7 months ago
"እንዛታ"
— አዲስ ትውፊታዊ ቴአትር ነገ በባህር ዳር በድምቀት ይመረቃል!
#ethiopia | በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የባህል፣ ኪነ-ጥበብ እና ዝክረ ታሪክ ጽሕፈት ቤት የተዘጋጀውና የአዝማሪዎችን እውነተኛ ሕይወት የሚዳስሰው "እንዛታ" የተሰኘ ድንቅ ትውፊታዊ ቴአትር ነገ ይመረቃል።
ቴአትሩ በጎንደር የሚገኙ አዝማሪዎች መንደር "ቡርቧክስ" ድረስ በመሄድ፣ የአዝማሪዎችን አጠቃላይ የሕይወት ዘይቤ በጥናት ላይ ተመስርቶ የቀረበ ነው።
የአዝማሪዎችን እውነተኛ የኑሮ ገጽታ፣ ሳቅ፣ ደስታና ሐዘን በመሰንቆ ክርና በአውታር መካከል የተደበቁ የሕይወት መንገዶችን ቁልጭ አድርጎ ያሳያል።
# እንዛታ !!
ገብረማርያም ይርጋ #gebremaryam Yirga
የአብክመ ባህል ኪነጥበብ እና ዝክረ ታሪክ ጽ/ቤት
#እንዛታ #ባህርዳር #ትውፊታዊቴአትር #አዝማሪ #ኢትዮጵያ #ኪነጥበብ #ጌጡተመስገን #getutemesgen

9 months ago
የዐፄ ቴዎድሮስን ሃውልት በከተማው አናት ገነት ተራራ ..!
አስባችሁታል የዐፄ ቴዎድሮስን ሃውልት በከተማው አናት ገነት ተራራ ቁሞ ስታዩት....🙄🙏
#ethiopia | የሀገራችን ባለውለታ ፣ የጥልቅ ሃሳብ ምንጭ ባለቤት
የስልጣኔ ምልክት ፣ ኢትዮጵያዊዉ መሪ አጼ ቴዎድሮስ 207 ዓመት የልደት መታሰቢያቸው ሲከበር ጎንደር ከተማ አስተዳደር የዐፄ ቴዎድሮስን ሃውልት በከተማው ገነት ተራራ ላይ ለመስራት መታሰቡንና ፕሮጀክት ይፉ በማድረግ አብስረዋል ።
ሊሰራ የታሰበዉ ፕሮጀክቱ እንደ በብራዚል ሪዮ ዴ ጄኔሮ እንደሚገኘውና በፈረንሳዊ-ፖላንዳዊው የቅርጻ ቅርጽ ባለሙያ ፖል ላንዶውስኪ እንደታነፀው ”ቤዛው ክርስቶስ” የተባለ አርት ዲኮ ሐውልት ዓይነት ወይም እንደሌሎች ህንድ ጉጅራት ታዋቂ ሀዉልቶች (የኔ እይታ ) ሲሆን በርካታ ተጨማሪ ሀሳቦችን የያዘ ልማት ሀሳብ ነው።
ይህ ፕሮጀክት ታላቁን ንጉሥ ከፍ ባለ ቦታ አቁሞ ሁሌም ስለ አንድነትና ስለ መሰልጠን የሚብሰከሰክ ትውልድ ለመፍጠር የሚረዳ ማነቃቂያም ይሆናል።
በዚህ አግባብ ከከተማው ህዝብና በመላው ዓለም፣ በሀገራችን ከሚኖሩ የጎንደር ወዳጆች ጋር በመተባበር ዕውን የሚደረግ ፕሮጀክት መሆኑ በዛሬው ዕለት ከንቲባ አቶ ቻላቸው ዳኘው በክብረ በአሉ ላይ ባደረጉት ንግግር ፕሮጀክቱን አብስረዋል ።
ከሰር የተያያዙ ፎቶዎች ከህንድ ጉጅራት ያገኘሁት እና የቢሆን ሀሳቤ ነው ። ከተሰራ አይቀር እንዲህ ...
ዛሬ የምንሰራው የነገ ታሪካችን ነዉ!
Gebremaryam Yirga ገብረማርያም ይርጋ

1 year ago
ኢትዮጵያችን ደርሰናል !
#ethiopia | በአዉሮፓ አለምአቀፍ ፌስቲቫል ቱርክ ትራባዞን አክሻባት አለምአቀፍ የባህል ፌስቲቫል የኢትዮጵያን ባህል፣ ኪነ-ጥበብና እሴቶች በማስተዋወቅ የባህል ዲፕሎማሲ ስራ ሲሰራ የቆየዉ የአብክመ ሙሉዓለም ባህል ማዕከል የኢትዮጵያ ልዑክ ቆይታቸዉን አገባደዉ ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል ።
ከተለያዩ የአዉሮፓ ሀገራትና ከኢሲያ ሀገራት ሀገራቸዉን ወክለዉ የተለያዩ የልዑካን ቡድኖች በተገኙበት ኢትዮጵያን እና ኢትዮጵያዊነትንም በዓለም አደባባይ ሲያስተዋውቁ የሰነበቱት ልዑካን ቡድን አባላት ወደ ሀገራቸዉ መድረሳቸውን የአብክመ ሙሉዓለም ባህል ማዕከል ዋና ዳይሬክተር አቶ ገብረማርያም ይርጋ አሳዉቀዋል ።
የኪነ ጥበብ ልዑኩ በቆይታቸው ኢትዮጵያዊ የጥበብ ሥራዎች አድናቆት እና የሜዳልያ ሽልማት የተሰጣቸዉ ሲሆን ከተለያዩ ዓለም አቀፍ የዘርፉ መሪዎች እና ባለሙያዎች ጋርም ትውውቅ የተደረገበት፣እሴቶቻችንና ሀብቶቻችንን ያስተዋወቅንበት መድረክ መሆኑን የአብክመ ሙሉዓለም ባህል ማዕከል ዋና ዳይሬክተር አቶ ገብረማርያም ይርጋ ገልጸዋል።
የሙሉዓለም ባህል ማዕከል ከዚህ በፊት በህንድና ሩሲያ ዓለም አቀፍ መድረኮች ላይ ከተለያዩ ዓለም አቀፍ ተቋማት እና ሀገራት ጋር በባህልና ኪነ ጥበቡ ዘርፍ ጠንካራ ግንኙነት በመፍጠር የተሻለ የባህል ዲፕሎማሲ ስራዎችን እየፈጸመ የመጣ ሲሆን በቀጣይም አጠናክሮ እንደሚቀጥል አሳዉቀዋል ።
ለዚህ ጉዞ መሳካት አስተዋጽኦ ለነበራቸው የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ከተማ ክላስተር ፣ መሬት ቢሮ ፣ ትራንስፖርት ባለስልጣን፣ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ፣ ባቱ እና የኢትዮጵያ አየር መንገድ እናመሰግናለን ።
ዛሬ የምንሰራው የነገ ታሪካችን ነው !
Gebremaryam Yirga ገብረማርያም ይርጋ
የአብክመ ሙሉዓለም ባህል ማዕከል ዋና ዳይሬክተር

አ ህ መ ት / A H M E T 
#ethiopia | በቱርክ በጥቁር ባህር እና በአረንጓዴ ተራሮች መካከል በምትገኘው ትራብዞን የባህር ዳርቻ ከተማ አክሻባት ውስጥ ፌስቲቫል ተደግሶ ቱርክ መሰንበታችንን ነግሪያችሁ ነበር። በቆይታችን አብሮን እንደኛ ሆኖ ሲያስተናግደን፣ ሲሆንልን ስለነበረው በልባችን ላይ ተጽፎ የሚቀመጥ ትዉስታን ስለፈጠረብን የሚተውን አ ህ መ ት ላጫዉታችሁ ።
አህመት በትራባዞን ስፖርት ዳይሬክተር ነው ። የልዑኩን ቡድናችንን ተቀብሎ በጨዋ እንግዳ አቀባበልና መስተንግዶ ያስተናገደን ብቻ ሳይሆን ጊዜውን የሰጠን ሰዉ ነው ።
አ ህ መ ት ደግነቱ፣ ገርነቱ እና ርህራሄው ከማንኛውም ቁሳዊ ሀብት የበለጠ ውድ ሀብቶች ናቸው ። አህመት እንደ እንግዳ ሳይሆን የድሮ ጓደኞቻችን ከረዥም ጉዞ በኋላ እንደተገናኙ እየቆጠረን ወደ ህይወቱ በደስታ ተቀበለን። አህመት ምንም ሳይጠብቅ ከኛ የሰጠን ሰው ነበር።
ትራብዞን ከደረስንበት ጊዜ ጀምሮ፣ የቤት ውስጥ ስሜት እንዲሰማን ለማድረግ ያላደረገልን፣ ያላስጎበኘን ቦታዎች የለም።
አህመትን በእውነት አስደናቂ ያደረገው ጸጥ ያለ ጥንካሬው እና ትህትናው ነው። ሁልጊዜ የሌሎችን ፍላጎት በትኩረት ይከታተላል ። ከሚናገረው በላይ አዳማጭ ነው ። የተረጋጋ፣ ቃላቱ የታሰቡ እና ተግባራቱ ከልብ የመነጨ ነበር ። ሲደክመን ማረፍን ያረጋግጣል። የደበረን ሲመስለዉ ያዝናናናል። ትኩረት ለሚሹ (ከመርሃግብር አንጻር) መመሪያ ይሰጠናል ።
አህመት የቱርክ የእንግዳ ተቀባይነት መንፈስ ገልጿል ቅንነት ፣ ሞቅ ያለ እና ሙሉ ልብ ስብዕና ያለዉ ሰው ነዉ።
አህመትን በ ቱርክ ትራብዞን ማግኘታችን ርኅራኄ እና የደግነትን ዋጋ አስተምሮናል። ትሕትናው ራሳችን ላይ ስነ ምግባር እና ዊዝደም ምን ያህል ትኩረት መስጠት እንዳለብን አሳስቦናል ። ለሀገር ስም ዘብ መቆምን።
ሀገር ዉስጥም ሆነ ከሀገር ዉጭ የምታስታዉሷቸዉ የየጉዟችሁ አጋፋሪዎች እና መልካም ሰዎች ይኖራሉ ። እኔና ባልደረቦቼ የተሰማን ከትራብዞን የወጣነው ስለ መልክአ ምድሩ፣ ስለ ምግቡ እና ስለ ባህሉ በሚያምር ትዝታ ነው ። ከምንም በላይ ግን ስለተጨነቀው ብቻ የቻለውን ሁሉ የሰጠንን ሰው ትዝታ ይዘናል ።
አ ህ መ ት ።
አህመት እንዳንተም ሠው አላየሁ። አገር እና ሰዉን መዉደድ። የበዛ ቅንነት፣ ሰዉነት ።

Comments