4 months ago
በሰሀራ በረሃ 49 ስደተኞች ህይወታቸው አልፎ ተገኙ።
ስደተኞቹ በህገወጥ መንገድ ሰፊውን በረሃ እያቋረጡ በነበረበት ወቅት እነሱን የያዘው ተሽከርካሪ በመገልበጡ ነው ህይወታቸው ያለፈው ተብሏል።
ከአደጋው የተረፉ ሁለት ስደተኞች 50 ኪሎሜትር ተጉዘው ለባለስልጣናት ከተናገሩ በኋላ የህይወት አድን ቡድን መሰማራታቸው ተገልጿል።
ስደተኞቹ የማሊ ዜግነት ሲኖራቸው በኒጀር እና አልጀሪያ አዋሳኝ አሳማካ ክልል ነው አደጋው የደረሰባቸው።
ይህ አሳዛኝ ክስተት በሰሀራ በረሃ እየደረሰ ያለውን አስከፊ የስደተኞች ሰቆቃ እንደሚያሳይ ተመልክቷል። #legit
Seledadotio

7 months ago
የከተማ ይዞታን ለማስመለስ ክስ በይርጋ ይታገዳል?
(የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በሰባት ዳኞች በተሰጠ የህግ ትርጉም የተሰጠ የህግ ትንታኔ)
#ethiopia | በጠበቃና የህግ አማካሪ አልማው ወሌ የኢትዮጵያ ፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከሰባት ያላነሱ ዳኞች የተሰየሙበት የሰበር ችሎት የካቲት 30 ቀን 2018 ዓ.ም በመ.ቁጥር 244308 የከተማ መሬት ይዞታን ለማስመለስ የሚቀርብ ክስ በይርጋ ይታገዳል ወይስ አይታገድም ? በሚለው አከራካሪ የህግ ነጥብ ላይ ሰበር ችሎቱ በሰጠው አስገዳጅ የሕግ ትርጉም ላይ የቀረበ አጭር ትንታኔ
የተከበሩ ጠበቃ እናመሠግናለን መልካም ንባብ
ኢትዮጵያ ፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከሰባት ያላነሱ ዳኞች የተሰየሙበት የሰበር ችሎት የካቲት 30 ቀን 2018 ዓ.ም በመ.ቁጥር 244308 ላይ በሰጠው አስገዳጅ የሕግ ትርጉም ላይ የቀረበ አጭር ትንታኔ 1
ክፍል አንድ፡ መግቢያ እና የሥነ-ሥርዓት ዳራ 1
ክፍል ሁለት፡ የሦስቱ ቀደምት አስገዳጅ ውሳኔዎች አጠቃላይ ትንታኔ 1
ክፍል አራት፡ የሰባት ዳኞች ችሎት አዲሱ የሕግ ትርጉም 3
ክፍል አምስት፡ ተግባራዊ የተደረጉት የፍትሐብሔር ሕግ ድንጋጌዎች ትንታኔ 4
ክፍል ስድስት፡ ስለ አዲሱ ትርጉም ጥንካሬዎች 4
ክፍል ሰባት፡ የውሳኔው ማጠቃለያ እና ቀጣይ አንድምታዎች 4
7.1 አዲሱን ሕግ በመታየት ላይ ባሉ ጉዳዮች ላይ ያለመተግበር ትክክለኛነት፡ የሽግግር ድንጋጌዎችን በጥብቅ መከተል 5
7.2 የአመሳስሎሽ ትርጓሜ ችግር፡ የሕግ ክፍተትን ለመሙላት በተመረጠው ምንጭ ላይ የታየ የፅንሰ-ሐሳብ (የዶክትሪን) መዛባት 6
7.3 የክፍል 7 ጥማቂ 8
ክፍል ስምንት፡ አጠቃላይ ግምገማ 9
የኢትዮጵያ ፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከሰባት ያላነሱ ዳኞች የተሰየሙበት የሰበር ችሎት የካቲት 30 ቀን 2018 ዓ.ም በመ.ቁጥር 244308 ላይ በሰጠው አስገዳጅ የሕግ ትርጉም ላይ የቀረበ አጭር ትንታኔ
ክፍል አንድ፡ መግቢያ እና የሥነ-ሥርዓት ዳራ
ከሰባት ያላነሱ ዳኞች የተሰየሙበት የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት የካቲት 30 ቀን 2018 ዓ.ም. የሰጠው ይህ ውሳኔ በመ/ቁጥር 210477 ላይ ተሰጥቶ የነበረውን አስገዳጅ የህግ ትርጉም በመለወጥ ተሰጠው (Overruling) ውሳኔ ሲሆን በአገሪቱ የንብረት ሕግ ስነ ህግ እድገት እና በአስገዳጅ የህግ ትርጉም ስርዓት ላይ የራሱ የሆነ አንድምታ ያለው መሆኑ ይታመናል፡፡ ይህ አዲስ አስገዳጅ የህግ ትርጉም ለውጥ በችሎቱ የተሰጠው በፌዴራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር 1234/2013 አንቀጽ 26(1) ድንጋጌ እና በሰበር ስነ ስርዓት መመሪያ ቁጥር 17/2015 አንቀፅ 14(2) በተዘረጋው ስርዓት ሲሆን ችሎቱ የተሰየመበትም ዋነኛ ምክንያትም የከተማ መሬት ይዞታን ለማስመለስ የሚቀርብ ክስ በይርጋ ይታገዳል ወይስ አይታገድም ? በሚለው አከራካሪ የህግ ነጥብ ላይ ሰበር ችሎቱ ቀደም ሲል በሰጣቸው አስገዳጅ ውሳኔዎች መካከል ሊታረቅ የማይችል ተቃርኖ በመፈጠሩ ነው፡፡ የጉዳዩ ምንጭ አቶ ጅላሎ ኩመል ሼህረዲ (አመልካች/ተከሳሽ) እና አቶ ታምራት መርከቡ ፍልቾ (ተጠሪ/ከሳሽ) በአዲስ አበባ ከተማ (ለሚ ኩራ ክፍለ-ከተማ፣ ወረዳ 08፣ ፊጋ ሰፈር በሚባል አካባቢ) በሚገኝ 2,000 ካሬ ሜትር የከተማ ቦታ ላይ ያደረጉት ክርክር ነው፡፡ ጉዳዩ ለሰባት ዳኞች ችሎት መመራቱ ሥነ-ሥርዓታዊ ሂደት ብቻ ሳይሆን ጥልቅ መሠረታዊ የሕግ ይዘት ያለው ጉዳይ ሲሆን ችሎቱም በሕግ አተገባበር ላይ ወጥነት እና ተገማችነትን የማረጋገጥ ኃላፊነቱን ለመውጣት በተጠቃሽ ውሳኔዎቹ መካከል የታየውን ተቃርኖ አስታራቂ እና ግልጽ አቋም ሊያዝበት የሚገባ መሆኑን በግልጽ አስፍሯል፡፡ ይህ እርስ በእርሱ የሚቃረኑ አስገዳጅ ውሳኔዎች ሥርዓታዊ የሆነ ችግር እንዳያስከትሉ ችሎቱ ራሱን በራሱ በማረም የወሰደው ዕርምጃ በኢትዮጵያ የአስገዳጅ የህግ ትርጉም ሥርዓት ውስጥ ያለውን ተቋማዊ ብስለት የሚያሳይ ነው ተብሎ ሊወሰድ የሚገባው ነው፡፡
ክፍል ሁለት፡ የሦስቱ ቀደምት አስገዳጅ ውሳኔዎች አጠቃላይ ትንታኔ
በመጀመሪያ ደረጃ በሰበር መዝገብ ቁጥር 43600 ጥር 05 ቀን 2002 ዓ.ም. የተወሰነውንና በቅጽ 10 የታተመውን አስገዳጅ የህግ ትርጉም በአጭሩ ስንመለከት ጉዳዩ አቶ ዳዊት መስፍን ከተጠሪ የመንግስት ቤቶች ኤጀንሲ ጋር ያደረጉት ክርክር ነበር፡፡ አቶ ዳዊት በአዲስ አበባ ከተማ (የቀድሞ ወረዳ 118፣ ቀበሌ 05) የሚገኝ መኖሪያ ቤት የባለቤትነት መብትን መሠረት በማድረግ ቤቱ እንዲለቀቅላቸው ክስ አቅርበው ነበር፡፡ ለዚህም በጥቅምት 23 ቀን 1985 ዓ.ም. የተሰጠ የከተማ ቤት ባለቤትነት ማረጋገጫ ደብተር አቅርበዋል፡፡ ተጠሪው (ኤጀንሲው) በበኩሉ፣ የፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 1845ን ማለትም የ10 ዓመቱን የውል ግዴታዎች ይርጋ ድንጋጌ በመጥቀስ የይርጋ መቃወሚያ አቅርቦ ነበር፡፡ የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት እና የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የይርጋ መቃወሚያውን በመቀበል ክሱን ውድቅ አድርገውት ነበር፡፡ ጉዳዩ የቀረበለት የሰበር ችሎት ግን የማይንቀሳቀስ ንብረትን በተመለከተ የሚቀርብ የመፋለም ክስ በይርጋ ቀሪ የሚሆንበት አግባብ መኖር አለመኖሩን ጭብጥ አድርጎ በመያዝ ጥልቅ ትንታኔ ሰጥቷል፡፡ የሰበር ችሎቱ ትንታኔውን የጀመረው ማናቸውም ኢትዮጵያዊ የንብረት ባለቤት መሆኑ በሕገ-መንግስቱ አንቀጽ 40(1) የተረጋገጠ መሆኑን በማንሳት ሲሆን፣ በመቀጠልም የፍትሐብሔር ሕጉን የንብረት ድንጋጌዎች ማለትም አንቀጽ 1126፣ 1168፣ 1184፣ እና 1186 ደንጋጌዎችን እንዲሁም በፍ/ህ/ቁጥር 1188 እስከ 1192 ድረስ ያሉትን ድንጋጌዎችን ሙሉ ይዘትና መንፈስ በዝርዝር ተመልክቷል፡፡ ችሎቱ ወሳኝ ብሎ ያነሳው ነጥብ የፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 1192 "ባለሀብትነትን የሚያስቀር የይርጋ ዘመን" ብሎ ያስቀመጠው ለሚንቀሳቀስ ንብረት ብቻ መሆኑን እና ስለ ማይንቀሳቀስ ንብረት በዝምታ ማለፉን ነው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በአንቀጽ 1206 ሥር የተደነገገው የመፋለም ክስ የባለቤትነት መብት ከሁሉ የሰፋ መብት መገለጫ መሆኑን፣ እና የማይንቀሳቀስ ንብረት ባለቤትነት ዘላቂነት (Perpetuity) ያለው መብት በመሆኑ በይርጋ ቀሪ እንዳይሆን የሕግ አውጪው ፍላጎት መሆኑን አብራርቷል፡፡ በዚህም መሠረት የፍ/ብ/ሕ/ቁ 1845 ድንጋጌን ተፈፃሚ ማድረግ የሕጉን አወቃቀርና መንፈስ የሚያፋልስ መሆኑን በመግለጽ፣ የማይንቀሳቀስ ንብረት የመፋለም መብት ክስ በይርጋ ቀሪ አይሆንም ወደሚል ድምዳሜ ደርሷል፡፡ ይህ ውሳኔ በፅንሰ-ሐሳብ ደረጃ ጠንካራ ቢሆንም፣ ዋነኛ ክፍተቱ ትንታኔው ሙሉ በሙሉ ታሳቢ ያደረገው "የግል ባለቤትነት መብት" (Private Ownership) መኖርን መሆኑ ነው፡፡ ጉዳዩ መኖሪያ ቤትን የሚመለከት ስለነበር ይህ አካሄድ ትክክል ቢሆንም፣ የባለቤትነት መብት በሕገ-መንግሥት በተከለከለበት መሬት ላይ ትንታኔው እንዴት ሊተገበር ይችላል ለሚለው ጥያቄ ምላሽ የሚሰጥ አልነበረም፡፡ ሆኖም ትርጉም በሌሎች ልዩ ህጎች ያሉትን የይርጋ ድንጋጌዎችን የማይነካ መሆኑ በማሳሳብ አልፏል፡፡
በሁለተኛ ደረጃ በሰ/መ/ቁጥ 69302 ታህሳስ 20 ቀን 2004 ዓ.ም. የተሰጠውን አስገዳጅ የህግ ትርጉም ስንመለከት፦ ጉዳዩ በአመልካች አቶ ሸለማ ነገሰ እና በተጠሪ አቶ ፋይሣ መንግስቱ መካከል በኦሮሚያ ክልል፣ ኖኖ ቤንጃ ወረዳ በሚገኝ የገጠር እርሻ መሬት ላይ የተደረገ ክርክር ነው፡፡ ተጠሪ አባቴ በሞት ከተለየበትמ 1985 ዓ.ም.
ጀምሮ አመልካች መሬቱን አላግባብ ስለያዘብኝ ይልቀቅልኝ ሲል ክስ ያቀረበ ሲሆን አመልካች በበኩሉ መሬቱን ለ18 ዓመታት መያዙን በመግለጽ ተከራክሯል፡፡ የስር ፍርድ ቤቶች መሬቱ እንዲለቀቅ የወሰኑ ቢሆንም የሰበር ችሎቱ ግን አርሶ አደሮች የእርሻ መሬት የማግኘትና ያለመፈናቀል መብት እንዳላቸው ሕገ-መንግሥቱ በአንቀጽ 40(4) መሠረት ማረጋገጡን ጠቅሶ፣ ይሁን እንጂ መሬቱን በሌላ ሰው የተነጠቀ አርሶ አደር ክስ ማቅረብ ስላለበት የጊዜ ገደብ የገጠር መሬት አዋጆች በግልጽ አለመደንገጋቸውን በማንሳት የሕግ ክፍተት መኖሩን አሳይቷል፡፡ የፍትሐብሔር ሕጉ የሁከት ይወገድልኝ ክስ የ2 ዓመት ይርጋን (አንቀጽ 1149(2)) መተግበር የአርሶ አደሩን ሕገ-መንግሥታዊ መብት አጥብቦ የሚገድብ በመሆኑ ውድቅ በማድረግ፣ በፍ/ብ/ሕ/ቁ 1677(1) ስር የተመለከተውን ድንጋጌ እንደ ድልድይ በዋቢነት በመጥቀስ የፍ/ብ/ሕ/ቁ 1845 የ10 ዓመት ይርጋ በገጠር መሬት ይዞታ ላይ ተግባራዊ እንዲሆን ወስኗል፡፡ ይህ ውሳኔ ምንም እንኳን ከመዝገብ ቁጥር 43600 ፈጽሞ የተለየ አቀራረብ ይዞ የመሬት ይዞታን ከባለቤትነት መብት ነጥሎ በማየት የ10 ዓመት ይርጋ ተግባራዊ ያደረገ ቢሆንም፣ የውል ድንጋጌ የሆነውን የፍ/ህ/ቁ 1845 ድንጋጌን በቀጥታ መሬት ላይ ለመተግበር የሄደበት መንገድ በበቂ ሁኔታ ያልተብራራ መሆኑ እንደ ሂሳዊ ድክመት ሊነሳበት ይችላል፡፡
በሦስተኛ ደረጃ በሰ/መ/ቁ 210477 ታህሳስ 27 ቀን 2014 ዓ.ም. የተወሰነውንና አሁን የተሻረውን ስንመለከት፣ ጉዳዩ በአዲስ አበባ ከተማ ቦሌ ክፍለ-ከተማ ውስጥ የሚገኝ የከተማ መሬት ይዞታን በተመለከተ በአመልካቾች (የአቶ ነጋሳ ዱቤ ወራሾች) እና በተጠሪዎች (ወ/ሮ ጸሐይ ቹቾ እና ወ/ሮ ሴደሬ ንጉሴ) መካከል የተደረገ ክርክር ነበር፡፡ ተጠሪዎች ቦታውን ከ1993 ዓ.ም. ጀምሮ ለ19 ዓመታት መያዛቸውን በመግለጽ የይርጋ መቃወሚያ አቅርበው የስር ፍርድ ቤቶችም መቃወሚያውን ተቀብለውት ነበር፡፡ ሆኖም የሰበር ችሎቱ ይህንን ውሳኔ በመሻር፣ የቀረበው ክስ "የመፋለም ክስ" መሆኑን በመግለጽ የቤትን ባለቤትነት የተመለከተውን የሰ/መ/ቁ 43600 አመክንዮ በቀጥታ በመዋስ "የከተማ መሬት ይዞታን በተመለከተ የሚቀርብ የመፋለም ክስ በይርጋ አይታገድም" የሚል አስገዳጅ ትርጉም ሰጥቶ ነበር፡፡ የዚህ ውሳኔ ዋነኛ ስህተት የባለቤትነት መብትን (Ownership) እና የይዞታ መብትን (Holding rights) አንድ አድርጎ ማየት መቻሉ ነው፡፡ ሕገ-መንግሥቱ በአንቀጽ 40(3) መሠረት ግለሰቦች በመሬት ላይ የባለቤትነት መብት እንደሌላቸው እየደነገገ፣ በሰ/መ/ቁ 210477 የተሰጠው አስገዳጅ የህግ ትርጉም ግን የባለቤትነት መብት ጥበቃን (ከይርጋ ነፃ መሆንን) በመሬት ይዞታ መብት ላይ በመተግበሩ መሠረታዊ የሆነ የፅንሰ-ሐሳብ እና የሕግ ስህተት ተፈጽሞበት የነበረ ጉዳይ ነው፡፡
ክፍል ሦስት፡ በውሳኔዎቹ መካከል የነበረው ተቃርኖ እና የሕግ ማዕቀፎች
በእነዚህ ሦስት ውሳኔዎች መካከል የተፈጠረው ተቃርኖ እጅግ የጎላ እንደነበር በቀላሉ መገንዘብ ይቻላል፡፡ በአንድ በኩል መዝገብ ቁጥር 43600 በቤት ባለቤትነት ላይ የመፋለም ክስ ይርጋ የለውም ሲል፣ በሌላ በኩል በሰ/መ/ቁ 69302 በገጠር መሬት ይዞታ ላይ የ10 ዓመት ይርጋ ተፈፃሚ አድርጓል፡፡ በተቃራኒው ደግሞ በሰ/መ/ቁ 210477 የከተማ መሬት ይዞታን አስመልክቶ የቀረበን ክርክር የባለቤትነት ጉዳይ ከሆነው ከሰ/መ/ቁ 43600 ጋር በማመሳሰል የከተማ መሬት ክስ በይርጋ አይታገድም በማለት ወስኗል፡፡ ይህ ሁኔታ በመሬት ይዞታዎች (በገጠር እና በከተማ) ላይ የተለያየ እና ምክንያታዊ ያልሆነ የይርጋ አተገባበር እንዲፈጠር አድርጎ የነበረ መሆኑ ከውሳኔዎቹ በግልፅ ይታያል፡፡
ይህንን ተቃርኖ ለመፍታት የሰባት ዳኞች ችሎት በርካታ ሕጎችን አንድ ላይ መመርመር ነበረበት፡፡ ከእነዚህም ውስጥ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ሕገ-መንግሥት አንቀጽ 40(3) ስለ መሬት የመንግስትና የሕዝብ ንብረትነት፣ አንቀጽ 40(4) ስለ አርሶ አደሮች መብት፣ እና አንቀጽ 40(7) በጉልበትና በገንዘብ ስለሚፈራ ንብረት ያካተቱት ድንጋጌዎች ይገኙበታል፡፡ በተጨማሪም የፍትሐብሔር ሕግ አንቀጽ 1192፣ አንቀጽ 1206 (ስለ መፋለም ክስ)፣ አንቀጽ 1149(2) (የሁከት ክስ ይርጋ)፣ እንዲሁም አንቀጽ 1677(2) እና 1845 ድንጋጌዎች ሙሉ ይዘታቸው ተፈትሸዋል፡፡ ከእነዚህ በተጨማሪም የከተማ ቦታ በሊዝ ስለመያዝ የወጣው አዋጅ ቁጥር 721/2004፣ የከተማ መሬት ይዞታ ምዝገባ አዋጅ ቁጥር 818/2006 እና የገጠር መሬት አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 1324/2016 አግባብነት ያላቸው የሕግ ማዕቀፎች በመሆናቸው በችሎቱ ታሳቢ ተደርገዋል፡፡
ክፍል አራት፡ የሰባት ዳኞች ችሎት አዲሱ የሕግ ትርጉም
ሰባት ዳኞች የተሰየሙበት የሰበር ችሎት ይህንን የተወሳሰበ የሕግ ጥያቄ ለመፍታት የተጠቀሱትን ቀደምት አስገዳጅ ውሳኔዎችን በመመርመር ለእያንዳንዳቸው ተገቢ ነው ያለውን ማብራሪ ሰጥቶባቸዋል፡፡ በመጀመሪያ በሰ/መ/ቁጥር 43600 የተሰጠውን አስገዳጅ የህግ ትርጉምን አልሻረውም፤ ይልቁንም ጉዳዩ መኖሪያ ቤትን የሚመለከት በመሆኑና መኖሪያ ቤት ላይ የባለቤትነት መብት ስላለ፣ ትንታኔው ከዚህ መዝገብ ጋር በቀጥታ እንደማይገናኝ በማስረዳት የጉዳዩን ልዩነት (Distinguishing) በማሳየት ትርጉሙ እንዲፀና አድርጎታል፡፡ በመቀጠልም በሰ/መ/ቁጥር 69302 ለገጠር መሬት የተሰጠውን የ10 ዓመት ይርጋ አስገዳጅ የህግ ትርጉም ትክክለኛነት የተቀበለ ቢሆንም፣ ይህንን የገጠር መሬት ቀደመት አስገዳጅ ትርጉም በቀጥታ በከተማ መሬት ላይ መተግበሩ ስህተት መሆኑን በማሳየት የስር ፍርድ ቤትን አካሄድ ነቅፏል፡፡ በመጨረሻም በሰ/መ/ቁጥር 210477 የተሰጠውን አስገዳጅ የህግ ትርጉም ሙሉ በሙሉ የሻረው ሲሆን ለውሳው ምሶሶ ያደረጋቸው አበይት ምክንያቶቹም የቀደመው አስገዳጅ የህግ ትርጉም የባለቤትነት መብትን እና የይዞታ መብትን በማምታታት፣ በመሬት ይዞታ መብት ላይ ሊቀርብ የማይችለውን የመፋለም ክስ የይርጋ መቃወሚያ በከተማ መሬት ይዞታ ላይ ተግባራዊ ማድረግ አይቻልም የሚሉት መሆናቸውን አዲሱ ትርጉም በግልጽ አስቀምጧል፡፡
ችሎቱ አዲሱን የሕግ ትርጉም ለመስጠትና ለመተንተን የተከተለው አመክንዮ አራት ደረጃዎችን ያካተተ ነበር፡፡ አንደኛ ትንታኔውን በሕገ-መንግስቱ አንቀጽ 40(3) ላይ በማስረፅ መሬት የግለሰብ ባለቤትነት ሊኖርበት የማይችል መሆኑን እና የፍ/ብ/ሕ/ቁ 1206 የመፋለም ክስ መሬት ላይ ተፈፃሚ እንደማይሆን አረጋግጧል፡፡ ሁለተኛ በከተማ መሬት ይዞታ ላይ የሚኖረው መብት (በሊዝም ሆነ በነባር) በነገር ላይ ያለ (In rem) ተጨባጭ የንብረት መብት እንጂ ተራ የኪራይ ውል ግንኙነት አለመሆኑን በማብራራት የመብቱን ህልውና ገልጿል፡፡ ሦስተኛ የሲቪል ሎው (Civil Law) የመፋለም ክስ ፅንሰ-ሐሳብ እና የኮመን ሎው (Common Law) የማስለቀቅ ክስ (Action of ejectment) ፅንሰ-ሐሳቦችን በማነፃፀር፣ ምንም እንኳን ይህ የኮመን ሎው አሠራር ለሕግ ሥርዓታችን እንግዳ ቢሆንም፣ በሕግ የታወቀ መብት እስካለ ድረስ ስያሜው ክሱን ለማስተናገድ እክል እንደማይሆን አብራርቷል፡፡ አራተኛ የሕግ ክፍተቱን ለመሙላት (Gap-filling) የፍ/ብ/ሕ/ቁ 1677(2) ድንጋጌን ድልድይ በማድረግ በፍ/ብ/ሕ/ቁ 1845 ሥር የተቀመጠውን አጠቃላይ የ10 ዓመት ይርጋ በከተማ መሬት ይዞታ ላይ ተግባራዊ አድርጓል፡፡ በዚህም መሠረት
የከተማ መሬት ይዞታን አላግባብ ከያዘ ሰው ላይ ለማስመለስ የሚቀርብ ክስ በአስር ዓመት ይርጋ ይታገዳል የሚል አዲስ አስገዳጅ የሕግ ትርጉም ሰጥቷል፡፡
ክፍል አምስት፡ ተግባራዊ የተደረጉት የፍትሐብሔር ሕግ ድንጋጌዎች ትንታኔ
በዚህ ውሳኔ ተግባራዊ የተደረገው የፍ/ህ/ቁ 1845 "በውል ስለሚመነጩ ግዴታዎች" ሥር የሚገኝ ሲሆን፣ ውልን ስለመፈፀም፣ ባለመፈፀም እና ውልን ስለማፍረስ የሚቀርቡ ክሶች በአስር ዓመት ይርጋ እንደሚታገዱ የሚደነግግ ነው፡፡ የመሬት ይዞታ ክርክር ደግሞ በባህሪው ከውል የሚመነጭ ሳይሆን ከሕገ-ወጥ ይዞታ ወይም ንጥቂያ የሚመነጭ ነው፡፡ ሆኖም ችሎቱ ይህንን ክፍተት ያገናኘው የፍ/ብ/ሕ/ቁ 1677(2) ድንጋጌን በዋቢነት በመጥቀስ ሲሆን ይህ ድንጋጌ የውል ደንቦች ከውል ውጭ በሆኑ ግዴታዎች ላይ ተፈፃሚ እንደሚሆኑ ይደነግጋል፡፡ ይሁን እንጂ ሕገ-ወጥ የመሬት ያዥ ያለበት "ግዴታ" ምን ዓይነት እንደሆነ (ከሕገ-ወጥ ድርጊት ወይስ ያለአግባብ ከመበልፀግ የመነጨ መሆኑን) ችሎቱ በግልጽ አላብራራም፡፡ እንዲሁም በፍ/ህ/ቁ 1846 መሠረት የይርጋው መቆጠር መነሻ ጊዜ ከመቼ እንደሚጀምር፣ በአንቀጽ 1851 መሠረት የይርጋ መቋረጥ እንዴት እንደሚስተናገድ፣ እና በፍ/ህ/ቁጥር 1854 መሠረት መጥፎ ልቦና (Bad faith) ያለው ሰው እንኳን በይርጋው መጠቀም የሚችል መሆኑ በመሬት ንጥቂያ ላይ የሚያመጣው ህጋዊ ውጤት/ ተፅዕኖ መኖር ያለመኖሩን በችሎቱ ትንታኔ ሥር በሰፊው ያልተዳሰሱ ግን መሰረታዊ የሆኑ የህግ ጥያቄዎች ሆነው አልፈዋል፡፡
ክፍል ስድስት፡ ስለ አዲሱ ትርጉም ጥንካሬዎች
የሰባት ዳኞች ችሎት የሰጠው ይህ ውሳኔ በኢትዮጵያ የንብረት ሕግ ስነ ህግ ዕድገት ላይ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያላቸው በርካታ ጥንካሬዎችን ይዟል፡፡ በመጀመሪያ ደረጃ ችሎቱ የፍትሐብሔር ሕጉን እና የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ሕገ-መንግሥትን የመሬት መብት ስሪት በአግባቡ በማዋሃድ የግል ባለቤትነትን እና የመሬት ይዞታ መብትን በጥልቀት ለመለየት መቻሉ ሊደነቅ የሚገባው ሕገ-መንግሥታዊ ትንታኔ ነው፡፡ በተጨማሪም በሰ/መ/ቁጥር 43600 የተሰጠውን አስገዳጅ የህግ ትርጉምን ሙሉ በሙሉ ከመሻር ይልቅ በሚገባው የሕግ አውድ (በቤት ባለቤትነት ላይ) ብቻ እንዲወሰን በማድረግ ትክክለኛ የአስገዳጅ የህግ ትርጉም አስተዳደር/አተገባበርን ለማሳየት ችሏል፡፡ እንዲሁም የባለቤትነትን እና የይዞታ መብትን ማምታታት በሰ/መ/ቁጥር 210477 የተሰጠውን መሠረታዊ የሕግ ስህተት ያለበትን አስገዳጅ የህግ ትርጉም በአግባቡ በማረም ለአስገዳጅ የሕግ ትርጉም ስርዓት ጥራት እና ታዓማኒነት አስተዋጽኦ አድርጓል፡፡ ችሎቱ የከተማ መሬት መብቶችን ተራ የውል ግንኙነት ሳያደርግ ከሁሉም ሰዎች ልንጠይቃቸው የምንችላቸው ተጨባጭ መብቶች (In rem) መሆናቸውን ማረጋገጡ እና ጉዳዩን በ7 ዳኞች በማየት ተቋማዊ ቅቡልነትነን (Institutional Legitimacy) ማጠናከሩ የውሳኔው ዐበይት ጥንካሬዎች ናቸው፡፡
ክፍል ሰባት፡ አዲሱ አስገዳጅ የሰበር ውሳኔ እና አዋጅ ቁጥር 1324/2016፡ የሕግ በጊዜ አተገባበር እና የአመሳስሎሽ ትርጓሜ መነጽር የተደረገ ዳሰሳ
7.1 መግቢያ
የካቲት 30 ቀን 2018 ዓ.ም. ሰባት ዳኞች በተሰየሙበት የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት የተሰጠው አስገዳጅ ውሳኔ ቁልፍ ትርጉሙ (Ratio decidendi)፤ የከተማ መሬት ይዞታን ሕገ-ወጥ ከሆነ መንገድ ከያዘው ሰው ላይ ለማስመለስ የሚቀርብ ክስ በ10 ዓመት ይርጋ ይታገዳል የሚለው ሲሆን ፣ "የሕግ በጊዜ አተገባበር" (Intertemporal law፤ ሕጎች በጊዜ ሂደት ያላቸውን ተፈፃሚነት የሚገዛ መርህ) እና "የአመሳስሎሽ ትርጓሜ" (Analogical reasoning) ተቀራራቢ የሕግ ድንጋጌዎችን በመጠቀም የሕግ ክፍተትን የመሙላት ሥነ-ዘዴ) በሚሉት ሁለት መነጽሮች ሲመረመር እጅግ አሳማኝ የሆኑ አካዳሚያዊ እና ተግባራዊ ጥያቄዎችን ሊስነሳ የሚችል ነው፡፡ ይህ አዲስ አስገዳጅ ውሳኔ እና ከእርሱ በፊት ነሐሴ 8 ቀን 2016 ዓ.ም የወጣው የፌዴራል የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም አዋጅ ቁጥር 1324/2016. መገጣጠም፣ የችሎቱን ሥነ-ሥርዓታዊ ትክክለኛነት እና የፅንሰ-ሐሳብ (የዶክትሪን) ምርጫዎች ለየብቻ እና በሂሳዊ መንገድ እንድንገመግም ሰፊ የትንታኔ መደላድል የሚፈጥር ይመስለኛል፡፡ በዚህ ረገድ ሊደረግ የሚችለው ትንታኔ የጉዳዩን ፍሬ-ነገሮች፣ የአዋጅ ቁጥር 1324/2016 ድንጋጌ አግባብነት ያላቸውን ድንጋጌዎች (በተለይም የይርጋ እና የሽግግር ድንጋጌዎችን)፣ እና የፍትሐብሔር ሕጉን የይርጋ ማዕቀፍ መሠረት በማድረግ ሊከናወን የሚችል ነው፡፡
በሌላ በኩል ውሳኔው አንዳንድ ድክመቶች እና ቀጣይ ማብራሪያ የሚሹ ክፍተቶችም የሚታዩበት መሆኑን የግል ምልክታ አድርጌአለሁ፡፡ የፍ/ብ/ሕ/ቁ 1845 የ10 ዓመት ይርጋ በከተማ መሬት ላይ ተግባራዊ እንዲሆን የተሰጠው ትንታኔ አጠር ያለ እና ተጨማሪ ማብራሪያ የሚሻ ነው፡፡ ይህንን ይርጋ ተግባራዊ ማድረግ በተለይም ከአገር ውጭ በነበሩ ወይም በተለያዩ አቅም በሚያሳጡ ሁኔታዎች ውስጥ ላሉ ዜጎች ሕገ-መንግሥታዊ መብት ላይ የሚያመጣው ተፅዕኖ ከፖሊሲ አኳያ አልተገመገመም፡፡ እንዲሁም በሰ/መ/ቁጥር 43600 የተሰጠውን የህግ ትርጉምን በተመለከተ "ተፈፃሚ ለማድረግም ሆነ ተቃርኖ አለው ለማለት አልተቻለም" የሚለው የችሎቱ አገላለጽ የተወሰነ ብዥታን የሚፈጥርና ይበልጥ ግልጽ ቢደረግ ይመረጥ የነበረ ነው፡፡ በዚሁ አስገዳጅ ውሳኔ ውስጥ በሌሎች ልዩ ህጎች የተመለከቱትን የይርጋ ድንጋጌዎችን በሚመለከት የተቀመጠውን አገላለፅ መጠቀም ያልተቻለበትን አግባብ ውሳኔው አያሳይም፡፡ ከዚህም በተጨማሪ የመፋለም ክስ ከመሬት ጋር እንደማይሄድ ከተገለጸ በኋላ፣ በትክክል ክሱ በምን ዓይነት የክስ ምክንያት (Cause of action) መቅረብ እንዳለበት ግልጽ አቅጣጫ አለመቀመጡ ለባለሙያዎች ክፍተት ትቷል፡፡ ከገጠር መሬት አዋጅ ድንጋጌዎች ጋር በማነፃፀር ለከተማ መሬት ተመሳስሎሽ ትንታኔ (Analogical reasoning) ያልተጠቀመበትን አግባብም መኖሩን ውሳኔው ማሳየቱን ችሎቱ እንዲህ አይነት የህግ ትርጉም ስልት ተግባር ላይ ለማዋል/ለመውሰድ የነበረውን መልካም አጋጣሚ ማምከኑን የሚያሳይ ነው፡፡ እንዲሁም ቅን ልቦ የሌለው ወይም መጥፎ ልቦና (Bad faith) ያለው የመሬት ነጣቂ የ10 ዓመት ይርጋን ተገን አድርጎ መብት ሊያገኝ የሚችልበትን የፍ/ህ/ቁጥር 1854 ድንጋጌ አንድምታ ችሎቱ አለመመርመሩ እንደ ውሳኔው ድክመቶች ሊነሱ የሚችሉ ነጥቦች ይመስሉኛል፡፡
7.2 አዲሱን ሕግ በመታየት ላይ ባሉ ጉዳዮች ላይ ያለመተግበር ትክክለኛነት፡ የሽግግር ድንጋጌዎችን በጥብቅ መከተል
ከላይ እንደተጠቀሰው በፍ/ብ/ህ/ሥ/ሥርዓት እና በሕግ ትርጓሜ መሠረታዊ መርሆች መሠረት፣ አዲስ የወጣ መሰረታዊ ሕግ (Substantive law) የሕግ አውጪው በግልጽ ካልደነገገ በስተቀር ወደኋላ ተመልሶ አይሰራም፡፡ ይህ ሕግ ወደኋላ ተመልሶ አለመሥራት መርህ (lex prospicit, non respicit) የሕግ ተገማችነት (Legal certainty) የጀርባ አጥንት ሲሆን፣ የተከራካሪ ወገኖች መብት እና ግዴታ የሚገዛው ድርጊቱ በተፈጸመበት ወይም ቢያንስ ክርክሩ በፍርድ ቤት በተጀመረበት ጊዜ በነበረው ሕግ መሆኑን ያረጋግጣል፡፡ አሁን በተያዘው ጉዳይ ይህ መርህ እጅግ ግልጽ በሆነ መንገድ ይሠራል፡፡ ተጠሪ (ከሳሽ) ክሳቸውን ያቀረቡት ሐምሌ 14 ቀን 2013 ዓ.ም.
ሲሆን፣ የክሱ መነሻ (ሕገ-ወጥ የመሬት ይዞታ ንጥቂያ) ተከሰተ የተባለው ደግሞ በ2011 ዓ.ም. (ወይም አመልካች እንደሚሉት በ1980 ዓ.ም.) ነው፡፡ በአንፃሩ አዲሱ የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም አዋጅ ቁጥር 1324/2016 ፀድቆ በነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ የወጣው በነሐሴ 08 ቀን 2016 ዓ.ም. ነው፡፡ ይህም ማለት ክርክሩ ከተጀመረና በተለያዩ የፍርድ ቤት እርከኖች ሲንከባለል ከቆየ ከዓመታት በኋላ ነው፡፡ ዋናው ቁም ነገር አዋጁ ራሱ ይህንኑ ሁኔታ የሚገዛ ግልጽ የሽግግር ድንጋጌ (Transitional provision) የያዘ መሆኑ ነው፡፡ የአዋጅ ቁጥር 1324/2016 አንቀጽ 65(1) በማያሻማ ቋንቋ እንዲህ ይደነግጋል፡- "የዚህ ሕግ ድንጋጌዎች ይህ አዋጅ ከመፅደቁ በፊት… ፍርድ ቤት ቀርበው ክርክር እየተደረገባቸው ባሉ ጉዳዮች ላይ ተፈፃሚ አይሆንም"፡፡ ይህ ድንጋጌ አዲሱ ሕግ፤ በአዋጁ የተካተቱ ማናቸውንም የይርጋ ጊዜያት ጨምሮ፣ ወደፊት ብቻ የሚሠራ እንጂ አዋጁ ከመውጣቱ በፊት በፍርድ ቤት በመታየት ላይ የነበሩ ጉዳዮችን ወደኋላ ተመልሶ እንደማያካትት የሕግ አውጪው የሰጠው ግልጽ መመሪያ ነው፡፡
ይህ የሽግግር ድንጋጌ በቀጥታ አግባብነት ያለው፣ የዚሁ አዋጅ አንቀጽ 64(2) ለመሬት ማስለቀቅ ክስ የ15 ዓመት የይርጋ ጊዜ ስለሚደነግግ ነው፡፡ ይህ ድንጋጌ ለዚህ ጉዳይ ተፈፃሚነት ቢኖረው ኖሮ ውጤቱን ሊቀይረው ይችል ነበር፡- ማለትም ፍርድ ቤቱ በተገበረው የ10 ዓመት ይርጋ ታግዷል የተባለው የተጠሪ ክስ፣ የይርጋው መቆጠር መነሻ ጊዜ አሰላል ታይቶ በ15 ዓመቱ የይርጋ ጊዜ ሥር ሊድን (ሊቀጥል) ይችል ነበር፡፡ ሆኖም ሰባት ዳኞች የተሰየሙበት የሰበር ችሎት ይህንን አዲስ የ15 ዓመት የይርጋ ጊዜ ከ2013 ዓ.ም. ጀምሮ በፍርድ ቤት በመታየት ላይ ባለ ጉዳይ ላይ ተግባራዊ አለማድረጉ ፍፁም ትክክል ነው ሊባል የሚችል ነው፡፡ እንዲያውም በሥነ-ሥርዓት ደረጃ ሲታይም አስገዳጅነት የነበረው ተግባር ነው፡፡ ይህን አድርጎ ቢሆን ኖሮ፣ አጠቃላይ የሆነውን ሕግ ወደኋላ ተመልሶ አለመሥራት መርህን እና የአንቀጽ 65(1)ን የተለየ የሽግግር መመሪያ በጣሰ ነበር፡፡
ስለሆነም ችሎቱ የሕግ ክፍተቱን ለመሙላት የተከተለው አካሄድ መገምገም ያለበት ክሱ በቀረበበት ጊዜ (በ2013 ዓ.ም.) በነበረው የሕግ ማዕቀፍ ውስጥ ሆኖ ነው፡፡ በዚያን ወቅት፣ የከተማ መሬት ይዞታን ለማስመለስ የሚቀርብ ክስን በተመለከተ የተለየ የይርጋ ጊዜ ባለመኖሩ የተፈጠረውን የሕግ ክፍተት ለመሙላት በሕግ ሥርዓቱ ውስጥ የነበሩት አማራጮች፣ የፍትሐብሔር ሕጉ (በተለይም አንቀጽ 1677 እና 1845)፣ ወይም ደግሞ ቀድሞ የነበረው የገጠር መሬት አዋጅ (አዋጅ ቁጥር 456/1997) ብቻ ነበሩ (የኋለኛው አዋጅም ቢሆን በሰበር መ/ቁ 69302 እንደተረጋገጠው ለዚህ ክስ የሚሆን ግልጽ የይርጋ ጊዜ አላስቀመጠም ነበር)፡፡ ችሎቱ ክፍተቱን ለመሙላት የፍ/ህ/ቁ 1677(2) እና 1845ን (ጠቅላላ የ10 ዓመት ይርጋን) የመረጠ ሲሆን፣ ይህ ምርጫ የተደረገው በወቅቱ በነበረው የሕግ ሥርዓት ተጨባጭ ሁኔታ ላይ ተመሥርቶ ነው፡፡ የሕግ አውጪው ከጊዜ በኋላ ለገጠር መሬት ክሶች የተለየ እና የረዘመ የይርጋ ጊዜ ማውጣቱ የችሎቱን ውሳኔ ወደኋላ ተመልሶ ሕገ-ወጥ አያደርገውም፡፡ ይልቁንም፣ ፍርድ ቤቱ ገና ላልወጣ ሕግ እውቅና ሰጥቶ ወደኋላ ተግባራዊ አለማድረጉ የዳኝነት ሥልጣን ያለበትን የጊዜ ገደብ መረዳቱን እና የሕግ አውጪውንና የሕግ ተርጓሚውን የሥልጣን ክፍፍል ማክበሩን ያሳያል፡፡ በመሆኑም ባለሰባት ዳኞች ሰበር ችሎት የሕግን በጊዜ አተገባበር (Intertemporal law) መርህ የተገበረበት መንገድ ጉድለት የለሽ ነው፡፡ ችሎቱ አግባብነት ያለውን የጊዜ ማዕቀፍ በትክክል ለይቷል፤ ክሱ በቀረበበት ጊዜ የነበረውን ሕግ ተግብሯል፤ እንዲሁም ከዓመታት በኋላ የሚወጣን ሕግ አስቀድሞ ከመገመትና ከመተግበር ታቅቧል ለማለት ያስደፍራል፡፡
7.3 የአመሳስሎሽ ትርጓሜ ችግር፡ የሕግ ክፍተትን ለመሙላት በተመረጠው ምንጭ ላይ የታየ የፅንሰ-ሐሳብ (የዶክትሪን) መዛባት
ምንም እንኳን ችሎቱ የሕግን በጊዜ አተገባበር መርሆችን የተከተለበት መንገድ ተገቢነት ያለው ቢሆንም፣ የሕግ ክፍተቱን ለመሙላት የመረጠው የአመሳስሎሽ (Analogical) ድልድይ ግን ቀጣይነት ያለው አካዳሚያዊ ክርክር የሚሻ ከባድ የሕግ ፍልስፍና ጥያቄን ማስነሳቱ አይቀሬ መስሎ ታይቶኛል፡፡የዚህ ሂሳዊ ግምገማዬ መነሻም ችሎቱ የሕግ ክፍተቱን ለመሙላት (Gap-filling) ጥረት ማድረጉ አይደለም፤ ለከተማ መሬት ክስ የተለየ ይርጋ ባለመኖሩ ይህን ማድረጉ ተገቢና አስፈላጊ ነበር፣ ነገር ግን ትችቱ የሚያነጣጥረው በአመሳስሎሽ የወሰደውን የይርጋ ጊዜ ባመጣበት የተለየ ምንጭ ላይ በማተኮር ነው፡፡ ችሎቱ የከተማ መሬት ይዞታ ክርክርን የሚገዛ የይርጋ ጊዜ በሕግ አለመኖሩን ሲገነዘብ፣ ከፍትሐብሔር ሕጉ ሦስተኛ መጽሐፍ (ስለ ንብረት ሕግ) በመውጣት፣ ወደ አራተኛው መጽሐፍ (ስለ ግዴታዎች) ተሻገረ። በዚያም የውል ሕግ ደንቦች ከውል ውጭ በሆኑ ግዴታዎች ላይ ተፈፃሚ እንደሚሆኑ የሚደነግገውን አንቀጽ 1677(2) ድንጋጌን እንደ ማሻገሪያ ድልድይ በመጠቀም በፅሑፍ አቀማመጡ ውልን ለመፈፀም፣ ላለመፈፀም ወይም ለማፍረስ ለሚቀርቡ ክሶች የተዘጋጀውን በቁጥር 1845 ድንጋጌ ሥር የሚገኘውን አጠቃላይ የ10 ዓመት ይርጋ ተግባራዊ አድርጎታል። ይህ አካሄድ ከዚህ ቀደም ለገጠር መሬት ክርክሮች በሰበር መ/ቁ 69302 ከተወሰደው የትንታኔ መንገድ ጋር ሙሉ በሙሉ ተመሳሳይ ነው፡፡
ሆኖም የሕግ አውጪው በገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም አዋጅ ቁጥር 1324/2016 የገጠር መሬትን ለማስመለስ የሚቀርብ ክስን የይርጋ ጊዜ በተመለከተ በራሱ ጊዜ ምላሽ ሲሰጥ፣ በአንቀጽ 64(2) ሥር ያስቀመጠው ገደብ 15 ዓመት እንጂ 10 ዓመት አልነበረም፡፡ ይህ የሕግ አውጪው ምርጫ በፅንሰ-ሐሳብ ደረጃ እጅግ ወሳኝ ነው፤ ምክንያቱም ለመሬት ማስለቀቅ ክሶች ተገቢ ነው ብሎ ያሰበው የጊዜ አድማስ ፍርድ ቤቱ በአመሳስሎሽ ከመረጠው የጊዜ ገደብ በእጅጉ የተለየ መሆኑን ያሳያልና፡፡ ከዚህም በላይ፣ የሕግ አውጪው የ15 ዓመትን ጊዜ መምረጡ የዘፈቀደ አልነበረም፡፡ ይህ ጊዜ በፍትሐብሔር ሕጉ አንቀጽ 1168 ሥር የማይንቀሳቀስ ንብረትን በተከታታይ ይዞታ እና ግብር በመክፈል (Adverse possession) ባለሀብት ለመሆን ከሚያስፈልገው የ15 ዓመት ጊዜ ጋር በትክክል ይገጠማል፡፡ ይህ መመሳሰል በግልጽ የሚያሳየው፣ የሕግ አውጪው የመሬት ማስለቀቅ ክስ ይርጋን ከንብረት ሕጉ የይዞታ መብት አሰጣጥ ጋር በማዛመድ (Calibrating) በንብረት መብት ማዕቀፍ ውስጥ ውስጣዊ ወጥነትን መፍጠሩን ነው፡፡
ይህ ምልከታ አንድ መሠረታዊ የስነ-ዘዴ (Methodological) ጥያቄን ቁልጭ አድርጎ ያጋልጣል፡፡ ይኸውም ችሎቱ የከተማ መሬት ማስለቀቅ ክስን (ወደ አንቀጽ 1168 የ15 ዓመት ይርጋ ከሚያመላክተው) የንብረት ሕግ አሠራር ይልቅ፣ (በአንቀጽ 1845 ወደ 10 ዓመት የሚያወርደው) የውል ግዴታ ጋር ማመሳሰል ለምን መረጠ? ጥያቄው አካዳሚያዊ ብቻ አይመስለኝም፡፡ በሲቪል ሎው የሕግ ሥነ-ዘዴ መሠረት፣ አንድ ፍርድ ቤት በአመሳስሎሽ ትርጓሜ የሕግ ክፍተትን ሲሞላ፣ አመሳስሎሹ መወሰድ ያለበት በጣም የጠበቀ የቅርብ ዝምድና ካለው የሕግ ማዕቀፍ (Nearest cognate legal regime)፣ ማለትም በውስጣዊ መርሆች፣ ዓላማዎች እና መዋቅር ከዋናው ጉዳይ ጋር እጅግ ከሚቀራረበው የሕግ
አካል ሊሆን እንደሚገባው ይታወቃል፡፡ የመሬት ይዞታ መብት (Holding rights)፣ የሰባት ዳኞች ችሎት ራሱ እንዳመነው፣ ተጨባጭ፣ የሚመዘገቡ፣ የሚተላለፉ እና መያዣ ሊሆኑ የሚችሉ፣ ከሁሉም ስዎች ልንጠይቃቸው የምንችላቸው (In rem) የንብረት መብቶች ናቸው፡፡ እነዚህ መብቶች ከግለሰቦች ጋር ብቻ ከሚያያዙ (Personal, inter partes) እና ፍጹም የተለየ መርህ ካላቸው የውል ግዴታዎች ጋር በመደባቸው አይገናኙም፡፡ አንድ ሕገ-ወጥ የመሬት ያዥ መሬቱን የመመለስ ግዴታ ያለበት፣ በነገር ላይ ያለን (In rem) መብት በመጣሱ እንጂ የውል ቃልን በማፍረሱ (Breach of contractual promise) አይደለም፡፡
ይህ የሕግ ባህሪ ታሳቢ ሲደረግ፣ ይበልጥ ፅንሰ-ሐሳባዊ ወጥነት (Doctrinal coherence) ያለው የአመሳስሎሽ ምንጭ ሊሆን የሚገባው የፍትሐብሔር ሕጉ የንብረት ድንጋጌዎች፤ በተለይም በአንቀጽ 1168 ሥር ያለው የ15 ዓመት ማዕቀፍ እንጂ የአራተኛው መጽሐፍ የውል ግዴታዎች ክፍል አልነበረም፡፡ የፍ/ህ/ቁ 1168 ድንጋጌ የማይንቀሳቀስ ንብረትን ለ15 ዓመት ከነግብሩ የያዘ ሰው የንብረቱ ባለቤት እንደሚሆን ይደነግጋል፡፡ ከዚህ በተቃራኒው በኩል ያለውን አመክንዮ ስናይ (ከመብቱ ለተነጠቀው ሰው አኳያ)፣ ንብረቱን በሕገ-ወጥ መንገድ የተነጠቀ ሰው መብቱን ለማስመለስ የሚችለውም በተመሳሳይ የ15 ዓመት ጊዜ ውስጥ መሆን አለበት የሚል መደምደሚያ ላይ ያደርሳል፡፡ ይህ ሚዛናዊ የሆነን ማዕቀፍ ይፈጥራል፡፡ በሌላ አገላለፅ ሕገ-ወጥ ያዡ መብት ለማግኘት 15 ዓመት ያስፈልገዋል፤ መብቱ የተነጠቀው ሰው ደግሞ መብቱን ለማስመለስ 15 ዓመት አለው ማለት ነው፡፡ በአንፃሩ ሰበር ችሎቱ የ10 ዓመቱን የውል ይርጋ መተግበሩ መዋቅራዊ አለመመጣጠንን (Asymmetry) የሚፈጥር ነው፡፡ ምክንያቱም ሕገ-ወጥ ያዡ ባለመብት ለመሆን አሁንም በአንቀጽ 1168 መሠረት 15 ዓመት ሲያስፈልገው፣ መብት የተነጠቀው ሰው ግን ከንብረት ሕጉ መዋቅር ጋር ምንም ዓይነት መዋቅራዊ ዝምድና በሌለው ሕግ መብቱን በ10 ዓመት ብቻ ያጣል የሚል መልዕክት አለው ማለት ነው፡፡
የሕግ አውጪው ከጊዜ በኋላ በአዋጅ ቁጥር 1324/2016 አንቀጽ 64(2) መሠረት ለገጠር መሬት ክስ የ15 ዓመት ይርጋ ማውጣቱ፣ ከላይ ለተነሳው ሂሳዊ ትንታኔ ከፍ ያለ ዋጋ ያለውን የማጠናከሪያ ድጋፍ የሚሰጥ ሁኖ ይገኛል፡፡ ምንም እንኳን ችሎቱ የሕግ አውጪውን ቀጣይ ውሳኔ አስቀድሞ ማወቅ ባይችልም፣ የሕግ አውጪው የወሰደው ምርጫ ግን ለመሬት ማስለቀቅ ክርክሮች ትክክለኛው የፅንሰ-ሐሳብ (የዶክትሪን) መሠረት የፍ/ህ/ቁጥር 1168 ድንጋጌ የንብረት ሕግ አመክዮ እንጂ የቁጥር 1845 ድንጋጌ የውል ሎጂክ አለመሆኑን ያረጋግጣል፡፡ የሕግ አውጪው የይርጋ ሥርዓቱን ከውል ይልቅ ከንብረት ሕግ ማዕቀፍ ጋር ማጣመሩ የሚያሳየው፣ የችሎቱ የአመሳስሎሽ ድልድይ በፅሑፋዊ ትርጓሜ ሊደገፍ የሚችል ቢሆንም በፅንሰ-ሐሳብ (በዶክትሪን) ደረጃ ግን አጥጋቢ አለመሆኑን (Doctrinally suboptimal) ነው፡፡
በመሆኑም አዲሱ አስገዳጅ የሰበር ውሳኔ (ለከተማ መሬት ክስ የ10 ዓመት ይርጋን ማስቀመጡ) እና ከእርሱ በፊት የወጣው አዋጅ ቁጥር 1324/2016 (በአንቀጽ 64(2) ለገጠር መሬት ክስ የ15 ዓመት ይርጋን መደንገጉ) መገጣጠም፣ በኢትዮጵያ የመሬት ሕግና የአስገዳጅ የህግ ትርጉም ላይ ያልታሰበ እና ከፍተኛ አንድምታ ያለው የይርጋ ጊዜ መከፈል (Bifurcation of limitation periods) ይዞ ተከስቷል፡፡ ከዚህ አንፃር አሁን በተጨባጭ ባለው ነባራዊ የሕግ ማዕቀፍ መሠረት፡-የይዞታ መብቱ በሕገ-ወጥ ያዥ የተጣሰበት የገጠር መሬት ባለይዞታ፣ መብቱን ለማስመለስ የሚያስችል የ15 ዓመት ጊዜ አለው (በአዋጅ 1324/2016 አንቀጽ 64(2) መሠረት) ሲኖረው ፍጹም ተመሳሳይ በሆነ ሁኔታ ውስጥ የሚገኝ የከተማ መሬት ባለይዞታ ግን በአዲሱ የሰበር ውሳኔ እና በፍ/ብ/ሕ/ቁ 1677(2) እና 1845 ደንጋጌዎች መሠረት የ10 ዓመት ጊዜ ብቻ ይኖረዋል ማለት ነው፡፡
ይህን ልዩነት በጠንካራ መርህ ላይ ተመሥርቶ ለማስረዳትና አሳማኝ ለማድረግ እጅግ አዳጋች ነው፡፡ ምክንያቱም የገጠርም ሆነ የከተማ መሬት ይዞታ መብቶች የሚመነጩት ከአንድ ዓይነት ሕገ-መንግሥታዊ መሠረት፤ ማለትም መሬት (የገጠርም ሆነ የከተማ) የመንግስትና የሕዝብ ንብረት መሆኑን ከሚያውጀውና የግል ባለቤትነትን ከሚከለክለው የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ሕገ-መንግሥት አንቀጽ 40(3) ነውና፡፡ የመብቱ ባህሪ (ከባለቤትነት ያነሰ ነገር ግን በነገር ላይ ያለ ከሁሉም ሰዎች ልንጠይቀው የምንችለው (In rem) ተጨባጭ የንብረት መብት መሆኑ) መሬቱ የሚገኘው በከተማ ክልል ውስጥ ሆነም በገጠር፣ በተጠቃሹ ሕገ-መንግሥታዊ ድንጋጌ ዕይታ አንድ ዓይነት ነው፡፡
የሕገ-መንግሥታዊ መሠረቱ አንድ ዓይነት ከሆነ፣ ለባለይዞታዎች የሚሰጠው የሕግ ከለላም በመርህ ደረጃ አንድ ዓይነት ሊሆን ይገባል፡፡ ለገጠር መሬት ባለይዞታ 15 ዓመት እየተሰጠ የከተማውን ባለይዞታ በ10 ዓመት መገደብ ምክንያታዊ የሆነ የፖሊሲ መሠረት (Rational policy basis) የሌለው ልዩነትን መፍጠር ሲሆን፣ ይህ ደግሞ ሰባት ዳኞች የተሰየሙበት ችሎት የተቃረኑ ውሳኔዎችን በማረም ሊያመጣው የፈለገውን የሕግ ወጥነት (Doctrinal consistency) የሚሸረሽር ነው፡፡
አንድ ሰው የከተማ እና የገጠር መሬት የተለያዩ ማሕበራዊና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳዎች እንዳላቸው፣ በተለያዩ የቁጥጥር ሥርዓቶች እንደሚመሩ፣ እና የክርክሮቹም ተጨባጭ ሁኔታዎች እንደሚለያዩ በማንሳት፣ ይህ ልዩነት የተለያየ የይርጋ ጊዜን ተገባራዊ ማድረግ እንደሚችል ይሞግት ይሆን ይሆናል፡፡ ይሁን እንጂ እንዲህ ዓይነቱ መከራከሪያ፣ የከተማ መሬት የይዞታ ሥርዓት ከገጠሩ ይበልጥ መደበኛ፣ በሰነድ የተደገፈ፣ እና በአስተዳደር ሥርዓት የተደራጀ ነው የሚለውን መደበኛ አስተሳሰብ ወደ ጎን ትቶ፣ የከተማ ባለይዞታ መብቱን ለመጠየቅ ከገጠሩ ባለይዞታ ያነሰ ጊዜ ሊሰጠው የሚገባው ለምንድን ነው? የሚለውን አሳማኝ በሆነ መንገድ ማስረዳት ይጠበቅበታል፡፡ እንዲያውም፣ በገጠር መሬት ይዞታ ላይ ያለው ሰፊ ኢ-መደበኛነት እና የሰነድ አያያዝ ክፍተት፣ መረጃዎች በገጠሩ አካባቢ ቶሎ ስለሚጠፉ፣ ለገጠር መሬት ክስ ከከተማው ያጠረ (ያልረዘመ) የይርጋ ጊዜ ሊያስፈልግ ይችላል ወደሚል ንድፈ-ሐሳባዊ መከራከሪያ ሊያመራን ይችላል፡፡ አሁን በህጉና በአስገዳጅ የህግ ትርጉም የተወለደው ዥንጉርጉር ሥርዓት ማለትም ገጠር 15 ዓመት፣ የከተማ 10 ዓመት ይርጋ ጊዜ እንዲሆን የተደረገበት ኩነት ይህንን ሎጂክ/አመክንዮ/ የተገላቢጦሽ ያደርገዋል፡፡
7.4 የክፍል 7 ጥማቂ
የሰባት ዳኞች ችሎት በዚህ ጉዳይ ላይ የሕግን በጊዜ አተገባበር (Intertemporal law) ያስተናገደበት መንገድ እንከን የለሽ (Flawless) ነው ሊባል የሚችል ቢሆንም ችሎቱ ክሱ በቀረበበት ጊዜ (በ2013 ዓ.ም.) የነበረውን የሕግ ማዕቀፍ በመተግበር፣ የሕግ ክፍተቱን በወቅቱ በነበሩ የፍትሐብሔር ሕግ ድንጋጌዎች በመሙላት፣ እና ገና ፀድቆ ላልወጣ አዋጅ (አዋጅ ቁጥር 1324/2016) ወደኋላ ተመልሶ የሚሠራ የተፈፃሚነት ኃይል ላለመስጠት መወሰኑ በሥነ-ሥርዓትም ሆነ በመሰረታዊ ህግ ይዘት ችግር የለውም፡፡ በወቅቱ ላልነበረ ሕግ አልተገበርክም ተብሎ ችሎቱን መተቸት የሚቻልበት የህግ አግባብ የለም፡፡ እንዲሁም የአዋጅ ቁጥር 1324/2016 የአንቀጽ 65(1)
የሽግግር ድንጋጌ ራሱ አዲሱ ሕግ በመታየት ላይ ባሉ ጉዳዮች ላይ እንደማይሠራ በማረጋገጥ ይህንን ያጠናክረዋል፡፡ ሆኖም ችሎቱ የሕግ ክፍተቱን ለመሙላት የመረጠው የአመሳስሎሽ ድልድይ፤ ማለትም ከአራተኛው መጽሐፍ (የግዴታዎች ሕግ) የተወሰደው የፍ/ብ/ሕ/ቁ 1845 የ10 ዓመት ይርጋ፣ የሕግ አውጪው ከጊዜ በኋላ በአዋጅ 1324/2016 አንቀጽ 64(2) ለገጠር መሬት ክስ የ15 ዓመት ይርጋን መደንገጉን ስናይ በፅንሰ-ሐሳብ (በዶክትሪን) ደረጃ የጎላ ክፍተት ያለበት ሆኖ ይታያል፡፡ የሕግ አውጪው የገጠር መሬት ይርጋን የ15 ዓመት የይዞታ (Adverse possession) ሥርዓት ከሚደነግገው የፍ/ብ/ሕ/ቁ 1168 ጋር ማጣመሩ፣ ለመሬት ማስለቀቅ ክሶች ተፈጥሯዊ እና ፅንሰ-ሐሳባዊ ወጥነት ያለው የአመሳስሎሽ ምንጭ የሚገኘው በንብረት ሕጉ ማዕቀፍ ውስጥ እንጂ በውል ግዴታዎች ማዕቀፍ ውስጥ አለመሆኑን የሚያስገነዝብ ሁኖ ይገኛል ችሎቱ ከፍ/ህ/ቁጥር 1168 ይልቅ አንቀጽ 1845 ድንጋጌን መምረጡ በፅሑፋዊ ትርጓሜ ሊደገፍ የሚችል ቢሆንም፣ በኢትዮጵያ የመሬት ሕግ ውስጥ ሁለት የተምታታ እና የሚጋጭ ሥርዓት (Dual and conflicting regime) ይዞ ብቅ ብሏል፡፡ ምንም እንኳን ሕገ-መንግሥታዊ መሠረታቸው እና የመብታቸው የሕግ ባህሪ አንድ ዓይነት ቢሆንም፣ የከተማ መሬት ክስ በ10 ዓመት፣ የገጠር መሬት ክስ ደግሞ በ15 ዓመት እንዲታገድ ማድረግ የህግ ባለሙያውንም ሆነ ሌላውን የማህበረሰብ ክፍል የሚያሳምን ሊሆን አይችልም፡፡
ይህ ሥርዓታዊ አለመጣጣም ከሁለት በአንዱ መንገድ ዕልባት እስካላገኘ ድረስ የኢትዮጵያን የንብረት ሕግ ስነ ህግ እድገና የአስገዳጅ ህግ ትርጉም ወጥነት ግብ በፅኑ መፈተኑን የሚይቀጥል መሆኑ ይገመታል፡፡ ስለሆነም ባለሰባት ዳኞች ሰበር ችሎት ለከተማ መሬት የሰጠውን አስገዳጅ ትርጉም ከፍ/ህ/ቁጥር 1168 መሰረተ ሃሳብና ከተገቢው የህግ አተረጓጎም ስልት አንፃር በድጋሚ በመገምገም በቅርብ ጊዜ በወጣው የገጠር መሬት ህግ ውስጥ ከተደነገገው የ15 ዓመት ማዕቀፍ ጋር ያጣጥመዋል፣ አለበለዚያ ደግሞ የሕግ አውጪው (ፓርላማው) ከገጠር መሬት ሥርዓት ጋር የተናበበ የይርጋ ድንጋጌን ያካተተ አጠቃላይ የከተማ መሬት አስተዳደር አዋጅ ያወጣል፡፡ ከፍ ሲል ደግሞ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ከላይ ከተጠቀሰው ህገ መንግስቱ ጥበቃ አንፃር አይቶ ህገ መንግስታዊ ትርጉም ሊሰጠበት ይችላል፡፡ ይህ የእርምት እርምጃ እስኪወሰድ ድረስ ለአንድ ዓይነት ሕገ-መንግሥታዊ መብት፤ በከተማ 10 ዓመት፣ በገጠር 15 ዓመት ሊሆን ይገባል ተብሎ የተከፋፈለው የይርጋ ጊዜ በኢትዮጵያ የመሬት ሕግ እና በአስገዳጅ የህግ ትርጉም ስርዓት ላይ ያልተፈታ ፅንሰ-ሐሳባዊ መዛባት (Doctrinal anomaly) ሆኖ መቀጠሉ አይቀሬ ነው፡፡ በመሆኑም ይህ በችሎቱ ውሳኔ እንደድክመት ሊነሳ የሚችል ተገቢ ምልክታ ነው የሚል እምነት አለኝ፡፡
ክፍል ስምንት፡ አጠቃላይ ማጠቃለያ
የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰባት ዳኞች ሰበር ችሎት የሰጠው ይህ ውሳኔ ተቃርኖ ያለባቸውን አስገዳጅ የህግ ትርጉሞችን ከማረቅና የስርዓቱን ወጥነትና ተገማችነት ከማስፈን አንፃ እጅግ መሠረታዊ እና አስፈላጊ ቢሆንም በአገሪቱ የንብረት እና የመሬት ሕግ ስነ ህግ ላይ ህገ መንግስታዊ መሰረትን ባልተጎናፀፈ አመክንዮ ተመሳሳይ ጥበቃ ያለውን የባለይዞታነት መብት በተለያዩ የይርጋ ጊዜያት እንዲገዙ ስርዓት ያበጀ በመሆኑ አከራካሪነቱ አይቀሬ ይመስለኛል፡፡ ውሳኔው በቀድሞ አስገዳጅ ውሳኔዎች መካከል የነበረውን ጥልቅ ተቃርኖ ሕገ-መንግሥታዊ መሠረትን እና የፍትሐብሔር ሕግን አግባብነት ያላቸውን መርሆች በሚገባ በመመርመር ተገቢውን የዳኝነት ጥበብ በመጠቀም ለመፈታት የተቻለበት መሆኑ ይታመናል፡፡ በተለይም የባለቤትነት መብትን (Ownership) ከይዞታ መብት (Holding rights) በሚገባ በመለየት፣ ለባለቤትነት የተፈጠሩ የሕግ ማዕቀፎችን የግል የመሬት ባለቤትነት በማይፈቅድ ሕገ-መንግሥታዊ ሥርዓት ውስጥ በቀጥታ ተግባራዊ ማድረግ የማይቻል መሆኑን አሳይቷል፡፡ ይህ የሕግ ትርጉም በኢትዮጵያ የከተማ መሬት ይዞታ ክርክሮች ላይ ፅንሰ-ሐሳባዊ ጥራትን፣ ሥርዓታዊ ወጥነትን እና ተገማችነትን በማምጣት ወደፊት ለሚነሱ የንብረት ሕግ ክርክሮች ጠንካራ መሠረት የሚጥል አንፀባራቂ የዳኝነት አሻራ ነው ተብሎ ቢውሰድ ማጋነን አይሆንብኝም፡፡ ሆኖም ከላይ በክፍል 7 ስር በሰፊው እንደተብራራው ችሎቱ የሕግ ክፍተቱን ለመሙላት የመረጠው የአመሳስሎሽ ድልድይ፤ ማለትም ከአራተኛው መጽሐፍ (የግዴታዎች ሕግ) የተወሰደው የፍ/ብ/ሕ/ቁ 1845 የ10 ዓመት ይርጋ፣ የሕግ አውጪው ከጊዜ በኋላ በአዋጅ 1324/2016 አንቀጽ 64(2) ለገጠር መሬት ክስ የ15 ዓመት ይርጋን መደንገጉን ስናይ በፅንሰ-ሐሳብ (በዶክትሪን) ደረጃ የጎላ ክፍተት ያለበት ሆኖ ይታያል፡፡ ስለሆነም ችሎቱ በራሱ አነሳሽነት የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ወይስ የፌዴፌሬሽን ምክር ቤት? ትክክለኛውን መስመስር ይለዩ ይሆን? በዚህ ነጥብ ላይ ሁላችንንም ሊያስተምር የሚችል የምርምር ስራ ወይም የውሳኔ ትችት እይታ በዘርፉ በበቁ በአወቁ የአገራችን ምሁራን ሊከናወን እንደሚችል ተስፋ አደርጋለሁ፡፡
አበቃ!!
ተፃፈ በአልማው ወሌ
መጋቢት 04 ቀን 2018 ዓ/ም
አዲስ አበባ
ማስታወሻ፦ ፅሁፉ ጥብቅ የምርምር ዘዴ በመከተል ያልተከናወነ መሆኑን ከወዲሁ እየገለፅሁ ለወደፊቱ ግን በዚሁ አርዕስትና ተያያዥ የህግ ጉዳዮች ላይ ፈጣሪ አምላክ ፍቃዱ ከሆነ ሙያዊ እና አካዳሚያዊ ደረጃውን የጠበቀ ስራ ይዠ ለመቅረብ እሞክራለሁ፡፡ ማናቸውም ስህተቶች የራሴው መሆናቸው እንዲታወቅልኝም እፈልጋለሁ፡፡
https://www.facebook.com/s...

9 months ago
“ኢትዮጵያውያን አሜሪካን በግብፅ እና በኢትዮጵያ መካከል እንድትመርጥ በፍጹም መጠየቅ የለባቸውም” — አምባሳደር ቲቦር ናጊ
በአሁኑ ወቅት ዓለማችን በ‘ግብይት ላይ የተመሰረተ ዲፕሎማሲ’ (Transactional Diplomacy) ማዕበል ውስጥ ትገኛለች።
በተለይም ያልተረጋጋው የአፍሪካ ቀንድ እና የቀይ ባህር ቀጠና የዚህ አዲስ የዲፕሎማሲ አካሄድ ዋነኛ መፈተኛ ሆነዋል። የቀድሞ ህጎች የማይሰሩበት፣ አዳዲስ አጋርነቶች የሚፈጠሩበትና የቆዩ ወዳጅነቶች የሚፈተኑበት ወቅት ላይ እንገኛለን።
እስራኤል ለሶማሊላንድ የሰጠችው ያልተጠበቀ እውቅና፣ የፕሬዝዳንት ኢሳይያስ አፈወርቂ ከዋሽንግተን ጋር ለመታረቅ ያሳዩት ፍላጎት፣ እና የፕሬዝዳንት ትራምፕ ወደ ካይሮ ያጋደለ አቋም የቀጠናውን ጂኦ-ፖለቲካዊ ገጽታ እየቀየሩት ነው። በዚህ ግራ የሚያጋባ ቀመር ውስጥ የኢትዮጵያ ሚና እና የወደፊት ዕጣ ፈንታ ምንድነው?
እነዚህንና ተያያዥ ጉዳዮችን በተመለከተ አንጋፋው ዲፕሎማት እና የትራምፕ የቀድሞ የአፍሪካ አምባሳደር ቲቦር ናጊ በአፍሪካ ቀንድ ስላለው እድገት ይናገራሉ።
አምባሳደር ቲቦር ናጊ ከሪፖርተር መጽሔት ጋር ያደረጉት ቆይታ እንደሚከተለው ቀርቧል።
እስራኤል እና ሶማሊላንድ፡ የካርታው ወደ እውነታነት መቀየር
ባለፈው ታህሳስ ወር (እ.ኤ.አ. ዲሴምበር 2025) እስራኤል ለሶማሊላንድ ይፋዊ እውቅና በመስጠት የመጀመሪያዋ የተባበሩት መንግስታት አባል ሀገር ሆናለች። ይህ እርምጃ በቀጠናው ትልቅ ድንጋጤን ፈጥሯል።
አምባሳደር ናጊ ለዓመታት የሶማሊላንድን እውቅና ሲሟገቱ የቆዩ በመሆናቸው ይህንን እርምጃ “እውነታን መቀበል” ሲሉ ይጠሩታል።
“እስራኤል እና ሶማሊላንድ በስተጀርባ ረጅም ድርድር ሲያካሂዱ ቆይተው ነው ይህንን አስገራሚ ዜና ይፋ ያደረጉት። እስራኤል በቀይ ባህር ላይ ስትራቴጂካዊ ቦታ ለማግኘት ስትል፣ ሶማሊላንድ ደግሞ ለ34 ዓመታት የጠፋባትን የህግ እውቅና (De jure legitimacy) ለማግኘት ሲሉ ይህንን ስምምነት አድርገዋል።”
እንደ አምባሳደሩ ገለፃ፣ ይህ እርምጃ ከአረብ ሊግ እና ከአፍሪካ ህብረት ተቃውሞ ቢገጥመውም፣ ሌሎች ሀገራት “አይተው ለመወሰን” (Wait and see) እየተጠባበቁ ነው። ይሁን እንጂ በ2026 ውስጥ ተጨማሪ ሀገራት ሶማሊላንድን እውቅና እንደሚሰጡ አምባሳደሩ ይተነብያሉ።
ትራምፕ፣ ግብፅ እና የዓባይ ጉዳይ፡ ኢትዮጵያውያን ሊረዱት የሚገባ ሀቅ
የፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ዳግም ወደ ስልጣን መምጣት በህዳሴ ግድብ ድርድር ላይ የራሱን ጥላ አሳርፏል። ትራምፕ በቅርቡ ከግብፅ ፕሬዝዳንት አብዱልፈታህ አል-ሲሲ ጋር በዳቮስ ሲገናኙ ግድቡን “አደገኛ” ሲሉ መግለጻቸውና የዓባይ ጉዳይ በአጀንዳቸው አናት ላይ እንደሚገኝ መናገራቸው ይታወሳል።
አምባሳደር ናጊ በዚህ ጉዳይ ላይ ለኢትዮጵያውያን ግልፅ የሆነ ማስጠንቀቂያ አዘል ምክር ሰጥተዋል፡-
“ኢትዮጵያውያን አሜሪካን በግብፅ እና በኢትዮጵያ መካከል እንድትመርጥ በፍጹም መጠየቅ የለባቸውም። ምክንያቱም በቀኑ መጨረሻ ግብፅ ለአሜሪካ የውጭ ፖሊሲ ከኢትዮጵያ ይልቅ እጅግ አስፈላጊ ናት። ይህ ተጨባጭ ሀቅ ነው።”
አምባሳደሩ አክለውም፣ አሜሪካ ታማኝ አስታራቂ ለመሆን ገለልተኛ መሆን ቢገባትም፣ ትራምፕ ግን ከካይሮ ጋር ያላቸውን ጥብቅ ግንኙነት ቅድሚያ እንደሚሰጡ ጠቁመዋል። ይሁን እንጂ ትራምፕ በድርድሩ ውስጥ በግላቸው ጥልቅ ተሳትፎ እንደማያደርጉ፣ ይልቁንም ውጤት ላይ ያተኮረ (Transactional) ስምምነት እንዲመጣ ግፊት እንደሚያደርጉ ገልጸዋል።
ኤርትራ እና አሜሪካ፡ የማይጨበጠው ተስፋ
ፕሬዝዳንት ኢሳይያስ አፈወርቂ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ለአሜሪካ ያላቸውን አቋም እያለዘቡ ቢመስሉም፣ አምባሳደር ናጊ ግን በሁለቱ ሀገራት መካከል የቅርብ ጥምረት ይፈጠራል ብለው አያምኑም።
“ከኢሳይያስ ጋር መደነስ አይቻልም” የሚሉት አምባሳደሩ፣ የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ በአንድ ወቅት የነገሯቸውን ጠቅሰዋል፡- “ኢሳይያስ በሚቀጥለው ቀን ጠዋት ተነስቶ እስኪወስን ድረስ ምን እንደሚያደርግ ማወቅ አይቻልም።” በዚህም ምክንያት ትራምፕም ቢሆኑ ከኤርትራ ጋር ባላቸው ግንኙነት እንደ መጀመሪያው የስልጣን ዘመናቸው ተስፋ ሊቆርጡ እንደሚችሉ ተንብየዋል።
የአሜሪካ አዲሱ የብሔራዊ ደህንነት ስትራቴጂ
በ2025 በወጣው የአሜሪካ የብሔራዊ ደህንነት ስትራቴጂ መሠረት፣ ዋሽንግተን በሌሎች ሀገራት ጉዳይ የምትገባው ጥቅሟ በቀጥታ ሲነካ ብቻ እንደሆነ ተደንግጓል። ለዚህም ነው አምባሳደር ናጊ “አሜሪካ የበጎ አድራጎት ድርጅት አይደለችም” የሚሉት።
እንደ አምባሳደሩ ገለፃ፣ አዲሱ የትራምፕ አስተዳደር ትኩረት የሚያደርገው በሚከተሉት ነጥቦች ላይ ነው፡-
ደህንነት፡ እንደ አልሸባብ ያሉ ቡድኖች ስጋት ሲሆኑ።
ኢንቨስትመንት፡ እንደ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ያሉ ስኬታማ ተቋማት ለአሜሪካ ኩባንያዎች እድል ሲፈጥሩ።
የሰው ኃይል (ቪዛ)፡ አሜሪካ የአፍሪካን የሰው ኃይል ትመዘብራለች የሚለውን ትችት ለማስቀረት እና ህገወጥ ስደትን ለመቆጣጠር የቪዛ አሰጣጥ ላይ ጥብቅ ቁጥጥር ማድረግ።
ማጠቃለያ
በአምባሳደር ናጊ እይታ፣ የአፍሪካ ቀንድ ሀገራት ከአሜሪካ ጋር ያላቸው ግንኙነት ከ“ታላቅ ወንድም እና ታናሽ ወንድም” ስሜት ወጥቶ ወደ እኩል የንግድ እና የጥቅም አጋርነት መሸጋገር አለበት። ኢትዮጵያም በብሪክስ (BRICS) በኩል የምታደርገውን የአጋርነት ብዝሃነት አሜሪካ እንደ ስጋት ሳይሆን እንደ ነባራዊ ሀቅ እንደምትመለከተው ገልጸዋል።
በመጨረሻም፣ በቀጠናው እየታዩ ያሉ ለውጦች—ከእስራኤል እውቅና እስከ ትራምፕ የንግድ ፖሊሲ—ኢትዮጵያ በዲፕሎማሲው ረገድ እጅግ ብልህና ስትራቴጂካዊ መሆን ያለባት ወቅት ላይ መሆኗን አምባሳደሩ አስምረውበታል።

11 months ago
ብሔራዊ ጥቅም
(የሀብታሙ ደባሱ የግል ሀሳብ)
#ethiopia | የአለምአቀፍ ግንኙነት እና ዲፕሎማሲ ንድፍ አውጭ በመባል በዓለም ደረጃ ስሙ የናኝው ሄንሪ ኪሲንጀር (Henry Kissinger) በተለያየ ጊዜያት ሀገር እና ብሔራዊ ጥቅምን በተመለከተ ያስቀመጣቸውን ትንታኔዎች መሰረት በማድረግ ግንዛቤን ለማዳበር ይረዳ ዘንድ እሳቤዎቹን ለማካፈል እሞክራለሁ።ይህ አንጋፋ ዲፕሎማት በዲፕሎማሲ ላይ ያለው አመለካከት በዓለም አቀፍ ግንኙነት ውስጥ እጅግ ተፅዕኖ ፈጣሪ ከሆኑ ጽንሰ-ሐሳቦች አንዱ ነው።ብሔራዊ ጥቅምን በተመለከተ የእሱ አቋም "እውነታዊነት" (Realism) ከሚባለው አስተሳሰብ የሚመነጭ ሲሆን፣ ዋና ትኩረቱ በብሔራዊ ጥቅም እና በስልጣን ሚዛን ላይ ነው።
🔴."እውነታዊነት" (Realpolitik- የኃይል ፖለቲካ):-ኪሲንጀር የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ በዋነኛነት በሀገራት ጥቅም (National Interest) መመራት እንዳለበት ያምናል-ከሞራል፣ከርዕዮተ ዓለም ወይም ከውስጥ ፖለቲካዊ ጉዳዮች በላይ ዲፕሎማሲ የሀገራትን ብሔራዊ ጥቅም ለመጠበቅና ለማራመድ የሚደረግ ተግባራዊና ስልታዊ ውይይት ነው። የሁለትዮሽ ድርድሮች እና ጥምረቶች (alliances) የሚፈጠሩት በጋራ እሴቶች ሳይሆን በጋራ ስጋቶች እና ጥቅሞች ላይ ተመስርተው ነው።
🔴.የስልጣን ሚዛን (Balance of Power):-ኪሲንጀር የዓለም አቀፍ ሥርዓት መረጋጋት (Stability) የሚረጋገጠው በስልጣን ሚዛን እንደሆነ አጥብቆ ያምናል።ዲፕሎማሲያዊ ሚና ዲፕሎማሲ በአንድ ሀገር የበላይነት እንዳይፈጠር የኃይል ክፍፍሉን በተከታታይ "የማስተካከል"ጥበብ ነው።ኃይለኛ የሆኑ ሀገራትን (Great Powers) በመካከላቸው የጥቅም ትስስር እንዲኖር በማድረግ ጦርነትን መከላከል እና ዓለም አቀፉን ሥርዓት ማረጋጋት እንደሆነ ይናገራል ።
🔴.የሕጋዊነት ጽንሰ-ሐሳብ (Legitimacy):-በኪሲንጀር አመለካከት፣ የዓለም አቀፍ ሥርዓት ሕጋዊነት ማለት ሁሉም ዋና ዋና ተዋናዮች (ሀገራት) አሁን ያለውን የሥርዓት አሠራር እና የወሰን መስመሮችን የሚቀበሉበት ሁኔታ ነው።ዲፕሎማሲ የሀገራትን ፍላጎት ሁሉ የሚያረካ ሳይሆን፣ ሁሉም ተዋናይ ምንም እንኳ ባይወደውም ከሥርዓቱ መውጣት የማይፈልግበትን የጋራ የመግባቢያ መሬት መፍጠር ነው።
🔴በታሪክ የተረጋገጠ ብሔራዊ ጥቅም:-ኪሲንጀር በዲፕሎማሲ ታሪክ ላይ ከፍተኛ ግንዛቤ ያለው ሲሆን፣ የዘመናዊ ዲፕሎማሲ መሠረት የተጣለው በ17ኛው ክፍለ ዘመን በካርዲናል ሪሼልዮ (Cardinal Richelieu) እና በ19ኛው ክፍለ ዘመን በኦስትሪያው ልዑል ሜተርኒች (Prince Metternich) መሆኑን ይጠቅሳል።
✍️እንደ መውጫ⁉️
በተግባር፣የኪሲንጀር ዲፕሎማሲ በታሪክ ውስጥ በሁለት ዋና ዋና ተግባራት ይታወቃል ከቻይና ጋር ያለውን ግንኙነት መክፈት (Opening China)በ1970ዎቹ መጀመሪያ ላይ ከአሜሪካ ጠላት ከነበረችው ከኮሙኒስት ቻይና ጋር በድብቅ ድርድር በመጀመር፣ ለሶቭየት ህብረት ምላሽ የሚሆን ስልታዊ "ትሪያንግል" ፈጠሯል።
የሸትል ዲፕሎማሲ (Shuttle Diplomacy) በ1973 የዮም ኪፑር ጦርነት (Yom Kippur War) በኋላ በእስራኤል እና በአረብ ሀገራት መሪዎች መካከል በተደጋጋሚ በመመላለስ ግጭቶችን ለመፍታት የተጠቀመበት ዘዴ ልዩ ነበር
በአጭሩ፣ ኪሲንጀር ዲፕሎማሲን እና ብሔራዊ ጥቅምን ጉዳይ የሚያየው የኃይል ፖለቲካ መሳሪያ አድርጎ ነው ሀገራት ጦርነት ሳይገቡ ጥቅማቸውን እንዲያስጠብቁ እና በዓለም አቀፉ ሥርዓት ውስጥ የሚመጣውን ለውጥ በተግባራዊና ስልታዊ መንገድ እንዲያስተዳድሩ የሚያስችል ጥበብ ነው።
ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅም መሳካት የድርሻዬን እወጣለሁ !
#ethiopia
ለበለጠ ወዳጅነት የፃሃፊውን የኤክስ(X) እና የፌስቡክ ገፅ ይከታተሉ :-
🔗የኤክስ(X)ገፅ:-https://x.com/HDebasu?t=eR...
🔗የፌስቡክ:-https://www.facebook.com/s...

በኬንያ በአውሮፕላን አደጋ የ12 ሰዎች ህይወት አለፈ
#ethiopia | ቱሪስቶችን ብቻ ጭኖ የነበረው አውሮፕላን ከድዪዣኒ ወደ ኪችዋ ሲጓዝ ቴምቦ ሪዞርት አጠገብ መከስከሱን የኬንያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን (KCCA) አስታውቋል።
ባለስልጣኑ ቱሪስቶቹ የየት ሀገር ዜጋ እንደሆኑ እስካሁን ማወቅ እንዳልተቻለ ገልጿል።
በአደጋው ዙሪያ ምርመራ መጀመሩን አስታውቋል። #legit #thiqaheth

12 months ago
ኢትዮጵያ በፈጣን እድገት ላይ ነች - IMF
#ethiopia | IMF ኢትዮጵያን ጨምሮ አምስት የአፍሪካ ሀገራትን ኢኮኖሚያቸው በፍጥነት እያደገ ከመጣ ሀገራት ዝርዝር አካተተ።
አለማቀፍ የገንዘብ ተቋም (IMF) በተቋሙ የኢኮኖሚ ባለሙያዎች ያስጠናውን ሪፖርት ይፋ አድርጓል ተብሏል።
በዚሁ መሰረት ኢትዮጵያ፣ ቤኒን፣ ኮትዲቫር፣ ሩዋንዳ እና ኡጋንዳ ኢኮኖሚያዊ እድገታቸው በፍጥነት እያደገ መምጣቱን ጠቁሟል።
በዚህ የጥናት ሪፖርቱ ካሁን በፊት በግንባር ቀደምትነት የሚጠቅሳትን ናይጄሪያን አላካተተም ተብሏል። #legit
#thiqah

1 year ago
የሕዳሴው ግድብ ተስፋዎች
#ethiopia | የሕዳሴ ግድብ መጠናቀቅ በሚከተሉት አራት ነጥቦች ላይ ተስፋ ይዞ የመጣል ብዬ አስባለሁ። እነዚህም ሳይንሳዊ እሳቤ፥ ራስን መቻል፥ የጋራ ተጠቃሚነት እና በተፋሰስ አገሮች መተማመን ናቸው። በአጭሩ እንደሚከተለው አቀርባለሁ።
1. ሳይንሳዊ እሳቤ
‘Nullius in verba’ ይላል በ1660ዎቹ የተቋቋመው የሮያል ማሕበር መርሕ/moto/ ። ይህ ሀረግ ከላቲን ቋንቋ የመጣ ሲሆን ‘ሰው የሚነግርህን ምንም ጉዳይ ላይ ቢሆን ሳትሞክር አትስማ፤ አትውሰድ ወይም አትቀብል’ የሚል ትርጓሜ ይሰጣል። ይህም የአውሮፓ የህዳሴ ዘመን መመሪያ ተደርጎ ይወሰድ ነበር።
የሕዳሴ ግድብ ሥራን ገና ከጅምሩ ለማየት እድሉን ካገኙ ሰዎች አንዱ ነኝ። ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ከተወጣጣ አንድ ቡድን ጋር የሕዳሴ ግድቡን የሥራ ሁኔታ ለመገምገምና ለመማር በተደጋጋሚ ጉብኝት አድርጌያለሁ። ስለዚህ ከመስማት ባለፈ ካለኝ ልምድ ጥቂት ማለት እችላለሁ:: በቀዳሚው ጉብኝቴ አንድ የማይረሳኝ ገጠመኝ አለኝ:: በሚያዚያ ወር መጀመሪያ 2006ዓ.ም. ላይ ባድረግነው ጉብኝት የሥራውን ሁኔታ ከጉባ ተራራ ላይ ሆነን የግድቡን ግንባታ ቁልቁል ተመለከትን። ከሩቅ ሆኖ ሲያዩት የግድቡ ሥራ በጣም ትንሽ ይመስል ነበር። ከዚያም በቅርበት የሥራውን ሁኔታ እንመልከት ብለን የግድቡ ሥር ደረስን። ይህን ግዜ ግድቡ ሳይሆን እኔ ትንሽ እንደሆንኩ ተሰማኝ።
ልክ እንደዚሁ የሕዳሴ ግድብ ትልቅነትና ስፋት ብዙ ነገርን ያሳንሳል። አሁን ለምሳሌ ግድቡን ለመስራት ጥቅም ላይ የዋለው የኮንክሪት መጠን 10ሚልዮን ሜትሪክ ቶን አካባቢ ይገመታል። በቀጥታ ለማወዳደር ቢያስቸግርም እስከዛሬ ድረስ በአዲስ አበባ ከተማ የኮንደሚኒየም ግንባታ የወሰደውን የኮንክሪት መጠን እጥፍ ሊሆን ይችላል። ከሚይዘው የውሃ መጠን አንፃር የህዳሴ ግድብ 74 ቢልዮን ሜትር ኩብ ውሃ ያጠራቅማል። አንድ ሰው ለመጠጥ በአማካኝ በቀን እስከ አምስት ሌትር ቢጠቀም ይህ ውሃ የዓለምን ሕዝብ ለአምስት ዓመታት ቀጥ አርጎ ሊይዝ ይችላል። ውሃው የማይሠርግ፣ የማይፈስ፣ እና የማይተን ቢሆን የኢትዮጵያን ሕዝብ እስከ ሦስት መቶ ዓመት ድርስ የመጠጥ ውሃ ፍጆታ ሊሸፍን ይችላል። ውሃ የሚተኛበትን የቆዳ ስፋት ብንመለከት ከ1800 ካሬ ኪሎሜትር በላይ ይሆናል። ይህም ማለት የአዲስ አበባ ከተማን የቆዳ ስፋት ከሦስት እጥፍ በላይ ያክላል። የእኔዋ መዘዞ ወይም የክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር የልጅነት ስፍራ የሆነችው በሻሻ እንደ ብዙዎቹ አነስተኛ ከተሞች ስፋታቸው አንድ ካሬ ኪሎሜትር እንኳ አይሞላም። ይህ ማለት የሕዳሴው ግድብ የሚያርፍበት ቦታ ሁለት ሽህ በሻሻን ወይም ሁለት ሽህ መዘዞን የሚያክል ቦታ ይይዛል ማለት ነው።
የግድቡን ሥራ ‘በርቀት ስመለከተው ያነስብኝ’ እና ‘ስቀርበው ያሳነሰኝን’ ጉዳይ ሳስብ እንኳንስ ያላዩትን ነገር ቀርቶ በዓይን የተመለከቱትንም ቢሆን መጀመሪያ የቆሙበትን ቦታ ግንዛቤ ውስጥ ማስገባት ከበዙ ስተት ሊያተርፍ ይችላል። ይህም የሰሙትንም ሆነ ያዩትን ነገር እንዳለ ከመውሰድና ከመቀበል ለሳይንሳዊ ልኬት ቅድሚያ መስጠት ይበልጥ ከእውነታው ያቀራርባል የሚለውን ትምህርቴን በተግባር እንዳረጋግጥ ረድቶኛል።
የሕዳሴው ግድብ መገባደድ የሳይንሳዊ ልኬት እና የሳይንሳዊ እሳቤ ወጤት ነው። ሳይንሳዊ እሳቤ እንደዚህ ጨዋታ ቀያሪ ለውጥ ያመጣል። የግድቡ ዳር መድረስ በራሱ የሳይንሳዊ እሳቤ እንዲስፋፋ ሰፊ በር ይከፍታል የሚል እምነት አለኝ። ይህም የሕዳሴ ግድብን እንደስሙ የኢትዮጵያ የሕዳሴ ዘመን ፈር ቀዳጅ አድርጎ መውሰድ ይቻላል።
2. እራስን መቻል
ዓባይ ለዘመናት የኢትዮጵያውያን ጥያቄ ነበር። በተመዘገበው ታሪካችን ከዛሬ 800 ዓመት ጀምሮ ዓባይን የመገደብ ፍላጎት እንደነበር ይጠቀሳል። እንደ ዐፄ ይስሐቅ ያሉት ነገስታት ከአውሮፓ ባለሞያዎች ለማስመጣት እና ለማሰራት ማሰባቸው ይወሳል። ሆኖም ንጉሱ ሀሳባቸውን እውን ላለማድረጋቸው ሁለት ምክንያቶች ይጠቀሳሉ። የመጀመሪያው ምክንያት የራስ የሆነ ባለሞያና የቴክኖሎጂ አቅም እጥረት ነው። በውስጥና በውጭ ፋታ የማይሰጥ ጦርነት እንደ ሁለተኛ ምክንያት ይቀርባል።
ሆኖም ኢቴረም የሚባለውን የምናባዊ ገገንዘብ/cryptocurrecy/ ተቋም መስራች ከሆኑት አንዱ ቪታሊክ ቡተሪን ‘The most important scares resources is legitimacy’ በሚል ርዕስ በጻፈው ጽሁፍ እንዳስቀመጠው በህዝብ ትብብር የሚሰራ ሥራ ትልቁ ጉዳይ ሕዝቡ ከሚያበረክተው አስተዋጽኦ ሕጋዊነት እና ባለቤትነት ጋር ይያያዛል። የሕዝብ መዋጮን በታማኝነት ወደ ሥራ መለወጥ ሌላ ትልቅ ጉዳይ ነው።
እንደ ዩኒቨርስቲ መምህርነቴ ለሕዳሴው ግድብ በሁለት ወር ደመወዜ ቦንድ ገዝቻለሁ። ብዙ የመንግስት ሰራተኛ እንዲዚሁ ካለው ገቢ ቦንድ ገዝቷል። የግል ዘርፉም በሕዳሴ ግድብ ገቢ ማሰባሰቢያ ሂደት ውስጥ በአንድም ሆነ በሌላ መልክ አስተዋጽኦ አበርክቷል። በውጭ የሚኖር ኢትዮጵያዊ እና ትውልደ ኢትዮጵያዊም ተሳትፎ በቀላሉ የሚታይ አይደለም። ከገቢ የማሰባሰብ አንጻር ሲታይ የሕዳሴው ግድብ በሕዝብ የተሰራ ሀውልት ነው ማለት ይቻላል። በሂደቱ ሁሉም ኢትዮጵያዊ የግድቡ ባለቤት ሆኗል። በሕዳሴው ግድብ ውስጥ ሁሉም የራሱን ፊት የሚያይ ይመስለኛል::
በሌላ በኩል የግድቡ ዳር መድረስ ከሕዝቡ የተሰበሰብው ሀብት ለታቀደለት ግብ ለመዋሉ ማሳያ ሆኖ ይኖራል። የመዋጮው ማረፊያ በታላቅ ስኬት ግዘፍ ነስቶ መታየት እና የአጠቃቀሙ ብሩህ ተስፋ ግድቡን የዘመናችን በሀገር የመተማመን ዐቢይ ስራ ያደርገዋ። በዚህም የህዳሴ ግድብ ሥራ ከሚሰጠው ጠቀሜታ በላይ ማህበረሰብን ትኩረት ላደረገ የፈጠራ ሥራ ትልቅ ምልክት ይሆናል። ኢትዮጵያዊያን እና ኢትዮጵያ በሀሳብ፣ በእውቀት፣ በትጋት እና በአመራር ታላቅ ክዋኔ እንደሚፈፅሙ የተማመኑበት ህያው ቅርስ ሆኖ ይኖራል በዩ ተሰፋ አደርጋለሁ።
3. የጋራ ተጠቃሚነት
ፓል ሮዳን የተባለ የምጣኔ ሀብት ባለሙያ ‘Big push’ የሚለውን ንድፈ ሃሳብ በ1940ዎቹ ካቀረበ በኋላ ለአንድ አገር የኢንዱስትሪ እድገት ከፍተኛ የሆነ ግፊት እንደሚያስፈልግ አስቀምጧል። በተግባርም ተሞክሮ በፍጥነት በማደግ ላይ ባሉ በኢስያ አገሮች ውጤት አስመዝግቧል ።
በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ተቋማት በተለይም በአምራች ዘርፉ ውስጥ የተሰማሩ ኢንዱስትሪዎች በአማካኝ ያላቸውን የማምረት አቅም 50 በመቶ እንኳን እንደማይጠቀሙ በተለያየ ጊዜ የተሰሩ ጥናቶች ያሳያሉ። በዚህ ዓመት መጨረሻ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ውስጥ የሚሰሩ ተቋማት ያለባቸውን ችግር የሚዳስስ ጥናት ውስጥ ተሳታፊ ነብርኩ። ጥናቱ እንደሚያሳየው ከሆነ ለ80 በመቶው የአምራች ኢንዱስትሪው የመብራት ኃይ መቆራረጥ የምርት ሥራን የሚገታ ምክንያት ተደርጎ ይቀመጣል። ለዚህ የመብራት ኃይል አቅርቦት ውስንነት ቀዳሚውን ቦታ ይይዛል።
የሕዳሴው ግድብ የኢትዮጵያን የኤሌክትሪክ ኃይል የማምንጨት አቅም በእጥፍ ይጨምረዋል። በትንሹ የመብራት አቅርቦትና የኢንዱስትሪ እድገትን በትዩዩ ብናስቀምጥ እንኳን የአምራች ዘርፉ እስካሁን የገጠመውን ችግር በመፍታት አሁን ካልበት ከ6 በመቶ ብዙም ያልዘለለው የምርት መጠን በእጥፍ ቢያድግ የኢትዮጵያ የአምራች ዘርፍ ይዘት ከሳሃራ በታች ካሉ አገሮች አማካኝ ሊያልፍ ይችላል። የአምራች ዘርፍ እድገት በራሱ የሌሎች ዘርፎችን ማለትም የግናባት፥ የግብርና፥ እና የአገልግሎት ዘርፎችን እድገት በማቀጣጠል የእትዮጵያን እድገት ሊያረጋግጥ የሚችልበት እድል ይዞ ይመጣል ብዬ ትልቅ ተስፋ አለኝ።
እዚህ ላይ አንደ የቻይና ታሪክ ብጠቅስ ደስ ይለኛል። ከክርስቶስ ልደት ከአመስት መቶ ዓመት በፊት ይሆናል። በተራራ በተከበበችው በቸንዱ ከተማ አካባቢ ትልቅ ወንዝ ነበር። ይህን ወንዝ በወቅቱ የነበሩት ንጉስ መጀመሪያ ለሁለት ከፈሉት። ቀጥለውም እያንዳንዱን የተከፈለ ወንዝ መልሰው ለሁለት እየከፈሉ በሂደት የወንዙ ኃይል በመቀነሰ ውሃውን ለመሰኖ ሥራ ማዋል ችለዋል። ከተራራ ላይ ተሰብስቦ ትልቅ ኃይል የፈጠረውን ወንዝ በብልኀት በመያዝ ትልቅ የመስኖ ሥራ ፈጥረዋል። ይህ ለዘመናዊ የመስኖ ሥራ አንድ ምሳሌ ሆኖ ኖሯል። የህዳሴ ግድብም ለዘመናት አሻፈረኝ ብሎ የኖረውን የዓባይ ወንዝ የውሃውን ፍሰት ለመብራት ኃይል ማመንጫ በመጠቀም በአጠቃላይ ለምጣኔ ሀብት እድገት ከሚያበረክተው አሰተዋጽኦ በተጨማሪ ለእያንዳንዱ ቤተሰብ በተለያየ መንገድ ይዳረሳል። ከዚህ አንፃር መጀመሪያ የሚጠቀሰው የኤሌትሪክ መብራት ተደራሽነት ነው። ተደራሽነቱ ገና ከ50 በመቶ ብዙም ባልተሻገረበት አገር ውስጥ ከህዳሴው ግድብ የሚመነጨው ኃይል ለኢንዱስትሪ እና ለሌሎች አገልገሎት ባይውል በኢትዮጵያ ያሉ ቤቶች ሁሉ ውስጥ በርካታ አንፖሎችን የማብራት አቅም ይፈጥራል። ልክ እንደዚሁ በአንድም ሆነ በሌላ መልኩ በሕዳሴው ግድብ የሚመነጨው የመብራት ኃይል የእህል ወፍጮ እንዲስፋፋ በማድረግ የእናቶቸን ድካም በእጅጉ ይቀንሳል።
ይህን ኃይሉን በመረዳት ይመስላል የአማርኛ መዛግብተ ቃላቶቻችን ዐባይ የሚለውን ቃል ዋና፣ ታላቅ፣ ቀዳሚ፣ አንጋፋ፣ አባት እና ከመሳሰሉት ቃላቶች ጋር አያይዘው ይተርጉሙታል:: በብዙ የሀገራችን ባህሎች ዋና፣ ታላቅ፣ ቀዳሚ፣ አንጋፋ ወይም አባት የሆነ ሁሉ ሰብሳቢ አሰባሳቢ ነው:: ዐባይም ከጥንት ከስሪቱ ከሁሉም አካባቢ ውሀ ሰብስቦ መፈጠሩ ለስሙ የመጠነ ቢያሰኘውም ውሀ ለሰጡት ኢትዮጵያውያን ጥቅም ሳይሰጥ በመፍሰሱ የአሰባሳቢነት ፀጋውን አጥቶ ቆይቷል:: ዛሬ ሁሉም ኢትዮጵያዊያን በሰሩለት ግድብ መልሶ የስሙን ፀጋ ለብሷል:: ሰብሳቢ አሰባሳቢ ዐባይ ዐባይ ሆኑዋል:: ለጋራ ተጠቃሚነት እና ኅብረት ቁሳዊም፣ ተግባራዊም፣ ትርክታዊም፣ መንፈሳዊም፣ ሥነልቦናዊም ታዛ ሆኑዋል።
4. የተፋሰሱ አገሮችን መተማመን
የዐባይ ወንዝ በዓለም ረጅሙ ወንዝ እንደመሆኑ ኢትዮጵያን ጨምሮ አስራ አንድ አገሮችን እንደሚያቋርጥ ይታወቃል። የተፋሰሱ አገሮች በተፈጥሯዊ የመሬት አቀማመጥ፥ በጅኦ ፖለቲካ፥ በቴክኖሎጅ እድገት ደረጃ ወይም በሌላ ምክንያት አንዱ ከአንዱ የተለያየ ቢሆንም ወንዙን ለመጠቀም ግን ሁሉም ይፈልጋል። ሆኖም ለረጅም ዘመናት የታችኛው ተፋሰስ አገሮች ከላይኛው ተፋሰስ አገሮች ይበልጥ ተጠቃሚ ሆነው እንደዘለቁ ግልጽ ነው።
የሕዳሴ ግድብን ሐሳብ ከማፍለቅ ጀምሮ እዚህ እስኪደረስ ኢትዮጵያ ብዙ ሂደቶችን አልፋለች። ዐፄ ኃይለሥላሴ የመነሻ ዲዛይን አሠርተው ነበር። የሚያስፈልገውን ገንዘብ ባለማግኘታቸው ወደ ግንባታ መግባት ሳይችሉ ቀርተዋል። የሚችል ትውልድ ሲመጣ ይሠራዋል ብለው ተናግረው አለፉ። በጠ/ሚ መለስ ጊዜ ወደ ሥራ መግባት ቻለ። በለውጡ ጊዜ ደግሞ በመቆም ላይ የነበረው የግድቡ ፕሮጀክት እንደ ገና ነፍስ ዘርቶ ወደ ፍጻሜው ደርሷል። ከተጀመረ ጀምሮ ከየትኛውም የዓለም የውኃ አካል በተለይ ብዙ የውጭ ጫና ደርሷል። የጸጥታው ምክር ቤት በተደጋጋሚ አጀንዳ ሆኖ ቀርቧል። ይህም የኢትዮጵያ ሕዝብና መንግስት በሕዳሴ ግድብ ምክንያት ምን ያክል ከባድ ጫና ውስጥ እንዳለፉ አንድ ማሳያ ነው።
ይህን ሁሉ ፈተና ተቋቁሞ የሕዳሴ ግድብ መገባደድ ከኢትዮጵያ አልፎ በተፋሰሱ አጠቃቀም ላይ በመጠኑም ቢሆን የለውጥ ብርሃን ፈንጥቋል። ማንም ወንዙን መጠቀም አይችልም ከሚል እሳቤ ወጥቶ ‘የኢትዮጵያ መንግስት አሳሪ ውል/binding contract/ ይግባ፤ ተፈጥሯዊ የወንዙ ውሃ ፍሰት እንዳይቀንስ መተማመኒያ/guaranty/ ይስጠን’ ወደሚሉ ጥያቄዎች ተለውጧል። እነዚህ ጥያቄዎች በራሳቸው በቀላሉ የሚታዩ ባይሆኑም የአንዱ ጥቅም ሌላውን በማይጎዳ መልኩ የጋራ ተጠቃሚነትን ማጎልበት እንደሚያስፈልግ በተፋሰሱ አገሮች መተማመንን በመፈጠር ላይ ይገኛል።
የቴክኖሎጅ ተደራሽነት ባደገበት በዚህ ዘመን የዓባይ ተፋሰስ አገሮች ከውድድርና ግጭት ወጥተው ሁሉን አቀፍ የሆነ የትብብር ማዕቀፍ በመንደፍ የሁሉንም አገሮች ተጠቃሚነት ማረጋገጥ የሚቻልበት እድል ሰፊ ይመስለኛል።
በጥቅሉ የሕዳሴ ግድብ መጠናቀቅ ከላይ ባነሳኋቸው ጉዳዮች ማለትም የሳይንሳዊ እሳቤ መስፋፋት፥ ሥራዎችን መከወን የሚያስችል የራስ አቅም መዳበር፥ የጋራ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ እና በተፋሰሱ አገሮች መካከል የሚፈጠር መተማመን ወደፊት ከሕዳሴው ግድብ የላቀ ሥራ ለመስራት ትልቅ ተስፋ ይሰጣሉ የሚል እምነት አለኝ። የተፈጠረውን መልካም እድል በሚገባ መጠቀም ደግሞ በዚህ ትውልድ እጅ ያለ አደራ ይመስለኛል።
አመሰግናለሁ!
(የህዳሴው ግድብ ላይ ከሁለት ዓመት በፊት የቀረበ)
ምስጋና ለNebiyou Baye
ፎቶ ከWondwossen Mulugeta
ዶክተር ብርሃኑ በሻህ እንደፃፈው

Sponsored by
Surafel
Comments