2 days ago
#uog
በ2019 ዓ.ም ጎንደር ዩኒቨርሲቲ አዲስ የተመደባችሁ የመጀመሪያ ዓመት መደበኛ ተማሪዎች እንዲሁም በ2018 ዓ.ም የሪሚዲያል ትምህርታችሁን ተከታትላችሁ ያለፋችሁ ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ቀናት ጥቅምት 04 እና 05/2019 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።
በተመሳሳይ በጎንደር ዩኒቨርሲቲ በድኅረ-ምረቃ ፕሮግራም ለመማር ያመለከታችሁ አዲስ ገቢ ተማሪዎች የመግቢያ ቀናት ጥቅምት 04 እና 05/2019 ዓ.ም መሆኑ ተገልጿል።
አዲስ ገቢ የመጀመሪያ ዲግሪ መደበኛ ተማሪዎች ለምዝገባ ልትይዟቸው የሚገቡ፦
● ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
● የ12ኛ ክፍል ሰርተፊኬት ዋናውና ኮፒው፣
● አራት 3x4 መጠን የሆኑ ጉርድ ፎቶግራፎች፣
● አንሶላ፣ ብርድ ልብስ፣ ትራስ ልብስ እና የስፖርት ልብስ።
የምዝገባ ቦታ፡-
● ለማኅበራዊ ሳይንስ መስክ መደበኛ አዲስ ገቢ ተማሪዎች በማራኪ ግቢ
● ለተፈጥሮ ሳይንስ መስክ መደበኛ አዲስ ገቢ ተማሪዎች በአጼ ቴዎድሮስ ግቢ
● ለድኅረ-ምረቃ ተማሪዎች በግቢው ረዳት ሬጅስትራር ጽ/ቤቶች
አዲስ ገቢ የመጀመሪያ ዲግሪ መደበኛ ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሰቲው ከመሔዳችሁ በፊት በኦንላይን (Registration.uog.edu.et) ምዝገባችሁን እንድትፈጸሙ ተብሏል። (የምዝገባ ሒደቱ ቅደም ተከተልን ከላይ ከተያያዘው ምስል ይመልከቱ።)
@tikvahuniversity

6 days ago
ሁለት ሰዎችን በመግደል የተሰወረው ግለሰብ በፖሊስ ተያዘ !!!
በጎንደር ከተማ ሁለት ሰዎችን በመግደል የተሰወረው ግለሰብ በቁጥጥር ስር መዋሉን የጎንደር ከተማ ሰላምና ፀጥታ መምሪያ አስታወቀ።
የጎንደር ከተማ ሰላምና ፀጥታ መምሪያ ኃላፊ አቶ አለልኝ ዓለም እንደገለፁት ፣ ግለሰቡ መስከረም 21 ቀን 2019 ዓ.ም ከምሽቱ 2:30 ላይ በማራኪ ክፍለ ከተማ በአየር ጤና ቀበሌ የወንጀል ድርጊቱን ፈፅሟል ።
መሰረት ደሳለኝ የተባለው ይህ ተጠርጣሪ ፣ የሽበር አዱኛ እና ታደላ ሞላ የተባሉ ባለትዳሮችን ህይወት በማጥፋት ከስፍራው ለማምለጥ ሞክሯል።
ሆኖም ራሱን ለመደበቅ የተለያዩ መኩራዎች ቢያደርግም በፀጥታ አካላት በተደረገው ጥብቅ ክትትልና በህብረተሰቡ በተደረገ ጥቆማ ፣ በአጭር ጊዜ ውስጥ ተይዞ በቁጥጥር ስር መዋሉን አቶ አለልኝ ገልጸዋል።
#ዳጉ_ጆርናል

7 days ago
የአሽከርካሪዎችን ዕገታ ለማስቆም ከመንግሥት ጋር እየሠራ እንደሆነ የኢትዮጵያ ትራንስፖርት አሠሪዎች ፌዴሬሽን አስታወቀ
በኢትዮጵያ በተለያዩ አካባቢዎች በአሽከርካሪዎች ላይ የሚደርሰውን ዕገታ ለማስቀረት እና ጤናማ የትራንስፖርት አገልግሎት ለመስጠት እየተሠራ ይገኛል።
የኢትዮጵያ ትራንስፖርት አሠሪዎች ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት አቶ ብርሃኔ ዘሩ ለአሐዱ ሬድዮ እንዳስታወቁት፣ በ2019 የበጀት ዓመት ችግሩን ለማቃለል ፌዴሬሽኑ ከመንግሥት ጋር በጥምረት እየሠራ ነው።
በወለንጭቲ፣ በአሊዶሮ፣ በጎንደርና በተለያዩ አካባቢዎች ትጥቅ ያነሱ አካላት በመኖራቸው በአሽከርካሪዎች ላይ የሚደርሰው ዕገታ በጊዜ ሂደት እንዲቆም ይደረጋል ብለዋል።
ችግሩ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻለ መምጣቱን የጠቆሙት ፕሬዚዳንቱ፣ አሽከርካሪዎች ፈተናዎችን ተቋቁመው አገልግሎት እየሰጡ እንደሚገኙ ተናግረዋል።
ዕገታው ሙሉ በሙሉ አለመቆሙን የጠቆሙት አቶ ብርሃኔ፣ በቀጣይም የችግሩን አሳሳቢነት በማየት ፌዴሬሽኑ ከሌሎች ተቋማት ጋር ለመሥራት ማቀዱን ገልጸዋል።
በተመስገን ተጋፋው
#አሐዱ_ሬዲዮ_94 .3
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ

11 days ago
በታሪካዊው የፋሲል ጊቢ የዓለም ቱሪዝም ቀንን አስመልክቶ የሕይወት በአብያተ መንግሥታት መርሃ ግብር ተካሄደ
#ethiopia | በጎንደር ከተማ በሚገኘው ታሪካዊው የፋሲል ጊቢ የዓለም ቱሪዝም ቀንን በማስመልከት የሕይወት በአብያተ መንግሥታት መርሃ ግብር ተካሂዷል።
በዚህ መርሃ ግብር ላይ የቱሪዝም ሚኒስትር ሰላማዊት ካሳ፣ የቱሪዝም ሚኒስትር ድኤታ ዶክተር እንደገና አበበ፣ የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የመንግሥት ኃላፊዎች፣ የተጠሪ ተቋማት ተወካዮች እና የዘርፉ ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል።
ሚኒስትር ሰላማዊት ካሳ ከጉብኝቱ በኋላ በሰጡት ማብራሪያ፣ በኢትዮጵያ የሚከበሩ ሕዝባዊና ሃይማኖታዊ በዓላት የበርካታ የውጭ ሀገር ጎብኚዎችን ቀልብ በመሳብ ለሀገሪቱ የቱሪዝም ገቢ ማደግ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከቱ መሆናቸውን ገልጸዋል።
የበዓላትን ባህላዊና ታሪካዊ እሴቶች ሳይበረዙ ለቀጣዩ ትውልድ ማስተላለፍ የሚያስችል ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ እንደሚገኝም ሚኒስትሯ ጠቁመዋል።
ይህም የሀገሪቱን የቱሪዝም ሀብቶች በጥንቃቄ በመጠበቅና በማስተዋወቅ ዘርፉ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ እንዲሆን ያደርገዋል ብለዋል።
በሌላ በኩል የቱሪዝም አገልግሎቱን በዲጂታል ቴክኖሎጂ ለማዘመን ከክልሎች ጋር በመቀናጀት የመረጃ ማሰባሰብ ስራ እየተከናወነ ሲሆን፣ ባለፈው የበጀት ዓመት ብቻ ከ800 በላይ አዳዲስና ነባር የቱሪዝም መዳረሻዎችን መለየት መቻሉን አብራርተዋል።
የዓለም ቱሪዝም ቀን አከባበር የኢትዮጵያን የቱሪዝም አቅምና የባህል ሀብቶች ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ለማስተዋወቅ ምቹ አጋጣሚ እንደሚፈጥር ተገልጿል።
#gondar #fasilgebbi #tourism #ethiopiatourism #worldtourismday #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

13 days ago
🚨 ወደ ትግራይ ክልል የሚደረጉ የየብስ ትራንስፖርት እና የሸቀጦች ዝውውር ሙሉ በሙሉ መቋረጡ ተገለጸ
ከመስከረም 13 ቀን 2019 ዓ.ም ጀምሮ ከተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች እና ከጅቡቲ መሠረታዊ አቅርቦቶችን እና ሸቀጣ ሸቀጦችን ጭነው ወደ ትግራይ ክልል በመጓዝ ላይ የነበሩ በርካታ የጭነት ተሽከርካሪዎች በመንገድ ላይ መቆማቸው ተሰማ።
🔹 ዋና ዋና ነጥቦች፦
የተሽከርካሪዎች መቆም፦ በወልድያ-ቆቦ-አለማጣ፣ በአባላ-መቀሌ እና በጨርጨር-መሆኔ መስመሮች ላይ የተሰማሩ ከባድ መኪኖች ከሶስት ቀናት በላይ መንገድ ላይ ቆመው እንደሚገኙ፤ በተለይም በወልድያ እና በቆቦ ከተሞች በርካታ አቅርቦት የጫኑ ተሽከርካሪዎች መታቆማቸው ተገልጿል።
የመንገዶች መዘጋት፦ በጎንደር-ጠለምት፣ በሁመራ (በሁለቱም የተከዜ በኩል)፣ በራያ እና በዋግህምራ በኩል ወደ ክልሉ የሚገቡና የሚወጡ የየብስ ትራንስፖርት እንቅስቃሴዎች ሙሉ በሙሉ መቋረጣቸው ተመላክቷል።
አጠቃላይ ሁኔታ፦ በአሁኑ ወቅት ወደ ክልሉ የሚገባም ሆነ የሚወጣ ማንኛውም የየብስ ትራንስፖርት እና የጭነት እንቅስቃሴ ሙሉ በሙሉ መገደቡ ተመላክቷል።
Seledadotio

20 days ago
የአፄ ፋሲል ግንብ አምሮበታል !!!
በጎንደር ከተማ የሚገኘው የአፄ ፋሲል ግንብ በቅርቦ መታደሱ ይታወቃል ። ከእድሳት በኃላ በበርካታ የሀገር ውስጥና በዉጭ ሀገር ቱሪስቶች እየተጎበኘ ይገኛል
ይምጡ!! የአፄ ፋሲል ግንብን ይጎብኙ !!
የአፄ ፋሲል ግንብ ወቅታዊ ገፅታን በቪዲዮ ይመልከቱ
Sponsored by
Surafel
25 days ago
በመቅደላ ጦርነት የተወሰደውና የአጼ ቴዎድሮስ ሊሆን የሚችል መጽሐፍ ቅዱስ በ47.5 ሚሊዮን ብር ለሽያጭ ቀረበ
#ethiopia | በ1868 ዓ.ም. በመቅደላ ዘመቻ ወቅት ከኢትዮጵያ ተወስዶ እንደነበር የሚገመተውና የአጼ ቴዎድሮስ ዳግማዊ መጽሐፍ ቅዱስ ሊሆን እንደሚችል የሚታመን ጥንታዊ የብራና መጽሐፍ ቅዱስ በ47.5 ሚሊዮን ብር ወይም 250 ሺህ ዩሮ ለሽያጭ ቀርቧል።
መጽሐፉ ከዛሬ ጀምሮ ለአንድ ሳምንት በአቡ ዳቢ ለሽያጭ እንደሚቀርብ ተገልጿል።
በግዕዝ ቋንቋ በብራና ላይ የተጻፈው ይህ ጥንታዊ መጽሐፍ የሉቃስን ወንጌል ሙሉ በሙሉ የያዘ ሲሆን፣ የዮሐንስ ወንጌልንም ከመጨረሻዎቹ 16 ጥቅሶች በስተቀር ሙሉ በሙሉ እንደያዘ ተገልጿል።
መጽሐፉ በ1730–1740 ዓ.ም. አካባቢ በጎንደር ውስጥ የተጻፈ እንደሆነ የተገመተ ሲሆን፣ ተአምራትንና የኢየሱስ ክርስቶስን ትንሣኤ የሚያሳዩ 235 ሥዕሎችን እንደያዘ ታውቋል። በተለያዩ ዲዛይኖች የተሠራ የቆዳ ሽፋንም እንዳለው ተገልጿል።
ዋና መቀመጫውን ኦስትሪያ ያደረገው “ኢንሊብሪስ” (Inlibris) የተባለ በተለይ ጥንታዊ መጻሕፍትን የሚሰበስብና የሚሸጥ ተቋም ነው መጽሐፉን በአቡ ዳቢ ለሽያጭ ያቀረበው።
የኢትዮጵያ ቅርሶችን በማጥናትና የተወሰዱ ቅርሶች ወደ ኢትዮጵያ እንዲመለሱ በመሥራት የሚታወቁት ዶ/ር አሉላ ፓንክረስት፣ መጽሐፉ በመቅደላ ዘመቻ ወቅት በእንግሊዝ ጦር አዛዥ ሌተናንት ጀነራል ሮበርት ናፒር ከኢትዮጵያ ተወስዶ እንደነበር ገልጸዋል።
ከዚያም መጽሐፉ በወቅቱ በሕንድ የእንግሊዝ ግዛት ከፍተኛ አዛዥ ለነበረ አካል በስጦታ መሰጠቱን እና በቀጣዮቹ 158 ዓመታት ውስጥ ከአንድ ሙዚየም ወደ ሌላ፣ እንዲሁም ከአንድ ግለሰብ ወደ ሌላ በሽያጭ ሲተላለፍ መቆየቱን አስረድተዋል።
ዶ/ር አሉላ እንደሚሉት፣ ከኢትዮጵያ በጦርነት ወቅት የተወሰደ ቅርስ በአሁኑ ወቅት ለግል ሽያጭ መቅረብ የለበትም የሚል ጠንካራ የሞራል መከራከሪያ አለ። በዚህም መሠረት መጽሐፉ ለግል ስብስብ ከመሸጡ በፊት ወደ ኢትዮጵያ እንዲመለስ ጥረት ሊደረግ ይገባል ብለዋል።
ቅርሱ ከኢትዮጵያ መወሰዱና አሁን ለሽያጭ መቅረቡ በሚዲያና በዲፕሎማሲ በኩል ጫና ከተፈጠረ፣ ግለሰቦችም ሆኑ ሙዚየሞች መጽሐፉን ለመግዛት እንደማይደፍሩ ተመራማሪው ገልጸዋል።
የሽያጩን ሂደት ለማስቆም ከኦስትሪያና ከተባበሩት ዓረብ ኤሚሬቶች ጋር በዲፕሎማሲ በኩል መነጋገር እንደሚያስፈልግም ዶ/ር አሉላ አመልክተዋል።
“ዘመኑ ተለውጧል፤ ስለ ቅርሶች መመለስ ያለው እይታም ተቀይሯል” ያሉት ዶ/ር አሉላ፣ ኢንሊብሪስ ሽያጩን በማቆም ይህ ድንቅ የብራና ጽሑፍ ወደ ሌላ የግል ስብስብ ገብቶ ከሕዝብ ዕይታ ከመሰወሩ በፊት ወደ ኢትዮጵያ ተመልሶ ለሕዝብ እይታ እንዲበቃ ጥረት መደረግ እንዳለበት ጠይቀዋል።
ለመጽሐፉ መመለስ የሚደረገው ጥረት አንድ ሳምንት ብቻ የጊዜ ገደብ እንዳለው የገለጹት ዶ/ር አሉላ፣ ቅርሱ ከተቻለ በነፃ፣ ካልሆነም ለሽያጭ ከቀረበበት ዝቅተኛ ዋጋ ተገዝቶ ወደ ኢትዮጵያ እንዲመለስ ሁሉም የሚችለውን ጥረት እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል።
ድምፅ ለመስጠት
Emperor Tewodros Bible Group link https://www.facebook.com/s...

1 month ago
የ7 ዓመት ህፃን አግታ 3 ሚሊዮን ብር የጠየቀች የቤት ሰራተኛ በጎንደር ከተማ ተያዘች
በአዲስ አበባ ከምትሰራበት ቤት የ7 ዓመቷን ህፃን አግታ ወደ ጎንደር በመውሰድ ከቤተሰቦቿ 3 ሚሊዮን ብር የጠየቀች የቤት ሰራተኛ በጎንደር ከተማ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ዋለች።
የጎንደር ከተማ ፖሊስ መምሪያ እንዳስታወቀው፣ መቅደስ ሞገስ የተባለችው ተጠርጣሪ ህፃኗን ካገተች በኋላ ወደ ጎንደር በመውሰድ በማራኪ ክፍለ ከተማ ዩኒቨርሲቲ አካባቢ ባለ ጫካ ውስጥ ደብቃት ነበር።
የመምሪያው አዛዥ ኮማንደር አንተነህ ቴዎድሮስ እንደገለጹት፣ ፖሊስ ከህብረተሰቡ በደረሰው ጥቆማ እና ባደረገው ክትትል ተጠርጣሪዋን መያዝ ችሏል።
ተጠርጣሪዋ ከግርማ ወንድአሁን ከተባለ የአክስቷ ልጅ ጋር በመተባበር ድርጊቱን እንደፈፀመች ፖሊስ ገልጿል። ሁለቱ ለህፃኗ ቤተሰቦች በስልክ በመደወል 3 ሚሊዮን ብር የጠየቁ ሲሆን፣ ከ370 ሺህ ብር በላይ ገንዘብ መቀበላቸውም ተገልጿል።
ፖሊስ በጉዳዩ የተሳተፉ ሌሎች ተጠርጣሪዎችንም ለመያዝ ክትትል እያደረገ መሆኑን አስታውቋል።
addisreporter2

በአዲስ አበባ ታገታ የተወሰደች ህፃንን ለማስለቀቅ ሶስት ሚሊዮን ብር የጠየቀች የቤት ሰራተኛ በጎንደር ከተማ በቁጥጥር ስር ዋለች
#ethiopia | በአዲስ አበባ ከተማ በቤት ሰራተኝነት ተቀጥራ ከምትሰራበት መኖሪያ ቤት የሰባት ዓመቷን ህፃን ፊዮና ሰለሞንን በማገት ወደ ጎንደር ከተማ በመውሰድ ከቤተሰቦቿ ገንዘብ ለመቀበል የሞከረችው ወጣት መቅደስ ሞገስ በቁጥጥር ስር መዋሏን የጎንደር ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ አስታወቀ።
የመምሪያው አዛዥ ኮማንደር አንተነህ ቴዎድሮስ እንደገለጹት ተጠርጣሪዋ ህፃኗን አግታ ወደ ጎንደር ካመጣች በኋላ በከተማዋ ማራኪ ክፍለ ከተማ ዩኒቨርሲቲ አካባቢ በሚገኝ ጫካ ውስጥ ደብቃ በነበረበት ወቅት በህብረተሰቡ ጥቆማና በፖሊስ በተደረገ ጥብቅ ክትትል ልትያዝ ችላለች።
ተጠርጣሪዋ ለጊዜው ካልተያዘው ግርማ ወንድአሁን ከተባለ የአክስቷ ልጅ ጋር በመተባበር ወንጀሉን የፈፀመች ሲሆን ለህፃኗ ቤተሰቦች ስልክ በመደወል ሶስት ሚሊዮን ብር የጠየቁ ቢሆንም ከሶስት መቶ ሰባ ሺህ ብር በላይ ተቀብለው መገኘታቸውን ኮማንደሩ አብራርተዋል።
ፖሊስ ከአደጋው ያመለከተውን ግብረ አበር ጨምሮ ከጉዳዩ ጋር እጃቸው ያለበትን ሌሎች አካላት በቁጥጥር ስር ለማዋል ጥብቅ ክትትል በማድረግ ላይ ይገኛል።
#gondar #addisababa #ethiopianpolice #crimenews #ethiopia #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

የ7 አመት ልጅ በማ ገት 3 ሚሊዮን ብር የጠየቀችው የቤት ሰራተኛ ተያዘች
#fastmereja I በአዲስ አበባ ከተማ ተቀጥራ ከምትሰራበት ቤት የ7 ዓመት ህፃንን በማ ገት 3 ሚሊዮን ብር የጠየቀችው የቤት ሰራተኛ፣ በጎንደር ከተማ በተደረገ የፖሊስ ክትትልና የህዝብ ጥቆማ በቁጥጥር ስር መዋሏን የጎንደር ከተማ ፖሊስ መምሪያ አስታወቀ።
እገ ታውን የፈጸመችው ወጣት መቅደስ ሞገስ የተባለች የቤት ሰራተኛ ህፃን ፊዮና ሰለሞንን ከአዲስ አበባ አ ግታ ወደ አማራ ክልል ጎንደር ከተማ በመውሰድ በቁጥጥር ስር መዋሏን የጎንደር ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ አዛዥ ኮማንደር አንተነህ ቴዎድሮስ ገልጸዋል።
እንደ ኮማንደሩ ማብራሪያ፣ ተጠርጣሪዋ ህፃኗን በከተማዋ ማራኪ ክፍለ ከተማ ዩኒቨርሲቲ አቅራቢያ በሚገኝ ጫካ ውስጥ ደብቃ የነበረ ቢሆንም፣ በተደረገበት ብርቱ ክትትልና ከህዝብ በተገኘ ጥቆማ ህፃኗን በሰላም ማዳን ተችሏል።
ተጠርጣሪዋ ወንጀሉን ካልተያዘው ግርማ ወንድአሁን ከተባለ የአክስቷ ልጅ ጋር በመቀናጀት የፈጸመችው ሲሆን፣ ለህፃኗ ቤተሰቦች ስልክ በመደወል 3 ሚሊዮን ብር በመጠየቅ ከ370 ሺህ ብር በላይ ተቀብለው እንደነበር ተረጋግጧል።
ፖሊስ ከተያዘችው የቤት ሰራተኛ በተጨማሪ ከወንጀሉ ጋር አብረው የተሳተፉ ሌሎች ተጠርጣሪዎችንና አጋሮችን በቁጥጥር ስር ለማዋል ጥብቅ ክትትል ማድረጉን ቀጥሏል።

ለ17 ዓመታት የተጓተተው፣
መገጭ የመስኖ ግድብ ግንባታ ተጠናቆ አገልግሎት ለመስጠት ተቃረበ ተብሏል
#ethiopia | በአማራ ክልል በጎንደር ከተማ ዙሪያ የሚገነባው የመገጭ የመስኖ ግድብ ግንባታ 94 በመቶ መድረሱን የመስኖ እና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር ገልጿል።
ይህ ግድብ በአጠቃላይ 33 ሚሊዮን ሜትር ኪዩብ ውሃ የመያዝ አቅም ያለው ሲሆን ከ9.4 ሚሊዮን ሜትር ኪዩብ የዋና ግድብ ሙሌት ውስጥ 8.25 ሚሊዮኑ መጠናቀቁንና ቀሪው 1.15 ሚሊዮን ሜትር ኪዩብ የውሃ ሙሌት በቅርብ ጊዜ ውስጥ እንደሚጠናቀቅ ተመልክቷል።
በ2.4 ቢሊየን ብር ወጪ በ2001 ዓ.ም የተጀመረው ይህ ፕሮጀክት በተለያዩ ምክንያቶች ሳቢያ ላለፉት 17 ዓመታት ተጓትቶ ቆይቷል።
በአሁኑ ወቅት የግድቡ ትርፍ ውሃ ማስወጫ፣ የመስኖ ውሃ መቆጣጠሪያ ሲቪል ሥራ፣ የመስኖ ውሃ ማስወጫ መጠንና ሃይል መቆጣጠሪያ እንዲሁም ለጎንደር ከተማ የመጠጥ ውሃ አቅርቦት የሚሆን ውሃ ማስወጫ ቱቦ እና መቆጣጠሪያ ገጠማ ሥራዎች ሙሉ በሙሉ መጠናቀቃቸው ተረጋግጧል።
#መገጭግድብ #መስኖ #ጎንደር #ልማት #የመስኖእናቆላማአካባቢሚኒስቴር #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

የገጠር ኮሪደር ፣ ለማህበረ ኢኮኖሚያዊ ሽግግር
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 18፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በኢትዮጵያ ከ80 በመቶ በላይ የሚሆነው ሕዝብ የሚኖረው በገጠር ነው።
ይሁን እንጂ፣ ይህ ከፍተኛ ቁጥር ያለው አምራች ኃይል ለዘመናት በተበታተነና ባህላዊ በሆነ የአኗኗር ዘይቤ ውስጥ ለመኖር ተገዷል።
ይህም ሁኔታ እንደ ጤና፣ ትምህርት፣ ንጹሕ ውኃ እና ኤሌክትሪክ ያሉ መሠረታዊ የመንግሥት አገልግሎቶችን ተደራሽ ማድረግን እጅግ ፈታኝ አድርጎት ቆይቷል።
በተጨማሪም፣ አብዛኛው የገጠር ማኅበረሰብ ከእንስሳት ጋር አብሮ ለመኖር ከመገደዱ ባሻገር፣ የሚጠቀመው ማገዶ ለአካባቢ ብክለትና ለከባድ የመተንፈሻ አካላት ሕመም ሲዳርገው ቆይቷል።
ይህን ሥር የሰደደ ዘመናዊ አገልግሎቶች የማግኘት ችግር ለመቅረፍ፣ የመደመር መንግሥት መጀመሪያ በትልልቅ ከተሞች ላይ ትኩረት በማድረግ አጠቃላይ ገጽታቸውን የሚያድስና ዘመናዊ አደረጃጀትን የሚያጎናጽፍ የከተማ ኮሪደር ልማትን በአዲስ አበባና ሌሎች በርካታ ከተሞች ተግባራዊ አድርጓል።
ሆኖም የዜጎችን ሕይወት በተሟላ መልኩ ለመቀየር እና ሁለንተናዊ ብልፅግናን ለማረጋገጥ የከተማ ኮሪደር ልማት ብቻውን በቂ ባለመሆኑ፣ በከተሞች የታየውን አመርቂ ውጤት ወደ ገጠሩ ማሸጋገር አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል።
በዚህም መሠረት በግንቦት ወር 2017 ዓ.ም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የአርሶ አደሩንና የአርብቶ አደሩን ሕይወት በመሠረታዊነት የሚለውጥ ሞዴል የገጠር መንደሮች ግንባታ ወይም «የገጠር ኮሪደር ልማት»ን ይፋ አድርገዋል።
የዚህ ሀገራዊ ውጥን ዋና ዓላማ አርሶ አደሩን ከጭስና ከጤና እንክብካቤ እጥረት በማላቀቅ፣ እንደ ሶላርና ባዮጋዝ ያሉ አኗኗርን የሚያቀልሉ አረንጓዴ ቴክኖሎጂዎችንና ዘመናዊ መኖሪያ ቤቶችን ተደራሽ ማድረግ ነው።
እንዲሁም የተበታተኑ ሰፈሮችን በሞዴል መንደሮች በማደራጀት የትምህርት፣ የጤና፣ የመስኖ እና የንጹሕ ውኃ አቅርቦቶችን ማመቻቸትና የገጠሩን ምርታማነት ከገበያ ጋር በማገናኘት ዘላቂ የኢኮኖሚ እድገት ማስመዝገብን ታሳቢ ያደረገም ነው።
በከተማ ደረጃ ያሉትን አገልግሎቶች በገጠር ማኅበረሰብ ዘንድ በማቅረብ ከገጠር ወደ ከተማ የሚደረግ ፍልሰትን መቀነስም ሌላኛው ዓላማ ነው።
በአሁኑ ወቅት ይህ ጥረት በተለያዩ ክልሎች በተጨባጭ ወደ ሥራ ተተርጉሟል። በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል «ሐማሳ ሞዴል መንደር» የመስኖ ልማትና ዘመናዊ መኖሪያ ቤቶችን አጣጥሞ የያዘ ሰፈር ተገንብቷል።
በሲዳማ ክልል «ማጪሾ ቀበሌ» አርሶ አደሩን ከጭስ ያላቀቀ ጽዱ መንደር ሲፈጠር፣ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ «ጉራፈርዳ ወረዳ» ደግሞ አቅመ ደካሞችንና አርሶ አደሮችን ያካተቱ ሞዴል ቤቶች ተገንብተዋል።
በተጨማሪም በአማራ ክልል በጎንደር ዙሪያ «ሳይና ሳቢያ ቀበሌ» እንዲሁም በኦሮሚያ ክልል በወንጪና ጅማ አካባቢዎች ተመሳሳይ የገጠር ኮሪደር ልማቶች በተስፋፋ ሁኔታ እየተከናወኑ ይገኛሉ።
በገጠር የሚገነቡ ሞዴል መንደሮቹ ቀላል ወጪ በሚጠይቁና በአካባቢው በሚገኙ ግብዓቶች የሚገነቡ ከመሆናቸውም በላይ አርሶ አደሩ ጤናማ እና ክብር ያለውን ህይወት እንዲኖር የሚያስችሉ በመሆናቸው፤ የተስተካከለ ኑሮን እና ከተሜነትን ወደ ገጠር ያመጣል ።
በአጠቃላይ፣ የገጠር ኮሪደር ልማት የገጠሩን ማኅበረሰብ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ መዋቅር በመቀየር፣ ኢትዮጵያ የያዘችውን ሁለንተናዊና አቃፊ የብልፅግና ጉዞ ለማፋጠን የታለመ መሠረታዊ ሀገራዊ ሽግግር ነው።
በቴዎድሮስ ሳህለ

2 months ago
“ታሪክ በትዝታ ላይ የተጫነ ሸክም አይደለም-የነፍስ መገለጥ እንጂ”
ጋዜጠኛ ዮናስ አየለ እንደጻፈው
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ከአሚኮ ጋር ያደረጉትን ቃለምልልስ አዳምጬ እንደጨረስኩ በቃለ ምልልሱ በርዕሰ ጉዳይ ደረጃ ጎልተው ከወጡ ዋና ዋና ጭብጦች መካከል አንዱ ነገረ ታሪክ እንደሆነ ተሰምቶኛል፡፡ ታሪክ-የሀገር ውስጥና የውጭ፤ የሩቅና የቅርብ ዘመን! ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቃለ ምልልሳቸው ያንጸባረቁትን ሚዛናዊና አምክኖአዊ የታሪክ እይታና ድምዳሜያቸውን አለማድነቅ ንፉግነት ነው፡፡ የአሥራ ዘጠነኛው ክፍለ ዘመን እንግሊዛዊ የታሪክ ጸሐፊና ፖለቲከኛ ሎርድ አክተን “History is not a burden on the memory but an illumination of the soul” ብሎ ሲጽፍ “ታሪክ የነፍስ መገለጥ እንጂ በትዝታ ላይ የተጫነ ሸክም አይደለም” ማለቱ ነበር፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቃለ ምልልሳቸው ያነሷቸው የታሪክ አንኳር ጉዳዮች እስከዛሬ ድረስ በሀገራችን የታሪክ አጻጻፍ(Historiography) እና በሕዝባዊ ትርክቶቻችን(በሚዲያዎችን ጭምር) በሚገባቸው ልክ ያልተወሱ፤ ቢወሱም ፈራ ተባ እየተባሉ የሚጠቀሱ፤ አለፍሲልም ባልተገባ የፖለቲካ እይታ ደንቃራ ተደርገው የተወሰዱ የታሪክ ግርዶሽ(eclipse of the history) ሆነው የኖሩ ስብራቶቻችን ነበሩ፡፡ ከነዚህ ቁልፍ ጉዳዮች መካከል ዋነኛዎቹ አንዱ የሕዝቦች ትስስር እና መስተጋብር ታሪክ ሲሆን ሌላኛው በአገረ መንግስት ምሥረታ ውስጥ የሸዋ ጂኦ-ስትራቴጂካዊ ሚናን የተመለከቱት ናቸው፡፡
በመጀመሪያ የአማራና የኦሮሞ ሕዝቦች በኩታ ገጠም ቀዬዎቻቸው እና የታሪክ እድል በፈጠረላቸው የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚና የባህል አጋጣሚዎች እንደሌሎች ማህበረሰቦች ሁሉ መጋባት መዋለዳቸው፤መተሳሰር መዋሀዳቸው ሀቅ የመሆኑን ያህል የታሪክ ጥናት እና የትርክቶቻችን ማጠንጠኛ አለመሆናቸው ይታወቃል፡፡ ከዚህ በባሰ ሁኔታ ደግሞ በነገሥታቱ መካከል የነበረው የፖለቲካ ጋብቻና የመሪዎቻችን ማህበራዊ መሠረት ጉዳይ ነውር እስኪመስል በእውነታው ልክ ሳይጠናና፣ሳይነገርለት ዘመናት አልፈዋል ፡፡ በሌላ በኩል በሸዋና አካባቢው ለረዥም ዘመን የኖሩ ሕዝቦች በአገረ መንግሥት ግንባታ ሂደት የተጫወቱት ሚናና የሚጋሩት ቀደምት የሥልጣኔ ባለቤትነት (ታሪክ ሰሪነት-Agency) ግጥምጥሞሽ በሀገር መሪ ደረጃ መወሳታቸው እጅግ ጉልህ ፋይዳ ያለው ጉዳይ ነው ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቃለ ምልልሳቸው ያነሷቸው የታሪክ እውነታዎች ያለጥርጥር ታሪካችንንና የታሪክ ምልከታችንን ደጋግመን መመርምር እንዳለብን የሚያስገነዝቡና የወገንተኝነት ጥያቄ በሚነሳባቸው ሃይማኖታዊ የታሪክ ምንጮች እንኳን የተቀመጡ ገሃድ እውነታዎች ናቸው፡፡ መመርመር ለሚፈልግ አጥኚ እነዚህ የታሪክ እውነታዎች በየነገሥታቱ ዜና መዋዕሎች (የዐጼ አምደ ጽዮን፣ ዐጼ ሱስንዮስ፣የዐጼ ገላውዲዮስ፣ የዐጼ ሠርጸ ድንግል ወዘተ)፤ የሃይማኖት ሰነዶች፣ የታሪከ ነገሥት ቅጂዎች፣ ወደ ኢትዮጵያ መጥተው የነበሩ አውሮፓውያን ተጓዦችና ጸሐፊያን (ፍራንስስኮ አልቫሬዝ፣ ፔድሮ ፔዝ፣ ማኑኤል አልሜዳ፣ ጄሮኒሞ ሎቦ፣ ጀምስ ብሩስ፣ ኮንቲ ሮሲኒ ወዘተ ) መዝግበው በተውልን ሰነዶች ሰፍረው የምናገኛቸው፤ ከትውልድ ወደ ትውልድ ሲተላለፉ የኖሩ ቱባ መረጃዎች ናቸው፡፡
ፍራንሲስኮ አልቫሬዝ የተወልን የጽሑፍ ሰነድና ሌሎች ሀገርኛ የቃል መረጃ ምንጮች ዐፄ ልብነድንግል(1498-1532 ዓ.ም.) እንደ መሪ የአማራና የኦሮሞ ብቻ ሳይሆን ምናልባትም የሌሎች ሕዝቦችም ማህበራዊ ዳራ የነበራቸው ንጉሠ ነገሥት እንደሆኑ የሚያስረዱ ሲሆን አልቫሬዝ የንጉሱ የእናት ወንድም የነበሩት አጎታቸው ዶሪ ባህረ ነጋሽ ኦሮሞ እንደነበሩና ባህረ ነጋሽ ዶሪ ሲሞቱ ሥልጣኑ በቀጥታ ወደልጃቸው ቡሎ መሸጋገሩን ጭምር በአይኑ ያየውን ጽፏል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በትኩረት መታየት የሚገባው ጉዳይ ስለዐጼ ልብነ ድንግል የጦር አዛዦች የተነገሩ የቃል መረጃዎች ናቸወ፡፡ ከእነዚህ መካከል የንጉሠ ነገሥቱ ሠራዊት የቦረንትቻ ባሕል ያውቅ እንደነበር በተክለጻዲቅ መኩሪያ መጻፉና ከዐጼ ልብነድንግል የጦር አዛዦች አንዱ የነበረው ቱሉ ደገልሀን በመራው ከኢማም አሕመድ ጋር የተካሄደ ጦርነት የዐጼው ጦር ሲያፈገፍግ ንጉሠ ነገሥቱ “ሁሉም ቢፈራ ቱሉ እንዴት ፈራ? ” ማለታቸው ስለሠራዊታቸው ሥብጥር የሚነግረን ነገር አለ፡፡
ኦቶማን ቱርኮችን እና የዘመኑ ተላላኪዎቻቸውን ለመዋጋት የንጉሠ ነገሥቱ ሠራዊት አንድ አካል ሆነው እስከ ኤርትራ ድረስ ዘምተው ስለነበሩ የኦሮሞ ተዋጊዎች ተጋድሎ የዐጼ ሠርጸድንግል(1542-1590 ዓ.ም.) ዜና መዋእል በግልጽ አስፍሯል፡፡ እነዚህ የኦሮሞና የሌሎች ሕዝቦች ተወላጅ ወታደሮች ትግራይ እንጢጮ አካባቢ ያካሄዱትን አውደ ውጊያ ዜና መዋዕሉ ይተርካል፡፡ ለመንግሥታቸውና ለሀገራቸው እስከባሕር ጠረፍ ድረስ ዘምተው ዋጋ መክፈላቸውም ተመዝግቧል፡፡ የዐጼ ሱስንዮስ(1607-1632 ዓ.ም.) ዜና መዋእል እና በዘመኑ ኢትዮጵያ መጥተው የነበሩ የአውሮፓ(የፖርቱጋል) ተጓዦች የጻፏቸው የመረጃ ምንጮች ንጉሠ ነገሥቱ ግንደበረት፣ሐምቦና አካባቢው ቤታቸው እንደነበር፤ አጎታቸው ለማሞ እንደሚባል፣ ወላጅ እናታቸው(ሐመልማል ወርቅ) የአዛዥ ኩሎ ልጅ የነበረች፤ የዚሁ የሐመልማል ወርቅ ጎሳ ተወላጅ የሆነ ቡኮ የተባለ ኦሮሞና ሠራዊቱ ለአባይ ቅርብ የሆነች ምዕራብ ሸዋ ላይ ዐጼ ሱስንዮስ ሲያገኙት የነበረውን ደስታና የፍቅሩን ጽናት ዜና መዋዕሉ ሳይሰስት ጽፎታል፡፡ ዐጼ ፋሲል(ከ1632 እስከ 1667 ዓ.ም.) አባቱ ሱስንዮስ እናቱ የወሎ ቃሉ ሰው(እቴጌ ሥልጣን ሞገሳ የሚል ስም የተሰጣት) እንደሆነች የታሪክ ምንጮች ያስረዱናል፡፡ በ1620ዎቹ ዓመታት ጀምሮ በኢትዮጵያ ይኖር የነበረው ፖርቱጋላዊ ቄስ ጄሮኒሞ ሎቦ ስለዐጼ ፋሲል እናትና ኦሮሞ ዘመዶቻቸው በአይን ምስክርነት የሚያውቀውን ጽፏል፡፡ የእቴጌ ሥልጣን ሞገሳ አያት ስለብዝሀ ሃይማኖት አስፈላጊነት የነበራቸውን ግልጽ ፖሊሲ ጭምር ሎቦ ዘግቦታል፡፡ የዐጼ በካፋ(1721-1730 ዓ.ም.) እና የዐጼ ኢዮአስ(1747-1761 ዓ.ም.) ጎንደር መቼም ለሕዝቦች ውህደትና ትስስር ጥሩ ማሳያ ነበረች፡፡ የየጁ ኦሮሞ ገዢ የነበረው የአሚቶ ሴት ልጅ ዝነኛዋ ውቢት ልጇ ዐጼ አዮአስ ነበር፡፡ ኢዮአስ ከኦሮሞ አጎቱ ከደጃች ሉቦ ጋር ሥልጣኑን በጎንደር እንዴት እንዳጸና፤ የቤተ መንግሥቱም የሥራ ቋንቋ አፋን ኦሮሞ እንደነበረ የንጉሠ ነገሥቱ ዜና መዋዕልና በጀምስ ብሩስ ቅጽ ሁለት መጽሀፍ የተመዘገቡ የታሪክ መረጃዎች ያስረዱናል፡፡
መነሻውን ወሎ በማድረግ ጎንደር ጸንቶ የኖረው የየጁ ሥርወ መንግሥት(ወረ ሼኮች) መሥራቾች የመርሳው አባ ጌትዬ፣ የልጃቸው ጓንጉል አባ ሴሩ እንዲሁም የልጅ ልጃቸው የራስ አሊ ጓንጉል(አሊ ትልቁ) ታሪክ በኢዮአስ ዜና መዋዕል፣ በጀምስ ብሩስ መጽሐፍና በሌሎች በርካታ ሰነዶች ታሪካቸው ተዘግቧል፡፡ በኋላ ላይ በሽፈራው በቀለ(ፕሮፌሰር) እና ሞላ ትኩዬ የቀረቡ ጥልቅ ጥናቶች ይህን እውነት በዝርዝር ያስረዱናል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቃለ ምልልሳቸው እንደጠቀሱት የእነዚህ መሪዎች የፖለቲካ ጋብቻ ታሪክ የሚያሳየን በሄዱበት አገር ሁሉ የሕዝቦች ትሥሥር እና የፖለቲካ ጋብቻ የኖረ ታሪካችን እና የጉልበታችን ምንጭ እንደነበረ ነው፡፡ በዳግማዊ ዐጼ ቴዎድሮስ ዘመን የተጻፉ የታሪክ ሰነዶች የወሎዋ ገዢ ወርቂቱ ወዳጆ(የማመዶች ሥርወ መንግሥት መሪ የኢማም አሊ አባ ቡላ ባለቤት) ንጉሥ ምኒልክ ከመቅደላ እስር ቤት እንዲያመልጡ ያደረጉ፤ አጃቢ ሠራዊት አሰማርተው ምኒልክን እስከሸዋ የሸኙ እንደነበሩ በዋናነት ከጸሓፌ ትእዛዝ ገብረ ሥላሴ ታሪከ ዘመን ዘ ዳግማዊ ምኒልክ ዜና መዋዕል እና በመቅደላ አምባ እስር ላይ የነበሩ አውሮፓውያን ከጻፏቸው መረጃዎች እንረዳለን፡፡
ሥልጣኔዎቻችን ሁሉ ተደምረን ያሳካናቸው እንደሆነ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቃለ ምልልሳቸው አንስተዋል፡፡ የዐድዋ ዘመቻና ድሉ ለዚህ አንዱ ማሳያ እንደሆነ ተጨባጭ የታሪክ ምንጮች ያስረዱናል፡፡ በ1888 ዓ.ም. ለዓድዋ ዘመቻ ከመላው ኢትዮጵያ የተመመው ሠረዊት ወፍላ ላይ የነበረው ሠልፍ የንጉሠ ነገሥቱ ዜና መዋዕል እንኳን እንዲህ ይገልጸዋል፡፡ “የመኳንንቱ የጦር መሣሪያ፣ወርቁ፣ ጣፋ፣ ብሩ፣ ሙጣው፣ ጫሜው፣ ሎሚታውና ኩፊታው፣ ከሌቻው፣ ወርቅ ለምዱ እንደጸሐይ ሲያበራ ዋለ፡፡” እንደጸሐይ የበራውን ሕብረ ባሕልና ሕብረ ማንነት ትርክቶቻችን በልኩ አጉልተው ያውቃሉ?
ሸዋና አካባቢው(ወሎን ጨምሮ) እንደ አንድ ጂዞ ስትራቴጂ ሥፍራ የሕዝቦች ውህደትና ትስስር መሠረት ሆኖት የመልክዓ ምድር መገኛው ለግብርና እና ለውጭ ንግድ የተመቸ በመሆኑ በኢትዮጵያ አገረ መንግሥት ግንባታ ታሪክ ውስጥ ቁልፍ ቦታ ይዞ መኖሩን ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቃለ ምልልሳቸው መግቢያ አስታውሰውናል፡፡ ሸዋና አካባቢው ከመንግሥታት ምስረታ ጋር በተገናኘ ከዘጠነኛው አንስቶ እስካሁን ያለው ረዥም የታሪክ ጉዞ በርግጥም ሊነገር፣ ሊተነተን የአደባባይ ትርክት አካል ሊደረግ የሚገባው እውነት ነው፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከሸዋ ሡልጣኔት ምስረታ( እ.አ..አ.896 ዓ.ም.) እስከ ዓድዋ ድል(1888 ዓ.ም.) ሥላወሷቸው የአርጎባ(የወላስማ/ወሊ አስማ ሥርወ መንግሥት)፣ የአማራ(ሰለሞናዊ ሥርወ መንግሥት)፣ ኦሮሞ(ቱለማው በተለይ)፣ወርጂ፣ ጉራጌ፣ ጋፋት፣ ወዘተ ሕዝቦች ትስስርም ይሁን የፖለቲካ ጋብቻ የተመለከተ ታሪክ ከበቂ በላይ የታሪክ ማስረጃ ምንጮች ቢኖሩንም በታሪክ ግርዶሹ ምክንያት የወል ትርክት አካል መሆን አልቻለም፡፡
ኤንሪኮ ቼሩሊ ከሐረር አግኝቶ ያሳተመው በአረብኛ የተጻፈው የሸዋ ሡልጣኔት ዜና መዋዕል እንደሚያመለክተው ሡልጣኔቱን እ.አ.አ. በ896/7 የመሰረቱት የማህዙሚ ጎሳ አባላት ናቸው፡፡ መንግሥታቸውም ከ9ኛው እስከ 13ኛው ክፍለ ዘመን ድረስ በተከታታይ በገዙ አሥራ አራት ሱልጣኖች እንደጸና የታሪክ መረጃ ምንጮች ያመለክታሉ፡፡ የሸዋ ሙስሊም ሡልጣኔቱ መቀመጫ ከተማ ከአዲስ አበባ በስተሰሜን ምሥራቅ 70 ኪሎ ሜትር ላይ የምትገኝ ወለላ የተባለች ሥፍራ እንደነበረች የጆርጅ ደብሊው ቢ ሀንቲንግፎርድ(1989) ጥናት ያመለክታል፡፡ የማህዙሚ ሥርወ መንግሥት ከመጨረሻዎቹ መሪዎች አንዱ የነበረው ሡልጣን ድልመራህ ወርጂዎች የይኖሩበት በነበረው አካባቢ በ1270ዎቹ በነበረ የርስ በርስ ጦርነት ድል ሳይቀናው ሲቀር ሕይወቱን ለማትረፍ ዐጼ(የአማራ ገዥ?) እንደሄደ ይህው የአረብኛ ዜና መዋእል ያስረዳል፡፡ የማህዙሚዎች የሸዋ ሡልጣኔት የተተካው በዋናነት የአርጎባዎች አገር በሆነው ይፋት(ዊፋት) ላይ በወላስማዎች ነበር፡፡ ወላስማዎች ከአጎራባቾቻው ጋር እየተጋቡ፣ እየተስማሙም እየተጋጩም የይፋት ሡልጣኔትን ከ13ኛው እስከ 15ኛው ክፍለ ዘመን ከሸዋ እስከ ምሥራቃዊ የኢትዮጵያ ጠረፍ እንዳስተዳደሩ ስፍር ቁጥር የሌለው የሰነድ( የኢብን ካልዱን ተማሪ የነበረው አል ማቅሪዚ ጽሑፍ- ኪታብ አል ኢልማም)፣ የአርኪዮሎጂና የቃል መረጃ ምንጮች አሉ፡፡
መነሻውን ሰሜን ሸዋ እና ደቡብ ወሎ ያደረገው የክርስቲያኑ ሰሎሞናዊ ሥርወ መንግሥት በአካባቢው ያሉ ሕዝቦች ተዋህደው ከ13ኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ በጋራ የመሠረቱት እንደሆነ አያጠያይቅም፡፡ አማራዎች፤ አርጎባዎች፣ ወርጂዎች፣ ጋፋቶች፣ ጉራጌዎች እና ኦሮሞዎች፣ አፋሮች፣ ሐረሪዎች ወዘተ በዚህ የሸዋ መንግሥታት የተጽዕኖ ምህዳር(Orbit) ውስጥ እንደሚገኙ ዜና መዋእሎች፣ የሃይማኖት ሰነዶች፣ የአርኪዮሎጂ ማስረጃዎች ከትውልድ ወደ ትውልድ ሲተላለፉ የኖሩ የቃል መረጃ ምንጮች ያመለክታሉ፡፡ ለምሳሌ ታደሠ ታምራት(ፕሮፌሠር) ከ13ኛው እስከ 16ኛው ክፍለ ዘመን የቤተ ክርስቲያንና መንግሥትን ግንኙነት ታሪክ ባጠኑበት መጽሐፋቸው የገላንና ያያ ሰዎች ሸዋ ውስጥ በ13ኛው ክፍለ ዘመን በኦዳ ዛፍ (ኮቢል የሚባል ዋርካ) ሥር ሃይማኖታዊ ሥርዓት ይፈጽሙ እንደነበር ገድለ አቡነ ቀውስጦስን ጠቅሰው ጽፈዋል(ገጽ 184)፡፡ ሸዋ የባለ ብዙ ማንነት ሕዝቦች ሀገር ከመሆኗ ባሻገር በ16ኛው ክፍለ ዘመን የተከናወኑ ዐበይት ጉዳዮች ላይ መረጃ የተወልን መነኩሴው አባ ባህሪይ እንደገለጸው “ሸዋ የመንግሥት ሀገር ነች” (ገጽ 130)፡፡ በየዘመናቱ ከሸዋ የተነሱ የፖለቲካ ኃይሎች፣ ፈረሰኛ ሠራዊታቸውን ይዘው በሰሜን እስከ ኤርትራ(በዐጼ ሠርጸ ድንግል ዘመን- የኤርትራዋ ባሬንቱ የዚህ የታሪክ ሂደት ውርስ አይደለችም ማለት አይቻልም፡፡) በምሥራቅ እስከ ዘይላ(ከዐጼ አምደጽዮን እስከ ገላውዲዮስ ዘመን)፣ በምዕራብ እስከ ሱዳን ፋዞግሊ(ዐጼ ሱስንዮስ ዘመን) በደቡብ እስከ ሞያሌ ተንቀሳቅሰው በአገረ መንግሥት ግንባታ ሂደት ውስጥ ቁልፍ ሚና ተጫተዋል፡፡
እነዚህ የሸዋ እና አካባቢው ሕዝቦችና ገዢዎች ትልቁን ንቅናቄያቸውን ያደረጉት ግን በ19ኛው ክፍለ ዘመን እንደሆነ ይታወቃል፡፡ ዐጼ ምኒልክና ራስ ጎበና ዳጬ የቱለማ ኦሮሞ፤ የሸዋ አማራ እና የሌሎችም ውህድ የሆነ ጦራቸውን አዝምተው ወሎ ወግተው ወረኢሉን የመንሥታቸው መቀመጫ ያደረጉት አርሲ፣ወለጋ፣ከሐረር ከመዝመታቸው በፊት ነበር፡፡ የመጫ ኦሮሞ ተወላጁን የጎጃሙን ንጉስ ተክለሃይማኖት(አዳል ተሰማ) በቱለማው መሪ ራስ ጎበና ዳጪ እምባቦ ላይ ያስገበሩት የጂኦ ፖለቲካዊ እና የሕዝቦች ትስስር እድሎች ጉልበት ፈጥሮላቸው፤ ኃይል አጎናጽፏቸው እንጂ በአጋጣሚ አይደለም፡፡ በርግጥ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የፖለቲካችን ደንቃራነት የፈጠረውን የታሪክ ግርዶሽ ያሸነፉ ፋና ወጊ ጥናቾች መውጣት ጀምረዋል፡፡ አንዱ “Invisible Actors: The Oromo and the Creation of Modern Ethiopia(1855-1913)” በሚል ርዕስ በብሪያን ጀምስ ዬትስ(2002) በኤሊኖይስ ዩኒቨርሲቲ ከተጠናው እጅግ ጠቃሚ የዶክትሬት ዲግሪ ማሟያ ጥናት ሲሆን ሌላው የደቻሳ አበበ(ዶ/ር) ጎበና ወታደራዊና ፖለቲካዊ ሕይወት ነው፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቃለ ምልልሳቸው የዘመናዊት ኢትዮጵያን እውን መሆን ያለ ምኒልክና ያለ ጎበና እንደማይታሰብ ሲጠቅሱ ይህንን እውነታ ማጉላታቸው ይመስለኛል፡፡
የሕዝቦች ትስስርና የፖለቲካ ጋብቻ በአማራና በኦሮሞ ሕዝብ መስተጋብር ብቻ የታጠረ አልነበረም-ሊሆንም አይችልም፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ ባህልና ሥልጣኔ መጋመዱ ረቂቅ ነው፡፡ ከጥንታዊ አክሱም ዘመን ጀምሮ በዝነኞቹ የአክሱም መቃብር ሀውልቶች እና በላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት ላይ ከምናገኛቸው የኪነ ሕንጻ ትእምርቶች(Symbols) መካከል የውሸት በሮች (False Doors) እና የውሸት መስኮቶች(False windows) የሙታን መንፈስ(ኤከራ) መመላለሻ እንደሆኑ በጥናት የተረጋገጠ ነው (ቢትራይስ ፕሌይን Annales d'Éthiopie 1965) ፡፡ ይህ የኤከራዎች መመላለስና የመነጋገር ባህል እና እምነት ከደቡባዊ ግብጽ አንስቶ እስከ ሰሜን ኬንያ ድረስ በሚኖሩ የኩሽ ሕዝቦች በሰፊው የሚታወቅ ረዥም ዘመን ያስቆጠረ ልምምድ ነው፡፡
ሌላው በልኩ ያልተጠና እና በትርክቶቻችን ውስጥ ትኩረት ያልተሰጠው በሕዝቦች መካከል ያለ ሥልጣኔ ትስስር ታሪክ የእያንዳዱን የዛግዌ ነገሥታት የሥልጣን ዘመናትን የተመለከተ ነው፡፡ ከታሪክ ነገሥት፣ ከልዩ ልዩ ዜና መዋዕሎች፣ ከፖርቱጋል ተጓዦች(ፓኤዝና አልሜዳ) ከብሪቲሽ ሙዝየም እንዲሁም ከኮንቲ ሮሲኒ የተገኙት ምንጮች የሚረጋግጡት የሁሉም የዛግዌ ዐጼዎች( ከአንድ ሁለቱ በስተቀር) የሥልጣን ዘመን 40፤40 ዓመታት ነበር፡፡ ይህ ጉዳይ በኦሮሞ የገዳ ሥርዓት የአንድ ትውልድ የሥልጣን ዑደት ጋር አንድ አይነት የሆነው በአጋጣሚ ነው ወይስ ዛግዌዎች እና ኦሮሞዎች የኩሽ ሕዝቦች በመሆናቸው ቀዳሚ ከሆነው የጋራ ሥልጣኔያቸው የሚቀዳ የአስተዳደር ሥርዓት ነው? እነዚህስ ሀቆች የወል ትርክቶቻችን መመሆን አለመቻላቸው በፖለቲካ ደንቃራነት የተፈጠረ የታሪክ ግርዶሽ(eclipse of history) እንጂ ሌላ ምን ሊባል ይችላል? በላሊበላ አብያተ ክርስቲያናትና እና በሸዋ በሚገኘው የአዳዲ ማርያም ቤተ ክርስቲያን ኪነሕንጻ መካከል ያለው ፍጹም ተመሳሳይነት ምንጩ ምንድነው? ሊጠና፣ ሊነገር ልንማርበት ይገባል፡፡
በርግጥም ታሪካችን ትዝታችን ላይ የተጫነ ሸክም ሳይሆን የነፍስ መገለጥ ነው የሚያሰኘው የሕዝቦች ትሥሥር፣ ውህደት የሥልጣኔ መጋራትና መወራረስ ታሪክ መታወቁ መንፈስን ሃርነት ማውጣቱ ይመስለኛል፡፡

የጎንደር ፋሲለደስ ባህል ኪነት አለም አቀፍ አልበም በይፋ ተመረቀ
#ethiopia | የጎንደር ፋሲለደስ ባህል ኪነት የባህላዊ ሙዚቃ አልበም ትናንት በጎንደር ከተማ በተካሄደ ደማቅ የምርቃት ሥነ-ሥርዓት በይፋ ተመረቀ።
በሙዚቃዊ፣ በሰላም ኢትዮጵያ እና በጎንደር ከተማ አስተዳደር ባህልና ኪነጥበብ ቢሮ ትብብር የተዘጋጀው አልበም፣ የጎንደርን እና የአማራ ክልልን የባህል ሙዚቃ ለአለም አቀፍ አድማጮች ለማስተዋወቅ ያለመ መሆኑ ተገልጿል።
በምርቃት ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የመንግስት ተወካዮች፣ አርቲስቶች፣ የባህል ባለሙያዎች፣ አጋር ተቋማት፣ የሚዲያ ተወካዮችና በርካታ የጥበብ አፍቃሪዎች ተገኝተዋል። የጎንደር ፋሲለደስ ባህል ኪነትም የቀጥታ የሙዚቃና የውዝዋዜ ትርኢት በማቅረብ ታዳሚዎችን አስደስቷል።
በአልበሙ ውስጥ የቡድኑ ድምፃውያን ሕይወት እያሱ፣ እህተነሽ ፋንታ፣ ሰሎሞን ጥጋቤን ጨምሮ ሌሎች የቡድኑ አባላት ተሳትፈዋል።
የሙዚቃ ዳይሬክተርነቱንም ሙዚቀኛ ምሳሌ ለገሰ መርተዋል። አልበሙ በባህላዊ የኢትዮጵያ መሳሪያዎች የተቀናበረ ሲሆን፣ በአዲስ አበባ ተቀርጾ የድምፅ ማስተካከያውና ማስተሪንጉ በጣሊያን በሚገኘው ማክስሳውንድ ቫይብ ስቱዲዮ ተከናውኗል።
በዝግጅቱ ላይ የጎንደር ፋሲለደስ ባህል ኪነትን ከ50 ዓመታት በላይ የሚያስቆጥር ታሪክ የሚያሳይ የፎቶግራፍ አውደ ርዕይም ለእንግዶች ቀርቧል። አውደ ርዕዩ የቡድኑን እድገት፣ ለኢትዮጵያ ሙዚቃና ትዕይንት ጥበባት ያበረከተውን አስተዋፅኦ እንዲሁም ያፈራቸውን ታዋቂ አርቲስቶች የሚያስታውሱ ታሪካዊ ፎቶግራፎችና ሰነዶችን አካቷል።
በዝግጅቱ ላይ የሙዚቃዊ ተወካይ ሲሳይ መንግስቴ፣ አልበሙ ከመደበኛ የሙዚቃ ስራ በላይ የኢትዮጵያን የባህል ሀብት ለማስጠበቅና ለአለም አቀፍ ተደራሽነት ለማብቃት የተደረገ ኢንቨስትመንት መሆኑን ገልጸዋል። ይህ ስራ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ በዓለም አቀፍ የሙዚቃ ገበያ ተወዳዳሪ ለማድረግ እና ለአዲስ ትውልድ ለማስተላለፍ ጠቃሚ እርምጃ መሆኑን ጠቁመዋል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #gondarfasilidesculture #የጎንደርፋሲለደስባህልኪነት #ethiopianmusic #ethiopianculture #gondar #traditionalmusic #ethiopia

(ዘ-ሐበሻ ዜና) በአማራ ክልል በቀጠለው አውዳሚ ግጭት እና አለመረጋጋት መዋቅር ውስጥ ሕጻናት ላይ የሚፈጸመው ሰብዓዊ ጥቃት ወደ አሰቃቂ ምዕራፍ መሸጋገሩ ይፋ ሆነ። የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ የክልሉን የ2018 በጀት ዓመት የእቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ለክልሉ ምክር ቤት ባቀረቡበት ወቅት፣ በግጭቱ እና በወቅታዊው ሁኔታ ውስጥ በርካታ ሕጻናት መደፈራቸውን እና የ900 ሕጻናት የአስገድዶ መድፈር ጥቃት ጉዳይ በችሎት መታየቱን በይፋ አረጋግጠዋል።
ይህ ይፋዊ መግለጫ የግጭቱን አስከፊ ሰብዓዊ ዋጋ እና በተለይም አቅመ ደካማ የሆኑ ሕጻናት ላይ እየደረሰ ያለውን የሰብዓዊ መብት ረገጣ እጅግ አሳሳቢነት ያሳያል። ይሁን እንጂ ርዕሰ መስተዳድሩ ከቀረቡት አጠቃላይ አሃዞች መካከል በግጭቱ አውድ እና በቀጥተኛ ጦርነት ተጽዕኖ ብቻ ስንት ሕጻናት የጥቃቱ ሰለባ እንደሆኑ በግልጽ አለመናገራቸው፣ ችግሩ ከተገለጸው በላይ የሰፋ እና የከፋ ሊሆን እንደሚችል የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾችን ስጋት አባብሶታል። በግጭት ቀጠናዎች ውስጥ የሚፈጸሙ የፆታዊ እና የጾታ-ተኮር ጥቃት ወንጀሎች ሪፖርት ሳይደረጉ የሚቀሩት ጉዳዮች እጅግ እልፍ መሆናቸው ይታወቃል።
በሌላ በኩል በባህር ዳር፣ በጎንደር እና በደሴ ከተሞች የጥቃቱ ሰለባ ለሆኑ ሕጻናት ማገገሚያ የተቋቋሙ ማዕከላት በበቂ ሁኔታ መደራጀታቸውን እና ድጋፍ እየሰጡ መሆናቸውን ርዕሰ መስተዳድሩ ገልጸዋል። ቢሆንም፣ የደረሰውን ጥልቅ ማህበራዊ፣ የጤና እና የሥነ-ልቦና ጉዳት ለመቋቋም የተዘረጋው መዋቅር አሁን ባለው የሀገሪቱ እና የክልሉ አስቸጋሪ የጸጥታ ሁኔታ ውስጥ ምን ያህል አቅም አለው የሚለው ጥያቄ በብዙዎች ዘንድ ይነሳል።
በግጭት ውስጥ የሚገኙ ሕጻናትን ከእንዲህ ዓይነቱ ዘግናኝ ጥቃት መጠበቅ፣ አጥፊዎችን ለህግ ማቅረብ እና ሰለባዎችን በዘላቂነት ማቋቋም የመንግስት ቀዳሚ ኃላፊነት ቢሆንም፤ የህግ የበላይነት በተሸረሸረበት እና ተቋማት ፈተና ውስጥ በወደቁበት አካባቢ የፍትህ ሂደቱ ፍጥነት እና አጋዥነቱ ጥያቄ ውስጥ ወድቋል። ይህ ሪፖርት የግጭቱ ሰለባዎች ዋነኛ ተጠቂዎች ህጻናት እና ሴቶች መሆናቸውን በድጋሚ ያረጋገጠ እና አፋጣኝ የመንግስትና የህብረተሰብ ጣልቃ ገብነትን የሚጠይቅ ብሔራዊ አሳሳቢ ጉዳይ ሆኗል።

ጎንደር ዩኒቨርሲቲ የዶ/ር በርናንድ እና ሲ/ር እማዋይሽ ጅምር ሆስፒታል ለሕዝብ አገልግሎት እንዲውል ስምምነት አደረገ
#ethiopia | በጎንደር ከተማ የተጀመረው የዶክተር በርናንድ አንደርሰን እና የሲስተር እማዋይሽ ገሪማ መታሰቢያ ጅምር ሆስፒታል ለኢትዮጵያ ህዝብ የጤና አገልግሎትና የምርምር ማዕከል ሆኖ እንዲቀጥል ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ከኑዛዜ ወራሾች እና ተጠቃሚዎች ጋር የጋራ መግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ።
ስምምነት በ2008 ዓ.ም ተጀምሮ የነበረውን ሀገራዊ አላማ ከውልና ማስረጃ እንዲሁም ከእንደራሴው አቶ ዳዊት ደርበው ጋር በመተባበር ዳር ለማድረስ ያስቻለ ምዕራፍ መሆኑ ነው።
በተደረገው ስምምነት መሠረት ሆስፒታሉ የማይሸጥ፣ የማይለወጥ፣ ቅርጽና ይዘቱ ሳይለወጥ እንዲሁም ስመ ንብረቱ ወደ ሌላ ሶስተኛ ወገን ሳይተላለፍ የለጋሾቹ የዘላለም መታሰቢያ ሆኖ እንዲኖር ዋስትና ይሰጣል።
የተከናወነው ስምምነት መሠረት ዩኒቨርሲቲው ህንጻውን አጠናቆ ለህዝብ የህክምና አገልግሎት፣ ለትምህርት እና ለምርምር ማዋል የሚችለውን ጠንካራ መሰረት የጣለ ሲሆን፣ በኑዛዜው የተገለጹት ተጠቃሚዎች መብቶችም ሙሉ በሙሉ እንዲከበሩ ተደርጓል።
በፊርማ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የተገኙት የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶክተር አሥራት አፀደወይን ለጋሾቹ ለህዝብ ጥቅም የለገሱት ይህ በጎ አድራጎት ለወደፊቱ ትውልድ ትልቅ አርአያ የሚሆንና የሀገሪቱን የጤና ዘርፍ እንዲሁም የህክምና ቱሪዝም የሚያሳድግ መሆኑን ገልጸዋል።
የወራሾችን በመወከል ንግግር ያደረጉት አቶ ዳዊት ደርበው እንደገለጹት፣ በዕለቱ የተገኙበት ዋና ምክንያት በሲስተር ማዋይሽ ገሪማ ኑዛዜ መሠረት የተጀመረውን ሆስፒታል አጠናቀው ወደ ተግባር ለማዋል እንደሆነ አስረድተዋል።
እርሳቸውም በኑዛዜው እንደራሴ በመሆን የተሰጣቸውን ሙሉ ስልጣን በመጠቀም ሥራውን ለማስፈጸም እንደተገኙ ገልጸው፣ ሁለተኛው ምክንያት ደግሞ ሲስተር ማዋይሽ በህይወት በነበረችበት ጊዜ ከጎንደር ዩኒቨርሲቲ ጋር አድርጋው የነበረውን ውል እንደገና በማነቃቃት የጀመሩትን ሂደት ለማጠናቀቅ መሆኑን አብራርተዋል።
ስምምነቱ ከተጠናቀቀ በኋላም ተሳታፊዎች የዶክተር በርናንድ አንደርሰን እና የሲስተር እማዋይሽ ገሪማ መታሰቢያ ሙዚየምን እንዲሁም የሆስፒታሉን ጅምር ግንባታ በጋራ ጎብኝተዋል።
#gondaruniversity #drbernardandsisteremawesh #gondar #ethiopia #healthcare #medicalresearch #legacy #publichealth

3 months ago
ጽናት
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ታሪካዊ የለውጥ ጉዞ
1947-2017
#ethiopia | የዶ/ር አሥራት ዓፀደወይን Asrat Atsedeweyn መጽሐፍ በጎንደር ከተማ እየተመረቀ ነው።
ይህ መጽሐፍ መታሰቢያነቱ ስጎንደር ዩኒቨርሲቲ ርስታቸወነ ስሰጡ 59 የጎንደር አርሶ አደሮች፧ እንዲሁም በተለያዩ ዘመናት በአመራርነት፤ በባለሙያነት፤ በሠራተኛነትና በአጋርነት አገልግለው ተቋሙን አሁን ላስበት ታላቅ ደረጃ ኣደረሱ ሞስንነ ባለውለታዎች በሙሉ ይሁን፡፡
***
ከመጽሐፉ ጀርባ (blurb)
ጎንደር የኒቨርሲቲ ኢትዮጵያ ካፈራቻቸው ዩኒቨርሲቲዎች በአንጋፋነት ተርታ የሚመደብ ነው:: በቅርቡም ሰባኛ ዓመቱንና የዩኒቨርሲቲው አስኳል የሆነውን ሆስፒታሉን መቶኛ ዓመት በደማቅ ሁኔታ መዘከሩ ይታወሳል። በዚህ የታሪክ አጋጣሚ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት የሆነው ዶ/ር አሥራት ዓፀደወይን እነሆ የዩኒቨርሲቲውን ታሪካዊ ጉዞ እርሱ ራሱ በተለያዩ የኃላፊነት እርከኖች ካከናወናቸው ተግባራት ጋር አዛምዶ የሚዘግብ፣ በጠንካራ መረጃ ላይ የተዋቀረ መጽሐፍ አቅርቦልናል።
በዚህም የዩኒቨርሲቲ ቆይታቸውን ከግለ ታሪካቸው ጋር አሰናስለው ለንባብ ያበቁትን የቀደምት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንቶችን ፈለግ ተከትሏል ማለት ይቻላል። የተቋሙ ታሪካዊ ጉዞ በስኬት የታጀበውን ያህል አያሌ ፈተዎችና ተግዳሮቶችም የተጋረጡበት ነበር። የመጽሐፉ ትልቁ ፋይዳም እነዚህን ስኬቶችና ተግዳሮቶች ነቅሶ በማውጣት ሰፊ ግንዛቤ መስጠቱ ላይ ነው:: በተለይም በደራሲው አመራር የተከናወኑትን P70/100 ዝክረ በዓል ዘርፈ ብዙ ዝግጅቶችና ክንዋኔዎች በዝርዝር ያትታል፤ ዘላቂ እርባናቸውንም ይጠቁማል። በመጨረሻም ከዩኒቨርሲቲ አመራር ተሞክሮው የቀሰማቸውን ትምህርቶች በተመሳሳይ ተቋም ግንባታ ላይ ላሉ ያካፍላል።
ባሕሩ ዘውዴ፣ የታሪክ ኤሜሪተስ ፕሮፌሰር አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ
***
የስኬታማ ተቋማትና የአገር ግንባታ በትውልዶች ቅብብሎሽ፣ በቁርጠኝነትና በመሪዎች እቅድ ላይይመረኮዛል። ዶ/ር አሥራት ዓፀደወይን በዚህ መጽሐፋቸው የጎንደር ዩኒቨርሲቲን የ7ዐ ዓመታት ጉዞ፣ በየዘመናቱ የነበሩ መሪዎችንና ባለድርሻ አካላትን አበርክቶ፣ እንዲሁም የራሳቸውን የኃላፊነት ዘመን ፈተናና ስኬት በጥልቀት አቅርበዋል። በከፍተኛ ትምህርት አመራርነት በነበረኝ የረጅም ጊዜ ኃላፊነት ተቋሙንም ሆነ ደራሲውን በቅርብ እንደማወቄ መጠን፤ ይህ መጽሐፍ ከተጨባጩ ዓለም የተገኘ ጥልቅ እውቀት የሚሰጥ፣ ለመሰል ተቋማት መሪዎችና ተመራማሪዎች ታላቅ ማስተማሪያና ማጣቀሻ እንደሚሆን ሙሉ እምነት አለኝ።
ሳሙኤል ክፍሌ (ዶ/ር)፣ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ኘሬዚደንት
***
ጎንደር ዩኒቨርሲቲ በፈተናዎች ውስጥ ያለፈ ታላቅ ዓለም አቀፍ ተቋም ቢሆንም፣ የነበረው የታሪክ ምዝገባ ግን በቂ አልነበረም:: የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶ/ር አሥራት ዓፀደወይን “ጽናት” በተሰኘው መጽሐፋቸው ይህንን የታሪክ ክፍተት ለመሙላት ሞክረዋል። መጽሐፉ፣ ተቋሙ በፈተናዎች ውስጥ አልፎ ለዛሬው ስኬት እንዲበቃ አሻራቸውን ያሳረፉ የቀድሞ ከፍተኛ አመራሮችን እውቅና ይሰጣል። በተጨማሪም፣ ዶ/ር አሥራት ላለፉት ስምንት ዓመታት በኘሬዚዳንትነት ሲያገለግሉ ያጋጠሟቸውን ከባድ ፈተናዎች እንዴት በብቃት እንደተወጧቸውና የዩኒቨርሲቲውን ስኬት እንዴት ማስቀጠል እንደቻሉ ያሳያል። ይህም ለተቋሙ ቀጣይ ጤናማ የአመራር ሽግግርና ለተተኪ አመራሮች ትልቅ ስንቅ የሚሆን ነው።
ዶ/ር ደሳለኝ መንገሻ፣ በኦሃዮ ስቴት ግሎባል ዋን ሄልዝ የኢትዮጵያ ዳይሬክተር እና የቀድሞ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት
እንኳን ደስ አለህ!

ጎንደር - ብርሃኑ ነጋ እና ፍትፍቴ መሰንቆ
* ለባህል ጥበቃ የሚታትረው ቡቻች
#ethiopia | ብርሃኑ ነጋ ይባላል። በጎንደር ግን ከስሙ ይልቅ "ቡቻች" በሚለው የልጅነት ስሙ ይታወቃል። ይህን ስም ያወጡለት እናቱ ናቸው።
የ31 ዓመቱ ቡቻች በአዘዞ ተወልዶ ያደገ ሲሆን፣ በፋሲለደስ ባህል ማዕከል ተወዛዋዥና ባህላዊ ከበሮ ተጫዋች ነው። በተጨማሪም የእስክስታዋ ንግሥት አርቲስት እንየ ታከለ የባህል ምግብ አዳራሽ የባንዱ ማናጀር ሆኖም ያገለግላል።
ዛሬ ግን በሌላ የፈጠራ ሥራው እየተደነቀ ነው። ከአባቱ ነጋ መኮንን የወረሰውን የባህል ፍቅር ወደ ተግባር በመቀየር፣ ፍትፍቴ መሰንቆ በእጁ እየሠራ ለገበያ ማቅረብ ጀምሯል። ከዚህ በተጨማሪ ከበሮ፣ ዋሽንትና ክራር በመሥራት የኢትዮጵያን ባህላዊ የሙዚቃ መሣሪያዎች ለማስቀጠል እየተጋ ነው።
ወጣቶች ብዙዎች ሥራ ፍለጋ በሚባዝኑበት ዘመን፣ ቡቻች ግን የአባቶቹን ውርስ በእጁ እያኖረ ወደ ሥራና ፈጠራ መቀየሩ የሚያስደንቅ ነው። ይህ ጥረቱ ለራሱ ብቻ ሳይሆን የጎንደርን እና የኢትዮጵያን የሙዚቃ ባህል ለትውልድ የሚያሸጋግር ውድ አስተዋፅኦ ነው።
በትጋት፣ በፅናትና በፈጠራ የተቀረጹት የቡቻች ነጋ እጅ ሥራዎች ከጎንደር ተነስተው ባህርዳርን አልፈው ዛሬ አዲስ አበባ ድረስ ደርሰዋል። በእጁ የሚሠሩ መሰንቆዎች፣ ዋሽንቶች፣ ክራሮችና ሌሎች ባህላዊ የሙዚቃ መሣሪያዎች በገበያ ተፈላጊ ሆነዋል።
በመጀመሪያ አንድ መሰንቆ በ2,500 ብር ይሸጥ ነበር። የሥራው ጥራት እየተሻሻለ፣ ፍላጎቱም እየጨመረ በመምጣቱ ዛሬ መደበኛው መሰንቆ እስከ 8,000 ብር ይሸጣል። በብረት መቃኛ (tuning pegs) እና በድምፅ ማጉያ ጃክ የተሟላ ዘመናዊ መሰንቆ ደግሞ 15,000 ብር ይደርሳል።
ይህ የዋጋ ለውጥ የሚያሳየው የእጅ ጥበቡ እውቅና እያገኘ መምጣቱን፣ የሥራው ጥራት ከፍ ማለቱን እና ባህላዊ የሙዚቃ መሣሪያዎችን ከዘመናዊ ቴክኖሎጂ ጋር በማዋሃድ ለተጫዋቾች የተሻለ አማራጭ ማቅረቡን ነው።
ቡቻች የሚሠራው መሣሪያ ብቻ አይደለም፤ የኢትዮጵያን ባህል፣ ታሪክና ሙዚቃ ለቀጣይ ትውልድ የሚያሸጋግር ሕያው ቅርስ ነው። እንደዚህ ያሉ ወጣት የጥበብ ባለሙያዎች ሊበረታቱና ሊደገፉ ይገባል።
ትጋት፣ ጥረት፣ ፈጠራ እና ለባህል ያለው ፍቅር በእውነት የሚያስመሰግኑ ናቸው።
እንደ ቡቻች ያሉ ወጣቶች የባህላችን ሕያው አምባሳደሮች ናቸው።
ለቡቻች
ደውሉለት፤ እዘዙት
+251-918-138857
+251-904-365617
#ሼር # Share

«ጽናት የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ታሪካዊ የለውጥ ጉዞ» የተሰኘው መጽሐፍ ሊመረቅ ነው
#ethiopia | አንጋፋው የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ከተመሠረተበት ጊዜ ጀምሮ ያለፈባቸውን ታሪካዊ ሂደቶች ተቋማዊ ለውጦችን የሚዳስሰው መጽሐፍ ሊመረቅ መሆኑ ተነግሯል።
መጽሐፉ የዩኒቨርስቲው ስኬቶችንና የዕድገት ጉዞውንም ጭምር ይዳስሳል ተብሏል።
ይህ መጽሐፍ የጎንደር ዩኒቨርሲቲን ታሪክ ከመመዝገብ ባሻገር የተቋማዊ ለውጥ ልምዶችን የአመራር ተሞክሮዎችንና የከፍተኛ ትምህርት ጉዞን የሚያሳይ የእውቀትና የታሪክ ምንጭ እንደሆነ ነው የተገለፀው።
«ጽናት የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ታሪካዊ የለውጥ ጉዞ» የተሰኘው ታሪካዊ መጽሐፍ የተጻፈው በዩኒቨርስቲው ፕሬዝዳንት መሆኑም ሰምተናል።
መጽሐፉ በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር አሥራት ዓፀደወይን የተጻፈ ሲሆን ሐምሌ 18 ቀን 2018 ዓ.ም በደማቅ ሁኔታ በይፋ ይመረቃል ተብሏል።
«ጽናት የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ታሪካዊ የለውጥ ጉዞ» በሚል ርእስ ተጽፎ የተዘጋጀው ይህ መጽሐፍ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች፣ የጎንደር ከተማ ነዋሪዎች እና የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ አባላት በተገኙበት ይመረቃል።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#ethiopia #getutemesgen #getunews #ኢትዮጵያጎንደርየመጽሐፍምረቃ #ጽናትየጎንደርዩኒቨርሲቲ #ታሪካዊየለውጥጉዞ #ጎንደርዩኒቨርስቲአዲስመጽሐፍ

አሜሪካ ጎንደር ገባች
#ethiopia | በኢትዮጵያ የዩናይትድ ስቴትስ ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋ ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት ታሪካዊቷ የጎንደር ከተማ የገቡ ሲሆን በቦታውም ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።
አምባሳደሩ ጎንደር ሲደርሱ የከተማዋ ከንቲባ አቶ ቻላቸው ዳኘው፣ የአማራ ክልል ከተማና መሰረተ ልማት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ሞላ መልካሙ፣ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶክተር አሥራት ዓፀደወይን እንዲሁም ሌሎች ከፍተኛ የመንግሥትና የዩኒቨርሲቲው የሥራ ኃላፊዎች በክብር ተቀብለዋቸዋል።
አምባሳደር ማሲንጋ እና የሚመሩት የልዑካን ቡድን በቆይታቸው በጎንደር ከተማ በዩኒቨርሲቲው አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል እንዲሁም በዓፄ ቴዎድሮስ ግቢ በሚገኘው የሃሪ ኤስ ትሩማን አሜሪካን ኮርነር የቤተ-መጻሕፍት ማዕከል ጉብኝት ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።
በጎንደር ከተማ ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ መረጃ መሠረት ከዚህ በተጨማሪም በትምህርት፣ በምርምር፣ በጤና አገልግሎትና በተቋማዊ አጋርነት ዘርፎች ያለውን የሁለትዮሽ ትብብር ይበልጥ ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ከዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራሮች ጋር ሰፊ ውይይት የሚያደርጉ ሲሆን የጎንደር ዩኒቨርሲቲም ይህ ጉብኝት በኢትዮጵያና በዩናይትድ ስቴትስ መካከል ያለውን ታሪካዊና ዘላቂ አጋርነት ይበልጥ የሚያጠናክር እንደሚሆን ያለውን ጽኑ እምነት ገልጿል።
በያፌት ገ/ህይወት
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu

የፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት ጥልቅ አንድምታ፤ መንግሥት የገነባው የትዕግሥትና የአርቆ አሳቢነት ቁመና
************************
ከከባድ የጦርነት አውድማና መገፋፋት በኋላ፣ አሸናፊና ተሸናፊ በእኩል ማዕድ ተቀምጠው የሰላምን ጽዋ ሲጋሩ፤ የተዘጉ በሮች ሲከፈቱ እና የፈረሱ የልብ ድልድዮች ሲጠገኑ መመልከት ምን ያህል ልብን በደስታ ይሞላል?
ይህ በዓለማችን እጅግ ብርቅ የሆነው የሰላም መንገድ፣ በፕሪቶሪያው ስምምነት በኩል በኢትዮጵያ ምድር እውን ሆኖ የሀገራችንን የፖለቲካ አቅጣጫ ወደ ተሻለ ብሩህ ተስፋ አሸጋግሮታል።
የፕሪቶሪያው ስምምነት የፖለቲካ ድርድር ብቻ ሳይሆን፣ መንግሥት ለሰላም ያለውን የጸና ቁርጠኝነት በተግባር ያሳየበት፣ አሸናፊ ሆኖ ሳለ ተሸናፊውን ኃይል በአክብሮት አቅፎ ወደ ጠረጴዛ ያመጣበት ታላቅ የትዕግስትና የአርቆ አሳቢነት ማሳያ ነው።
በዚህም ስምምነት መሠረት በትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደርን ማቋቋም ከመቻሉም ባሻገር፣ ከስልሳ ሺህ በላይ የሚሆኑ የታጠቁ ኃይሎችን ትጥቅ በማስፈታትና አስፈላጊውን ክፍያ በመፈጸም ወደ ኅብረተሰቡ እንዲቀላቀሉ ተደርጓል።
ከዚህም አልፎ በርካታ የጦር ምርኮኞች በነፃነት ወደ ቀያቸው እንዲመለሱ የተደረገ ሲሆን፣ ተቋርጠው የነበሩ መሠረታዊ አገልግሎቶች (እንደ አየር መንገድ እና ቴሌኮም) ሙሉ በሙሉ ተመልሰዋል።
መንግሥት ለዜጎቹ ካለው ጥልቅ ፍቅር የተነሳ፣ በአዲስ አበባና በተለያዩ ከተሞች የሚገኙ የታጠቁ ኃይሎች ቤተሰቦችን ሀብትና ንብረት ከመውረስ ታቅቦ፣ በአንድ ሰው የፖለቲካ ጥፋት ሙሉ ቤተሰብ መጎዳት የለበትም በሚል ሰፊ አመለካከት ሀብታቸውን ጠብቆ አስረክቧል።
ይህ ዓይነቱ ርኅራኄና የሰላም እርምጃ በርካቶችን ያስደሰተ ቢሆንም፣ የሰላሙን መንገድ ያልወደዱና በስምምነቱ ያኮረፉ ፀረ-ሰላም ኃይሎች ዛሬም ድረስ አልጠፉም። እነዚህ ኃይሎች በትግራይ ክልል በየጊዜው ትንኮሳዎችን ከመፍጠራቸውም በላይ፣ የትግራይን ወጣቶች በጉልበት እያፈሱና እየሸጡ በሱዳን የእርስ በርስ ጦርነት ውስጥ እንዲማገዱ በማድረግ በሕዝቡ ላይ የማይሽር የውስጥ ቁስል እየፈጠሩ ይገኛሉ።
ከዚህ ጋር ተያይዞ በሀገራችን የተፈጠረው እጅግ አስገራሚው እውነታ ደግሞ፣ "ለሕዝብ እንታገላለን" የሚሉ ኃይሎች በሕዝቡ ላይ እያመጡት ያለው መከራ ነው። ዛሬ ላይ አንድ የትግራይ ተወላጅ በትግራይ ክልል ከሚኖረው ይልቅ በአዲስ አበባ፣ በባሕር ዳር፣ በጎንደር፣ በሐዋሳ ወይም በአዳማ እጅግ የላቀ ሰላም አግኝቶ ያለምንም ስጋት ወጥቶ ይገባል።
በተመሳሳይ ለአማራ ሕዝብ እንታገላለን የሚሉ ኃይሎች ባሉበት ቀዬ ያለው ነዋሪ በፍርሃት፣ በግድያና በዘረፋ ሲታመስ፤ አንድ የአማራ ተወላጅ በኦሮሚያ፣ በደቡብ ወይም በሶማሌ ክልል የተሻለ ሰላም አግኝቶ ይኖራል። ለኦሮሞ ሕዝብ መብት ቆመናል የሚሉ ኃይሎች በሚንቀሳቀሱባቸው አካባቢዎች ያለው ነዋሪ ከቀዬው ሲሰደድ፣ በአንጻሩ በአማራ፣ በአፋር ወይም በሶማሌ ክልል የሚኖር የኦሮሞ ተወላጅ የተሟላ ሰላም አግኝቷል።
ይህ እውነታ በግልጽ የሚያሳየው ከሕዝብ ተነጥሎ፣ ሕዝብን አስለቅሶና ዘርፎ የሚደረግ ማንኛውም ትግል ከጥፋት በቀር የሚያመጣው አንዳች ፋይዳ እንደሌለ ነው።
መንግሥት ይህንን ሁሉ እያየ ወደ ተሟላ ጦርነትና ግጭት ከመግባት ይልቅ ትዕግስትን የመረጠው ያለ ምክንያት አይደለም። የኢትዮጵያ ወቅታዊ የፖለቲካ አውድ ልክ እንደ አንድ "መጥረቢያ" ነው። በመጥረቢያው ዘይቤ መሠረት ሦስት ተዋናዮች አሉ፤ ቆራጩ የብረት ክፍል፣ ብረቱ የገባበት የእንጨት እጀታ፣ እና መጥረቢያውን ይዞ የሚቆርጠው።
የብረቱ ክፍል የራሱ ዓላማ የለውም፣ የእንጨቱን ትዕዛዝ ይፈጽማል፤ እንጨቱም ቢሆን የራሱ ፍላጎት የለውም፣ በመጥረቢያው አዛዥ እጅ ይመራል። በመሆኑም መንግሥት ከብረቱ ወይም ከእንጨቱ ጋር በመላተም ጊዜውን ከማጥፋት ይልቅ፣ የኢትዮጵያን ሰላም የሚያደፈርሰው ዋነኛ ምንጭ የት እንደሆነ በሚገባ ተገንዝቦ አደጋውን ለመቀልበስ የሚያስችል ጠንካራ የመከላከያ ቁመና ገንብቷል።
ብረቱንና እንጨቱንም ቢሆን በተቻለ መጠን በማስተማር፣ በመታገስና በመመለስ፣ የኢትዮጵያ ሰላምና ዕድገት የጋራ ተጠቃሚ እንደሚያደርጋቸው ለማስገንዘብ በከፍተኛ ብስለት እየሠራ ይገኛል።
ከዚህ ሁሉ የፈተናና የትዕግስት ጉዞ ጀርባ የምትታየው ኢትዮጵያ፣ ባለፉት ዓመታት "ልትፈርስ ነው፣ ልትወድቅ ነው" የተባለባትን የክፉዎች ትርክት ቀልብሳ በአዲስ የማንሰራራት መንፈስ ውስጥ ትገኛለች።
ኢትዮጵያ አትወድቅም ብቻ ሳይሆን፣ ወደፊትም የተኙትን የምታነቃ፣ የወደቁትን የምታነሳና ሊበለጽጉ ሲገባቸው ያልገባቸውን ወንድምና እህቶቿን ይዛ ወደ ከፍታ የምትገሰግስ ታላቅ ሀገር ናት። ለዚህም ማሳያው የፖለቲካ ልዩነት ያላቸው የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች ሳይቀሩ፣ የ"መደመር" እሳቤን በልባቸው አኑረው፣ ስለ ሚዛናዊ የክልሎች ተጠቃሚነት፣ ስለ ኮሪደር ልማትና ስለ ተለያየ ኢኮኖሚ ግንባታ በአንድ ልብ መምከራቸው ነው።
ይህ የሐሳብ መወራረስና መቀራረብ፣ የኢትዮጵያ ሕዝብ አንድነቱን አጽንቶ፣ ልዩነቶቹን በውይይት ፈትቶ፣ የወደፊቱን የብልጽግና ጉዞ በጋራ ለማፋጠን የሚያስችል የማይናወጥ መሠረት መጣሉን የሚያበስር አስደሳች ምዕራፍ ነው።

"በነገራችን ላይ፣ ዛሬ፣ በትግራይ ውስጥ ከሚኖር ትግራዋይ በላይ፣ በሰላም ወጥቶ መግባት የሚችል፣ አፈሳ የማይካሄድበት፣ በደሴ፣ በጎንደር፣ በባህር ዳር፣ በአዲስ አበባ፣ በቢሾፍቱ፣ አዳማ፣ አርባምንጭ፣ ሀዋሳ ያለ ትግራዋይ፣ ትግራይ ካለው ሰው በላይ ሰላም አለው። ትግራይ ካለው ሰው በላይ በሰላም ወጥቶ መግባት ይችላል። የሚያሳዝነው ይሄ ጉዳይ ግን ትግራይ ብቻ አይደለም። አማራ አካባቢ የሚንቀሳቀሱ ሃይሎች፣ 'ለአማራ ህዝብ ሰላም፣ ደህንነት፣ ጥቅም እንታገላለን' ብለው የሚሉ ሃይሎች በሚንቀሳቀሱባቸው አካባቢዎች ካለው የአማራ ተወላጅ ይልቅ፣ ኦሮሚያ፣ ደቡብ፣ ሱማሌ ያለው አማራ ሰላም አለው። እነዚህ እንታገላለን የሚሉ ሃይሎች ያሉበት አካባቢ የበለጠ ፍራቻ፣ የበለጠ ግድያ፣ የበለጠ ዘረፋና መታገዶች አሉ።
"ኦሮሚያ አካባቢ ለኦሮሞ እንታገላለን ብለው የሚመሉ፣ የሚገዘቱ ሃይሎች ከሚንቀሳቀሱበት አካባቢ በላይ፣ በአማራ ክልል የሚንቀሳቀስ፣ በሱማሌ የሚንቀሳቀስ፣ በአፋር የሚንቀሳቀስ ኦሮሞ የተሻለ ሰላም አለው። ዜጎች በገዛ ቀያቸው፣ መንደራቸው፣ በገዛ ልጆቻቸው እየታመሱ ይገኛሉ። ከቀያቸው ሸሽተው መኖር የተሻለ ሰላም የሚያገኙበት እየሆነ መጥቷል። ከህዝብ ተነጥሎ፣ ህዝብ አስለቅሶ፣ ህዝብ ዘርፎ፣ የሚደረግ ትግል ደግሞ የትም ማድረስ እንደማይችል ከታሪኮቻችን መማር የምንችል ይመስለኛል።
መንግስት አብዛኛውን ጉዳይ በትዕግስት የሚያየው፣ ወደ ግጭት የማይገባው፣ ለምንድነው ያላችሁ እንደሆነ፣ አላማ ቢስ ነው። አላማ የለውም። ይሄንን ግጭት ከፈጸምን በኋላ 'አሳካን' ብለን የምንናገረው አንዳች ቁምነገር የለም። በዚያም በዚህም ብንገል፣ ብንሞት ትርጉም የለውም። ኢትዮጵያ ውስጥ በተለይ ትግራይ አካባቢ ያለው የፖለቲካል አውድ የመጥረቢያ ፖለቲካ ሰለባ ነው ትግራዋይ እና ኢትዮጵያዊያን የሆኑት።"
ጠ/ሚ/ር ዐቢይ አህመድ ዛሬ በፓርላማው ከተናገሩት

የ“እኔ እበልጥ” ትርክት ስብራትን በተጨባጭ እየጠገነ ያለው የ“መደመር” አካታች እሳቤ
*****************************
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፣ “እኔ እበልጣለሁ የሚል አግላይ አስተሳሰብ የዘመናት ድህነታችን ምንጭ ነው፤ ከዚህ ወጥተን እንደ አንድ ዜጋ ልንተባበር ይገባል” በማለት የችግራችንን መሠረት አስቀምጠዋል።
ይህ የበላይነት ስሜት እና አግላይ አስተሳሰብ የዜጎችን ማኅበራዊ እና ጂኦግራፊያዊ እንቅስቃሴ በመገደብ ሀገራዊ የገበያ ትስስርን የሚያደናቅፍ መዋቅራዊ ማነቆ ሆኖ ቆይቷል።
የፖለቲካ ሥልጣንን እንደ ዜሮ-ድምር ፍልሚያ በሚቆጥር እሳቤ ውስጥ መኖር፣ ሀገራዊ ትብብርን እና የሰው ሀብት ልማትን በእጅጉ ይጎዳል።
ይህን ሥር የሰደደ አግላይ ትርክት ለመቀልበስ የለውጡ መንግሥት የ“መደመር” እሳቤን በማራመድ ዜሮ-ድምር የሆነውን የፖለቲካ ፉክክር በአካታች ሀገራዊ አንድነት ለመተካት እየሠራ ይገኛል።
ይህም ሰኔ 27 ቀን 2018 ዓ.ም ጠቅላይ ሚኒስትሩ በአርባምንጭ ከተማ ባደረጉት ንግግር በግልጽ ተንጸባርቋል።
በወቅቱም፣ እውነተኛ የብልጫ መለኪያ ተጨባጭ ወቅታዊ ሥራ እና ምርታማነት እንጂ ስም ወይም ታሪክ እንዳልሆነ አበክረው ገልጸዋል።
ሰላምን እንደ ኢኮኖሚያዊ እሴት በመቁጠር ቱሪስቶችን መንከባከብ፣ ሌብነትን መጸየፍ እና አካባቢን ማጽዳት ለጋራ ብልጽግና ወሳኝ መሆናቸውን አስገንዝበዋል።
ሀገራዊ አንድነትን እና አካታችነትን ወደ ተጨባጭ ሀብት ለመቀየርም መንግሥት በ“ገበታ” ፕሮጀክቶች እና በብዝኃ ዘርፍ ኢኮኖሚ ሪፎርም በርካታ ሥራዎችን እያከናወነ ይገኛል።
ከእነዚህም መካከል ከ1 ሺህ 300 በላይ ሰዎችን ማስተናገድ የሚችለው እና በአርባ ምንጭ ሐይቅ ላይ 360 ዲግሪ የሚሽከረከር ሬስቶራንትን ያካተተው የአርባምንጭ ኮንፈረንስ ሪዞርት አንዱ ነው።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንደጠቀሱት፣ ከዚህ ቀደም አንድ የውጭ ባለሀብት አካባቢው ለቅንጦት ልማት ዝግጁ አይደለም ብሏቸው የነበረ ቢሆንም፤ መንግሥት የሀገር ውስጥ አቅምን በማስተባበር ይህን ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ ሪዞርት እውን ማድረግ ችሏል።
ይህ ደግሞ ከመገፋፋት እና "እኔ እበልጥ" ከመባባል ይልቅ፣ ሀገራዊ አቅምን በማስተባበር ተዓምር መፍጠር እንደሚቻል ማሳያ ነው።
ከአርባምንጭ በተጨማሪ በሐዋሳ፣ በቢሾፍቱ፣ በጎንደር፣ በባሕር ዳር፣ በአፋር እና በደንዲ የተሠሩት ግዙፍ የመሠረተ ልማት እና የቱሪዝም ፕሮጀክቶች በሀገራችን የኢኮኖሚ ዕድገትን እኩል ለማዳረስ ያለሙ ናቸው።
እነዚህ ሥራዎች የሚያሳዩት “እኔ እበልጥ” ከሚል አግላይ ፖለቲካ ወጥተን በጋራ ስንቆም የውጭ ማረጋገጫ ሳያስፈልገን የሀገራችንን እምቅ ሀብት ወደ ተግባር መቀየር እንደምንችል ነው።
እውነተኛው የሀገር ግንባታ የሚጀምረው ከእያንዳንዳችን የዕለት ተለት ተግባር ነው። አዎ፣ ሁላችንም በሕይወታችን፣ በሥራ ገበታችን እና በማኅበራዊ መስተጋብራችን "እኔ እበልጥ" ከሚል አግላይ አስተሳሰብ ወጥተን ሀገራችንን ለመገንባት መነሳት አለብን።
ትልቅ አቅም ያለን ሕዝቦች ነን፤ ከተባበርን እና አቅማችንን ካስተባበርን ልንደርስበት የማንችለው ከፍታ የለም።
የምታኮራ እና የበለጸገች ኢትዮጵያን ለትውልድ ለማስረከብ ዛሬውኑ በመደመር መንፈስ መነሳት ጊዜ የማይሰጠው ጉዳይ መሆን አለበት፡፡
በለሚ ታደሰ
#ethiopia #medemer #dineforgeneration #tourism #development #ebc

ሚስ ወርልድ ኢትዮጵያ ሩት ይርጋለም በጎንደር የባህልና ታሪክ ጉብኝት
የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር የባህልና ጥበባት አምባሳደር አድርጎ የሾማት ሚስ ወርልድ ኢትዮጵያ ሩት ይርጋለም፣ የኢትዮጵያን ባህል፣ ጥበብና ታሪክ ለማስተዋወቅ የታለመ ጉብኝት በጎንደር ከተማ አድርጋለች።
በቆይታዋ የጎንደር ባህል ማዕከልን፣ የሙዚቃና የቴአትር ባለሙያዎችን በመጎብኘት የባህል ጭፈራና እስክስታ ልምምድ አድርጋለች። እንዲሁም በአፄ ፋሲል ቤተ መንግሥት የታሪክና የኪነ ህንፃ ቅርሶችን ተመልክታ ስለ ታሪካዊ እሴታቸው ገለጻ ተደርጎላታል።
ጉብኝቱ ሩት ይርጋለም በቬትናም በሚካሄደው 73ኛው የሚስ ወርልድ ውድድር ኢትዮጵያን በምትወክልበት ወቅት የአገሪቱን ባህል፣ ታሪክና ጥበብ በብቃት ለማስተዋወቅ የሚያስችላትን እውቀት ለማጠናከር የታለመ መሆኑ ተገልጿል።
📷 Focus Studio

የእርዳታ ተማጽኖ
"እናት ከልጇ ሕይወት በላይ የምትመኝ ነገር የለም።"
#ethiopia | እናት አለምፀሐይ በላ በጎንደር ከተማ የምትኖር ሲሆን፣ የ8 ዓመቷ ልጇ መክሊት ማራቸው በከባድ የልብ ሕመም እየተሰቃየች ትገኛለች።
የሕክምና ባለሙያዎች ለሕፃኗ አስቸኳይ የልብ ቀዶ ሕክምና እንደሚያስፈልጋት ገልጸዋል።
እንደቤተሰቡ እናቷ ገለጻ፣ ለሕክምናው ወደ 1.2 ሚሊዮን ብር የሚጠጋ ወጪ ያስፈልጋል፤ ይህን ወጪ ለመሸፈን የእናቷ አቅም አይበቃም።
ስለዚህ ሕፃን መክሊት የሕይወት ዕድል እንድታገኝ፣ አቅምዎ በፈቀደው መጠን የገንዘብ ድጋፍ በማድረግ ወይም ይህን መልዕክት በማጋራት ድርሻዎን ይወጡ።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
ሂሳብ ቁጥር፦ 1000768176969
አለምፀሀይ በላይ እና/ ወይም እናቴነሽ ተገኘ
"ትንሽ ድጋፍዎ ለአንዲት ሕፃን ትልቅ የሕይወት ተስፋ ሊሆን ይችላል።"
🙏 መልእክቱን በማጋራት ለሌሎችም ያድርሱ።
ሰ.ቁ +251-928-302847
አለምፀሐይ በላይ - እናት
#savemeklit #heartsurgery #ethiopia #gondar #helpchild #donate #getu #charity #hope #savealife

ሚስ ወርልድ ኢትዮጵያ ሩት ይርጋለም በጎንደር የባህልና ታሪክ ጉብኝት ጀመረች
#ethiopia | የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር የባህልና ጥበባት አምባሳደር አድርጎ የሾማት ሚስ ወርልድ ኢትዮጵያ ሩት ይርጋለም፣ የኢትዮጵያን ባህል፣ ጥበብና ታሪክ ለማስተዋወቅ የታለመ ጉብኝት በጎንደር ከተማ ጀምራለች።

Comments