የኢትዮጵያ አስደናቂ የብዝሃ ኢኮኖሚና እምቅ የቱሪዝም አቅም በሲኤንኤን (CNN) ዕይታ
ዓለም አቀፉ የቴሌቪዥን ጣቢያ ሲኤንኤን (CNN) "Connecting Africa" በተሰኘው ታዋቂ ዝግጅቱ፤ ኢትዮጵያ ከለመደችው የቡና ኤክስፖርት ባለፈ በቱሪዝም፣ በማዕድን፣ በታዳሽ ኃይል እና በግዙፍ መሰረተ ልማቶች ላይ እያስመዘገበች ያለውን አስደናቂ የኢኮኖሚ ሽግግር በስፋት ዳስሷል። የጣቢያው ዘጋቢ ቪክቶሪያ ሩባድሪ በልማት ስፍራዎቹ በአካል በመገኘት ባቀረበችው ዘገባ፣ ሀገሪቱ ያላትን እምቅ ሀብት በተጨባጭ ወደ ተግባር እየቀየረች መሆኑን እማኝነቷን ሰጥታለች።
ዘጋቢዋ በልዩ ትኩረት ከተመለከተቻቸው መስኮች አንዱ የኢትዮጵያ የቱሪዝም ዘርፍ ነው። ኢትዮጵያ ያላትን እምቅ የቱሪዝም ሀብት እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ በሚገባው ልክ ሳትጠቀም ብትቆይም፣ አሁን ላይ ግን በመደመር እሳቤ ከዋና ዋና የኢኮኖሚ ምሰሶዎች አንዱ ሆኗል። በተለይም በፈረንጆቹ 2023 በተባበሩት መንግስታት የትምህርት፣ ሳይንስና ባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) በዓለም ቅርስነት የተመዘገበውንና 250 ሺህ ሄክታር መሬት የሚሸፍነውን የባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ በመጎብኘት፣ ስፍራው በዓለም ላይ በመጥፋት ላይ ያሉ የእንስሳት ዝርያዎች መገኛ መሆኑን ዘገባው አውስቷል። መንግስት ለዘርፉ በሰጠው ልዩ ትኩረት ደረጃቸውን የጠበቁ ኢኮ-ሎጆችና የመንገድ መሰረተ ልማቶች መገንባታቸው የሀገር ውስጥና የውጭ ጎብኚዎችን በከፍተኛ ደረጃ እየሳበ ይገኛል። የቱሪዝም ዘርፉ እመርታ እያሳየ ያለው በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አነሳሽነት የተጀመሩት የገበታ ለሸገር፣ ገበታ ለሀገር እና ገበታ ለትውልድ ፕሮጀክቶች ባመጡት ትልቅ አቅም መሆኑን ዘገባው በስፋት ያትታል።
የሀገሪቱ የልማት ራዕይ በቱሪዝም ብቻ የተገደበ አይደለም። ኢትዮጵያ ቀጣናዊ ትስስርን የሚያጠናክሩ ግዙፍ ፕሮጀክቶችን እውን እያደረገች ትገኛለች። ከ12 ቢሊዮን ዶላር በላይ በሆነ ወጪ እየተገነባ ያለውና በ2030 ሙሉ ለሙሉ ተጠናቆ አገልግሎት ሲጀምር በአፍሪካ ተወዳዳሪ የማይገኝለት ግዙፍ ፕሮጀክት የሆነው የቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ለዚህ ማሳያ ነው።
ማረፊያው የሀገሪቱን ንግድና ቱሪዝም ወደ ላቀ ደረጃ ያሸጋግራል ተብሎ ይጠበቃል። በተጨማሪም በአፍሪካ ቀዳሚው የውሃ ኃይል ማመንጫ የሆነው ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ፣ የሚሊዮኖችን ቤት ወደ ብርሃን ከመቀየሩም ባሻገር ከራስ ፍጆታ እስከ ቀጣናዊ የኃይል ትስስር ትልቅ ሚና እየተጫወተ ይገኛል።
ኢትዮጵያ ኢኮኖሚዋን በብዝሃ ዘርፍ ለማሳደግ የጀመረችው ጥረት በማዕድን ዘርፉም ደማቅ አሻራ አሳርፏል። በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሚገኘው የኩርሙክ የወርቅ ፋብሪካ በሺህዎች የሚቆጠሩ ሰራተኞችን አቅፎ እየተገነባ የሚገኝ ትልቅ የማዕድን ሀብት ማውጫ ነው። በሌላ በኩል፣ 140 ዓመታት ያስቆጠረችው መዲናችን አዲስ አበባ፣ ታሪኳን በሚመጥን መልኩ በሚያስደንቅ የልማትና የለውጥ ጉዞ ላይ እንደምትገኝ እና ለሀገሪቱ ሰፊ የኢኮኖሚ ራዕይ አይነተኛ ማሳያ መሆኗ በዘገባው ተጠቁሟል።
በአጠቃላይ የሲኤንኤን ጥልቅ ዘገባ፣ ኢትዮጵያ ኢኮኖሚዋን በብዝሃ ዘርፍ ላይ እንዲመሰረት በማድረግ የሀገሪቱን ብሎም የቀጣናውን የኢኮኖሚ ምህዳር ለመቀየር የጀመረችው ጉዞ ስኬታማ መሆኑን የሚያሳይ ነው። ፖሊሲ ከማውጣት ጀምሮ ቅርሶችን እስከመጠገንና ተቋማትን እስከማዋቀር የተሰሩት ስራዎች ኢትዮጵያን ተመራጭ የኢንቨስትመንትና የቱሪዝም መዳረሻ እያደረጓት ይገኛል።

2 months ago