ቅዱስ ዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ ከክፉ ነገር ሁሉ ይከልለን፤ ምለሰጃው እና ረድኤቱም አይለየን🙏
የተወለደው በገሊላ አውራጀ በቤተ ሳይዳ ነው፣ አባቱ ዘብዴዎስ ይባላል ገና በወጣትነቱ ዘመን ከወንድሙ ከያዕቆብ ጋር ለሐዋርያነት ከተጠራበት ጊዜ ጀምሮ የጌታውን እግር ተከትሎ አድጓል ቅዱስ ዮሐንስ፡፡ ወልደ ዘብዴዎስ፣ ወልደ ነጎድጓድ፣ ነባቤ መለኮት /ታኦሎጎስ/፣ ቁጽረ ገጽ በመባል ይታወቃል። ወንጌላዊው ቅዱስ ዩሐንስ ከ12ቱ ሐዋርያት አንዱ ሲሆን የመጀመሪያው ወጣት የመጨረሻው ሽማግሌ ሐዋርያ እሱ ነበር፡፡ የጌታ ደቀ መዝሙር ከመሆኑ በፊት የመጥምቀ መለኮት የቅዱስ ዮሐንስ ደቀ መዝሙር ከነበሩት አንዱ ነው፡፡ ለጌታችን ባሳየው ልዩ ቀረቤታና ፍቅር ምክንያት “ፍቁረ እግዚእ” የሚል ስያሜ አግኝቷል፡፡ ፍቅሩንና ታማኝነቱንም ጌታ በተሰቀለ ጊዜ “እሱን ያገኘ ያገኘኛል” ብሎ ሳይፈራ ከመስቀሉ ስር በመዋል አስመስክሮአል፡፡
በዩሐንስ 19÷26 እንደተጻፈው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ላይ ሳለ በመጨረሻዋ ሰዓት ቅዱስ ዮሐንስን ሲያየው እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን “እነኋት እናትህ ታጽናናህ” ብሎ ሰጥቶታል፡፡ እኛንም እመቤታችሁ እናታችሁ ቅድስት ድንግል ማርያም ናትና ታጽናናችሁ፣ ተስፋ አለኝታ ትሁናችሁ ማለቱ ነው፡፡ እርሷንም “እነሆ ልጅሽ፣ ይርዳሽ ያጽናናሽ” ብሎ ለእኛ ለክርስቲያኖችም በቅዱስ ዮሐንስ አማካኝነት ለእመቤታችን መስጠቱን እናያለን፡፡ እመቤታችን በቤተ ዮሐንስ እንደኖረች ሁሉ በልበ ምእመናንም አድራ በሃይማኖት የምታጸና፣ ምግባረ ሃይማኖትን፣ ሕገ ትሩፋትን የምታሰራ፣ ከልጅዋ ከወዳጅዋ ከመድኃኔዓለም ክርስቶስ ድኀነተ ስጋንና ድኀነተ ነፍስን፣ በረከተ ስጋንና በረከተ ነፍስን የምታሰጠን መሆንዋን ነው፡፡
ቅዱስ ዮሐንስ እንደ ጌታው ቃል እመቤታችንን ወደ ቤቱ ይዟት ሄደ ከእርሱ ጋርም አስራ አምስት ዓመት ተቀምጣለች፡፡ ሐዋርያው የጌታ ትንሣኤ በተነገረ ጊዜ ቅዱስ ጴጥሮስን ቀድሞ ከመቃብረ ክርስቶስ እንዲገኝ ያደረገው የፍቅሩ ጽናት ነበር፡፡ የቅዱስ ዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ የድንግልና ሕይወትም ረቂቁን ምስጢረ መለኮት ለማየት አስችሎታል፡፡ ምስጢረ ሥጋዌን አስተካክሎ አደላድሎ በመጻፍ አምልቶ አስፍቶ አስተምሯል፡፡ የፍቅረ እግዚአብሔርንና የፍቅረ ቢጽን ጠቃሚነት በስፋት ጽፏል፡፡ ሰማያትን ሰንጥቆ የሚበር ንስር፣ ልዑለ ስብከት፣ ምሥጢራትን የሚያይ ወንጌላዊ ዮሐንስ፣ ነገሩ ሁሉ በምስጢረ መለኮት የተቀመመ ነው፡፡ ገዳማውያንም ቅዱሳንን አብነት አድርገው ስለ ክርስቶስ ፍቅር ዓለምን ንቀው ይመንናሉና ገዳማቸውን እንደግፍ በዓታቸውን እናጸና፡፡
ድጋፍ ለማድረግ፦ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም
ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391
ወይም
አቢሲኒያ ባንክ
141029444
የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444

1 month ago