5 hours ago
" በዚህ አስቸጋሪ ወቅት ኢትዮጵያ ራሷን ከመከላከል በቀር ሌላ አማራጭ የላትም " - ጌዲዮን ጤሞቲዮስ (ዶ/ር)
👉 " ሁለቱን አገራት በእኩል ሚዛን ለማስቀመጥ የሚሞክር ማንኛውም አቋም ለአፍሪካ ቀንድ ሰላም እና ደኅንነት አይጠቅምም ! "
ኢትዮጵያ በኤርትራ ወረራ እንደተፈጸመባት እና ራሷን ከመከላከል ውጪ ሌላ አማራጭ እንደሌላት በመግለጽ ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (UN) በደብዳቤ አሳወቀች።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጤሞቲዮስ (ዶ/ር) ወቅታዊ ሁኔታዎችን በተመለከተ ለመንግሥታቱ ድርጅት የፀጥታ ጥበቃ ምክር ቤት አባላት ደብዳቤ መጻፋቸውን ቢቢሲ ዘግቧል።
በዚህም ደብዳቤ፤ የኤርትራ ሠራዊት ድንበር አልፎ ወደ ኢትዮጵያ ግዛት መግባቱን ገልጸዋል።
ኢትዮጵያ በሁለት የተለያዩ ጊዜያት ለፀጥታው ም/ቤት አባላት በላከችው ደብዳቤ " ኤርትራ በተደጋጋሚ በፈጸመችው ጸብ አጫሪነት እና ድንበር ጥሶ የመግባት እርምጃ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ደኅንነት ላይ አደጋ መደቀኑን " በመጥቀስ ትኩረት እንዲሰጠው መጠየቃቸውን አስታውሰዋል።
" ኤርትራ የፀብ አጫሪነት ድርጊቷን በአሁኑ ጊዜ ከፍ ወዳለ ደረጃ አሸጋግራ ሜካናይዝድ ክፍሎችን ጨምሮ ወታደሮቿን በጥልቀት ወደ ኢትዮጵያ ግዛት አሰማርታለች " ያሉት ጌዲዮን (ዶ/ር) ፥ " ይህም ሦስት የትግራይ ዞኖችን በማካተት በኢትዮጵያ ግዛት ውስጥ ከ30 አስከ 60 ኪሎ ሜትር በሚደርስ ርቀት ወደ ውስጥ ገብተዋል " ብለዋል።
ሚኒስትር ጌዲዮን የኤርትራ ድርጊት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ቻርተር ውስጥ የሰፈሩትን መሠረታዊ መርሆዎች በግልጽ የሚጥስ ነው በማለት " ይህም ኢትዮጵያ ራሷን የመከላከል ሕጋዊ መብት እንድትጠቀም የሚያስገድድ ነው " ሲሉ ጽፈዋል።
ለፀጥታው ም/ቤት የጻፉት ደብዳቤ የተፈጸመውን ወረራ ለማሳወቅ ብቻ ሳይሆን ኢትዮጵያ ለምትወስደው የመከላከል እርምጃ ድጋፍ ጠይቀዋል።
" በዚህ አስቸጋሪ ወቅት ኢትዮጵያ ራሷን ከመከላከል በቀር ሌላ አማራጭ የላትም " በማለት ምክር ቤቱ ኢትዮጵያ የገጠማትን ሁኔታ በመረዳት ድጋፍ እንዲደያርግላት እና ከጎኗ እንዲቆም ጠይቀዋል።
ሚኒስትሩ፣ ኢትዮጵያ ከኤርትራ በኩል ለረዥም ጊዜ ሲፈጸሙ ለነበሩ ትንኮሳዎች በትዕግሥት እና ራስን በመቆጠብ መቆየቷን አመልክተዋል።
በመሆኑም " ሁለቱን አገራት በእኩል ሚዛን ለማስቀመጥ የሚሞክር ማንኛውም አቋም ለአፍሪካ ቀንድ ሰላም እና ደኅንነት አይጠቅምም " ብለዋል።
" ኤርትራ ወራሪ ናት፤ ኢትዮጵያ ደግሞ የወረራ ሰለባ ናት። ኤርትራ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት እና የግዛት አንድነት እየጣሰች ነው " ሲሉም አሳውቀዋል።
ኢትዮጵያ ራሷን ከመከላከል በቀር ሌላ አማራጭ እንደሌላትም ገልጸዋል።
መስከረም 28 ቀን 2019 ዓ/ም
@tikvahethiopia
ኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ ሕግን መሠረት በማድረግ ሉዓላዊነቷ እና የግዛት አንድነቷን የመከላከልና የማስጠበቅ ሕጋዊ መብት እንዳላት አሳወቀች። የተባበሩት መንግስታት (UN) ምክትል ዋና ፀሐፊ አሚና ጄን ሙሀመድ አዲስ አበባ ይገኛሉ። ዛሬ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) ጋር ተገናኝተው መክረዋል። ሚኒስትሩ፥ ኤርትራ በኢትዮጵያ ላይ እየፈጸመች ስላለው ቀጣይነት ያለው የጠብ አጫሪነት ተግባና…
👉 " ሁለቱን አገራት በእኩል ሚዛን ለማስቀመጥ የሚሞክር ማንኛውም አቋም ለአፍሪካ ቀንድ ሰላም እና ደኅንነት አይጠቅምም ! "
ኢትዮጵያ በኤርትራ ወረራ እንደተፈጸመባት እና ራሷን ከመከላከል ውጪ ሌላ አማራጭ እንደሌላት በመግለጽ ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (UN) በደብዳቤ አሳወቀች።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጤሞቲዮስ (ዶ/ር) ወቅታዊ ሁኔታዎችን በተመለከተ ለመንግሥታቱ ድርጅት የፀጥታ ጥበቃ ምክር ቤት አባላት ደብዳቤ መጻፋቸውን ቢቢሲ ዘግቧል።
በዚህም ደብዳቤ፤ የኤርትራ ሠራዊት ድንበር አልፎ ወደ ኢትዮጵያ ግዛት መግባቱን ገልጸዋል።
ኢትዮጵያ በሁለት የተለያዩ ጊዜያት ለፀጥታው ም/ቤት አባላት በላከችው ደብዳቤ " ኤርትራ በተደጋጋሚ በፈጸመችው ጸብ አጫሪነት እና ድንበር ጥሶ የመግባት እርምጃ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ደኅንነት ላይ አደጋ መደቀኑን " በመጥቀስ ትኩረት እንዲሰጠው መጠየቃቸውን አስታውሰዋል።
" ኤርትራ የፀብ አጫሪነት ድርጊቷን በአሁኑ ጊዜ ከፍ ወዳለ ደረጃ አሸጋግራ ሜካናይዝድ ክፍሎችን ጨምሮ ወታደሮቿን በጥልቀት ወደ ኢትዮጵያ ግዛት አሰማርታለች " ያሉት ጌዲዮን (ዶ/ር) ፥ " ይህም ሦስት የትግራይ ዞኖችን በማካተት በኢትዮጵያ ግዛት ውስጥ ከ30 አስከ 60 ኪሎ ሜትር በሚደርስ ርቀት ወደ ውስጥ ገብተዋል " ብለዋል።
ሚኒስትር ጌዲዮን የኤርትራ ድርጊት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ቻርተር ውስጥ የሰፈሩትን መሠረታዊ መርሆዎች በግልጽ የሚጥስ ነው በማለት " ይህም ኢትዮጵያ ራሷን የመከላከል ሕጋዊ መብት እንድትጠቀም የሚያስገድድ ነው " ሲሉ ጽፈዋል።
ለፀጥታው ም/ቤት የጻፉት ደብዳቤ የተፈጸመውን ወረራ ለማሳወቅ ብቻ ሳይሆን ኢትዮጵያ ለምትወስደው የመከላከል እርምጃ ድጋፍ ጠይቀዋል።
" በዚህ አስቸጋሪ ወቅት ኢትዮጵያ ራሷን ከመከላከል በቀር ሌላ አማራጭ የላትም " በማለት ምክር ቤቱ ኢትዮጵያ የገጠማትን ሁኔታ በመረዳት ድጋፍ እንዲደያርግላት እና ከጎኗ እንዲቆም ጠይቀዋል።
ሚኒስትሩ፣ ኢትዮጵያ ከኤርትራ በኩል ለረዥም ጊዜ ሲፈጸሙ ለነበሩ ትንኮሳዎች በትዕግሥት እና ራስን በመቆጠብ መቆየቷን አመልክተዋል።
በመሆኑም " ሁለቱን አገራት በእኩል ሚዛን ለማስቀመጥ የሚሞክር ማንኛውም አቋም ለአፍሪካ ቀንድ ሰላም እና ደኅንነት አይጠቅምም " ብለዋል።
" ኤርትራ ወራሪ ናት፤ ኢትዮጵያ ደግሞ የወረራ ሰለባ ናት። ኤርትራ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት እና የግዛት አንድነት እየጣሰች ነው " ሲሉም አሳውቀዋል።
ኢትዮጵያ ራሷን ከመከላከል በቀር ሌላ አማራጭ እንደሌላትም ገልጸዋል።
መስከረም 28 ቀን 2019 ዓ/ም
@tikvahethiopia
7 hours ago
አዲስ የታሰረ የቃል ኪዳን ተስፋ በኢትዮጵያ ሰማይ ሥር
****************
ኢትዮጵያ 7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ በስኬት ማካሄዷን ተከትሎ፣ አዲሱ የመደመር መንግሥት መስከረም 25 ቀን 2019 ዓ.ም በይፋ ተመስርቷል።
ይህ ዕለት የኢትዮጵያ አዲስ የተስፋ አድማስ የተበሰረበትና የሕዝቡ ዲሞክራሲያዊ ውሳኔ ዕውን የሆነበት ታሪካዊ ምዕራፍ ነው።
አዲሱ የመደመር መንግሥት ምስረታ ላለፉት ዓመታት የተጣሉትን የዕድገትና የተስፋ መሠረቶች አጠናክሮ በማስቀጠል፣ የሀገራችንን ሁለንተናዊ ብልጽግና ለማረጋገጥ ያለመ ነው።
የመደመር እይታ ያለፉ ስኬቶችን በማስቀጠል፣ ክፍተቶችን በመሙላትና የቀጣይ ትውልድን ተስፋ በማገናኘት ሀገራዊ አንድነትንና ትብብርን ማዕከል ያደረገ አሰራርን ይዞ ይመጣል ተብሎ ይጠበቃል።
ላለፉት ዓመታት በመደመር መንግሥት ከተከናወኑ አበይት ተግባራት መካከል በቴክኖሎጂ፣ በኢንዱስትሪ፣ በማኅበራዊና ፖለቲካዊ ዘርፎች፣ በምግብ ሉዓላዊነት፣ በከተማ ልማት እንዲሁም በዲፕሎማሲ የተመዘገቡት ስኬቶች በዋናነት ይጠቀሳሉ።
በተጨማሪም የሕዳሴ ግድብን ማጠናቀቅና የቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ራዕይ ሌሎች ማሳያዎች ናቸው።
አዲሱ የመደመር መንግሥት በተመሰረተበት የሁለቱ ምክር ቤቶች የጋራ የመክፈቻ ሥነ-ሥርዓት ላይ ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀሥላሴ የ2019 ዓ.ም የመደመር መንግሥት ዋና ዋና የትኩረት አቅጣጫዎችንና ግቦችን አብራርተዋል።
ፕሬዝዳንቱ በንግግራቸው፤ በሀገራችን ዘላቂ ሰላምን፣ ኅብረትንና ትብብርን ማስፈን፣ ጥራትን መሠረት ያደረገ መዋቅራዊ ሽግግር ማድረግ እንዲሁም የትምህርት፣ የጤና እና የማኅበራዊ ጥበቃ አገልግሎቶችን በጥራት ማሳደግ ዋነኛ ትኩረቶች መሆናቸውን ገልጸዋል።
በተጨማሪም የኤሌክትሪክ ተደራሽነትን ወደ 65 በመቶ፣ የጤና መድኅን ሽፋንን ወደ 85 በመቶ፣ እንዲሁም የተማሪዎች የምገባ ሽፋን ወደ 70 በመቶ ማሳደግ የተያዙ አበይት ግቦች መሆናቸውን አንሥተዋል።
በመሆኑም የመደመር መንግሥት ምስረታ የፖለቲካና የኢኮኖሚ ማሻሻያዎችን ወደ ላቀ ደረጃ በማሸጋገር፣ የሕግ የበላይነትን በማስከበርና የሕዝቦችን አብሮነት በማጠናከር ኢትዮጵያን ወደ ተሻለ የሰላም፣ የፍትሕና የልማት ምዕራፍ የሚያሸጋግር አዲስ የቃል ኪዳን መስመር ይከፍታል።
በልዩ እሸቱ
#የመደመርመንግሥት
#ethiopia #ebc #medemer #medemergovernment #statebuilding

13 hours ago
የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መልዕክት
በዛሬው እለት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በእጩነት የቀረቡትን የሚኒስትሮች ምክር ቤት አባላትን አጽድቋል።
ሹመት የምንዝናናበት ሳይሆን የምንፈጋበት፣ የምንሰራበት፣ ኢትዮጵያን ለማጽናት፣ ኢትዮጵያን ለማበልጸግ፣ ኢትዮጵያን ወደ ስልጣኔ ጉዞ ለማስኬድ ከፍተኛ ጥረት የሚደረግበት መስክና የሀገር ትልቅ አደራ ነው።
በሚቀጥሉት ዓመታት ኢትዮጵያ በውሳኔዋ ሉዓላዊ፣ በልዩነት ውስጥ የተሳሰረች፣ እሴት በመፍጠርና ጠብቆ በማቆየት ረገድ ምርታማ፣ ቀጣናዊና አህጉራዊ መልህቅ በመሆን የምትመራ፣ እንዲሁም ለቀጣዩ ትውልድ በምታሸጋግራቸው አቅሞች ጸንታ እንድትቀጥል ሰፊ ስራ ይጠበቃል።
የመደመር መንግሥት ይህንን እውን ለማድረግ ቁርጠኛ ነው!

Sponsored by
Surafel
19 hours ago
የዓለም ሻምፒዮኑ ጀግናው ክብሮም ንጉሴKebrom muaythia and kickboxing champion . ደማቅ የእውቅና እና የምስጋና ፕሮግራም ሊደረግለት ነው!
የሀገራችንን ሰንደቅ ዓላማ በዓለም አቀፍ መድረክ ላይ ከፍ ላደረጉ፣ የኢትዮጵያን ስም በኩራት ላስጠሩ ጀግኖች እውቅና መስጠትና ማበረታታት የሁላችንም ታሪካዊ ድርሻ ነው!
ኢትዮጵያውስጥ Ethio Fight Night አሸናፊ እንዲሁም
በታኅሣሥ ወር 2023 ዓ.ም (December 2023) በጣሊያን ሀገር በታዋቂው Fight Clubbing አዘጋጅነት በተካሄደው የዓለም የሞይታይ ሻምፒዮና (Muay Thai World Championship) ላይ በ67 ኪሎ ግራም ክብደት ሙሉ ኢትዮጵያን ወክሎ በመወዳደር፣ የዓለም ሻምፒዮን (World Champion) በመሆን የወርቅ ሜዳሊያ ያስገኘውና የሀገር ኩራት የሆነው የሳሪስ አዲሱ ሰፈር ልጅ ክብሮም ንጉሴ (The King) ታላቅ የክብር እና የምስጋና መርሃ ግብር ተዘጋጅቶለታል።
ክብሮም ንጉሴ በዓለም አቀፍ የማርሻል አርት መድረኮች (እንደ Bellator እና WPG Combat ያሉ) የብራዚልና የሌሎች ሀገራት ጠንካራ ተፎካካሪዎችን በበላይነት በመርታት የሚታወቅ፣ የሁለት ጊዜ የጣሊያን K1 ሻምፒዮን እና የኢንተርኮንቲኔንታል ሻምፒዮን በመሆን በፅናትና በደምና በላቡ የተጓዘ እውነተኛ የኢትዮጵያ አልማዝ ነው።
ይህንን ታላቅ ድል እና የሀገር ባለውለታ በደማቅ ሁኔታ ለመዘከር፣ መላው የሳሪስ ወጣቶች ከተለያዩ አጋር ድርጅቶችና ባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር ደማቅ የምስጋና እና የእውቅና መርሃ ግብር (Appreciation & Recognition Ceremony) አዘጋጅተዋል።
ይህ የምስጋና እና የእውቅና መርሃ ግብር ከ 500 በላይ ታዳሚዎች የሚሳተፉበት ሲሆን፣ የኢትዮፋይት (EthioFight)night )&etfc አዘጋጆች ፡ተወዳዳሪዎች እና አዘጋጆች፣ ታዋቂ የማህበራዊ ሚዲያ ተፅዕኖ ፈጣሪዎች፣ የሳሪስ ወጣቶችና የአካባቢው ማህበረሰብ እንዲሁም የክብር እንግዶችና አጋር ድርጅቶች በነቂስ የሚገኙበት ይሆናል።
የሰፈራችንን፣ የከተማችንንና የሀገራችንን ጀግና በጋራ ሆነን እንቀበለው፤ እናበረታታው! ሁላችሁም ሚዲያዎችና ስፖርት አፍቃሪዎች በዚህ ታሪካዊ ፕሮግራም ላይ እንድትታደሙ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።

1 day ago
ኢትዮጵያ ኤርትራን ወራር በመፈጸም የከሰሰች ሲሆን ወታደሮቿ በአስቸኳይ የኢትዮጵያን ምድር ለቀው እንዲወጡ ማስጠንቀቂያ ሰጥታለች።
የኤርትራ ወታደሮች ወደ ሉዓላዊ የኢትዮጵያ ግዛት መግባታቸውን ኢትዮጵያ አሳውቃለች።
እነዚህ የኤርትራ ኃይሎች በአስቸኳይ ከሀገሪቱ ግዛት እንዲወጡ አስጠንቅቃለች።
ለ ' ብሉምበርግ ' ቃላቸውን የሰጡት የኢ.ፌ.ዴ.ሪ መንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር እናትአለም መለሰ፣ " በሉዓላዊ ግዛታችን ውስጥ የሚንቀሳቀሱ ሁሉም የውጭ ኃይሎች በአስቸኳይ ሊወጡ ይገባል " ብለዋል።
በተለይም በትግራይ ክልል ውስጥ የሚንቀሳቀሱ የኤርትራ ኃይሎች የኢትዮጵያን ግዛት ሳይዘገዩ በፍጥነት ለቀው መውጣት እንዳለባቸው አስጠንቅቀዋል።
መስከረም 27 ቀን 2019 ዓ/ም
@tikvahethiopia Photo

“የባሕር በር ጉዳይ ብሔራዊ አጀንዳችን ነው” - የምክር ቤት አባላት
*******************
የባሕር በር ጉዳይ የግለሰብ ወይም የፓርቲ አጀንዳ ሳይሆን የሁሉም ኢትዮጵያዊ ዜጋ ሀገራዊ አጀንዳ መሆኑን የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ገለጹ።
ጉዳዩ የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም ከማስጠበቅ እንዲሁም የሀገራችንን ልማትና ሥልጣኔ ከማስቀጠል ጋር በቀጥታ የተያያዘ መሠረታዊ ጉዳይ መሆኑንም አስገንዝበዋል።
በሰጥቶ መቀበል መርህ በሰላማዊ መንገድ የባሕር በር ለማግኘት እየተሠራ መሆኑን ጠቁመው፣ ይህ ብሔራዊ አጀንዳ እንዲሳካ ኢትዮጵያውያን ሁላችንም በአንድነት መቆም አለብን ብለዋል።
ብሔራዊ ጥቅምን ማስቀደም፣ አንድነትን ማጠናከርና በሀገራዊ ጉዳዮች ላይ በጋራ መቆም ወቅቱ የሚጠይቀው ዋነኛ ሀገራዊ ኃላፊነት መሆኑንም አባላቱ ገልጸዋል።
የፖለቲካ ፉክክርና አብሮ መሥራት ሚዛኑን ጠብቆ ለሀገር ጥቅም እንዲውል ቅድሚያ መስጠት እንደሚገባም ጠቁመዋል።
“ሁላችንም ሀገራችንን ማስቀደም መቻል አለብን” ያሉት አባላቱ፣ የተጀመረው አዲስ የፖለቲካ ባህል ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበትና አብሮ መሥራት እንደሚገባ አመላክተዋል።
በሀገራዊ ጉዳይ ላይ ልዩነት ካለም በግጭት ሳይሆን በምክክር መፍታት እንደሚገባ የገለጹት አባላቱ፣ የሕዝብን ሰላም ማረጋገጥ ለሀገር ልማትና ዕድገት መሠረት መሆኑን አክለዋል።
በተጨማሪም መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎትን ጨምሮ የዲጂታላይዜሽን ሪፎርሞች አገልግሎት አሰጣጥን ከማሳለጥ ባለፈ ብልሹ አሠራርና ሌብነትን ለመቀነስ የሚያግዙ መሆናቸውን ተናግረዋል።
የተጠያቂነት ሥርዓትን ማስፈን፣ መንግሥታዊ አገልግሎትን ከብልሹ አሠራር ማጽዳትና መልካም አስተዳደርን በአስተሳሰብ እና በተግባር ጭምር ማስረጽ እንደሚገባም ጠቁመዋል።
ሀገራዊ አንድነት፣ ሰላም፣ ምርታማነትና ብሔራዊ ጥቅምን ማስጠበቅ በጋራ መሥራትን የሚጠይቁ ዋነኛ ሀገራዊ አጀንዳዎች መሆናቸውን በማንሳት፣ የባሕር በር አጀንዳም በዚሁ አግባብ በትብብር ሊሠራበት የሚገባ የሁሉም ዜጎች የጋራ አጀንዳ መሆኑን ገልጸዋል።
በኢንቲሃድ አብራር
#ethiopia #seaaccess #nationalinterest #nationalunity #peace #accountability #ebc

" ከዚህ ቀደም በነበረ ጦርነት ወቅት የኤርትራ ወታደሮችን አልባሳትና ተሽከርካሪዎቻቸውን ስለምናውቅ በቀላሉ ለመለየት ችለናል " - ነዋሪዎች
የ2013ቱን የትግራይ ጦርነት ተከትሎ ወደ ኢትዮጵያ፣ ትግራይ ክልል ገብተው የነበሩትና ከዛ በኋላ የኢትዮጵያን የተለያዩ አካባቢዎች ይዘው የሚገኙ የኤርትራ (ሻዕቢያ) ወታደሮች አሁን ላይ ወደ ትግራይ ክልል ዘልቀው እየገቡ ናቸው።
ከህወሓት ጋር የተሰለፉት የሻዕቢያ ወታደሮች ትግራይ ክልል ውስጥ መጠነ ሰፊ ወታደራዊ እንቅስቃሴ እያደረጉ ይገኛሉ።
ቢቢሲ ዛሬ ያነጋገራቸው የዓዲግራት ነዋሪዎች ትግራይ ውስጥ ዘልቀው ገብተዋል።
" ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የኤርትራ ወታደሮች ከረቡዕ መስከረም 27 ቀን 2019 ዓ/ም ማለዳ ጀምሮ በዓዲግራት በኩል ወደ ሌሎች የትግራይ አካባቢዎች በጭነት ተሽከርካሪዎችና በእግራቸው ሲያቋርጡ ተመልክተናል " ብለዋል።
ነዋሪዎች ከኤርትራ ድንበር 40 ኪሎ ሜትር የምትርቀውን ዓዲግራት ከተማን በማለፍ የኤርትራ ወታደሮች ወደ መቐለ አቅጣጫ ሲጓዙ ማየታቸውን ገልጸዋል።
" ወታደሮቹ በጭነት መኪኖችና በእግራቸው ወደ መቐለ መስመር ወዳለችው እዳጋ ሐሙስ አልፈው ሲሄዱ ተመልክተናል " ብለዋል።
በአካባቢው የትግራይም ሆነ የፌደራሉ መንግሥት ሠራዊት አባላት ባለመኖራቸውና ከዚህ ቀደም በነበረው ጦርነት ወቅት የኤርትራ ወታደሮችን አልባሳትና ተሽከርካሪዎቻቸውን ስለሚያውቁ በቀላሉ ለመለየት እንደቻሉ ገልጸዋል።
ወታደሮቹ ከመኪና በተጨማሪ በእግርም የሚጓዙ ስለነበሩ ለመለየት ያልተቸገሩት ነዋሪዎቹ፣ ነጣ ያለ እና ቅጠልያ ወደታራዊ ልብስ የለበሱ ናቸው።
" መኪኖቻቸው ሲኖ የሚመስሉ የጭነት መኪኖች እና የኤርትራ የሰሌዳ ቁጥር ያላቸው ናቸው " ብለዋል።
በቀደሙት ቀናት ከኤርትራ ተነስተው በዛላምበሳ በኩል ፋጺ ወደሚባል አካባቢ የኤርትራ ወታደሮች መግባታቸውን ሲሰሙ እንደነበርም አመልክተዋል። ዛሬ ደግሞ ዓዲግራትን ሲተልፉ ነበር።
ነዋሪዎቹ ወታደሮቹን ጭነው የገቡት የጭነት መኪኖች "በግምት ከ40 በላይ" እንደሚሆኑና በእግር ሲጓዙ የነበሩት "ብዙ" መሆናቸውን ጠቅሰዋል።
አንድ የዓዲግራት ከተማ ባለሥልጣን ስማቸው ሳይጠቀስ ለኤኤፍፒ እንደተናገሩት፣ የኤርትራ ወታሮች ለቀናት በአካባቢው እንደነበሩና " ሕዝቡ ስጋት እንደተፈጠረበት " ገልጸዋል።
አንድ የዐይን ምስክር ደግሞ " በትላልቅ የጭነት መኪኖች፣ በክፍት መኪኖች እና በሌሎች ተሽከርካሪዎች የተጫኑ የኤርትራ ወታሮች ከከባድ መሣሪያዎች ጋር " ከዓዲግራት በስተደቡብ እያመሩ መሆናቸውን ለኤኤፍፒ ተናግረዋል።
በተመሳሳይ ሮይተስ ያነጋገራቸው የዓዲግራት ነዋሪዎች በከተማዋ በኩል በሁለት የጭነት መኪኖች የተጫኑ በርካታ የኤርትራ ወታደሮችን ረቡዕ ጠዋት ማየታቸውን ገልጸዋል።
ለሮይተርስ ቀላቸውን የሰጡ የታጠቁ ግጭቶች ቦታና ክስተቶች መረጃ ፕሮጀክት (ACLED) የምስራቅ አፍሪካ ባለሙያ የኤርትራ ኃይሎች በዛላምበሳ በኩል ድንበር አልፈው ዓዲግራት መድረሳቸውን ገልጸዋል። እንደ ባለሙያው ገለጻ፣ የኢትዮጵያ ጦር እነዚህ ወታደሮችን የጫኑ ተሽከርካሪዎችን በጉዋዳ አካባቢ በድሮን መምታቱን ተናግረዋል።
የኤርትራ የማስታወቂያ ሚኒስትር የሆኑት የማነ ገብረመስቀል ፤ የኤርትራ ወታደሮች በኢትዮጵያ ድንበር ተሻግረው ተገኝረዋል መባሉን ውድቅ አድርገዋል።
በከዚህ ቀደሙ ጦርነት ወቅትም ኤርትራ ሰራዊቷ በኢትዮጵያ እንደሌለ፣ ጦሯ የሚወነጀልባቸውን ግፎች እንዳልፈጸመ በተደጋጋሚ ስትክድ እነደነበር የሚዘነጋ አይደለም።
ቢቢሲ፣ ሮይተርስ
መስከረም 27 ቀን 2019 ዓ/ም
@tikvahethiopia የዓዲግራት ከተማ ነዋሪዎች የኤርትራ (ሻዕቢያ) ጦር ሠራዊት ወደ ከተማቸው እንደገባ አሳወቁ። የኤርትራ ጦር በኢትዮጵያ ምድር፣ ትግራይ ክልል ወደ ምትገኘው የዓዲግራት ከተማ መግባቱን ነዋሪዎች ለጀርመን ድምጽ ሬድዮ ተናግረዋል። ነዋሪዎቹ ፥ ወታደሮቹ ወደ መቐለ መስመር / አቅጣጫ ሲያመሩ እንደተመለከቱ ገልጸዋል። በመቐለ ከተማ የሚገኙ የመረጃ ምንጭ የኤርትራ ወታደሮች " በበርካታ ከባድ ተሽከርካሪዎች…

(ዘ-ሐበሻ ዜና) የኢትዮጵያ መንግስታዊው ሚዲያ በሱማሊያ ፕሬዝደንት ላይ የፃፈውን የትችት አስተያየት ከ24 ሰአታት በኋላ አጠፋው፡፡ መንግስታዊው የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ትላንት ኦክቶበር 6 ቀን 2026 በድረ ገፁ በእንግሊዘኛ አንድ ፅሁፍ ለንባብ አብቅቶ ነበር፡፡ ይህ ፅሁፍ የሱማሊያዊውን ፕሬዝደንት ሀሰን ሼክ መሀሙድን ‹‹‹እንደከሀዲ›› አድርጎ የሚገልፅ ነው፡፡
በፅሁፉ ውስጥ ፕሬዝደንቱ በግብፅ አል አላሜን ከተማ ተገኝተው ከሱዳን፣ ከግብፅና ከኤርትራ መሪዎች ጋር ያደረጉትን የ4ትዮሽ ስምምነት አጥብቆ ተችቷል፡፡ ገዝሙ ኢዲቻ በተባሉ ሰው የቀረበው ይህ ፅሁፍ ኢትዮጵያ ለአስርት አመታት ያህል ለሱማሊያ ሰላም ትልቅ ሚና ስትጫወት መቆየቷን ጠቅሶ ‹‹ሱማሊያ የኢትዮጵያን ጥቅም በሚጎዱ እንደዚህ አይነት ስብስቦች ውስጥ መሳተፍ የለባትም›› የሚል መከራከሪያን የሚያነሳ ነበር፡፡
ሱማሊያ በአል አላመን ስምምነት ውስጥ መሳተፏ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን የቆየ ወታደራዊና ዲፕሎማሲያዊ አጋርነት የሚቃረን መሆኑንም የሚገልፅ ሲሆን ይህንን ፅሁፍ በርካታ የሱማሊያ ፖለቲካ አክቲቪስቶች ሲቃወሙት ታይተዋል፡፡
አክቲቪስቶቹ ‹‹ሱማሊያ እንደማንኛውም ሉአላዊ መንግስት የራሷን ብሄራዊ ጥቅም የሚያንፀባርቅ ዲፕሎማሲያዊ ተሳትፎ የማድረግ መብት አላት›› በማለት የገለፁ ከመሆኑም በላይ ፅሁፉ በኢትዮጵያ መንግስታዊ ሚዲያ መቅረቡ ደግሞ የአገሪቱ አቋም ተደርጎ ሊወሰድ እንደሚችል ሲሟገቱ ታይተው ነበር፡፡ ይህንን ተከትሎ የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ፅሁፉን ከድረ ገፁ ላይ እንዳስወገደው ለመመልከት ችለናል፡:

ኤርትራ "ኢትዮጵያ ራስን በመከላከል ስም ልትወረኝ ነው" ስትል ከሰሰች
#fastmereja I የኤርትራ መንግሥት ፕሬስ ሚኒስቴር እንዳስታወቀው፣ የኢትዮጵያ መንግሥት "ሉዓላዊ የባህር በር ማግኘት" እና የባህርኃይል አቅምን ለመገንባት በሚል ሽፋን በኤርትራ ላይ የጥቃት ጦርነት ለመክፈት እንቅስቃሴ እያደረገ ነው አለ። የኤርትራ መንግሥት ቃለ አቀባይ የማነ ገብረመስቀል ከሰዓታት በፊት እንደገለጹት፣ የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት እና ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንኖች በሰሜናዊው የኢትዮጵያ ክፍል ከተከሰተው ግጭት ጋር ተያይዞ በኤርትራ ላይ የሐሰት ውንጀላዎችን በመሰንዘር አጀንዳቸውን በ"ራስን የመከላከል" ስም ለመሸፈን እየሞከሩ ነው ብለዋል።
በመግለጫው እንደሰፈረው፣ በቅርብ ሳምንታት ውስጥ የተሰሙ ከፍተኛ የሰራዊት ጄኔራሎች አስተያየቶች የኢትዮጵያን እውነተኛ አላማ የሚያሳዩ ናቸው። በተለይም አንድ ከፍተኛ ጄኔራል ለአገር ውስጥ ሚዲያ በሰጡት ቃል "ዘመቻውን ስንጀምር ትግራይ ላይ አንቆምም... ዋናው አላማችን ባንዲራችንን ቀይ ባህር ላይ ማቆም ነው" ማለታቸው አሳሳቢ መሆኑን የኤርትራ መንግሥት አመልክቷል። እንዲሁም "መቀሌ ማቆሚያ አይደለችም፣ የመጨረሻ መድረሻችን አሰብ ነው" የሚሉ ንግግሮች የኢትዮጵያን እቅድ ግልጽ የሚያደርጉ እንደሆኑ ገልጿል።
የኢትዮጵያ መንግሥት ሆን ብሎ ጦርነቱን በራስን መከላከል ስም ለመሸፈን የሚደረገው ጥረት ቀባይነት የሌለው እና ክልላዊ ጸጥታን አደጋ ላይ የሚጥል ነው ሲል የኤርትራው ቃለ አቀባይ ማነ ገብረመስቀል በመግለጫቸው ገልጿል።

ኢትዮጵያ ውስጥ የኤርትራ ጦር ድንበር ጥሶ ገብቷል መባሉን ተከትሎ የዜጎች የተቃውሞ ድምፅ እየተሰማ ነው
#fastmereja I የኤርትራ ጦር የኢትዮጵያን ድንበር ጥሶ ወደ ሀገር ውስጥ ገብቷል በሚል በተስፋፋው መረጃ እና የተከሰተውን ሁኔታ አስመልክቶ በርካታ ኢትዮጵያውያን ከፍተኛ ተቃውሞ እያሰሙ መሆናቸውን የደረሰን መረጃ ያመለክታል። በወቅታዊው ጉዳይ ላይ ስጋታቸውን የገለጹት ዜጎች፣ የሀገሪቱ ሉዓላዊነትና የግዛት አንድነት በግልጽ እንደተደፈረ በመጥቀስ ጦሩ በአስቸኳይ ከኢትዮጵያ መሬት እንዲወጣ ጥሪ እያቀረቡ ይገኛሉ።
የተከሰተውን አሳሳቢ ሁኔታ አስመልክቶ በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያ መድረኮች ላይ እየተሰሙ ያሉ ድምጾች እንደሚያሳዩት፣ ዜጎች የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት መጠበቅ የሁሉንም ዜጋ ቀዳሚ ሃላፊነት መሆኑን በማስታወስ የሚመለከታቸው የመንግስት አካላት በአፋጣኝ እጅግ ጥብቅና ግልጽ የሆነ ምላሽ እንዲሰጡበት አጥብቀው እየጠየቁ ይገኛሉ። የድንበር ጥሰቱ በሁለቱ አገሮች መካከል ያለውን አንጻራዊ ሰላም ሊያናጋው ይችላል የሚል ስጋትም በህብረተሰቡ ዘንድ ጎልቶ እየታየ ነው።
እስካሁን ባለው ሁኔታ ጉዳዩን አስመልክቶ ከፌዴራል መንግስትም ሆነ ከሚመለከታቸው የጸጥታ አካላት በይፋ የተሰጠ አጠቃላይ መግለጫ ያለመኖር ቢታወቅም፣ በሀገር ውስጥ ያለው የህዝብ ቁጣና ስጋት እየጨመረ መምጣቱን ከወጡት መረጃዎች ለመረዳት ተችሏል።

(ዘ-ሐበሻ ዜና) የኤርትራ ጦር ወደ ትግራይ ክልል ይበልጥ ጠልቆ በመግባት ከመቀሌ ቀጥላ ክልሉ ሁለተኛዋ ትልቅ ከተማ የሆነችውን አዲግራትን መቆጣጠሩን ተከትሎ፣ የኢትዮጵያ መንግስት የኤርትራን ድርጊት "ወረራ" ሲል በይፋ ኮነነ።
የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ወ/ሮ እናትዓለም መለሰ ለብሉምበርግ የዜና አውታር እንደተናገሩት፣ "በትግራይ ውስጥ የሚንቀሳቀሱት የኤርትራ ኃይሎች ያለምንም የጊዜ ገደብ ከኢትዮጵያ ሉዓላዊ ግዛት ለቀው መውጣት አለባቸው" በማለት የመንግስትን ጥብቅ አቋም አንጸባርቀዋል። ምንም እንኳን የኤርትራ ጦር በኢትዮጵያ ግዛት ውስጥ መኖሩ ከዚህ ቀደም በከፍተኛ የፖለቲካ እና የወታደራዊ መኮንኖች ሲነገር ቢቆይም፣ የሚኒስትሯ የዛሬው መግለጫ ግን ኤርትራ ጦሯን በቀጥታ በማስገባት ሉዓላዊ አገር መውረሯን የሚያረጋግጥ "ይፋዊ የመንግስት ማረጋገጫ" ሆኖ ተመዝግቧል።
ይህ ወታደራዊ ውጥረት ያገረሸው፣ ከ2014ቱ የትግራይ ጦርነት ማብቃት በኋላ ከፌደራል መንግስት ጋር ዳግም መቃቃር ውስጥ የገባው ህወሓት፣ ከመስከረም 13 ቀን ጀምሮ አዲስ ወታደራዊ ጥቃት መክፈቱን ተከትሎ ነው። ህወሓት ይህንን ጥቃት የከፈተው በአማራ ክልል ከሚንቀሳቀሰው 'AFN*M' እና በኦሮሚያ ከሚንቀሳቀሰው የኦሮ*ሞ ነጻነት ሠ*ራዊት (O*LA) ጨምሮ ከስድስት ሌሎች አማፂ ቡድኖች ጋር አዲስ ወታደራዊ ጥምረት ከፈጠረ በኋላ ነው።
መንግስት እንደሚከሰው፣ የኤርትራ መንግስት ይህንን የኢትዮጵያ አማፂያን ጥምረት በተለይም ህወሓትን በስተጀርባ ስትደግፍ ቆይታለች። እንደ መንግስት ትንተና የ"አስመራ ስትራቴጂ የራሷን ጦር ሳታስገባ፣ በእጅ አዙር አማፂያኑን በመደገፍ የኢትዮጵያን መንግስት ማተራመስ እና የመከላከያ ሠራዊቱን አቅም ማዳከም ነበር። የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት አቅም ከኤርትራ ጦር እጅግ የገዘፈ በመሆኑ፣ አስመራ ይህንን የእጅ አዙር የከበባ ስትራቴጂን እንደ ዋነኛ መከላከያዋ አድርጋ ወስዳው ነበር።"
የፖለቲካ ተንታኞች እንደሚሉት "በአሁኑ ወቅት አዲስ አበባ ድንበሯን የመጠበቅ እና ሉዓላዊነቷን የማስከበር እጅግ ፈታኝ አጣብቂኝ ውስጥ ትገኛለች። የውጭ አገር ጦር በዚህ ደረጃ ወደ አገር ውስጥ ጠልቆ መግባቱ፣ የቆየውን ፖለቲካዊ ስጋት ወደ አስቸኳይ ብሔራዊ አደጋ የቀየረው ሲሆን፣ የኤርትራ እርምጃም ሁለቱን አገራት ወደ ለየለት ቀጥተኛ ጦርነት ይበልጥ አቅርቧቸዋል።"

የኢትዮጵያን የውጪ ግንኙነት ከተቀባይነት ወደ ተጽዕኖ ፈጣሪነት የሚያሻግር እና የደመኝነት እይታ ያላቸውን የሚመክር ስራ እንደሚሰራ ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀስላሴ ተናገሩ
መስከረም 27 ቀን 2019 ዓ.ም. (አሐዱ ሬድዮ) ፕሬዝዳንቱ ይህን የተናገሩት የኢፌዲሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክርቤት እና የፌዴሬሽን ምክርቤት 7ኛ የስራ ዘመን 1ኛ ዓመት የጋራ መደበኛ ስብሰባ መክፈቻ ላይ ባደረጉት ንግግር ነው።
በንግግራቸውም የ2019 ዓ.ምን ዋና ዋና ትኩረቶች የዘረዘሩ ሲሆን በአንደኛነት ሰላም ለኢትዮጵያ እድገትና ግስጋሴ ያለውን ዋጋ ያጠና እና ከማንኛውም ጊዜ በላይ ህብረትን፣ ትብብርንና ኢትዮጵያን የሚያስቀድም ተግባር እንደሚከናወን አስታውቀዋል።
ጥራትን መሰረት ያደረገ ሁለንተናዊ መዋቅራዊ ሽግግርም የሚደረግ ሲሆን ትምህርት፣ ጤናና ማህበራዊ ጥበቃን ከስፋት ወደ ጥራት በማሸጋገር ዜጋን ማእከሉ ያደረገ ልማት እንደሚፋጠንም አረጋግጠዋል።
ለእድገታችን ቁልፍ ፋይዳ ባላቸው የኢንዱስትሪና የግብርና ግብአቶች እንዲሁም ዘመናዊ የመሰረተ ልማት ግንባታ አቅማችን ራሱን እንዲችል ይደረጋል ሲሉም ገልፀዋል።
የፕሮጀክትና የፕሮጀክት ፋይናንስ አፈጻጸም ዘመናዊ፣ ፈጣን፣ ቀልጣፋና ተጠያቂነት ያለው እንዲሆን መስራትም ሌላኛው የትኩረት አቅጣጫ በመሆኑ የመንግስት ገቢና ወጪን በአግባቡ የመቆጣጠር አቅም ያድጋል ብለዋል።
በፌደራል መንግስትና በክልሎች መካከል ያለው የስራ ቅንጅት እና የአፈጻጸም ኩነት የተባበረ፣ የተደጋገፈ፣ ቀልጣፋና እንከን አልባ እንዲሆን እንደሚደረግም አክለዋል።
በሌላ በኩል የኢትዮጵያን የውጭ ግንኙነት ከተቀባይነት ወደ ተጽእኖ ፈጣሪነት የሚያሻግር፣ በተለይም ወዳጆችን በማበራከት የሚተጋ፣ የደመኝነት እይታ ያላቸውን ደግሞ የሚመክር፣ ለቀጠናዊ ሰላምና ኢኮኖሚያዊ ትስስር ምንጊዜም ቅድሚያ የሚሰጥ፣ ተነሳሽነቶች ያሉትና አለም አቀፍ ተቀባይነታችንን የሚያሳድግ ይሆናል ሲሉ ተናግረዋል።
ፕሬዝዳንቱ አክለውም እነዚህን ዋና ዋና ትኩረቶች መሰረት በማድረግ በማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና የአገልግሎት ዘርፍ ከፍተኛ ምርታማነት ይመዘገብባቸዋል ተብለው ከሚጠበቁት መካከል የኤሌክትሪክ ተደራሽነት 65 በመቶ እንደሚያድግ ገልፀዋል።
የውሃ ተጠቃሚነትም በስፋት እንዲዳረስ የሚደረግ ሲሆን የጤና መድህን ሽፋን ወደ 85 በመቶ እንዲያድግ እና የደን ሽፋን ደግሞ አሁን ካለበት 26 በመቶ ከፍ እንዲል እንዲሁም የመሶብ አገልግሎት ማእከላት ቁጥር እንዲበራከቱና ከፍ እንዲሉ፣ የተማሪዎች ምገባ ሽፋንም 70 በመቶ እንዲያድግ ይደረጋል ብለዋል።
የሀገራችን የፍትህ ዘርፍ እንዲዘምንና በሀገራዊ ምክክር የቀረቡ ምክረ ሀሳቦች ወደ ተግባር እንዲገቡ እንደሚሰራ አስታውቀዋል።
የ2019 ዓ.ም የትኩረት አቅጣጫዎችንና ያለፉትን የስራ ክንዋኔዎች በሚገባ የተነተነ፣ መልካሙንና ክፍተቶችን የለየ እና የኢትዮጵያን ብሄራዊ ጥቅሞች ይበልጥ የሚያስከብርና ፈጣን እድገቷን የሚያረጋግጥ እንደሚሆን ገልፀዋል።
እነዚህን እውን ለማድረግም በተያዘው አመት አዳዲስ አሰራሮችንና አደረጃጀቶችን መከተሉ ከማንኛውም ጊዜው በላይ አስፈላጊ መሆኑን ያነሱ ሲሆን የአመቱን እቅድ ለመፈጸም የሚመደቡ አካላት የህዝብን ፍላጎት ያስቀደሙ፣ የዛሬንና የወደፊት ራእያችንን ጭምር የሚያመለከቱ እንዲሁም ዋዛ ፈዛዛ ልምምድን የሚጠየፉ እና ትጋት ያላቸው አገልጋዮች እንዲሆኑ እንደሚጠበቅ ፕሬዝዳንቱ አሳስበዋል።
በስፍራሽ ደመላሽ
#አሐዱ_ሬዲዮ_94 .3
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ Photo

ኢትዮጵያ የራሷን የተፈጥሮ ሃብት አቅም ለማስተዋወቅ 3ኛውን የአፍሪካ የተፈጥሮ ሀብት ፖሊሲ ፎረም መጠቀም እንዳለባት ተገለፀ
መስከረም 27 ቀን 2019 ዓ.ም. (አሐዱ ሬድዮ) ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ልማት ባንክና ከሌሎች አጋሮች ጋር በመተባበር ያዘጋጀችው 3ኛው የአፍሪካ የተፈጥሮ ሀብት ፖሊሲ ፎረም በሀገራት መካከል ያለውን ኢኮኖሚያዊ ትስስር ማጠናከር ላይ ትኩረት በማድረግ ከማክሰኞ እለት ጀምሮ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ይገኛል።
የምጣኔ ሃብት ባለሙያ አቶ ዘላለም በቀለ ኢትዮጵያ በምስራቅ አፍሪካም ሆነ በመላው አህጉሪቱ ያለውን የራሷን የኢኮኖሚና የተፈጥሮ ሀብት አቅም በመለየት፣ የንግድ ማስተዋወቅ ስራዎችን በስፋት መስራት እንዳለባት ተነግረዋል ፡፡
ይህ ፎረም አፍሪካውያን ሀገራት በንግድ፣ በፋይናንስና በመሰረተ ልማት ዘርፎች እርስ በርሳቸው በመደጋገፍ ኢኮኖሚያቸውን የሚያሳድጉበት ትልቅ እድል የሚፈጥር እንደሆነም መቁመዋል።
ኢትዮጵያ ፎረሙ እንደ መልካም አጋጣሚ በመጠቀም፣ ለኢኮኖሚ እድገቷ ወሳኝ የሆኑ እንደ የባህር በር እና የንግድ መስመር ያሉ ሀገራዊ አጀንዳዎቿን ለተሳታፊ ሀገራት ለማሳወቅና ዲፕሎማሲያዊ ድጋፍ ለማሰባሰብ መጠቀም አለባት ያሉት ደግሞ መምህርና ፖለቲከኛ ዶ/ር ጌትዬ ትርፌ ናቸው።
ኢትዮጵያን ጨምሮ የአፍሪካ ሀገራት በተፈጥሮ ሀብት የበለጸጉ ቢሆኑም፣ ሀብታቸውን በአግባቡ ባለመጠቀማቸው ተገቢውን ጥቅም እዳላገኙ ባለሙያዎቹ ገልፀዋል ፡፡ በዚህ ረገድ ሀገራቱ በጋራ መስራት እንደሚገባቸው አፅንኦት ሰጥተዋል።
በደረጄ መንግስቱ
#አሐዱ_ሬዲዮ_94 .3
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ

2 days ago
#ebola⚠️
በጎረቤት ሃገር ኬንያ የመጀመሪያው ከውጭ የገባ የኢቦላ ቫይረስ ተጠቂ ግለሰብ መሞቱ ሲረጋገጥ በቫይረሱ የተያዘው ሰው ጋር ንክኪ ያላቸውን ሰዎች የመለየት ስራ እየተሰራ መሆኑን የሃገሪቱ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር አሳውቋል።
• የኢትዮጵያ ጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ " በወረርሽኞች ዙሪያ ሁሌም ዝግጁ ነን " ያሉ ሲሆን የተለመዱና የአየር እና የየብስ መግቢያዎቻችን ላይ የሚሰሩ የምርመራ ስራዎች በሙሉ የቀጠሉ መሆናቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።
በጎረቤት ሀገር ኬንያ የመጀመሪያው ከውጭ የገባ የኢቦላ (ቡንዲቡግዮ) ቫይረስ በሰው ላይ መገኘቱና የታካሚው ሕይወት ማለፉ የኬንያ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር በትላንትናው ዕለት ይፋ አድርጓል።
የኬንያ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው፣ በቫይረሱ ተይዞ ሕይወቱ ያለፈው ግለሰብ ላለፉት ሰባት ዓመታት በኮንጎ ዴሞክራሲያዊት ሪፐብሊክ (ዲ.አር.ሲ) ይኖር የነበረ የኬንያ ዜጋ ነው።
ግለሰቡ ከዲ.አር.ሲ በየብስ ጉዞ ወደ ዩጋንዳ ካምፓላ ካመራ በኋላ፣ ኦክቶበር 3 ቀን 2026 (እ.ኤ.አ) በአውሮፕላን ናይሮቢ ጆሞ ኬንያታ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ መድረሱ ተገልጿል።
በሆስፒታል በለይቶ ማቆያ ውስጥ ህክምና ሲከታተል የቆየ ቢሆንም፣ በብሔራዊ የቫይሮሎጂ ሪፈረንስ ላቦራቶሪ (NVRL) እና በኬኤምአርአይ (KEMRI) በተደረገ ምርመራ በቡንዲቡግዮ ኢቦላ ቫይረስ (Bundibugyo Ebola Virus) መያዙ ተረጋግጦ ሕይወቱ አልፏል።
ኬንያ ከሟቹ ጋር ንክኪ የነበራቸውን የቤተሰብ አባላት፣ የጤና ባለሙያዎችና አብረውት የተጓዙ መንገደኞችን የመለየትና በለይቶ ማቆያ የማስገባት ስራ እያከናወነች ትገኛለች ተብሏል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ የኢትዮጵያ የቅርብ ጎረቤት የሆነችው ኬንያ ላይ በሽታው መከሰቱን ተከትሎ የኢትዮጵያ ዝግጁነት ምን እንደሚመስል የጤና ሚኒስቴርን ጠይቋል።
የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ በሰጡን ምላሽ በወረርሽኞች ዙሪያ ሁሌም ዝግጁ ነን ያሉ ሲሆን የተለመዱና የአየር እና የየብስ መግቢያዎቻችን ላይ ሁሌም የሚሰሩ የምርመራ ስራዎች አሉ እነዛን በሙሉ እየተሰሩ የቀጠሉ መሆናቸውን አብራርተዋል።
ዶ/ር መቅደስ የዓለም ጤና ድርጅት (WHO) ማንቂያ ደወል ሲያሰማና ሀገራት በሽታው መግባቱን ይፋ ሲያደርጉ፣ ከእነዚያ ሀገራት በሚገቡ መንገደኞች ላይ ጥብቅ ፍተሻና የክትትል ስራዎች ወዲያውኑ እንደሚተገበሩ አመልክተዋል።
"እኛ ሁልጊዜ ዝግጅት ላይ ነን፤ ስክሪን እንሰራለን፣ በአየርም በየብስም ያለው ይሰራል" ያሉት ሚኒስትሯ "ዘ ሞመንት ደብሊው ኤች ኦ (WHO) አክቲቬት ሲያደርግና አገሮች ዲክሌር ካደረጉበት ሰዓት ጀምሮ ከዛም አገር የሚመጡት ላይ ተመሳሳይ ነገሮችን ኢንፎርስ ይደረጋል፤ የተለመዱ ስራዎች ስላሉን እነዛን በሙሉ አክቲቬት አድርገናል" ብለዋል።
ቫይረሱ ከዚህ ቀደም በዲ.አር.ሲ እና በዩጋንዳ በታየበት ወቅት ጀምሮ የቅድመ ዝግጅት እርምጃዎች ሲወሰዱ መቆየታቸውን ያስታወሱት ዶ/ር መቅደስ፣ አሁን በሽታው ወደ ኬንያ መግባቱ ሲረጋገጥም የዝግጅት ደረጃው ተጠናክሮ መቀጠሉን አብራርተዋል።
"ገና ዲአርሲ ገባ ከተባለበት ጊዜ ጀምሮ፣ ዩጋንዳም ሲመጣ፣ አሁን ደግሞ እዚህኛውም(ኬንያ) ሲመጣ ደረጃው እያሻሻለ እየጨመረ የሚሰሩ ስራዎች ጀምረናል። ከባለድርሻ አካላት ጋር፣ የድንበር አካባቢ (ክሮስ ቦርደር) ከሚሰሩት ጋር በመረጃ መነባበብ፣ ቅድመ ዝግጅት፣ ቅኝትና ምላሽ እነዚህን በሙሉ አክቲቬት አድርገናል፤ በዛ መልክ ላይ ነው ያለነው" ሲሉ የኢትዮጵያን ወቅታዊ አቋምና ዝግጁነት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አስረድተዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ

ቪዛና ኢታ ሶሉሽንስ ለ148 ሺህ ነጋዴዎች ዲጂታል ክፍያ ሊያደርሱ ነው
#ethiopia | ቪዛ (Visa) እና ኢታ ሶሉሽንስ (ETTA Solutions PLC) በኢትዮጵያ እስካሁን ከተጀመሩ የነጋዴ ዲጂታይዜሽን ፕሮግራሞች ትልቁ እንደሆነ የተገለጸውን የጋራ ፕሮግራም አስጀምረዋል። ፕሮግራሙ በመላ አገሪቱ ለ148 ሺህ ነጋዴዎች ደህንነቱ የተጠበቀ የዲጂታል ክፍያ መቀበያ አገልግሎት ለማዳረስ ያለመ ነው።
በስትራቴጂካዊ አጋርነቱ መሠረት 148 ሺህ የዞሪያ (Zoorya) ክፍያ መቀበያ መሳሪያዎችና በሺዎች የሚቆጠሩ ዘመናዊ የሽያጭ ቦታ (POS) ተርሚናሎች ለነጋዴዎች ይሰራጫሉ። ይህም በአዲስ አበባ ከሚገኙ ትላልቅ የችርቻሮ መደብሮች ባሻገር በአካባቢ ሱቆች፣ በገበያ ነጋዴዎች፣ በምግብ ቤቶች፣ በፋርማሲዎችና በትንንሽ ንግዶች የዲጂታል ክፍያ ተቀባይነትን ያሰፋል።
ነጋዴዎች ቪዛ (Visa) ካርዶችን በንክኪ ብቻ መቀበል የሚያስችላቸው ሲሆን፣ ካርድ፣ የኪውአር (QR) ኮድ፣ የሞባይል ገንዘብና ከሂሳብ ወደ ሂሳብ የሚደረጉ ክፍያዎችንም በአንድ መሳሪያ መቀበል ይችላሉ። መሳሪያዎቹ የኤሌክትሮኒክ ደረሰኝ አሰጣጥንና የንግድ ሥራ አስተዳደርን ከክፍያ አገልግሎት ጋር በማጣመር ነጋዴዎች የሽያጭና የክምችት መረጃዎቻቸውን በቀላሉ እንዲያስተዳድሩ ያግዛሉ።
የኢታ ሶሉሽንስ ዋና ሥራ አስፈጻሚና የዞሪያ ፔይ (ZooryaPay) ቦርድ ሰብሳቢ ዶክተር ተመስገን ገብረሕይወት፣ አጋርነቱ የኢትዮጵያን የንግድ ሥርዓት ወደ ንክኪ አልባ ዲጂታል ክፍያ ለማሸጋገር የሚያግዝ ትልቅ እርምጃ መሆኑን ገልጸዋል። እንደ እሳቸው ገለጻ፣ ኩባንያው ባለፈው ዓመት ብቻ ከ120 ቢሊዮን ብር በላይ የሚገመት የንግድ ልውውጥ በሥርዓቶቹ በኩል ማስኬዱን ጠቁመዋል።
አዲሱ ፕሮግራም ከክፍያ መቀበያ በተጨማሪ ለነጋዴዎች የፋይናንስ ተደራሽነትን ለማሳደግም ያለመ ነው። በነጋዴዎች የግብይት ታሪክ ላይ በመመስረት የብድር ብቁነት መገለጫ እንዲዘጋጅላቸው የሚያደርግ ሲሆን፣ ኢታ ሶሉሽንስ ከኦፕታሲያ (Optasia) ጋር ባለው አጋርነት አማካይነት ነጋዴዎች ከአጋር ባንኮች የሥራ ማስኬጃ ብድር ለማግኘት የሚያመች ሁኔታ ለመፍጠር እየሰራ ነው።
የኢታ ሶሉሽንስ መድረክ አውቶሜሽን፣ የክፍያ መቀበያ፣ ኢ-ኮሜርስና የብድር አገልግሎትን በአንድ ሥርዓት የሚያገናኝ ሲሆን፣ ይህም ነጋዴዎች ሽያጫቸውን ከማስተዳደር ጀምሮ ክፍያ እስከመቀበልና የፋይናንስ ዕድል እስከማግኘት ድረስ ያለውን ሂደት በተቀናጀ መልኩ እንዲያከናውኑ ያስችላል።
ፕሮግራሙ በመጀመሪያ በአዲስ አበባ የሚጀምር ሲሆን፣ በቀጣዮቹ ወራት ወደ መላ ኢትዮጵያ እንደሚስፋፋ ተገልጿል። በዚህም በኢትዮጵያ የዲጂታል ክፍያ ተቀባይነትን ከማስፋት ባሻገር ትንንሽና ጥቃቅን ንግዶች የግብይት መረጃቸውን በመጠቀም ወደ መደበኛ የፋይናንስ አገልግሎት እንዲቀርቡ ለማድረግ ዕድል ይፈጥራል።
ጌትነት ተመስገን
📷 ከበደ መክብብ
#ethiopia #visa #ettasolutions #zoorya #zooryapay #digitalpayments #digitaltransformation #fintech #financialinclusion #contactlesspayments #merchantdigitization

ዘ-ሐበሻ ዜና) የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ (EIH) አሁን ባለው የአዲስ አበባ ሂልተን ሆቴል ቅጥር ግቢ ውስጥ 150 ክፍሎች ያሉት አዲስ ‘Hilton Garden Inn’ እና የጤናና ደህንነት ማዕከልን (Wellness facility) በ55 ሚሊዮን ዶላር ወጪ ሊገነባ መሆኑን አስታወቀ።
ይህ ግንባታ አዲስ አበባ በህዳር ወር 2020 ዓ.ም. (እ.ኤ.አ ኖቬምበር 2027) ለምታስተናግደው 32ኛው የዓለም የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ የከተማዋን የእንግዳ ማስተናገድ አቅም ለማሳደግ ያለመ ነው። ከተማዋ ለጉባኤው ከ80,000 በላይ የውጭ ልዑካንን የምትጠብቅ ሲሆን፣ አሁን ያላት የሆቴል መኝታ አቅም ግን 25,000 ገደማ ብቻ ነው። በመሆኑም የዚህ አዲስ ሆቴል ግንባታ በፈረንጆቹ ኦክቶበር 2027 ተጠናቆ ለአገልግሎት ክፍት እንደሚሆን ታቅዷል።
የፕሮጀክቱ ስምምነት ዛሬ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ አዲስ ዋና መሥሪያ ቤት የተፈረመ ሲሆን፤ የዲዛይን እና ግንባታ ሥራውን ‘ኤልሚ ኦሊንዶ ኮንትራክተርስ’ ተረክቦታል። ‘ዚያስ አርክቴክቸር እና ኢንጂነሪንግ’ ደግሞ የፕሮጀክቱ አማካሪ ሆኖ ተሰይሟል።
በተያያዘ ዜ ኤልሚ ኦሊንዶ ኮንትራክተርስ ከሆልዲንግሱ ጋር ያለው ስራ በዚህ ብቻ አላበቃም፤ ኢትዮጵያን የዓለም አቀፍ የአውትሶርሲንግ አገልግሎቶች መዳረሻ ለማድረግ ያለመና 3,000 ሰዎችን ማስተናገድ የሚችል የቢዝነስ ፕሮሰስ አውትሶርሲንግ ማዕከል በ25.56 ሚሊዮን ዶላር ለመገንባት የሚያስችል ተጨማሪ ስምምነት ተፈራርሟል። ይህ የBPO ፕሮጀክት የሀገሪቱን ኢኮኖሚ ለማብዛት፣ የውጭ ምንዛሪ ለማስገኘት እና የመንግስት የልማት ድርጅቶችን አቅም ለማጠናከር ከፍተኛ አስተዋፅዖ ይኖረዋል ተብሎ ይታመናል።

ሰላም፣ እንደምን አደራችሁ?
በነባራዊ ሁኔዎች የተቃኙ የመደመር መንግሥት አቅጣጫዎች
አዲስ አበባ፣ መስከረም 27፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የመደመር መንግሥት በ2019 ዓ.ም ትኩረት የሚሰጣቸውን ዋና ዋና ስትራቴጂካዊ አቅጣጫዎች በሕዝብ ተወካዮችና ፌዴሬሽን ምክር ቤቶች 7ኛ የሥራ ዘመን 1ኛ ዓመት የጋራ መደበኛ ስብሰባ መክፈቻ ላይ ይፋ አድርጓል።
አቅጣጫዎቹ ኢትዮጵያ እየተጓዘችበት ያለውን ሀገራዊ እድገት ብሎም የሀገር ውስጥ፣ ቀጣናዊ እና ዓለም አቀፋዊ ሁኔታዎች ከግምት ውስጥ ያስገቡ ናቸው፡፡
እነዚህ አቅጣጫዎች ሀገራዊ አንድነትን ከመገንባት ጀምሮ፣ ኢኮኖሚያዊ እድገትና ብልጽግናን ማረጋገጥ፣ የአገልግሎት ዘርፉን ማዘመን እና የዲፕሎማሲ ተጽዕኖን ማሳደግ የሚያስችሉ አጠቃላይ የፖሊሲ ግቦችን ያካተቱ ናቸው።
ሰላም ለሀገር ሕልውና፣ ለልማት እና ለዜጎች ሁለንተናዊ እድገት መሰረት መሆኑን በጥልቀት በመገንዘብ፣ በ2019 ዓ.ም ከመቼውም ጊዜ በላይ ለዘላቂ ሰላም መረጋገጥ ትልቅ ትኩረት ይሰጣል።
በዚህም የሀገርን ዘላቂ ጥቅም የሚያስቀድም፣ የዜጎችን አንድነት የሚያጠናክር እና ከልዩነቶች ይልቅ የጋራ እሴቶችን የሚያጎላ አሰራር ይተገበራል። ይህም በማንኛውም መስክ የሚከናወኑ ተግባራት በሙሉ ሀገራዊ ሕልውናን እና ልማትን ማዕከል ያደረጉ ይሆናሉ።
ሀገራዊ ኢኮኖሚው እና ማህበራዊ የአሰራር እይታው ከብዛት ወይም ከቁጥር ባሻገር በጥራት ላይ የተመሰረተ ሽግግር እንዲያደርግ ይደረጋል።
በየዘርፉ የሚከናወኑ ተግባራት ዘላቂነትን፣ ምርታማነትን እና ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነትን ማዕከል በማድረግ ኢኮኖሚና ማህበራዊ ዘርፎች እርስ በርስ እየተደጋገፉ የሚራመዱበት አጠቃላይ ሀገራዊ ሽግግር እውን ይሆናል።
ባለፉት ዓመታት በትምህርት፣ በጤና እና በማህበራዊ ጥበቃ ዘርፎች የተመዘገቡትን የተደራሽነት ወይም የስፋት ስኬቶች ወደ ላቀ ጥራት የማሸጋገር ትኩረት ቀጣይ ተልዕኮ ነው።
ሀገራዊ የኢኮኖሚ እድገትን አስተማማኝ እና ዘላቂ ይሆን ዘንድ መሰረታዊ ግብዓቶች ማለትም ለኢንዱስትሪና ለግብርና ዘርፍ የሚሆኑ ምርቶችን በሀገር ውስጥ የማምረት አቅም ይጎልብታል።
ታላላቅ ፕሮጀክቶችን የትራንስፖርት፣ የኃይል እና የዲጂታል መሰረተ ልማቶችን መገንባት፣ ማስፋፋት እና ማዘመን በራስ አቅም ይከናወናል።
በዚህም ቀደም ብለው በስኬት እንደተጠናቀቁት እንደ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ያሉ ትላልቅ የልማት ፕሮጀክቶች በተያዘላቸው ጊዜ እና በጀት እንዲጠናቀቁ ይደረጋል።
የፋይናንስ አጠቃቀምን እና የፕሮጀክት አፈጻጸምን በዘመናዊ አሰራር የታገዘ፣ ግልጽነት እና ተጠያቂነት የሰፈነበት ማድረግ ዋነኛ የትኩረት አቅጣጫ ነው።
ሀገራዊ ዕዳን በሥርዓት እና በኃላፊነት ማስተዳደር፣ የመንግሥትን ወጪና ገቢ በጥብቅ ዲሲፕሊን መቆጣጠር እና የሀገር ውስጥ ገቢን ማሳደግና የሕዝብ አገልግሎትን ቀላልና ቀልጣፋ ማድረግ የዚህ ዓመት ሌላኛው አንኳር አጀንዳ ነው።
ከዓለም አቀፍ አጋሮች ጋር ያለውን ግንኙነት ማጠናከር እና አዳዲስ ወዳጆችን ማፍራት፣ ለአፍሪካ ቀንድ እና ለቀጣናው ሰላም፣ ፈጣን የኢኮኖሚ ትስስር እና የጋራ እድገት ግንባር ቀደም በመሆን የኢትዮጵያ የውጭ ግንኙነት እና ዲፕሎማሲያዊ ምሕዳርም ከተራ ተቀባይነት ወደ ተጽዕኖ ፈጣሪነት የሚሸጋገርበት መንገድ ም በቀጣይ የሚተገበር ነው፡፡
የ2019 ዓ.ም የመደመር መንግሥት የትኩረት አቅጣጫ፣ ኢትዮጵያን በጠንካራ ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ እና ዲፕሎማሲያዊ መሰረት ላይ ለማቆም ያለመና ሕዝባዊ ተሳትፎን ማዕከል ያደረገ አጠቃላይ ሀገራዊ የልማት ጥሪ ነው።
#የመደመር_መንግሥት

"በሌሎች እሳቤ ኢትዮጵያን ከመቀየር ይልቅ ለኢትዮጵያ ሲባል የሌሎችን እሳቤ አቃንቶ መቀበል ተገቢ አካሄድ ነው።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
#የመደመርመንግሥት
#ethiopia #ebc #pmabiyahmed
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
#የመደመርመንግሥት
#ethiopia #ebc #pmabiyahmed
2 days ago
ኢትዮጵያን ይምረጡ | Vote
አትሌት ትዕግሥት አሰፋ በ2026 የዓለም አትሌቲክስ የዓመቱ የላቀ አትሌት ሽልማት እጩዎች ስብስብ ውስጥ ተካተተች
#ethiopia | ስመ-ገናናዋ የኢትዮጵያ የማራቶን አትሌት ትዕግሥት አሰፋ ለ2026 የዓለም አትሌቲክስ የዓመቱ ምርጥ አትሌት ክብር በዕጩነት መመረጧን የዓለም አትሌቲክስ በዛሬው ዕለት ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።
አትሌቷ በ2026 የለንደን ማራቶን በሴቶች ብቻ ውድድር የዓለም ክብረወሰንን በ2 ሰዓት ከ15 ደቂቃ ከ41 ሴኮንድ በማሻሻል አንደኛ ወጥታለች።
በተጨማሪም በበርሊን ማራቶን የቦታውን ውድድር ለሦስተኛ ጊዜ በበላይነት ማጠናቀቋ የሚታወስ ሲሆን፣ ያስመዘገበችው የ2 ሰዓት ከ11 ደቂቃ ከ04 ሴኮንድ ሰዓት በሴቶች ማራቶን ታሪክ ሦስተኛው ፈጣን ሰዓት ሆኖ ተመዝግቧል።
በ2023 የዓለም አትሌቲክስ ከስታዲየም ውጭ የዓመቱ ምርጥ አትሌት ተብላ የተሸለመችው አትሌት ትዕግሥት አሰፋ፣ በያዝነው ዓመት በማራቶን ያሳየችው የላቀ ብቃት አሁንም ለታላቁ ሽልማት በዕጩነት እንድትቀርብ አድርጓታል።
አሸናፊውን ለመለየት የሚረዳው የደጋፊዎች የድምፅ አሰጣጥ ስነ-ስርዓት ከመስከረም 26 እስከ ጥቅምት 7 ቀን 2019 ዓ.ም ድረስ የሚካሄድ ሲሆን፣ የስፖርቱ አፍቃሪያንና የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ቤተሰቦች ድምፅ በመስጠት ድጋፋቸውን እንዲሰጡ ጥሪ ቀርቧል።
ድምፅዎን ለትዕግሥት አሰፋ ለመስጠት ከታች ያለውን ሊንክ ይጠቀሙ።
Who has your vote?
👉 https://bit.ly/4y66IHT
#tigistassefa #worldathletics #marathon #ethiopianathletics #athletics #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

በ 2019 በጀት ዓመት የኢትዮጵያን ኤሌክትሪክ ተደራሽነትን 65 በመቶ የጤና መድህን ሽፋንን ደግሞ 85 በመቶ ለማድረስ መታቀዱ ተገለጸ
የሕዝብ ተወካዮችና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች 7ኛ የስራ ዘመን 1ኛ ዓመት የጋራ መደበኛ ስብሰባ ላይ ንግግር ያደረጉት ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀስላሴ በ 2019 በጀት ዓመት በማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ዘርፎች የዜጎችን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ አበይት ተግባራ እንደሚከናወኑ አስታውቀዋል።
በዚህም መሰረት የሀገሪቱን የኃይል ተደራሽነት 65 በመቶ ለማድረስ ታቅዷል ብለዋል።
በሌላ በኩል የማህበረሰብ አቀፍ የጤና መድህን ሽፋንን ወደ 85 በመቶ ከፍ ለማድረግ ፣ በትምህርት ቤት የተማሪዎች የምገባ ሽፋንን ወደ 70 በመቶ ለማሳደግ እንዲሁም የአካባቢ ጥበቃና የደን ሽፋንን አሁን ካለበት 26 በመቶ በላይ ከፍ ለማድረቅ መታቀዱን ገልጸዋል።
በበጀት ዓመቱ የንጹህ ውሃ አቅርቦት ተጠቃሚነትን በስፋት ማዳረስ እንዲሁም የመሶብ አገልግሎት ማዕከላት ቁጥርና አቅም በከፍተኛ ደረጃ እንዲበራከቱ ማድረግ ሌላው የመንግስት አቅጣጫ መሆኑን ጠቁመዋል።
ይህንን ዕቅድ እውን ለማድረግ መንግስት አዳዲስ አሰራሮችና አደረጃጀቶች እንደሚከተል የጠቆሙት ፕሬዝዳንቱ የዓመቱን ዕቅድ የሚያስፈጽሙ አካላት ዋዛ ፈዛዛ ልምምዶችን በመተው በትጋትና በህዝብ አገልጋይነት ስሜት መስራት እንዳለባቸው አሳስበዋል።

(ዘ-ሐበሻ ዜና) በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የኤርትራ አምባሳደር ሶፊያ ተስፋማርያም፣ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ለዘመናት በኢትዮጵያ ላይ ሲከተለው የቆየውን ፖለቲካዊ አካሄድ እና "የስትራቴጂካዊ መቻቻል" ፖሊሲን በጽኑ የሚተች ሰፋ ያለ ትንታኔ አውጥተዋል። አምባሳደሯ በትንታኔያቸው ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ "የኢትዮጵያን ችግር እንዴት እንፍታው?" የሚል የተሳሳተ ጥያቄ ከማንሳት ይልቅ፣ ለተከታታይ የኢትዮጵያ መንግሥታት ሲሰጥ የነበረውን ያለገደብ የፖለቲካ እና የደህንነት ድጋፍ ሊመረምር ይገባል ብለዋል። ዋናው ችግር የኢትዮጵያ ሕዝብ ሳይሆን፣ መንግሥታት የሀገሪቱን ጂኦ-ፖለቲካዊ አቀማመጥ በመጠቀም ከተጠያቂነት የሚያመልጡበት የውጭ ኃይሎች የድጋፍ ስልት መሆኑን አስረድተዋል።
ከቀዝቃዛው ጦርነት ጊዜ ጀምሮ እስከ አሁን ያለው የብልጽግና ፓርቲ መንግሥት ድረስ፣ ተከታታይ የኢትዮጵያ መሪዎች ሀገሪቱ ያላትን ስትራቴጂካዊ አስፈላጊነት በመጠቀም የውጭ ፖለቲካዊ፣ ወታደራዊ እና የገንዘብ ድጋፍን ማግኘት መቻላቸውን ትንታኔው ያብራራል። ይህ የውጭ ኃይሎች ስትራቴጂካዊ ትብብርም ለመንግሥታቱ እንደ ፖለቲካዊ ጋሻ በማገልገል፣ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች እና የውስጥ ጭቆናዎች ተጠያቂነት እንዳይኖራቸው ማድረጉን አምባሳደሯ ተችተዋል። በዚህም ሳቢያ ተራው ዜጋ ከፍተኛ የሆነ ሰብዓዊ እና ኢኮኖሚያዊ ዋጋ እየከፈለ እንደሚገኝ አክለዋል።
በተጨማሪም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ጎልቶ የመጣውን የቀይ ባህር እና የባህር በር ጉዳይ በተመለከተ፣ አምባሳደር ሶፊያ የኢትዮጵያ ፍላጎት በድርድር፣ በንግድ ስምምነቶች እና በጋራ ተጠቃሚነት ላይ በተመሰረተ ቀጠናዊ ትስስር ሊፈታ እንደሚችል አመላክተዋል። ዓለም አቀፍ ሕግ ወደብ አልባ መሆንን የሌላን ሉዓላዊ አገር ግዛት ወይም የባህር ሃብት የመጠየቅ መብት አድርጎ እንደማይቀይረው በማስገንዘብ፣ የጂኦግራፊያዊ አቀማመጥ እጥረትን ለመፍታት ትብብር እንጂ አዲስ የሉዓላዊነት መብት መፍጠር መፍትሄ አይሆንም ሲሉ ሞግተዋል።
አምባሳደሯ "የኢትዮ-ኤርትራ ቀውስ" እየተባለ የሚራገበው ትርክት፣ የኢትዮጵያን ውስጣዊ የፖለቲካ መከፋፈል እና የትጥቅ ግጭቶች ለመሸፈን በፖለቲካ ልሂቃን እና በግጭት ነጋዴዎች ሆን ተብሎ የተፈበረከ መሆኑን አስታውቀዋል። ኤርትራ ለሚሰነዘሩ ትንኮሳዎች እና አነቃቂ ንግግሮች አጸፋዊ ምላሽ አለመስጠቷን እንደ መባባስ መቆጠር እንደሌለበት እና ይህ እራስን የመግታት እርምጃ ለቀጠናው መረጋጋት ትልቅ አስተዋጽኦ እንዳለው አብራርተዋል። የኢትዮጵያን የውስጥ ችግሮች ውጫዊ በማድረግ ወደ ኤርትራ ማላከክ መፍትሄ እንደማያመጣ ጠቁመዋል።
አምባሳደር ሶፊያ ጽሁፋቸውን ሲቋጩም... ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ የኢትዮጵያን ሕዝብ መደገፍ ቢኖርበትም፣ ለመንግሥት ግን ያለገደብ ነጻ ፈቃድ (መስጠቱን ሊያቆም ይገባል ሲሉ አሳስበዋል። የውጭ አጋሮች ፖለቲካዊ መቻቻልን ከማስቀደም ይልቅ ተጠያቂነትን፣ የዓለም አቀፍ ሕግጋት መከበርን እና የጎረቤት አገራትን ሉዓላዊነት የሚያስከብር ጠንካራ የዲፕሎማሲ አካሄድ ሊከተሉ እንደሚገባ ጥሪ አቅርበዋል።

" ከኢትዮጵያ ጋር ላለን ጠንካራ ግንኙነት ከፍተኛ ዋጋ እንሰጣለን " - ጌዲዮን ሳር
የእስራኤል ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የሆኑት ጌድዮን ሳር ከኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌድዮን ጢሞቲዮስ ጋር በኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታዎች እና በሁለትዮሽ ግንኙነት ዙሪያ ውይይት ማካሄዳቸውን ገልጹ።
ሚኒስትሩ ፤ የኢትዮጵያን አንድነትና ጸጥታ አስጠብቆ ማቆየት ለሀገሪቱም ሆነ ለቀጠናው ሰላም ያለው ወሳኝ ሚና ላይ ውይይት ማድረጋቸውን አመልክተዋል።
በምሥራቅ አፍሪካ ቀጠና ሰላምና መረጋጋትን ለማስፈን ሁለቱ አገራት የጋራ ፍላጎት እንዳላቸውና ትብብራቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል።
እስራኤል ከኢትዮጵያ ጋር ላላት የረጅም ጊዜ ጠንካራ ወዳጅነት ከፍተኛ ዋጋ የምትሰጥ መሆኑን አፅንዖት በመስጠት፣ የሁለቱን አገራት ሁለገብ ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከር ዝግጁ መሆኗን በውይይቱ እንዳረጋገጠች አሳውቀዋል።
ይህ ውይይት የተደረገው የእስራኤል ጎረቤት ግብፅ የቀጠናው ሀገራት የሆኑትን የኤርትራ፣ ሶማሊያ፣ ሱዳን መሪዎች ሀገሯ ላይ ሰብስባ ስለ ቀይ ባህር፣ ስለ አባይ ወንዝ ፣ እስራኤል የሀገርነት እውቅና ስለሰጠቻት ሶማሌላንድ ስለሚሰጣት እውቅናና ድጋፍ ማውገዝ እና ሌሎች ጉዳዮች ላይ መክራ " የጋራ " ያለችውን መግለጫ ካወጣች ከ2 ቀን በኋላ ነው።
እስራኤል፣ ጠንካራ ከሚባሉ የኢትዮጵያ ወዳጅ ሀገራት መካከል አንዷ ስትሆን ኢትዮጵያ የባህር በር ለማግኘት የምታደርገውን ጥረት በይፋ ወጥተው ከደገፉ እና ከኢትዮጵያ ጎን ነን ካሉ ሀገራት በግንባር ቀደምትነት ትጠቀሳለች።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መስከረም 26 ቀን 2019 ዓ/ም
@tikvahethiopia #egypt በግብፅ ፕሬዚዳንት አብዱልፈታህ አል-ሲሲ ጥሪ በግብፅ ኒው ኤል-አለሚን ከተማ የግብፅ እንዲሁም የኢትዮጵያ ጎረቤታች የሆኑት የሱዳን ፣ የኤርትራ እና የሶማሊያ የመሪዎች ስብሰባ ተካሂዶ ነበር። ስብሰባው ላይ የነበሩት ፦ - የግብጹ ፕሬዚዳንት አብዱል ፈታህ አልሲሲ - የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ (በግብፅ አውሮፕላን ተልኮላቸው ወደ ግብፅ የሄዱ) - የሶማሊያ ፕሬዚዳንት ሀሰን ሼክ…

3 days ago
ኢትዮጵያ በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ ከወጭ ንግድ 11.2 ቢሊየን ዶላር ገቢ ማግኘቷ ተገለጸ
የሕዝብ ተወካዮችና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች 7ኛ የስራ ዘመን 1ኛ ዓመት የጋራ መደበኛ ስብሰባ ላይ ንግግር ያደረጉት ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀስላሴ የ2018 በጀት ዓመት የመንግስት ስራ አፈጻጸም ሪፖርት አቅርበዋል።
ፕሬዝዳንት ታዬ በበጀት ዓመቱ ሀገሪቱ ከፍተኛ የተባለውን 11.2 ቢሊየን ዶላር ገቢ ማግኘቷን አስታውሰው ይህ ገቢ በሀገሪቱ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የተገኘ መሆኑን ገልጸዋል።
ኢትዮጵያ ከውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት ያገኘችው ገቢ 4.5 ቢሊዮን ዶላር መድረሱን ተናግረዋል።
የአምራች ኢንዱስትሪዎች እድገት በተመለከተ 15.8 በመቶ ውጤት ማስመዝገቡን እና የብድር አቅርቦት ወደ 1.3 ትሪሊዮን ብር ማደጉን አስታውቀዋል።
ፕሬዝዳንቱ አክለውም ጠቅላላ የሀገር ውስጥ ገቢ ከ 1ትሪሊየን 9 መቶ ቢሊዮን ብር በላይ መድረሱን ጠቁመዋል።
የሰብል ምርት ከ 7 ዓመት በፊት ከነበረበት 3 መቶ 35 ኩንታል ወደ 1.3 ቢሊዮን ኩንታል ከፍ ማለቱን ተናግረዋል።
ይህ ውጤት የመንግስት አመራሮች ባደረጉት ጥረት የመጣ መሆኑን አንስተው “ሀገሪቱ በተለያዩ ውስጣዊ እና ውጫዊ ጫና ሆና የተገኘ ውጤት በመሆኑ ልዩ ያደርገዋል” ብለዋል።
የተገኘው ውጤት ኢትዮጵያ የምታስመዘግበው ውጤት ፈተናዎች የሚቋቋም ብቻ ሳይሆን የኢኮኖሚ ሉዓላዊነት ለማረጋገጥ የሚደረገውን ጥረት የሚያሳይ ነው ሲሉ ተናግረዋል።
አክለውም “መንግስት የኢትዮጵያን ዘላቂ ብሔራዊ ጥቅም ለማስከበር ያለውን አቅም በማደራጀት የሀገሪቱን እድገትና ብልፅግና ያረጋግጣል” ብለዋል።
በሕይወቴ ጌትነት

መንግስት በ2019 በጀት ዓመት ትኩረት የሚያደርግባቸውን 8 አበይት ጉዳዮች ይፋ አደረገ
ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀስላሴ መንግስት በ2019 በጀት ዓመት ልዩ ትኩረት ሰጥቶ የሚንቀሳቀስባቸውን ስምንት ዋና ዋና ጉዳዮች ይፋ አደረጉ።
የሕዝብ ተወካዮችና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች 7ኛ የስራ ዘመን 1ኛ ዓመት የጋራ መደበኛ ስብሰባ ላይ ንግግር ያደረጉት ፕሬዝዳንቱ መንግስት በበጀት ዓመቱ በዋናነት ሰላም ለሀገር እድገትና ግስጋሴ ያለውን ከፍተኛ ዋጋ በማጤን ህብረትን ፣ ትብብርን እና ኢትዮጵያን የሚያስቀድም ተግባር ያከናውናል ብለዋል።
በተጨማሪም ጥራትን መሰረት ያደረገ ሁለንተናዊ መዋቅራዊ ሽግግር ለማምጣት ትኩረት ተሰጥቶ እንደሚሰራ አስታውቀዋል።
በማህበራዊ ዘርፍ የትምህርት ፣ የጤና እና የማህበራዊ ጥበቃ ስራዎችን ከስፋት ወደ ጥራት በማሸጋገር ዜጋን ማዕከል ያደረገ ልማት ትኩረት እንደሚሰጥበት የገለጹት ፕሬዝዳንቱ ለእድገት ቁልፍ ፋይዳ ባላቸው የኢንዱስትሪና የግብርና ግብዓቶች እንዲሁም በዘመናዊ የመሰረተ ልማት ግንባታ ሀገራዊ አቅም ራሱን እንዲችል ለማድረግ እንደሚሰራ ተናግረዋል።
በኢኮኖሚና ፋይናንስ ዘርፍ ደግሞ የፕሮጀክትና የፕሮጀክት ፋይናንስ አፈፃፀም ዘመናዊ ፣ ቀልጣፋ እና ተጠያቂነት ያለው እንዲሆን ይደረጋል ብለዋል።
የታክስ መሰረትን በማዘመን ዕዳን ወግ ባለው መልኩ ማስተዳደር እና የመንግስት ገቢና ወጪን በአግባቡ የመቆጣጠር አቅም እንዲያድግ ልዩ ትኩረት ይሰጣል ብለዋል።
በአስተዳደር እና የውጭ ግንኙነት መስክም በፌዴራል መንግስት እና በክልሎች መካከል ያለው የስራ ቅንጅት እና የአፈጻጸም ክትትል እንከን አልባ እንዲሆን እንደሚሰራ ፕሬዝዳንቱ ገልጸዋል።
አክለውም የኢትዮጵያን የውጭ ግንኙነት ከተቀባይነት ወደ ተፅዕኖ ፈጣሪነት በማሸጋገር በተለይም ወዳጆችን በማብዛት እና ለቀጠናዊ ሰላምና ኢኮኖሚያዊ ትስስር ቅድሚያ የሚሰጡ ተነሳሽነቶችን በማጎልበት አለም አቀፍ ተቀባይነትን ለማሳደግ እንደሚሰራ ገልጸዋል።
በፋሲል አረጋይ

የኬንያው ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላለፉ
*******************
የኬንያው ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ በኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለሁለተኛ የሥራ ዘመን በድጋሚ ለተመረጡት ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላልፈዋል።
ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ ባስተላለፉት መልዕክት፣ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰጠው ይህ ታሪካዊ ውሳኔ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የአመራርነት ጥበብና ለኢትዮጵያ ባላቸው ብሩህ ራዕይ ላይ የተጣለውን ታላቅ ህዝባዊ እምነት የሚያረጋግጥ መሆኑን ገልጸዋል።
አክለውም ኢትዮጵያን ወደ ላቀ የዕድገትና የለውጥ ምዕራፍ ለማሸጋገር በሚደረገው ሁለንተናዊ ጥረት ኬንያ ምንጊዜም መልካም ምኞቷን እንደምትመኝ ያስታወቁት ፕሬዚዳንቱ፤ የሁለቱን ሀገራት የጋራ ጥቅም ይበልጥ ለማስከበር፣ የቀጠናውን ሰላምና ዕድገት ለማረጋገጥ እንዲሁም በዓለም አቀፍ መድረኮች በትብብር ለመስራት ኬንያ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ታሪካዊ ወዳጅነት ይበልጥ አጠናክራ ለመቀጠል ሙሉ ዝግጁ መሆኗን አረጋግጠዋል።
በብሌን ደምበሎ
#ethiopia #kenya #pmabiyahmed #williamruto #hornofafrica

(ዘ-ሐበሻ ዜና) የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀስላሴ መንግስት በ2019 በጀት ዓመት ትኩረት አድርጎ የሚሰራባቸውን ዋና ዋና አቅጣጫዎች እና ሀገራዊ ግቦችን ይፋ አድርገዋል።
ፕሬዚዳንቱ በንግግራቸው እንዳብራሩት .. ዘንድሮ ሰላምን፣ ህብረትን እና የሀገርን አንድነት ማስቀደም ቀዳሚ ትኩረት ይሆናል። ከዚህም ጋር ተያይዞ በፌደራል መንግስት እና በክልሎች መካከል ያለውን የስራ ቅንጅት እንከን አልባ ማድረግ፣ እንዲሁም በሀገራዊ ምክክሩ የቀረቡ የምክረ-ሃሳቦችን ወደ ተግባር መቀየር ዋነኛ ተግባራት መሆናቸውን አስታውቀዋል። የሀገሪቱን የውጭ ግንኙነት ከተቀባይነት ወደ ተጽዕኖ ፈጣሪነት ለማሸጋገር፣ ወዳጆችን ለማብዛት እና ቀጠናዊ ሰላምን ለማረጋገጥ እንደሚሰራም ጠቁመዋል።
በኢኮኖሚው ዘርፍ መንግስት በያዝነው በጀት ዓመት የ10.1 በመቶ እድገት ለማስመዝገብ በትጋት እንደሚሰራ ፕሬዚዳንቱ ገልጸዋል። ከዚህም በተጨማሪ የዋጋ ግሽበትን ወደ ነጠላ አሃዝ ዝቅ ማድረግ፣ የታክስ ገቢን ከጠቅላላ የሀገር ውስጥ ምርት (GDP) አንጻር ወደ 9.62 በመቶ ማሳደግ፣ የፕሮጀክቶች አፈጻጸምን ማዘመን፣ እንዲሁም አስተማማኝ የባህር በርን በሰላማዊ መንገድ እና በጋራ ጥቅም መርህ ማረጋገጥ ቁልፍ የኢኮኖሚ ግቦች መሆናቸው ተገልጿል።
በማህበራዊ እና መሰረተ ልማት ዘርፎችም ሰፊ ስራዎች የታቀዱ ሲሆን፤ የኤሌክትሪክ ተደራሽነትን 65 በመቶ፣ የጤና መድህን ሽፋንን 85 በመቶ፣ እንዲሁም የተማሪዎች ምገባ ሽፋንን 70 በመቶ ለማድረስ ግብ ተቀምጧል። የውሃ ተጠቃሚነትን በስፋት ማዳረስ፣ የደን ሽፋንን አሁን ካለበት 26 በመቶ ከፍ ማድረግ እና የፍትህ ዘርፉን ይበልጥ ማዘመን ሌሎች የትኩረት አቅጣጫዎች ናቸው።
በመጨረሻም በዓለም አቀፍ መድረክ ኢትዮጵያ ኃላፊነት የተቀበለችበትን 32ኛውን የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ (COP 32) በስኬት ለማዘጋጀት ትኩረት ተሰጥቶ የሚሰራ ሲሆን፣ በበጀት ዓመቱም ከ1.6 ሚሊዮን በላይ የውጭ ጎብኚዎችን ወደ ሀገር ውስጥ ለመሳብ ሁለገብ ጥረት ይደረጋል ብለዋል።
ታዬ እነዚህን ብለዋል፡ -
* የሀገራችን የኤሌክትሪክ ተደራሽነት 65 በመቶ የሚያድግ ይሆናል።
* የውሃ ተጠቃሚነት በስፋት እንዲዳረስ ይደረጋል።
* የጤና መድህን ሽፋን ወደ 85 በመቶ እንዲያድግ ይደረጋል።
* የደን ሽፋን አሁን ካለበት 26 በመቶ ከፍ እንዲል ይደረጋል።
* የመሶብ አገልግሎት ማዕከላት ቁጥር እንዲበራከቱና ከፍ እንዲሉ ይደረጋል።
* የተማሪዎች ምገባ ሽፋን 70 በመቶ እንዲያድግ ይደረጋል።
* የሀገራችን የፍትህ ዘርፍ የበለጠ እንዲዘምን ይደረጋል።
* በሀገራዊ ምክክር የቀረቡ የምክረ ሃሳቦች ወደ ተግባራ እንዲገቡ ይደረጋል።
* አሰማማኝ የባህር መሻታችን በጋራ ጥቅም፣ ሰጥቶ በመቀበል እና በሰላማዊ መንገድ እውን እንዲሆን ጥረት ይደረጋል።
* አጠቃላይ የታክስ ገቢ ከጠቅላላ የሀገር ውስጥ ምርት አንጻር ወደ 9.62 በመቶ ከፍ እንዲል ይደረጋል።
* የዋጋ ግሽበት ወደ ነጠላ አሃዝ እንዲወርድ ይደረጋል።
* አጠቃላይ የታክስ ገቢም ከፍ እንዲል ይደረጋል።
* በዓለም መድረክ ኢትዮጵያ ኃላፊነት የተቀበለችው 32ኛው የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ (ኮፕ 32) ዝግጅት ሀገራችን ለጉዳዩ ያላትን ከፍ ያለ የሃሳብ እና የተግባር ተርታ በዓለም ፊት የምታሳይበት በመሆኑ፣ በቁም ነገሩ ወይም በሰብስቴንሲቭ ጉዳዮች እና በመሰናዶ ዝግጅት የተሟላለት እና ተጠቃሽ ጉባኤ እንዲሆን ይሰራል።
* በተጨማሪም ከ1.6 ሚሊዮን በላይ ሰዎች ኢትዮጵያን እንዲጎበኙ ሁለገብ ጥረት ይደረጋል።
* እነዚህንም በማሳካት የኢኮኖሚ እድገታችን 10.1 በመቶ እንዲሆን በትጋት የሚሰራ ይሆናል።

Comments