ፓኪስታን በኢራን ጦርነት ዙሪያ የሳዑዲ፣ የቱርክ እና የግብፅ ከፍተኛ ዲፕሎማቶችን ለስብሰባ ጠርታለች
የፓኪስታን መንግስት በአሜሪካ እና በኢራን መካከል እንደ አስታራቂ ሆኖ እየሰራ ሲሆን፤ በኢስላማባድ ውይይቶች እየተካሄዱ ነው።
ከሳዑዲ አረቢያ፣ ከግብፅ እና ከቱርክ የተውጣጡ ከፍተኛ ዲፕሎማቶች በኢራን ላይ እየተካሄደ ባለው የአሜሪካ-እስራኤል ጦርነት ዙሪያ ለመወያየት እና ግጭቱን ለማርገብ ከፓኪስታን አቻቸው ጋር ለሁለት ቀናት ለሚቆይ ውይይት በኢስላማባድ ተሰባስበዋል።
የፓኪስታን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኢሻቅ ዳር ፤ኢራን በፓኪስታን ሰንደቅ ዓላማ የሚጓዙ "ተጨማሪ 20 መርከቦች" ወይም በቀን ሁለት መርከቦች በሆርሙዝ የባህር ወሽመጥ በኩል እንዲያልፉ መፍቀዷን አስታውቀዋል።
የፓኪስታን ጠቅላይ ሚኒስትር ሸህባዝ ሻሪፍ እንደተናገሩት፤ ለኢስላማባዱ ውይይት እንደ ዝግጅት አካል "ከወንድሜ ከኢራኑ ፕሬዝዳንት መሱድ ፔዜሽኪያን ጋር ከአንድ ሰዓት በላይ የቆየ ዝርዝር የስልክ ውይይት አድርጌያለሁ" ብለዋል።
በኢስላማባድ የተካሄደው ስብሰባ ብዙዎች እንደሚሉት ብቸኛው አዋጭ አማራጭ የሆነውን ዲፕሎማሲ እና ውይይትን ያካተተ የወሳኝ ሂደት ጅምር መሆኑንም አልጀዚራ በዘገባዉ አመላክቷል፡፡
እንደ ፕሬዝዳንቱ ጽሕፈት ቤት ገለጻ፤ ፔዜሽኪያን የኢስላማባድን ጥረት ያደነቁ ሲሆን፤ በኢራን ላይ የሚሰነዘረውን ጥቃት ለማስቆም ፓኪስታን ለምታደርገው የማስታረቅ ጥረት አመስግነዋል።
ሁለቱ መሪዎች ባለፉት ሳምንታት ስለ ግጭቱ እና ፓኪስታን ግጭቱን ለማቆም ስላላት ቁርጠኝነት ቀደም ብለው ተነጋግረው ነበር።
ኢስላማባድ ከቴህራን ጋር የቆየ ግንኙነት እና በባህረ ሰላጤው አገራት ዘንድ የቅርብ ትስስር ያላት ሲሆን፤ ሻሪፍ እና የጦር ኃይሉ ጠቅላይ አዛዥ ፊልድ ማርሻል አሲም ሙኒር ከአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጋር የግል መቀራረብ ፈጥረዋል።
አልጀዚራ እንደዘገበዉ፤ ፓኪስታን በአሜሪካ እና በኢራን መካከል እንደ "ዋነኛ መልዕክት አቀባይ" በመሆን በማስታረቅ ጥረቱ ውስጥ በሁለቱ ወገኖች መካከል መልዕክቶችን በማስተላለፍ ላይ ትገኛለች።
እስከዳር ግርማ

4 months ago