Logo
SeledaPost
አንጋፋው የጎንደር ኢማም ኡስታዝ ሙሐመድ ዘይኑ ተገደሉ

​በጎንደር ከተማ የታወቁት የመስጂድ ኢማም ኡስታዝ ሙሐመድ ዘይኑ ትላንት ምሽት በታጣቂዎች እጅ መገደላቸው ተሰማ።

እንደ ሀሩን ሚዲያ ዘገባ ከሆነ  ግድያው የተፈጸመው ኡስታዙ የተራዊህ ሰላት ሰግደው ወደ ቤታቸው ሲመለሱ በወላጅ አባታቸውና በወንድማቸው ፊት ነው።

​ታጣቂዎቹ በወቅቱ በነበሩ 11 ሰዎች ላይም ከባድ ድብደባና ዘረፋ መፈፀማቸውን በዘገባው ተመላክቷል።

ድርጊቱ የተፈጸመው በከተማዋ መሀል "ቅዳሜ ገበያ" ተብሎ በሚጠራው አካባቢ፣ ከጃሚዓል ከቢር መስጂድ ጥቂት ሜትሮች ርቀት ላይ ነውም ተብሏል

ዛሬ ቀብራቸው የተፈፀመው ​ኡስታዝ ሙሐመድ ዘይኑ ለረጅም ዓመታት የከተማዋን ዑለማ ምክር ቤት ያገለገሉ ሲሆን፣ በቁርዓን አቀራረባቸውና በታታሪ የሃይማኖት አገልጋይነታቸው የሚታወቁ አንጋፋ ምሁር ነበሩ።

ድርጊቱ  በማህበረሰቡ ዘንድ ከፍተኛ ሃዘንን ፈጥሯል።

seledadotio
seledadotio
3 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.