Logo
SeledaPost
"የሕወሓትን መንገድ መከተል የበለጠ ጥፋት ያስከትላል” የኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ ማስጠንቀቂያ

የጥምቀት በዓል በወልቃይት ዞን በተከዜ ወንዝ ዳርቻ ተከብሯል። በዚህ ክብረ በአል ላይ ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ ተገኝተው ንግግር ያደረጉ ሲሆን፤ ማሳሰቢያ እና ማስጠንቀቂያ አዘል መልእክቶችን አስተላልፈዋል።

የወልቃይት ጠገዴ ሕዝብ አማራዊ ማንነቱን በህግ አግባብ ለማጽናት እየሰራ ነው ሲሉ ቀጥለው፤ ዛሬም እንደትናንቱ አንድነታችን አጠናክረን ልንቀጠል ይገባል ብለዋል።

የወልቃይት ጠገዴ ሕዝብ እውነትን ይዞ እየታገል ያለ ሕዝብ በመሆኑ ፍትህ ወዳድ ኢትዮጵያዊያንና የአለም ሕዝብም እውነታውን እየተረዱ ለነጻነትና ለአማራዊ ማንነታችን ስንል የከፈልነውን የማይካድራ የጅምላ ጭፍጨፋ ያውቃሉ ብለዋል።በዚህም በቅርቡ በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኧርቪን ማሲንጋ በቦታው በመገኘት ያደረጉ ውይይት ማሳያ ነው ብለዋል።

የአማራና የትግራይ ህዝብ በኢትዮጵያ ታሪክ ክፉውንም ደጉንም አብሮ ያሳለፈ ወንድማማች ህዝብ ነው ብለዋል። በአብሮነት ለመኖር ከእኛ ከወንድሞቻችሁ ጋር በመነጋገርና በመወያየት እንጂ የህወሓትን መንገድ መከተል የበለጠ ጥፋት ያመጣል ሲሉ ገልጸው የወልቃይት ጠገዴ ህዝብ ጎንደሬ አማራነቴን አትቀሙኝ አለ እንጂ ከትግራይ ህዝብ ጋር አብረን አንኖርም አላለም ሲሉ ተናግረዋል።

"ጥምቀትን በተከዜ ወንዝ ዳርቻ ማክበራችን እንቀጥላልን፣ አስተዳደራችን አጠናክረን ነጻነታችን በህግ አግባብ እናጸናለን" የሚጠናከር እንጂ የሚፈርስ አስተዳደር የለም ብለው አንዳንድ አካላት ለፖለቲካ ፍጆታ ሲሉ የሚያናፍስሱትን የተለመደ የአሉቧልታ ወሬ ልናዳምጥ አይገባም ብለዋል።

seledadotio
seledadotio
7 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.