Logo
FIDEL POST NEWS
ወንዶች የፍቅር አጋራቸውን ግፋ ቢል ስንት ደቂቃ በትኩረት ያዳምጧቸዋል ?

​በብሪታንያ የሚገኘው ላድብሮክስ የተባለ ተቋም በ2,000 ሰዎች ላይ ባደረገው ጥናት፣ ወንዶች ለማዳመጥ ያላቸውን አቅም የሚመለከቱ አስገራሚ ውጤቶችን ይፋ አድርጎ ነበር።

በጥናቱ መሰረት፣ ወንዶች ለሚስቶቻቸው ወይም ለፍቅረኞቻቸው ቢበዛ ለ6 ደቂቃ ብቻ ነው በትኩረት ማዳመጥ የሚችሉት፤ ከዚያ በኋላ ግን ሃሳባቸው ይበታተናል።

​በአንጻሩ ስለ ስፖርት፣ ስለ መኪና ወይም ስለ ግላዊ ጉዳዮች ከወንድ ጓደኞቻቸው ጋር ሲያወሩ እስከ 15 ደቂቃ ድረስ ሙሉ ትኩረታቸውን ሰጥተው ማዳመጥ እንደሚችሉ ተገልጿል።

በተለይ በወሬው መሃል ስለማያውቋቸው ሰዎች፣ ስለ ልብስ ወይም ስለ ታዋቂ ሰዎች የሚነሳ ከሆነ የወንዶች ትኩረት በፍጥነት እንደሚቀንስ ጥናቱ አመልክቷል።

​ምንጭ፦ በላድብሮክስ የተደረገ ጥናት
5 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.