የያንጎ ፌሎውሺፕ ኢትዮጵያን ጨምሮ በስድስት የአፍሪካ ሀገራት ተጀመረ።
ይህም የቀጣዩን ትውልድ ዐቅም በሳይንስ እና ቴክኖሎጂ እንዲሁም በምኅንድስና እና ሒሳብ ዘርፍ ለማጎልበት የሚያስችል ነው::
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ - ታኅሣሥ 09 ቀን 2018ዓ.ም።
ዓለም አቀፋዊ የቴክኖሎጂ ተቋም የሆነው ያንጎ ግሩፕ፣ የያንጎ ፌሎውሺፕ ቀጣይ ምዕራፍ - በመላው አፍሪካ የሳይንስ እና ቴክኖሎጂ እንዲሁም የምኅንድስና እና ሒሳብ ዘርፍ ችሎታን ለማጎልበት ዓልሞ እንደተነደፈ አስታውቋል።
ያንጎ ፌሎውሺፕ፣ ወጣቶችን በማማከር እና አቅጣጫ በመጠቆም እንዲሁም ግብዓቶችን እና የግንኙነት መረቦችን በመዘርጋት፣ ተሳታፊዎች ማኅበረሰባቸውን የሚጠቅሙ ሐሳቦችን እንዲያመነጩ ብሎም ወደ ተግባር እንዲቀይሩ እገዛ ያደርጋል።
በዛምቢያ እና በአይቮሪኮስት በተሳካ ሁኔታ የተጀመረው የያንጎ ፌሎውሺፕ ፕሮግራም አድማሱን በማስፋት ወደ አራት ተጨማሪ ሀገራት፣ ማለትም ኢትዮጵያ፣ ሞዛምቢክ፣ ጋና እና ሴኔጋል ደርሷል።
መዳረሻዎቹን እያሰፋ የመጣው የያንጎ ፌሎውሺፕ ፕሮግራም፣ የገንዘብ ድጋፍን እና የባለሙያዎችን ሰፊ እገዛ ያካተተ ከመሆኑም ባሻገር፣ በድንበር ያልተገደበ ሰፊ የፌሎው ተጠቃሚ ማኅበረሰብ ግንኙነቶችን በማመቻቸት ተሳታፊዎች ለኅብረተሰባቸው መፍትሔ ፈጣሪ እንዲሆኑ የሚያስችል ነው።
መርሐ ግብሩ፣ የመጨረሻ ዓመት ተማሪዎቹን፣ በወደፊት የሥራ ሕይወታቸው ውጤታማ እንዲሆኑ የሚያስችሉ ድንቅ የሥራ ልምዶች እና ክሂሎቶችን እንዲያገኙ በማመቻቸት ለስኬታማ ነገአቸው ዝግጁ ካደረገ በኋላ፣ በቀጣዩ ዓመት ደግሞ አዳዲስ ስኬታማ ባለሙያዎችን እና በድንበር የማይገደብ የተግባቦት መረብን በመፍጠር ከአፍሪካ ልዩ ልዩ አካባቢዎች የተውጣጡ ወጣቶችን በዐቅም ለማጎልበት ዝግጅቱን ጨርሷል፡፡
በመላው አፍሪካ ያለው የሠለጠኑ የሳይንስ ሊቃውንት፣ መሐንዲሶች እና የቴክኖሎጂ ባለሙያዎች ፍላጎት ወደነዚህ መስኮች ከሚገቡት ተማሪዎች ቁጥር ጋር ሲነጻጸር እጅጉን የማይመጣጠን ነው።
የዓለም ባንክ እንዳስቀመጠው ከሆነ ደግሞ፣ ከሰሐራ በታች ባሉ የአፍሪካ ሀገራት ዘላቂ የኢኮኖሚ ዕድገታቸውን ለመደገፍ ከ2.5 ሚሊዮን በላይ የሳይንስ እና ቴክኖሎጂ እንዲሁም የምኅንድስና እና ሒሳብ ዘርፍ ባለሙያዎች ያስፈልጓቸዋል፡፡
በተመሳሳይ ሁኔታ፣ በፍጥነት በማደግ ላይ ያለው የአፍሪካ ሕዝብ የወጣቶች ቁጥር ከፍያለ የክሂሎት ክፍተት ይስተዋልበታል፡፡ ጥራት ያለው የዲጂታል ወይም የቴክኒክ ሥልጠና የማግኘት ዕድል ያላቸው ከ10-15% የሚሆኑ አፍሪካውያን ወጣቶች ብቻ ሲሆኑ ከ5% ያነሱት ደግሞ በፕሮግራሚንግ፣ በመረጃ ትንተና ወይም በሳይበር ደህንነት እና መሰል መስኮች ልምድ ያገኛሉ።
በየዓመቱ ከ10-12 ሚሊዮን የሚገመቱ ወጣቶች ወደ ሥራው ዓለም የሚቀላቀሉ ቢሆንም በየዓመቱ የሚኖሩት ክፍት የሥራ ዕድሎች ከ3 ሚሊዮን አይዘሉም፡፡ በመሆኑም ይህንን ችግር ለመቅረፍ ብቃት ያላቸው የሳይንስ እና ቴክኖሎጂ እንዲሁም የምኅንድስና እና ሒሳብ ዘርፍ ባለሙያዎችን ማፍራት የግድ ይላል።
ያንጎ፣ ይህንን መርሐ ግብር በበርካታ አካባቢዎች በማስፋት፣ አስተማማኝ ዐቅም ያለው እና ለወደፊት ዝግጁ የሆነ ሥልጡን የሳይንስ እና ቴክኖሎጂ እንዲሁም የምኅንድስና እና ሒሳብ ዘርፍ ባለሙያዎች ለመገንባት ትልቅ ዓላማ የሰነቀ ሲሆን ሠልጣኞች በማኅበረሰባቸው ውስጥ ለሚፈጠሩ ተግዳሮቶች መፍትሔዎችን እንዲያዘጋጁ የማስቻል ርዕይ አለው።
ፕሮግራሙ ትብብርን፣ ፈጠራን እና ብቃት ያለው አመራርን የሚያበረታታ ሲሆን አህጉሪቱን የሚያጠቃልልና የቀድሞ ተማሪዎችን የሚያሳትፍ ጠንካራ አውታረ መረብ በመገንባት ላይ ይገኛል።
በቅርቡ የወጣው ሀገራዊ መረጃ እንደሚያሳየው፣ ኢትዮጵያ ከባድ የሰው ኃይል ብክነት ተግዳሮት ከፊቷ ተጋርጦባታል፡፡የወጣቶቿ ሥራ አጥነት አሁንም ከፍ ያለ ሆኖ ይታያል፡፡ ይህችግር በተለይም በከተሞች አካባቢ ከ25 በመቶ በላይ የሚደርስ ሲሆን ወጣት ሴቶች ደግሞ በሥራ አጥነት ከፍተኛውን ቁጥር ይይዛሉ፡፡
ትምህርታቸውን ካጠናቀቁ በኋላ በግምት 42% የሚሆኑት የዩኒቨርሲቲ ተመራቂዎች መደበኛ ሥራ ለማግኘት ይቸገራሉ፡፡ ይህም በተመራቂዎች ብዛት እና በሥራ ገበያ ፍላጎት መካከል ያለውን ክፍተት አጉልቶ ያሳያል።
በተቻለ መጠን የሳይንስ እና ቴክኖሎጂ እንዲሁም የምኅንድስና እና ሒሳብ ዘርፍ ባለሙያዎችን በማፍራት እና ዕድሉን ለሁሉም በማስፋፋት ረገድ የተሻሻሉ እመርታዎች ቢኖሩም የተሳትፎ እና የሥራ ውጤቶቹ ከዘርፉ ፍላጎት አንጻር ብዙ የሚቀራቸው ናቸው፡፡ በተለይ በጾታ ድልድሉ በኩል፣ ሴቶች በከፍተኛ ሁኔታ ውክልና የማይኖራቸው ሲሆን ከወንድ እኩዮቻቸው በበለጠ ለሥራ አጥነት ወይም መደበኛ ላልሆነ ሥራ ተጋላጭ ናቸው።
ከዚህም በላይ ቀጣሪዎች እና ጥናቶች እንደሚጠቁሙት፣ አሁን ላይ ገበያው ለሚፈልገው ዲጂታል እና ፈጠራ-ተኮር ሥራዎች የሚያስፈልጉ የቴክኒካል እና የተግባር ሥልጠናዎች የሚያሟሉ ጥቂት ተመራቂዎች ብቻ በመኖራቸው በኢኮኖሚው ውስጥ ከፍ ያለ የችሎታ አለመመጣጠን ይታያል።
በያንጎ ግሩፕ ውስጥ ዋና የቢዝነስ ኃላፊ የሆኑት አዴኒዪአዲቤዮ - በጋዜጣዊው መግለጫ ላይ "አፍሪካ፣ ለፈጠራ የሚተጋ እና ችግር ፈቺ ኃይልን ማምጣት የሚችል ልዩ ችሎታአላት። የያንጎ ፌሎውሺፕም፣ እነዚህን ችሎታዎች ለማገዝ እና ወጣት ፈጣሪዎችን ከአማካሪዎች፣ ከግብዓቶች እና ከእውቀት ጋር በማገናኘት ወጣቶቹ ማኅህበረሰቦቻቸውን የሚጠቅሙ መፍትሔዎችን እንዲያዳብሩ ለማስቻል የተነደፈ ተግባራዊ ፕሮግራም ነው፡፡
በዚህ ዓመት፣ፕሮግራማችን በስድስት ሀገራት ውስጥ የሚካሄድ ሲሆን፣የዕውቀት ሽግግርን በመፍጠር እና ቴክኖሎጂን በመጠቀም በአህጉሪቱ ላይ እውነተኛ ተፅእኖ ለመፍጠር ያልማል፡፡” ብለዋል፡፡
መርሐ ግብሩ ከተጀመረበት ጊዜ አንሥቶ ውጤታማ ስለመሆኑ፣ እስከዛሬ ድረስ በፕሮጀክቱ ውስጥ ያለፉው ጤታማ ሠልጣኞች እና ተሳታፊዎች በየአካባቢያቸው ትልልቅ የማኅበረሰብ ፕሮጀክቶችን ጀምረው እና ውጤታማ ሆነው በአርአያነት መመዝገባቸው ቋሚ ምስክር ነው።
የያንጎ የአካባቢ ማዕከሎች፣ ስኬታማ ወጣቶችን በማስተማር እና በዐቅም በማጎልበት ቁልፍ ሚናን ይጫወታሉ፡፡ ይህም ፕሮግራሙ ችሎታንና እና አካባቢያዊ ሥነ-ምኅዳርን እንደሚያጠናክር የሚናገር ነው።
ለያንጎ ፌሎውሺፕ እንዴት ማመልከት ይቻላል?
መርሐ ግብሩ አሁን በሳይንስ እና ቴክኖሎጂ እንዲሁም በምኅንድስና እና ሒሳብ ዘርፍ፣ ዕድሜያቸው ከ18–25 ድረስ ያሉ ኢትዮጵያውያን ወጣቶችን ለመቀበል ክፍት ነው፡፡ ፍላጎት ያላቸው አመልካቾች እስከጥር 18 ቀን 2018ዓ.ም. ድረስ ድረ ገጻችንን https://yangofellowship.co... በመጠቀም ማመልከት ይችላሉ፡፡.

8 months ago