4 months ago
"ዋሽንግተን የቴህራንን ገንዘብ ለመካከለኛው ምሥራቅ አጋሮቿ ለማከፋፈል እያጤነችው" - ስኮት ባሰንት
#ethiopia | አሜሪካ ኢራን የታገደባትን ገንዘብ የገልፍ ሀገራትን መልሶ ለመገንባት ልትጠቀመው ነው ተባለ።
የአሜሪካ ገንዘብ ቢሮ ኃላፊ ስኮት ባሰንት "ዋሽንግተን የቴህራንን ገንዘብ ለመካከለኛው ምሥራቅ አጋሮቿ ለማከፋፈል እያጤነችው" ሲሉ ጠቁመዋል።
ገንዘቡ "በኢራን የድሮን እና የሚሳዔል ጥቃት የወደሙ መሠረተ ልማቶችን እና ጉዳቶችን መልሶ ለመጠገን ይውላል" ብለዋል።
ባሰንት "አሜሪካ ይህንን እርምጃ ለመውሰድ የሚያስችላት የአተገባበር እቅድ (proposal) ቀርቧል" ሲሉ ተናግረዋል።
"ፕሮፖዛሉ አሁን የደረሰውን ብቻ ሳይሆን ወደፊት ሊፈጸም የሚችል ጥቃትን ያካተተ ነው" ብለዋል።
የባሰንት አስተያየት የተሰማው ኢራን በዩናይትድስቴትስ የተያዘባት ገንዘብ እንዲለቀቅ እንደምትፈልግ ከገለፀች በኋላ ነው።
የኢራን ጠቅላይ መሪ ሞጅታባ ኮሚኒ አማካሪ ሞህሰን ረዛይ በትናንትናው እለት "የታገደብን 24 ቢሊዮን ዶላር ሳይለቀቅ አንደራደርም" ብለው ነበር።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #timeskuwait #thiqaheth #usa

5 months ago
የእስራኤል ፓርላማ ተበተነ
#ethiopia | ፓርላማው ራሱን ለማፍረስ የሚፈቅደውን አዋጅ ማጽደቁን አስታውቋል። ይህ ውሳኔ በእስራኤል ጠቅላላ ምርጫ እንዲካሄድ የሚያስገድድ ነው ተብሏል።
ይህም የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ቢኒያም ኔታንያሁን በምርጫው የማሸነፋቸውን እድል ያጠበዋል የሚል ስጋት አሳድሯል።
የእስራኤል ህግ አውጭዎች 120 መቀመጫ ያለው የሀገሪቱ ፓርላማ እንደ አዲስ እንዲዋቀር ያልተለመደ ውሳኔ ማሳለፋቸው አነጋጋሪ ሆኗል።
ውሳኔው ከሳምንታት በኋላ የመጨረሻውን እውቅና ያገኛል ተብሎ ይጠበቃል። ጠቅላላ ምርጫ የሚደረግበት ቀንም በቀጣይ ይገለጻል ተብሏል።
እስራኤል የመጨረሻውን ምርጫ ያደረገችው በ2022 ሲሆን፣ ቀጣዩ ምርጫ በሀማስ ጥቃት ምክንያት ተራዝሞ ቆይቷል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #reuters #thiqaheth

ዩክሬን ድሮኔ መንገድ ስቶ ኢስቶኒያ በመግባቱ ይቅታ ጠይቃለሁ አለች
#ethiopia | የዩክሬን የጦር ሰው አልባ አውሮፕላን (ድሮን) በስህተት የኢስቶኒያን የአየር ክልል ጥሶ መግባቱን የሰሜን አትላንቲክ ቃል ኪዳን ድርጅት (ኔቶ) ያስታወቀ ሲሆን፥ ድሮኑም በኔቶ የፀረ-አየር መከላከያ መትቶ መጣሉ ተገልጿል።
ይህን ተከትሎ የዩክሬን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሄሮይሂ ትይኪ በኤክስ (X) ማህበራዊ ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት “ኢስቶኒያን ይቅርታ እንጠይቃለን” በማለት ይፋዊ ይቅርታ ጠይቀዋል።
ነገር ግን ለተፈጠረው የቴክኒክ ስህተት ሩሲያን ተጠያቂ ያደረጉት ሚኒስትሩ፥ “ሞስኮ ሆን ብላ የድሮኑን አቅጣጫ እንዲቀይር አድርጋለች” ሲሉ ክስ ሰንዝረዋል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu
#ዩክሬን #ኢስቶኒያ #ኔቶ #ሩሲያ #የአየር_ክልል_ጥሰት #meduza #thiqaheth

"ሀሰን ሼክ አደገኛ ቀይ መስመር ላይ ነው" - አፍያሬ እልሚ
#ethiopia | የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ መሀመድ የስልጣን ዘመናቸውን አራዘሙ።
ፕሬዝዳንቱ ለአንድ አመት ያክል በስልጣን እንደሚቆዩ አስታውቀዋል።
ይህን ተከትሎ አፍያሬ እልሚ የተባሉ የሶማሊያ ፖለቲካ ተንታኝ፣ "የፕሬዝዳንቱ እርምጃ የሶማሊያን የምርጫ ስርዓት ሊያበላሽ ይችላል" ሲሉ ተቃውመዋል።
የፖለቲካ ምሁሩ፣ "ሀሰን ሼክ አደገኛ ቀይ መስመር ላይ ነው" ብለዋቸዋል። ድርጊቱንም፣ "የሀገሪቱን ህገ መንግስት አደጋ ላይ ይጥላል" ብለውታል።
"ወቅቱን የጠበቀ ምርጫ አለመካሄድ ዋጋ ያስከፍላል" ያሉት ምሁሩ "የሶማሊያ የእርስበርስ ጦርነት ምክንያት የነበረው የስልጣን ጉጉት ነው" ብለዋል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን) #getutemesgen #getu
#somaliguardian #thiqaheth

Sponsored by
Surafel
5 months ago
የዓለም ጤና ድርጅት በኢቦላ ቫይረስ ምክንያት ዓለማቀፍ የጤና አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አወጀ
#ethiopia | የዓለም ጤና ድርጅት (WHO) በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ እና በኡጋንዳ በከፍተኛ ሁኔታ እያገረሸ የመጣውን የኢቦላ ቫይረስ ስርጭት ተከትሎ፣ ወረርሽኙን ይፋዊ የዓለማቀፍ የህዝብ ጤና ስጋት አድርጎ አውጇል።
የድርጅቱ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቴዎድሮስ አድሃኖም በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው (ኤክስ) ባስተላለፉት መረጃ፣ እስካሁን ባለው ጊዜ ውስጥ በቫይረሱ ሳቢያ የ 88 ሰዎች ህይወት ማለፉንና 300 ያህል ሰዎች ደግሞ በበሽታው መያዛቸውን አረጋግጠዋል።
ዋና ዳይሬክተሩ አክለውም የኢቦላ ቫይረስ ልክ እንደ ኮቪድ-19 ወረርሽኝ ሁሉ የመቀጣጠልና በከፍተኛ ፍጥነት የመስፋፋት አቅም እንዳለው በማስገንዘብ፣ የከፋ ጉዳት ሳይደርስ አስቸኳይና ጥብቅ የሆኑ የመከላከል ስራዎች በአለም አቀፍ ደረጃ እንዲተገበሩ ጥሪ አቅርበዋል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን) #getutemesgen #getu
#ebolavirus #publichealthemergency #who #drtedros #africahealth #globalhealth #breakingnews #thiqaheth

የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር የዩኤኢ "ድብቅ ጉዞ" ማስተባበያ ተሰጠው
#ethiopia | ጠቅላይ ሚኒስትር ቢኒያም ኔታንያሁ በጦርነቱ ወቅት "በድብቅ" የተባበሩት አረብ ኤምሬትን ጎብኝተዋል መባሉን የአቡዳቢ ባለስልጣናት አስተባብለዋል።
ኔታንያሁ በኢራንና እስራኤል ጦርነት ወደ አቡዳቢ በማቅናት ከፕሬዝዳንት መሀመድ አልናህያን ጋር በጦርነቱ ዙሪያ መክረዋል ተብሏል።
የተባበሩት አረብ ኤምሬት ግን ግልጽ ያልሆነ እና ከህዝብ የተደበቀ ጉብኝት አልተደረገም ብላለች።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን) #getutemesgen #getu #asiaone #thiqaheth

የማሊ ጦር የተቃጣበትን "የሽብር ጥቃት ማክሸፉን" አስታወቀ
#ethiopia | ጦሩ በዋና ከተማዋ ባማኮ እና ሌሎች ከተሞች ሰርጎ ገብ "የአማፂ" ቡድን አባላት ጥቃት አድርሰዋል ብሏል።
ጥቃት አድራሾቹ የባማኮ አየር ማረፊያን ለመቆጣጠር ኢላማ አድርገው እንደነበር ተገልጿል።
"አማፂያኑ" ከአልቃይዳ ጋር ትስስር ያላቸው መሆናቸውን አስታውቋል።
የውጭ ሀገር ኤምባሲዎች በበኩላቸው ዜጎቻቸውን ረጅም ጉዞ ከማድረግ እንዲቆጠቡ አሳስበዋል።
ጦሩ ስለደረሰ ጉዳት የሰጠው ማብራሪያ የለም።
ገለልተኛ ተቋማትም ቢሆኑ ከሽብር ጥቃቱ ጋር በተያያዘ የደረሰ ጉዳት ስለመኖሩ ያወጡት ሪፖርት የለም።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን) #getutemesgen #getu #cbsnews #thiqaheth

ሁለቱ ሀገራት ተደራዳሪዎች ልከዋል?
#ethiopia | ኢራን እና አሜሪካ የልዑካን ቡድናቸውን ወደ ፓኪስታን መላካቸው ተዘግቧል።
ከአሜሪካ በኩል የፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ልዩ መልዕክተኛ የሚመራ፣ ከኢራን በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራግቺ የሚመራ የተደራዳሪ ቡድን ወደ ኢስላማባድ አቅንቷል ተብሏል።
ባሳለፍነው ሰኞ እለት ሊጀመር የታቀደው ሁለተኛው ዙር ድርድር የአሜሪካ ምክትል ፕሬዚዳንት ጄዲ ቫንስ ለመሳተፍ ወደ ፓኪስታን ቢያቀኑም፣ የኢራን ተደራዳሪዎች ባለመገኘታቸው ድርድሩ ሳይካሄድ ቀርቷል።
የኢራኑ መሪ ሞጅታባ ኻሚኒ ግን የኢራን በወቅቱ ተደራዳሪዎች "ወደ ፓኪስታን ማቅናታቸውን" ገልጸው ነበር። ይህ ንግግራቸው ግን መጨረሻው እውነት ሆኖ አልተገኘም።
አሁን ደግሞ የአልጄዚራ ዘገባ እንዳለው ከሆነ፣ ኢራን እና አሜሪካ የልዑካን ቡድናቸውን ወደ ፓኪስታን ልከዋል።
ሁለቱ ሀገራት ከዚህ ቀደም በነበራቸው ውይይት የኑክሌር ምርት ጉዳይ ዋነኛ ማጠንጠኛ ቢሆንም አሁን ደግሞ የሆርሙዝ ሰርጥ የመስተዳደር ኃላፊነት ሌላ አጀንዳ ሆኗል ተብሏል።
በአንፃሩ ፕሬዚዳንት ትራምፕ ለ15 የተደረሰው የተኩስ አቁም ስምምነት ለተጨማሪ ቀናት መራዘሙን ማስታወቃቸው አይዘነጋም።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን) #getutemesgen #getu #aljazeera #thiqaheth

6 months ago
የታይዋን ፕሬዝዳንት የአየር ክልል ተዘግቶባቸው የአፍሪካ ጉዛቸውን ተሰረዘ
#ethiopia | የታይዋኑ ፕሬዝዳንት ላይ ቺንግ ቴ ወደ አፍሪካዊቷ ሀገር ኢስዋቲኒ ለማቅናት አቅደው የነበረ ቢሆንም፣ የአየር ክልል ፍቃድ በማጣታቸው ጉዟቸውን ለመሰረዝ ተገደዋል።
ሲሸልስ፣ ሞሪሸስ እና ማዳጋስካር ለፕሬዝዳንቱ በረራ የአየር ክልላቸውን ክፍት ለማድረግ ፍቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተዋል።
የታይዋን ፕሬዝዳንታዊ ፅህፈት ቤት ሃላፊ ፓን ሜንጋን እንደገለጹት፣ ሀገራቱ ቀደም ሲል ፍቃደኝነታቸውን አሳውቀው የነበረ ቢሆንም ከጥቂት ቀናት በኋላ ግን በድንገት ሃሳባቸውን ቀይረዋል።
ታይዋን ለዚህ የአቋም ለውጥ ዋነኛው ምክንያት ከቤጂንግ (ቻይና) የሚመጣ ዲፕሎማሲያዊ ጫና መሆኑን በግልጽ ተናግራለች።
"ቻይና ታይዋንን በዓለም አቀፍ መድረክ በዲፕሎማሲ ለማግለል የምታደርገው ጥረት አካል ነው" — የታይዋን ባለስልጣናት
ፕሬዝዳንት ላይ ቺንግ ቴ ወደ ስፍራው ማቅናት የፈለጉት፣ የታይዋን የቅርብ ወዳጅ የሆኑት የኢስዋቲኒው ንጉሥ ሚስዋቲ 40ኛ ዓመት የንግሥና በዓል ላይ ለመታደም ነበር።
ኢስዋቲኒ በአሁኑ ወቅት ለታይዋን ሙሉ ዲፕሎማሲያዊ እውቅና ከሰጡ 12 የዓለማችን ሀገራት መካከል አንዷ መሆኗ ይታወቃል።
ይህ ክስተት ቻይና የታይዋንን የውጭ ግንኙነት መስመር ለመዝጋት የምታደርገውን ጥብቅ ቁጥጥርና በአፍሪካ ሀገራት ላይ ያላትን የፖለቲካ ተጽዕኖ በድጋሚ ያሳየ ሆኗል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን) #getutemesgen #getu
#premiumtimes #taiwan #eswatini #china #africa #diplomacy #thiqaheth

"ኔቶ ለአሜሪካ ህዝብ ጀርባውን ሰጥቷል" ፕሬዚዳንት ትራምፕ
#ethiopia | የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከኔቶ ዋና ፀሐፊ ማርክ ሩቴ ጋር ባደረጉት የሁለት ሰዓት ውይይት፣ ወታደራዊ ጥምረቱ በወሳኝ የጦርነት ወቅት ከአሜሪካ ጎን አለመቆሙን በመጥቀስ ብርቱ ትችት ሰንዝረዋል።
ፕሬዚዳንቱ በተለይም ከኢራን ጋር በነበረው ወታደራዊ ፍጥጫ ወቅት የኔቶ አባል ሀገራት ራሳቸውን ማግለላቸው እንዳበሳጫቸው ገልጸዋል። "ዋሽንግተን ጦርነት ውስጥ በገባችበት ወቅት ከጎናችን ለመቆም የተነሳ የለም፣ ወደፊትም አይቆሙም" ሲሉ የጥምረቱን አስተማማኝነት ጥያቄ ውስጥ ከትተዋል።
"ኔቶን በፈለግነው ሰዓት አላገኘነውም" በማለት ቅሬታቸውን የገለጹት ትራምፕ፣ ጥምረቱ ለአሜሪካ ህዝብ የሚገባውን ድጋፍ ከመስጠት ይልቅ ጀርባውን ማዞሩን ተናግረዋል።
የኔቶ ዋና ፀሐፊ ማርክ ሩቴ በበኩላቸው፣ ከትራምፕ ጋር የነበራቸው ቆይታ "ግልፅ እና ጥሩ" እንደነበር ቢገልጹም፣ ፕሬዚዳንቱ ስለሰነዘሩት ጠንከር ያሉ ትችቶች ግን ዝርዝር ምላሽ ከመስጠት ተቆጥበዋል። ይህ የትራምፕ አቋም አሜሪካ ከኔቶ ጋር ያላትን የወደፊት ግንኙነት ምን ሊሆን ይችላል? የሚለውን አነጋጋሪ አድርጎታል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #thiqaheth #trump #nato #markrutte #usa #iran #breakingnews #ethiopia #thiqaheth #novinite

7 months ago
❗️የፀጥታው ምክር ቤት ለዛሬ አስቸኳይ ጉባኤ ጠራ።
የተመድ የፀጥታው ምክር ቤት በዛሬው እለት እሁድ ስብሰባ የጠራው በኢራን እና እስራኤል ጉዳይ ለመምከር ነው።
ስብሰባው የሚመራው የየካቲት ወር ሊቀመንበርነትን በተረከበችው ዩናይትድ ኪንግደም አማካኝነት እንደሆነ ተገልጿል።
ኢራን ምክርቤቱ በእስራኤል የተፈጸመባትን ጥቃት በተመለከተ እንዲያወግዝ በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ አባስ አራግቺ በኩል በደብዳቤ ጠይቃለች።
ነገር ግን ፈረንሳይ፣ ባህሬን እና ኮሎምቢያ የፀጥታው ምክርቤት በኢራን እና እስራኤል ጦርነት አስቸኳይ ስብሰባ እንዲጠራ ጠይቀዋል ተብሏል። #newsmax
ThiqahEth
seledadotio

የፑቲን ክንድ የቴሌግራሙ መስራች ፓቨል ዱሮቭ ላይ በረታች
📌የክሱ መነሻ እና የቴሌግራም ምላሽ
#ethiopia | * ክሱ፦ ሩሲያ ዱሮቭን "የሽብርተኞችን መልዕክት በማስተላለፍ እና ለወንጀለኞች አመቺ መድረክ በመፍጠር" ትከሳለች።
* የኩባንያው ምላሽ፦ ቴሌግራም የቀረበበትን ክስ "መሰረተ ቢስ" ሲል አጣጥሎታል። ኩባንያው የግላዊነት ጥበቃን (Privacy) እንደ መርህ እንደሚከተል እና ከመንግስታት ጫና ነፃ መሆኑን በተደጋጋሚ መግለጹ ይታወቃል።
"ማክስ"፦ አዲሱ የሩሲያ ተስፋ?
የሚገርመው ግን ምርመራው የተከፈተው ሩሲያ "ማክስ" (Max) የተሰኘ የራሷን መተግበሪያ ይፋ ካደረገች በኋላ መሆኑ ነው።
* መንግስታዊ ትዕዛዝ፦ የሩሲያ መንግስት ሁሉም ዜጎች ቴሌግራምን በመተው ይህንን አዲስ መተግበሪያ በስልካቸው ላይ እንዲጭኑ ትዕዛዝ አስተላልፏል።
* ግቡ፦ የውጭ መተግበሪያዎች ላይ ያለውን ጥገኝነት መቀነስ እና የዲጂታል መረጃዎችን በሀገር ውስጥ ቁጥጥር ስር ማዋል እንደሆነ ይገመታል።
ባጭሩ፦ ሩሲያ በፓቨል ዱሮቭ ላይ የከፈተችው ምርመራ ዜጎቿን ወደ ሀገር በቀሉ "ማክስ" መተግበሪያ ለመግፋት እንደ ስትራቴጂ እየተጠቀመችበት እንደሆነ ብዙዎች ይተቻሉ።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #telegram #paveldurov #russia #maxapp #technews #theindependent #thiqaheth

8 months ago
ኪም ጆንግ ኡን ለዘማች ቤተሰቦች የቤት ቁልፍ አበረከቱ
#ethiopia | የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን፣ ከሩሲያ ጎን ተሰልፈው በዩክሬን ጦርነት ህይወታቸውን ላጡ ወታደሮች ቤተሰቦች በዋና ከተማዋ ፒዮንግያንግ አዳዲስ የመኖሪያ ቤቶችን አስገንብተው አስረክበዋል።
ኪም በዚሁ ወቅት እንደገለጹት፣ መንግስታቸው ለዘማች ቤተሰቦች የሚያደርገውን አስፈላጊ ድጋፍ እና እንክብካቤ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ቃል ገብተዋል። ይህ እርምጃ ሀገሪቱ ለሞስኮ ያላትን የጸና ወታደራዊ አጋርነት እና ለጦርነቱ የከፈለችውን መስዋዕትነት የሚያሳይ ነው ተብሏል።
የክፍለ ጦሩ ተሳትፎ በቁጥር ሲታይ፦
* ወደ ሩሲያ የተላኩ ወታደሮች፦ 15,000
* በጦርነቱ ህይወታቸውን ያጡ፦ 2,000 ገደማ
* የተሰጠው ማበረታቻ፦ በዋና ከተማዋ ፒዮንግያንግ ውስጥ የተሰሩ ዘመናዊ ቤቶች።
ይህ የቤቶች ስርጭት ለቤተሰቦቹ እንደ መጽናኛ ቢታይም፣ የሰሜን ኮሪያ ወታደሮች በሩቅ ምስራቅ አውሮፓ እየከፈሉት ያለው የህይወት ዋጋ ግን ከቀን ወደ ቀን እየጨመረ መምጣቱን መረጃዎች ያመለክታሉ።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #northkorea #kimjongun #russiaukrainewar #pyongyang #worldnews #militaryalliance #ethiopia #thiqaheth #upi

11 months ago
በኬንያ በአውሮፕላን አደጋ የ12 ሰዎች ህይወት አለፈ
#ethiopia | ቱሪስቶችን ብቻ ጭኖ የነበረው አውሮፕላን ከድዪዣኒ ወደ ኪችዋ ሲጓዝ ቴምቦ ሪዞርት አጠገብ መከስከሱን የኬንያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን (KCCA) አስታውቋል።
ባለስልጣኑ ቱሪስቶቹ የየት ሀገር ዜጋ እንደሆኑ እስካሁን ማወቅ እንዳልተቻለ ገልጿል።
በአደጋው ዙሪያ ምርመራ መጀመሩን አስታውቋል። #legit #thiqaheth

1 year ago
ራችማንድራ ፓደል የኔፓል የሽግግር መንግስት ፕሬዚዳንት ሆነው ተመረጡ
#ethiopia | አዲሱ ፕሬዚዳንት ተቃዋሚዎች እንዲረጋጉ ጥሪ አቅርበዋል። ፓደል፣ "የተቃዋሚዎችን ጥያቄ ለመመለስ ሁሉንም ጥረቶች እያደረግን ነው" ብለዋል።
"ሁሉም ወገኖች ነገሮች እንደሚስተካከሉ በዚህ ሊተማመኑ ይገባል" ሲሉም ተናግረዋል።
በነበረው ተቃውሞ 34 ሰዎች መሞታቸውንና 1,368 ሰዎች መጎዳታቸውን ፕሬዚደንቱ አስታውሰዋል።
በግርግሩ 14 ሺሕ 307 እስረኞች ማምለጣቸውን የኔፓል ፖሊስ ቃል አቀባይ ቢኖድ ጊማየር አስታውቀዋል። #yenisafaq #thiqaheth

"ህንድ ፕሬዝዳንት ትራምፕን ይቅርታ ትጠይቃለች" አሜሪካ
📌ህንድና አሜሪካ የንግድ ስምምነት ላይ የመድረስ እድል አላቸው ተብሏል።
#ethiopia | የአሜሪካ ንግድ ቢሮ ኃላፊ ሆዋርድ ሉትኒክ ህንድ ወደ ድርድሩ ለመመለስ ቅድመ ሁኔታዎችን ማሟላት እንዳለባት አሳስበዋል።
"ጠቅላይ ሚኒስትር ሞዲ ከትራምፕ ጋር መግባባት ላይ መድረስ አለባቸው" ሲሉም ተናግረዋል።
ኃላፊው አክለው፣ "ህንድ ፕሬዝዳንት ትራምፕን ይቅርታ ትጠይቃለች" ብለዋል። ምክንያት ያሉት ደግሞ ትራምፕ ህንድ ከሩሲያ ነዳጅ እንዳትገዛ ቢያስጠነቅቁም አሁንም መግዛት መቀጠሏን ነው።
ካልሆነ ግን እንደ ሩሲያ እና ቻይና ማዕቀብ ሊጣልባት እንደሚችል ጠቁመዋል። #trtworld #thiqaheth

"የአሜሪካ ቪዛ በውዴታ የሚገኝ እንጂ መብት አይደለም"
- በአዲስ አበባ የአሜሪካ ኤምባሲ
#ethiopia | በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ለኢትዮጵያውያን ተጓዦች አዲስ ማስጠንቀቂያ አዘል መልዕክት አስተላልፏል።
በማህበራዊ ትስስር ገጹ ዛሬ ባወጣው መግለጫ፣ "ህገወጥ መጠጦችን መጠቀምና ማንኛውንም የአሜሪካ ህግ መጣስ የአሜሪካ ቪዛ አያስገኝም" ሲል ገልጿል።
በትምህርትም ሆነ በጉብኝት በቀጣይ ወደ አሜሪካ ለመጓዝ ያሰቡ ሰዎች ከእነዚህ ወንጀሎች እንዲቆጠቡ አሳስቧል።
ኤምባሲው፣ "የአሜሪካ ቪዛ በውዴታ የሚገኝ እንጂ መብት አይደለም" ብሏል።
"ቪዛ ከተሰጠ በኋላም የአሜሪካ ቪዛ ምርመራ ማድረግ አይቆምም" ያለው ኤምባሲው፣ "ህጉን ተላልፈው ከተገኙ ቪዛውን እንቀማችኋለን" ሲል አስታውቋል። #usembassyaddisabbaba #thiqaheth

"ለቻይና ድል ብዙ አሜሪካውያን ሞተዋል" - ትራምፕ
#ethiopia | ዶናልድ ትራምፕ ፑቲን፣ ኪም እና ዢ በአሜሪካ እያሴሩ ነው ሲሉ ወነጀሉ። ሶስቱ መሪዎች በቻይና ከወታደራዊ ትርዒት ጎን ለጎን መወያየታቸው ተገልጿል።
"ዥ ምንም እንኳን በአሜሪካ ላይ እያሴራችሁ ቢሆንም ለፑቲንና ኪም ሰላምታየን አድርስልኝ" ያሉት ትራምፕ "ፕሬዚዳንት ዥ አሜሪካ ለቻይና ነፃነት የከፈለችውን መስዋዕትነት ያስታውሱታል?" ሲሉ ጠይቀዋል።
"ለቻይና ድል ብዙ አሜሪካውያን ሞተዋል" ብለዋል ትራምፕ። #foxnews #thiqaheth

"የሞት ቅጣት እርምጃን እንጠቀማለን" ትራምፕ
#ethiopia | ፕሬዚዳንት ትራምፕ በግድያ ወንጀል የተከሰሱ ተጠርጣሪዎች የሞት ፍርድ እንዲፈረድባቸው አዘዙ።
ትራምፕ በዋይትሃውስ የካቢኔ ስብሰባ ላይ ባደረጉት ንግግር በዋና ከተማዋ ዋሽንግተን የወንጀል ድርጊቶችን ለመቀነስ ያግዛል ያሉትን እርምጃ እንደሚወስዱ ገልጸዋል።
"የሞት ቅጣት እርምጃን እንጠቀማለን" ያሉት ፕሬዚዳንቱ፣ "ይህ እርምጃ ጠንካራ የወንጀል መከላከያ ዘዴ ነው" ሲሉም ተናግረዋል።
በዋሽንግተን ግድያ የሚፈጽሙ ወንጀለኞች የፍርድ ውሳኔ የሚሰጣቸው በዲሲ የከተማ ፍርድ ቤት ነው። በዚህ ፍርድ ቤት ከፍተኛው ቅጣት የእድሜ ልክ እስራት ነው ተብሏል።
በአሜሪካ የሞት ፍርድ የሚተላለፈው በፌደራሉ ፍርድ ቤት ሲሆን ለሞት ቅጣት የሚዳርጉ ወንጀሎች ሲፈጸሙ ብቻ ውስን የሞት ፍርድ ውሳኔዎችን እንደሚያሳልፍ ተገልጿል። በዋሽንግተን ለሞት ፍርድ የሚያበቃ አስተማማኝ ማስረጃ የለም ተብሏል።
ትራምፕ በዋና ከተማዋ ዋሽንግተን በዚህ ወር መግቢያ ላይ በመቶዎች የሚቆጠሩ ወታደሮችን ለሰላም ማስከበር አሰማርተዋል።
ፕሬዚደንቱ በምርጫ ወቅት ዲሞክራቶች ባሸነፉባቸው ባልቲሞር ቺካጎ እና ኒውዮርክ ከተሞች ለማሰማራት አማራጮችን እያዩ ነው ተብሏል።
ትራምፕ ይህ ውሳኔያቸው በዜጎች እና በአንዳንድ የፖለቲካ ተንታኞች ዘንድ ከፍተኛ ትችት እና ተቃውሞ ያስከተለባቸው ሲሆን፣ ዲሞክራቶችም "አምባገነን" ሲሉ ትራምፕን ተችተዋል።
ትራምፕ በበኩላቸው "አውቃለሁ ብዙ ሰዎች እንደሚተቹኝ እኔ ግን አምባገነን አይደለሁም" ብለዋል። "ወንጀልን ለማጥፋት አምባገነን ብሆን እመርጣለሁ" ሲሉ ተናግረዋል።#euronews #thiqaheth

በአፍጋኒስታን በትራፊክ አደጋ የ71 ሰዎች ህይወት አለፈ
#ethiopia | ወደ ካቡል ሲጓዝ የነበረ አውቶብስ ከተሳቢና ሞተር ሳይክል ጋር በመጋጨቱ አደጋው እንደደረሰ ተገልጿል።
አደጋው የደረሰው በህያት ግዛት ነው ተብሏል። #radiogov #thiqaheth

"ዘለንስኪ ጦርነቱን ማቆም ትችላለህ፣ ወይም መዋጋትህን ቀጥል" - ትራምፕ
#ethiopia | ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ዘለንስኪ ከሩሲያ ጋር ለሰላማዊ ድርድር ቁርጠኛ እንዲሆኑ አሳሰቡ።
ትራምፕ ትሩዝ ሶሻል በተሰኘው የግል የማህበሩ ሚዲያ ትስስር ገፃቸው ላይ "ሩሲያ ዝግጁ ናት አንተ መዘጋጀት አለብህ" ሲሉ ዘለንስኪን አስጠንቅቀዋል።
"ዘለንስኪ ጦርነቱን ማቆም ትችላለህ፣ ወይም መዋጋትህን ቀጥል" ብለዋል ፕሬዚዳንቱ።
ትራምፕ "ጦርነቱ እንዴት እንደተጀመረ አስታውስ፣ ኦባማ ነው ያለጦርነት ከ12 አመት በፊት ክሪሚያን አሳልፎ የሰጠው" ብለዋል።
"እንደዚያም ሆኖ ያኔ ዩክሬን ኔቶን እቀላቀላለሁ አላለችም ነበር" በማለት ገልጸዋል።
ዶናልድ ትራምፕ በዚሁ አስተያየታየው ዩክሬን ክሪሚያን መልሳ መቆጣጠርም ሆነ የኔቶ አባል መሆን እንደማትችል አስታውቀዋል። #irishindependent #thiqaheth

31 ሱዳናውያን በድንገተኛ ጥቃት ተገደሉ
#ethiopia | በሰሜን ዳርፉር በሚገኝ የስደተኞች መጠለያ ካምፕ ላይ የአየር ላይ ተፈፅሟል ተብሏል።
በዚህም 31 ተገደሉ የተባለ ሲሆን፣ ከሟቾቹ ውስጥ 7 ህፃናትና አንዲት ነፍሰጡር እናት እንደሚገኙበት ተገልጿል።
ከሟቾቹ በተጨማሪ 13 ሰዎች ተጎድተው ሆስፒታል ገብተዋል ተብሏል።
ጥቃቱ በፈጥኖ ደራሽ ሀይሉ እንደተፈጸመ ቢገለፅም፣ ቡድኑ እስካሁን ድረስ ሀላፊነት አልወሰደም።
#yahoonews #thiqaheth

"ከባድ ውሳኔ ነው" - ጠቅላይ ሚኒስትር ኢሺባ
#ethiopia | የጃፓን ጠቅላይ ሚኒስትር ሽገሩ ኢሺባ ፓርቲ በምክር ቤት ምርጫ ተሸነፈ።
ኢሺባ የሀገሪቱ ከፍተኛ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምርጫ ውጤትን "ከባድ ውሳኔ ነው" ብለውታል።
በስልጣን የመቆየት ፍላጎት እንዳላቸው የተናገሩት ጠቅላይ ሚኒስትሩ የአሜሪካን ታሪፍ ማስቀረት የመጀመሪያ ስራቸው እንደሚሆን ገልጸዋል።
#channelsnewsasia #thiqaheth

"እስራኤል ለተኩስ አቁም ተስማምታለች" - ፕሬዝዳንት ትራምፕ #ethiopia | ትራምፕ ለጋዛ የተኩስ አቁም የመጨረሻ እቅድ አስገቡ። ፕሬዝዳንት ትራምፕ በአዲሱ እቅዳቸው በእስራኤልና በሃማስ መካከል ለ60 ቀናት የሚቆይ የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲደረግ ፍላጎት እንዳላቸው ገልፀዋል። ትራምፕ በትሩዝ ሶሻል ገፃቸው፣ "ተወካዮቼ ስለጋዛ ከእስራኤል ባለሥልጣናት ጋር ረጅምና ውጤታማ ስብሰባ አድርገዋል" ብለዋል። "እስራኤል ለተኩስ አቁም ተስማምታለች" ያሉት ፕሬዚደንቱ፣ ሀማስ ስምምነቱን እንዲቀበል ጠይቀዋል። "ጦርነቱን ለማቆም ከሁለቱም ወገኖች ጋር አብረን እንሰራለን" ብለዋል ዶናልድ ትራምፕ። #thiqaheth
1 year ago
በህንድ የመድኃኒት ፋብሪካ ላይ በተከሰተ ፍንዳታ 36 ሰዎች ሞቱ።
የፍንዳታ አደጋው የተከሰተው የኬሚካል ማብላያ ላይ እሳት በመፈጠሩ ነው ተብሏል።
በህንፃው ውስጥ ከ100 በላይ ሰዎች ይኖራሉ ተብሎ እንደሚታመን ተገልጿል። ThiqahEth
seledadotio
seledadotio
የፍንዳታ አደጋው የተከሰተው የኬሚካል ማብላያ ላይ እሳት በመፈጠሩ ነው ተብሏል።
በህንፃው ውስጥ ከ100 በላይ ሰዎች ይኖራሉ ተብሎ እንደሚታመን ተገልጿል። ThiqahEth
seledadotio
seledadotio
1 year ago
በዩ ኤስ ኤይድ መቋረጥ ተጨማሪ 14 ሚሊዮን ሰዎችን ለሞት አጋልጧል ተባለ። #ethiopia የአሜሪካ ተራዲዖ ድርጅት (USAID) ስራውን በቅርቡ ካልጀመረ በ2030 በአለማቀፍ ደረጃ 14 ሚሊዮን ሰዎች እንደሚሞቱ የላንሴት ህክምና ቡድን ይፋ ያደረገው ጥናት ያመለክታል። የትራምፕ አስተዳደር ለዩ ኤስ ኤይድ የሚያደርገውን ድጋፍ በማቋረጥ ድርጅቱ እንዲዘጋ አድርጓል። #thenewdaily #thiqaheth
Sponsored by
Surafel
Comments