ ላይ እየሰራት የነበረች ስትሆን በተገለፀው አካባቢ መኖር ከጀመረች 4 ወራትን አስቆጥራለች።
ሐምሌ 20 ቀን 2016 ዓ/ም የወንድሟ ልጅ የሆነውን ተከሳሽ ሻምበል ሙሉጌታ እሷ ጋር ተቀምጦ የቀን ስራ ለመስራት ከክፍለ ሀገር መምጣቱንና አብረው መኖር መጀመራቸውን ከአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ የሰው መግደል ወንጀል ምርመራ መምሪያ ለማወቅ ችሏል።
መስከረም 27 ቀን 2017 ዓ/ም ከምሸቱ 12 ሰአት አካባቢ ስራ ውላ ወደ ቤቷ ገብታ ከወንድሟ ልጅ ጋር እራት በልተው አመሻሹ ላይ በተፈጠረ አለመግባባት ተቆጣችኝ በሚል ሰበብ አንገቷን በማነቅ መሬት ላይ በመጣል ህይወቷ እንዲያልፍ ካደረገ በኋላ በሽንኩርት መክተፊያ ቢላዋ የተለያዩ የሰውነት ክፍሏን በመቆራረጥና በመለያየት በሦስት ፊስታል ነጣጥሎ በማሰር ጨለማን ተገን በማድረግና ማንም እንደማያየው በማረጋገጡ አንዱን ፌስታል መፀዳጃ ቤት ሁለተኛውን ደግሞ ለግንባታ የተቆፈረ ቦታ ላይ በመጣል አፈር በማልበስና ሦስተኛውን ፌስታል ግንብ ስር ሊጥልም ችሏል፡፡
ፖሊስ የተለያዩ ማስረጃዎችን በመሰብሰብ ወንጀሉን ፈፅሟል ተብሎ የተጠረጠረውን ግለሰብ በመያዝ ቅሪተ አካሎችን የጣለበት ቦታ መርቶ እንዲያሳይ አድርጓል፡፡
የማችን አስክሬን በመሠብሰብ ለቤተሰብ በመስጠት በተከሳሹ ላይ የምርመራ ስራውን በሰው እና በሰነድ ማስረጃ ያጠናቀቀው ፖሊስ የተጠናቀቀውን የምርመራ መዝገብ ለዐ/ህግ በማቅረብና ክስ በማስመስረት የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ሁለተኛ ወንጀል ችሎት ተከሳሽ ሻምበል ሙሉጌታን ጥፋተኛ ሆኖ በማግኘቱ የሞት ፍርድ ውሳኔ ወስኖበታል፡፡
*
ዘገባ፦ ኢንስፔክተር እመቤት ኃብታሙ
seledadotio

በለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 6 ክልል ልዩ ቦታው ኢካ ሳይት ብሎክ 705 የቤት ቁጥር 59 ውስጥ መስከረም 27 ቀን 2017 ዓ/ም ከምሽቱ 4 ሠዓት ነው ወንጀሉ የተፈፀመው።

Addis Ababa police

ተቆጣሽኝ በሚል አክስቱን የገደለው ግለሰብ የሞት ቅጣት ውሳኔ ተላለፈበት።
#fastmereja I በለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 6 ክልል ልዩ ቦታው ኢካ ሳይት ብሎክ 705 የቤት ቁጥር 59 ውስጥ መስከረም 27 ቀን 2017 ዓ/ም ከምሽቱ 4 ሠዓት ነው ወንጀሉ የተፈፀመው።

Via: አዲሰ አበባ ፖሊስ

4 months ago
ፓኪስታን በኢራን ጦርነት ዙሪያ የሳዑዲ፣ የቱርክ እና የግብፅ ከፍተኛ ዲፕሎማቶችን ለስብሰባ ጠርታለች
የፓኪስታን መንግስት በአሜሪካ እና በኢራን መካከል እንደ አስታራቂ ሆኖ እየሰራ ሲሆን፤ በኢስላማባድ ውይይቶች እየተካሄዱ ነው።
ከሳዑዲ አረቢያ፣ ከግብፅ እና ከቱርክ የተውጣጡ ከፍተኛ ዲፕሎማቶች በኢራን ላይ እየተካሄደ ባለው የአሜሪካ-እስራኤል ጦርነት ዙሪያ ለመወያየት እና ግጭቱን ለማርገብ ከፓኪስታን አቻቸው ጋር ለሁለት ቀናት ለሚቆይ ውይይት በኢስላማባድ ተሰባስበዋል።
የፓኪስታን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኢሻቅ ዳር ፤ኢራን በፓኪስታን ሰንደቅ ዓላማ የሚጓዙ "ተጨማሪ 20 መርከቦች" ወይም በቀን ሁለት መርከቦች በሆርሙዝ የባህር ወሽመጥ በኩል እንዲያልፉ መፍቀዷን አስታውቀዋል።
የፓኪስታን ጠቅላይ ሚኒስትር ሸህባዝ ሻሪፍ እንደተናገሩት፤ ለኢስላማባዱ ውይይት እንደ ዝግጅት አካል "ከወንድሜ ከኢራኑ ፕሬዝዳንት መሱድ ፔዜሽኪያን ጋር ከአንድ ሰዓት በላይ የቆየ ዝርዝር የስልክ ውይይት አድርጌያለሁ" ብለዋል።
በኢስላማባድ የተካሄደው ስብሰባ ብዙዎች እንደሚሉት ብቸኛው አዋጭ አማራጭ የሆነውን ዲፕሎማሲ እና ውይይትን ያካተተ የወሳኝ ሂደት ጅምር መሆኑንም አልጀዚራ በዘገባዉ አመላክቷል፡፡
እንደ ፕሬዝዳንቱ ጽሕፈት ቤት ገለጻ፤ ፔዜሽኪያን የኢስላማባድን ጥረት ያደነቁ ሲሆን፤ በኢራን ላይ የሚሰነዘረውን ጥቃት ለማስቆም ፓኪስታን ለምታደርገው የማስታረቅ ጥረት አመስግነዋል።
ሁለቱ መሪዎች ባለፉት ሳምንታት ስለ ግጭቱ እና ፓኪስታን ግጭቱን ለማቆም ስላላት ቁርጠኝነት ቀደም ብለው ተነጋግረው ነበር።
ኢስላማባድ ከቴህራን ጋር የቆየ ግንኙነት እና በባህረ ሰላጤው አገራት ዘንድ የቅርብ ትስስር ያላት ሲሆን፤ ሻሪፍ እና የጦር ኃይሉ ጠቅላይ አዛዥ ፊልድ ማርሻል አሲም ሙኒር ከአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጋር የግል መቀራረብ ፈጥረዋል።
አልጀዚራ እንደዘገበዉ፤ ፓኪስታን በአሜሪካ እና በኢራን መካከል እንደ "ዋነኛ መልዕክት አቀባይ" በመሆን በማስታረቅ ጥረቱ ውስጥ በሁለቱ ወገኖች መካከል መልዕክቶችን በማስተላለፍ ላይ ትገኛለች።
እስከዳር ግርማ

5 months ago
ወንዶች የፍቅር አጋራቸውን ግፋ ቢል ስንት ደቂቃ በትኩረት ያዳምጧቸዋል ?
በብሪታንያ የሚገኘው ላድብሮክስ የተባለ ተቋም በ2,000 ሰዎች ላይ ባደረገው ጥናት፣ ወንዶች ለማዳመጥ ያላቸውን አቅም የሚመለከቱ አስገራሚ ውጤቶችን ይፋ አድርጎ ነበር።
በጥናቱ መሰረት፣ ወንዶች ለሚስቶቻቸው ወይም ለፍቅረኞቻቸው ቢበዛ ለ6 ደቂቃ ብቻ ነው በትኩረት ማዳመጥ የሚችሉት፤ ከዚያ በኋላ ግን ሃሳባቸው ይበታተናል።
በአንጻሩ ስለ ስፖርት፣ ስለ መኪና ወይም ስለ ግላዊ ጉዳዮች ከወንድ ጓደኞቻቸው ጋር ሲያወሩ እስከ 15 ደቂቃ ድረስ ሙሉ ትኩረታቸውን ሰጥተው ማዳመጥ እንደሚችሉ ተገልጿል።
በተለይ በወሬው መሃል ስለማያውቋቸው ሰዎች፣ ስለ ልብስ ወይም ስለ ታዋቂ ሰዎች የሚነሳ ከሆነ የወንዶች ትኩረት በፍጥነት እንደሚቀንስ ጥናቱ አመልክቷል።
ምንጭ፦ በላድብሮክስ የተደረገ ጥናት

ሴት ምሁራን ወደ አመራርነት እየመጡ አይደለም ተባለ!
#fastmereja I በኢትዮጵያ በከፍተኛ ትምህርት ተቋም ውስጥ የሚገኙ ሴት ምሁራን ከወንድ አጋሮቻቸው እኩል ጥሩ የአካዳሚክ ውጤት አስመዝግበው ቢገኙም የከፍተኛ የአመራር ቦታዎች ላይ እንደማይታዩ አንድ ጥናት አመለከተ።
የኢትዮጵያ የሴቶች መብት ተሟጋች ባዘጋጀው የፓናል ውይይት ላይ ከጉዳዩ ጋር ቀጥታ ተያያዥነት ያላቸው ባለሙያዎች ምክረ ሀሣብ አቅርበዋል።
ዛሬ መጋቢት 3 ቀን 2018 ዓ.ም በፕላቲኒየም ሆቴል በተካሄደ በዚህ የፓናል ውይይት እንደተመለከተው ሴቶች በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ውስጥ ተሳትፎ ቢኖራቸውም በውሳኔ ሰጭነት ቦታ ላይ ቁጥራቸው አነስተኛ ሆኖ ተገኝቷል።
በዕለቱ የጥናት ወረቀቱን ያቀረቡት ዶክተር ገነት ዘውዴ የቀድሞ ትምህርት ሚኒስትር ሲሆኑ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስና ዓለምአቀፍ ግንኙነት ተባባሪ ፕሮፌሰር ዶክተር ፍሬህይወት ስንታየሁ ደግሞ ልምድና ተሞክሯቸውን አካፍለዋል።
እንደ አቅራቢዎቹ መረጃ በተለየ መልኩ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የተካሄደው ጥናት እንደሚያሳየው በአመራር ደረጃ የሚገኙ ሴቶች ቁጥር አነስተኛ ነው።በአንድ በኩል ሴቶች ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋም እንዲገቡ ቢደረግም ባህላዊ እይታ ነግሶ በመቆየቱና ወንዶች ብቻ በመሪነት ስለሚታዩ አቅሙ እና የአመራር ክህሎትን ያዳበሩ ሴቶች ወደ ዩኒቨርስቲው አመራር ሲመጡ አይታይም ሲል ጥናቱ ድምዳሜ ያቀርባል።
ዶክተር ገነት ዘውዴ አኃዞችን በማቅረብ ሴት የዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንቶች በቁጥር 3 መሆናቸውን ጠቅሰው በአገራችን የሚነገሩ ተረትና ምሣሌዎችም የሴትን አለመቻል የሚያንፀባርቁ ስለሆነ ተፅዕኖው ቀላል እንደማይሆን አመልክተዋል።
በተጨማሪም በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የ75 አመት ታሪክ ውስጥ ሴት ፕሬዚዳንት ኖራ እንደማታውቅ ጥናት አቅራቢዋ አምባሳደር ዶክተር ገነት ዘውዴ አመልክተዋል።
ሴት ምሁራን ወደ አመራር ቦታ ቀረብ እንዳይሉ የሚያደርጉ እንቅፋቶች በሦስት ደረጃዎች እንደሚታዩ ጥናቱ ያመለከተ ሲሆን ይህም በማህበራዊ ፣ መዋቅራዊና በግለሰብ ደረጃ ያሉ መሆናቸውን ጠቁሟል።
ከሦስቱ ውስጥ ማህበራዊ እንቅፋቶች ጎልተው የወጡ ሲሆን በተለይ ሴቶች በአስተዳደግም በሚፈጠሩ ተፅዕኖዎች የመሪነት ዕድሎቻቸው እንዳይሰፉ ይደረጋል።አጠቃላይ በማህበረሰቡ ውስጥ ስለ ሴት የመሪነት ሚና ያለው ምልከታ ሴቶች በከፍተኛ የአካዳሚክ አመራር ቦታ ላይ መድረሳቸውን እንደሚገድብ ጥናቱ ላይ ተመልክቷል።
በፓናሉ ላይ የተሳተፉ የፓርላማ አባላት፣የሲቪክ ማህበራት ተወካዮች እና ሴት ምሁራን ሴቶች አቅሙና የትምህርት ዝግጅቱ እስካላቸው ድረስ የዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንትነትን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የአመራር ቦታዎች የማይዙበት ምክንያት የለም፣ ይህን ለማድረግ በመንግሥትም ግልፅ ፓሊሲ ተቀምጦ፣የመተግበሪያ እና የተጠያቂነት አሠራር ተዘርግቶ ለተግባራዊነቱ መሠራት አለበት ሲሉ ሀሣብ ሰንዝረዋል።
የፓናሉ ውይይቱ መክፈቻ ላይ የኢትዮጵያ የሴቶች መብት ተሟጋች ዋና ዳይሬክተር ፌቨን አርአያ እንዳሉት የፓናል ውይይቱ አላማ ሴት ምሁራን በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውስጥ በአመራር ቦታዎች እንዲመጡ ማድረግ ነው።
ሴቶች ወደ አመራር ቦታ እንዳይመጡ ያደረጓቸውንም ተግዳሮቶች ለይቶ በማውጣት የመፍትሔ ሀሣብ መፈለግና ለተግባራዊነቱ ዕውን መሆን ሁላችንም የበኩላችን ማድረግ አለብን ሲሉ ተናግረዋል።
ይህ የፓናል ውይይት እንዲሳካ የገንዘብ ድጋፍ ያደረገው የኢትዮጵያ ሴቶች ማህበራት ቅንጅት መሆኑም ለማወቅ ተችሏል።

መምህር ዛላለም ወንድሙ አሜሪካ ለአገልግሎት ሄደው ነው ያረፉት
በመምህሩ ሞት ዙርያ ፊደል ፖሰት ያገኛቸው ተጨማሪ መረጃዎች;
👉መምህሩ አሜሪካ ዋሸንግተን ዲሲ ለአገልግሎት ሄደው በመሀል አሟቸው ከሶስት ቀን ህመም በኋላ ነው ያረፉት።
👉የመምህሩ አስከሬን በሳምንት ጊዜ ወስጥ ወደ አዲስ አበበ ይመጣል ተብሎ ይጠበቃል።
👉 ቀብራቸው የቤተ ክርስቲያኗ ፓትሪያክ ፣ኤጵስ ቆጶሳት ፣ቀሳውስት ዘማሪዎች እና ምዕመናን በተገኙበት ይከናውናል ተብሎ ይጠበቃል።
👉በግል የንግድ ስራ የሚተዳደሩት ተወዳጁ መምህር አድነው ወንድሙ የተባለ እንደሳቸው ቤተ ክርስቲያንን የሚያገለግል ወንድም አላቸው።
👉መምህሩ ለስብከት አገልግሎት ገንዘብ መቀበል የማይፈልጉ ፣ብዙ ስብከታቸው በስነ ምግባር እና በክርስታናዊ ተጋድሎ ላይ ያተኮረ ነበር።
👉ለአገልግሎት ሲመጡ ለደቂቃ እንኳን ሰአት የማያረፍዱ ፣በሰአት የሚጨርሱ፣ ትምህርታቸው ግልፅ እና አጭር ነበር።
👉ትምርታቸውን በስፋት ለማዳረስ ከወንድማቸው ጋር ዩቲዩብ በመክፈት በርካታ መንፈሳዊ ስብከትና ትምህርቶችን ሰጥተዋል።
👉መምህሩ "ስለ እግዚአብሄር የሚናገር ሳይሆን እንደ እግዜአብሄር ቃል የሚኖር ሰው ነው መሆን ያለብን " በማለት መንፈሳዊ ነገር በተግባር ሊታይ የግድ እንደሚገባ በማስተማር ይታወቁ ነበር።

ቻው የእናቴ ልጅ" - የብዙዎችን ልብ የሰበረው አስደናቂ ስንብት
ዛሬ በሶሻል ሚዲያ አነጋጋሪ የነበረ አንድ ቪዲዮ አለ፤ እሱም እህት ከወንድሟ ስትለይ የሚያሳይ ሲሆን የብዙዎችን ልብ ነክቷል።
ቪዲዮው በእጅጉ የሚያሳዝን እና ደጋግመው የሚያዩት ስሜትን የሚነካ ነው። ዕድሜያቸው የገፋ ወንድም እና እህት ናቸው።
ምን ያክል መነፋፈቅ፣ መከባበርና በስስት የመተያየት መልካም ስብዕና እንደሆነ ያስገርማል
ወንድም ሊጠይቃት ሄዶ ተሰናብቶ ወደ መጣበት ሲመለስ እህት የምታሳየው ፍቅር፣ አክብሮትና መናፈቅ ነው ።
ለመለያየት በእጅጉ ከብዷቸዋል። እህት ታለቅሳለች፣ ወንድ ልጅ ያው ሰው ፊት አያለቅስም ብሎ በልቡ ዞር ብሎ ያለቅሳል። ስሜቱ ግን ፊቱ ላይ ይታያል፡፡
ዛሬ ላይ በርካቶች በተጨካከኑበት እና ከራስ አልፈው ማሰብ ባልቻሉበት በዚህ ዘመን፣ እነኚህ ትልቅ ምሳሌዎች ናቸው::
ሁሉም ጋር ሊኖር የሚገባ መተሳሰብ፣ መዋደድ፣ መከባበር፣ መነፋፈቅ ይህ ነው::
ደም ለደም መሳሳብ፣ ከወንድም እና እህት በላይ የለም!

6 months ago
ሙሓዘ ጥበባት ዳንኤል ክብረት
የኢቢሲ የሥራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ ማንነት?
#ተወዳጅ ሚድያ እና ኮምዩኒኬሽን ፣ መዝገበ-አእምሮ ( የአማርኛ ኢንሳይክሎፒዲያ ) ፕሮጀክቱ ለአገር የሠሩ ሰዎችን ታሪክ እየሰነደ እንደሆነ ይታወቃል። ይህ ታሪክ በዲጂታል ሚድያዎች ፣በመፅሀፍ፣በድምፅ ትረካና በሌሎችም መንገዶች እየቀረበ እንደሆነ ይታወቃል።በተለይ ጉግል ላይ ታሪካቸው ሲፈለግ የማይገኝ ሰዎች አሁን የሙያ አበርክቷቸው በቀላሉ ኢንተርኔት ላይ በግልፅ ተቀምጦ ይገኛልደ ባለፉት 4 ዓመት ከ 5 ወር ጊዜ ውስጥ የ423 ሰዎችን የሕይወትና የሥራ ታሪክ ለመሰነድ የቻልን ሲሆን 600 ገፅ ባላቸው ሁለት የተለያዩ መፅሐፎች ላይም ታሪኮቹ ዘመን ተሻጋሪ ሆነው እንዲቀመጡ አድርገናል።
ከእነዚህ ውስጥ የሚድያ ሰዎችም፣ የቴአትር ባለሙያዎች ይገኙበታል። አጠቃላይ 74 ከፍተኛ የሚድያ አመራሮች፣ሚኒስትሮች ፣ሚኒስትር ዴኤታዎች፣ የግል ሚድያ መሥራቾች፣ዋና አዘጋጆች እና መካከለኛ አመራሮች ተካተዋል። 35 ያህሉ በዋና ሥራ አስፈጻሚ ደረጃ ያሉ ሲሆን የሁሉም ታሪክ በተሟላ ደረጃ ለመሰነድ ተችሏል። የእነዚህን አመራሮች እና የሚድያ ሰዎች ታሪክ ሰንዶ ለአንባቢ ተደራሽ ማድረግ ፈታኝ ቢሆንም አሳክተነዋል። በዚህ ተግባራችንም ተጠናክረን እንቀጥላለን።
በዚህ የስነዳ ሥራ ታሪካቸው መዝገበ አእምሮ ላይ የሚሰነድላቸው ሙሓዘ ጥበባት ዳንኤል ክብረት ይጠቀሳሉ።ሙሓዘ ጥበባት ዳንኤል ክብረት በታሪክና ባህል ዙሪያ በርካታ መፅሐፍትን በመድረስ ትልቅ አሻራ አኑረዋል።ከ30 በላይ መፅሀፍትን የደረሱት እኒህ ሰው የሀይማኖት ሰባኪ፣ ፀሀፊ እና ዲስኩር አቅራቢ በመሆን ለአገራቸው አገልግሎት ሰጥተዋል። የበጎ ሰው የሽልማት ድርጅትን የመሠረቱት ዲያቆን ዳንኤል በአሁኑ ሰዓት የጠቅላይ ሚኒስትሩ የማህበራዊ ዘርፍ አማካሪ ሚኒስትር ናቸው። በዛሬው ዕለት ደግሞ፣ የኢቢሲ የቦርድ ሊቀመንበር በመሆን ተሹመዋል። ዕዝራ እጅጉ እና ሂላሪያ ተስፋዬ የዲያቆን ዳንኤል ክብረትን ታሪክ ሰንደውታል።
#ቅድመ ነገር
በነገረ ሀይማኖት፣ በሥነጽሑፍ፣ በማኅበራዊ ጉዳዮች፣ በጥናትና ምርምሮች ከምልዓት በተጠጋ መሰጠት ያገለገሉ ሰው ናቸው፣ ሙሓዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት።
የተወለዱት ደሴ ከተማ ነው። በወላጅ አባታቸው የንግድ ሥራና እንቅስቃሴ ምክንያት፣ ነፍስ በማያውቁበት እድሜ የመላ ቤተሰቡ ቋሚ መኖሪያ ወደ ባህርዳር ከተማ ተዛወረ። በመሆኑም አብዛኛውን ለሕይወት ስንቅ ሆኖ የቆያቸውን የእውቀት መሠረት ያገኙት በዚሁ በባህርዳር ከተማ ነው።
የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርታቸውን አጼ ሰርጸ ድንግል አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት፣ መለስተኛ ደረጃን በፋሲል መለስተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እንዲሁም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ጣና ሐይቅ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተከታትለዋል። ከዚህ መደበኛ ትምህርታቸው ጎን ለጎን ወላጅ እናታቸው ለትምህርትና ንባብ የሰጡት ትኩረት የንባብ ልምዳቸውን በእጅጉ እንደቃኘው በተለያየ ጊዜ በሰጧቸው ቃለመጠይቆች ደጋግመው ያወሳሉ።
#የሥነጽሑፍ ፍቅር
በልጅነት እድሜ ከዘመናዊ ትምህርት ጎን ለጎን፣ ባደጉበት ፈለገ ገነት ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስትያን ሰንበት ትምህርት ቤት መንፈሳዊ ትምህርትን በሚገባ ቀስመዋል። ይህም አገልግሎታቸው ከፍ ብሎ ቤተክርስትያንን በዲቁና እንዲያገለግሉ የክህነት መዓረግ አስገኝቷቸዋል። ከዚያም ባሻገር ወደ አካባቢው ከሚያቀኑ በእውቀትና በመንፈሳዊ ጽናት የታወቁ አባቶች መምህራን ብዙ ትምህርትን የመቅሰም እድል ነበራቸው፣ ተጠቅመዉበታልም።
ይህ ሁሉ ተዳምሮ በልጅነት እድሜ የተለያዩ ሥነጽሑፋዊ ሥራዎችን እንዲጽፉ፣ አልፎም በትምህርት ቤት በጠዋት የተማሪዎች ሰልፍ ሰዓት መድረክ ላይ ወጥተው እንዲያቀርቡ አስችሏቸዋል። የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ሳሉም በሰልፍ ሰዓት ለተማሪዎች ዜና ያቀርቡ ነበር። በንባብ የተገነባ መሠረት ላይ የተጣለ ማንነታቸውም ለሥነጽሑፍ በተለየ እንዲሳቡ አድርጓቸዋል።
#ከአዲስ አበባ እስከ ኬንያ
ከባህር ዳር አዲስ አበባ ያቀኑት በ1982 ዓ.ም ነው። አዲስ አበባ እንደገቡም ኮተቤ መምህራን ኮሌጅ በኢትዮጵያ ቋንቋዎችና ሥነጽሑፍ በዲፕሎማ ትምህርታቸውን መከታተል ጀመሩ። በዚያም ከመደበኛ ትምህርታቸው ጎን ለጎን በአቅራቢያ በሚገኘው በኮተቤ ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስትያን መንፈሳዊ አገልግሎት ይሰጡ ነበር።
የአንደኛ ዓመት ተማሪ እያሉ ታድያ በፖለቲካ እንቅስቃሴ የተናጠችው ኢትዮጵያ፣ ወጣት ተማሪዎቿ ወደ ብላቴ እንዲሄዱ ተወሰነባት። ዲያቆን ዳንኤልም በዚህ መሠረት ወደብላቴ የውትድርና ማሠልጠኛ ከሄዱ ተማሪዎች መካከል ሆኑ። ይህ ከተለያዩ ኢትዮጵያ አካባቢዎች ወጣቶችን በአንድ እንዲሰባሰቡ እድል የፈጠረው አጋጣሚ፣ ለዳንኤል የተለያዩ ባህሎችን፣ የሀገር መልኮችን እንዲያዩ እድል የፈጠረላቸው ነበር።
የብላቴ ሥልጠና ተጠናቅቆ ምረቃ ሳይደርስ ግን ደርግ ወርዶ ኢሕአዴግ ገባ። በሥልጠናው የተሳተፉ ወጣቶችም አብዛኞቹ ወደ ኬንያ ሄዱ። ዳንኤልም በኬንያ የተወሰኑ ወራት ቆይተው፣ ኢሕአዴግ መንበረ ሥልጣኑን አደላድሎ ከያዘ በኋላ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ። ትምህርታቸውን አቋርጠው የነበሩ ወጣቶች ሁሉ ወደ ትምህርት እንዲመለሱ ተባለና ወደ ትምህርት ገበታቸው ተመለሱ። በአንድ ዓመት ውስጥም የሦስት መንፈቅ ትምህርት ተከታትለው ዲፕሎማቸውን በከፍተኛ ማዕረግ ተቀብለው አጠናቀቁ።
#መምህርነት
ከዚህ በኋላ በተመረቁ ተማሪዎች ምደባ መሠረት ሰሜን ሸዋ ክፍለ ሀገር (በቀድሞ አጠራር) ደረሳቸው። ምንም እንኳ አዲስ አበባ ላይ ሥራ ያገኙና ምደባውን መተው የሚችሉ ቢሆንም፥ “እንዲሁ በነጻ የተማርኹትን ያህልም ቢሆን ማገልገል አለብኝ” በማለት ምድባውን ተቀብለው፣ እንደውም ‘ቢቻል ሰው ሊሄድ የማይመርጥበት ራቅ ያለ ስፍራ መድቡኝ’ አሉ። በጊዜው ግን አሠራሩ በሚፈቅደው መሠረት የደረሳቸው በሰሜን ሸዋ ክፍለ ሀገር ጅሩ ነበርና በዚያ የአማርኛ መምህር ሆነው ማገልገል ጀመሩ።
በዚያም የመምህራን እጥረት ስለነበር፣ ከአማርኛ ባለፈ ታሪክ እና አካባቢ ሳይንስ (ጂኦግራፊ) ያስተምሩ ነበር። ከዚያ ጎን ለጎን መንፈሳዊ አገልግሎቶችን በመስጠትና በማስተማር የአካባቢውን ማኅበረሰብ አገልግለዋል።
የማገልገል ጽኑ ፍላጎት እና ባመኑበት ‘ለብቻም ቢሆን የመቆም’ ጽናት ውስጥ ሆነው፣ የመምህርነት አገልግሎታቸውን ጨርሰው አዲስ አበባ ተመለሱ።
ቀጥለውም ዲፕሎማ በተመረቁበት ኢትዮጵያ ቋንቋዎችና ሥነጽሑፍ ትምህርት ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የመጀመሪያ ዲግሪ ተቀብለዋል። ትምህርታቸውን ከማጠናቀቃቸው በፊትም ሆነ በኋላ፥ በማኅበረ ቅዱሳን በመደበኛ አገልግሎት ሠርተዋል። ሐሳብ አመንጭቶ መጽሐፍ ከመጻፍ በላይ የማሳተምና ማሰራጨት ክብደቱን በመረዳት የመጽሐፍ ህትመት ሥራ ውስጥ የገቡ ሲሆን፣ ለበርካታ ዓመታትም ‘አግዮስ’ የተባለውን የራሳቸውን የመጽሐፍ ማሳተሚያና ማሰራጫ ከፍተው በዘርፉ ሠርተዋል።
ከዚህም ባሻገር የምክር አገልግሎት ይሰጡ የነበረ ሲሆን፣ በኋላም በ2010 ዓ.ም የመጣውን ፖለቲካዊ ለውጥ ተከትሎ፥ የጠቅላይ ሚኒስትር የማኅበራዊ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር ሆነው ተሰይመዋል።
#የመጽሐፍ ሥራዎች
መሓዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ከሠላሳ ሦስት በላይ መጻሕፍትን ለአንባብያን አድርሰዋል። እነዚህም እንደ ‘ብቻዬን እቆማለሁ’፣ ‘ጠጠሮቹ እና ሌሎችም’፣ ‘የሰርቆ አደሮች ስብሰባ’ ከሚሉና ከመሳሰሉ ከተወሰኑ የወግ ስብስብ መጽሐፎች ባለፈ፣ ዳጎስ ያሉ በጥናትና ጥልቅ ንባብ ላይ የተመሠረቱ፣ ሃይማኖታዊ ብሎም ታሪካዊ ይዘት ያላቸው ሥራዎች ናቸው።
ዳንኤል እስከ 2016 ዓ.ም ሲካሄድ የቆየው የበጎ ሰው ሽልማት ድርጅት መሥራች ናቸው። ከዚህም ባሻገር የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃና መምሪያ ማኅበረ ቅዱሳን መሥራቾች መካከል ይገኙበታል። በዚህ ማኅበር ውስጥ የሚታተሙ መጽሔት፣ ጋዜጣና መጻሕፍት ዝግጅት ክፍል ላይም ለበርካታ ዓመታት ሠርተዋል። ስምዓ ጽድቅ ጋዜጣ እና ሐመር መጽሔትም ላይ በርካታ የጽሑፍ ሥራዎቻቸው ይገኛሉ።
የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅትን ጨምሮ በቅርብ በፋና ሚድያ ኮርፖሬት የቦርድ አባል ብሎም ሊቀመንበር ሆነው አገልግለዋል። ቱሪዝምን ጨምሮ በተለያዩ ለሀገር ይጠቅማል ብለው ባመኑበት መስክ እና ተቋም የቦርድ አባልና ሊቀመንበር ሆነዋል፣ ሠርተዋል።
‘የዳንኤል ክብረት ዕይታዎች’ የሚለው መጦመሪያ ድረገጻቸው ላይ የሚያሰፍሯቸው ጽሑፎች ብሎም በተለያዩ መድረኮች በመገኘት የሚያቀርቧቸውና የሚሰጧቸው ማኅበራዊ ኂሶች ብዙ ትኩረት የሚስቡና ተጽእኖ ፈጣሪ ነበሩ፣ ናቸው። በቃል ብቻ ሳይሆን በመጽሐፎችም መንፈሳዊ አገልግሎቶችን ሲሰጡ ቆይተዋል። ለተጨማሪ ጥናትና ምርምር የሚሆኑ የሆኑ ሥራዎቻቸውም ጥቂት አይደሉም።
ብዙ የደከምኩባቸው የሚሏቸው ሁለት መጻሕፍት አሉ። አንደኛው ‘ኢትዮጵያዊው ሱራፊ’ የተሰኘው በአቡነ ተክለሃይማኖት የሕይወት ታሪክ ዙሪያ የሠሩት ሲሆን ሌላው ‘አራቱ ኃያላን’ የተሰኘ መጽሐፍ ነው። በቅርብና መጨረሻ ላይ ለንባብ ካቀረቡት ዳጎስ ያለ መጠን ያለው ‘የትርክት እዳና በረከት’ መጽሐፋቸው በፊትም፣ ‘እጨጌ እንባቆም ከየመን እስከ ደብረሊባኖስ’፣ ‘ራዕየ ዮሐንስ’፣ ‘ከእቴጌ ዕሌኒ እስከ ቅድስት ወለተ ጴጥሮስ’ የተሰኙ የመጽሐፍ ሥራዎቻቸው ከብዙ በጥቂት የሚጠቀሱ ናቸው።
#ቤተሰብ
ሙሓዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት፣ ከትዳር አጋራቸው ወይዘሮ ጽላት ጌታቸው ጋር ላለፉት 22 ዓመታት በትዳር ቆይተዋል። በዚያም ሦስት ወንዶች (አቤሜሌክ ዳንኤል፣ ባሮክ ዳንኤል እና ባህራን ዳንኤል) እና አንዲት ሴት ልጅ (አንኪዮን ዳንኤል) አባት ለመሆን በቅተዋል።
ሙሓዘ ጥበባት የሚለውን ማዕረግ፣ ‘ኢትዮጵያዊው ሱራፊ’ የተሰኘውን መጽሐፍ ባስመረቁበት ወቅት ‘ስም ከግብር አብሮ ይሄዳልና...’ ሲሉ፣ የጎንደር ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ ብጹዕ አቡነ ኤልሳ የሰጧቸው ስያሜ ነው። ሙሓዘ ጥበባት ማለት ‘የጥበብ መፍሰሻ’ ማለት ነው።
#ምስክርነት
ዲያቆን ዳንኤል ክብረት በመገናኛ ብዙኃን አመራርና አሠራር ጥሩ እውቀትና ልምድ አለው፡፡ አዳዲስ አሠራሮች እንዲጎለብቱ ሃሳብ በማፍለቅና እንዲሳካ ጥረት የማድረግ ብቃት አለው፡፡ አሁንም የጋዜጠኞች ሙያዊ ነጻነትና የሚዲያው ኤዲቶሪያል አቅም እንዲጎለብት እንዲሁም ተቋማዊ አቅሙ እንዲያድግ አስተዋጽኦ ያደርጋል የሚል እምነት አለኝ፡፡
ነፃነት ተስፋዬ የሚድያና ኮምዩኒኬሽን ባለሙያ
##########
ሙአዘ ጥበባት ዳንኤል ክብረት በይዘት ደረጃ ካየነው በባህል ኪነጥበበ እና በታሪክ ዙሪያ የኢትዮጵያን መልክ በፅሑፎቹ እና በንግግሮቹ ለማሳየት ከፍተኛ አበርክቶ ሰጥቷል። ፅሑፎቹ ከሀገር ውስጥ እስከ ውጭ ሀገር እስከ ሦስተኛ ዲግሪ መመረቂያ ጥናቶች የተሠሩባቸው አሁንም ይበልጥ ሊጠኑ የሚገባቸው ትልቅ ዋጋ ያላቸው ናቸው። ዲያቆን ዳንኤል በፅሑፎቹ ኢትዮጵያዊ የሆኑ ፍልስፍናዎችን፣ ጥበባትን፣ ታሪክን፣ ሀይማኖትን፣ ባህልን፣ ሥነ ጽሁፍን ፍንትው አድርጎ በማሳየት የራሱን አሻራ ያኖረ ነው። አበርክቶውም ትልቅ ነው።
እርሱ በፅሑፍ ብቻ ሳይሆን የአደባባይ ሰው በመሆኑ ትውልድ በማነፅ፣ ሥነ-ምግባርን በማስጠበቅ፣ ኢትዮጵያን በመመርመርና በመግለጥ፣ ማኅበራዊ ኂስ በጥበብ በመስጠት፣ ያነበባቸውን መፅሀፎች ወይም ያካበተውን ዕውቀት ጥበባዊ ስልት በተላበሰ ምጡቅ መንገድ በማቅረብ ይታወቃል።
የራሱን አሳታሚ ድርጅትና የበጎ ሰው የሽልማት ድርጅትን በመመሥረትና በመምራት ለእውቀት እና እውቅና መስፋፋት ዋና ሚና ተጫውቷል።
በመንግሥት ኃላፊነቱም ቀድሞ ሲከውን የነበረውን ተግባር በላቀ ሀገራዊ ኃላፊነት እየተወጣ የማህበራዊ ጉዳይ አማካሪ እንደመሆኑ መጠንም ተቋማትን በመመሥረትና በማጠናከር ሚናው ትልቅ እንደሆነ እረዳለሁ።
ዲያቆን ዳንኤል ከ30 በላይ መፅሀፍትን እንደማሳተሙ ጊዜ አጠቃቀሙ እንዴት ይሆን? የሚል ጥያቄ ተደጋግሞ ይነሳል። እርሱ ግን ምናልባት በሰላሳ አመት የጽሁፍ ታሪኩ ከሰላሳ በላይ መጻሕፍትን እና እጅግ ብዙ መጣጥፎችን በሙበርከት ፕሮሊፊክ እና ዐቢይ ሥፍራ የሚደጠው ደራሲ እና የሃሳብ መሪ መሆኑን አስመስክሯል።ለሁሉም እንደሁኔታው ጊዜ በመመደብ ለሁላችን አርዓያ ነው።
ተመራማሪው ዳንኤል፣ ከመዛግብት ተነስቶ የሚፅፋቸውን ታሪኮች አይቻለሁ። በመካከለኛው ዘመን በአገራችን የተደረጉ ብዙ ክስተቶችን ለታሪክ ጥናት እጅግ ጠቃሚ ግብዓት እንዲሆን አድርጎ ከሀገር ውስጥም ከውጭም የሰነደ ነው። ይህ ቀላል አይደለም።
ዲያቆን ዳንኤል ክብረትን ሳስታውስ ብላቴን ጌታ ህሩይን ያስታውሰኛል። እርሳቸው በአንድ በኩል የመንግስት የሥራ ኃላፊነት ይዘው በአንድ በኩል ይፅፋሉ። ምርምሮችንም ያደርጉ ነበር። ዲያቆን ዳንኤል ድንቅ የፈጠራ ክህሎቱን በመጠቀም የሚያቀርባቸው ሥራዎች ከንባብ እና ነገሮች በጥልቀት ተረድቶ የሚያቀርባቸው በመሆኑ ኢትዮጵያን የማሳየት አቅም አላቸው ብዬ አምናለሁ። አበርክቶው እና ጽኑ ሰብዕናው በአጭሩ ተተርኮ የሚያበቃ አይደለም።
ረዳት ፕሮፌሰር ነቢዩ ባዬ የባህልና ኪነ ጥበብ ሚኒስትር ዴኤታ
######
ሙሓዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረትን የማውቀው ከ20 ዓመት በፊት ነው ። የዐውደ ምሕረቱ ፈርጥ ፣የቤተክርስቲያን አጽራር መከታ ከወንድሞች ጋር ሙሉ ጊዜውን ሰጥቶ ሲያገለግልና ለብዙዎቻችን መንፈሳዊ መሠረት ጣይ በነበረ ጊዜ አውቀዋለሁ። በሚጽፋቸው መንፈሳዊና ትዝብት አዘል ማኅበረሰባዊ ጽሑፎች ያልተማረ ,ያልተገሰጸ በነፍሱ ሀሴት ያላደረገ በዙሪያው የነበረ ማንም አልነበረም። በተለይ በማኀበረ ቅዱሳን የሐመር መጽሔትና የስምዐ ጽድቅ ጋዜጣ በሚያዘጋጅበት ወቅት የከተባቸው ጽሑፎች ዘመን የተሻገሩ እስካሁን ለብዙዎች መንፈሳዊ ሙላት የኾኑ ጥዑም ዘለላዎች ናቸው።
የጻፋቸው መጽሐፍት እንዲሁም በብሎጉ በዕይታ ያስቀመጣቸው ትዝብቶቹ በቤተክህነቱም በቤተመንግሥቱም ቅቡልነታቸው የበዛ ነበር።
የቀረቡት ኹሉ ግለሰባዊ ማንነቱን ሊገነዘቡለት የማይከብዳቸው ዳንኤል በዐውደ ምሕረትም ሆነ በመድረክ ራሱን ሳያካብድ ለአገርና ለቤተክርስቲያን በጥልቀት በሚያውቀው የታሪክ አረዳዱ እያገለገለ የሚገኝ ምስጉን ወንድም ነው።
ኢዮብ ስዩም

የበረሃው ምስጢር ፍፃሜ፦ የሰይፍ አል-ኢስላም ጋዳፊ ሁለት ገፅታዎች
ጥር 26 በሊቢያ ናፉሳ ተራሮች ላይ የተሰማው የጥይት ድምፅ፣ የአንድን ሰው ህይወት ብቻ ሳይሆን የሊቢያን የ40 ዓመታት ታሪክ ዳግም የቀሰቀሰ ነበር።
የሙአመር ጋዳፊ ተመራጭ ልጅ ሰይፍ አል-ኢስላም በዚንታን ከተማ በሚገኝ መኖሪያው መገደሉ፣ ሀገሪቱን በሀዘን እና በደስታ ስሜት መካከል ከፍሏታል።
1. የሰይፍ አል-ኢስላም የግል ህይወት፦ በመጋረጃ የተሸፈነው ቤተሰብ
ሰይፍ አል-ኢስላም ጋዳፊ ከወንድሞቹ በተለየ መልኩ የግል ህይወቱን ከሚዲያ እይታ ለማራቅ ይጥር ነበር።
ሚስት እና የፍቅር ህይወት፦ ሰይፍ አል-ኢስላም በለንደን በነበረው ቆይታ ከምዕራባውያን ጋር የነበረው ቅርርብ ለበርካታ ወሬዎች በር ከፍቶ ነበር። በተለይ ከእስራኤላዊቷ ተዋናይ ኦርሊ ዌይነርማን ጋር የነበረው ግንኙነት በወቅቱ መነጋገሪያ ነበር። ሆኖም በኋላ ላይ፣ ሰይፍ ከሩሲያዊት ሴት ጋር በድብቅ ትዳር መመስረቱን እና ይህች ሚስቱ በዚንታን በነበረበት አስቸጋሪ ዓመታት ከጎኑ እንደነበረች ይነገራል።
ልጆቹ፦ ሰይፍ ቢያንስ ሁለት ልጆች እንዳሉት የሚታመን ሲሆን፣ እነዚህ ልጆች በአባታቸው እና በአያታቸው ስም ምክንያት ለደህንነታቸው ሲባል ስማቸው እና የሚኖሩበት ስፍራ በሚስጥር ተይዟል። ከሊቢያ ውጭ (ምናልባትም በሩሲያ ወይም በአፍሪካ ሀገራት) በስደት እንደሚኖሩ ይገመታል። ሰይፍ በመጨረሻው የህይወት ዘመኑ የልጆቹን ድምፅ የሚሰማው በስልክ ብቻ እንደነበር የቅርብ ምንጮች ይገልጻሉ።
2. የተመዘገቡት ወንጀሎች፦ የጥቁር መዝገብ ዳሰሳ
ሰይፍ አል-ኢስላም በዓለም አቀፉ ማህበረሰብ እና በሊቢያ ህዝብ ዘንድ ለፍርድ እንዲቀርብ የሚፈለግበት ዋነኛው ምክንያት በ2011 አመፅ ወቅት የፈፀማቸው ተግባራት ናቸው።
በሰው ልጆች ላይ የተፈፀመ ወንጀል፦ የዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት (ICC) ሰይፍን በግድያ እና በስቃይ (persecution) ወንጀል ይፈልገው ነበር። በሊቢያ ከተሞች ሰላማዊ ሰልፈኞችን በከባድ መሳሪያ እንዲደበደቡ ትዕዛዝ ሰጥቷል በሚል ይከሰሳል።
የደም ወንዝ ዛቻ፦ ሰይፍ በቴሌቪዥን ቀርቦ "ሊቢያን የደም ወንዝ እናደርጋታለን" በማለት የተናገረው ንግግር፣ በኋላ ላይ ለተከሰተው የንፁሃን እልቂት እንደ ማበረታቻ ተቆጥሮበታል።
የገንዘብ ምዝበራ፦ የጋዳፊ ቤተሰብ ከሊቢያ ህዝብ የነዳጅ ሀብት በመቶ ቢሊዮን የሚቆጠር ዶላር አባክነዋል በሚል ከሚከሰሱት መካከል ሰይፍ ግንባር ቀደሙ ነበር።
3. "ተስፋ" ወይስ "አምባገነን"?
የሰይፍ አል-ኢስላም ታሪክ ያለ ሚዛናዊ እይታ ሊጠናቀቅ አይችልም። እርሱ በሊቢያውያን ዘንድ በሁለት መንገድ ይታያል፦
ሀ. እንደ ለውጥ ፈላጊ (The Reformist)
ከ2011 በፊት፣ ሰይፍ ሊቢያን ወደ ዘመናዊነት ለመቀየር የጣረ ሰው ተደርጎ ይታያል።
ሊቢያ የጅምላ ጨራሽ መሣሪያዎቿን እንድታስወግድ በማድረግ ከዓለም ጋር እንድትታረቅ አድርጓል።
በርካታ የፖለቲካ እስረኞች እንዲፈቱ እና የሰብዓዊ መብት ተቋማት እንዲቋቋሙ ጥረት አድርጓል።
በለንደን ስኩል ኦፍ ኢኮኖሚክስ (LSE) የተማረው እውቀቱ፣ ሊቢያን ወደ ዴሞክራሲ ያሸጋግራታል የሚል ትልቅ ተስፋ በምዕራባውያን ዘንድ ጥሎ ነበር።
ለ. እንደ አምባገነን ቀጣይ (The Heir of Tyranny)
የስልጣን ወንበሩ ሲናወጥ ግን ያ የሰለጠነ ገፅታው ተቀይሯል።
ከህዝቡ ይልቅ ለቤተሰቡ ስልጣን ታማኝ በመሆን፣ በገዛ ወገኖቹ ላይ ጦርነት አውጇል።
"እኛ ካልገዛን ሊቢያ ትጠፋለች" የሚለው የአባቱ ፍልስፍና ተከታይ ሆኖ ተገኝቷል።
4. የዚንታን ፍፃሜ እና የሊቢያ የወደፊት እጣ
ሰይፍ አል-ኢስላም ከተገደለ በኋላ የሊቢያ ፖለቲካ አዲስ ምዕራፍ ውስጥ ገብቷል። የእሱ መገደል ለአንዳንዶች "የፍትህ መረጋገጥ" ሲሆን፣ ለሌሎች ደግሞ "ሊቢያን ሊያረጋጋ የሚችል ሰው ማጣት" ነው።
ለደጋፊዎቹ፦ ሰይፍ በትርምስ ውስጥ ለነበረችው ሊቢያ ብቸኛው መረጋጋት ሊያመጣ የሚችል "ልዑል" ነበር። ለእነሱ ሰይፍ የሞተው እንደ ሰማዕት ነው።
ለተቃዋሚዎቹ፦ የእሱ መገደል የጋዳፊን አገዛዝ ናፋቂዎች ተስፋ ያስቆረጠ እና ለወደፊት ዴሞክራሲያዊት ሊቢያ መንገድ የከፈተ ክስተት ነው።
ማጠቃለያ
የሰይፍ አል-ኢስላም ጋዳፊ ህይወት በለንደን የድሎት ህይወት ተጀምሮ በዚንታን በረሃማ ተራሮች ላይ በደም ተደምድሟል። የፈፀማቸው ወንጀሎች የታሪክ ጠባሳ ሆነው ቢቀሩም፣ በሊቢያ ፖለቲካ ውስጥ የነበረው ተፅዕኖ በቀላሉ የሚረሳ አይደለም። ዛሬ ላይ ሰይፍ የለም፤ ነገር ግን ሊቢያ አሁንም በእሱ "የደም ወንዝ" ዛቻ እና በነበረው "የለውጥ ተስፋ" መካከል የራሷን ማንነት ፍለጋ ላይ ትገኛለች።
የእሱ ሞት የአንድን ግዙፍ ቤተሰብ ታሪክ ቢዘጋም፣ የሊቢያ ህዝብ ግን አሁንም ወደፊት የሚመራውን እውነተኛ መሪ በመጠባበቅ ላይ ነው።

መሠረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ከግብረሶዶማውያን ተቋማት ጋር ግንኙነት እንዳይኖራት የተቃወሙትን ከአባልነት ሰረዘች!
የመሠረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ግብረሰዶማዊነትን አካታች ከሆኑ የውጭ ሀገር ሜኖናይት ተቋማትና "ቤተክርስቲያናት" ጋር ምንም ዓይነት ግንኙነት እንዳይኖራት ሲሟገቱ የነበሩትን ሦስት የቤተክርስቲያኒቱን አባላትንና አገልጋዮች ከአባልነት መሠረዟን በትናንትናው ዕለት አሳውቃለች። እነዚህ ወንድሞች ቤተክርስቲያኒቱ ከግብረሶዶማውያን ተቋማት ጋር ግንኙነትና የአጋርነት ስምምነት እንዳይኖራት ከመሞገት ባለፈ ግብረሶዶማዊነትን የተቀበሉ ሜኖናይት ቤተክርስቲያናት እ.ኤ.አ በ2028 ዓ.ም የሚሳተፉበት ዓለም አቀፍ ኮንፍራንስ በአዲስአበባ እንዳይካሄድ ብርቱ ትግል አድርገው ኮንፍራንሱ መሠረዙ ይታወቃል።
ይሁንና በአሁኑ ወቅት የመሠረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን የበቀል እርምጃ በሚመስል መልኩ ቀጥሎ የጠቀስኳቸውን ሦስት ወንድሞችን ከአባልነት ሰርዛለች።
1. ዶ/ር ስዩም አንቶኒዮስ
ዶ/ር ስዩም የቀዶ ሕክምና ባለሙያ ነው፤ ሙያውንና መንፈሳዊ መርሆችን በመንተራስ ግብረሰዶማዊነትን በኢትዮጵያ በመቃወም የሚቀድመው የለም። እንዲሁም በብዙ መድረኮችና በቤተክርስቲያኑም የቃለ እግዚአብሔር አስተማሪም ነው። ዶ/ር ስዩም የመሠረተ ክርስቶስ አገልጋይ ብቻ አይደለም፤ የመላ ኢትዮጵያዊያን እንጂ። በግብረሰዶማዊነትና በፆታ ቅየራ ዙሪያ ዲኖሚኔሽን-ዘለል በሆነ መልኩ እየተጋበዘ ያለመታከት የልምምዶቹን አስከፊነት ይፋ አድርጓል። የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ በግብረሰዶማዊነት ዙሪያ አቋም ሲይዝ ከሚያማክራቸው ባለሙያዎች ውስጥ ዶ/ር ስዩም ግንባር ቀደም ተጠቃሽ ነው።
ይህ ቅን፣ ትጉህና አንደበተ ርቱዕ የሕክምና ዶ/ር ከእንግዲህ በየትኛውም የመሠረተ ክርስቶስ አጥቢያ ስለ ግብረሰዶማዊነት አስከፊነት ማስተማር አይችልም፤ ምክንያቱም ቤተክርስቲያኒቱ "ዶ/ር ስዩም አመፀኛ ስለሆነ አትስሙት" የሚል ቃና ያለው መግለጫ በትናንትናው ዕለት አውጥታለች። ግብረሰዶማዊነት ላይ ማመፅ አመፀኛ የሚያስብል ከሆነም ውሳኔው እሰየው የሚያሰኝ ነው።
የሚገርመው ዶ/ር ስዩም በኢትዮጵያ ሕዋ ሥር የግብረሶዶማዊነትን ገመና ሲገልጥ ጉዞው አልጋ በአልጋ አልነበረም፤ በተለያዩ ጊዜያት ከአንዳንድ በልምምዱ ሥር ካሉ ዛቻና ማስፈራሪያ ደርሶበታል፤ እንዲሁም ልምምዱን በስመ-ሰብዓዊ መብት የሚደግፉ አንዳንድ መንግሥታዊ ያልሆኑ የውጭ ድርጅቶች የዶ/ር ስዩምን ፀረ-ግብረሰዶማዊ እንቅሰቃሴን የሚመለከቱት የጎሪጥ ነው። አሁን የመሠረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን በዶ/ር ስዩም ላይ እንደዚህ ዓይነት የውግዘት እርምጃ በመውሰዷ የሚደሰት ማንም የለም...ሲያስፈራሩትና ሲዝቱበት ለነበሩ የልምምዱ ደጋፊዎች ግን የመሠረተ ክርስቶስ ውሳኔ አንጀት አሪስ እንደሚሆንላቸው በእርግጠኝነት መናገር ይቻላል።
2. ወ/ም ሰለሞን ገ/ማርያም
በሙያው አግሮ-ኢኮኖሚስት ነው፤ በሰለጠነበት በዚህ ሙያ መንግስታዊና መንግስታዊ ባልሆኑ ድርጅቶች ውስጥ በከፍተኛ ባለሙያነትና ኃላፊነት አገልግሏል። ወንድም ሰለሞን በሰራባቸው ድርጅቶች ሁሉ መርሁ በክርስቶስ ጽድቅና በንፁሕ ሕሊና ማገልገል ነው። ከዚህም የተነሳ በቅርብ የሚያውቁት ዋጋ እያስከፈለው እንኳን ለእውነት መወገን ምርጫው እንደሆነ ይመሰክሩለታል። ይህን አቋሙን ከሁለት ወራት በፊት በሀሌታ ቴሌቪዥን በነበረው ቆይታ ከሰጣቸው ምላሾች በግልፅ መገንዘብ ይቻላል።
ወንድም ሰለሞን በትናንትናው ዕለት ከአባልነት የሰረዘችውን ቤተክርስቲያን ለዓመታት አገልግሏታል። በተለይም ለልጆችና ለወጣቶች አገልግሎት ልዩ ትኩረት በመስጠት ለነገ ተተኪ መሪዎች ዝግጅት የበኩሉን አስተዋጽኦ ሲያበረክት ነበር። ስለ እርሱ አገልግሎት የአዋሳ አጥቢያዎችና ክልሉ ይመስክሩ፤ የወንጂ አጥቢያዎችና አሁን ያለበት የመሪ ብርሃን አጥቢያ ቤተክርስቲያናት ይመስክሩ!
3. ወንድም አሰፋ ደሜ
ከፍተኛ የስታቲስክና የቢዚነስ አድሚንስትሬሽን ባለሙያ ነው። መንግስታዊና መንግስታዊ ባልሆኑ ተቋማት በተለያዩ ኃላፊነቶች አገልግሏል፤ ቤተክርስቲያን ውስጥም እስከ መሪነት በብዙ ዘርፎች ያገለገለና እያገለገለ ያለ ወንድም ነው። ወንድም አሰፋ ደሜ ከዶ/ር ስዩምና ከወንድም ሰለሞን ጋር በመሆን ከላይ በጠቀስኩት በሀሌታ ቴሌቪዥን መርሐግብር ላይ በወቅታዊ ጉዳይ ዙሪያ የሰጠው ማብራሪያ ሊንክ በኮመንት ሳጥን ውስጥ ይገኛል።
በመጨረሻም...ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በፕሮቴስታንት ቤተክርስቲያናት አስተዳደራዊ መዋቅር ውስጥ ከክርስቶስ ስም ይልቅ ለስማቸው ክብር ጠብ እርግፍ የሚሉ አምባገነን "አይነኬ" መሪዎች ብቅ እያሉ ነው። ራሳቸው በፌስቡክ ገፃቸው ስለለቁት መረጃ ጥያቄ ሲጠየቁ "ስማችን ጎደፈብን" ብለው ይጮኸሉ። ስማቸውን ለማስከበር ሲሉም የመንግሥት የፖሊስ መዋቅር እንጠቀማለን እያሉ ስለ ቤተክርስቲያን ንጽሕና የሚሟገቱትን ያስፈራራሉ። ሆኖም ይህም ጊዜ ያልፋል፤ ሁሉም የዘራውን የሚያጭድበት ቀንም እሩቅ አይደለም።
እግዚአብሔር ያያል!!!
Via getahun heramo

7 months ago
"የሕወሓትን መንገድ መከተል የበለጠ ጥፋት ያስከትላል” የኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ ማስጠንቀቂያ
የጥምቀት በዓል በወልቃይት ዞን በተከዜ ወንዝ ዳርቻ ተከብሯል። በዚህ ክብረ በአል ላይ ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ ተገኝተው ንግግር ያደረጉ ሲሆን፤ ማሳሰቢያ እና ማስጠንቀቂያ አዘል መልእክቶችን አስተላልፈዋል።
የወልቃይት ጠገዴ ሕዝብ አማራዊ ማንነቱን በህግ አግባብ ለማጽናት እየሰራ ነው ሲሉ ቀጥለው፤ ዛሬም እንደትናንቱ አንድነታችን አጠናክረን ልንቀጠል ይገባል ብለዋል።
የወልቃይት ጠገዴ ሕዝብ እውነትን ይዞ እየታገል ያለ ሕዝብ በመሆኑ ፍትህ ወዳድ ኢትዮጵያዊያንና የአለም ሕዝብም እውነታውን እየተረዱ ለነጻነትና ለአማራዊ ማንነታችን ስንል የከፈልነውን የማይካድራ የጅምላ ጭፍጨፋ ያውቃሉ ብለዋል።በዚህም በቅርቡ በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኧርቪን ማሲንጋ በቦታው በመገኘት ያደረጉ ውይይት ማሳያ ነው ብለዋል።
የአማራና የትግራይ ህዝብ በኢትዮጵያ ታሪክ ክፉውንም ደጉንም አብሮ ያሳለፈ ወንድማማች ህዝብ ነው ብለዋል። በአብሮነት ለመኖር ከእኛ ከወንድሞቻችሁ ጋር በመነጋገርና በመወያየት እንጂ የህወሓትን መንገድ መከተል የበለጠ ጥፋት ያመጣል ሲሉ ገልጸው የወልቃይት ጠገዴ ህዝብ ጎንደሬ አማራነቴን አትቀሙኝ አለ እንጂ ከትግራይ ህዝብ ጋር አብረን አንኖርም አላለም ሲሉ ተናግረዋል።
"ጥምቀትን በተከዜ ወንዝ ዳርቻ ማክበራችን እንቀጥላልን፣ አስተዳደራችን አጠናክረን ነጻነታችን በህግ አግባብ እናጸናለን" የሚጠናከር እንጂ የሚፈርስ አስተዳደር የለም ብለው አንዳንድ አካላት ለፖለቲካ ፍጆታ ሲሉ የሚያናፍስሱትን የተለመደ የአሉቧልታ ወሬ ልናዳምጥ አይገባም ብለዋል።

8 months ago
#አዶናይ llተጥሎ የተገኘው ልጅl
(ክፍል 5)
ድራማው አሁን Misale Media ላይ ተለቀቀ!
👇👇👇
https://youtu.be/nEQwc1VYU...
ድራማው አሁን በ Misale Media ላይ ተለቀቀ!!
ተጥሎ የተገኘው ልጅ አዶናይ አድጎ ሀብትና ንብረት እንዳይወስድ በመስጋት ልጅነቱን ሳይጨርስ ይህችን አለም እንዲሰናበታት በአክስቱ በኩል ሴራ እየተሴረበት ነው። አዶናይ ግን ሞት እንቢ ሆኖ ሰባተኛ አመቱን ደፍኗል፤ አክስቱ እንደፈራችው አድጎ የዚያን ቤት ሀብት ንብረት ይወርስ ይሆን? ከወንድሙ ናቲ ጋርስ ዕጣ ፈንታቸው ምን ይሆን? ክፍል 5 ድራማው Misale Media ላይ አሁን ስለተለቀቀ እንድታዩት ጋብዘናል።
ያለ ጥርጥር ትወዱታላችሁ!!!
አዳዲስ የምንለቃቸው ፊልሞች እንዲደርሷችሁ ቻናሉን #ሰብስክራይብ፣ #ሼርና #ላይክ በማድረግ ቤተሰብ እንድትሆኑ እንጋብዛለን።

"እኛ ከወንድሞቻችን ኢትዮጵያዊያን ጋር ምንም አይነት ችግር የለብንም" ሲሉ የግብፁ ፕሬዝደንት ተናገሩ፡፡
#ethiopia | በካይሮ የአፍሪካ ሩሲያ የትብብር ፎረም መካሄድ መጀመሩን ትላንት በዘሀበሻ መዘገባችን ይታወሳል፡፡
በዚህ ስብሰባ ላይ የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጄይ ላቭሮቭና በርካታ የሩሲያ ዲፕሎማቶች የተገኙ ሲሆን የ50 የአፍሪካ አገራት ሚኒስትሮችም ተሳታፊ መሆናቸውን ገልፀን ነበር፡፡ ይህ ፎረም ዛሬም ቀጥሎ ሲቀጥል የግብፁ ፕሬዝደንት አብዱል ፈታህ አል ሲሲ ተገኝተው ለተሳታፊዎች ንግግር አድርገዋል፡፡
በዚህ ንግግራቸው ላይ ስለኢትዮጵያም አንስተው ነበር፡፡ አል ሲሲ ሲናገሩ ‹‹ግብፅ ከኢትዮጵያዊያን ወንድሞቿ ጋር ምንም አይነት ችግር የለባትም፡፡ እንዲሁም ከኢትዮጵያዊያን ጋር ግጭት ውስጥ መግባትም ሆነ ጥላቻ ማስፈን አትሻም›› ብለዋል፡፡
ጨምረውም ‹‹የግብፅ ዋነኛ ጥያቄ በአባይ ወንዝ ላይ ያላት የውሀ መብቷ እንዳይጎዳ ብቻ ነው፡፡ ይህንን መብቷን ለማስጠበቅ ደግሞ በህዳሴው ግድብ ላይ ህጋዊና አሳሪ ስምምነት ላይ መድረስ አስፈላጊ ነው፡፡ ስምምነቱ ለሁሉም አካላት ዋስትና የሚሰጥ ይሆናል›› በማለት ገልፀዋል፡፡
ፕሬዝደንት አል ሲሲ ንግግራቸውን ሲቀጥሉም ‹‹የግብፅ ፖሊሲ ወጥነት ያለውና በየትኛውም አገር ውስጣዊ ጉዳይ ላይ ያለመግባት ላይ የተመሰረተ ነው፡፡ በሌሎች አገራት ውስጥ መተራመስ እንዲፈጠር የሚያደርግ ፖሊሲም የላትም፡፡
ምንም እንኳ እኛ ከኢትዮጵያ ጋር አለመግባባት ቢኖረንም ፈፅሞ ለኢትዮጵያ ስጋት የሚሆን ነገር ፈጥረን አናውቅም›› በማለት ገልፀው ግብፅ ማንኛውም አለመግባባት በውይይትና በፖለቲካዊ መፍትሄ እንጂ በግጭት ወይንም በሀይል ይፈታል የሚል እምነት እንደሌላት አስታውቀዋል፡፡

የያንጎ ፌሎውሺፕ ኢትዮጵያን ጨምሮ በስድስት የአፍሪካ ሀገራት ተጀመረ።
ይህም የቀጣዩን ትውልድ ዐቅም በሳይንስ እና ቴክኖሎጂ እንዲሁም በምኅንድስና እና ሒሳብ ዘርፍ ለማጎልበት የሚያስችል ነው::
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ - ታኅሣሥ 09 ቀን 2018ዓ.ም።
ዓለም አቀፋዊ የቴክኖሎጂ ተቋም የሆነው ያንጎ ግሩፕ፣ የያንጎ ፌሎውሺፕ ቀጣይ ምዕራፍ - በመላው አፍሪካ የሳይንስ እና ቴክኖሎጂ እንዲሁም የምኅንድስና እና ሒሳብ ዘርፍ ችሎታን ለማጎልበት ዓልሞ እንደተነደፈ አስታውቋል።
ያንጎ ፌሎውሺፕ፣ ወጣቶችን በማማከር እና አቅጣጫ በመጠቆም እንዲሁም ግብዓቶችን እና የግንኙነት መረቦችን በመዘርጋት፣ ተሳታፊዎች ማኅበረሰባቸውን የሚጠቅሙ ሐሳቦችን እንዲያመነጩ ብሎም ወደ ተግባር እንዲቀይሩ እገዛ ያደርጋል።
በዛምቢያ እና በአይቮሪኮስት በተሳካ ሁኔታ የተጀመረው የያንጎ ፌሎውሺፕ ፕሮግራም አድማሱን በማስፋት ወደ አራት ተጨማሪ ሀገራት፣ ማለትም ኢትዮጵያ፣ ሞዛምቢክ፣ ጋና እና ሴኔጋል ደርሷል።
መዳረሻዎቹን እያሰፋ የመጣው የያንጎ ፌሎውሺፕ ፕሮግራም፣ የገንዘብ ድጋፍን እና የባለሙያዎችን ሰፊ እገዛ ያካተተ ከመሆኑም ባሻገር፣ በድንበር ያልተገደበ ሰፊ የፌሎው ተጠቃሚ ማኅበረሰብ ግንኙነቶችን በማመቻቸት ተሳታፊዎች ለኅብረተሰባቸው መፍትሔ ፈጣሪ እንዲሆኑ የሚያስችል ነው።
መርሐ ግብሩ፣ የመጨረሻ ዓመት ተማሪዎቹን፣ በወደፊት የሥራ ሕይወታቸው ውጤታማ እንዲሆኑ የሚያስችሉ ድንቅ የሥራ ልምዶች እና ክሂሎቶችን እንዲያገኙ በማመቻቸት ለስኬታማ ነገአቸው ዝግጁ ካደረገ በኋላ፣ በቀጣዩ ዓመት ደግሞ አዳዲስ ስኬታማ ባለሙያዎችን እና በድንበር የማይገደብ የተግባቦት መረብን በመፍጠር ከአፍሪካ ልዩ ልዩ አካባቢዎች የተውጣጡ ወጣቶችን በዐቅም ለማጎልበት ዝግጅቱን ጨርሷል፡፡
በመላው አፍሪካ ያለው የሠለጠኑ የሳይንስ ሊቃውንት፣ መሐንዲሶች እና የቴክኖሎጂ ባለሙያዎች ፍላጎት ወደነዚህ መስኮች ከሚገቡት ተማሪዎች ቁጥር ጋር ሲነጻጸር እጅጉን የማይመጣጠን ነው።
የዓለም ባንክ እንዳስቀመጠው ከሆነ ደግሞ፣ ከሰሐራ በታች ባሉ የአፍሪካ ሀገራት ዘላቂ የኢኮኖሚ ዕድገታቸውን ለመደገፍ ከ2.5 ሚሊዮን በላይ የሳይንስ እና ቴክኖሎጂ እንዲሁም የምኅንድስና እና ሒሳብ ዘርፍ ባለሙያዎች ያስፈልጓቸዋል፡፡
በተመሳሳይ ሁኔታ፣ በፍጥነት በማደግ ላይ ያለው የአፍሪካ ሕዝብ የወጣቶች ቁጥር ከፍያለ የክሂሎት ክፍተት ይስተዋልበታል፡፡ ጥራት ያለው የዲጂታል ወይም የቴክኒክ ሥልጠና የማግኘት ዕድል ያላቸው ከ10-15% የሚሆኑ አፍሪካውያን ወጣቶች ብቻ ሲሆኑ ከ5% ያነሱት ደግሞ በፕሮግራሚንግ፣ በመረጃ ትንተና ወይም በሳይበር ደህንነት እና መሰል መስኮች ልምድ ያገኛሉ።
በየዓመቱ ከ10-12 ሚሊዮን የሚገመቱ ወጣቶች ወደ ሥራው ዓለም የሚቀላቀሉ ቢሆንም በየዓመቱ የሚኖሩት ክፍት የሥራ ዕድሎች ከ3 ሚሊዮን አይዘሉም፡፡ በመሆኑም ይህንን ችግር ለመቅረፍ ብቃት ያላቸው የሳይንስ እና ቴክኖሎጂ እንዲሁም የምኅንድስና እና ሒሳብ ዘርፍ ባለሙያዎችን ማፍራት የግድ ይላል።
ያንጎ፣ ይህንን መርሐ ግብር በበርካታ አካባቢዎች በማስፋት፣ አስተማማኝ ዐቅም ያለው እና ለወደፊት ዝግጁ የሆነ ሥልጡን የሳይንስ እና ቴክኖሎጂ እንዲሁም የምኅንድስና እና ሒሳብ ዘርፍ ባለሙያዎች ለመገንባት ትልቅ ዓላማ የሰነቀ ሲሆን ሠልጣኞች በማኅበረሰባቸው ውስጥ ለሚፈጠሩ ተግዳሮቶች መፍትሔዎችን እንዲያዘጋጁ የማስቻል ርዕይ አለው።
ፕሮግራሙ ትብብርን፣ ፈጠራን እና ብቃት ያለው አመራርን የሚያበረታታ ሲሆን አህጉሪቱን የሚያጠቃልልና የቀድሞ ተማሪዎችን የሚያሳትፍ ጠንካራ አውታረ መረብ በመገንባት ላይ ይገኛል።
በቅርቡ የወጣው ሀገራዊ መረጃ እንደሚያሳየው፣ ኢትዮጵያ ከባድ የሰው ኃይል ብክነት ተግዳሮት ከፊቷ ተጋርጦባታል፡፡የወጣቶቿ ሥራ አጥነት አሁንም ከፍ ያለ ሆኖ ይታያል፡፡ ይህችግር በተለይም በከተሞች አካባቢ ከ25 በመቶ በላይ የሚደርስ ሲሆን ወጣት ሴቶች ደግሞ በሥራ አጥነት ከፍተኛውን ቁጥር ይይዛሉ፡፡
ትምህርታቸውን ካጠናቀቁ በኋላ በግምት 42% የሚሆኑት የዩኒቨርሲቲ ተመራቂዎች መደበኛ ሥራ ለማግኘት ይቸገራሉ፡፡ ይህም በተመራቂዎች ብዛት እና በሥራ ገበያ ፍላጎት መካከል ያለውን ክፍተት አጉልቶ ያሳያል።
በተቻለ መጠን የሳይንስ እና ቴክኖሎጂ እንዲሁም የምኅንድስና እና ሒሳብ ዘርፍ ባለሙያዎችን በማፍራት እና ዕድሉን ለሁሉም በማስፋፋት ረገድ የተሻሻሉ እመርታዎች ቢኖሩም የተሳትፎ እና የሥራ ውጤቶቹ ከዘርፉ ፍላጎት አንጻር ብዙ የሚቀራቸው ናቸው፡፡ በተለይ በጾታ ድልድሉ በኩል፣ ሴቶች በከፍተኛ ሁኔታ ውክልና የማይኖራቸው ሲሆን ከወንድ እኩዮቻቸው በበለጠ ለሥራ አጥነት ወይም መደበኛ ላልሆነ ሥራ ተጋላጭ ናቸው።
ከዚህም በላይ ቀጣሪዎች እና ጥናቶች እንደሚጠቁሙት፣ አሁን ላይ ገበያው ለሚፈልገው ዲጂታል እና ፈጠራ-ተኮር ሥራዎች የሚያስፈልጉ የቴክኒካል እና የተግባር ሥልጠናዎች የሚያሟሉ ጥቂት ተመራቂዎች ብቻ በመኖራቸው በኢኮኖሚው ውስጥ ከፍ ያለ የችሎታ አለመመጣጠን ይታያል።
በያንጎ ግሩፕ ውስጥ ዋና የቢዝነስ ኃላፊ የሆኑት አዴኒዪአዲቤዮ - በጋዜጣዊው መግለጫ ላይ "አፍሪካ፣ ለፈጠራ የሚተጋ እና ችግር ፈቺ ኃይልን ማምጣት የሚችል ልዩ ችሎታአላት። የያንጎ ፌሎውሺፕም፣ እነዚህን ችሎታዎች ለማገዝ እና ወጣት ፈጣሪዎችን ከአማካሪዎች፣ ከግብዓቶች እና ከእውቀት ጋር በማገናኘት ወጣቶቹ ማኅህበረሰቦቻቸውን የሚጠቅሙ መፍትሔዎችን እንዲያዳብሩ ለማስቻል የተነደፈ ተግባራዊ ፕሮግራም ነው፡፡
በዚህ ዓመት፣ፕሮግራማችን በስድስት ሀገራት ውስጥ የሚካሄድ ሲሆን፣የዕውቀት ሽግግርን በመፍጠር እና ቴክኖሎጂን በመጠቀም በአህጉሪቱ ላይ እውነተኛ ተፅእኖ ለመፍጠር ያልማል፡፡” ብለዋል፡፡
መርሐ ግብሩ ከተጀመረበት ጊዜ አንሥቶ ውጤታማ ስለመሆኑ፣ እስከዛሬ ድረስ በፕሮጀክቱ ውስጥ ያለፉው ጤታማ ሠልጣኞች እና ተሳታፊዎች በየአካባቢያቸው ትልልቅ የማኅበረሰብ ፕሮጀክቶችን ጀምረው እና ውጤታማ ሆነው በአርአያነት መመዝገባቸው ቋሚ ምስክር ነው።
የያንጎ የአካባቢ ማዕከሎች፣ ስኬታማ ወጣቶችን በማስተማር እና በዐቅም በማጎልበት ቁልፍ ሚናን ይጫወታሉ፡፡ ይህም ፕሮግራሙ ችሎታንና እና አካባቢያዊ ሥነ-ምኅዳርን እንደሚያጠናክር የሚናገር ነው።
ለያንጎ ፌሎውሺፕ እንዴት ማመልከት ይቻላል?
መርሐ ግብሩ አሁን በሳይንስ እና ቴክኖሎጂ እንዲሁም በምኅንድስና እና ሒሳብ ዘርፍ፣ ዕድሜያቸው ከ18–25 ድረስ ያሉ ኢትዮጵያውያን ወጣቶችን ለመቀበል ክፍት ነው፡፡ ፍላጎት ያላቸው አመልካቾች እስከጥር 18 ቀን 2018ዓ.ም. ድረስ ድረ ገጻችንን https://yangofellowship.co... በመጠቀም ማመልከት ይችላሉ፡፡.

የአፋልጉኝ ተማጽኖ
#ethiopia | አባቴ Shumi Edea እሁድ ታህሳስ 05-2018 ዓ.ም ቀን 9:30 አከባቢ ከአጎቴ (ከወንድሙ) ቤት [ወለቴ ማርያም መውጫ Condominium] በድንገት እንደወጣ አልተመለሰምና ያያችሁት ካላችሁ በሚከተሉት ስልኮች እንድታሳውቁን በእግዚአብሔር ርኅራሄ እንለምናችሁ አለን ::
ከቤት ሲወጣ ጋቢ ደርቦ ፣ Blueblack መለዮ(ኬፕ)፣ ደብዘዝ ያለ ጌሾአማ ኮት፣ ጠቆር ያለ ሱሪ እና ነጭ ጫማ አድርጎ ነበረ
Yosef Shumi 0912819540
ናታን ሹሚ 0919409727
ጉታ ኤዴአ 0912089208
ዳዊት አሰፋ 0900574369
#ሼር #share

ውድ ኢትዮጵያውያን ለሐገር ባለውለታው ለታላቁ ደራሲ ሐብታሙ አለባቸው ድጋፍ እናድርግለት
(ይትባረክ ዋለልኝ)
#ethiopia | ታላቁ ደራሲ ሐብታሙ አለባቸው እንዴት እንደዚህ ሊሆን ቻለ? በማለት በቁጭት ለእርሱ ያላቸሁን አድናቆትና ፍቅር መሰረት በማድረግ ለዚህ የሃገር ባለውለታ ደራሲ ልንደርስለት ይገባል ብላችሁ ባለፉት ሁለት ቀናት በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ገንቢ ሐሳባችሁን ስታካፍሉ ለነበራችሁ ውድ ኢትዮጵያውያን በቅድሚያ እጅግ የከበረ ምስጋናዬን በቤተሰቡና በራሴ ስም ከልብ ላመሰግናችሁ እወዳለሁ::
እኔ ጋዜጠኛ ይትባረክ ዋለልኝ እባላለሁ: የደራሲ ሀብታሙ አለባቸው የ20 ዓመት ጓደኛ ነኝ:: ሐብታሙ አለባቸው እኔ ሐብትሽ ነው የምለው ጓደኛዬ ብቻ ሳይሆን ወንድሜ ነው:: የእኔንና የሐብትሽን የቅርብ ጓደኝነት የሚያውቁ በርካታ ሰዎች የመቀሌ ዩንቨርሲቲ መምህራን : የመንግስት ኃላፊዎች: ጋዜጠኞች ጉዳዩን የሰሙ ሁሉ ዛሬ ድረስ ከተለያዩ የሐገሪቱ ክልሎች የሐብትሽ ጉዳይ አስጨንቋቸው ሲደውልልኝ ነው የቆዩት::
ከብዙዎቹ ደዋዮች መካከል ጋዜጠኛናደራሲ ቴዎድሮስ ተ/አረጋይ እና ጋዜጠኛ ሁሴን ከድር ደውሉ ባቢ አንድ ነገር ማድረግ አለብን አሉኝ :: " እኔም እሺ ሐብታሙ ምንም ቢቸግረው እርዱኝ የማይል ሰው እንደሆነ ባውቅም :: ደጋግሜ ወደ ሐብትሽ ጋር ስልኩ ዝግ ነው:: ወዲያው ቤተሰቦቹን በቅርብ ስለማውቃቸው መጀመሪያ ብዙ ጊዜ ከጎንደር አዲስ አበባ እየተመላለሰ በሐብትሽ ጉዳይ ከእኔና ከሌሎች ወዳጆች ጋር እላይ እታች ለሚለው ምርጥ ወንድሙ ሙሉቀን አለባቸው ጋር ደወልኩ :: በተመለከትነው ጉዳይ ሐዘን ቢሰማንም ይህን ሁኔታ እንደመልካም አጋጣሚ ቆጥረን ምን እናድርግ የሚለው ጉዳይ ላይ ተነጋገርን::ወንድሙ ሙሉቀን የሚኖረው ጎንደር ስለሆነ በማግስቱ እርሱ ከጎንደር ወደ አዲስ አበባ እንዲመጣ ተነጋገርን:: ድጋፍ አድርጉልኝ የሚል ስብዕና ባይኖረውም ሐብትሽ የኢትዮጵያን ሐብት ነውና እርሱን መደገፍ እንደ ሐገር ግዴታ ስላለብን ብለንጉዳዩን ለህዝብ አሳውቀን ድጋፍ የሚያስፈልገውን ሁሉ ለህዝብ እናሳውቃለን በሚለው ሐሳብ ላይ ተነጋግረ በመስማማት ተለያየን:: በማግስቱ ሐሙስ ጠዋት ሙሉቀን አዲስ አበባ ገባ::
ከዚያም ለሐብትሽ መደረግ የሚገባቸውን ተግባሮች ቅደም ተከተል በማውጣት ከትላንት ጀምሮ ስራ ሲሰራ ቆይቷል:: በዚህም ቅድሚያ መደረግ ያለበት ጉዳይ ላይ ስራ ተጀምሯል:: ሐብታሙ አለባቸው ድጋፍ ለማድረግ
ለዚህ አላማ ትላንት በሁለት ቤተሰቡ ሙሉቀን አለባቸው እና መሰረት መኮንን ስም ትላንት የባንክ አካውንት ተከፍቷል::በአሁኑ ወቅት ሐብትሽ ሕክምናውንእየተከታተለ ይገኛል::
ሐብትሽ ደራሲ ብቻ አይደለም:: ልታይ ልታይ የማይል እጅግ አዋቂ እና በተማሪዎቹ የተወደደ ጎበዝ ምምህርም ነው:: በሰው ዘንድ እጅግ የተወደደ ደግና ልበ ስሱ ሰው ነው:: ሁል ጊዜ የሚጨነቀው ስለሚፅፈው ሐሳብ :: የሚጨነቀው ስለ ሐገሩ ነው:: ስለ ራሱ ህይወት ሳይሆን ስለተቸገሩ ኢትዮጵያውያን ነው ጭንቀቱ:: ሐብትሽ ለተቸገሩ ገንዘቡን ብቻ ሳይሆን ንብረቱን አውጥቶ የሚሰጥ አስደናቂ ስብዕና ያለው ሰው ነው:: ሐብትሽ ምንም ቢቸግረው እራሱን ይጎዳል እንጂ ቸገረኝ የማይል አስገራሚ ሰው ነው::
በሐገር ውስጥና በመላው ዓለም የምትኖሩ ውድ ኢትዮጵያውያን ወንድማችን ደራሲ ሐብታሙ አለባቸው ዛሬ የሁላችንን ድጋፍ ይሻል::በመሆኑም በዋናነት ሐብትሽ ተረጋግቶ የሚኖርበት አነስተኛ ቤት የሚያገኝበትንና ለመቋቋሚያ የሚሆን የገንዘብ ድጋፍ እንድናደርግለት ስል በቤተሰቡ በጏደኞቹና በራሴ ስም ከልብአመሰግናለሁ:: ለሐብትሽ ትንሽ ድጋፍ ብናደርግለት ለሐገር ዋጋ የሚጠቅሙ በርካታ ስራዎቹን ነገ ማግኝት እንደምንችል ምንም ጥርጣሬ የለኝም::ሰይፉ ፋንታሁንም በታላቁ ደራሲ በሐብትሽ ሁኔታ እጅግ ተጨንቆ በታላቅ ኃላፊነት ስለሐብታሙ አለባቸው አጠቃላይ ሁኔታ ትላንትና ከወንድሙ ሙሉቀን አለባቸው ጋር ቆይታ አድርጏል:: እሁድ ምሽት ፕሮግራሙ ይለቀቃል::
ለታላቁ ደራሲ ሐብታሙ አለባቸው ድጋፍ ለማድረግ ለዚህ አላማ ትላንት በሁለት ቤተሰቡ ሙሉቀን አለባቸው እና መሰረት መኮንን ስም በተከፈተው የባንክ አካውንት ድጋፍ ማድረግ ትችላላችሁ::
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ :-1000735581396
ሙሉቀን አለባቸው እና መሰረት መኮንን
ስልክ ቁጥር:- + 251 918063957
ማሳሰቢያ
=====
ለደራሲ ሐብታሙ አለባቸው ከዚህ የባንክ አካውንት ውጪ በቲክቶክም ሆነ በየትኛውም መንገድ የተከፈተ የድጋፍ ማሰባሰቢያ የለም:: #share በማድረግ እንተባበር

በቻይና የእናቱን የአንገት ሀብል ቆራርጦ ለትምህርት ቤት ጓደኞቹ ያከፋፈለው የ8 አመት ልጅ አነጋጋሪ ሆኗል
በቻይና ሻንዶንግ ግዛት ዣኦዡዋንግ የአንድ ደሀ ቤተሰብ ታሪክ በድንገት የአካባቢው መነጋገሪያ ማዕከል ሆናለች።
መጀመሪያ ላይ እናቱ ሳን ምንም ምታወቀው ነገር አልነበረም። አንድ ቀን ግን ሴት ልጅቷ ከክፍል ጓደኞቿ አንዷ ከወንድሟ 'የወርቅ ቁራጭ' በስጦታ እንደተቀበለች እንደሰማች ለእናቷ ነገረች። እናቷም ደነገጠች።
እናትየውም ተገርማ ልጇን ስለ ጉዳዩ ጠየቀችው። ስምንት ዓመቱ ልጅም 'አዎ፣ የወርቅ ቁርጥራጮቹን ሰጥቻቸዋለሁ! ሐብልሽን ሰባብሬ ሰጠኋቸው' ሲል ያለምንም ማመንታት መለሰ። ይህንን የሰማችው እናት ከሰማይ የተዳፋባት መሰላት ሲል ሳውዝ ቻይና ሞርኒግ ፖስት ዘግቧል።
በኋላ፣ አጠቃላይ ክስተቱ ከቤቱ የሲሲቲቪ ካሜራ ቀረጻ (CCTV footage) ተጋለጠ። ቀረጻው ላይ ልጁ በአንድ እጁ ፒንሳ በሌላኛው ደግሞ ላይተር ይዞ የእናቱን ሐብል ለመቁረጥ ሲሞክር ያሳያል። ሳይሳካለት ሲቀር በመጨረሻ በጥርስ ነክሶ ወደ ትናንሽ ቁርጥራጮች ሰባበረው።
እናትየዋ ስንት ቁርጥራጮች ለማን እንደሰጠ ማወቅ ትፈልጋለች? ነገር ግን ልጁ ማስታወስ አልቻለም። የሐብሉን ቁርጥራጮች በሙሉ ወደ ትምህርት ቤት አልወሰደም። ነገር ግን የተቀሩትን ቁርጥራጮች ቤት ውስጥ የት4 እንዳስቀመጣቸውም ረሳው። ወላጆቹ ለሰዓታት ከፈለጉ በኋላ አንድ ትንሽ ቁራጭ ብቻ ነው ያገኙት።
ስምንት ግራም የሚመዝነው ሐብል የሳን የሰርግ ትዝታ ነው። በአሁኑ ጊዜ በአንዲት ግራም ወርቅ በቻይና ያለው ዋጋ ወደ 1,200 ዩዋን ነው። በዚህ መሠረት የሐብሉ ዋጋ 9,600 ዩዋን ይሆናል። በኢትዮጵያም ወደ 211 ሺ ብር ይጠጋል።

9 months ago
የሞባይል ስልክ ወንዶችን ለመካንነት ይዳርጋል ?
በአሜሪካ በአማካይ 2 ሚልዮን የሚሆኑ ወንዶች በዓመት መካንነት አንደሚከሰትባቸው ጥናቶች ያሳያሉ ።ብዙ ጊዜ ልጅ ያለመውለድ ችግር የሴቶች ብቻ ይመስለናል:: ነገር ግን የዓለም የጤና ድርጅት እንደሚለው 8% በወንዶች ምክንያት ብቻ የሚከሰት መካንነት ነው ።ለወንድ መሃንነት ተጠያቂ የሚደረጉ ብዙ ነገሮች አሉ።
ዛሬ ግን ስለወንዶች መካንነት የተሳሳቱ አፈታሪኮች(Myths) እናያለን፤
🔹 ሲጋራ ማጨስ መካንነትን አያስከትልም
አብዛኛውን ወንዶች ሲጋራ ማጨስ ለመካንነት አይዳርግም ብለው ያምናሉ ነገር ግን እንደ የእንግሊዝ የህክምና ማህበር ገለጻ መሰረት ሲጋራ ማጨስ መካንነትን በ 30% ይጨምራል::በተለይም በቀን ከ 5 በላይ ሲጋራ የሚያጬሱ ወንዶች የዚህ ሰለባ ተጠቂ እንደሆኑ መረጃዎች ያሳያሉ::
አጫሾች ላይ የተደረገ ጥናት እንደሚያሳየው ነባዘራቸው ላይ የተወሰነ ቶባኮ እንደሚኖር እና እነዚህ ኬሚካሎች የነባዘር ቁጥርን እንዲሁም የወንድ ነባዘር የሚንቀሳቀስበት ፍጥነትም ይቀንሳል።
🔹 ላፕቶፕ እና የእጅ ስልኮች ከወንድ የዘር ሴሎችን ጋር ምንም አያገናኘውም
በሃገራችን በተለያዩ ማህበራዊ ድህረገጾች ስመለከት ላፕቶፕ እና የእጅ ስልኮች መካንነትን እንደማያስከትሉ እና ችግር እንደሌለው ይናገራሉ ::
በ አሜሪካ የ ማህፀን እና የፅንስ ስፔሻሊስት የሆኑት (Dr. Christopher S. Sipe of Fertility Centers of Illinois)እንደገለጹት ከሆነ ከ ላፕቶፕ የሚመነጨው ሙቀት የወንድ የዘር ሴሎችን መጠን እና ፍጥነት ይቀንሳል::ብዙ ሰዎች ላፕቶፕ ታፋቸው ላይ አስቀምጠው ይጠቀማሉ። ይህንን ሙቀት የሚቀንሱ አንዳንድ ሞዴሎች ቢኖሩም ላፕቶፕን ዴስክ ወይም ጠረፔዛ ላይ አስቀምጠን እንድንጠቀም ይመክራል።
እንዲሁም በስልክ ላይ በተሰራ ምርምር የወንድ ነባዘር ከስልክ በሚመነጭ ራዲዬሽን ሲጋለጥ ጉዳት ይደርስበታል::ለዚህም እንደመፍትሄ የቀረበው የሞባይል ስልኮቻችንን በጎን ኪስ አለማስቀመጥ እና ቦርሳዎችን መጠቀም ይጠቀሳሉ ::
🔹 በአጠቃላይ መካንነትን የሚያስከትሉ ብዙ ምክንያቶች አሉ::በቀላሉ እለት ተእለት የማናስተውላቸው ነገር ግን ለጤናችን እጅግ በጣም ጠቃሚ መረጃዎችን ችላ ባለማለት ጤናችንን እንጠብቅ::via.zena since

ከቁጭ ከተማ እስከ ቻይና 🇨🇳
#ethiopia | የተወለድሁበትን ቀን በትክክል አላውቀውም። እናቴን ስጠይቃት ˝ጥቁሩ በሬ ገደል የገባ ጊዜ ነው ˝ አለችን...አባቴ ደግሞ "ቁጭ ከተማ ስትመሰረት አንተ ተወለድሃል" ይለኛል...
ከሰፈራችን አንድ ቀን ቀድሞኝ የተወለደ ልደቱን ጳጉሜ 5 ቀን ስለሚከብር የኔንም ጳጉሜ 6 ቀን በአራት ዓመት አንዴ ማክበር ጀምሬአለሁ... በነገራችን ላይ፥ ጳጉሜ በትርፍ ስለምትቆጠር የሰፈሩ ሰው "ትርፍ ልጅ" እያለ ነው ሚጠራኝ... እያልሁ እንደ ልቦለድ ሀሳባችሁን ከምሰርቅ ወደ እውነተኛ ታሪኬ በምናብ ልውሰዳችሁ።
ያደግሁበት ሰፈር አንዳችን ካንዳችን ቤት በልተና በአልፎ ሃጅ ሰው ተመተን ነው ፡፡ ስለዚህ አንድ ሽልጦ ሰጥቶ ይልክሃል ወይም በኩርኩም ብሎ ስታለቅስ አንድ ሽልጦ ይሰጥሃል፡፡ የሰፈሩ ተፅኖ ይመስለኛል ገና በለጋ እድሜዬ በሽልጦና በአስር ሳንቲም የማ ሳዳን ምጣድ ከመናሃሪያ ወደ ምጣድ ተራ በማመላለስ ስራ ጀመርሁ፡፡ እማ ሳዳ ከቡሬ ቅዳሜ እና ረዕቡ የሸክላ ምጣድ ነጋዴ ናቸው።
ኩሽኔታ ሲገፉ በፊት ሁኜ ኩሽኔታውን በገመድ በመሳብ (ጭቃ ስለሆነ ከተማው ኩሽኔታው ስማይሽከረከር ነው በገመድ ሚጎተተው)ና ከማ ሳዳ የማገኛት ሳንቲም በማጠራቀም በአንድ ብር ሁለት ደብተር ገዝቼ ሆሮሰቃ ትምህርት ቤት ገባሁ፡፡
ታላቅ እህቴንና እኔ ገንዘብ ሚያስገኝ ሰራ መስራት እነዳለብን ወስነን ቄጤማ (ጨፌ) ቋንጥ ከምትባል ስፈራ ከነ ዝናው ተሰማ፤ ከነ ከፋለ ማሃሪ ከነ ትዕዛዙ እና ከሌሎች ጋር አብሬ እየሄድሁ የታሰረችዋን ቄጤማ በአስር ሳንቲም በቁጭ ከተማ በማዞር በቀን ሃምሳ ሳንቲም ገቢ ማድረግ ጀመርሁ፡፡
ከሁለተኛ ክፍል ወደ ሦስተኛ ክፍል ብዘዋወርም ችግር ቤታችን ውስጥ ስለበረታ ትምህርቴን መቀጠል አልቻልሁም፡፡ እናታችን የደረሰባት ጉዳት ከወንድ አደለም ከሰው የማያስቀርብ ስለነበር ቀሪ ዘመኗን ተንበርክካ አረቄ በማወጣት ና አልፎ አልፎ በቅምጥ የሚሰሩ እንደ ዳጉሳ ማረም ያሉ ስራዎችን እየሰራች የለት ጉርሳችንን ለማሟላት ጥረት ብታደርግም ከቀን ቀን ህመሙ እየተሰማት መጣ፡፡
እናቴ "ሰው ቤት ገብተህ ጥጃና በግ ትጠብቃለህ። ምታመጣውን ሳንቲም አስቤ ሳይሆን ከሀብታም ቤት ጠግበህ ታድራለህ" አለችና ነፍሳሳር ከሚባል ቦታ ለአንድ አመት በዘጠና ብር ተቀጠርሁ፡፡
እዛው ያለሁበት ሰፈር ለቀን ስራ ስትመጣ እናቴ ቀን የተሰጣትን ንፍሮ በመቀነቷ ቋጥራ ˝የሰው ቤት እንጀራ ምን ቢጋገር ብዙ፤ ሳይርብ አይበላም ሳይቅበዘበዙ ፡፡ ማሙሸ እንካ ይቺን ብላ የምትለኝ እስካሁን ከውስጤ አልጠፋም፡፡
ከዚያ በኋላ
...
ሁለት አመት ከታደለ ደግነህና ከተዋበ ደግነህ፤ አንድ አመት ከምናሉ ፤አንድ አመት ከምረቴ፤ አንድ አመት ከአለበል ተሾመ ጋር ለ 6 ተከታታ አመታት ያፈራሁት ገንዘብ አልነካበትም ብላ እናቴ አጠራቅማ ጊደር ስንገዛ ይሞትብናል፤ በግ ስናረባ ይጠፉብናል ምክንያቱን አላውቅም፡፡
ለምን ብየ ፈጣሪየን እያማረርሁ እያለ እኔ ልወለድ አንድ ቀን ሲቀረኝ አጎቴ ኩላብ ወርውሮ አባቴን ደረቱን ስለወጋው"ገዳዩ ወንድምሽ የሞተውም ባልሽ አዘንሽ ቅጥ አጣ ከቤትም አልወጣ" እንደተባለው በማን ላይ ልመስክር ብላ እግሯ ወደመራት ስትሄድ ውላ ዋን ገዳም ከሚባል ቦታ በመስኖ ከለማ ቦቆሎ ማሳ ውሰጥ እኔን ስትወልደኝ የማህፀን መውረድ ስላጋጠማት በችግር እና በህመም ስተሰቃይ ኑራ በ1995 ዓ.ም በሞት ተለየችኝ።
ይህ ልብ ወለድ አደለም እውነተኛ ታሪክ ነው።
ነሐሴ 20/2013 ዓ.ም
ቤጂንግ (ቻይና)
ለሊት 4:45
አሸብር አካልነህ

“ከወንድሞቻችን ጋር መኖር የሚያስችለንን ስራ መስራት አለብን:: በተፈናቃይ ስም የሚነግዱ ፖለቲከኞች አሉ። የአማራና የትግራይ የህዝብ ለሕዝብ መድረኮችን ይበልጥ በማጠናከር የነበረውን የሕዝቦች አንድነትን መመለስ ይገባልም። በማይካድራ የተፈጸመው ግድያ ዙሪያ ወንጀለኞች መጠየቅ አለባቸው አምናለሁ። ከዚህ የተፈናቀሉ ንጹሀን ወደ ነበሩበት ቦታ መመለስ አለባቸው። የወልቃይት ጠገዴ ተወላጆችም በሱዳንና በሌሎች ሀገራት ተሰደው ይኖራሉ። ስለዚህም እርስታቸው መመለስ አለባቸው። እኔ የማምነው፣ የሕዝብን ስሜት በማዳመጥ መስራት አለብን ብዬ ነው።፡ ፖለቲከኞች በሚፈጥሩት ችግር ሳቢያ ሕዝብ ወደ ችግር ውስጥ መግባት የለበትም።”
- አቶ ጌታቸው ረዳ በወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን ተገኝተው ዛሬ ካደረጉት ንግግር
- አቶ ጌታቸው ረዳ በወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን ተገኝተው ዛሬ ካደረጉት ንግግር
Sponsored by
Surafel
10 months ago
ዋርካው ዘመሙ አሉ‼️
ገጻቸው የሚስብ ከጨረቃ የደመቁ፤
ለሰውነት ሲባሉ መልገምን የማያውቁ፤
ባለ ግርማ ሞገስ አድባር የታወቁ፤
ወደ ውስጥ ቀርበው ሰውን የሚረዱ፤
ከሸፍጥ፣ ከክፋት፣ ከተንኮል የፀዱ፤
ዋርካው ዘመሙ አሉ ደከሙ ተጎዱ፡፡
አንደበተ ርቱዕ ቃላቸው አፈ ማር፤
ለልብ የሚቀርቡ ’ሚያኮሩ በተግባር፤
ባለ እንከን አልባ ልብ ከፍካት የጠሩ፤
ሁሌ ሰላም እንጅ ጥላቻ ’ማይዘሩ፤
አንድነትን ዘርተው ሰላምን ያፈሩ፤
ዋርካው ዘመሙኮ መሸ ደና እደሩ፡፡
ማፈግፈግ አይወዱ ፈተና ቢያመጡ፤
ሀሰትን ተዋጊ መድረሻ ሚያሳጡ፤
በተሰለፉበት ድል አርገው ’ሚመጡ፤
እውነተኛ አባት ባካል በመንፈሳቸው ፤
ሕዝባቸው ሲከፋ የምትደማ ነፍሳቸው፤
ዋርካው ዘመሙ አሉ ደረሰች ጊዜያቸው፡፡
ከልኂቅ እስከ ደቂቅ ተባብሮ አለቀሰ፤
በአባትነት ወጉ ደረት እየደቃ እንባ እያፈሰሰ፤
የሰላሙ ጥላ፣ የሕዝቡ አዳራሽ የልጆቹ ፋና
ተቀዳሚ ሙፍቲ ዋርካው ዘሟልና፡፡
የሀብከ ብርሃኔ ጥላሁን
👉ከታች ያለው ስምንት የቴምር ፍሬ ፎቶ ግንቦት 13/2817 ዓ.ም ከወንድሜ ጋዜጠኛ የኑስ መሐመድ Yenus Muhammed ጋር ልንጠይቃቸው መኖሪያ ቤታቸው የሄድን ዕለት እንድመገብ የሰጡኝ ቴምር ፍሬዎች ናቸው።
የኑሴ ሁሌ በጣም አመሰግናለሁ 🙏

እንኳን ለ2018 ለኢሬቻ በአል አደረሳችሁ!
ኢሬቻ በኦሮሞ ሕዝብ ዘንድ ለፈጣሪ አምላክ ምስጋና የሚቀርብበት፤ ከሰው ጋር ሰላም፣ ፍቅር እና አብሮነት የሚከናወንበት፤ አዲስ ተስፋና ብሩህ ዘመን የሚበሰርበት በዓል ነው።
በዩኔስኮ የተመዘገው የኦሮሞ ገዳ ሥርአት አካል የሆነው የኢሬቻ በዓል የሀገራችንን መልከ-ብዝሃነት፤ ጥልቅ ዉበት ለመላዉ ዓለም ካሳዩ እና ካስተዋወቁ በዓላት መካከል አንዱ ነው።
የኦሮሞ ህዝብ ከሌሎች ወንድም እህት ህዝቦች ጋር በመሆን ባካሄደዉ መራር ትግል ከተቀዳጃቸው ድሎች መካከል አንዱ የኢሬቻ ሆረ ፊንፊኔን ክብረ በዓል በጥንታዊ ስፍራው ማክበር መቻል ሲሆን ይህም ባለፉት 7 አመታት በከፍተኛ ድምቀት ባህላዊ እሴቱን እና ቱፊቱን ጠብቆ በመዲናችን አዲስ አበባ እየተከበረ ይገኛል።
የመዲናችን አጠቃላይ ህዝብም ከወንድም እህቱ የኦሮሞ ህዝብ ጋር በአብሮነት በሚያከብረው በዚህ ታላቅ በዓል ላይ እንደወትሮው ሌሎች የአደባባይ በዓላት ሲከበሩ ለበዓላቱ ድምቀት እና ባማረ መልኩ መጠናቀቅ እንደሚያደርገው ሁሉ አብሮነትን፣ ወንድማማችነትን፣ እህትማማችነትን በሚያጸና መልኩ፤ በከተማው ውስጥ ከሚኖሩ የኦሮሞ ሕዝቦችም ሆነ በእንግድነት ከሚመጡት ወገኖቹ ጋር በመሆን በዓሉ እሴቱን ጠብቆ እንዲከበር ለማድረግ በመንገድ ጽዳት፣ በአደባባይ ማስዋብ እና በሌሎችም በርካታ በጎ ፈቃድ ስራዎች ከምንጊዜውም በላቀ መልኩ ለአገር ገጽታ ግንባታ፣ ለዘላቂ ቱሪዝም መስህብነት፣ ለከፍተኛ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ በሚያመች መልኩ በሕብረ ብሄራዊ አንድነት መንፈስ ቅድመ ዝግጅቱን አጠናቅቋል።
መላው የከተማችን ነዋሪዎች በከተማችን የአደባባይ በዓላት ሲከበሩ በዓላቱ ከዋዜማዉ አንስቶ እስኪጠናቀቁ ድረስ በተለያዩ የበጎ ፈቃድ ተግባራት በመሳተፍ እያበረከታችሁ ላለዉ እጅግ የላቀ ሚና እያመሰገንኩ፣ ይህ ተግባር ውብ እና ድንቅ ባህሎቻችን ከእኛ አልፈው ለመላዉ ዓለም የምናበረክታቸው፤ የእኛነታችን መለያ ጌጥ በመሆናቸው እንደወትሮው ሁሉ የዘንድሮውን የኢሬቻ በዓል በድምቀት ባህላዊ እሴቱን ጠብቆ ባማረ መልኩ ለማክበር ያደረግነውን ቅድመ ዝግጅት ከዋዜማው ጀምሮ በጋራ በምናከናውነው ተግባር የከተማችንን የሰላም ተምሳሌትነት፣ የህዝባችንን የሰላም ዘብነት እና እንግዳ ተቀባይነት በማረጋገጥ ይሆናል።
በድጋሚ እንኳን ለ 2018 ኢሬቻ ሆረ-ፊንፊኔ ክብረ በዓል አደረሳችሁ!
ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ
Baga Kabaja Ayyaana Irreechaa bara 2018tin Isin gahe, nuun gahe!
Ayyanni Irreecha Ummanni Oromoo sirana waaqa umaa umaatiif galata ittin dhiyessudha.
Jaarmiyaalee Sirna Gadaa; kan Yuuneeskon Galmaahe, keessaa tokko kan ta'ee Ayyaanni Irreechaa calaqqeewwan bifa danuu, Bareedinaa fi Hawwata Addaa, Adunyaaf agarsiisan keessaa isa tokko yoo ta'u, mallattoo Nageenyaa, Kan jaalalaa, Kan waloominaa, Araara fi sirna
Injifannoowwan Uummatni Oromoo, Uummattoota Obbolaa, Sabaaf sablammoota hunda waliin ta'uun Qabsoo hadhaahaa adeemsiseen goonfate keessaa inni tokko Ayyaana Irreecha Hora Finfinnee iddoo ganamaa isaatti deebihee akka kabajamu gochuu isaati. Kanaanis uummatni Oromoo waggootan 7n darban Magaalaa Finfinnee keessatti Karaa Seenaa, Aadaa, fi Duudhaa isaa eeggateen sadarkaa olaanan Sabaaf Sablammoota hunda waliin kabajaa jira.
Aadaa Waloon jiraachuu cimaa, fi waldanda'uun kan beekkaman jiraattotni Magaalaa Finfinnees, Ayyaana Obboleeyyan isaa Uummatni Oromoo Kabaju kana akkuma kana dura ayyaanotni uummataa kanneen biroo bifa hawwataa ta'een karaa nagaahan kabajamii akka xumuramaniif hijjechaa ture, Bifa Obbolummaa, fi Waliin jireenya keenya dagaagsu fi itichuu danda'uun uummata Oromoo Magaalaa keenyaa fi keessummootaa fageenya irraa dhufan waliin ta'uun, Ayyaanichi Duudhaa isaa eeggatee akka kabajamuuf, Hojii qulqullinaan, Adabaabayiiwwan adda addaa Bareechun, kenna tajaajilaani, fi hojiilee gocha gaarii adda addaatin kan kanaan dura ture caalatti bifa Hawwata turizimii walitti fufaa fi Sochii diinagdee olaanaf oolun Afuura Obbolummaa Sabdaneessummaan socho'uun kabajuuf qophii isaa xumuree jira.
Jabana kana Jiraattotni Magaalaa Keenyaa hundi Ayyaanotni Uummataa kanneen Adabaabayii irratti kabajaman hunda jala bultii irraa kaasee hanga xumuramanitti hojiilee Gocha gaarii adda addaa irratti hirmaachun nageenya fi miidhagina isaaniif shoora olaanaa waan taphattaniif maqaa koo fi maqaa Bulchiinsa Magaalaa Finfinneetin isin galateeffachuun barbaada.Hanga xummura ayyanichattii gocha fakkenyummaa kana cimsuin akka ittifuftan amantaan qaba.
Irra deebihuun, Baga Kabaja Ayyaana Irreechaa Bara 2018tin isin gahe!
Waaqayyo Itoophiyaa fi Uummattoota ishee haa eebbisu!

ያልተነገረው እዉነታ !
አማርኛ የሚጠቀምበት ፊደል 78.8% የግዕዝ ነዉ !
በዓለም ከ7000 በላይ ቋንቋዎች በመግባቢያነት እንደሚያገለግሉ ይነገራል። በዓለም ላይ ከሚገኙ ቋንቋዎች 6 በመቶው የሚሆኑትን 94 በመቶ የዓለም ህዝብ በመግባቢያነት ይጠቀምባቸዋል።
እንደ ሳይንሳዊ ጥናት አድራጊ ምሁራን አባባል፤ የሰው ልጅ ፊደልን በሚሊዮኖች ዓመታት የዕድገት ደረጃዎች ለውጡ ቋንቋውን ከሥልጣኔ ዕድገቱ ጋር አብሮ እያራመደ ሲመጣ ያገኘው ውጤቱ መሆኑን ይገልፃሉ
በእነዚህ ሥዕላዊ ምልክቶች (Pictographic Symbols) ከመጠቀም አልፎም ወደ ጽሑፍ ቋንቋ (Writing Language) በቅቷል የሚል ማብራሪያ ይሰጣሉ፡፡
የሳይንሳዊ ጥናት ተመራማሪዎች ከላይ እንደተገለጸው፤ የሰው ልጅ ለንግግሩ ጽሑፋዊ መግለጫ የሆነውን ፊደል መፍጠር እንደቻለ አረጋግጠዋል፡፡
የግብፅን ሂሮግሊፍክ (ሥዕላዊ ጽሑፍ) መሠረት በማድረግ፣ ከክርስቶስ ልደት በፊት 1800-1500 በሴማውያን ከተፈለሰፈው ጥንት ሲናዊ (Proto - sinaific) ፊደል፣ በርካታ ሌሎች ፊደላት መገኘት ችለዋል፡፡ ከተፈለሰፉት መካከል ግን እንደ ዐረብኛ፣ ዕብራይስጥኛና ኢትዮጵያዊኛ ያሉት እናት ፊደላቸውን መምሰል እየተውና እየራቁ በመሔድ የተገኙ ናቸው፡፡
እዚህ ላይ ግን አንድ ልንገነዘበው የሚገባን ነገር ይኖራል፡፡ ሃይማኖታዊም ሆነ ሳይንሳዊ አመለካከት ያላቸው ሁለት ክፍሎች፤ በፊደል ታሪካዊ አመጣጥ ላይ የተለያየ አቀራረብ ቢኖራቸውም በአጠባበቅና በአጠቃቀም በኩል ግን በአብዛኛው አንድነት ያላቸው መኾኑን ልንረዳ ይገባል፡፡
ከላይ እንደተመለከትነው፤ የሰው ልጅ ፊደልን ከማግኘቱ በፊት ለፊደል መፈልሰፍ መሰረት የሆኑት ሥዕላዊ ምልክቶችን ይጠቀም እንደነበረ ተገንዝበናል፡፡ እነዚህ ሥዕላዊ ምልክቶች የግብፅ ሂሮግሊፊክ እና የመሶጶታሚያው ኩኒፎርም በመባል የሚታወቁ ናቸው፡፡ በዓለም ውስጥ ያሉት ፊደሎችም በሙሉ ከእነዚህ ሥዕላዊ ምልክቶች የተገኙ መሆናቸው ተረጋግጧል፡፡
የግዕዝ ፊደል የሚባሉት 26ቱ ድምፆችና አራቱ ዲቃሎች ባለቤት የሆነችው
ሀ፣ ለ፣ ሐ፣ መ፣ ሠ፣ ረ፣ ሰ፣ ቀ፣ በ፣ ተ፣ ኀ፣ ነ፣ አ፣ ከ፣ ወ፣ ዐ፣ ዘ፣ የ፣ ደ፣ ገ፣ ጠ፣ ጰ፣ ጸ፣ ፀ፣ ፈ፣ ፐ እንዲሁም ኰ፣ ጐ፣ ቈ፣ ኈ ፡፡
ኢትዮጵያ በጥንታዊው የሥነ ጽሑፍ ታሪክ በዓለም የመጀመሪያውን ረድፍ የምትይዝ አገር ያደርጋታል ፡፡
በእንግሊዝ፤ በፈረንሳይ፣ በጀርመን ዛሬ የሚፃፉት ሁሉ ከኢትዮጵያ ሥነ-ፅሁፍ በኋላ የመጡ ናቸው፡፡ ከኢትዮጵያ ሥነ ጽሑፍ ጋር የሚወዳደሩት ትልልቆቹ የግሪክ፣ የአራማይክ፣ የላቲን፣ የመሳሰሉቱ ናቸው፡፡ …” በማለት ኢትዮጵያን ታላቅ ከሚያደርጓት ሀብቶቿ አንዱ ይኸው የግዕዝ ሥነ ፅሑፍ መሆኑን በግዕዝ ቋንቋና ፊደል በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያንና ቅዱሳት መጻሕፍትዋ ላይ የጻፏቸውን ጨምሮ የአያሌ መጣጥፎችና መጻሕፍት ደራሲ የሆኑት ምሁር ፕሮፌሰር ኤፍሬም ይስሐቅ በሐመር መጽሔት ሐምሌ/ነሐሴ ፲፱፻፺፮ ዓ.ም እትም፤ “…ላይ በስፋትና
በዝርዝር አስቀምጠዋል ።
የሰው ልጅ አለኝታውና ማዕረጉ፣ ሞገሱና ኩራቱ ታሪኩ ነው፡፡ ታሪክ ደግሞ ታሪክነቱን ሊያገኝ የሚችለው የሰው ልጅ ራሱ ከትውልድ ወደ ትውልድ ጠብቆ በሚያስተላልፋቸው ወጐቹ፣ ቋንቋዎቹ፣ አፍአዊ ኪነቃሎቹ፣ ፊደልና ሥነ ጽሑፎቹ አማካኝነተ መኾኑ አያከራክርም፡፡ ታሪኩን በራሱ ፊደል መዝግቦ ከትውልድ ወደ ትውልድ የሚያስተላልፍ አገር ደግሞ በእጅጉ የታደለ ነው፡፡ የሚሉት የ “ብቸኛው አፍሪካዊ ፊደል (The Sole African Alphabet) መጽሐፍ አቅራቢ በኢትዮጵያ ፊደል ላይ ጥልቅ ግንዛቤ እንዳላቸውና ከፍተኛ ጥናት እንዳካሄሔዱም መጽሐፋቸው የሚመሰክርላቸዉ ዶክተር በዚሁ ከላይ በተገለጸው መጽሐፋቸው እስከ ገጽ 10 ድረስ የኢትዮጵያ ፊደል ከ3000 ዓመታት የማያንስ ዕድሜ ያለውና በዓለም ላይ በቀደምትነት ከተፈለሰፉት ፊደላት መሐከል መሆኑን በመጥቀስ ያሞካሹታል፡፡ ታድያ! ይህን ያህል ያደነቁትንና ከኢትዮጵያም አልፈው አፍሪካዊ ፊደል ብለው ክብር የሰጡትን ፊደል እንዴት እንዳልነበረ ለማድረግ ተፈለገ ? ያሰኛል፡፡
በሰለጠነው ዓለም በቋንቋህ አስተርጓሚ ቆሞልህ ታወራለህ ለአስተርጓሚው መንግስት ከፍሎልህ አንተ በነጻ ታወራለህ ቋንቋ መግባቢያ ስለሆነ አትነፈግም ወይም ቋንቋ ስለማትችል አናክምህም አይሉም በትርጉም ያክሙሃል እኛ የተውነውንና የቀበርነውን የኛን ፊደል ጀርመኖች አጥንተው የኛን መጻህፍት ከትራሳችን ስር ወስደው ተርጉመውና ተራቀው ለዓለም በሚያቀርቡት መድኃኒት አንቱ ተብለውበታል በዩንቨርሲቲዎቻቸው በስፋት በማስተማር ተዝቆ የማያልቅ እውቀትን ያፍሱበታል ።
በኛ ሀገር ግን በዚህ ክልል ይህ ቋንቋ እንዳይነገር ይህ ፊደል ልጆች እንዳያውቁት እያሉ ከፍተኛ ጥላቻን በመስበክ እነሱ አቀላጥፈው የሚናገሩትን ቋንቋ ሚድያ ከፍተው የሚነግዱበትን ቋንቋ ልጁን እንዳትማር እንዳታውቅ ብሎ ትውልድን ማደንቆር ምን ይሉት ስልጣኔ ይሆን?
እንዲህ ትውልድን ለመግደል ወንድም ከወንድሙ ጋር እንዳይግባባ ማድረግ ህሊናን ከማጣት ውጪ ሌላ ምን ይባላል ? የሚለውን ብንተወዉ እንኳን ቋንቋን አለማወቅ ግን ብዙ ጉዳት አለው ያሉና ቋንቋን ማወቅ ማንን ሲጎዳስ አየን? የሚሉ በርካታ ሀገራት ግዕዝን እያስተማሩ ይገኛል ።
የጀርመን የቋንቋ ጥናት ተቋም፣ግዕዝን እስከ ሦስተኛ ዲግሪ ሲያስተምር በዓለም ላይ መነቃቃትን ፈጠረና ግዕዝ ዓለማአቀፋዊ ትኩረት ሳበ፡፡ በ 2008 ዓም የካናዳው ቶሮንቶ ዩኒቨርሲቲ ግዕዝን ከዕብራይስጥ፣ከግሪክ ፣ ከፅርዕ፣ከአራማይክ፣ከላቲን ፣ ከአረብኛና ሌሎች ጥንታዊ የዓለም ቋንቋዎች ጋር እያስተማረ ነው፡፡
የምስራቅ አፍሪካን ታሪክና ባህል ለማጥናት ግዕዝ ተመራጭ ሆኗል፡፡በሚያዚያ 2009 ዓ ም የአሜሪካው ዋሽንግተን ዩኒቨርሲቲም ግዕዝን ማስተማር መጀመሩን ይፋ ባደረገ በጥቂት ጊዜ ውስጥ ግዕዝን ለመማር ተማሪዎች ሰልፍ ይዘው ታይተዋል፡፡
በዋሽንግተን ዩኒቨርሲቲ የግዕዝ መምህር የሆኑት ፕሮፊሰር ሀምዛ ዛፊር”ግዕዝ የአፍሪካ ጉዳዮችን ብቻ ሳይሆን የዓለም ሃይማኖቶችን አመጣጥ ለማጥናት ተመራጭ ቋንቋ ነው”ይላሉ፡፡
ከዚህ በተጨማሪ ግዕዝ፣ለባህላዊ መድሐኒት ቅመማ፣ለዘመን ቆጠራ ፣ለሂሳባዊ ስሌት፣ ለሥነ ፈለክ ምርምር፣ስለ ከበሩ ማዕድናት ጥናትና ምርምር፣ስለ ማይታወቁ ዓለማትና በውስጣቸው ስላሉ ልዩ ልዩ ፍጥረታት ምርምር ወዘተ አጋዥ ቋንቋ ነው፡፡
“ፊደል፡- ንግግርን በጽሑፍ ለማስፈር የሚያስችልና ድምጽን ወክሎ የሚቆም ምልክት (ለምሳሌ ሀ፣ ለ …) በማለት የምንጠራቸው ሆሄያት ከሀ-ሆ ወይም ከሀ-ፐ) ያለው የፊደላት ስምና መልክ ወይም ቅርፅ” ከግእዝ መሆኑን በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የታተመው የኢትዮጵያ ጥናትና ምርምር አማርኛ መዝገበ ቃላት ፊደል የሚለውን ማንበብ በቂ ነዉ ።
አንድ ቋንቋ ወይም አገር የራሱ ፊደል አለው ብሎ መናገር የሚቻለው የቋንቋውን ድምፆች የሚወክሉ ሆሄያትን የያዘ ፊደል መፈልሰፍ ሲችል ነው፡፡ ስለሆነም አማርኛ የሚጠቀምበት ፊደል 78.8% የግዕዝ በመሆኑ ፊደሉ የአማርኛ ነው ማለት ይከብዳል፡፡ እናም ግዕዝን አንፈልግም ስንል የአማርኛንም ቋንቋ መጥላታችን ነዉ
አማርኛ ቋንቋ ብልጥ ነው። ፊደል ባይኖረውም ፊደልን የተዋሠው ከግዕዝ ነው። ብዙ ሠዎች አማርኛ የራሡ ፊደል ያለው ይመስላቸዋል። ነገር ግን አብዛኛዎቹን ፊደሎች የተዋሰው ከሀገሩ ልጅ ከግዕዝ ቋንቋ ነው። የተወሠኑ ፊደሎችን ብቻ ለራሡ ድምፅ ጨመረ። የተቀሩት የግዕዝ ቋንቋ ፊደሎች ናቸው። በተውሶ የዳበረ ቋንቋ ነው።
ለነገሩ ትግርኛም፣ አደርኛም፣ ጉራግኛም ፊደሎቻቸውን የተዋሡት ከግዕዝ ነው። ሌላ ሀገር ሆና ዛሬ የተገነጠለችው ኤርትራ ሣትቀር የቋንቋዋ ፊደል የግዕዝ ነው። እነዚህ ቋንቋዎች የተዋሡት ከጐረቤታቸው፣ ከቅርባቸው ነው። ሩቅ አልሄዱም። በፊደል ሕግ ሩቅ መሔድ ብዙ አያዋጣም። አንዳንድ የኢትዮጵያ ቋንቋዎች የላቲን ፊደልን በመጠቀማቸው የተነሣ ዛሬ ተጐጅዎች ሆነዋል።
ተጐጂ የሆኑበት ምክንያት የላቲን ፊደሎች በውስጣችው አናባቢ (Vowel) የላቸውም። በላቲን ተነባቢው (Consonant) ሲፃፍ አናባቢው አብሮ ነው የሚፃፈው። ስለዚህ የላቲን ፊደል የተጠቀሙ የሃገራችን ቋንቋዎች አንድ ነገር ለመፃፍ ሲፈልጉ በጣም ረጅም ይሆንባቸዋል። ለምሣሌ
በአማርኛ በላቲን
አበበ Aababa
አንዱ ቃል በእጥፍ ይጨምራል። ስለዚህ ፍቅር እሰከመቃብርን ወደ ላቲን ወደሚጠቀሙ የሃገራችን ቋንቋዎቸ ብንተረጉመው ብዙ ቅጽ መጽሐፍ ሊወጣው ይችላል። የግዕዝ ፊደሎች በውስጣቸው አናባቢውን (Vowel) ሰለሚይዙ አፃፃፋቸው ስብሰብ ይላል። ቅለትም አለው።
ለማንኛዉም ግዕዛውያን ስለምን የራሳችን ፊደል እያለን በማይገባ ጥላቻ የኛነታችንን ሀብት ጥለን በሰው ሀገር ፊደል እንጎለዳደፋልን?ሰከን ብሎ የሚጠቅመውን በቅን ልቦና ማየትና ይዞ መጓዝ ለሀገርም ለትውልድም ይጠቅማልና እመለስበታለሁ ።
የኔታ ቲዩብ በታዴ የማመይ ልጅ

Comments