Logo
FIDEL POST NEWS
የሕንድ ከፍተኛ ባለሥልጣን በአውሮፕላን አደጋ ሕይወታቸው አለፈ

​የሕንድ በሀብቷ ቀዳሚ የሆነችው የማሃራሽትራ (ግዛት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አጂት ፓዋር ፣ ዛሬ ረቡዕ በደረሰ አሰቃቂ የአውሮፕላን አደጋ ከነበረባቸው 4 ሰዎች ጋር ሕይወታቸው ማለፉ ተረጋግጧል።

​አደጋው የተከሰተው፦ ባለሥልጣኑ ለምርጫ ቅስቀሳ ወደ ትውልድ ቀያቸው በማቅናት ላይ ሳሉ፣ የግል አውሮፕላናቸው ባራማቲ አውሮፕላን ማረፊያ ላይ ለማረፍ ሲሞክር ተከስክሶ እሳት በመነሳቱ ነው።

​ተጎጂዎች፦ በአውሮፕላኑ ውስጥ የነበሩት አምስቱም ሰዎች (ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩን ጨምሮ፣ ሁለት ረዳቶቻቸው እና ሁለት የአውሮፕላኑ ሰራተኞች) በሙሉ ሕይወታቸው አልፏል።

​የአውሮፕላኑ ዓይነት፦ ሊርጄት 45 የተሰኘ ሲሆን፣ የኒው ዴልሂው "VSR Group" ንብረት እንደሆነ ታውቋል።

​ምክንያት፦ የአደጋው መንስኤ በዝርዝር ባይታወቅም፣ በወቅቱ የነበረው ከባድ ጭጋግ እና ታይነት መቀነስ (Poor visibility) ለክስተቱ መንስኤ ሳይሆን እንዳልቀረ የሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን ጠቁሟል።

​የ66 ዓመቱ አጂት ፓዋር በሕንድ ፖለቲካ ውስጥ ትልቅ ተፅዕኖ የነበራቸውና በማሃራሽትራ ግዛት ለረጅም ጊዜ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርነት ያገለገሉ አንጋፋ መሪ ነበሩ። የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ የተሰማቸውን ጥልቅ ሀዘን ገልጸዋል።
6 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.