✈️ ቦይንግ በኢትዮጵያ በተከሰከሰው አውሮፕላን አደጋ ለሞተ ሰው ቤተሰቦች 28 ሚሊዮን ዶላር እንዲከፍል ታዘዘ
#ethiopia | ፍርድ ቤቱ በብይኑ የካሳ ክፍያው እንዲፈጸም ያዘዘው በአደጋው ለሞተችወ የተባበሩት መንግስታት የአካባቢ ጥበቃ ተሟጋች ሺካ ጋርግ ቤተሰቦች ነው።
በአሜሪካ ፣ ቺካጎ የሚገኝ አንድ የፌዴራል ፍርድ ቤት የአውሮፕላን አምራቹን ቦይንግ የ737 ማክስ ጄት አውሮፕላኑ ተከስክሶ ለሞተው የተባበሩት መንግስታት የአካባቢ ጥበቃ ሰራተኛ ቤተሰብ ቢያንስ 28 ሚሊዮን ዶላር ካሳ እንዲከፍል አዟል ሲል ሮይተርስ ዘግቧል።
ይህ ከስድስት አመት በፊት በተከሰተው አደጋ አመት በፊት ኢንዶኔዥያ ውስጥ ሌላ የ737 ማክስ ቦይንግ ተከስክሶ ነበር።
በእነዚህ ሁለት አደጋዎች በድምሩ 346 ሰዎች ሞተዋል።
እነዚህን ሁለት አደጋዎች ተከትሎ በቦይንግ ላይ ብዙ ክሶች ተመስርተዋል።
ከእነዚህ ክሶች ውስጥ ለመጀመሪያው ውሳኔ ረቡዕ ተሰጥቷል። ፍርድ ቤቱ ካሳው በአደጋው ለሞተው የተባበሩት መንግስታት ሰራተኛ ሺካ ጋርግ ቤተሰብ እንዲከፈል አዟል።
የጋርግ ቤተሰብ ጠበቃ እንደተናገሩት፣ ሁለቱ ወገኖች ረቡዕ ጠዋት ስምምነት ላይ ደርሰዋል። በስምምነቱ መሠረት፣ የጋርግ ቤተሰብ በፍርድ ቤቱ ውሳኔ የታዘዘውን ሙሉ መጠን ከ26 በመቶ ወለድ ጋር በመደመር በድምሩ 35.85 ሚሊዮን ዶላር ያገኛሉ።
በቦይንግ ቃል አቀባይ በሰጡት መግለጫ፣ ኩባንያው በሁለቱ የአውሮፕላን አደጋዎች ውስጥ ውድ ሰዎቻቸውን ላጡ ሁሉ ጥልቅ ሀዘኑን ይገልጻል።
በመግለጫው ላይ "አብዛኛዎቹን እነዚህን የካሳ ጥያቄዎች በሽምግልና ብንፈታም፣ ቤተሰቦቹ አሁንም ለካሳ የፍርድ ቤት ክስ የማቅረብ መብት አላቸው፣ እኛም ያንን መብት እናከብራለን" ብለዋል።
የጋርግ ቤተሰብን የወከሉት ጠበቆች ሻኒን ስፔክተር እና ኤልዛቤት ክራውፎርድ በሰጡት መግለጫ "ይህ ውሳኔ ቦይንግ ለሰራው ጥፋት በይፋ ተጠያቂ መሆኑን ያረጋግጣል" ብለዋል።
የሟች ጋርግ ጠበቆች እንደተናገሩት፣ የ32 አመቱ ሺካ ጋርግ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራ 302 ተሳፋሪ ነበረች። በረራው ከኢትዮጵያ አዲስ አበባ ወደ ናይሮቢ፣ ኬንያ በመጓዝ ላይ የነበረ ቢሆንም ከተነሳ በደቂቃዎች ውስጥ ተከስክሷል።
ክሱ የ737 ማክስ አውሮፕላን ንድፉ የተሳሳተ ነው። ቦይንግ ተሳፋሪዎችንና ስለ አደጋው ማስጠንቀቅ አልቻለም የሚል ክስ ይዟል ሲል ፊደል ፖስት ዘግቧል።

9 months ago