የፕሮፌሰር ማለደ ማሩ የሕይወት ታሪክ ተፅፎ ተመረቀ
(ከዕዝራ እጅጉ ሙላት)
#ethiopia | ለግማሽ ክፍለ ዘመን ወይም ለ 52 ዓመታት በሕክምናው ዘርፍ ያገለገሉት የፕሮፌሰር ማለደ ማሩ የሕይወት ታሪክ ተፅፎ ቅዳሜ መጋቢት 19 2018 ዓ.ም ተመርቋል።
ቀበና በሚገኘው የኢትዮጵያ የኅብረተሰብ ጤና ማህበር አዳራሽ በተካሄደው የምረቃ መርሀ ግብር፣ የፕሮፌሰሩ አብሮ አደጎች እና ተማሪዎች የተገኙ ሲሆን የመፅሐፉም ደራሲ ዶክተር ሰሎሞን በርሄ ናቸው።
ፕሮፌሰር ማለደ ማሩ፣ ለልብ ህክምና ከፍተኛ ትኩረት የሰጡ ባለሙያ ሲሆኑ የጎንደር ዩኒቨርሲቲም አምና የጤና ሳይንስ ኮሌጅ የአስተዳደር ህንፃውን በስማቸው ሰይሞ ትልቅ ዕውቅና መስጠቱም ይታወቃል።
በመፅሐፍ ምረቃ መርሀ- ግብሩ ላይ ፕሮፌሰር ሽብሩ ተድላ ዶክተር አፀደ ወይን አስራት የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት፣ ተገኝተው ንግግር ያደረጉ ሲሆን ሰዎች በሕይወት እያሉ የሙያ ታሪካቸው በዚህ መልኩ ተሰንዶ በመፅሐፍ መልክ መቅረቡ ለአዲሱ አገር ተረካቢ ትውልድ ትልቅ ነገር ነው ብለዋል።
"የቼቼላው አባታችን " በሚል ርዕስ ታሪካቸው በመታተሙ ደስ የተሰኙት ታላቁ የአገር ባለውለታ ፕሮፌሰር ማለደ ማሩ፣ በመሸብኝ ሰዓት ስላስታወሳችሁኝ አመሠግናለሁ ብለዋል።
ይህን የእርሳቸውን መፅሐፍ ለማሳተም ኮሚቴ ተዋቅሮ ሥራው የተከናወነ ሲሆን ባለታሪኩ ፕሮፌሰር ማለደም ለኮሚቴው ልባዊ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
"የቼቼላው አባታችን "የተሰኘው በፕሮፌሰር ማለደ ማሩ ላይ ትኩረቱን ያደረገ መፅሐፍ 200 ገፆች ያሉት ሲሆን በ1000 ቅጂዎች ለህትመት የበቃ እንደሆነም ለማወቅ ተችሏል።
መፅሐፉ ከነገ መጋቢት 21 2018 አንስቶ በጃፋር የመፅሃፍ መደብር የሚገኝ ሲሆን ዋጋውም ብር 500 መሆኑን ደራሲው ለተወዳጅ ሚድያ በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል። በተጨማሪም መፅሐፉ በባህርዳር እና በጎንደር የመፅሐፍ መሸጫ መደብሮች እንደሚገኝ ተነግሯል።

7 months ago