Logo
SeledaPost
ቻው የእናቴ ልጅ" - የብዙዎችን ልብ የሰበረው አስደናቂ ስንብት

ዛሬ በሶሻል ሚዲያ አነጋጋሪ የነበረ አንድ ቪዲዮ አለ፤ እሱም እህት ከወንድሟ ስትለይ የሚያሳይ ሲሆን የብዙዎችን ልብ ነክቷል።

ቪዲዮው በእጅጉ የሚያሳዝን እና ደጋግመው የሚያዩት ስሜትን የሚነካ ነው። ዕድሜያቸው የገፋ ወንድም እና እህት ናቸው።

ምን ያክል መነፋፈቅ፣ መከባበርና በስስት የመተያየት መልካም ስብዕና እንደሆነ ያስገርማል

ወንድም ሊጠይቃት ሄዶ ተሰናብቶ ወደ መጣበት ሲመለስ እህት የምታሳየው ፍቅር፣ አክብሮትና መናፈቅ ነው ።

ለመለያየት በእጅጉ ከብዷቸዋል። እህት ታለቅሳለች፣ ወንድ ልጅ ያው ሰው ፊት አያለቅስም ብሎ በልቡ ዞር ብሎ ያለቅሳል። ስሜቱ ግን ፊቱ ላይ ይታያል፡፡

ዛሬ ላይ በርካቶች በተጨካከኑበት እና ከራስ አልፈው ማሰብ ባልቻሉበት በዚህ ዘመን፣ እነኚህ ትልቅ ምሳሌዎች ናቸው::

ሁሉም ጋር ሊኖር የሚገባ መተሳሰብ፣ መዋደድ፣ መከባበር፣ መነፋፈቅ ይህ ነው::

ደም ለደም መሳሳብ፣ ከወንድም እና እህት በላይ የለም!

seledadotio
seledadotio
5 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.