Logo
Getu Temesgen
ውድ ኢትዮጵያውያን ለሐገር ባለውለታው ለታላቁ ደራሲ ሐብታሙ አለባቸው ድጋፍ እናድርግለት

(ይትባረክ ዋለልኝ)
#ethiopia | ታላቁ ደራሲ ሐብታሙ አለባቸው እንዴት እንደዚህ ሊሆን ቻለ? በማለት በቁጭት ለእርሱ ያላቸሁን አድናቆትና ፍቅር መሰረት በማድረግ ለዚህ የሃገር ባለውለታ ደራሲ ልንደርስለት ይገባል ብላችሁ ባለፉት ሁለት ቀናት በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ገንቢ ሐሳባችሁን ስታካፍሉ ለነበራችሁ ውድ ኢትዮጵያውያን በቅድሚያ እጅግ የከበረ ምስጋናዬን በቤተሰቡና በራሴ ስም ከልብ ላመሰግናችሁ እወዳለሁ::

እኔ ጋዜጠኛ ይትባረክ ዋለልኝ እባላለሁ: የደራሲ ሀብታሙ አለባቸው የ20 ዓመት ጓደኛ ነኝ:: ሐብታሙ አለባቸው እኔ ሐብትሽ ነው የምለው ጓደኛዬ ብቻ ሳይሆን ወንድሜ ነው:: የእኔንና የሐብትሽን የቅርብ ጓደኝነት የሚያውቁ በርካታ ሰዎች የመቀሌ ዩንቨርሲቲ መምህራን : የመንግስት ኃላፊዎች: ጋዜጠኞች ጉዳዩን የሰሙ ሁሉ ዛሬ ድረስ ከተለያዩ የሐገሪቱ ክልሎች የሐብትሽ ጉዳይ አስጨንቋቸው ሲደውልልኝ ነው የቆዩት::

ከብዙዎቹ ደዋዮች መካከል ጋዜጠኛናደራሲ ቴዎድሮስ ተ/አረጋይ እና ጋዜጠኛ ሁሴን ከድር ደውሉ ባቢ አንድ ነገር ማድረግ አለብን አሉኝ :: " እኔም እሺ ሐብታሙ ምንም ቢቸግረው እርዱኝ የማይል ሰው እንደሆነ ባውቅም :: ደጋግሜ ወደ ሐብትሽ ጋር ስልኩ ዝግ ነው:: ወዲያው ቤተሰቦቹን በቅርብ ስለማውቃቸው መጀመሪያ ብዙ ጊዜ ከጎንደር አዲስ አበባ እየተመላለሰ በሐብትሽ ጉዳይ ከእኔና ከሌሎች ወዳጆች ጋር እላይ እታች ለሚለው ምርጥ ወንድሙ ሙሉቀን አለባቸው ጋር ደወልኩ :: በተመለከትነው ጉዳይ ሐዘን ቢሰማንም ይህን ሁኔታ እንደመልካም አጋጣሚ ቆጥረን ምን እናድርግ የሚለው ጉዳይ ላይ ተነጋገርን::ወንድሙ ሙሉቀን የሚኖረው ጎንደር ስለሆነ በማግስቱ እርሱ ከጎንደር ወደ አዲስ አበባ እንዲመጣ ተነጋገርን:: ድጋፍ አድርጉልኝ የሚል ስብዕና ባይኖረውም ሐብትሽ የኢትዮጵያን ሐብት ነውና እርሱን መደገፍ እንደ ሐገር ግዴታ ስላለብን ብለንጉዳዩን ለህዝብ አሳውቀን ድጋፍ የሚያስፈልገውን ሁሉ ለህዝብ እናሳውቃለን በሚለው ሐሳብ ላይ ተነጋግረ በመስማማት ተለያየን:: በማግስቱ ሐሙስ ጠዋት ሙሉቀን አዲስ አበባ ገባ::

ከዚያም ለሐብትሽ መደረግ የሚገባቸውን ተግባሮች ቅደም ተከተል በማውጣት ከትላንት ጀምሮ ስራ ሲሰራ ቆይቷል:: በዚህም ቅድሚያ መደረግ ያለበት ጉዳይ ላይ ስራ ተጀምሯል:: ሐብታሙ አለባቸው ድጋፍ ለማድረግ
ለዚህ አላማ ትላንት በሁለት ቤተሰቡ ሙሉቀን አለባቸው እና መሰረት መኮንን ስም ትላንት የባንክ አካውንት ተከፍቷል::በአሁኑ ወቅት ሐብትሽ ሕክምናውንእየተከታተለ ይገኛል::

ሐብትሽ ደራሲ ብቻ አይደለም:: ልታይ ልታይ የማይል እጅግ አዋቂ እና በተማሪዎቹ የተወደደ ጎበዝ ምምህርም ነው:: በሰው ዘንድ እጅግ የተወደደ ደግና ልበ ስሱ ሰው ነው:: ሁል ጊዜ የሚጨነቀው ስለሚፅፈው ሐሳብ :: የሚጨነቀው ስለ ሐገሩ ነው:: ስለ ራሱ ህይወት ሳይሆን ስለተቸገሩ ኢትዮጵያውያን ነው ጭንቀቱ:: ሐብትሽ ለተቸገሩ ገንዘቡን ብቻ ሳይሆን ንብረቱን አውጥቶ የሚሰጥ አስደናቂ ስብዕና ያለው ሰው ነው:: ሐብትሽ ምንም ቢቸግረው እራሱን ይጎዳል እንጂ ቸገረኝ የማይል አስገራሚ ሰው ነው::

በሐገር ውስጥና በመላው ዓለም የምትኖሩ ውድ ኢትዮጵያውያን ወንድማችን ደራሲ ሐብታሙ አለባቸው ዛሬ የሁላችንን ድጋፍ ይሻል::በመሆኑም በዋናነት ሐብትሽ ተረጋግቶ የሚኖርበት አነስተኛ ቤት የሚያገኝበትንና ለመቋቋሚያ የሚሆን የገንዘብ ድጋፍ እንድናደርግለት ስል በቤተሰቡ በጏደኞቹና በራሴ ስም ከልብአመሰግናለሁ:: ለሐብትሽ ትንሽ ድጋፍ ብናደርግለት ለሐገር ዋጋ የሚጠቅሙ በርካታ ስራዎቹን ነገ ማግኝት እንደምንችል ምንም ጥርጣሬ የለኝም::ሰይፉ ፋንታሁንም በታላቁ ደራሲ በሐብትሽ ሁኔታ እጅግ ተጨንቆ በታላቅ ኃላፊነት ስለሐብታሙ አለባቸው አጠቃላይ ሁኔታ ትላንትና ከወንድሙ ሙሉቀን አለባቸው ጋር ቆይታ አድርጏል:: እሁድ ምሽት ፕሮግራሙ ይለቀቃል::

ለታላቁ ደራሲ ሐብታሙ አለባቸው ድጋፍ ለማድረግ ለዚህ አላማ ትላንት በሁለት ቤተሰቡ ሙሉቀን አለባቸው እና መሰረት መኮንን ስም በተከፈተው የባንክ አካውንት ድጋፍ ማድረግ ትችላላችሁ::

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ :-1000735581396
ሙሉቀን አለባቸው እና መሰረት መኮንን
ስልክ ቁጥር:- + 251 918063957

ማሳሰቢያ
=====
ለደራሲ ሐብታሙ አለባቸው ከዚህ የባንክ አካውንት ውጪ በቲክቶክም ሆነ በየትኛውም መንገድ የተከፈተ የድጋፍ ማሰባሰቢያ የለም:: #share በማድረግ እንተባበር

8 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.