3 days ago
የቀድሞው የኢትዮጵያ አየር መንገድ መሪ ተወልደ ገብረማሪያም የኤር ኢንዲያ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆነው ተሾሙ
የሕንድ ሁለተኛው ትልቁ አየር መንገድ የቀድሞውን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈፋሚ ተወልደ ወልደማሪያምን ዋና ሥራ አስፈጻሚው አድርጎ መሾሙን አስታወቀ።
የኢትዮጵያ አየር መንገድን ከአስር ዓመት በላይ የመሩት እና አየር መንገዱን ከአፍሪካ ግዙፉ እንዲሁም ቀዳሚው በማድረግ አሁን ከደረሰበት ደረጃ ላይ በማድረስ ቁልፍ ሚና የነበራቸው ተወልደ፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ያካሄደውን የባለ ብዙ ሚሊዮን ዶላር ማስፋፋት እና ባለ ብዙ አውሮፕላኖች ባለቤት እንዲሆን ያስቻሉ መሆናቸው ይነገራል።
አቶ ተወልደ ገብረማሪያም በኢትዮጵያ አየር መንገድ ስኬት ላይ ብቻ ሳይሆን ፈተናዎች በገጠሙት ጊዜ ተቋሙ ተግዳሮቶችን ተቋቁሞ በስኬት እንዲያልፍ አድርገዋል።
በተለይም በአየር መንገዱ ታሪክ ውስጥ ከባድ በነበሩት የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ወቅት በርካታ አየር መንገዶች ለኪሳራ እና ከሥራ ውጪ ለመሆን ሲገደዱ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በሥራው ላይ ለውጥ በማድረግ ትርፋማ ለመሆን አስችለውታል።
በተጨማሪም ከአዲስ አበባ ወደ ናይሮቢ ሲበር ተከስክሶ ሁሉም መንገደኞች እና የአውሮፕላኑ ሠራተኞች ከሞቱበት የቦይን 737 ማክስ አውሮፕላን አደጋ ወቅት የአየር መንገዱን ጥንካሬ ዝና ጠብቀው ከቀውሱ ለመውጣት መቻላቸው ከሚጠቀሱላችው ስኬቶቻቸው መካከል ናቸው።
አቶ ተወልደ ገብረማሪያም አሁን የዋና ሥራ አስፈጻሚውን ቦታ የሚረከቡት ኤር ኢንዲያ አየር መንገድ ባለፈው የአውሮፓውያን ዓመት አውሮፕላኑ ተከስክሶ 260 መንገደኞች ከሞቱ በኋላ በከባድ ፈተና ውስጥ ይገኛል።
አየር መንገዱ በተጨማሪም ከፍተኛ የገንዘብ እና የሥራውን የማካሄድ ፈተና የገጠመው ሲሆን፣ ከደረሰበት አደጋ ተያይዞ በአቪየሽን ተቆጣጣሪ አካላት ጥብቅ ቁጥጥር የሚደረግበት ነው።
አቶ ተወልደ የመሪነት ኃላፊነቱን የሚረከቡት ኤር ኢንዲያ በሚያጓጉዛቸው መንገደኞች ብዛት በሕንድ ውስጥ ካሉ አየር መንገዶች ሁለተኛው ትልቁ አየር መንገድ ነው።
ታታ ግሩፕ 75 በመቶ የባለቤትንት ድርሻውን እንዲሁም የሴንጋፖር አየር መንገድ 25 ባለቤትነት ያለው ወደ 200 የሚጠጉ አውሮፕላኖች እና ከ31 ሺህ በላይ ሠራተኞች የሚሰስተደድረው አየር መንገዱ ወደ 90 ዓለም አቀፍ እና የአገር ውስጥ የበረራ መስመሮች አሉት።
በኢትዮጵያ አየር መንገድ ውስጥ ከ20 ዓመታት በላይ በተለያዩ ኃላፊነቶች ላይ የሠሩት አቶ ተወልደ ገብረማሪያም የአየር መንገዱ ዋና ሥራ አስፈጻሚ የሆኑት በጥር 2003 ዓ.ም. ነበረ።
አቶ ተወልደ በተባበሩት መንግሥታት ውስጥ ዘላቂነት ባለው ትራንስፖርት ዘርፍ ከፍተኛ የአማካሪዎች ቡድን አባል ሆነው ሠርተዋል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ አባል በሆነበት የስታር አሊያንስ ዋና የቦርድ አባል፣ የዓለም አቀፉ የትራንስፖርት ማኅበር (አይኤቲኤ) የቦርድ አባል በተጨማሪም የአፍሪካ የአየር መንገዶች ማኅበር (ኤኤፍአርኤኤ) የዋና ኮሚቴ አባል በመሆን አገልግለዋል።
አቶ ተወልደ የአፍሪካ የጉዞ ማኅበር (ኤቲኤ) የቦርድ አባል እና የኢትዮጵያ የቱሪዝም ድርጅት (ኢቲኦ) የዳይሬክተሮች ቦርድ አባልም ነበሩ።
አቶ ተወልደ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆነው ባገለገሉባቸው በርካታ ዓመታት የተለያዩ ሽልማቶችን አግኝተዋል።
ከሽልማቶቹ መካከል የዓመቱ የአፍሪካ ምርጥ ዋና ሥራ አስፈጻሚ፣ ምርጥ የአፍሪካ የቢዝነስ መሪ፣ የቀጣናዊ የአየር መንገድ አመራር ሽልማት እንዲሁም ምርጥ ፆታን ያማከለ ሥራ አስፈፃሚ የሚሉት ይጠቀሳሉ።
የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በኢኮኖሚክስ፣ ሁለተኛ ዲግሪያቸውን ከዩናይትድ ኪንግደም ኦፕን ዩኒቨርስቲ በንግድ አስተዳደር ያገኙ ሲሆን ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የክብር ዶክትሬትም ተበርክቶላቸዋል።
አቶ ተወልደ ገብረ ማሪያም ከአስር ዓመት በላይ በስኬት የመሩትን የኢትዮጵያ አየር መንገድን የለቀቁት በጤና ሁኔታን በምክንያት ጠቅሰው በ2014 ዓ.ም. ነበር።
BBC

4 days ago
(ዘ-ሐበሻ ዜና) የአሜሪካ የፌደራል አቪዬሽን አስተዳደር (FAA) የቦይንግ አውሮፕላን አምራች ኩባንያ አነስተኛው ሞዴል የሆነውን ቦይንግ 737 ማክስ 7 ለንግድ በረራ አገልግሎት እንዲውል ሰኞ ዕለት ማጽደቁን አስታውቋል። አውሮፕላኑ ለመጀመሪያ ጊዜ ይፋ ከተደረገ ከአስር ዓመታት ገደማ በኋላ የተሰጠው ይህ የእውቅና ማረጋገጫ፣ ኩባንያው ለዓመታት ሲገጥሙት የነበሩትን የደህንነት፣ የጥራት እና የምርት ተግዳሮቶች በማለፍ ረገድ እንደ ትልቅ ምዕራፍ ተቆጥሯል። ለረጅም ጊዜ የዘገየው ይህ ማክስ 7 አውሮፕላን የቦይንግ 737 የንግድ አውሮፕላኖች ቤተሰብ አካል ሲሆን፣ ይህ ሞዴል ለኩባንያው ከፍተኛ የገቢ ምንጭ ቢሆንም ላለፉት ተከታታይ ዓመታት የበርካታ ቀውሶች ማዕከል ሆኖ ቆይቷል።
የዚህ አውሮፕላን ማረጋገጫ ሂደት እጅግ ሊዘገይ የቻለው፣ በ2018 እና 2019 በኢንዶኔዥያ እና በኢትዮጵያ 346 ንጹሃን ዜጎችን የቀጠፈውን ትልቁን የማክስ 8 አውሮፕላን አደጋ ተከትሎ በተፈጠረው ከፍተኛ የቁጥጥር ማዕቀፍ እና የቴክኒክ ችግሮች ምክንያት ነው። ኤፍ ኤ ኤ (FAA) ማረጋገጫውን የሰጠው ለዓመታት ተጨማሪ ሙከራዎችን፣ የዲዛይን ለውጦችን እና በደህንነት ስርዓቶች ላይ ጥብቅ ግምገማ ካደረገ በኋላ መሆኑን አስታውቋል። ከእነዚህም አሳዛኝ አደጋዎች በኋላ አስተዳደሩ የቦይንግ አውሮፕላኖችን የሚያጸድቅበትን አሰራር ሙሉ በሙሉ የቀየረ ሲሆን፣ በኩባንያው ላይ የሚያደርገው ጥብቅ ክትትል ከማክስ 7 ፈቃድ አሰጣጥ በኋላም እንደሚቀጥል አሳስቧል።
የፌደራል አቪዬሽን አስተዳደሩ አውሮፕላኑ ወደ በረራ ከመመለሱ በፊት ቦይንግ ወሳኝ የደህንነት ማሻሻያዎችን እንዲያደርግ አስገድዶ ነበር። ከእነዚህም መካከል የበረራ መቆጣጠሪያ ሶፍትዌርን ማዘመን፣ ለአብራሪዎች የሚሰጠውን የማስጠንቀቂያ ስርዓት ማሻሻል፣ እና ከመጠን በላይ ሙቀትን ለመከላከል የሞተር ፀረ-በረዶ (anti-ice) ስርዓትን እንደገና ዲዛይን ማድረግ ይገኙበታል። በተጨማሪም የደህንነት ተቆጣጣሪዎች የኩባንያውን የደህንነት አስተዳደር ስርዓት እና አጠቃላይ የደህንነት ባህልን ጨምሮ የአመራረት ሂደቱን ለመከታተል በቦይንግ የማምረቻ ተቋማት ውስጥ በቋሚነት እንደሚቆዩ አስተዳደሩ ገልጿል።
የቦይንግ የንግድ አውሮፕላኖች ፕሬዝዳንት እና ዋና ስራ አስፈፃሚ ስቴፋኒ ፖፕ በበኩላቸው፣ የኩባንያው መሃንዲሶች እና የሙከራ ባለሙያዎች ወረርሽኙን እና አዳዲስ የማረጋገጫ ሂደቶችን ጨምሮ በርካታ ተግዳሮቶችን በጽናት ማለፋቸውን ተናግረዋል። ይህ አዲሱ ማክስ 7 አውሮፕላን በዋናነት ለአጭር እና መካከለኛ ርቀት በረራዎች ጥቅም ላይ ይውላል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን፣ ሳውዝ ዌስት ኤርላይንስን ጨምሮ በርካታ አየር መንገዶች ቀደም ብለው ባዘዙት መሰረት አውሮፕላኑን ለመረከብ በመጠባበቅ ላይ ይገኛሉ።

6 days ago
በፔሩ የቱሪስት አውሮፕላን ተከስክሶ 13 ሰዎች ሞቱ
ፔሩ ውስጥ ቱሪስቶችን ጭኖ ሲበርር የነበረ አነስተኛ አውሮፕላን ተከስክሶ፣ በውስጡ የነበሩት 13 ሰዎች በሙሉ ሕይወታቸው ማለፉን የአገሪቱ ባለሥልጣናት እና መገናኛ ብዙኃን ገለጹ።
‘ሴስና ካራቫን ሲ-208’ የተባለው አውሮፕላን ቅዳሜ ዕለት የተከሰከሰው ‘ናዝካ ላይንስ’ በተሰኘው አርኪኦሎጂ ስፍራ በኩል እየበረረ በነበረበት ወቅት ነው። አውሮፕላኑ 11 ተሳፋሪዎች እና ሁለት ፓይለቶች ይዞ ነበር።
ከተሳፋሪዎቹ መካከል ሁለት ጀርመናውያን፣ ሁለት የስፔን ዜጎች እና ሰባት ጣሊያናውያን ቱሪስቶች እንደነበሩ የፔሩ የመንግሥት የዜና ወኪል ዘግቧል። አደጋው የደረሰበት ምክንያት እስካሁን አልታወቀም።
በደቡባዊ ፔሩ የሚገኘው ‘ናዝካ ላይንስ’፣ በበረሃ አሸዋ ላይ የተሳሉ ጥንታዊ የእንስሳት ስዕሎች የሚታዩበት እና በዩኔስኮ የዓለም ቅርስነት የተመዘገበ ታዋቂ የቱሪስት ስፍራ መስህብ ነው።
ብዙውን ጊዜ ቱሪስቶች ስዕሎቹ ምን ያህል ስፋት ያለው ስፍራ ላይ እንዳረፉ ለመመልከት በአነስተኛ አውሮፕላኖች ይበራሉ
የፔሩ ፖሊስ አመራሩ ሜጀር ጆርጅ አንደራዴ "ከአደጋው አስከፊነት የተነሳ በሕይወት የተረፈ ሰው የለም። እስካሁን የአራት ሰዎችን አስከሬን አግኝተናል" ማለታቸውን ኤኤፍፒ ዘግቧል።
‘ፒስኮ’ በተባለው የፔሩ ከተማ ከሚገኝ አየር ማረፊያ የተነሳው አውሮፕላን የተከሰከሰው ፑዌብሎ ቪየሆ የተባለው ክልል ውስጥ ነው።
የዜና ወኪሉ ሮይተርስ ባወጣው አንድ ቪዲዮ ላይ የእሳት አደጋ ሠራተኞች ከስብርባሪዎች ጭስ የሚወጣበት የአደጋ ስፍራ ላይ ውሃ ሲረጩ ያሳያል።
‘ዴ ናስካ’ ግዛት አስተዳደር ባወጣው መግለጫ አውሮፕላኑ ‘ኤሮዲያና’ የተሰኘው የፔሩ የአገር ውስጥ አየር መንገድ ንብረት መሆኑን አስታውቋል።
አየር መንገዱ በበኩሉ ጉዳዩ "የሚመለከታቸው ባለሥልጣናት ከሚያወጧቸው መመሪያዎች ጋር በተጣጣመ መልኩ የበረራ መርሃ ግብሩን እንደሚገመግም" መግለጹን ሮይተርስ ዘግቧል።
ይህ ታዋቂ የቱሪስት መስህብ ባለፉት አስርት ዓመት ውስጥ ሌሎች የአውሮፕላን አደጋዎችንም አስተናግዷል።
በአውሮፓውያኑ 2022 አንድ አነስተኛ የቱሪስት አውሮፕላን በናዝካ ላይስ በኩል ሲበርር ተከስክሶ ሰባት ተሳፋሪዎች ሞተዋል።
2010 ላይ ደግሞ ሌላ የቱሪስት አውሮፕላን ወድቆ ተሳፍረው የነበሩ ስድስት ሰዎችን ገድሏል።

1 month ago
በአውሮፕላን አደጋው እስካሁኗ ደቂቃ ድረስ 11ሰዎች ሞተዋል
#ethiopia | በፈረንሳይ በደረሰ የአውሮፕላን መከስከስ አደጋ የ11 ሰዎች ሕይወት አለፈ።
በምስራቅ ፈረንሳይ ቶምብላይን ከተማ አቅራቢያ በደረሰ የአነስተኛ አውሮፕላን መከስከስ አደጋ አብራሪውን ጨምሮ የ11 ሰዎች ሕይወት አልፏል፡፡
ለአንድ ፓራሹት ማሰልጠኛ ት/ቤት አገልግሎት ሲሰጥ የነበረው ሲቭል አውሮፕላን ከናንሲ ኢሴይ አውሮፕላን ማረፊያ ተነስቶ ብዙም ሳይቆይ መከስከሱ ተመላክቷል፡፡
በተፈጠረው አደጋም አብራሪውን ጨምሮ በአውሮፕላኑ ውስጥ የነበሩ የ11ዱም ሰዎች ሕይወት ማለፉን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
ከሟቾች መካከል አምስቱ የትምህር ቤቱ ተማሪዎች ሲሆኑ አምስቱ ደግሞ መምህራን እንደነበሩ ተጠቁሟል፡፡
የፈረንሳይ ትራንስፖርት ሚኒስቴር በተከሰተው አሰቃቂ አደጋ የተሰማውን ሐዘን ገልጾ የአደጋውን መንስኤ ለማጣራት እየተሰራ መሆኑን አስታውቋል፡፡
#ፈረንሳይቶምብላይንከተማ #ፈረንሳይየአውሮፕላንአደጋ #ጊጡተመስገንሚዲያኮሚኬሽን #getutemesgenmediacommunication

በሳዑዲ አረቢያ እና በፈረንሳይ በደረሱ ሁለት አሰቃቂ የአየር ላይ አደጋዎች የ25 ሰዎች ሕይወት አለፈ
በዓለም አቀፍ ደረጃ በዛሬው ዕለት በተከሰቱ ሁለት ተከታታይ የአየር ላይ አደጋዎች ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል።
በሳዑዲ አረቢያ እና በፈረንሳይ የደረሱት እነዚህ አደጋዎች በዓለም አቀፉ ሚዲያ ትኩረት የሳቡ ዋነኛ ክስተቶች ሆነዋል።
የመጀመሪያው አደጋ የተሰማው ከሳዑዲ አረቢያ ሲሆን፣ የሀገሪቱ የነዳጅ ግዙፍ ኩባንያ ሳዑዲ አራምኮ (Saudi Aramco) የሆነ ሄሊኮፕተር በሀገሪቱ ምስራቃዊ የባህር ዳርቻ ራስ ታኑራ በተባለችው ቁልፍ የነዳጅ ማዕከል አካባቢ ተከስክሷል።
በሄሊኮፕተሩ ተሳፍረው የነበሩ 14 የሳዑዲ ዜጎች በሙሉ ወዲያውኑ ሕይወታቸው አልፏል።
በሌላ በኩል በፈረንሳይ በተመሳሳይ ዕለት በደረሰ የሲቪል አውሮፕላን አደጋ የ11 ሰዎች ሕይወት ማለፉ ተረጋግጧል።
አውሮፕላኑ ጥቂት ሰዎችን አሳፍሮ በመብረር ላይ በነበረበት ወቅት የተከሰከሰ ሲሆን፣ በአደጋው ሳቢያ በአውሮፕላኑ ውስጥ የነበሩት ተሳፋሪዎች በሙሉ ሕይወታቸውን አጥተዋል።
የሀገሪቱ የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች ከአደጋው የተረፈ ሰው አለመኖሩን ያረጋገጡ ሲሆን፣ የተጎጂዎችን ሙሉ ማንነት ለማወቅ ሥራዎች እየተከናወኑ ነው።
በአሁኑ ወቅት በሁለቱም ሀገራት የደረሱትን የእነዚህን አስደንጋጭ አደጋዎች ትክክለኛ መንስኤ ለማወቅ የሚመለከታቸው የሲቪል አቪዬሽን እና የደህንነት ባለስልጣናት ጥልቅ ምርመራ መጀመራቸውን አስታውቀዋል።
Seledadotio

3 months ago
(ዘ-ሐበሻ ዜና) የሚኒስትሮች ምክር ቤት እንደ እሳት፣ የመሬት መንቀጥቀጥ፣ የመሬት መንሸራተት፣ ጎርፍ፣ የኬሚካል መፍሰስ እና የአውሮፕላን አደጋዎች ላሉ ድንገተኛ የተፈጥሮ እና ሰው ሰራሽ አደጋዎች የመጀመሪያ ፈጣን ምላሽ የሚሰጥ "የኢትዮጵያ እሳት እና ሌሎች ድንገተኛ አደጋዎች አገልግሎት"ን የሚያቋቁም ደንብ አጸደቀ። የዚህ አዲስ ተቋም ተጠሪነት ለብሔራዊ የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ይሆናል።
አዲሱ አገልግሎት ሰጪ ተቋም ሀገራዊ የአደጋ ምላሽ መስፈርቶችን እና አሰራሮችን ከማዘጋጀት ባለፈ፣ በድንገተኛ አደጋ ምላሽ ዘርፍ ለተሰማሩ ግለሰቦች እና ተቋማት የሙያ ፈቃድ ይሰጣል። የሰው ሀይሉም ከመደበኛ ሰራተኞች በተጨማሪ ከፊል-ወታደራዊ እና የቅድመ-ሆስፒታል ህክምና ባለሙያዎችን ያካተተ ይሆናል።
ተቋሙ ሀገራዊ የአደጋ መረጃ ቋት የማደራጀት እና የልምምድ ስራዎችን የማከናወን ኃላፊነት የተሰጠው ሲሆን፤ ስራውን በብቃት ለመወጣት እንዲችልም አነስተኛ አውሮፕላኖች፣ ሄሊኮፕተሮች፣ ጀልባዎች እና የሳተላይት መገናኛ ሬዲዮዎችን ጨምሮ ዘመናዊ ቁሳቁሶች ይሟሉለታል። የተቋሙ በጀት ከመንግስት እና በቅርቡ ከተቋቋመው የኢትዮጵያ የአደጋ ስጋት ምላሽ ፈንድ የሚሸፈን ይሆናል። ብሔራዊ የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽንም የደንቡን መጽደቅ የሀገሪቱን የአደጋ መከላከል አቅም የሚያሳድግ ትልቅ እርምጃ ነው ሲል አድንቆታል።

በቦይንግ 737 ማክስ አደጋ ህይወቷ ለጠፋው ሳምያ ስቱሞ ቤተሰቦች የ49.5 ሚሊዮን ዶላር ካሳ ተፈረደ!
በቺካጎ የሚገኝ የፍርድ ቤት ዳኝነት፣ እ.ኤ.አ በ2019 በኢትዮጵያ አየር መንገድ የቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላን አደጋ ህይወቷ ለጠፋው አሜሪካዊቷ ሳምያ ስቱሞ ቤተሰቦች የ49.5 ሚሊዮን ዶላር የካሳ ክፍያ እንዲፈጸም ወሰነ።ይህ የፍርድ ቤት ውሳኔ በዓለም ዙሪያ የ346 ሰዎችን ህይወት በቀጠፉት በሁለቱ የቦይንግ 737 ማክስ አሰቃቂ አደጋዎች ምክንያት በቦይንግ ኩባንያ ላይ የተሰጠ ሁለተኛው ትልቅ የዳኝነት ውሳኔ ነው።
የ24 ዓመቷ ሳምያ ስቱሞ በአውሮፕላን ደህንነት ላይ የምትሰራ ወጣት የነበረች ሲሆን፣ እ.ኤ.አ መጋቢት 10 ቀን 2019 የአውሮፕላን በረራ ቁጥር ET 302 ከአዲስ አበባ ተነስቶ ወደ ናይሮቢ በመጓዝ ላይ ሳለ ቢሾፍቱ አቅራቢያ በደረሰው አደጋ ህይወታቸው ካለፈው 157 ሰዎች መካከል አንዷ ነበረች። ይህ አደጋ ከመድረሱ ከአምስት ወራት በፊት በኢንዶኔዢያ የሊዮን ኤር አውሮፕላን በተመሳሳይ ችግር ተከስክሶ የነበረ ሲሆን፣ የቺካጎ ፍርድ ቤት ውሳኔ ቦይንግ ኩባንያ በአውሮፕላኑ የቴክኖሎጂ አሰራር ላይ ለነበረበት ከፍተኛ የቸልተኝነት ጉድለት ተጠያቂ መሆኑን በድጋሚ ያረጋገጠ ሆኗል።
seledadotio

4 months ago
ሩሲያ ሀዘን ላይ ናት
#ethiopia | በክሬሚያ ግዛት በተከሰከሰው የሩሲያ ወታደራዊ አውሮፕላን ውስጥ የነበሩ ሁሉም ተሳፋሪዎች እና የበረራ ሰራተኞች ህይወታቸውን ማጣታቸው ተሰማ።
የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ መሠረት፤ 'ኤ ኤን-26' የተሰኘው ይህ ወታደራዊ አውሮፕላን 23 ተሳፋሪዎችን እና 6 የበረራ ባለሙያዎችን (በድምሩ 29 ሰዎችን) አሳፍሮ በረራ ላይ ነበር። በጥቁር ባህር አካባቢ ሲደርስም በድንገት ከራዳር እይታ ውጭ ሆኖ የግንኙነት መስመሩ ሙሉ በሙሉ ተቋርጧል።
አውሮፕላኑ በቀጥታ ከተራራ ጋር በመጋጨቱ ምክንያት አደጋው ሊከሰት እንደቻለ የተገለጸ ሲሆን፤ ክስተቱ በምንም ዓይነት የውጭ የጦር መሳሪያ ጥቃት ወይም ትንኮሳ እንዳልሆነ ተረጋግጧል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ሩሲያ #ክሬሚያ #አውሮፕላን_አደጋ #ሰበር_ዜና #russia #planecrash #crimea #breakingnews #newsupdate

5 months ago
በደቡብ ኮሎምቢያ በደረሰ የወታደራዊ አውሮፕላን አደጋ የሟቾች ቁጥር 66 ደረሰ
ትናንት በደረሰው አደጋ ሌሎች በርካታ ሰዎች ደግሞ መጎዳታቸውን የላቲን አሜሪካዊቷ ሀገር የቅርብ ጊዜ መረጃ አመልክቷል።
እንደ መጀመሪያው መረጃ ከሆነ በአውሮፕላኑ ውስጥ 125 ሰዎች (114 ተጓዦች እና 11 የበረራ ሰራተኞች) የነበሩ ሲሆን፣ አብዛኛዎቹም ወታደሮች ናቸው።
ወታደራዊ ምንጮች ለሀገሪቱ መገናኛ ብዙሃን እንደገለጹት በአደጋው 58 የጦር ሰራዊት አባላት፣ 6 የአየር ኃይል አባላት እና 2 የፖሊስ መኮንኖች ህይወታቸው አልፏል።

Sponsored by
Surafel
5 months ago
#ቃለየሱስ በቀለ - የአቪየሽን ወርቃማው ጋዜጠኛ
#ethiopia | ተወዳጅ ሚድያ እና ኮምዩኒኬሽን ፣ መዝገበ-አእምሮ ( የአማርኛ ኢንሳይክሎፒዲያ ) ፕሮጀክቱ ለአገር የሠሩ ሰዎችን ታሪክ እየሰነደ እንደሆነ ይታወቃል። ይህ ታሪክ በዲጂታል ሚድያዎች ፣በመፅሀፍ፣በድምፅ ትረካና በሌሎችም መንገዶች እየቀረበ እንደሆነ ይታወቃል።በተለይ ጉግል ላይ ታሪካቸው ሲፈለግ የማይገኝ ሰዎች አሁን የሙያ አበርክቷቸው በቀላሉ ኢንተርኔት ላይ በግልፅ ተቀምጦ ይገኛልደ ባለፉት 4 ዓመት ከ 5 ወር ጊዜ ውስጥ የ423 ሰዎችን የሕይወትና የሥራ ታሪክ ለመሰነድ የቻልን ሲሆን 600 ገፅ ባላቸው ሁለት የተለያዩ መፅሐፎች ላይም ታሪኮቹ ዘመን ተሻጋሪ ሆነው እንዲቀመጡ አድርገናል።
#በዚህ የስነዳ ሥራችን ውስጥ በቅፅ 3 ከተካተቱት 20 ዘርፎች ውስጥ የሥራ ዘርፎች ውስጥ ሚድያ አንዱ ነው። በአሁኑ የሚድያ ሰዎችም፣ የቴአትር ባለሙያዎች እየተሰነዱ ይገኛሉ። አጠቃላይ 74 ከፍተኛ የሚድያ አመራሮች፣ሚኒስትሮች ፣ሚኒስትር ዴኤታዎች፣ የግል ሚድያ መሥራቾች፣ዋና አዘጋጆች እና መካከለኛ አመራሮች ተካተዋል። 35 ያህሉ በዋና ሥራ አስፈጻሚ ደረጃ ያሉ ሲሆን የሁሉም ታሪክ በተሟላ ደረጃ ለመሰነድ ተችሏል። የእነዚህን ሰዎች ታሪክ ሰንዶ ለአንባቢ ተደራሽ ማድረግ ፈታኝ ቢሆንም አሳክተነዋል። በዚህ ተግባራችንም ተጠናክረን እንቀጥላለን።
#ዛሬን ሰንደን የምናስነብባችሁ የሚድያ ባለሙያ የቃለየሱስ በቀለን የሙያ ታሪክ ነው። በሚድያው ሥራ ሩብ ክፍለ- ዘመን የዘለቀው ቃለየሱስ በአቬሽን እና ማዕድን ላይ ትኩረት ሰጥቶ በመዘገብ ትልቅ አሻራ አኑሯል። በጋዜጠኝነት ሙያ ውስጥ በአገራችን በአንድ ርዕስ ላይ ትኩረት ሰጥቶ ወይም ተክኖ መዘገብ ባልተለመደበት ሁኔታ ቃለየሱስ ችሎ አሳይቷል። ከባለታሪኩ የተገኘውን መረጃ በማግኘት፣ የቅርብ ሰዎቹን በማነጋገር የሙያ ታሪኩ ተሰንዷል። ዕዝራ እጅጉ እና ታደሠ ማሞ አጠናክረውታል።
፨፨፨፨፨ ፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨ ፨፨፨፨፨፨፨፨፨
#ትውልድና ዕድገት
‹‹የትኛውም አውሮፕላን ወደ አየር አኮብኩቦ መነሳቱ የተለመደ የጉዞው አማራጭ ቢሆንም አውሮፕላኑ ካሰበበት ደርሶ ማረፉ ደግሞ የግድ መሆን ያለበት ተግባር ነው፡፡››የሚል የአቪየሽን አባባል አለ፡፡በዚህ አባባል ተንደርድረን ወደ ውስጥ እንዝለቅ፡፡ሁሉም ዘርፍ የየራሱ አነፍናፊ ጋዜጠኞች እንዳሉት ሁሉ ቃለየሱስ በቀለ የተባለ ህልመኛና ደፋር ጋዜጠኛ በአቪየሽኑ ዘርፍ በተለየ መንገድ የራሱን የብዕር አሻራ ማኖር መቻሉ የዚህ ፅሁፋችን መነሻ ነው፡፡
#ቃለየሱስ በቀለ የውልደቱም ሆነ የእድገቱ መነሻ የምስራቅ ሸዋ አዳማ (ናዝሬት) ከተማ ናት፡፡ሀምሌ 18/1967 ዓ.ም በአዳማ ሀይለ ማሪያም ማሞ ሆስፒታል ቃለየሱስ የተባለ ብላቴና ከተፋፋመ ምጥ ውስጥ ወቅቱ አብዮታዊ ለውጥ ኢትዮጵያን በሚንጥበት በዚያ ጊዜ የለውጥ አየሩን እየማጉ ድምፃቸውን በማሰማት ይቺን ምድር ከተቀላቀሉት ጨቅላዎች አንዱ ሆኖ ተመዝግቦ በስሙ የልደት ካርድ ወጣለት፡፡
#ይህ ሰው ከመዋዕለ ህፃናት እስከ ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ያለውን የትምህርት ጉዞውን ያሳለፈው በናዝሬት ቅዱስ ዮሴፍ ት/ቤት ነው፡፡ትምህርት ቤቱ ከቀለም ትምህርት በተጨማሪ ተማሪዎችን በግብረ ገብና በመፅሀፍ ቅዱስ ትምህርት አንፆ በማብቃት ረገድ የተዋጣለት እንደነበር ቃለየሱስና አብረውት የተማሩት ሁሉ የሚመሰክሩት ሀቅ ነው፡፡
#በ1986 ዓ.ም ውጤታማ ሆኖ የአዲስ አበባ ንግድ ስራ ኮሌጅን ደጃፍ መርገጥ የቻለው ቃለየሱስ በኮሌጁ ሁለት ዓመታት በአካውንቲነግ ሙያ ተምሮ ቢያሳልፍም የሂሳብ ባለሙያ ሆኖ መቀጠሉ ስላልተዋጣልኝ ከልጅነቴ ጀምሮ አልመውና እፈልገው የነበረውን የጋዜጠኝነት ሙያ ለመቀላቀል መንከራተት የየዕለት ተግባሬ ሆነ ይላል፡፡ያኔምደፋር ብዕሩን ስሎ አሰሳውን የጀመረውና በእንግሊዝኛ ቋንቋ አርቲክሎችን እየዘጋጀ ለዴይሊ-ሞኒተር እና ዘ-ሪፖርተር ጋዜጦች ማቅረብ መጀመሩ የምኞት ጭላንጭሉን ወገግ አደረገለት፡፡
#ጋዜጠኝነት
እንደምኞትና ፍላጎቱም መንከራተቱ ፍሬ አፍርቶ ሳምንታዊ የቢዝነስ ጋዜጣ በሆነው ፎርቹን ጋዜጣ ላይ በሪፖርተርነት ተቀጥሮ ማገልገል ጀመረ፡፡ምኞትና ህልሙ መሬት እንዲረግጡ ቀዳሚውን ዕድል ያመቻቸለት የፎርቹን ጋዜጣ መስራችና ማኔጂንግ ኤዲተር የሆነው አቶ ታምራት ሀይለ ጊዮርጊስ በቃለየሱስ የህይወት ጉዞ ውስጥ ትልቅ ዋጋ አለው፡፡የጋዜጠኝነት ሀ ሁን ከማስቆጠር ጀምሮ ከዚያም ባሻገር አንደ ዓለም ባንክ፣የአሜሪካ ኤምባሲና ብሪቲሽ ካውንስል ያሉ ተቋማት በሚያዘጋጁት የሚዲያ ስልጠናዎች ላይ ተሳታፊ እንድሆን ዕድሉን ከማመቻቸት አልፎ ጠንካራ የጋዜጠኝነት ሰብዕናን እንድላበስ ያደረገኝ ባለውለታዬ ታምራት ነው ይላል ቃለየሱስ፡፡
#ወትሮም ለጋዜጠኝነት ታላቅ ጉጉት የነበረው ቃለየሱስ ዜና እንዴት ይፃፋል፣የዜና ግብዓቶች እንዴት ይሰበሰባሉ፣የዜና አስተማማኝ ምንጮችን እንዴት ማዳበር ይቻላል፣ፊቸር አርቲክል እንዴት ይፃፋል የሚሉና ሌሎችም ስልጠናዎችን አግኝቶ በብዕሩ መጠንከር የቻለው በፎርቹን ጋዜጣ ቆይታው እንደሆነ ያስታውሳል፡፡መች ይሄ ብቻ ከሀገር ውጪም በዓለም አቀፍ የአየር ትራንስፖርት በኤር ባስ አማካኝነት ከበረራና የበረራ ደህንነት መረጃ አሰጣጥ ጋር በተያያዘ ስልጠናዎችን በስፋት በመውሰድ የማረጋገጫ ሰርቲፊኬቶችን ተቀብሏል፡፡
#ቃለየሱስ ባለውለታዎቼ ብዙ ናቸው ይላል፡፡የፎርቹን ጋዜጣ ኤዲተር የነበሩት መላኩ ደምሴና ይበቃል ጌታሁን በጋዜጠኝነት ሥነ ምግባር ኮትኩተው ለውጤት አብቅተውኛል ካለ በኋላ በአጠቃላይ የፎርቹን ኤዲተሮች እኔን ጠፍጥፈው ሠርተውኛል ብል ማጋነን አይሆንም በሚል ያለፈበትን የጋዜጠኝነት ህይወት በአጭሩ ገልፆታል፡፡
#ከፎርቹን የሁለት ዓመታት ቆይታ በኋላ ሪፖርተር ጋዜጣን በመቀላቀል ለ18 ዓመታት ከከፍተኛ ሪፖርተርነት እስከ ኤዲተርነት ያገለገለው ቃለየሱስ ከሪፖርተር ጋዜጣ መሥራች አቶ አማረ አረጋዊ ጋር መሥራት መታደል ነው ይላል፡፡ከአቶ አማረ ጋዜጠኝነትን ብቻ ሳይሆን የአገር ፍቅርና ብሔራዊ ጥቅምን (National Interest)፣ደግነትንና ለሠራተኞቹ ያለውን ፍቅርና አክብሮት እንዲሁም ለጋዜጠኞች የሙያ ነፃነት ሰጥቶ ሠርቶ የሚያሠራበትን መልካም ትምህርት ቀስሜያለሁ ብሏል፡፡በሪፖርተር ሳለሁም በርካታ የሙያ ማሻሻያዎችንና የአጭር ጊዜ ሥልጠናዎችን በአገር ውስጥም ሆነ በውጭ አገሮች አግኝቻለሁ በማለት ትናንቱን ያመሰግናል፡፡
#በዘ -ሪፖርተር እንግሊዝኛ ጋዜጣ የማቀርባቸው ዘገባዎቼ በአብዛኛው ቢዝነስ ተኮር ነበሩ የሚለው ቃለየሱስ በተለይ በአቪዬሽንና በማዕድን ዘርፎች ላይ አተኩር ስለነበር፤በእነዚህ ዙሪያ በሚሠሩ የውጭ መጽሔቶች ለእኛም ጻፍልን የሚሉ ጥያቄዎች ቀርበውልኝ እ.ኤ.አ. ከ2006 ጀምሮ ኤርላይን ፍሊት ማኔጅመንት፣ወርልድ ኤር ኒውስ፣ኤርላይን ኢኮኖሚክስ፣አፍሪካን ኤሮስፔስና ዓረቢያን ኤሮስፔስ፣አቪዬሽን ኢንተርናሽናል ኒውስ፣አፍሪካን ቢዝነስ እና አፍሪካን ማይኒንግ ጆርናል ለተባሉ መጽሔቶች በፍሪላንስነት ለረዥም ዓመታት ሠርቻለሁ ይላል፡፡
እ.ኤ.አ.በ2008 በእንግሊዝ አገር በሚካሄድ “Best Aerospace Journalist of the Year” ሽልማት ታጭቼና ለንደን ተጋብዤ ዋናውን ሽልማት ባላሸንፍም፣"How Safe Are African Airlines?" በሚል ርዕስ በኤርላይን ፍሊት መጽሔት ላይ ያሳተምኩት ጽሑፍ ከ500 ለውድድር ከቀረቡ ጽሑፎች አምስቱ ምርጥ ውስጥ ለመግባት በመቻሉ፣ሰርተፊኬት ተበርክቶልኛል ብሏል፡፡
#በ2007 ዓ.ም. በትግራይ ሽመልባ የኤርትራ ስደተኞች መጠለያ ካምፕ ጉብኝት በማድረግ፣ ስለኤርትራዊያን ስደተኞች አሳዛኝ ሕይወት "The Woes of Eritrean Refugees” በሚል ርዕስ በዘ- ሪፖርተር ጋዜጣ ያሳተምኩት ሰፊ ጽሑፍ ጄኔቭ በሚገኘው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽነር (UNHCR) ዋና መሥሪያ ቤት ተመርጦ፣ለረዥም ጊዜ በድረ ገጻቸው ላይ ለንባብ ተቀምጦ ነበር፡፡በሻሸመኔ መልካ ኦዳ ስለሚገኙ የራስ ተፈሪያን ማኅበረሰቦች በቦታው ተገኝቼ የሠራሁት "The Plight of Rastafarians in Ethiopia" ዘገባ ከራስ ተፈሪያን ማኅረሰብ ምሥጋናና ዕውቅና አስገኝቶልኛል ይላል፡፡
ቃለየሱስን አንባቢያን የሚያውቁት ስለኢትዮጵያ አየር መንገድና በሀገሪቱ የተለያዩ ክፍሎች ስለሚካሄዱ የማዕድንና የነዳጅ ፍለጋዎች ተከታታይ በርካታ ዜናዎችን በሪፖርተር ጋዜጣ ላይ በመሥራቱ ነው፡፡ ከዚያ ባለፈም ከተለያዩ ዓለም አቀፍ ሚዲያዎችና ጋዜጠኞች ጋር የመሥራት ዕድሉን አግኝቷል፡፡
#የተለያዩ ዓለም አቀፍ ሚዲያዎች ለሥራ ወደ ኢትዮጵያ በሚመጡበት ወቅትም እነሱን በማገዝ የተለያዩ ሥራዎችን ከውኗል፡፡ከእነዚህም መካከል “CNN, Aljazeera, SKY News, The Economics, National Geographic, Los Angeles Times, News Week, New York Times, Christian Science Monitor, Chicago Tribune…” እና ሌሎችም ከተሳተፈባቸው ውስጥ ይገኙበታል፡፡
እ.ኤ.አ. በ2019 አደጋ የደረሰበት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላንን በተመለከተ ሲኤንኤን (CNN) በሠራቸው ዘገባዎች ላይ በረዳት ፕሮዲዩሰርነት የሠራ ሲሆን፣በወቅቱ ላበረከተው አስተዋጽኦ ከሲኤንኤን ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ምሥጋና ተችሮታል፡፡በዘገባዎቹ ላይም ሙሉ ስሙን በማስፈር ተገቢውን ዕውቅና ሰጥተውታል፡፡የአሜሪካው አልጄዚራ ኢንግሊሽ ቡድን ስለአውሮፕላን አደጋው ዶክመንተሪ ለማዘጋጀት አደጋው ከደረሰ ከአንድ ዓመት በኋላ ወደ ኢትዮጵያ በመጣበት ወቅትም፣አብሮ የአገር ውስጥ ፕሮዲዩሰር (Local Producer) ሆኖ ሠርቷል፡፡
መቼ ይሄ ብቻ ቃለየሱስ የ”Fault Lines” ፕሮግራም አዘጋጅ ከሆነው ጆሽ ረሺንግ (Josh Rushing) እና ፕሮዲዩሰሯ ካቢታ ቺኩሩ ጋር የሠሩት ዶክመንተሪ የተለያዩ አህጉሮችን የሸፈነ ሲሆን፣ለኤሚ አዋርድ ዕጩ ሆኖ ቀርቦም ነበር፡፡
#ከ18 ዓመታት አገልግሎት በኃላ እ.ኤ.አ. በ2020 ሪፖርተር ጋዜጣን ተሰናብቶ ኦሪጅንስ ሚዲያን በማቌቋምና ከኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 ሬዲዮ ጣቢያ የአየር ሰዓት በመውሰድ፣‹‹ኢትዮ የንግድና የኢንቨስትመንት መድረክ››የተሰኘ ፕሮግራም በሳምንት ለሁለት ቀናት እያዘጋጀ ለሦስት ዓመታት ያህል አቅርቧል፡፡ኦሪጅንስ የሚል የጉዞ (Travel Magazine) ለማሳተም እየንቀሳቀሰ የነበረ ቢሆንም፣በኮቪድ ወረርሽኝና በሰሜኑ የአገራችን ክፍል በተቀሰቀሰው ጦርነት ምክንያት ለፍሬ ሊበቃለት እንዳልቻለ በቁጭት ያስታውሳል፡፡
#ገጠመኞቹ
#ቃለየሱስ በጋዜጠኝነት ሙያ የገጠሙኝ ፈተናዎች ብዙ ናቸው ይላል፡፡ሙያው ራሱ የሚያስደስት ነገር እንዳለው ሁሉ ብዙ የሚያስጨንቁና የሚከብዱ ነገሮችም አሉት።ጋዜጠኛው ከህሊናው ጋር ተሟግቶና ሚዛኑን ጠብቆ የሚሰራው ነገር አንዱ ሲሆን።ዘገባን ወቅት ጠብቆ መስራትም የራሱ ፈተና አለው። ሚዛናዊነቱ ሳይጓደልም እንኳን ስለአንድ ነገር ሲፃፍ ወይም ሲዘገብ በዜናው ምከንያት የሚጠቀሙ ወገኖች ሊኖሩ ይችላሉ።
ወዲህ ደግሞ ጉዳቱም የዛን ያህል ነው።አንድ ሚዲያ በሚሰራው ዘገባ ባለስልጣንም ሆነ ካምፖኒ ሊሆን ይችላል የነበረውን አቅም ሊያጣ ይችላል።ይህ የሚዲያ ባህሪ ነው።ፈተናዎቹ የበዙ ቢሆኑም ጋዜጠኛው ሲፅፍ ሚዛናዊነት የተለበሰ መሆን አለበት ባይ ነው ቃለየሱስ።
#ቃለየሱስ ረጅም ዓመት የሠራው ህትመት ሚዲያ ላይ ነው።በአንድ ወቅት ከቺጋጎ ትሪቡን ጋዜጠኛ ጋር ወደ ትግራይ በማቅናት በኢትዮ ኤርትራ ስላለው ሁኔታ ለመዘገብ አመሩ፡፡ሽሬ አካባቢ ሽመልባ የሚባል የኤርትራ ስደተኞች ያሉበትን ስፍራ ጎብኝተውና አነጋግረዋቸው ወደ ሽራሮ ሄዱ፡፡የጦርነቱ ከተማ ወደነበረችው ባድመ ሄደውም ነዋሪዎችን፣አርሶ አደሮችና የከተማውን አስተዳደር ቃኝተውና ቃለመጠይቅ አድርገው ወደ ኤርትራ ድንበር ተጠጉ፡፡
#የኤርትራን መሬት ከወንዝ ባሻገር እያዩና የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት አባላት ሲያስጎበኟቸው የተቀበሩ ፈንጂዎች ስለነበሩ በተባበሩት መንግስታት የሰላም አስከባሪ ሀይል አማካኝነት የፈንጂ ማስወገድ ስራው እየተሰራ ስለነበር የምንረግጠውን መንገድ ጠቆሙን ካለ በኋላ ቀይ ቀይ የተደረገባቸውን ድንጋዮች አሳይተውን ለእግር ፉካ የምትሆን ድንጋይ አሳዩን።ቀይ ምልክት የተደረገባቸውን ድንጋዮች ትተን ሌላ ከረገጥን ልንሞት እንደምንችል ነገሩን።በፈንጂ መሀከል በጭንቅና በዝግታ ያሳለፍንውን ምንጊዜም አልረሳውም ይላል ቃለየሱስ።
ሌላ ጊዜ ደግሞ በአቬየሽን፣በነዳጅ እና ማዕድን ፍለጋ ስራዎች ዙሪያ ለመዘገብ ወደ ሱማሌ ክልል ይሄዳል፡፡ከኦጋዴን ነፃ አውጪ ጋር የነበሩ ውጊያዎች ስለነበሩ አንድ ጊዜ አቦሌ ከሚባል በደቡብ ምዕራብ በሚገኝ ኩባንያ የነዳጅ ስራ ፍለጋ በሚያደረግ ካምፕ ላይ ታጣቂዎቹ ጥቃት ሰንዝረው 9 ቻይናውያን እና ወደ 65 የሚጠጉ ኢትዮጵያውያን ህይወት ያልፋል።
ያንን ለመዘገብ ወደ አካባቢው የሄደው ቃለየሱስ ከቺጋጎ ትሪቡን ጋዜጠኛው ፖልስ አሎቤ ጋር ያለ እንቅልፍ ረጅም ቀናት በማሳለፋቸው በሀሩራማው ኦጋዴን ውስጥ ለረጅም ሰአታት ራሱን ስቶ ወደ ሆስፒታል ተወስዶ በህክምና የነቃበትን ጊዜም ያስታውሳል።ቃለየሱስ ገጠመኞቹ የትየለሌ ናቸው፡፡በችሎት ዘገባ እንዲሁም ጋምቤላ ለዘገባ ሄዶ ያጋጠሙትንም ሁሌ እያስታወሰ ይገረምባቸዋል፡፡ በተለያዩ የአቪዬሽን ስብሰባዎችና እንዲሁም በአውሮፕላን አምራች ካምፓኒዎች በአካል እየተገኘም የሚያማልሉ ዘገባዎችን አስነብቧል፡፡
#ስለ ቃለየሱስ የታላላቅ ሰዎች ምስክርነቶች
"ቃለ ኢየሱስ በቀለ ሪፖርተር ጋዜጣ ላይ በትጋት ከሠሩ ባለሙያዎች አንዱ ነው።" ይላል የሪፖርተር ጋዜጣ መስራች አማረ አረጋዊ። ምስክርነቱንም በመቀጠል፦
"... ቃለ ኢየሱስ በአቬሽን እና በማዕድን ዘገባዎች ላይ ያተኩር እንጁ የተሰጠውን ደስ ብሎት የሚሠራ ጋዜጠኛ ነው። የጋዜጠኝነት የሥነ ምግባር ደንብን አውቆ የሚተገብር ባለሙያ ነው። ፕሮፌሽናሊዝም እንዲሰፍን የሚታገል ጠንቃቃ ባለሙያ መሆኑን መመስከር እወዳለሁ።" በማለት ገልጿል
፨፨፨፨፨፨ ፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
#የአቶ ግርማ ዋቄ ምስክርነት
#ቃለ ኢየሱስ በቀለን ረጅም ጊዜ አውቀዋለሁ። ለአቬሽን የተለየ ፍቅር አለው። አለምአቀፍ ኮንፈረንሶች ላይ ንቁ ተሳትፎ ያደርጋል። ከዚያም በዕውቀት ላይ የተመሠረተ ፅሁፍ ያቀርባል።ብስለቱ ይደንቃል። ከሌሎች የስሚ ስሚ ሰምቶ ሳይሆን አንድን ጉዳይ ከስር ከመሠረቱ አውቆ የመዘገብ ችሎታውን አደንቅለታለሁ። ስለ አፍሪካ አየር መንገድ ፣ ስለ ኢትዮጵያ አየር መንገድ በወጉ ተረድቶ ስለሚፅፍም ፅሑፉ ተነባቢ ለመሆን ችሏል። ኢትዮጵያ ውስጥ አቬሽን ጋዜጠኝነት በጥልቀት ሲሠሪ የማውቀው እርሱን ነው።ሌሎችም አሉ። እርሱ ግን ከፍ አድርጎ በልህቀት የሚሠራ በመሆኑ ይለያል።
ገና አየር መንገድ ሲመጣ መረጃ ለማግኘት ፍላጎት ያሳያል። ዕውነትን ለማግኘት ይጎለጉላል። አፍሪካም ውስጥ ፈጠን ብሎ አቬሽን ጋዜጠኝነት ላይ የገባ በመሆኑ ይህም ግንባር ቀደም ያደርገዋል። ቃለኢየሱስ ካለበት ካናዳ ሆኖ የአቬሽን ጋዜጠኝነትን ሙያ እንዲያሳድግ ምክሬን እለግሰዋለሁ።
አቶ ግርማ ዋቄ
የቀድሞ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈፃሚ
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
‹‹እኔ ቃለየሱስ በቀለን የማውቀው ከ1993 ዓ.ም. ጀምሮ ለሁለት ዓመታት ፎርቹን ጋዜጣ አብረን ስንሠራ ጀምሮ ነው›› የሚለው የሪፖርተር ጋዜጣ ማኔጂንግ ኤዲተር የሆነው መላኩ ደምሴ ነው፡፡‹‹ከዚያም በኌላ ለ18 ዓመታት አብረን በሪፖርተር ጋዜጣ ሠርተናል፡፡ከጀማሪ ሪፖርተርነት አንስቶ እስከ አርታኢነት በዘለቀው የሥራ ጉዞው በሚገባ አውቀዋለሁ፡፡በተለይ በአቪዬሽንና በማዕድናት ዘርፍ እጅግ በጣም በርካታ ዘገባዎችን የሠራ ሲሆን፣በሁሉም ሥራዎቹ አንጀት አርስ የሚባል ጋዜጠኛ ነው፡፡ጋዜጠኝነትን ከልቡ ከማፍቀሩ የተነሳ አብረው ለሚሠሩ ጋዜጠኞች ጭምር የሙያውን ፍቅር የማጋባት ችሎታ ያለው ነው፡፡ቃለየሱስ ዘገባዎችን ሲሠራ የሁሉንም ባለጉዳዮች ደምፅ ከማካተት በተጨማሪ፣አንባቢያን ለርዕሰ ጉዳዩ ቅርበት እንዲፈጥሩ የሚያስችል ስሜትን የተካነ ነው፡፡
‹‹ኢትዮጵያ ውስጥ በተለይ በአቪዬሽን ዘገባ በግንባር ቀደምነትነት የሚጠቀስ ጋዜጠኛ ማነው ቢባል በመጀመሪያው ረድፍ ላይ የሚገኘው ቃለየሱስ ነው፡፡በዓለም ላይ አሉ የሚባሉ አውሮፕላን አምራች ኩባንያዎችን፣አየር መንገዶችን፣በአቪዬሽን ዘርፍ ውስጥ የተሰማሩ የሥራ ኃላፊዎችንና ባለሙያዎችን ሳይቀር በተለያዩ አገሮች በማግኘት በሪፖርቶቹ ውስጥ ድምፃቸውን ከማካተቱም በላይ በቃለ ምልልስ ጭምር ለአንባቢያን ተደራሽ በማድረግም ወደር የለውም፡፡የአውሮፕላን አደጋዎች ሲያጋጥሙም ሆነ የተለዩ ክስተቶች ሲኖሩ ከሚሠራቸው ዘገባዎች በተጨማሪ፣በተለያዩ ቴሌቪዥን ጣቢያዎች ለማብራሪያ የሚፈለገው ቃለየሱስ ነው፡፡በውጭ ለሚዘጋጁና ቁጥራቸው ቀላል ለማይባል የአቪዬሽን መጽሔቶች በርካታ ዘገባዎችን በመሥራትም ታዋቂ ነው፡፡
‹‹በማዕድናት ዘርፍም ከካሉብ ነዳጅ የጀመረው የጋዜጠኝነት ህይወቱ በተለያዩ ክልሎች የሚደረጉ የነዳጅ፣የወርቅ፣የብረት፣የፖታሽ፣የታንታለም፣የኦፓልና ሌሎች የከበሩ ማዕድናት ፍለጋ ሥራዎችን በስፋት የዳሰሰ ነው፡፡በኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ግድብ ግንባታዎች፣በጂኦ ተርማል ፕሮጀክቶች፣ በፀሐይና በንፋስ ኃይል ማመንጫዎች፣በሲሚንቶና በሌሎች የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴዎችም ሰፋፊ ዘገባዎችን በማበርከት ስመጥር ሆኖ ዘልቌል፡፡በፖለቲካው መስክ ደግሞ በተለያዩ አገራዊ ምርጫዎች ከአዲስ አበባ ውጪ በክልሎች ተሰማርቶ አመርቂ ሪፖርቶችን በማቅረብ ችሎታውን ማስመስከር የቻለ ነው፡፡ከሪፖርተር በገዛ ፈቃዱ ከተሰናበተ በኃላም በኤፍኤም 107.8 ሬዲዮ ጣቢያ የአየር ሰዓት ወስዶ ያቀርባቸው የነበሩ የቢዝነስ ፕሮግራሞቹ፣የቃለየሱስን ችሎታ ከጋዜጣ አንባቢያን ወደ ሬዲዮ አድማጮች በማዝለቅ ረገድ ትልቅ ግምት የሚሰጣቸው ነበሩ፡፡
‹‹ቃለየሱስ ግልጽ፣ ቅን፣ ሰብዓዊነትን የሚያስቀድም፣ኃላፊነት የሚሰማው፣ በአስገራሚ ትውስታው የረሳናቸውን ጉዳዮች የማስታወስ ችሎታ ያለው፣በቀልድም ሆነ በቁምነገር የሚታወቅ፣ ከማንኛውም ሰው ጋር ወዳጅነት ለመፍጠር ምንጊዜም ዝግጁ የሆነ፣በተለይ በሪፖርተር የሥራ ባልደረቦቹ ዘንድ በእጅጉ ተወዳጅና ምሥጉን ጋዜጠኛ ነው፡፡በተጨማሪም በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ በሚሰጣቸው ሰፊና ጥልቅ ትንተናዎቹ የሚታወቅ ሲሆን፣ብዙዎችም በዚህ መጠን ለነገሮች ትኩረት ሰጥቶ የማስረዳት ብቃቱን በአድናቆት የሚመሰክሩለት ነው፡፡እኔም ከሁለት አሠርት ዓመታት በላይ አብሬው ስለሠራሁ ችሎታውን በዚህ መጠን ስገልጽ በከፍተኛ ስሜት ሲሆን፣ይህንን ከመሰለ ብርቱና ታታሪ ጋዜጠኛ ጋር የመሥራት ዕድል በማግኘቴ በእጅጉ ደስተኛ ነኝ›› በማለት መላኩ ምስክርነቱን አጠቃሏል፡፡
ካፒቴን ሰሎሞን ግዛው ስለ ቃለየሱስ በሰጡት ምሥክርነት ‹‹እኔ እሱን ለአየር መንገዱ ልዩ እንደ ሆነ ሰው አየዋለሁ።በጣም ትሁት፣አዳማጭ የሆነ ሰው ነው።ከየት እንዳመጣው ባላውቅም ልዩ የሆነ የኢንግሊዘኛ ፀሀፊ ነበር።በሁለት ምክንያት የሱን ፅሁፍ አነብ ነበር፡፡አንዱ በፅሁፉ ለመደሰትና እንደ ግጥም ስለምወደው ነው።ሌላው ከእውቀቱ ወይም አንብቦም ይሁን ባላውቅም የፅሁፎቹ ይዘት በሚያውቀው ነገር ላይ የተመሰረተ በመሆኑ ነው።በዚህም በጣም አበረታታዋለሁ።
‹‹ከተዋወቅን 15 ዓመታት ሆኖናል።በውጪ ህትመቶች ላይ የሚያወጣቸው ስራዎች ቃለየሱስ ብሎ ስሙ ይገለፅ ይሆናል እንጂ ማንም ነጭ የሚፅፈው አይነት ፅሁፍ ነው።የፅሁፉ ይዘትና አያያዝ ደረጃውን የጠበቀ ነው።የሚፅፍባቸው መፅሄቶች ደረጃቸውን የጠበቁና ትላልቅ ናቸው።ነገር ግን ደረጃቸውን ጠብቀዋል የሚባሉትም አንዳንዴ ትርኪምርኪ ሲፅፉም ይታያል።ግን የሱ ፅሁፍ በጣም የሚያኮራ ነው።ሌላው ዜግነቱን የሚወድ ሰው ነው።ተጨባጭ በሆነ መልኩ ለኢትዮጵያ አየርመንገድ በቦታው ካሉት ህዝብ ግንኙነቶች እሱ ብዙ የሰራ ይመስለኛል።እውቅናና ሽልማት ሊሰጠው በርታ ሊባል የሚገባው ልጅ ነው።ወገቡን ይዞ ነበር ለአየር መንገዱ ይሰራ የነበረው።አሁንም ቢሆን ባለበት ሆኖ ለአየርመንገዱ ነገሮችን መስመር የሚያሲዝ ሰው ነው››ብለዋል፡፡
፨፨፨፨፨፨፨
የቀድሞ የሲቪል አቬሽን ዋና ዳይሬክተር የነበሩት አቶ ወሰንየለህ ሁነኛው በበኩላቸው ‹‹ከተዋወቅን ከ7 ዓመት በላይ ይሆነናል።እኔ ከማቃቸው የሚዲያ ሰዎች በጋዜጠኝነት የሱን ያህል ብዙም አቬሽን ዘርፉ ላይ ገብቶ እያንዳንዱን ነገር አይቶ የኢትዮጵያ አየር መንገድም ይሁን የግል ኦፕሬተሮቹም ጋር እንደሱ የሚፅፍ አላየሁም።እሱ ነው የተሻለ ጠይቆ አንብቦ ተረድቶ አስተዋጽዖ ለማድረግ የሚጥረው።በዛ ወቅት ቃለ እየሱስ ጥሩ ዘጋቢ ነበር።ብዙ መፅሄቶች ላይ ይሳተፋል አንዳንድ አለም አቀፍ ስብሰባዎች ላይ ይሄዳል። በኢትዮጵያ አየርመንገድና በሲቪል አቬየሽን ላይ የተለየ እውቀት ያለው ነው።ምክንያቱም በየእለቱ ስለሚከታተል ኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን አቬየሽን ኢንዱስትሪ በደንብ ያውቀው ነበርና ነው።
‹‹አቬየሽን ኢንዱስትሪው በእነዚህ መፅሄቶች በብዙ መንገድ ይጠቀማል።ህብረተሰቡ አቬየሽኑም ሆነ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ራሱን ከማስተዋወቁ በላይ ምን ላይ እንዳለ እና በተለየ አካል እንዲሰራለት ትክክለኛነቱን ይረጋገጣል።እንዲሁም ምን ያህል የግል ኦፕሬተሮች ምን ያህል በኢኮኖሚው ይሳተፋሉ የሚለውንም ለህብረተሰቡም ለመንግስትም መረጃ ይሰጣል።ስራዎቹ ለብዙ ነገሮች የመረጃ ምንጮች ሆነው ያገለግላሉ ።
‹‹ቃለእየሱስ በዚያ ወቅት የሚያደርገው የኢትዮጵያን አቬየሽን ኢንዱስትሪ ከሌላው እያነፃፀረ በሚያውቀው ልክ ለህብረተሰቡ ሙሉ መረጃ ይሰጣል።ለግል ኦፕሬተሮችም ለኢትዮጵያ አየር መንገድም ግብዐት የሚሆኑ ብዙ ነገሮችን ያደርጋል።በተዘዋዋሪም ያስተዋውቃል።እውነተኛ መረጃ ሲያቀርብ ሰው ስለ አቬየሽን ኢንዱስትሪ ያለውን እውቀት ያዳብራል።አብዛኛው ሰው ስለ ግል ኦፕሬተር አያውቅም አውሮፕላን አላቸው ወይ ? ብሎ የሚጠይቅም ብዙ ሰው ነው።በዚህ ጉዳይ ላይ በብዛት የሚሰራው ቃለእየሱስ ነበር››ብለዋል፡፡
‹‹በኢትዮጵያ የጉዞና ቱሪዝም ዘርፍ ላይ የቃለየሱስ አስተዋፅኦ ትልቅ ነው።››ብለው ምስክርነታቸውን መስጠት የጀመሩት አቶ ተወልደ ገብረማርያም የቀድሞ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ናቸው፡፡‹‹ቃለየሱስና እኔ ለረጅም ጊዜ እንተዋወቃለን በ«Reporter» ጋዜጣ ሲሰራ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዜናዎችንና እድገቶችን ይዘግብ ነበር።በቀጣይ የአቪዬሽን ዘርፍ ላይ ጥልቅ ፍላጎት አሳየ፤እኛም ከIATA ጋር እንዲገናኝ አደረግነው፣በተለይም በየዓመቱ በተለያዩ የዓለም ክፍሎች የሚካሄዱ የIATA አመታዊ አጠቃላይ ጉባኤዎች (AGM) ላይ የፕሬስ ኮንፈረንሶች ላይ ይሳተፍ ነበር።
‹‹በአፍሪካ አየር እና አቪየሽን (African Aerospace and Aviation) መጽሔት እና በሌሎች ከአቪየሽን ጋር የተያያዙ መጽሔቶች ላይ ጽሁፎችን ይጽፍ ነበር።በአጋርነትም ብዙ ፕሮጀክቶችን አከናውነናል። እኔም የኢትዮጵያ ቱሪዝም ቦርድ ሊቀመንበር በነበርኩበት ሰዓት፣የራሱን የጉዞና ቱሪዝም መጽሔት እንዲጀምር ወይም እንዲያስብበት ሀሣብ አቀርብለት ነበር፤እርሱም ይህን ሀሳብ በአዎንታ ይመልከተው ነበር።
‹‹በአጠቃላይ፣ ይህ ዘርፍ እስከዛሬም በቂ የሚዲያ ሽፋንና የማስተዋወቂያ መድረክ ስላልነበረው፣ ቃለየሱስ ይህን ክፍተት ልብ ብሎ በማጤን በኢትዮጵያ የጉዞና ቱሪዝም ዘርፍ ልማት ላይ ከፍተኛ ስራ ሰርቷል።በእኔ አመለካከት፣ያበረከተው አስተዋፅኦ አስደናቂ ነው፣ለሥራውም እውቅናና ምስጋና ሊቀርብለት ይገባል››ብለዋል፡፡
ሲጠቃለል ከ15 አመት በላይ በአለም አቀፍ የአቪየሽን ስብሰባዎችን በአሜሪካ፣አውሮፓ፣አፍሪካ፣ መካከሉኛው ምስራቅ እና ኤሽያ ተሳትፌያለሁ 36 ሃገሮችንም የማየት እድል ገጥሞኛል የሚለው የአቪየሺን ባለወርቃማ ብዕሩ ቃለየሱስ በቀለ እ.ኤ.አ.ከ2023 መጨረሻ ጀምሮ ኑሮውን በካናዳ ያደረገ ሲሆን፤ለአፍሪካ ኤሮስፔስና አቪየሽን ኢንተርናሽናል ኒውስ በፍሪላንስነት በማገልገል ላይ ይገኛል፡፡

6 months ago
በኮሎምቢያ በደረሰ የአውሮፕላን አደጋ የባለሥልጣናትን ሕይወት ጨምሮ የ15 ሰዎች ሕይወት አለፈ
#ethiopia | በሰሜን ምሥራቅ ኮሎምቢያ ከቬንዙዌላ ድንበር አቅራቢያ በደረሰ አሰቃቂ የአውሮፕላን የመከስከስ አደጋ፣ የሕግ ባለሙያዎችንና ከፍተኛ የፖለቲካ አመራሮችን ጨምሮ የ15 ሰዎች ሕይወት ማለፉ ተረጋገጠ።
እንደ ዘገባዎች ከሆነ፣ አውሮፕላኑ በረራ ላይ እያለ አደጋው ያጋጠመው ፓለቲከኞችን አሳፍሮ በመጓዝ ላይ ሳለ ነው። በአደጋው ሕይወታቸው ከጠፋው መካከልም የሚከተሉት ታዋቂ ግለሰቦች ይገኙበታል፦
* ዲዮጀነስ ኩንቴሮ፡ የኮሎምቢያ የተወካዮች ምክር ቤት የካታቱምቦ ክልል ተወካይ።
* ካርሎስ ሳልሴዶ፡ የኮንግረንስ ምርጫ እጩ።
የሀገሪቱ የትራንስፖርት ሚኒስትር በሰጡት መግለጫ፣ በአደጋው ክፉኛ ማዘናቸውን ገልጸው በአውሮፕላኑ ውስጥ ከነበሩት ባለሥልጣናት መካከል በሕይወት የተረፈ ሰው አለመኖሩን ይፋ አድርገዋል።
ምንም እንኳ የኮሎምቢያ ባለሥልጣናት የአደጋውን ትክክለኛ መንስኤ ለማወቅ ምርመራ እያደረጉ ቢሆንም፣ አውሮፕላኑ ከመከስከሱ ቀደም ብሎ ግን የድንገተኛ አደጋ ምልክት መብራቱ (Emergency light) አገልግሎት እየሰጠ እንዳልነበር ፍንጮች መኖራቸው ተጠቁሟል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #colombia #planecrash #breakingnews #aviationsafety #restinpeace #ኮሎምቢያ #የአውሮፕላንአደጋ #ዜና

የሕንድ ከፍተኛ ባለሥልጣን በአውሮፕላን አደጋ ሕይወታቸው አለፈ
የሕንድ በሀብቷ ቀዳሚ የሆነችው የማሃራሽትራ (ግዛት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አጂት ፓዋር ፣ ዛሬ ረቡዕ በደረሰ አሰቃቂ የአውሮፕላን አደጋ ከነበረባቸው 4 ሰዎች ጋር ሕይወታቸው ማለፉ ተረጋግጧል።
አደጋው የተከሰተው፦ ባለሥልጣኑ ለምርጫ ቅስቀሳ ወደ ትውልድ ቀያቸው በማቅናት ላይ ሳሉ፣ የግል አውሮፕላናቸው ባራማቲ አውሮፕላን ማረፊያ ላይ ለማረፍ ሲሞክር ተከስክሶ እሳት በመነሳቱ ነው።
ተጎጂዎች፦ በአውሮፕላኑ ውስጥ የነበሩት አምስቱም ሰዎች (ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩን ጨምሮ፣ ሁለት ረዳቶቻቸው እና ሁለት የአውሮፕላኑ ሰራተኞች) በሙሉ ሕይወታቸው አልፏል።
የአውሮፕላኑ ዓይነት፦ ሊርጄት 45 የተሰኘ ሲሆን፣ የኒው ዴልሂው "VSR Group" ንብረት እንደሆነ ታውቋል።
ምክንያት፦ የአደጋው መንስኤ በዝርዝር ባይታወቅም፣ በወቅቱ የነበረው ከባድ ጭጋግ እና ታይነት መቀነስ (Poor visibility) ለክስተቱ መንስኤ ሳይሆን እንዳልቀረ የሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን ጠቁሟል።
የ66 ዓመቱ አጂት ፓዋር በሕንድ ፖለቲካ ውስጥ ትልቅ ተፅዕኖ የነበራቸውና በማሃራሽትራ ግዛት ለረጅም ጊዜ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርነት ያገለገሉ አንጋፋ መሪ ነበሩ። የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ የተሰማቸውን ጥልቅ ሀዘን ገልጸዋል።

🚨 ሰበር ዜና፡ በህንድ በደረሰ የአውሮፕላን አደጋ የግዛት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ህይወት አለፈ
#ethiopia | በምዕራብ ህንድ ማሃራሽትራ ግዛት በደረሰ አሰቃቂ የግል አውሮፕላን አደጋ፣ የግዛቲቱ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና አራት ሌሎች ሰዎች ህይወታቸው ማለፉ ተረጋገጠ።
የአደጋው ዝርዝር ሁኔታ፦
አደጋው የደረሰው የግል አውሮፕላኑ ከመደበኛው የበረራ መስመር ወጥቶ መሬት ላይ በመከስከሱ ነው። በአውሮፕላኑ ውስጥ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩን ጨምሮ ረዳቶቻቸው እና የበረራ ሰራተኞች የነበሩ ሲሆን፣ የነፍስ አድን ሰራተኞች በፍጥነት ወደ ስፍራው ቢደርሱም በአውሮፕላኑ ውስጥ የነበሩትን አምስት ሰዎች በሙሉ ህይወት ማዳን አልተቻለም።
የአደጋው መንስኤ፦
የህንድ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን የአደጋውን መንስኤ ለማወቅ ምርመራ መጀመሩን ገልጿል። የመጀመሪያ ደረጃ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት፦
* በአደጋው ወቅት በአካባቢው አስቸጋሪ የአየር ሁኔታ እንደነበረ ተጠቁሟል።
* የቴክኒክ ብልሽት ይኑር አይኑር በዝርዝር እየተመረመረ ይገኛል።
የተሰጡ ምላሾች፦
የህንድ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት በደረሰው አደጋ የተሰማቸውን ጥልቅ ሀዘን ገልጸዋል። የግዛቲቱ አስተዳደር ብሄራዊ የሀዘን ቀን ሊያውጅ እንደሚችል የተነገረ ሲሆን፣ ታዛቢዎች ይህ አደጋ በማሃራሽትራ ግዛት ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ ውስጥ ትልቅ ክፍተት የሚፈጥር መሆኑን እየገለጹ ይገኛሉ።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #india #maharashtra #breakingnews #planecrash #politicalnews #safetyfirst #aviationaccident #ethiopianews

8 months ago
በአውሮፕላን አደጋ የሞቱት ሊቢያዊ ጄኔራል ማን ነበሩ? ጋዳፊን ይቃወሙ ነበር፣ በርስ በርስ ጦርነቱም ተሳትፈዋል
የሊቢያ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጄኔራል መሐመድ አል-ሐዳድ ከቱርክ ይፋዊ ጉብኝት ሲመለሱ የነበሩበት የግል አውሮፕላን መከስከስ ከፍተኛ ትኩረት ስቧል። በትሪፖሊ የሚገኘው መንግስት የእሳቸውንና በአውሮፕላኑ ውስጥ የነበሩ ሌሎች አራት ሰዎች መሞታቸውን አረጋግጧል።
የሊቢያ ጦር ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም በሀገሪቱ ወታደራዊ አመራር ውስጥ ቁልፍ ከሆኑ ሰዎች አንዱ ነበሩ። እ.ኤ.አ. በ1967 በሚስራታ የተወለዱ ሲሆን፣ በ1987 ከሊቢያ ወታደራዊ አካዳሚ ተመርቀዋል። በስራ ዘመናቸው እ.ኤ.አ. የ2011 የርስ በርስ ጦርነት ላይ የተሳተፉ ሲሆን፣ የሙአመር ጋዳፊን ስርዓት በተዋጉት አብዮታዊ ኃይሎች ውስጥ አገልግለዋል። በዚህም ከጦርነቱ በኋላ በነበረችው ሊቢያ ውስጥ ጉልህ ወታደራዊ መሪ በመሆን ዝናን አትርፈዋል።
ከጋዳፊ ውድቀት በኋላ አል-ሐዳድ በሊቢያ ጦር ውስጥ ወሳኝ የኃላፊነት ቦታዎችን የያዙ ሲሆን፣ እ.ኤ.አ. በ2021 የሀገሪቱን ወታደራዊ ኃይሎች በብሔራዊ አንድነት መንግስት (GNU) ስር መልሶ ለማደራጀትና ለማዋሃድ የሚደረገውን ጥረት በመምራት ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ሆነው ተሾመዋል።
በስራ ዘመናቸው ወታደራዊ ኃይልን በማጠናከር እና ከቱርክና ከብሪታኒያ ጨምሮ ከአለም አቀፍ አጋሮች ጋር መተባበር ጋር ትኩረት አድርገው ነበር።
እንደ ሊቢያ መገናኛ ብዙኃን ዘገባዎች ከሆነ፣ ሚሊሻዎችን የማዋሃድ እና አንድ ወታደራዊ መዋቅር የመፍጠር ስትራቴጂያቸው በሊቢያ ስርዓትንና ደህንነትን ለማስፈን ወሳኝ ሰው ነበሩ። እንዲሁም የቀጠናውን ደህንነት ለመጠበቅ ከሰሜን አፍሪካ እና ከአውሮፓ ሀገራት ጋር ለነበረው ትብብር አስተዋጽኦ አድርገዋል።
አል-ሐዳድን ይዞ የነበረው አውሮፕላን በሃይማና ወረዳ ከሚገኘው ኬሲካቫክ መንደር ሁለት ኪሎ ሜትር ያህል ርቀት ላይ ተከስክሷል። የቱርክ የፍትህ ሚኒስትር ይልማዝ ቱንች ስለ አደጋው ምርመራ መጀመሩን ገልጸዋል።

ጀነራሉ የተሳፈሩበት አውሮፕላን ተከስክሶ ሞቱ
#ethiopia | የሊቢያ ጠቅላይ ሚኒስትር አብዱልሃሚድ ድቤይቤህ የሊቢያ ጦር አዛዥ መሐመድ አሊ አህመድ አል-ሃዳድ እና ሌሎች አራት ሰዎች በቱርክ ዋና ከተማ አንካራ አቅራቢያ በደረሰ የአውሮፕላን አደጋ መሞታቸውን አረጋግጠዋል።

የሊቢያው ጦር አዛዥ በአውሮፕላን አደጋ ህይወታቸው አለፈ
የሊቢያው ጦር አዛዥ ጄኔራል መሐመድ አሊ አህመድ አል-ሃዳድ እና ሌሎች አራት ከፍተኛ የሊቢያ ባለሥልጣናት ማክሰኞ ምሽት ከቱርክ መዲና አንካራ ወደ ሊቢያ ዋና ከተማ ትሪፖሊ በመመለስ ላይ ሳሉ አንካራ አቅራቢያ በደረሰ የአውሮፕላን አደጋ መሞታቸውን አልጀዚራ ዘግቧል።
የቱርክ የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር አሊ ያርሊካያ 'ኤክስ' (X) በተሰኘው የማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ እንደገለጹት፣ ' ፋልኮን 50 የተሰኘችው የግል ጄት ማክሰኞ ምሽት ምሽት 2:10 ሰዓት ከአንካራው ኢሰንቦጋ አየር ማረፊያ ተነስታ ነበር። አውሮፕላኗ 2:52 ሰዓት ላይ ከመቆጣጠሪያ ክፍሉ ጋር የነበራት የሬዲዮ ግንኙነት ተቋርጧል።
ሚኒስትሩ አክለውም አውሮፕላኑ ግንኙነቱ ከመቋረጡ በፊት በሃይማና የአደጋ ጊዜ ማረፊያ ጠይቆ እንደነበር ገልጸዋል።
የቱርክ ወታደራዊ ኃይል የአውሮፕላኑን ስብርባሪ ከአንካራ 74 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኘው በሃይማና ወረዳ ቀሲክካቫክ መንደር አቅራቢያ አግኝተውታል።
የሊቢያ ጠቅላይ ሚኒስትር አብዱል ሃሚድ ድበይባ በጉዳዩ ላይ ያላቸውን ጥልቅ ሀዘን በመግለጽ መግለጫ አውጥተዋል። በመግለጫውም “ይህ አደጋ ለሀገሪቱ ትልቅ አሳዛኝ ክስተት ነው። ለጦር ኃይሉና ለሀገሪቱ ሕዝብ የማይተካ ኪሳራ ነው። ሀገራቸውን በታማኝነት እና በቅንነት ያገለገሉ፣ የሥነ-ምግባር እና የብሔራዊ ቁርጠኝነት ተምሳሌት የሆኑ ሰዎችን አጥተናል” ብለዋል።

9 months ago
✈️ ቦይንግ በኢትዮጵያ በተከሰከሰው አውሮፕላን አደጋ ለሞተ ሰው ቤተሰቦች 28 ሚሊዮን ዶላር እንዲከፍል ታዘዘ
#ethiopia | ፍርድ ቤቱ በብይኑ የካሳ ክፍያው እንዲፈጸም ያዘዘው በአደጋው ለሞተችወ የተባበሩት መንግስታት የአካባቢ ጥበቃ ተሟጋች ሺካ ጋርግ ቤተሰቦች ነው።
በአሜሪካ ፣ ቺካጎ የሚገኝ አንድ የፌዴራል ፍርድ ቤት የአውሮፕላን አምራቹን ቦይንግ የ737 ማክስ ጄት አውሮፕላኑ ተከስክሶ ለሞተው የተባበሩት መንግስታት የአካባቢ ጥበቃ ሰራተኛ ቤተሰብ ቢያንስ 28 ሚሊዮን ዶላር ካሳ እንዲከፍል አዟል ሲል ሮይተርስ ዘግቧል።
ይህ ከስድስት አመት በፊት በተከሰተው አደጋ አመት በፊት ኢንዶኔዥያ ውስጥ ሌላ የ737 ማክስ ቦይንግ ተከስክሶ ነበር።
በእነዚህ ሁለት አደጋዎች በድምሩ 346 ሰዎች ሞተዋል።
እነዚህን ሁለት አደጋዎች ተከትሎ በቦይንግ ላይ ብዙ ክሶች ተመስርተዋል።
ከእነዚህ ክሶች ውስጥ ለመጀመሪያው ውሳኔ ረቡዕ ተሰጥቷል። ፍርድ ቤቱ ካሳው በአደጋው ለሞተው የተባበሩት መንግስታት ሰራተኛ ሺካ ጋርግ ቤተሰብ እንዲከፈል አዟል።
የጋርግ ቤተሰብ ጠበቃ እንደተናገሩት፣ ሁለቱ ወገኖች ረቡዕ ጠዋት ስምምነት ላይ ደርሰዋል። በስምምነቱ መሠረት፣ የጋርግ ቤተሰብ በፍርድ ቤቱ ውሳኔ የታዘዘውን ሙሉ መጠን ከ26 በመቶ ወለድ ጋር በመደመር በድምሩ 35.85 ሚሊዮን ዶላር ያገኛሉ።
በቦይንግ ቃል አቀባይ በሰጡት መግለጫ፣ ኩባንያው በሁለቱ የአውሮፕላን አደጋዎች ውስጥ ውድ ሰዎቻቸውን ላጡ ሁሉ ጥልቅ ሀዘኑን ይገልጻል።
በመግለጫው ላይ "አብዛኛዎቹን እነዚህን የካሳ ጥያቄዎች በሽምግልና ብንፈታም፣ ቤተሰቦቹ አሁንም ለካሳ የፍርድ ቤት ክስ የማቅረብ መብት አላቸው፣ እኛም ያንን መብት እናከብራለን" ብለዋል።
የጋርግ ቤተሰብን የወከሉት ጠበቆች ሻኒን ስፔክተር እና ኤልዛቤት ክራውፎርድ በሰጡት መግለጫ "ይህ ውሳኔ ቦይንግ ለሰራው ጥፋት በይፋ ተጠያቂ መሆኑን ያረጋግጣል" ብለዋል።
የሟች ጋርግ ጠበቆች እንደተናገሩት፣ የ32 አመቱ ሺካ ጋርግ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራ 302 ተሳፋሪ ነበረች። በረራው ከኢትዮጵያ አዲስ አበባ ወደ ናይሮቢ፣ ኬንያ በመጓዝ ላይ የነበረ ቢሆንም ከተነሳ በደቂቃዎች ውስጥ ተከስክሷል።
ክሱ የ737 ማክስ አውሮፕላን ንድፉ የተሳሳተ ነው። ቦይንግ ተሳፋሪዎችንና ስለ አደጋው ማስጠንቀቅ አልቻለም የሚል ክስ ይዟል ሲል ፊደል ፖስት ዘግቧል።

ፍርድ ቤቱ በብይኑ የካሳ ክፍያው እንዲፈጸም ያዘዘው በአደጋው ለሞተችወ የተባበሩት መንግስታት የአካባቢ ጥበቃ ተሟጋች ሺካ ጋርግ ቤተሰቦች ነው።

ክሱ የ737 ማክስ አውሮፕላን ንድፉ የተሳሳተ ነው። ቦይንግ ተሳፋሪዎችንና ስለ አደጋው ማስጠንቀቅ አልቻለም የሚል ክስ ይዟል።

ጆርጂያ ውስጥ በደረሰ የአውሮፕላን አደጋ 20 የቱርክ ወታደሮች ሕይወታቸው አለፈ
#ethiopia | መከላከያ ሚኒስቴር እንዳስታወቀው፣ ከአዘርባጃን ወደ ቱርክ በመጓዝ ላይ የነበረ አንድ የቱርክ C-130 ወታደራዊ የጭነት አውሮፕላን በጆርጂያ ግዛት ውስጥ፣ ከአዘርባጃን ድንበር አቅራቢያ ተከስክሷል።
በደረሰው አሳዛኝ አደጋ በአውሮፕላኑ ውስጥ የነበሩ ሃያ (20) የቱርክ ወታደራዊ ሠራተኞች በሙሉ ሕይወታቸውን እንዳጡ የቱርክ የመከላከያ ሚኒስቴር ማረጋገጫ ሰጥቷል።
አደጋው የተከሰተው አውሮፕላኑ ከአዘርባጃን ከተነሳ በኋላ ወደ ቱርክ እያመራ ባለበት ወቅት ሲሆን፣ የአደጋው መንስኤ እስካሁን በግልጽ አልታወቀም።
የጆርጂያ ባለሥልጣናት ከአዘርባጃን እና ቱርክ ጋር በመተባበር የፍለጋና የማዳን ሥራዎችን ማከናወናቸውን የሚገልጽ መረጃም ተመላክቷል ያለው መናኸሪያ ኤፍ ኤም ነው።

የአውሮፕላን አደጋ በአሜሪካ
#ethiopia | በአሜሪካ ኬንታኪ የጭነት አውሮፕላን ተከስክሶ የሰባት ሰዎች ህይወት ማለፉ ተሰማ፡፡
ማክሰኞ ማምሻውን በሊውሲቭል ኬንታኪ በመነሳት ላይ የነበረ አውሮፕላን በደረሰ አደጋ ሰባት ሰዎች ህይወት ማለፉ ተገልጻል፡፡
እንደ አካባቢው አስተዳደር መረጃ መሰረት ከሞቱት ሰዎች ሶስቱ የአውሮፕላኑ ሰራተኞች ሊሆኑ እንደሚችሉ ገልፆ።
በሉዊሲቪል አለም አቀፍ አየር ማረፊያ የአውሮፕላኑ መፈንዳትን ተከትሎ በደረሰባቸው አደጋ ህይወታቸው ሳያልፍ እንደቀረ አስታውቋል፡፡
የማቾች ቁጥር ይህ ብቻ ይሁን አይሁን እስካሁን ግልፅ መረጃ ስላለመገኘቱ ተገልጻል፡፡
የአውሮፕላኑን አደጋ ተከትሎ በአካባቢው የነበሩ ሌሎች 11 ሰዎች ላይ ጉዳት ማጋጠሙ እንዲሁ ታውቋል፡፡
በአካባቢው ያሉ ሰዎች ጥንቃቄን እንዲያደርጉ የአካባቢው ፖሊስ አሳስቧል።
ቢቢሲ

🌎 በዓለም ላይ ዕድለኛው ሰው ነው፤ ግን በየቀኑ ይሰቃያል
241 ሰዎች ሕይወት የቀጠፈው የኤር ኢንዲያ አውሮፕላን አደጋ ብቸኛው ተራፊ ነው። የ39 ዓመቱ ቪሽዋስኩማር ራሜሽ ራሱን "በዓለም ላይ ዕድለኛው ሰው" ሲል ይጠራዋል — በተመሳሳይ ጊዜ ግን ለመናገር የሚያዳግት የአካልና የአእምሮ ሕመም ውስጥ እንደሚኖር ይናገራል።
አሳዛኙ ክስተት የተከሰተው ባለፈው ሰኔ ወር ላይ፣ ከአህመዳባድ ወደ ለንደን በሚደረግ በረራ ላይ አውሮፕላኑ ከተነሳ ብዙም ሳይቆይ ነው። በቅድመ ምርመራ መሠረት፣ አውሮፕላኑ ከተነሳ ከጥቂት ሰከንዶች በኋላ ወደ ሞተሮች የሚሄደው ነዳጅ በመቋረጡ የቦይንግ 787 አውሮፕላን ተከሰከሰ ። በእሳትም ተያያዘ።
ራሜሽ መቀመጫውን ፈቶ ከፍርስራሹ ውስጥ መውጣት ቢችልም፣ ታናሽ ወንድሙ አጃይ ግን ከጎኑ ሞተ።
"ብቸኛዋ ተርፊ እኔ ነኝ። አሁንም ማመን አልቻልኩም። ተአምር ነው" ሲል ወደ ሌስተር ከተመለሰ በኋላ በሰጠው የመጀመሪያ ቃለ ምልልስ ላይ ለቢቢሲ ተናግሯል።
"ወንድሜን አጣሁ። እርሱ ድጋፌ ነበር። በቅርብ ዓመታት ውስጥ ሁል ጊዜ ከጎኔ ነበር" ሲል በእንባ እየተናነቀወ ተናግሯል።
😥 ብቸኝነት እና ስነልቦናዊ ጉዳት
ወደ ብሪታንያ ከተመለሰ በኋላ ራሜሽ ድህረ-አሰቃቂ ጭንቀት (PTSD) እና ከባድ የስነልቦና ምልክቶች እየታገለው ነው። "አሁን ብቻዬን ነኝ። ራሴን ክፍሌ ውስጥ እዘጋለሁ፣ ከሚስቴም ሆነ ከልጄ ጋር አልነጋገርም። ዝም ማለት ብቻ ነው የምፈልገው" ብሏል።
የእርሱ የስነ ልቦና ሀኪሞች እንደሚሉት፣ በብሪታንያ እስካሁን የሕክምና እንክብካቤ አላገኘም፣ እናቱ ደግሞ "በየቀኑ በር ላይ ተቀምጣ ከማንም ጋር አትነጋገርም" ብለዋል።
"በዚያ ቀን ስለተፈጠረው ነገር ማውራት አልችልም። ሌሊቱን ሙሉ ስለእርሱ አስባለሁ፣ በአእምሮ እሰቃያለሁ። ለእኛ ለቤተሰቡ በሙሉ እያንዳንዱ ቀን የሚያም ነው" ሲል ተናግሯል።
💥 ዓለምን ያስደነገጠው አደጋ
በበረራው ላይ ከነበሩት 169 ህንዳውያን እና 52 ብሪታንያውያን ተሳፋሪዎች በተጨማሪ በመሬት ላይ የነበሩ 19 ሰዎች ሞተዋል። ከአደጋው በኋላ የነበሩት ትዕይንቶች በዓለም ዙሪያ ተሰራጭተዋል።
ራሜሽ ደም ለብሶ እና ደንዝዞ ከኋላው ጭስ እየተንቦገቦገ በብናኙ ውስጥ ሲራመድ ትዝ ይለዋል።
በኋላም ከህንድ ሆስፒታል ሆኖ፣ ከአደጋ ጊዜ መውጫ አጠገብ ከነበረው ከመቀመጫ ቁጥር 11A ራሱን ነፃ አውጥቶ እንዴት ከአውሮፕላኑ መውጣት እንደቻለ ተናግሯል። በዚያም የህንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ ጎብኝተውታል።
💔 ከሥቃዩ ጋር መኖር
የእርሱ አካላዊ ቁስሎች ብዙ ናቸው፡ ለቢቢሲ እንደገለጸው፣ በእግሩ፣ በትከሻው፣ በጉልበቱ እና በጀርባው የማይቋቋመው ህመም አለው። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ መሥራትም ሆነ መንዳት አልቻለም።
"ስራመድ፣ በመደበኛነት አልራመድም። በቀስታ፣ በቀስታ ነው። ባለቤቴ ትረዳኛለች" ይላል።
በሌስተር የሚገኙ ደጋፊዎቹ ሳንጄቭ ፓቴል እና ራንድ ሳገር "የጠፋና የተጎዳ" ሰው አድርገው ይገልጹታል፣ ከፊቱ ረጅም የማገገሚያ መንገድ እንዳለበት ይናገራሉ።
"ቤተሰቡ በአካልም፣ በአእምሮም እና በገንዘብ ቀውስ ውስጥ ነው" ሲል ፓቴል ይናገራል።
ቤተሰቡ በህንድ የሚገኝ የአሳ ማጥመድ ንግድ ወድቋል። ኤር ኢንዲያ ጊዜያዊ የ21,500 ፓውንድ ካሳ አቅርቧል፣ ይህም አማካሪዎቹ በቂ እንዳልሆነ ይናገራሉ።
🗣️ "ና እና አዳምጠን"
የራሜሽ ወገን ኤር ኢንዲያ ከእርሱ እና ከተጎጂዎች ቤተሰቦች ጋር ለመገናኘት ሦስት ጊዜ ፈቃደኛ አልሆነም ሲል ይከሳል። "ዛሬ የምናደርገው ለእርዳታ የሚቀርብ ጩኸት ነው። እዚህ መቀመጥ የነበረባቸው እኛ አይደለንም—የአየር መንገዱ ኃላፊነት ያለባቸው ሰዎች ናቸው" ሲል ሳገር ተናግሯል።
"መጥታችሁ አዳምጡን፣ ቢያንስ የዚህን ሥቃይ ክፍል ለመፈወስ እርዱን።"
የታታ ግሩፕ አካል የሆነው ኤር ኢንዲያ በሰጠው መግለጫ፣ ከተጎጂዎች ቤተሰቦች ጋር መገናኘቱን እንደቀጠለ እና ራሜሽንና ወኪሎቹን ለመገናኘት አስቀድሞ እንዳቀረበ ተናግሯል። "የእርሱ እና የተጎዱ ቤተሰቦች ሁሉ እንክብካቤ የእኛ ፍጹም ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ ሆኖ ይቀጥላል" ብሏል።
በኤር ኢንዲያ ታሪክ ውስጥ ከነበሩት እጅግ ገዳይ አደጋዎች መካከል አንዱን "በተአምር" የተረፈው ሰው ዛሬ የሁለት ህይወቶች ሸክም ተሸክሟል፡ የተረፈው ህይወት — እና የጠፋው ህይወት።

241 ተሳፋሪዎች ከሞቱበት የአውሮፕላን አደጋ ቢተርፍም ከስቃይ ያልዳነው ራሜሽ…
#ethiopia | ባሳለፍነው ሰኔ ወር መንገደኞችንና የበረራ ሰራተኞችን ጨምሮ 242 ሰዎችን የያዘ አውሮፕላን ተከስክሶ 241 ያህሉ ህይወታቸው ማለፉ ይታወሳል፡፡
ከዚያ አስከፊ አደጋ በህይወት የተረፈው የ39 ዓመቱ ቪስዋሽኩመር ራሜሽ፥ ተዓምር እንደሆነ በገለጸው ሁኔታ ከአደጋው ተርፎ በህይወት በመቆየቱ እድለኛ መሆኑን ተናግሯል፡፡
ራሜሽ ወንድሙን ጨምሮ በአውሮፕላኑ የተሳፈሩ ሌሎች ሰዎች በሙሉ ከሞቱበት አስከፊ አደጋ ተርፎ ዛሬ ላይ በህይወት ቢኖርም፥ በድኅረ አደጋ ጭንቀት እየተሰቃየ ይገኛል፡፡
በወቅቱ የህክምና ድጋፍ ተደርጎለት እንግሊዝ ሌስተር ወደሚገኘው መኖሪያ ቤቱ ቢመለስም፥ በዚሁ የድኅረ አደጋ ጭንቀት የስነ ልቦና ችግር ምክንያት ከባለቤቱም ሆነ ከ4 ዓመት ልጁ ጋር ለመነጋገር ተቸግሯል፡፡
"በቤቴ ውስጥ ብቸኛ ሰው ሆኛለሁ፥ ከባለቤቴም ከልጄም ጋር ማውራት አልቻልኩም፥ ከሰው ተነጥዬ ባዶ ክፍል ውስጥ ለብቻዬ ነው ያለሁት" ሲል ለቢቢሲ ተናግሯል፡፡
"በአደጋው ወቅት ስለነበረው ሁኔታ መናገር በጣም ከባድ ነው፥ ምንም መናገር አልችልም፥ከማንም ጋር መነጋገር አልፈልግም፥ ሌሊት እንቅልፍ የለኝም" ሲል እሱም ሆነ ቤተሰቡ ያሉበት ሁኔታ በስቃይ የተሞላ እንደሆነ ገልጿል፡፡
አዕምሮው ሰላም ከማጣቱ ባሻገር ከአደጋው ለመሸሽ ሲሞክር እግሩና ትከሻውን ጨምሮ በደረሰበት አካላዊ ጉዳት በህመም ላይ መሆኑንም ተናግሯል፡፡
የስነ ልቦና አማካሪዎች በበኩላቸው፥ ራሜሽ 'ፒቲኤስዲ' በመባል በሚታወቀው የድኅረ አደጋ ጭንቀት የስነ ልቦና ችግር እየተሰቃየ መሆኑን አስረድተዋል፡፡
በአደጋው ወቅት በተፈጠሩት ሁኔታዎች ለዚህ ስነ ልቦናዊ ቀውስ መዳረጉንና ቤተሰቦቹም ጭምር በሁኔታው ከፍተኛ ጉዳት እንደደረሰባቸው ገልጸው፥ ከዚህ አስቸጋሪ ሁኔታ ለማገገም ብዙ ጊዜ ሊፈጅበት ይችላል ነው ያሉት፡፡
አደጋው ከተከሰተበት ጊዜ አንስቶ በአየር መንገዱ በአግባቡ ክትትል አልተደረገለትም የሚሉት የስነ ልቦና አማካሪዎቹ፥ የሚመለከታቸው የተቋሙ ኃላፊዎች ቀርበው የሚያስፈልገውን ድጋፍ ሊያደርጉ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡
የህንድ አየር መንገድ ለተጎጂው 21 ሺህ 500 ፓውንድ ጊዜያዊ የካሳ ክፍያ መክፈሉ የተገለጸ ሲሆን፥ ከደረሰበት ጉዳት አንጻር ይህ በቂ አለመሆኑን አማካሪዎቹ ገልጸዋል፡፡
FMC

በኬንያ በአውሮፕላን አደጋ የ12 ሰዎች ህይወት አለፈ
#ethiopia | ቱሪስቶችን ብቻ ጭኖ የነበረው አውሮፕላን ከድዪዣኒ ወደ ኪችዋ ሲጓዝ ቴምቦ ሪዞርት አጠገብ መከስከሱን የኬንያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን (KCCA) አስታውቋል።
ባለስልጣኑ ቱሪስቶቹ የየት ሀገር ዜጋ እንደሆኑ እስካሁን ማወቅ እንዳልተቻለ ገልጿል።
በአደጋው ዙሪያ ምርመራ መጀመሩን አስታውቋል። #legit #thiqaheth

11 months ago
የኢትዮጵያ አየር መንገድ አደጋ ሊደርስበት ተቃርቦ እንደነበር ተዘገበ
በህንድ የኢንዲራ ጋንዲ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ የአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች ላይ ባለው ከባድ የሥራ ጫና ምክንያት፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ እና የቪስታራ አየር መንገድ አውሮፕላኖች በኅዳር 10 ቀን 2023 አደጋ ሊደርስባቸው ተቃርቦ እንደነበር የአውሮፕላን አደጋ ምርመራ ቢሮ ባወጣው የመጨረሻ ዘገባ ላይ አስታወቀ።
አንድ የ ኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦይንግ 787 አውሮፕላን ሊነሳ ሲዘጋጅ፣ ከጎኑ የ ቪስታራ አየር መንገድ አውሮፕላን ለማረፍ እየተቃረበ ነበር።
በከፍተኛ ነፋስ ምክንያት የቪስታራ አውሮፕላን የማረፍ ሙከራውን ሲያቋርጥ፣ ከኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን ጋር ሊጋጭ ተቃርቦ እንደነበር መገለጹን ካፒታል ዘግቧል።

1 year ago
የውጊያ ጄት በትምህርት ቤት ውስጥ ተከስክሶ ቢያንስ 19 ተማሪዎች ሲሞቱ ከ50 በላይ የሚሆኑት መቁሰላቸው ተገለጸ
📌የብሔራዊ ሃዘን ቀን ታውጇልም ተብሏል
#ethiopia | በባንግላዲሽ ዋና ከተማ ዳካ በሚገኝ አንድ የኮሌጅ ቅጥር ግቢ ውስጥ የባንግላዲሽ አየር ኃይል ማሰልጠኛ ጄት ተከስክሶ ቢያንስ 19 ሰዎች ሲሞቱ ከ50 በላይ የሚሆኑት ደግሞ ጉዳት ደርሶባቸዋል ተብሏል። አብዛኞቹ ተጎጂዎች ወጣት ተማሪዎች እንደሆኑ ተገልጿል። አገሪቱ ብሔራዊ የሐዘን ቀንን እንዳወጀችም ተሰምቷል።
ኤፍ-7 ቢጂአይ (F-7 BGI) የተሰኘው አውሮፕላን በአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር ከቀትር በኋላ 7 ሰአት ላይ ከፍ ካለ በኋላ፣ ከአስራ ሁለት ደቂቃ ገደማ በኋላ በዋና ከተማዋ ሰሜናዊ ክፍል በኡታራ ዲያባሪ አካባቢ በሚገኘው ማይልስቶን ትምህርት ቤት እና ኮሌጅ ካንቲን አቅራቢያ ተከስክሷል ሲል የኢንተር-ሰርቪስ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት (ISPR) ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።
የባንግላዲሽ ጋዜጣ ፕሮቶም አሎ እንደዘገበው ወታደራዊው አውሮፕላን አደጋው ሲከሰት በርካታ ወጣት ተማሪዎች በቦታው በነበሩበት ወቅት የምሳ ሰዓት ላይ ከትምህርት ቤቱ ካንቲን አጠገብ ተከስክሷል ብሏል ዘገባው። የመጀመሪያው የሟቾች ቁጥር አንድ ብቻ የነበረ ሲሆን፣ የእሳት አደጋና ሲቪል መከላከያ ዳይሬክተር ጀኔራል ብሪጋዴር ጀኔራል መሐመድ ዛሂድ ከማል ወደ ስፍራው ከደረሱና ለመገናኛ ብዙኃን መግለጫ ከሰጡ በኋላ የሟቾች ቁጥር በእጅጉ ጨምሯል ነው የተባለው።
ነገ ማክሰኞም የብሔራዊ የሐዘን ቀን ታውጇል ነው የተባለው፡፡
የባንግላዲሽ ኤፍ-7 የቻይና ቼንግዱ ኤፍ-7 ዘመናዊ ስሪት ሲሆን እሱም በሶቪየት ሚግ-21 ላይ የተመሰረተ ነው ተብሏል። በዓለም አቀፍ ደረጃ ጊዜ ያለፈበት ቢሆንም፣ ወጪ ቆጣቢነቱ እና ለአብራሪ ስልጠናና ለተገደበ የውጊያ ሚናዎች ተስማሚ በመሆኑ አገልግሎት ላይ ይገኛል ነው የተባለው።
ቻይና የመጨረሻዎቹን 16 የኤፍ-7 ቢጂአይ አውሮፕላኖችን ለባንግላዲሽ በ2013 ዓ.ም. ከሰጠች በኋላ ምርቱ ቆሟል ተብሏል ሲል የዘገበው መናኸሪያ ሬዲዮ።

አስክሬናቸው ግን ይግኝ ይሆን ?
* የዲያጎ ጆታ ላምቦርጊኒ ሙሉ በሙሉ ወድሟል
#ethiopia | በጣም ከሚያሳዝኑት ዜናዎች መካከል አንዱ
በስፔን እና በፖርቱጋል ድንበር አካባቢ የተሰማው ነው።
የሊቨርፑሉ ኮከብ ዲያጎ ጆታ ሲነዳት የነበረችው የቅንጦት መኪና ላምቦርጊኒ ሙሉ በሙሉ ወድማለች።
የመኪናው ሁኔታ የአውሮፕላን አደጋ የመሰለ ሲሆን፣ መንገዱም ብዙ አደጋዎች የሚደርሱበት እንደሆነ ተዘግቧል።
ይህ አደጋ እጅግ በጣም ያማል።
ለዲያጎ ቤተሰብ እና ወዳጆች
ለስፖርት ማህበረሱ መፅናናትን እንመኛለን።
እንዴት መኪና እንዲህ ይሆናል? #hagerie_tv

Comments