Logo
Getu Temesgen
ዋርካው ዘመሙ አሉ‼️

ገጻቸው የሚስብ ከጨረቃ የደመቁ፤
ለሰውነት ሲባሉ መልገምን የማያውቁ፤
ባለ ግርማ ሞገስ አድባር የታወቁ፤
ወደ ውስጥ ቀርበው ሰውን የሚረዱ፤
ከሸፍጥ፣ ከክፋት፣ ከተንኮል የፀዱ፤
ዋርካው ዘመሙ አሉ ደከሙ ተጎዱ፡፡

አንደበተ ርቱዕ ቃላቸው አፈ ማር፤
ለልብ የሚቀርቡ ’ሚያኮሩ በተግባር፤
ባለ እንከን አልባ ልብ ከፍካት የጠሩ፤
ሁሌ ሰላም እንጅ ጥላቻ ’ማይዘሩ፤
አንድነትን ዘርተው ሰላምን ያፈሩ፤
ዋርካው ዘመሙኮ መሸ ደና እደሩ፡፡

ማፈግፈግ አይወዱ ፈተና ቢያመጡ፤
ሀሰትን ተዋጊ መድረሻ ሚያሳጡ፤
በተሰለፉበት ድል አርገው ’ሚመጡ፤
እውነተኛ አባት ባካል በመንፈሳቸው ፤
ሕዝባቸው ሲከፋ የምትደማ ነፍሳቸው፤
ዋርካው ዘመሙ አሉ ደረሰች ጊዜያቸው፡፡

ከልኂቅ እስከ ደቂቅ ተባብሮ አለቀሰ፤
በአባትነት ወጉ ደረት እየደቃ እንባ እያፈሰሰ፤
የሰላሙ ጥላ፣ የሕዝቡ አዳራሽ የልጆቹ ፋና
ተቀዳሚ ሙፍቲ ዋርካው ዘሟልና፡፡
የሀብከ ብርሃኔ ጥላሁን
👉ከታች ያለው ስምንት የቴምር ፍሬ ፎቶ ግንቦት 13/2817 ዓ.ም ከወንድሜ ጋዜጠኛ የኑስ መሐመድ Yenus Muhammed ጋር ልንጠይቃቸው መኖሪያ ቤታቸው የሄድን ዕለት እንድመገብ የሰጡኝ ቴምር ፍሬዎች ናቸው።

የኑሴ ሁሌ በጣም አመሰግናለሁ 🙏

10 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.