7 hours ago
(ዘ-ሐበሻ ዜና) 'ትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት' የተሰኘው ስብስብ በቅርቡ ሶስት ሰላማዊ የፖለቲካ ታጋዮች መታሰራቸውን ተከትሎ ባወጣው መግለጫ፣ ድርጊቱ በሀገሪቱ የፖለቲካ ምህዳር ላይ ከፍተኛ አሉታዊ ጫና እንደሚያሳድር ገልጾ፣ መንግስት የታሰሩትን ግለሰቦች ያለ ቅድመ ሁኔታ እንዲፈታ አሳሰበ። ስብስቡ በዚሁ ወቅታዊ መግለጫው "የሠላማዊ ትግል በሮችን በሙሉ ዘግቶ የጦርነት በሮች እንዲከፈቱ ሳይታክት የሚሠራ አለ ወይ?" ሲል ጠንከር ያለ ጥያቄ አቅርቧል።
ስብስቡ ነሐሴ 1 ቀን 2018 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ እንዳመለከተው፣ በሰላማዊ የፖለቲካ ትግል ለውጥ ማምጣት ይቻላል ብለው የሚያምኑት አቶ አበበ አካሉ፣ አቶ ይስኃቅ ወልዳይ እና ጠበቃ አበራ ንጉሥ ሐምሌ 27 ቀን 2018 ዓ.ም ለእስር መዳረጋቸው በህዝቡ ዘንድ ከፍተኛ ድንጋጤን ፈጥሯል። ይህንን ክስተትም እጅግ አስደንጋጭ ሆኖ እንዳገኘው አስታውቋል።
አሁን ስራ ላይ ባለው ህገ መንግስት አንቀጽ 29 ንዑስ አንቀጽ 2 ላይ ማንኛውም ሰው ያለ ማንም ጣልቃ ገብነት ሀሳቡን በነጻነት የመግለጽ፣ በምንም አይነት የማሰራጫ ዘዴ መረጃን የመሰብሰብ፣ የመቀበልና የማሰራጨት መብቱ የተረጋገጠ መሆኑን መግለጫው አስታውሷል። ይሁን እንጂ አሁን ባለው ተጨባጭ ሁኔታ፣ ከህገ መንግስቱ ባፈነገጠ መልኩ ከውዳሴ በስተቀር ምንም አይነት የተቃውሞ እና የትችት ድምጾች እንዳይሰሙ ማሳደድ ያልተጻፈ ህግና መርህ መሆኑን ስብስቡ በመግለጫው አትቷል።
ይህ አካሄድ "ሰላማዊ ትግል ሙሉ በሙሉ ተዘግቶ ሌሎች አማራጮች እንዲናኙ የሚሰራ ግራ ሃይል ተፈጥሯል ወይ?" የሚል ጥርጣሬ እንዳሳደረበት 'ትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት' በግልጽ አስቀምጧል። በመሆኑም መንግስት በጠባብ ቀዳዳ የምትታየውን የፖለቲካ ምህዳር ጭራሹኑ ከማጥፋት ክፉኛ ሊጠነቀቅ ይገባል በማለት፣ በእስር ላይ የሚገኙት የሰላማዊ ፖለቲካ ታጋዮች የዋስትና መብታቸው ተከብሮ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ በአስቸኳይ እንዲፈቱ ጥሪውን አስተላልፏል።

8 hours ago
ነገ ነሐሴ 2 ቀን በተለያዩ አካባቢዎች የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት ይቋረጣል
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የጥገና ሥራ ለማከናወን ባቀደው መሠረት፣ ነገ ነሐሴ 2 ቀን 2018 ዓ.ም በተለያዩ አካባቢዎች የኃይል አቅርቦቱ ለጊዜው ይቋረጣል።
⏰ከጠዋቱ 2፡00-9፡30
👉ጀርመን አደባባይ፣ ጎፋ ካምፕ፣ መካነ ኢየሱስ፣ ጎፋ ዳታ ሴንተር፣ ጎፋ ስቶር፣ ኳስ ሜዳ፣ አይሱዙ ጋራዥ፣ ሶፉመር ብሎኬት ማምረቻ፣ ባቱ ኮንዶሚኒየም እና አካባቢው፣
👉መካኒሳ አረቄ ፋብሪካ፣ አሚጎ ካፌ፣ ቫቲካን ኤምባሲ፣መካኒሳ አቦ ቤ/ክ፣ የመከላከያ ሚ/ር፣ ጥቁር አባይ የቤትና የቢሮ ዕቃዎች ማምረቻ፣ ሰላም አስከባሪ እና አካባቢው፣
👉ካራ ቆሬ፣ መድኃኔዓለም፣ኢትዮሆፕ ት/ቤት፣ ካራቆሬ ውሃ፣ ካራቆሬ ኮንዶሚኒየም እና አካባቢው፣
👉አየር ጤና፣ መድሐኒዓለም መውጫ፣ ሬዲዮ ፋና፣ ቻይና ካምፕ፣ ዘነብ ወርቅ እና አካባቢው፣
⏰ከጠዋቱ 3፡00-10፡30
👉አራብሳ የአዲስ አበባ ከተማ መስተዳደር እንጀራ ማምረቻ ፋብሪካ፣ ጨርቆስ አራብራ፣ አራብሳ አዲሱ ኮንዶሚንየም በከፊል፣ ገላን በከፊል፣ አራብሳ ኮንዶሚየም እና አካባቢው፣
👉 ኢትዮ ቻይና፣ የአስተማሪዎች መኖሪያ ቤት፣ ለሚኩራ ወረዳ 5፣ አራብሳ ፓሊስ ጣቢያ፣ አቦ ቤተክርስቲያን እና አካባቢው፣ የውሃ ማጣሪያ ታንከር፣ ቴሌ ታወር እና አካባቢው፣
⏰ ከጠዋቱ 3፡00-10፡00
👉ሰበታ ከተማ፣ አለምገና ሚካኤል፣ ኢትዮ ሴራሚክ፣ ሜታ፣ ገዳም ሰፈር፣ ዳለቲ ኢንዱስትሪ፣ ዳለቲ ቄራ፣ ገዳምባ፣ አለምገና ኢንዱስትሪ እና አካባቢው፣
👉 ሱሉልታ ከተማ፣ ጭሮ ደደር ወረዳ፣ መልካ ቦሎ ወረዳ፣ ሜታ ወረዳ፣ ጎሮ ጉቱ ወረዳ እና አካባቢዎች፣
⏰ ከጠዋቱ 3፡00-11፡00
👉ቂሊንጦ ኮንዶሚየም፣ አዲስ አበባ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዮኒቨርስቲ፣ ቂሊንጦ ላይ ሰፈር፣ ቂሊንጦ ሚካኤል፣ ሌስ ፍራንስ ት/ቤት፣ ቤጂንግ ሆስፒታል፣ አሳማ ጊቢ እና አካባቢው፣
👉 ኮዬ አደባባይ፣ ዋሊያ ቢራ፣ አለም ባንክ፣ ኢንዲያና ት/ቤት፣ ታፍ ማደያ፣ አቃቂ ብሩህ ተስፋ ት/ቤት፣ ኮፊ ሲቲ እና አካባቢው፣
⏰ ከጠዋቱ 2፡00-11፡30
👉ገላን ልደታ ቤ/ክ አካባቢ፣ገላን ኮንዶሚኒየም፣ ገላን ብሎኬት ማምረቻ፣ገላን ከርሰ ምድር እና አከባቢው
👉አዳማ፣ አዳሚቱሉ፣ መቂ ከተማ፣ በህርዳር ቀበሌ 16፣ ህዳሴ ሰፈር እና አከባቢው የሃይል አቅርቦት ይቋረጣል፡፡
ስለሆነም በአካባቢው የምትገኙ ክቡራን ደንበኞቻችን ይህንኑ በመገንዘብ ከወዲሁ ተገቢውን ቅድመ ዝግጅት እንድታደርጉ በአክብሮት እናሳውቃለን፡፡
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት

1 day ago
አልማ ለ2019 በጀት ዓመት ከ4.3 ቢሊዮን ብር በላይ የልማት ሀብት ለማሰባሰብ አቀደ
#ethiopia | የአማራ ልማት ማህበር (አልማ) የ2018 በጀት ዓመት አፈጻጸምን በመገምገም የ2019 በጀት ዓመት ዕቅዱን ያስተዋወቀ ሲሆን፣ የዕቅዱን ስኬት ለማረጋገጥ የቅድመ ዝግጅት ምዕራፍን በሙሉ ማጠናቀቅ እንደሚገባ ዋና ሥራ አስፈጻሚው አቶ መላኩ ፈንታ አሳስበዋል።
በዋና መሥሪያ ቤቱ ለሁለት ቀናት በተካሄደው የምክክር መድረክ፣ ከ11 ዞኖች የተውጣጡ የማኔጅመንት አባላትና የወረዳ ጽሕፈት ቤት ኃላፊዎች ተሳትፈው በቀጣዩ ዓመት የሚተገበሩ ዋና ዋና የልማት ፕሮጀክቶች ላይ ተወያይተዋል።
ስትራቴጂክና ኢኖቬሽን ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ አበረ መኩሪያ እንደገለጹት፣ በ2019 በጀት ዓመት ከአባላት 4.3 ቢሊዮን ብር፣ ከዳያስፖራ ከ34 ሚሊዮን ዶላር በላይ እና ከአጋር ተቋማት 55 ሚሊዮን ዶላር የልማት ሀብት ለማሰባሰብ ታቅዷል።
በተያዘው ዕቅድ 2,051 የመማሪያ ክፍሎች፣ 38 የጤና ተቋማት፣ 8 የቴክኒክ ኮሌጅ ወርክሾፖች እና 2 ሸዶች እንዲገነቡ ታቅዷል። ይህን ግዙፍ ዕቅድ ለማሳካት የህዝብ ተሳትፎን ማሳደግ፣ ከአጋር አካላትና ከዳያስፖራው ጋር የተጠናከረ ትብብር መፍጠር ወሳኝ መሆኑ ተገልጿል።
አቶ መላኩ ፈንታ በማጠቃለያ ንግግራቸው፣ በ2019 በጀት ዓመት የዲጂታል ሽግግርን ማፋጠን፣ የአፈጻጸም ጥራትን ማሻሻል፣ የተቋሙን ብራንድ ማጠናከርና ዘላቂ የፋይናንስ አቅም መፍጠር ዋና ትኩረቶች እንደሚሆኑ ገልጸዋል።
በመድረኩ መጨረሻ በ2018 በጀት ዓመት የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ የዞንና የወረዳ አልማ ጽሕፈት ቤቶች፣ እንዲሁም ለተመራጭ ሠራተኞች የማበረታቻ ሽልማትና የምስክር ወረቀት ተሰጥቷል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)

የጥገና ሥራ ለማከናወን የሚቋረጥ የኃይል አቅርቦት
ነሐሴ 1 ቀን 2018 ዓ.ም የጥገና ሥራ ለማከናወን የኃይል አቅርቦት የሚቋረጥባቸው አካባቢዎች፦
✅ከጠዋቱ 3:00-10:00
👉ገርጂ ኮንዶሚኒየም፣ ገርጂ ተወካዮች ምክርቤት መኖሪያ ፣ ሰንሻይን ሪልስቴት ፣ አየር መንገድ በቀራኒዮ፣ በአሸዋ ሜዳ፣ በጦቢያ፣ በካጂማ፣ በመሐል ከተማ፣ በዓለሙ ማደያ ፣ በጎርአርባ እና አካባቢው፣
👉 በገላን መኖሪያ ቤቶች፣ በገመዳ ማህበር፣ በስላሴ ወሌ፣ በአባበ ጀርባ፣ በለገዲማ በባቡር ሐዲድ፣ በሲዳሞ አዋሽ፣ በገንደ ቆሬ እና አካባቢው፣
👉 በአቃቂ ኬላ፣ በገላን ኢንዱስትሪ መንደር፣ በወሰርቢ፣ በበላይነህ ክንዴ፣ ካፍ ማደያ ፣ በቱሉ ዲምቱ ማኅበር ቤቶች፣ በቱሉ ዲምቱ የጋራ መኖሪያ ቤቶች፣ በቱሉዲምቱ አርሴማ እና አካባቢው፣
✅ከጠዋቱ 2፡00-10፡30
👉ጣፎ፣ክብር ደመና፣ሰላም ቪሌጅ፣ጣፎ ገብርኤል፣ጋሪ ረታ፣ ባጃጅ ተራ፣አያት ለገጣፎ፣ሱሉልታ ቆዳ ፋብሪካ ፣ ኮሶ በር፣ አቢሲኒያ ሲሚንቶ፣ ሙሎ፣ ገላን እና አካባቢው፣
✅ከጠዋቱ 2፡00-11፡00
👉ለቡ አርሴማ ፊትለፊት፣ ዊጃን ሶል ፋብሪካ፣ ን/ስልክ ፖሊስ፣ ዮበክ ሪልእስቴት፣ ጎፋ ካምፕ ኮንዶሚኒየም፣ ጀርመን አደባባይ፣ ጉራጌ ሰፈር፣ ትግሬ ሰፈር፣ ካፍ ነዳጅ ማደያ ጀርባ፣ አርሴማ ቤተክርስቲያን፣ በብስራተ- ገብርኤል፣ በጀርመን አደባባይ፣ በቆሼ እና አካባቢው፣
✅ከጠዋቱ 3፡00-11፡00
👉በቡራዪ ከተማ ፣ በአኔ ዲማ ፣ በቡራዩ ድሬ፣ በኬላ፣ በመናገሻ ጭሮ፣ ጨለንቆ፣ ደደር፣ ሃራዋቻ፣ ኩፋንዚክ፣ ሶቃ፣ መከላ ባህርዳር፣ ልደታ፣ ይባብ፣ ትንሾች፣ ባታ 100 ካሬ፣ ቆጠቲና፣ዱዱ፣ ወልዲያ፣መርሳ እና ሲሪንቃ እና አካባቢው፣
ስለሆነም በአካባቢው የምትገኙ ክቡራን ደንበኞቻችን ይህንኑ በመገንዘብ ከወዲሁ ተገቢውን ቅድመ ዝግጅት እንድታደርጉ በአክብሮት እናሳውቃለን፡፡
#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት
Seledadotio

Sponsored by
Surafel
2 days ago
የደረጃ “ለ” ነጋዴዎች
👉መልእክት ያልደረሳችሁ ወይም
👉መልእክቱ ከሐምሌ 25 በኋላ የደረሳችሁ ያለቅጣት እስከ ነሐሴ 20 ቀን 2018 ዓ.ም መክፈል ስለምትችሉ በትዕግስት እንድትጠባበቁ ሲል የአ.አ ገቢዎች ቢሮ አሳስቧል።
ከሐምሌ 25 በፊት መልእክት የደረሳችሁ ግብር ከፋዮች ግን እስከ ሐምሌ 30 ቀን 2018 ዓ.ም በኦንላይን እንድትከፍሉ አሳስቧል።
የ2018 የግብር ዘመን የደረጃ “ለ” ግብር ከፋዮች አብዛኞቹ በኦንላይን የክፍያ ስርዓት ግብራቸውን መክፈላቸውና የተቀሩትም እየከፈሉ መሆኑ ተመላክቷል።
በከተማዋ በተለያዩ የንግድ ዘርፎች የተሰማሩ 456 ሺህ 433 የደረጃ “ለ” ግብር ከፋዮች እንደሚገኙና ከእነዚህ ግብር ከፋዮችም 9 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር ለመሰብሰብ መታቀዱም ተገልጿል።
የደረጃ “ለ” ነጋዴዎች ግብር ከተቀጣሪዎች ያነሰ መሆኑና ይህም የሆነው የከተማ አስተዳደሩ አነስተኛ ነጋዴዎችን ለማበረታታትና ለማሳደግ ባለው ቁርጠኝነት ምክንያት እንደሆነ መግለጫው አመላክቷል።
እስከ ሐምሌ 25 መልእክት የደረሳችሁ ግብር ከፋዮች እስከ ሐምሌ 30 ቀን 2018 ዓ.ም በኦንላይን እንድትከፍሉ፣ መልእክት ያልደረሳችሁ ወይም ከሐምሌ 25 በኋላ የደረሳችሁ ደግሞ ያለቅጣት እስከ ነሐሴ 20 ቀን 2018 ዓ.ም መክፈል ስለምትችሉ በትዕግስት እንድትጠባበቁ ሲልም ቢሮው አሳስቧል።
ግብር በዛብኝ የሚል ቅሬታ ላለው ማንኛውም ግብር ከፋይ የቅሬታ አፈታት ስርዓት ተዘርግቶ ወደ ተግባር የተገባ መሆኑንም ጠቁሟል።
በስልክ የጽሁፍ መልዕክት የተላከው የደረጃ “ለ” ዓመታዊ ግብር፣ ግብር ከፋዮች በቅድመ ታክስ የከፈሉትን ገንዘብ ተቀናሽ አድርጎ የያዘ እንደሆነም ተገልጿል።(ምንጭ፣ የአ.አ ገቢዎች ቢሮ)

የስንዴ ወፍጮ ቤት ሰርተው ልጃቸውን ለቁም ነገር ያበቁ ለዳውን ሲንድረም የተጋለጡ አባት
#ethiopia | የዳውን ሲንድረም ያለባቸው ሰዎች ልጅ ማሳደግ አይችሉም የሚለውን የተሳሳተ አመለካከት በመስበር በሶሪያ የሚኖሩት አባት ጃድ ኢሳ ሁሉን የሚያስተምር ታሪክ አስመዝግበዋል።
በስንዴ ወፍጮ ቤት ውስጥ ጠንክረው በመስራት ብቸኛ ልጃቸውን ሳደር ኢሳን በፍቅር፣ በእንክብካቤ እና በሙሉ ድጋፍ ያሳደጉት አባቱ፣ ለልጃቸው የትምህርት ስኬት ትልቅ መሠረት ሆነዋል።
የአባታቱ የማይወላወል ፍቅርና የሥራ ትጋት ብርታት የሆነው ሳደር በትምህርቱ ጠንክሮ በመማር የጥርስ ሐኪም መሆን ችሏል።
የወጣቱ ዶክተር አባት በታላቅ ኩራት "ልጄ ዶክተር ነው" ብለው በየቦታው እንዲናገሩ ሲሆን ፣የጃድና የሳደር ታሪክ እውነተኛ ወላጅነት የሚለካው በፍቅር፣ በመስዋዕትነትና በፅናት እንጂ በቅድመ-ግምት ወይም በጤና ሁኔታ አለመሆኑን ለዓለም ማሳያ ሆኗል።
በያፌት ገ/ህይወት
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu

የከተማ አስተዳደሩ በአነስተኛ የንግድ ስራ ላይ የደረጃ ‹‹ለ›› ግብር ከፋዮች እንዲበረታቱ ፣ የግብር ጫና እንዳይደርስባቸውና ትርፋማነታቸውን በማጎልበት ወደ ቀጣይ ደረጃ እንዲሸጋገሩ በቁርጠኛነት እየሰራ መሆኑን ቢሮው አስታወቀ ፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ በደረጃ ግብር ከፋዮች አከፋፈል ፣በሚነሱ ጥያቄዎችና ቅሬታዎች አፈታት ዙሪያ ለሚዲያ ተቋማት ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል ።
ቢሮው ባለፉት 2 አመታት ሰፋፊ የሪፎርም ተግባራት ማከናወኑን በጋዜጣዊ መግለጫው የተገለፀ ሲሆን የሪፎርም ተግባራቱ መሰረታዊ ዓላማዎችም ፍትሐዊ የግብር አሰባሰብ ስርዐት መዘርጋት ፣ የመልካም አስተዳደር እና የአገልግሎት አሰጣጥ እንዲሁም የሌብነትና ብልሹ አሰራሮችን መቅረፍ መሆናቸው ተጠቁሟል፡፡
የ2018 የግብር ዘመን የደረጃ ‹‹ለ›› ግብር ከፋዮች ጋር በተያያዘም አብዛኞቹ ግብር ከፋዮች በተቋሙ በተዘረጋ የኦንላይን የክፍያ ስርዓት መወጣታቸውና የተቀሩትም እየከፈሉ ናቸው ተብሏል፡፡
በተጨማሪም በከተማዋ በተለያዩ ንግዶች ፣ በኪራይና በራይድ የንግድ ዘርፎች የተሰማሩ 456 ሺህ 433 የደረጃ ግብር ከፋዮች የሚገኙ መሆናቸው የተጠቆመ ሲሆን ከእነዚህ ግብር ከፋዮች በአጠቃላይ 9.2 ቢሊዮን ብር ለመሰብሰብ መታቀዱ ተመላክቷል፡፡
ይህ ዓመታዊ የደረጃ ‹‹ለ›. ግብር ከፋዮች ገቢ በመንግስትና በግል ድርጅት ውስጥ ከሚገኙ ተቀጣሪ ደሞዝተኞች ዓመታዊ ደሞዝ ገቢ ግብር ጋር ሲነፃፀር በጣም አነስተኛ እንደሆነ ተገልጿል
ይህም በዋነኛነት ዐላማው የከተማ አስተዳደሩ በአነስተኛ የንግድ ስራ ላይ የተሰማሩ ነጋዴዎች እንዲበረታቱ፣ የግብር ጫና እንዳይደርስባቸውና ትርፋማነታቸውን በማጎልበት ወደ ቀጣይ ደረጃ እንዲሸጋገሩ ካለው አቋምና ቁርጠኛነት የመነጨ መሆኑም ተብራርቷል፡፡
በመሆኑም እስከ ሀምሌ 25 ድረስ ዓመታዊ ግብራችሁን እንድትከፍሉ መልዕክት በስልካችሁ የተላከላችሁ ግብር ከፋዮች በሙሉ እስከ ሀምሌ 30/2018 ዓ.ም ድረስ የግብር ግዴታችሁን በኦንላይን በመክፈል ከቅጣትና ወለድ እራሳችሁን እንዲጠብቁ ጥሪ ተላልፏል፡፡
ይሁንና በተለያዩ ምክንያቶች ቴክስት ያልደረሳችሁ ግብር ከፋዮች እንዲሁም ከሀምሌ 25 በኃላ ቴክሰት( መልዕክት ) የተላከላችሁ ግብር ከፋዮች ወደ ቅጣት የማይገቡ በመሆኑ እስከ ነሀሴ 20/2018 ዓ.ም ዓመታዊ ግብራችውን መክፈል እንደሚችሉ በመግለፅ ቴክስት ያልተላከላቸው ግብር ከፋዮች ባሉበት ሆነው በትዕግስት እንዲጠባበቁ ቢሮው ይገልፃል ፡፡
በተያያዘም ቴክስት (መልዕክት ) ከተላከለት በኃላ ‹‹ግብር በዛብኝ›› የሚል ቅሬታ ላለው ማንኛውም ግብር ከፋይ የቅሬታ አፈታት ስርዓት ተዘርግቶ ወደ ተግባር የተገባ መሆኑን የተገለፀ ሲሆን ቅሬታ ያለው ግብር ከፋይ በወረዳ ደረጃ ቅሬታ አቅርቦ መረጃው ለክፍለ ከተማ ከተላከ በኃላ በክፍለ ከተማ በተደራጀ የቀን ገቢ ገማች አማካኝነት ድጋሚ የቀን ገቢ ግምት በማካሄድ ቅሬታዎች የሚፈቱበት አሰራር መዘርጋቱ ተገልፆል፡፡
ከቅድመ ታክስ ክፍያ ጋር በተያያዘ ለደረጃ ‹‹ለ›› ግብር ከፋዮች በቴክስት የተላከ ዓመታዊ የግብር መጠንም ግብር ከፋዮች በቅድመ ታክስ የከፈሉትን የገንዘብ መጠን ተቀናሽ በማድረግ የተላከ እንደሆነም በጋዜጣዊ መግለጫው ተመላክቷል፡፡ በ2019 በጀት አመት እንደ ከተማ 502.27 ቢሊየን ፣ በገቢዎች ቢሮ 380 ቢሊየን ብር ገቢን በፍትሐዊነት ለመሠብሰብ መታቀዱም ተገልፆል፡፡
አዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ

(ዘ-ሐበሻ ስፖርት) የቅድመ ውድድር ዘመን ዝግጅቱን እያደረገ የሚገኘው አርሰናል፣ በአየርላንዷ ዱብሊን ከተማ ከስፔኑ ሪያል ቤቲስ ጋር ባደረገው ጨዋታ ያልተጠበቀ ሽንፈት ማስተናገዱን ተከትሎ የተጫዋቾቹ ስሜት በእጅጉ መጎዳቱን አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ ገለጹ።
መድፈኞቹ ባልተለመደ ሁኔታ የመከላከያ ክፍላቸው ክፉኛ ተዳክሞ በታየበት የመጀመሪያው አጋማሽ ብቻ ሶስት ግቦችን ለማስተናገድ ተገደዋል። ምንም እንኳን ቤቲሶች የኳስ ቁጥጥሩን ለአርሰናል አሳልፈው ቢሰጡም፣ እጅግ አደገኛ በሆኑ ሙከራዎች እና ዒላማቸውን በጠበቁ ኳሶች የአርቴታን ልጆች ብልጫ ወስደውባቸዋል።
ከመጀመሪያው አጋማሽ መጥፎ አቋም በኋላ በመልበሻ ክፍል ውስጥ ስለነበረው ድባብ የተጠየቁት አርቴታ "በጣም ተበሳጭተዋል፣ ከባድ ጊዜ ነበር ያሳለፉት። በንዴት ጦፈዋል፤ ግን ይሄ ጥሩ ነው። እኛም የምንፈልገው ይሄንን ነው" ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል።
አርቴታ አክለውም "ዋናው ነገር ማሸነፍ ነበር፣ ግን አልቻልንም፤ ስለዚህ በውጤቱ ማዘናችን አይቀርም። ሆኖም መጥፎ ውጤት ማምጣት ለቀጣይ የተሻለ ስራ የድል ረሃብን ስለሚፈጥር አንዳንድ ጊዜ ጠቃሚ ነው" ብለዋል።
የዓለም ዋንጫ ተሳትፎን ተከትሎ ዴክላን ራይስ፣ ኤቤሬቺ ኤዜ፣ ኖኒ ማዱኤኬ እና ቡካዮ ሳካ አሁንም ስብስቡን አልተቀላቀሉም። የስፔን ብሔራዊ ቡድን ተጫዋቾቹ ሚኬል ሜሪኖ፣ ዴቪድ ራያ እና ማርቲን ዙቢሜንዲም እንዲሁ አልተመለሱም። አምበሉ ማርቲን ኦዴጋርድ ግን ከኖርዌይ ብሔራዊ ቡድን ተሳትፎው መልስ ግላዊ ልምምድ ጀምሯል።
ይሁን እንጂ አርሰናል እነዚህ ቁልፍ ተጫዋቾች ባይኖሩትም በቋሚ አሰላለፉ አራት ዓለም አቀፍ ተከላካዮችን፣ እንዲሁም ኢታን ኑዋኔሪ፣ ካይ ሃቨርትዝ፣ አዲሱ ፈራሚ ክሪስቶስ ዞሊስ እና ማክስ ዶውማንን በአማካይ ስፍራ፣ ቪክቶር ጊዮከረስን ደግሞ በአጥቂ መስመር አሰልፎ ነበር።
ባለፈው ሳምንት ጂሮናን 4-1 ባሸነፈበት አሰላለፍ ወደ ሜዳ የገባው አርሰናል፣ በጨዋታው መባቻ ጊዮከረስ ያገኘውን ግሩም አጋጣሚ የቤቲሱ ግብ ጠባቂ አልቫሮ ቫሌስ በእግሩ መልሶበታል። ሆኖም በ9ኛው ደቂቃ ላይ አርሰናሎች ጠንካራ ከሆኑበት የማዕዘን ምት ቤቲሶች ቀዳሚውን ግብ አግኝተዋል። ተቀያሪው ግብ ጠባቂ ኬፓ አሪዛባላጋ በፓብሎ ፎርናልስ የተመታውን ኳስ በአግባቡ ባለማንበቡ፣ ሮድሪጎ ሪኬልሜ ያለምንም ከልካይ ኳሷን መረብ ላይ አሳርፏል።
በአማካይ ስፍራ የተሰለፈው ወጣቱ ማይልስ ሉዊስ-ስኬሊ ከሌሎች የተሻለ እንቅስቃሴ ያሳየ ሲሆን፣ ሪካርዶ ካላፊዮሪ ወደ ፊት በሚሄድበት ጊዜ ቦታውን እየሸፈነ ድንቅ ስራ ሰርቷል። የግሪኩ ክንፍ ተጫዋች ዞሊስ የግብ ጠባቂውን ስህተት ተጠቅሞ አቻ የሚያደርግበትን ኳስ ቢያገኝም ኢላማውን ሳይጠብቅ ወደ ውጪ ወጥቶበታል።
ከ20 ዓመታት በኋላ ወደ ሻምፒዮንስ ሊግ የተመለሰው ሪያል ቤቲስ፣ በአርሰናል ስህተቶች ላይ በሚገባ ተጫውቷል። በ26ኛው ደቂቃ ኬፓ የሰራውን ደካማ የኳስ አወጣጥ ስህተት ተጠቅሞ ኔልሰን ዴኦሳ ከ25 ያርድ ርቀት ላይ አስደናቂ ግብ አስቆጥሯል። በ32ኛው ደቂቃ ዞሊስ ያሻገረውን ኳስ ፒዬሮ ሂንካፒ በጭንቅላቱ በመግጨት ለአርሰናል አንድ ግብ ቢመልስም፣ በ43ኛው ደቂቃ ላይ ካይ ሃቨርትዝ የሰራውን ስህተት ተጠቅሞ ፓብሎ ፎርናልስ የቤቲስን ሶስተኛ ግብ ከመረብ አዋህዷል።
በሁለተኛው አጋማሽ አርቴታ ጋብሪኤል ማርቲኔሊን እና ጋብሪኤል ማጋልሃስን ጨምሮ ሰባት ተጫዋቾችን ቀይረው አስገብተዋል። የ16 ዓመቱ ተከላካይ ማርሊ ሳልሞን እና የ19 ዓመቱ ሉዊ ኮፕሊም የመሰለፍ እድል ቢያገኙም፣ ኮፕሊ ገብቶ በሰባት ደቂቃ ውስጥ በደረሰበት የጉልበት ጉዳት ለመውጣት ተገዷል። በቅያሪዎች ብዛት የጨዋታው ምት የቀዘቀዘ ሲሆን፣ ጋብሪኤል ጄሱስ የተሻለ ሙከራ ቢያደርግም፣ አርቴታ በሜዳው ዳርቻ በብስጭት ሲንጎራደዱ ታይተዋል፤ መድፈኞቹም ያጡትን ክፍተት ማጥበብ ሳይችሉ ጨዋታው ተጠናቋል።

ሐምሌ 30 ቀን 2018 ዓ.ም የጥገና ሥራ ለማከናወን የኃይል አቅርቦት የሚቋረጥባቸው አካባቢዎች
✅ከጠዋቱ 4፡00-11፡00
👉ኮተቤ፣ መሪ፣ አያት አደባባይ፣ ሲቪል ሰርቪስ፣ መሪ ሚካኤል፣ ተ/ብርሃን አምባዬ፣ ቡራዩ መስጊድ እና አካባቢው፣
👉ሪፍት ቫሊ ዩኒቨርሲቲ ፣ ፀርሐ ፅዮን ቤ/ክ ፣ ቡራዩ ወለጋ ሰፈር፣ ድሬ ከአስፋልት በታች፣ ጉዳ፣ ኬላ፣ ጉዮ እና አካባቢው፣
👉ታጠቅ ኢንዱስትሪ መንደር በከፊል፣ቶልቻ፣ድሬ ከአስፋልት በላይ፣ ገፈርሳ ውሀ ግድብ፣ ሲሊ፣ ከረላ፣ መናገሻ እና አካባቢው፣
✅ከጠዋቱ 2፡00-10፡30
👉ለገጣፎ ባጫ ሞል፣ሚካኤል ቤ/ክ፣ የካአባዶ፣ ኮዬ ፈጬ እና አካባቢው፣
✅ከጠዋቱ 3፡00-10፡00
👉10 ኪሎ በከፊል፣ ዶሮ እርባታ ፣ ቀንብሬ፣ አፍሪካ ልሕቀት ማዕከል፣ አርኪ ውሃ፣ ሱሉልታ መሐል ከተማ፣ ለገዲማ ፣ ጫንጮ አቢሲኒያ እና አካባቢው፣
👉ሲሚንቶ፣ ሳሊተ ምሕረት ቤ/ክ ፣ ጆርጅ ዘይት ቤት፣ ሜታ ቢራ አካባቢ አካባቢው የኤሌክትሪክ ኃይል ይቋረጣል።
ስለሆነም በአካባቢው የምትገኙ ክቡራን ደንበኞቻችን ይህንኑ በመገንዘብ ከወዲሁ ተገቢውን ቅድመ ዝግጅት እንድታደርጉ እናሳውቃለን።

(ዘ-ሐበሻ ዜና) የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የኢትዮጵያ ህዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ (ኢህአፓ) የህዝብ ግንኙነት ኃላፊን ጨምሮ ከፓርቲው ጋር ግንኙነት ያላቸውን ሶስት ግለሰቦች ህገ-መንግስታዊ ስርአቱን በኃይል ለመናድ አሴረዋል በሚል ወንጀል ከሷቸዋል። ፖሊስ በነዚህ ግለሰቦች ላይ ተጨማሪ ምርመራ ለማድረግ የ14 ቀናት የጊዜ ቀጠሮ ጠይቋል።
ክሱ የቀረበው የፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቢሮ ለፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ አንደኛ ደረጃ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት ባቀረበው የቅድመ ምርመራ ጥያቄ ላይ ነው። ይህ የሆነው ኢህአፓ የሶስቱን ግለሰቦች መታሰር ካረጋገጠ ከአንድ ቀን በኋላ ነው። የታሰሩት ግለሰቦች የፓርቲው የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ይስሃቅ ወልዳይ፣ ከፓርቲው ጋር ግንኙነት ያላቸውን ግለሰቦች በህግ ሲወክሉ የነበሩት ጠበቃ አበራ ንጉስ አየነው፣ እና መምህር እንዲሁም የኢህአፓ አባል የሆነው አበበ አካሉ ክብረት ናቸው።
የኢህአፓ ዋና ፀሀፊ ሚስጥረ-ስላሴ ታምራት እስሩ መጀመሩን አረጋግጠው፣ ጠበቃ አበራ ንጉስ እና ይስሃቅ ወልዳይ መጀመሪያ በቁጥጥር ስር ሲውሉ፣ አበበ አካሉ ደግሞ በማግስቱ መታሰሩን ገልፀዋል። ፓርቲው ባወጣው አጭር መግለጫ፣ ግለሰቦቹ በሰላማዊ መንገድ ሀሳብን በነፃነት በመግለፃቸው ብቻ መታሰራቸውን አውግዞ፣ ሰላማዊ የፖለቲካ ትግል ወንጀል ስላልሆነ በአስቸኳይ እንዲፈቱ ጠይቋል።
በሌላ በኩል የፌደራል ፖሊስ የክስ መዝገብ እንደሚያትተው፣ ግለሰቦቹ የታሰሩት በፖለቲካዊ እንቅስቃሴ ሳይሆን በኃይል ስልጣን ለመያዝ በተቀናጀ ሴራ ውስጥ በመሳተፋቸው ነው። የፖሊስ የምርመራ ቢሮ እንዳለው፣ ተጠርጣሪዎቹ ህጋዊውን የፖለቲካ ፓርቲ እንደ ሽፋን በመጠቀም ከፓርቲው ህገ-ደንብ እና አላማ ውጪ መንግስትን በኃይል ለመገልበጥ ተንቀሳቅሰዋል። ፖሊስ አክሎም ግለሰቦቹ "የሀገር ውስጥ እና የውጭ ታሪካዊ ጠላቶች" ከተባሉት ህወሓት፣ ፅምዶ ከተባለ ቡድን እና ሌሎች ፀረ-ሰላም ኃይሎች ጋር በቅንጅት ሲሰሩ እንደነበር ወንጅሏል። በአዲስ አበባ አባላትን በመመልመል፣ የፀጥታ ኃይሎችን እንቅስቃሴ በመከታተል እና መረጃዎችን ለታጠቁ ኃይሎች በማስተላለፍ ተሳትፈዋል ተብለዋል።
ፖሊስ በክሱ ላይ እንዳሰፈረው ተጠርጣሪዎቹ የፖለቲካ፣ የወታደራዊ ስልጠና፣ የሚዲያ ፕሮፓጋንዳ እና የድርጊት መርሃ-ግብር አስፈፃሚ ክንፎችን በማዋቀር ህገ-ወጥ አደረጃጀት ፈጥረዋል። አንከር ሚዲያ፣ ኢትዮ-ፎረም እና ኢትዮ 360 ሚዲያን ጨምሮ በውጭ ከሚገኙ መገናኛ ብዙሃን ጋር በመተባበር ህዝቡን በመንግስት ላይ ለማነሳሳት የሀሰት መረጃዎችን ሲያሰራጩ እንደነበርም ተጠቅሷል።
ከዚህም ባሻገር ከከፍተኛ የህወሓት አመራሮች ጋር በሚስጥር በመገናኘት በአዲስ አበባ በሚገኙ የመንግስት የፀጥታ ተቋማት እና ከፍተኛ ባለስልጣናት ላይ የሽብር ጥቃት ለማድረስ ዝግጅት ሲያደርጉ በፀጥታ ኃይሎች ጥብቅ ክትትል በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገልጿል። ጉዳዩ እጅግ ውስብስብ እና ሀገራዊ አንድነትን የሚያፈርስ መሆኑን የገለፀው ፖሊስ፣ ተጠርጣሪዎቹ በዋስ ቢለቀቁ ምስክሮችን ሊያባብሉ ወይም ሊያስፈራሩ ይችላሉ በሚል ተጨማሪ የ14 ቀን የምርመራ ጊዜ እንዲሰጠው ፍርድ ቤቱን ጠይቋል።

በመዲናዋ የደረጃ “ለ” ግብር ከፋዮች የግብር ጫና እንዳይደርስባቸው እየተሰራ ነው
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ በመዲናዋ በአነስተኛ የንግድ ስራ ላይ የተሰማሩ የደረጃ “ለ” ግብር ከፋዮች እንዲበረታቱ፣ የግብር ጫና እንዳይደርስባቸውና ትርፋማነታቸውን በማጎልበት ወደ ቀጣይ ደረጃ እንዲሸጋገሩ በቁርጠኛነት እየሰራሁ ነው አለ።
ቢሮው በደረጃ “ለ” ግብር ከፋዮች አከፋፈል በሚነሱ ጥያቄዎችና ቅሬታዎች አፈታት ዙሪያ በሰጠው መግለጫ፤ ባለፉት ሁለት ዓመታት ሰፋፊ የሪፎርም ተግባራት ተከናውነዋል።
የሪፎርም ተግባራቱ ፍትሐዊ የግብር አሰባሰብ ስርዓት መዘርጋት፣ የመልካም አስተዳደር እና የአገልግሎት አሰጣጥ እንዲሁም የሌብነትና ብልሹ አሰራሮችን መቅረፍ የሚያስችሉ መሆናቸው ተጠቁሟል፡፡
የ2018 የግብር ዘመን የደረጃ “ለ” ግብር ከፋዮች አብዛኞቹ በኦንላይን የክፍያ ስርዓት ግብራቸውን መክፈላቸውና የተቀሩትም እየከፈሉ መሆኑ ተመላክቷል።
በከተማዋ በተለያዩ የንግድ ዘርፎች የተሰማሩ 456 ሺህ 433 የደረጃ “ለ” ግብር ከፋዮች እንደሚገኙና ከእነዚህ ግብር ከፋዮችም 9 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር ለመሰብሰብ መታቀዱም ተገልጿል።
የደረጃ “ለ” ነጋዴዎች ግብር ከተቀጣሪዎች ያነሰ መሆኑና ይህም የሆነው የከተማ አስተዳደሩ አነስተኛ ነጋዴዎችን ለማበረታታትና ለማሳደግ ባለው ቁርጠኝነት ምክንያት እንደሆነ መግለጫው አመላክቷል።
እስከ ሐምሌ 25 መልእክት የደረሳችሁ ግብር ከፋዮች እስከ ሐምሌ 30 ቀን 2018 ዓ.ም በኦንላይን እንድትከፍሉ፣ መልእክት ያልደረሳችሁ ወይም ከሐምሌ 25 በኋላ የደረሳችሁ ደግሞ ያለቅጣት እስከ ነሐሴ 20 ቀን 2018 ዓ.ም መክፈል ስለምትችሉ በትዕግስት እንድትጠባበቁ ሲልም ቢሮው አሳስቧል።
ግብር በዛብኝ የሚል ቅሬታ ላለው ማንኛውም ግብር ከፋይ የቅሬታ አፈታት ስርዓት ተዘርግቶ ወደ ተግባር የተገባ መሆኑንም ጠቁሟል።
በስልክ የጽሁፍ መልዕክት የተላከው የደረጃ “ለ” ዓመታዊ ግብር፣ ግብር ከፋዮች በቅድመ ታክስ የከፈሉትን ገንዘብ ተቀናሽ አድርጎ የያዘ እንደሆነም ተገልጿል።
በአዲስ አበባ ከተማ በ2019 በጀት ዓመት 502 ነጥብ 27 ቢሊየን፣ በገቢዎች ቢሮ 380 ቢሊየን ብር ገቢን በፍትሐዊነት ለመሠብሰብ መታቀዱም ተጠቁሟል።

3 days ago
በሳር ቤት አደባባይ ሱቅ
1ኛ ፎቅላይ
23 ካሬ
👉ጠቅላላ ዋጋ=6.9 ሚሊየን ብር
👉ቅድመ ክፍያ=2.5ሚሊየን
16 ካሬ
👉ጠቅላላ ዋጋ=4.6ሚሊየን ብር
👉ቅድመ ክፍያ=2.5ሚሊየን ብር
14 ካሬ
👉ጠቅላላ ዋጋ=3.96 ሚሊየን ብር
👉ቅድመ ክፍያ=2.5ሚሊየን ብር
2ኛ ፎቅ ላይ
23ካሬ
👉ጠቅላላ ዋጋ=5.1ሚሊየን ብር
👉ቅድመ ክፍያ=2 ሚሊየን ብር
20ካሬ
👉ጠቅላላ ዋጋ=4.4ሚሊየን ብር
👉ቅድመ ክፍያ=2 ሚሊየን ብር
13 ካሬ
👉ጠቅላላ ዋጋ=2.8ሚሊየን ብር
👉ቅድመ ክፍያ=2ሚሊየን ብር
3ኛ ፎቅ ላይ
25ካሬ
👉ጠቅላላ ዋጋ=4.9ሚሊየን ብር
👉ቅድመ ክፍያ=1.3ሚሊየን
20ካሬ
👉ጠቅላላ ዋጋ=4ሚሊየን ብር
👉ቅድመ ክፍያ=1.3ሚሊየን ብር
12ካሬ
👉ጠቅላላ ዋጋ=2.4ሚሊየን ብር
👉ቅድመ ክፍያ=1.3ሚሊየን ብር
4ኛ ፎቅ ላይ
36 ካሬ
👉ጠቅላላ ዋጋ=5.9ሚሊየን ብር
👉ቅድመ ክፍያ=900ሺ ብር
25 ካሬ
👉ጠቅላላ ዋጋ=4.1ሚሊየን ብር
👉ቅድመ ክፍያ=900ሺ ብር
20 ካሬ
👉ጠቅላላ ዋጋ=3.3ሚሊየን ብር
👉ቅድመ ክፍያ=900ሺ ብር
15ካሬ
👉ጠቅላላ ዋጋ=2.4ሚሊየን ብር
👉ቅድመ ክፍያ=900ሺ ብር
5ኛ ፎቅ ላይ
36ካሬ
👉ጠቅላላ ዋጋ=5.3ሚሊየን ብር
👉ቅድመ ክፍያ=900ሺ ብር
25 ካሬ
👉ጠቅላላ ዋጋ=3.9ሚሊየን ብር
👉ቅድመ ክፍያ=900ሺ ብር
20 ካሬ
👉ጠቅላላ ዋጋ=2.9ሚሊየን ብር
👉ቅድመ ክፍያ=900ሺ ብር
12ካሬ
👉ጠቅላላ ዋጋ=2ሚሊየን ብር
👉ቅድመ ክፍያ=900ሺ ብር
በ0901211153 ይደውሉልን
1ኛ ፎቅላይ
23 ካሬ
👉ጠቅላላ ዋጋ=6.9 ሚሊየን ብር
👉ቅድመ ክፍያ=2.5ሚሊየን
16 ካሬ
👉ጠቅላላ ዋጋ=4.6ሚሊየን ብር
👉ቅድመ ክፍያ=2.5ሚሊየን ብር
14 ካሬ
👉ጠቅላላ ዋጋ=3.96 ሚሊየን ብር
👉ቅድመ ክፍያ=2.5ሚሊየን ብር
2ኛ ፎቅ ላይ
23ካሬ
👉ጠቅላላ ዋጋ=5.1ሚሊየን ብር
👉ቅድመ ክፍያ=2 ሚሊየን ብር
20ካሬ
👉ጠቅላላ ዋጋ=4.4ሚሊየን ብር
👉ቅድመ ክፍያ=2 ሚሊየን ብር
13 ካሬ
👉ጠቅላላ ዋጋ=2.8ሚሊየን ብር
👉ቅድመ ክፍያ=2ሚሊየን ብር
3ኛ ፎቅ ላይ
25ካሬ
👉ጠቅላላ ዋጋ=4.9ሚሊየን ብር
👉ቅድመ ክፍያ=1.3ሚሊየን
20ካሬ
👉ጠቅላላ ዋጋ=4ሚሊየን ብር
👉ቅድመ ክፍያ=1.3ሚሊየን ብር
12ካሬ
👉ጠቅላላ ዋጋ=2.4ሚሊየን ብር
👉ቅድመ ክፍያ=1.3ሚሊየን ብር
4ኛ ፎቅ ላይ
36 ካሬ
👉ጠቅላላ ዋጋ=5.9ሚሊየን ብር
👉ቅድመ ክፍያ=900ሺ ብር
25 ካሬ
👉ጠቅላላ ዋጋ=4.1ሚሊየን ብር
👉ቅድመ ክፍያ=900ሺ ብር
20 ካሬ
👉ጠቅላላ ዋጋ=3.3ሚሊየን ብር
👉ቅድመ ክፍያ=900ሺ ብር
15ካሬ
👉ጠቅላላ ዋጋ=2.4ሚሊየን ብር
👉ቅድመ ክፍያ=900ሺ ብር
5ኛ ፎቅ ላይ
36ካሬ
👉ጠቅላላ ዋጋ=5.3ሚሊየን ብር
👉ቅድመ ክፍያ=900ሺ ብር
25 ካሬ
👉ጠቅላላ ዋጋ=3.9ሚሊየን ብር
👉ቅድመ ክፍያ=900ሺ ብር
20 ካሬ
👉ጠቅላላ ዋጋ=2.9ሚሊየን ብር
👉ቅድመ ክፍያ=900ሺ ብር
12ካሬ
👉ጠቅላላ ዋጋ=2ሚሊየን ብር
👉ቅድመ ክፍያ=900ሺ ብር
በ0901211153 ይደውሉልን
3 days ago
ኢትዮጵያዊቷን አትሌት ወደ ወንድ የሚያደላ የሆርሞን መብዛት አለባት በሚል ምክንያት ወደ አሜሪካ ሳትጓዝ ቀረች።
የፆታ ውዝግብ( የሆርሞን መብዛት ) ያለባት ኢትዮጵያዊት አትሌት ወደ አሜሪካ አልተጓዘችም ። በጋና አክራ የአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና በ400ሜ በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ለኢትዮጵያ የወርቅ ሜዳሊያ ያስመዘገበችውና በአሁኑ የአሜሪካ ኦሪገን....
ዩጂን ከ20 አመት በታች አትሌቲክስ ሻምፒዮና ጠንካራ ዝግጅት ስታደርግ የቆየችው እንዲሁም ለአሸናፊነት ቅድመ ግምት የተሰጣት አጃይባ አሊየ ወደ አሜሪካ ሳትጓዝ ቀርታለች።
አትሌት አጃይባ በሻምፒዮናው ላይ እንድትወዳደር ስም ዝርዝሯ የገባ እና የአሜሪካ ቪዛ ተሰጥቷት ነበር።
ለሲዲ ስፖርት ስማቸው እንዳይገለፅ የፈለጉ ባለሙያ አትሌቷ ከፆታ ውዝግብ ማለትም (ወደ ወንድ የሚያደላ የሆርሞን መብዛት) ጋር በተገናኘ ወደ ስፍራው ሳትሄድ ቀርታለች ማለታቸውን ጋዜጠኛ ሶፎንያስ እና ጋዜጠኛ ግርማቸው ተናግረዋል ።
ከዚህ ቀደም ኢትዮጵያውያኖቹ ፋንቱ ሜጌሶ እና ወርቅ ውሃ ጌታቸው እንዲሁም ደቡብ አፍሪካዊቷ ካስተር ሰሜንያ በተመሳሳይ ጉዳይ ስማቸው ሲነሳ እንደነበር አይዘነጋም ።
በሌላ በኩል ደግሞ የአትሌት አጃይባ ስም ውድድሩ ቦታ መለጠፉ ግዮን ማለዳ ተመልክቷል ። የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን እና አጋፋሪዎቹ እርስ በእርሱ የሚጣረስ ምክንያት ማቅረብ ሌላ ተጨማሪ ጥፋት ነው ።
ጉዳዩ ፈጣንና አስተማሪ እርምጃ ከሚመለከተው አካል ይሻል ትልቅ እድል ነው ያገኘችው በፍጥነት መፍትሔ ማግኘት አለባት ።

(ዘ-ሐበሻ ዜና) የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ የሀማስን ትጥቅ ለማስፈታት በቀረበው እና ሀማስ ባለፈው ሳምንት በተቀበለው የ"ቦርድ ኦፍ ፒስ" (የሰላም ቦርድ) እቅድ ላይ እስራኤል እንዳልተስማማች ለመጀመሪያ ጊዜ በይፋ ተናግረዋል። ኔታንያሁ ማክሰኞ ዕለት በፌስቡክ ገፃቸው ባወጡት የቪዲዮ መልእክት፣ ሀማስ ሙሉ በሙሉ ትጥቁን እስኪፈታ ድረስ እስራኤል አሁን በጋዛ ከያዘችው ይዞታ ወደ ኋላ እንደማታፈገፍግ በፅኑ አረጋግጠዋል።
ይህ የኔታንያሁ አቋም እስራኤል በጋዛ ወደነበረው የመጀመሪያው "ቢጫ መስመር" እንድትመለስ ከሚጠይቀው የአሜሪካ ድጋፍ ካለው የትጥቅ ማስፈታት እቅድ ጋር የሚቃረን ነው። እስራኤል በጥቅምት 2025 ከሀማስ ጋር በተደረገው የተኩስ አቁም እና ታጋቾችን የመልቀቅ ስምምነት መሰረት ወደዚህ መስመር አፈግፍጋ የነበረ ቢሆንም፣ ከዚያን ጊዜ ወዲህ ግን በሰርጡ ላይ ያላትን የቁጥጥር ድርሻ ከ53 በመቶ ወደ 60 በመቶ አሳድጋለች። የሰላም ቦርዱ ሀማስ መሳሪያውን ማስረከብ እስኪጀምር ድረስ እስራኤል ከቢጫው መስመር በላይ ማፈግፈግ እንደማይጠበቅባት ቢያመለክትም፣ ኔታንያሁ ግን የእስራኤል ጦር አሁን ካለበት ቦታ ንቅንቅ እንደማይል አስታውቀዋል።
ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ እና ቡድናቸው የሀማስን ትጥቅ ማስፈታት እንደሚችሉ በማሰብ ረቂቅ እቅድ እንደላኩላቸው የገለጹት ኔታንያሁ፣ እስራኤል ግን እቅዱን ሳትቀበል የራሷን ማስተካከያ መልሳ መላኳን አስረድተዋል። ይሁን እንጂ ይህ ረቂቅ በአሜሪካ፣ ግብፅ፣ ኳታር፣ ቱርክ እና ሀማስ መካከል በተደረገ የተናጠል ድርድር የተገኘ በመሆኑ ከእስራኤል ጋር ለድርድር ክፍት ይሆናል ተብሎ አልተጠበቀም ነበር። አንድ ከፍተኛ የአሜሪካ ባለስልጣን እንዳሉት፣ ይህ የትጥቅ ማስፈታት እቅድ እስራኤል ቀደም ብላ የተቀበለችው የትራምፕ የ20 ነጥብ የሰላም እቅድ አካል በመሆኑ፣ እስራኤል እቅዱን የምታደናቅፍ ከሆነ ትራምፕ በኢየሩሳሌም ላይ እጅግ እንደሚያዝኑ ተናግረዋል።
ይህንን ተከትሎ የሰላም ቦርዱ ከፍተኛ ልዑካን ኔታንያሁን ለማሳመን ሰኞ ዕለት ወደ ኢየሩሳሌም ያቀኑ ቢሆንም፣ ጥረታቸው ፍሬ አላፈራም። ቦርዱ ለእስራኤል በሚያደላ መልኩ የእቅዱን ማሻሻያ ለማድረግ ፍንጭ ቢያሳይም፣ የእስራኤልን ፍላጎት ለማስተናገድ መሞከር ወራት የፈጀውን የሀማስን ስምምነት ሊያሳጣ ይችላል የሚል ስጋት ተፈጥሯል።
በሌላ በኩል ማክሰኞ ዕለት፣ የሀማስ ከፍተኛ ባለስልጣን ጋዚ ሃማድ "ፒርስ ሞርጋን አንሴንሰርድ" በተሰኘው ታዋቂ ፕሮግራም ላይ ቀርበው ባደረጉት ቃለ ምልልስ፣ ጥቅምት 7 ቀን 2023 እስራኤል ላይ ባደረሱት ጥቃት ንፁሃንን ኢላማ እንዳላደረጉ መናገራቸው አነጋጋሪ ሆኗል። አብዛኛዎቹ አሰቃቂ ድርጊቶች በራሳቸው በታጣቂዎቹ ካሜራ የተቀረፁ ቢሆንም፣ ሃማድ "ምናልባት አንዳንድ ስህተቶች ተፈጥረው ሊሆን ይችላል" ከማለት ውጪ የንፁሃንን ግድያ አስተባብለዋል።
የ9 ወር ህፃን የነበረውን ክፊር ቢባስን ጨምሮ ስለታገቱ ቤተሰቦች በጋዜጠኛው በተጠየቁበት ወቅትም፣ በጦርነቱ መጀመሪያ ሀማስ ንፁሃንን ለመልቀቅ አቅርቦት የነበረውን ሀሳብ እስራኤል ውድቅ አድርጋዋለች ሲሉ ተሟግተዋል። ይሁን እንጂ በወቅቱ እስራኤል ታጋቾች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲለቀቁ ስትጠይቅ፣ ሀማስ በበኩሉ በሺህ የሚቆጠሩ እስረኞች እንዲለቀቁ እና ጦርነቱ እንዲቆም ቅድመ ሁኔታ ማስቀመጡ ይታወሳል። ጋዜጠኛው የሙዚቃ ድግስ ላይ የነበሩ በመቶዎች የሚቆጠሩ ንፁሃን ለምን እንደተገደሉ ላነሳው ጥያቄ፣ ሃማድ "እሱ በእቅዳችን ውስጥ አልነበረም" ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል።

4 days ago
(ዘ-ሐበሻ ዜና) አርሰናል የኒውካስል ዩናይትዱን አማካይ ብሩኖ ጊማሬስን ለማስፈረም ያቀረበው የመጀመሪያ የዝውውር ጥያቄ ውድቅ ተደርጓል። ኒውካስሎች በሴንት ጄምስ ፓርክ የሁለት ዓመት ኮንትራት (እንዲሁም ተጨማሪ የአንድ ዓመት አማራጭ) የቀረውን የ28 ዓመቱን ብራዚላዊ ኮከብ ማቆየት እንደሚፈልጉ አሳውቀዋል። ተጫዋቹ እሁድ ዕለት ከብራዚል የተነሳ ሲሆን፣ ከክለቡ ጋር ባደረገው ስምምነት መሰረት በስፔን ላ ማንጋ በሚገኘው የኒውካስል የቅድመ-ውድድር ልምምድ ላይ ከቡድን አጋሮቹ ጋር ተቀላቅሏል።
ብሩኖ ጊማሬስ በ2022 ከፈረንሳዩ ክለብ ሊዮን በ40 ሚሊዮን ፓውንድ ኒውካስልን ከተቀላቀለ በኋላ፣ ለክለቡ ባደረጋቸው 195 ጨዋታዎች 31 ግቦችን ማስቆጠር ችሏል።
ይህ የዝውውር ሂደት የኒውካስሉ አሰልጣኝ ኤዲ ሃው መልቀቃቸውን ተከትሎ የመጣ ነው። ጊማሬስ በኢንስታግራም ገጹ ላይ የቀድሞ አሰልጣኙን ምስል በማጋራት "የዚህ ክለብ ንጉስ!! ላደረግህልን ሁሉ እናመሰግናለን፤ የተሻልኩ ተጫዋች እና ሰው ስላደረግከኝ አመሰግናለሁ" በማለት አድናቆቱን ገልጿል። የእግር ኳስ ባለሙያው ጁሊያን ላውረንስ እንዳሉት፣ የኤዲ ሃው መልቀቅ አንዱ ምክንያት ጊማሬስ በመጨረሻ ወደ አርሰናል እንደሚሸጥ ማወቃቸው ነው።
ላውረንስ ይህንን የዝውውር ሂደት በሁለቱ ክለቦች መካከል የተጀመረ "የቼዝ ጨዋታ" ሲሉ ገልጸውታል። አርሰናል ከተጫዋቹ ግምት በላይ ለመክፈል እንደማይፈልግ እና ኒውካስል በበኩሉ ከፍተኛ ገንዘብ ለማግኘት እንደሚጥር ባለሙያው አብራርተዋል። ይሁን እንጂ የኒውካስልን የፋይናንስ ሁኔታ እና የተጫዋቹን ከአርሰናል ጋር ምንም አይነት የግል ችግር አለመኖር መሰረት በማድረግ፣ ዝውውሩ በሚቀጥሉት ሳምንታት ሊጠናቀቅ እንደሚችል ይጠበቃል።
ሚኬል አርቴታ ተጫዋቹን የሚፈልግበት ዋነኛ ምክንያት ጫናን ተቋቁሞ ኳስን የማንሸራሸር ብቃቱ ነው። አርሰናል ተጫዋቹን ማስፈረም ከቻለ፣ ዴክላን ራይስ እና ማርቲን ኦዴጋርድን በሁለት ጎኑ በማድረግ በአማካይ ስፍራ (ቁጥር 6) ላይ እንደሚያሰልፈው ይጠበቃል። ጄይ ቦዝሮይድ በስካይ ስፖርት ትንታኔው ላይ እንደጠቆመው፣ የራይስ እና የጊማሬስ ጥምረት በፕሪሚየር ሊጉ ምርጡ የአማካይ ክፍል ይሆናል።

805.3 ሚሊዮን ችግኞች በአንድ ጀምበር፤ የኢትዮጵያውያን ተአምራዊ ውሎ
*********************
ዛሬ በመላው ኢትዮጵያ “ተስፋን እንትከል” በሚል መሪ ቃል በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ዜጎች በአንድ ልብ እና በአንድ መንፈስ በመንቀሳቀስ በአንድ ጀምበር 805.3 ሚሊዮን ችግኞችን በመትከል አዲስ ታሪክ ፅፈዋል።
ኢትዮጵያውያን የዕድሜ ልዩነት ሳይበግራቸው ከሕፃናት እስከ አዛውንት ከአካል ጉዳተኞች እስከ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ሃላፊዎች በጋራ በመሆን አረንጓዴ አሻራቸውን አሳርፈዋል። ይህ የነቃ ተሳትፎም የማህበረሰቡን አንድነትና ለአካባቢ ጥበቃ ያላቸውን ጽኑ ቁርጠኝነት በግልጽ ያሳየ ነው።
ይህ መርሃ ግብር ልጆችን በማሳተፍ ስለ አካባቢ ጥበቃ አስፈላጊነት በተግባር የሚማሩበት ልዩ መድረክ ሆኗል። ህፃናት ከወዲሁ የችግኝ እንክብካቤን እንደ ባህል እንዲለምዱና የነገዋን አረንጓዴ አገር የመረከብ ሃላፊነታቸውን ገና በሕፃንነታቸው እንዲረዱ ያግዛል።
በተጨማሪም ሀገራዊ አንድነትን በተግባር ከመግለጹ በላይ ለአየር ንብረት ለውጥ አሳሳቢ ፈተናዎች ምላሽ ለመስጠትና የኢትዮጵያን የመጻኢ ዘመን ዕጣ ፈንታ በጽኑ መሠረት ላይ ለመገንባት ያለመ ንቅናቄ ነው።
ይህ የተቀናጀ ሀገራዊ ርብርብ የትናንቱ የአድዋ ድል የነፃነት አርበኝነት በተፈጥሮ ጥበቃ የሚደገምበት የዘመናችን የጀግንነት ምዕራፍ ተደርጎ ይወሰዳል።
ቀደምት አባቶች በአድዋ ተራሮች ላይ ልዩነቶቻቸውን አክስመው ለሀገር ነፃነት እንደቆሙ ሁሉ የዛሬው ትውልድም ድህነትንና የተፈጥሮ መራቆትን ለማሸነፍ ዕውቀቱን ጉልበቱንና ፍቅሩን አስተባብሮ ኢትዮጵያን አረንጓዴ የማልበስ ኃላፊነቱን እየተወጣ ይገኛል።
የምትተከለው እያንዳንዷ ችግኝ የተራቆቱ መሬቶች መልሰው እንዲያገግሙ የአፈር መሸርሸርና የጎርፍ አደጋዎች እንዲቀንሱ እንዲሁም የከርሰ ምድር ውሃ እንዲበለጽግ በማድረግ ረገድ ትልቁን ድርሻ ታበረክታለች።
ከአካባቢ ጥበቃ ፋይዳው ባሻገር መርሐ ግብሩ የሀገሪቱን ምጣኔ ሀብት የሚያነቃቃ ታላቅ ዕድል ፈጥሯል። በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ወጣቶች በችግኝ ማፍላት በጉድጓድ ዝግጅትና በተከላ ሥራዎች በመሰማራት ሰፊ የሥራ ዕድል ያገኙ ሲሆን በተለይም እንደ ቡና፣ አቮካዶና ማንጎ ያሉ የኢኮኖሚ ጠቀሜታ ያላቸው ተክሎች ትኩረት ማግኘታቸው ለአርሶ አደሩ ተጨማሪ የገቢ ምንጭ በመሆን የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ መሠረት ጥሏል።
በተጨማሪም ይህ ሀገራዊ ጥረት በዓለም አቀፍ ደረጃ የአየር ንብረት መዛባትን ለመቋቋም የሚረዳና ኢትዮጵያ ለዓለም አረንጓዴ ልማት ያላትን ቁርጠኝነት የሚያሳይ ሕያው ውርስ ነው።
ይህ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር በቅድመ ዝግጅት ከተያዘው እቅድ በላይ በመፈጸም በዛሬዉ ዕለት ብቻ 805.3 ሚሊዮን ችግኞች የተተከሉ ሲሆን 26.2 ሚሊየን ሰዎች ተሳትፈዋል በዚህም 291.4 ሺህ ሄክታር መሬት መሸፈን ተችሏል በዚህም ታሪካዊ ስኬት ተመዝግቧል።
ይህ በዓይነቱ ልዩ የሆነው አገራዊ የችግኝ ተከላ ዘመቻ የህዝባችንን የተቀናጀ የተቀናጀ ጥረት እና ለአካባቢ ጥበቃ ያለውን ቁርጠኝነት በአለም አቀፍ ደረጃ ታላቅ ሁነት ሆኖ አልፏል።
በዘንድሮው አመት እስካሁን ባለው ጊዜ ከ6.5 ቢሊዮን በላይ ችግኞች መተከላቸው የተገለጸ ሲሆን የተያዘውን አጠቃላይ እቅድ ለማጠናቀቅ ቀሪ የሆኑት 1.5 ቢሊዮን ችግኞች ደግሞ በሚቀጥሉት ወራት ተተክለው የሚጠናቀቁ ይሆናል።
የዚህ ታሪካዊ ዘመቻ እውነተኛ ስኬት የሚለካው በተከላው ሂደት ብቻ ሳይሆን ከተከላ በኋላ በሚደረግ ቀጣይነት ያለው እንክብካቤና ጥበቃ በመሆኑ እያንዳንዱ ዜጋ የተከላቸውን ችግኞች ተንከባክቦ ለፍሬ የማብቃት አደራ አለበት።
በብሌን ደምበሎ

5 days ago
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ለነገው የአንድ ጀምበር አረንጓዴ ዐሻራ የተደረገ ቅድመ ዝግጅት (በምሥል)
#ethiopia #climateaction #greenlegacy #southwestethiopiaregion #greenethiopia #ebc
#ethiopia #climateaction #greenlegacy #southwestethiopiaregion #greenethiopia #ebc
5 days ago
በነገው የአንድ ጀምበር ችግኝ ተከላ በንቃት ለመሳተፍ ተዘጋጅተናል - የኢሉአባቦር ዞን ነዋሪዎች
*****************
የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን (ዶ/ር) ሀገራዊ ጥሪ በመቀበል በነገው ዕለት በሚካሄደው የአንድ ጀምበር የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር በንቃት ለመሳተፍ መዘጋጀታቸውን የኢሉአባቦር ዞን ነዋሪዎች ገለጹ።
የዞኑ ነዋሪዎች እንዳሉት፣ ባለፉት ተከታታይ ዓመታት በአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር በተከሏቸው ችግኞች በየአካባቢያቸው የተራቆቱ ስፍራዎች መልሰው አገግመዋል።
የአካባቢ ጥበቃ ሥራው ሥነ ምሕዳር እንዲያገግም፣ የአፈር ለምነት እንዲሻሻል እንዲሁም ምርትና ምርታማነት እንዲጨምር አስችሏል።
የተከሏቸውን ፍራፍሬ ለምግብነት በማዋል እና ለገበያ በማቅረብ ተጠቃሚ መሆን መጀመራቸውንም ነዋሪዎቹ ለኢቢሲ ተናግረዋል።
በዞን ደረጃ የነገውን የአንድ ጀምበር የችግኝ ተከላ ዕቅድ ለማሳካት የሚያስችል በቂ ቅድመ ዝግጅት ስለመደረጉ ተገልጿል።
አስቀድሞ በተለዩ 299 የችግኝ ተከላ ሳይቶች የጉድጓድ ቁፋሮ ተከናውኖ የሚተከሉ ችግኞችም ወደየስፍራው ተጓጉዘዋል ነው የተባለው።
በሚፍታህ አብዱልቃድር
#ethiopia #climateaction #greenlegacy #iluabbaborzone #greenethiopia #ebc

6 days ago
(ዘ-ሐበሻ ስፖርት) ክሪስቶስ ቶሊስ ለመድፈኞቹ ባደረገው የመጀመሪያ የቅድመ-ውድድር ዘመን ጨዋታ ግብ በማስቆጠር፣ የአርሰናል ደጋፊዎች በቀጣዩ የውድድር ዘመን ከእርሱ ምን ሊጠብቁ እንደሚችሉ አስደሳች ፍንጭ ሰጥቷል። አርሰናል የስፔኑን ክለብ ጅሮናን 4 ለ 1 ባሸነፈበት በዚህ የመክፈቻ የአቋም መፈተሻ ጨዋታ፣ አዲሱ ፈራሚ ድንቅ እንቅስቃሴ አሳይቷል። ወደ ቤሺክታሽ ያቀናውን ሊያንድሮ ትሮሳርድን ለመተካት ከቤልጂየሙ ክለብ ክለብ ብሩጅ በ34 ሚሊዮን ፓውንድ የዝውውር ሂሳብ ወደ ሰሜን ለንደን ያመራው የ24 ዓመቱ ግሪካዊው ኢንተርናሽናል፣ በ30ኛው ደቂቃ ላይ አርናው ማርቲኔዝን በሚያምር ሁኔታ በማለፍ መሬት ለመሬት የመታው ኳስ ተከላካይ ታክኮ መረብ ላይ አርፏል።
ከዚህች ግብ 14 ደቂቃዎች አስቀድሞ የሚኬል አርቴታውን ስብስብ ቀዳሚ ያደረገችውን የመጀመሪያ ግብ ያስቆጠረው ጀርመናዊው አጥቂ ካይ ሃቨርትዝ ነበር። የ16 ዓመቱ ታዳጊ ማክስ ዶውማን ተከላካዮችን ሰንጥቆ ያቀበለውን ማራኪ ኳስ፣ ሃቨርትዝ ከጅሮናው ግብ ጠባቂ ፓውሎ ጋዛኒጋ ጋር ፊት ለፊት ተገናኝቶ በእርጋታ ወደ ግብነት ቀይሮታል።
ከእረፍት መልስ በ49ኛው ደቂቃ ላይ የጅሮናው ማርቲኔዝ ከማዕዘን የተሻገረለትን ኳስ ከፍ ብሎ በግንባሩ ገጭቶ በማስቆጠር የግብ ልዩነቱን ማጥበብ ቢችልም፣ ደስታቸው ግን ከሶስት ደቂቃዎች በላይ አልዘለቀም። ድንቁ ታዳጊ ዶውማን ወዲያውኑ የአርሰናልን የሁለት ግብ መሪነት መልሶ አረጋግጧል። የጎል ዝናቡ በዚህ ያላበቃ ሲሆን፣ ገብርኤል ጄሱስ በአምስት ደቂቃዎች ልዩነት ውስጥ ሌላ ግብ ከመረብ በማዋሃድ መድፈኞቹን 4 ለ 1 በሆነ ሰፊ ውጤት አሸናፊ ማድረግ ችሏል።
አርቴታ በስፔኑ ግጥሚያ ጠንካራ ቋሚ አሰላለፍ ይዘው ወደ ሜዳ የገቡ ሲሆን፣ ከዓለም ዋንጫ ተሳትፎ የተመለሱት ቪክቶር ጂዮክሬስ፣ ሃቨርትዝ እና ፒዬሮ ሂንካፒ እያንዳንዳቸው ለ30 ደቂቃዎች ያህል በሜዳ ላይ አሳልፈዋል። አርሰናል ሁለተኛውን የቅድመ-ውድድር ዘመን የአቋም መፈተሻ ጨዋታውን ለማድረግ ወደ ደብሊን የሚያመራ ሲሆን፣ በቀጣዩ ኦገስት 5 በአቪቫ ስታዲየም ከሪያል ቤቲስ ጋር ይፋለማል።

(ዘ-ሐበሻ ዜና) በትግራይ ክልል ከ 3.7 ሚሊዮን በላይ ሰዎች በኤልኒኞ ምክንያት ለተከሰተ ከባድ ድርቅ መጋለጣቸውን ተከትሎ፣ የሰብአዊ ዕርዳታ ኤጀንሲዎች የ623 ሚሊዮን ዶላር የገንዘብ እጥረት (ክፍተት) እንደገጠማቸው አሳወቁ። የትግራይ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን (TDRMC) እና አለም አቀፍ አጋሮች ባወጡት የጋራ ሪፖርት መሰረት፣ አደጋውን ለመቀልበስ ከሚያስፈልገው 626.8 ሚሊዮን ዶላር ውስጥ እስካሁን የተገኘው 3.38 ሚሊዮን ዶላር ብቻ ሲሆን፣ ይህም ከሚያስፈልገው አጠቃላይ በጀት 99 በመቶው ያልተሸፈነ መሆኑን በማሳየት ሁኔታውን እጅግ አሳሳቢ አድርጎታል።
በድርቁ አደጋ የዕርዳታ ፈላጊ ከሆኑት ወገኖች መካከል ከ900 ሺህ በላይ የውስጥ ተፈናቃዮች እና አንድ ሚሊዮን የሴፍቲኔት ፕሮግራም ተጠቃሚዎች ይገኙበታል። የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት የጋራ ትንበያ በመጪው የ2026 የክረምት ወቅት ዝናብ ሊዘገይ፣ ቀድሞ ሊያቆም፣ የተራዘመ ደረቃማ ጊዜ እና ከፍተኛ የሙቀት መጠን ሊኖር እንደሚችል ያረጋገጠ ሲሆን፣ በክልሉ ከሚገኙ 50 የገጠር ወረዳዎች ውስጥ 21ዱ እጅግ "በከፍተኛ ደረጃ አደገኛ" በተባለው ምድብ (Risk Level 5) ውስጥ ተመድበዋል።
አደጋው ሙሉ በሙሉ ጉዳት ከማድረሱ በፊት የቅድመ መከላከል ጣልቃ ገብነት ለማድረግ የ6 ሳምንታት ጠባብ ጊዜ ብቻ የቀረ ሲሆን፣ አስቸኳይ የምግብ ዕርዳታው ብቻ 366.78 ሚሊዮን ዶላር ይፈልጋል። ከዚህ በተጨማሪ የንጹህ መጠጥ ውሃ እና ንፅህና (50.95 ሚሊዮን ዶላር)፣ የስነ-ምግብ፣ የግብርና እና የጤና ዘርፎች የየራሳቸው የሆነ ከፍተኛ በጀት ጠይቀዋል። ይህ የገንዘብ እጥረት በፍጥነት ተቀርፎ የዕርዳታ አቅርቦት ካልተጀመረ፣ በቀጠናው የከፋ የሰብአዊ ቀውስ ሊከሰት እንደሚችል ኮሚሽኑ አጥብቆ አስጠንቅቋል።

የስዊድን ፖሊስ በሀገሩ ስለጠፉት ኢትዮጵያውያን ምን አለ?
#ethiopia | በስዊድን ጎተንበርግ በተካሄደው የ2026 የጎቲያ ካፕ የዓለም አቀፍ የታዳጊዎች እግር ኳስ ውድድር ላይ ከተሳተፉ በኋላ ደብዛቸው የጠፋው ኢትዮጵያውያን ታዳጊዎች በገዛ ፈቃዳቸው መሄዳቸውንና በጉዳዩ ላይ ምንም ዓይነት የወንጀል ወይም የሰው ህገወጥ ዝውውር ምልክት እንዳልተገኘ የስዊድን ፖሊስ አስታወቀ።
ከሀምሌ 12 እስከ 18 በተካሄደው በዚህ ውድድር ላይ ሲሳተፉ የቆዩትና ዕድሜያቸው ከ14 እስከ 17 ዓመት የሚሆኗቸው አብዛኞቹ ታዳጊዎች ከአንድ አዋቂ የቡድን መሪያቸው ጋር በድምሩ ወደ 20 የሚጠጉ የቡድኑ አባላት ያረፉበትን ትምህርት ቤት ለቀው የተሰወሩት በውድድሩ የመጨረሻ ቀን ነበር።
የውድድሩ አዘጋጆች ቡድኑ ማደሪያውን ያለ ምንም ቅድመ ማሳወቂያ ለቆ መሄዱን ከተረዱ በኋላ ወዲያውኑ ለፖሊስ ጥቆማ ማድረሳቸው ታውቋል።
የስዊድን ፖሊስ ከአስፈላጊ አካላት ጋር በመተባበር የቡድኑ አባላት ያሉበትን አድራሻ ለማወቅ ጥረቱን የቀጠለ ሲሆን እስካሁን ግን ምንም ዓይነት ሕገ-ወጥ ድርጊት ስለመፈጸሙ የሚያሳይ ማስረጃ እንደሌለ ገልጿል።
የኢትዮጵያው ክለብ ተወካይ ተጫዋቾቹ በደህና ሁኔታ ላይ እንደሚገኙና ከቤተሰቦቻቸው ጋር መገናኘታቸውን ለስዊድን መገናኛ ብዙኃን የገለጹ ቢሆንም፣ በአሁኑ ወቅት ያሉበትን ትክክለኛ ቦታ ወይም ወደ ኢትዮጵያ መመለሳቸውን ግን ከማረጋገጥ ተቆጥበዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ባወጣው መግለጫ በክስተቱ ማዘኑን ገልጾ ቡድኑ በራሱ መንገድ ባመቻቸው ጉዞ የተሳተፈ እንጂ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንን ወክሎ እንዳልተጓዘ አብራርቷል።
አክሎም ህዝቡ ታዳጊዎቹ የብሔራዊ ቡድን አባላት እንደሆኑ አድርገው የሚያቀርቡ የተሳሳቱ ዘገባዎችን እንዳይቀበል አሳስቧል።

7 days ago
ጄጄ ግሩፕ በኡራኤል ባለ 12 ወለል ህንፃ ግንባታ ከ700 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ አስጀመረ!
#fastmereja :- በኮንስትራክሽን እና ሪል እስቴት ዘርፍ የተሰማራው ጄጄ ግሩፕ (JJ Group)፣ በኡራኤል አደባባይ አካባቢ ከ700 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የሚጠይቅ ባለ 12 ወለል ባለብዙ አገልግሎት ህንፃ ግንባታ በይፋ ማስጀመሩን በዛሬዉ እለት አስታወቀ።
ህንፃው ለንግድ፣ ለቢሮ እና ለመኖሪያ አገልግሎት የሚውል ሲሆን እስከ ሁለት የከርሰ-ምድር (Basement) እና 12 ወለሎችን (G + 12) የያዘው ይህ ህንፃ፣ ከ10 እስከ 47 ካሬ ሜትር ስፋት ያላቸው ከ60 እስከ 70 የሚደርሱ የንግድ ሱቆች፣ በ4ኛው ወለል ላይ የተዘጋጁ የቢሮ ቦታዎች እንዲሁም 31 ባለ ሁለት መኝታ የመኖሪያ አፓርትመንቶችን ያካተተ እንደሆነ ተገልጿል።
ህንፃው ለተረጋጋ የመኖሪያ alalar™ ሲባል ለንግድና ለመኖሪያ ክፍሎቹ የተለያየ መግቢያና መውጫ እንዲኖረው ተደርጎ የተዋቀረ እንደሆነም ነዉ የተገለፀዉ።
የድርጅቱ ዋና ስራ አስፈፃሚ እና የኢትዮጵያ ሪል እስቴት አልሚዎች ማህበር ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ ጀበል ጀማል እንደገለፁት ድርጅታቸው ባለፉት 13 ዓመታት በዘርፉ በነበረው ልምድ ከ4ዐ በላይ ህንፃዎችንና ፋብሪካዎችን ገንብቶ ማስረከቡን ጠቁመው፣ በቅርቡ ይፋ የሚሆነው የሪል እስቴት አዋጅና ደንብ የገዢዎችንና የአልሚዎችን መብት የሚያስከብር መሆኑን ተናግረዋል።
እንደ ስራ አስፈፃሚው ገለጻ፣ የንግድ ሱቆቹን በ8 ወራት፣ የመኖሪያ አፓርትመንቶቹን ደግሞ በ2 ዓመታት ጊዜ ውስጥ አጠናቆ ለደንበኞች ለማስረከብ ማቀዱንም ገልፀዋል።
አቶ ጀበል አክለውም "ገንዘብ በዝግ አካውንት ተቀምጦ በስራው እድገት ልክ በባንክና በባለሙያ እየተረጋገጠ የሚለቀቅበት አሰራር መዘርጋቱ በዘርፉ ላይ ታማኝነትን ይፈጥራል" ብለዋል።
በተጨማሪም የፕሮጀክቱን መበሰር ምክንያት በማድረግ በቅድመ-ሽያጭ (Pre-sale) ደረጃ 10 አፓርትመንቶች ብቻ በልዩ ቅናሽ ለገዢዎች መቅረባቸው ተገልጿል።

(ዘ-ሐበሻ ዜና) በአሜሪካ እና በሳዑዲ አረቢያ መካከል በቅርቡ የተፈረመውን ታሪካዊ የኑክሌር ስምምነት ተከትሎ፣ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ያስቀመጡት ድንገተኛ ቅድመ-ሁኔታ በሁለቱ ሀገራት የዲፕሎማሲ ግንኙነት ላይ ከፍተኛ ውዥንብር መፍጠሩ ተገለጸ።
የቀድሞ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት የኑክሌር ስርጭት መከላከል ከፍተኛ ባለስልጣን እና በአሁኑ ወቅት የብሩኪንግስ ተቋም ከፍተኛ ተመራማሪ የሆኑት ሮበርት አይንሆርን፣ ይህንን ውዥንብር አስመልክተው ለአል ማጃላ መጽሔት ማብራሪያ ሰጥተዋል።
በአሜሪካው የኃይል ሚኒስትር ክሪስ ራይት እና በሳዑዲ አቻቸው መካከል ይፋዊ የፊርማ ስነ-ስርዓቱ ከተከናወነ በኋላ፣ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በማህበራዊ ሚዲያ ገጻቸው ላይ ባስተላለፉት መልዕክት "ሳዑዲ አረቢያ ከእስራኤል ጋር ያላትን ግንኙነት መደበኛ ካላደረገች ስምምነት አይኖርም" የሚል አዲስ ቅድመ-ሁኔታ አስቀምጠዋል።
ባለሙያው ሮበርት አይንሆርን እንዳሉት፣ ይህ ያልተጠበቀ ውሳኔ የሳዑዲ ባለስልጣናትን ብቻ ሳይሆን ከፍተኛ የአሜሪካ መንግስት ባለስልጣናትንም ጭምር በእጅጉ አስገርሟል። የረጅም ጊዜ ድርድር ውጤት የሆነው ይህ የ123 ስምምነት፣ ከፕሬዝዳንቱ መግለጫ በኋላ የመጨረሻ እጣ-ፈንታው ምን ሊሆን እንደሚችል እጅግ አጠራጣሪ ሆኗል።
ትራምፕ ስምምነቱ ከተፈረመ በኋላ ይህንን ቅድመ-ሁኔታ ለምን እንዳመጡት ትክክለኛው ምክንያት ባይታወቅም፣ ባለሙያው የሚከተሉትን ግምቶች አስቀምጠዋል፦ የትራምፕ አስተዳደር ያመጣው ስምምነት የቀድሞው የባይደን አስተዳደር ሲደራደርበት ከነበረው ያነሰ ጥብቅነት ያለው ነው የሚሉ ትችቶችን ለማስቀረት ታስቦ ሊሆን ይችላል። ፕሬዝዳንቱ የፊርማ ስነ-ስርዓቱ በኃይል ሚኒስትሩ መካሄዱ ቅር አሰኝቷቸው፣ ስምምነቱን በራሳቸው ቁጥጥር ስር ለማድረግ የወሰዱት እርምጃ ሊሆን ይችላል። ሳዑዲ አረቢያ አቋሟን እንደማትቀይር እያወቁ፣ ይህንን ቅድመ-ሁኔታ ወደፊት ሌሎች የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ ጥቅሞችን ከሳዑዲ ለማግኘት እንደ መደራደሪያ ሊጠቀሙበት አስበው ሊሆን ይችላል። (ምንም እንኳን የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ እጅ አለበት ቢባልም፣ ዋይት ሀውስ ግን ፕሬዝዳንቱ ውሳኔውን የወሰኑት በራሳቸው መሆኑን ገልጿል)።
አንድ ስምምነት ከተፈረመ በኋላ አዳዲስ ቅድመ-ሁኔታዎችን ለማከል መሞከር የተለመደ የዲፕሎማሲ አሰራር እንዳልሆነ አቶ አይንሆርን ያስገነዝባሉ። ይህ አካሄድ ሌሎች ሀገራት ወደፊት ከአሜሪካ ጋር ወደ ስምምነት ለመግባት ያላቸውን አመኔታ ሊሸረሽር እንደሚችል አስጠንቅቀዋል።
ምንም እንኳን በአሁኑ ወቅት ስምምነቱ አጣብቂኝ ውስጥ ቢገባም፣ ወደ ትግበራ ከተለወጠ ግን ለሁለቱም ሀገራት ጉልህ ጠቀሜታ አለው። አሜሪካ የኑክሌር ኢንዱስትሪዋን እንድታነቃቃ እና ቻይናና ሩሲያ በሳዑዲ የኑክሌር ኃይል ዘርፍ ውስጥ እንዳይገቡ ለመከላከል ይረዳታል። ሳዑዲ አረቢያ በበኩሏ የኃይል ምንጮቿን እንድታሰፋ እና የኢኮኖሚ ልማት ግቦቿን እንድታሳካ ትልቅ ድጋፍ ይሆናታል።
ሆኖም ስምምነቱ የራሱ የሆኑ ስጋቶች እንዳሉትም ተጠቁሟል። በተለይም በሳዑዲ አረቢያ ውስጥ ሀገር በቀል የዩራኒየም ማበልጸግ ስራን ለማጥናት የሁለት ዓመት ጊዜ መፈቀዱ፣ አሜሪካ የማበልጸጊያ ቴክኖሎጂዎች እንዳይስፋፉ ስትከተለው ከነበረው የቆየ ፖሊሲ ያፈነገጠ እና ትልቅ ስጋት ሊፈጥር የሚችል ጉዳይ መሆኑን ባለሙያው አብራርተዋል።

8 days ago
(ዘ-ሐበሻ ስፖርት) የኒውካስሉ ተወዳጅ የቀድሞ አሰልጣኝ ኬቨን ኪጋን ካረፉ ገና አስር ቀናት ብቻ ቢቆጠሩም፣ ክለቡ ሌላ ያልተጠበቀ መርዶ አስተናግዷል፦ የኪጋንን ህልም እውን በማድረግ ክለቡን ለክብር ያበቁት አሰልጣኝ ኤዲ ሃው ከኃላፊነታቸው መልቀቃቸውን ይፋ አድርገዋል።
ከእጅግ አስከፊው የ2025-26 የውድድር ዘመን በኋላ በኃላፊነታቸው ለመቀጠል እና ክለቡን መልሰው ለመገንባት ቃል ገብተው የነበሩት ኤዲ ሃው፣ አዲሱ የፕሪሚየር ሊግ የውድድር ዘመን ሊጀመር ሶስት ሳምንታት ብቻ ሲቀሩት ውሳኔያቸውን ቀልብሰዋል።
ማክሰኞ ምሽት በቅድመ-ውድድር ዝግጅት ኒውካስል ከብሪስቶል ሲቲ ጋር ባደረገው የወዳጅነት ጨዋታ 4-1 በሆነ አሳፋሪ ውጤት መሸነፉ ብዙ ነገሮችን የቀየረ ይመስላል። ከሜዳቸው ውጪ ስታዲየሙን ሞልተው የነበሩት የኒውካስል ደጋፊዎች ያሰሙት የተቃውሞ እና የቁጣ ድምፅ፣ ይህ "ትርጉም አልባ" የሚመስል የወዳጅነት ጨዋታ ትልቅ መዘዝ ይዞ እንደሚመጣ አመላካች ነበር።
በማግስቱ ረቡዕ ጠዋት እንደተሰማው ኤዲ ሃው ኃላፊነታቸውን ለመልቀቅ ወስነዋል። የቅርብ ምንጮች እንደሚያሳዩት ይህ ውሳኔ የቅጽበት የብስጭት ውሳኔ ሳይሆን፣ ከከባዱ የውድድር ዘመን መገባደጃ አንስቶ አሰልጣኙ በውስጣቸው ሲያብሰለስሉት የቆዩት እና ሊሸከሙት ያልቻሉት ከባድ ሸክም ውጤት ነው።
ለኤዲ ሃው፣ ይህ ስንብት እጅግ አስደናቂ ለነበረው የኒውካስል ቆይታቸው የማይመጥን አሳዛኝ ማብቂያ ነው። ከ30 ዓመታት በፊት ኬቨን ኪጋን እጅግ ተቃርበውት የነበረውን፣ ደጋፊውም ለ70 ዓመታት ሲናፍቀው የነበረውን ትልቅ ዋንጫ ወደ ሴንት ጀምስ ፓርክ ያመጡት እርሳቸው ነበሩ።
እ.ኤ.አ በ2021 ክለቡ በፕሪሚየር ሊጉ 19ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጦ ወደ መውረድ አፋፍ በደረሰበት ወቅት ኃላፊነቱን የተረከቡት ሃው፣ ኒውካስልን በሊጉ ማቆየት ብቻ ሳይሆን በሚቀጥለው ዓመት ወደ ቻምፒዮንስ ሊግ መድረክ መልሰውታል። በ2024-25 ደግሞ በካራባኦ ካፕ የፍጻሜ ጨዋታ የሊጉን ሻምፒዮን ሊቨርፑልን በዌምብሌይ አሸንፈው ታሪካዊ ዋንጫ በማንሳት ስማቸውን በኒውካስል ታሪክ በወርቅ ቀለም አጽፈው ነበር።
ይህ የዋንጫ ድል የሳዑዲው የኢንቨስትመንት ፈንድ (PIF) በባለቤትነት ለሚያስተዳድረው እና የፕሪሚየር ሊጉን ዋንጫ ለሚያልመው ኒውካስል እንደ ትልቅ መነሻ መታየት ነበረበት። ሆኖም፣ የ2025ቱ ክረምት የሁሉንም ነገር አቅጣጫ ቀየረው።
በተለይም አሌክሳንደር ኢሳክን በክለቡ ለማቆየት የተደረገው ተስፋ አስቆራጭ እና መራር ትግል፣ በመጨረሻም ስዊድናዊው አጥቂ በብሪታንያ የዝውውር ሪከርድ በዝውውር መስኮቱ መዘጋጃ ዕለት ወደ ሊቨርፑል ማምራቱ ክለቡን ክፉኛ ጎድቶታል። ኒውካስል የኢሳክን ክፍተት ሊተካ የሚችል ተጫዋች ማምጣት አልቻለም። እንደ ሁጎ ኤኪቲኬ፣ ቤንጃሚን ሴስኮ እና ጆአዎ ፔድሮ ያሉ ታላላቅ ኢላማዎቹን ለተቀናቃኝ የፕሪሚየር ሊግ ክለቦች አሳልፎ ሰጠ።
በምትኩ ክለቡ እና ኤዲ ሃው በጋራ ያመጧቸው ኒክ ዎልቴማዴ፣ ዮአን ዊሳ እና አንቶኒ ኤላንጋ አጠቃላይ 180 ሚሊዮን ፓውንድ ($243m) ቢወጣባቸውም፣ ያሳዩት አቋም እና የገጠማቸው የጉዳት ችግር የተከፈለባቸውን ዋጋ ፈጽሞ ሊያጸድቅ አልቻለም። የኤላንጋ እና ዎልቴማዴ ብቃት ሲዋዥቅ፣ አጥቂው ዊሳ በሙሉ የውድድር ዘመኑ በሊጉ ያስቆጠረው አንድ ጎል ብቻ ነበር። በ43 ሚሊዮን ፓውንድ የመጣው ጃኮብ ራምሴይም በቁርጭምጭሚት ጉዳት ሲሰቃይ ጊዜውን አሳልፏል።
የዝውውር ውድቀቱ በሜዳ ላይ ውጤት ቢሸፈን ኖሮ የኤዲ ሃው ጫና ያን ያህል አይከፋም ነበር። ሆኖም የ2025-26 የውድድር ዘመን ለኒውካስል እውነተኛ ቅዠት ሆኖ አለፈ።
በዓመቱ መጀመሪያ ጥሩ አጀማመር ያሳየው ክለቡ፣ ከአዲሱ ዓመት በኋላ ግን የመውረድ ስጋት ወዳለባቸው ቡድኖች ወረደ። ከጥር መጨረሻ አንስቶ እስከ የውድድር ዘመኑ ማብቂያ ድረስ ካደረጋቸው 16 ጨዋታዎች በ10ሩ በመሸነፉ፣ ከ6ኛ ደረጃ ወደ 12ኛ ደረጃ በማሽቆልቆል ደጋፊውን በሀዘን እና በቁጣ ሞላው።
ይባስ ብሎ በኤፍኤ ካፕ እና በካራባኦ ካፕ በማንችስተር ሲቲ በቀላሉ ሲሰናበት፣ በቻምፒዮንስ ሊጉ ደግሞ ባርሴሎና በድምር ውጤት 8-3 በሆነ አሳፋሪ የጎል ናዳ አዋርዶ ከውድድሩ አስወጣው።
የኤዲ ሃው የወደፊት እጣ ፈንታ ጥያቄ ውስጥ የገባው ገና በጊዜ ነበር። በሚያዝያ ወር ኒውካስል በተከታታይ ለሶስተኛ ጊዜ በቦርንማውዝ ከተሸነፈ በኋላ፣ የክለቡ ታሪካዊ ሌጀንድ አላን ሺረር እንዲህ ብሎ ነበር፦ "ለኤዲ ምን ያህል ከባድ ጊዜ እንደሆነ ባውቅም፣ የወደፊት እጣ ፈንታው ምን እንደሚሆን አላውቅም። ዳግም የመዋጋት እና ክለቡን የማንሳት አቅሙ ያለው አይመስለኝም። በሚቀጥለው የውድድር ዘመን ኤዲ ሃው ኒውካስልን ያሰለጥናል ብዬ አላስብም።"
ሺረር እንዳለውም ሆነ ኤዲ ሃው ኒውካስልን ወደ ቀደመ ክብሩ የመመለስ ትልቅ ታሪክ ሰርተው፣ ነገር ግን በኋለኛው አመታቸው በዝውውር ውድቀት እና በሜዳ ላይ አስከፊ ውጤቶች ታጅበው የሴንት ጀምስ ፓርኩን በር ዘግተው ወጥተዋል።

በሀዋሳ ከተማ በረዶ ቀላቅሎ በጣለ ከባድ ዝናብ የአንድ ሰው ህይወት አለፈ
👉አደጋው በ1ሰው ላይ ከባድ እና በ8 ሰዎች ላይ ቀላል ጉዳት ኡድርሷል
በሀዋሳ ከተማ ትናንት ምሽት በተከሰተው ያልተለመደ ኃይለኛ ንፋስ እና በረዶ ቀላቅሎ በጣለ ዝናብ ምክንያት የአንድ ሰው ህይወቱ ማለፉን የከተማዋ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ አስታውቋል።በአደጋው አንድ ሰው ላይ ከባድ የአካል ጉዳት ሲደርስ በ8 ሰዎች ደግሞ ቀላል ጉዳት እንደደረሰባቸው ተገልጿል።
የሀዋሳ ከተማ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ የመምሪያ ኃላፊ አቶ ወንድሙ ቶርባ ለብስራት ሬዲዮ እንደተናገሩት በአደጋው በርካታ ቤቶች ጣሪያዎች በኃይለኛው ንፋስ ተነስተው በመውደቃቸው በሰዎችና በንብረት ላይ ጉዳት ደርሷል።በተጨማሪም የኮንክሪት የኤሌክትሪክና የቴሌ ፖሎች በመውደቃቸው በከተማዋ በባህል አዳራሽ ምሥራቅ እና መሀል ክፍለ ከተማዎች አካባቢ የኃይል መቋረጥ መከሰቱን ገልጸዋል።
በአደጋው ሁለት መኪኖችና አንድ ባጃጅ ላይ የዛፍ ቅርንጫፎች በመውደቃቸው የመስታወት መሰበር ጉዳት ቢደርስም ከባድ ጉዳት እንዳልደረሰባቸው ተጠቁሟል። በባጃጁ ውስጥ የነበሩ ሰዎች ከአደጋው በፊት ወጥተው በመጠለላቸው ከጉዳት መትረፋቸው ተገልጿል።በከተማዋ የተሰሩት የኮሪደር ልማት ላይ የደረሰ ጉዳት ስለመኖሩ ለአቶ ወንድሙ ብስራት ሬዲዮ ጥያቄ ያነሳ ሲሆን አዳዲስ የተሰሩ የኮሪደር ልማት ስራዎች እና ቦዮች ወይም ካናሎች ጎርፍ በቀላሉ እንዲፈስ ስለረዱ ከጎርፍ ጋር ተያይዞ የሚመጣውን አደጋ በከፍተኛ ሁኔታ ቀናንሰውታል በኮሪደር ልማቱ ላይ የደረሰ የጎርፍ ጉዳት የለም ሲሉ ተናግረዋል።
የከተማ አስተዳደሩና የተለያዩ አካላት በማድረግ ባሉት የመስክ ምልከታ መሠረት አስቸኳይ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ወገኖች ድጋፍ ለማድረግ ሥራዎች እየተጀመሩ መሆኑ ተገልጿል።አደጋው ለ8 ደቂቃ ያህል አጭር ጊዜ ቢቆይም የንፋሱና የበረዶው መጠን ከፍተኛ እንደነበር ተጠቁሟል። ህብረተሰቡም የቅድመ ማስጠንቀቂያ መረጃዎችን በመከታተል ጥንቃቄ እንዲያደርግ ጥሪ ቀርቧል።

“አደይ አዲስ ዓመት ታላቅ የንግድ ኤክስፖ እና ፌስቲቫል” ይፋ ሆነ
#fastmereja I የ2019 አዲስ ዓመት ምክንያት በማድረግ በአዲስ ኮንቬንሽን ሴንተር ሊካሄድ የታቀደው “አደይ አዲስ ዓመት ታላቅ የንግድ ኤክስፖ እና ፌስቲቫል” ይፋ ተደርጓል። ኤክስፖው ከነሐሴ 21 ቀን 2018 ዓ.ም እስከ ጳጉሜን 05 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ለ15 ቀናት እንደሚቆይ አዘጋጆቹ አስታውቀዋል።
ይህ ታላቅ የንግድ እና የፌስቲቫል መድረክ በማስተር ፒስ ትሬዲንግ እና ራይት ኤቨንትስ ትብብር የተዘጋጀ ሲሆን፣ አዘጋጆቹ ለሚዲያ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳመለከቱት ዝግጅቱ ለስሚት እና ለአካባቢው ነዋሪዎች የገበያ አማራጮችን በቅርበት የሚያቀርብ ነው። በኤክስፖው ላይ ከ200 በላይ የሀገር ውስጥ አምራቾች፣ አስመጪዎች፣ የዕደ-ጥበብ ባለሙያዎች እና የአገልግሎት ሰጪ ተቋማት ምርትና አገልግሎታቸውን በተፎካካሪ እና በተመጣጣኝ ዋጋ እንደሚያቀርቡ ተገልጿል።
ከንግድ እንቅስቃሴው ጎን ለጎን ፌስቲቫሉ በየቀኑ 15 አርቲስቶች የሚሳተፉበት የቀጥታ የሙዚቃ ኮንሰርት፣ የፋሽን ሾው፣ የህፃናት መጫወቻዎች እና የበጎ አድራጎት ስራዎችን ያካተተ እንደሚሆን ተጠቅሷል። በተጨማሪም የኪነ-ጥበብ መድረኮችን ጨምሮ የመጽሐፍት አውደ ርዕይ እና ሽያጭ ይካሄዳል።
በ15 ቀናቱ የፌስቲቫል ቆይታ ከ80,000 በላይ ጎብኚዎች እና ደንበኞች ይገበያያሉ ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን፣ አዘጋጆቹ ቅድመ ዝግጅታቸውን አጠናቀው የኤግዚቢሽን ቦታዎችን በመሸጥ ላይ እንደሚገኙ አስታውቀዋል።
#ኹነት

9 days ago
(ዘ-ሐበሻ ዜና) በጅቡቲ የኢትዮጵያ አምባሳደር የሆኑት አምባሳደር ለገሰ ቱሉ፣ በሰሜን ኢትዮጵያ ለተፈጠረው አውዳሚ ጦርነት መቋጫ የሆነው የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት ትግበራን በተመለከተ፣ የህወሓት እሳቸው "ጽንፈኛ" ያሉት አመራሮች እያራመዱት ያለው ፖለቲካዊ ትርክት የትግራይን ህዝብ ፍላጎት የረሳ እና የሰላም ሂደቱን አደጋ ላይ የጣለ መሆኑን የሚያብራራ ትችት አወጡ። አምባሳደሩ "TPLF’s rhetoric and Ethiopia’s reality on the ground: When politics forgets people" (የህወሓት ፖለቲካዊ ትርክቶች እና የኢትዮጵያ ነባራዊ ሁኔታ፦ ፖለቲካ ህዝብን ሲረሳ" በሚል ርዕስ በኒው አፍሪካን መጽሔት ድረገጽ ላይ ዛሬ ባሳተሙት ጽሁፍ፣ ዘላቂ ሰላም ሊመጣ የሚችለው አካላት ከግል እና ከፓርቲ ፍላጎት ይልቅ የዜጎችን ደህንነት ሲያስቀድሙ ብቻ መሆኑን አስገንዝበዋል።
አምባሳደሩ በጽሁፋቸው እንዳስመዘገቡት ከጦርነቱ በኋላ እጅግ አሳሳቢ ከሆኑት ጉዳዮች አንዱ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮችን ወደ ቀዬአቸው የመመለስ ስራ ነው። የፌደራል መንግስት ተፈናቃዮች ያለምንም የፖለቲካ ቅድመ ሁኔታ እና መጓተት ወደ ቤታቸው ሊመለሱ ይገባል የሚል ጽኑ አቋም ቢኖረውም፣ ህወሓቶች ግን የሰብዓዊ እርዳታን እና የተፈናቃዮችን ጉዳይ ካልተፈቱ የፖለቲካ አጀንዳዎቻቸው ጋር በማያያዝ የህዝቡን ስቃይ ለፖለቲካ መደራደሪያነት እያዋሉት መሆኑን ኮንነዋል። ቤተሰቦች በፖለቲካዊ ዲስኩር ብቻ ህይወታቸውን መልሰው ሊገነቡ አይችሉም ያሉት አምባሳደሩ፣ በአከራካሪ ግዛቶች ዙሪያም የፌደራል መንግስት ጉዳዩ በህገ-መንግስታዊ ስርአቱ እና በሰላም ስምምነቱ መሰረት እንዲፈታ ጥረት ቢያደርግም፣ አመራሮቹ እነዚህን ተቋማዊ አሰራሮች ውድቅ በማድረግ እና የጊዜያዊ አስተዳደሩን ስልጣን ጥያቄ ውስጥ በማስገባት እንቅፋት እየፈጠሩ ይገኛሉ ብለዋል።
የፕሪቶሪያው ስምምነት ህገ-መንግስታዊ እና ዲሞክራሲያዊ አስተዳደርን ለመገንባት ምርጫ እንዲካሄድ ቢደነግግም፣ ህወሓቶች የፓርቲው የውስጥ ፖለቲካዊ ልዩነቶች እስኪፈቱ በሚል ሰበብ ምርጫን ላልተወሰነ ጊዜ እንዲራዘም እያደረጉ መሆኑ ተገልጿል። በተጨማሪም የፌደራል መንግስት፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች እና የብሄራዊ ምክክር ኮሚሽን ያቀረቡትን የሽምግልና እና የውይይት ጥሪዎች በተደጋጋሚ ውድቅ ማድረጋቸው የእርቅ እድሎችን እያጠበበው መምጣቱን አምባሳደር ለገሰ አስረድተዋል።
ተቋማትን እያፈረሱ እና የሽግግር ፍትህ ስርአቱን እየተቃወሙ በተመሳሳይ ጊዜ ፍትህ እንፈልጋለን ማለታቸውም ግልጽ የሆነ የተግባር ተቃርኖ መሆኑን አንስተዋል።
ዳግም ወታደራዊ ቅስቀሳ እና የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ስጋት
የሰላም ስምምነቱ ትጥቅ መፍታት፣ ከወታደራዊ መዋቅር መውጣት እና ወደ ሰላማዊ ህይወት መቀላቀልን (DDR) ቅድሚያ ቢሰጥም፣ አመራሮቹ ግን አሁንም ወታደራዊ ቅስቀሳ እያደረጉ፣ ከባድ የጦር መሳሪያዎችን እየደበቁ እና ወጣቶችን በግዴታ እየመለመሉ መሆኑ እጅግ አሳሳቢ መሆኑን አምባሳደሩ ገልጸዋል። ከዓመታት የጦርነት ስቃይ በኋላ ወጣቶች ወደ ትምህርት እና ስራ መመለስ ሲገባቸው ዳግም ለጦርነት መመልመላቸው ተቀባይነት የሌለው ተግባር ነው። ይህ ድርጊታቸው የአውሮፓ ህብረትን እና በሰላም አደናቃፊዎች ላይ የቪዛ ማዕቀብ የጣለችውን አሜሪካን ጨምሮ ዓለም አቀፍ አጋሮችን ጭምር በእጅጉ እንዳሳሰበ አምባሳደሩ አስታውሰዋል።
የትግራይ ህዝብ ከዚህ በላይ ጦርነት እና ስቃይ እንደማይገባው ያሳሰቡት አምባሳደር ለገሰ ቱሉ፣ የፕሪቶሪያው ስምምነት ወደ ዘላቂ ሰላም መሻገሪያ ጠንካራ መሰረት መሆኑን አውቆ ማክበር እንደሚገባ አጽንኦት ሰጥተዋል። ዳግም ወደ ጦርነት እና ወታደራዊ ፉክክር መግባት ትግራይን ብቻ ሳይሆን መላው ኢትዮጵያን አደጋ ላይ የሚጥል መሆኑን በማስጠንቀቅ፣ ፖለቲከኞች የጥቃት ፖለቲካን ትተው ለኢትዮጵያ ህዝብ ሲሉ የዲሞክራሲያዊ ውድድር ፖለቲካን ሊመርጡ እንደሚገባ ጥሪያቸውን አቅርበዋል።
በአምባሳደሩ ጽሁፍ ዙሪያ፣ ይህ መረጃ እስከቀረበበት ጊዜ ድረስ ከሕወሐት ወገን የተሰጠ ምላሽ የለም።

ሐዋሳ በከባድ ዝናብ ተመታች‼️
👉ጎርፍና ኃይለኛ ንፋስ ከዝናብ ጋር በቀጣይ ቀናቶችም ሊቀጥሉ ይችላሉ።
አሁን ባለው የክረምት ወቅት ሀዋሳን ጨምሮ በዙሪያዋ ከፍተኛ መጠን ያለው ዝናብ እየጣለ ይገኛል። የኢትዮጵያ ሜትሮሎጂ ባለስልጣን በሰጠው መረጃ መሠረትም የዝናቡ መጠን በቀጣዮቹ ቀናት ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚችል ተገልጿል።
በከተማዋ እየጣለ ባለው ከባድ ዝናብ፣ በረዶና ኃይለኛ ንፋስ በአንዳንድ አካባቢዎች ዛፎችንና የኤሌክትሪክ ምሰሶዎችን በመጣሉ በሰው ሕይወትና በንብረት ላይ ጉዳት አስከትሏል። በተጨማሪም በመሠረተ ልማት ላይ በደረሰ ውድመት ምክንያት በአንዳንድ የከተማዋ ክፍሎች የመብራት አገልግሎት ተቋርጧል።
የከተማ አስተዳደሩ በደረሰው ጉዳት የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን ገልፆ፤ በተጎዱ አካባቢዎች ፈጥኖ በመድረስ ተጎጂዎችን ወደ ሕክምና የማድረስና በንብረት ላይ የደረሰውን ጉዳት በመለየት ተገቢውን ድጋፍ የማድረግ ሥራዎችን አስጀምሯል።
በቀጣይም የክረምቱ ወቅት እስኪያልቅ ድረስ መሰል የተፈጥሮ አደጋዎች ሊያጋጥሙ ስለሚችሉ፣ ጉዳቱን ለመቀነስና ለመከላከል የሚያስችሉ የቅድመ ጥንቃቄ ሥራዎች ተጠናክረው እየተከናወኑ ይገኛሉ።
በመሆኑም በቀጣዮቹ ቀናት ኃይለኛ ንፋስ የታጀበ ዝናብና የጎርፍ አደጋ ሊከሰት ስለሚችል ህብረተሰቡ አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርግ አስተዳደሩ ያሳስባል።
በተለይም ዛፎች፣ ያረጁ የኤሌክትሪክ ምሰሶዎች እና አጥሮች ሊወድቁ ስለሚችሉ፣ በዝናብ ወቅት ከእነዚህ አካባቢዎች በመራቅ ራሳችሁንና ቤተሰቦቻችሁን እንድትጠብቁ ከተማ አስተዳደሩ ጥሪ አቅርቧል።
ሐዋሳ ከተማ ኮሙኒኬሽን

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ከኢንተርፖልና ከማላዊ ፖሊስ ጋር በመተባበር በአደገኛ ሕገ-ወጥ የሰዎች አዘዋዋሪነት ወንጀል የተጠረጠረውን አድነው ባሻው ውዳሞን በማላዊ በቁጥጥር ሥር በማዋል ወደ ኢትዮጵያ አምጥቷል።
ተጠርጣሪው ከግብረ አበሮቹ ጋር በመሆን በተለይም ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ከሀድያ እና ከንባታ ዞኖች በርካታ ወጣቶችን ሕይወታቸውን እንደሚያሻሽል በመሐላና በአጉል ተስፋ በማታለል ወደ ደቡብ አፍሪካ ሲያዘዋውር መቆየቱ በሰውና በሰነድ ማስረጃ ተረጋግጧል።
ተጓዦችን ከ600 ሺህ እስከ 800 ሺህ ብር ያስከፍል የነበረ ሲሆን፣ በቅድመ ክፍያ በኢትዮጵያ እስከ 100 ሺህ ብር እና ከዚያ በላይ በባንክ ይቀበል እንደነበር የምርመራ መዝገቡ ያመላክታል።
ተጓዦቹን በሞያሌ በኩል ወደ ኬንያ ካሻገረ በኋላ በጋንቦ ጫካ ውስጥ በድብቅ በማስቀመጥ በየ24 ሰዓቱ ትንሽ ሩዝ ከቁራጭ ዳቦ ጋር ብቻ በመስጠት ለከፍተኛ ረሃብና የውሃ ጥም የዳረጋቸው ሲሆን፣ በሞተርና በእግር ሴሎ በረሃን እንዲያቋርጡ አስገድዷቸዋል።
ናይሮቢ ካደረሳቸው በኋላም በአንድ ክፍል ውስጥ በማጎር ከቤተሰቦቻቸው ተጨማሪ ገንዘብ እንዲያስልኩ በማስገደድ፣ ገንዘብ ማስላክ ያልቻሉትን በዱላ በመደብደብና በኤሌክትሪክ ንዝረት በማሰቃየት ተጨማሪ ገንዘብ በኢትዮጵያ ባሉ ግብረ አበሮቹ በኩል እንዲከፈለው አድርጓል።
በተጨማሪም ተጓዦቹን ከናይሮቢ ወደ ሞምባሳና ታንዛኒያ በዕቃ መጫኛ ኮንቴነሮች፣ በተሳቢና በሸራ በተሸፈኑ መኪኖች ውስጥ አጉሮ በመጫን ታንዛኒያ በሚገኝ ጫካ ውስጥ ጥሏቸው የተሰወረ ሲሆን፣ አብዛኞቹ ወጣቶች ደቡብ አፍሪካ ሳይደርሱ በተለያዩ ሀገራት በፖሊስ ቁጥጥር ሥር ውለው እስከ ሦስት ዓመት እስራት ከተቀጡ በኋላ እስከ 170 ሺህ ብር ከፍለው ወደ ሀገር መመለሳቸው ተገልጿል።
ፌደራል ፖሊስ ከ2015 ዓ.ም ጀምሮ ባደረገው ክትትል ተጠርጣሪውን በማላዊ ፖሊስ አስይዞ ሐምሌ 22 ቀን 2018 ዓ.ም ተረክቦ ወደ ሀገር ያመጣው ሲሆን፣ ህብረተሰቡ በEFPApp፣ በ991 እና በSPS ጥቆማ በመስጠት ትብብሩን እንዲቀጥል ጥሪ አቅርቧል።

(ዘ-ሐበሻ ዜና) በሪያል ማድሪድ ቤት ድባቡ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየሻከረ መጥቷል። ክለቡ የዓለም እግር ኳስ ፈርጥ እና የቡድኑ ዋልታ በሆነው ቪኒሽየስ ዙሪያ እያደረገ ያለው የኮንትራት ድርድር አጣብቂኝ ውስጥ በመግባቱ፣ የ26 ዓመቱ ኮከብ በስፔን ዋና ከተማ ስላለው የረጅም ጊዜ ቆይታው ከፍተኛ ጥርጣሬ ውስጥ የወደቀበት ወቅት ላይ ይገኛል። የኮንትራት ማራዘሚያው ሒደት አለመሳካቱ፣ የቤርናባው የበላይ ጠባቂዎች ሁኔታውን እያስተናገዱበት ባለው መንገድ ላይ ጠንካራ ትችቶች እንዲሰነዘሩባቸው በሩን ወለል አድርጎ ከፍቷል።
ይህን ጠንካራ ትችት የሰነዘረው የቀድሞው የሪያል ማድሪድ እና ቫለንሲያ ግብ ጠባቂ ሳንቲያጎ ካኒዛሬስ ነው። በካዴና ኮፔ የ'ትዬምፖ ዴ ሁዌጎ' ፕሮግራም ላይ በሰጠው አስተያየት፣ ሎስ ብላንኮዎቹ በቪኒሽየስ ዙሪያ ያላቸውን የትርክት ቁጥጥር እንዳጡ በግልጽ ተናግሯል። ቪኒሽየስ አሁን ባለው ኮንትራት መሰረት በሚቀጥለው ክረምት በነጻ ሊለቅ ስለሚችል፣ ክለቡ የፋይናንስ እና የስፖርታዊ ጥቅሙን ለማስጠበቅ ቀድሞ ጠንካራ አቋም መውሰድ ነበረበት ብሏል።
ካኒዛሬስ ቁጣውን ሲገልጽ፣ "ሪያል ማድሪድ ለሁሉም ነገር ይዘገያል። ተጫዋቹ የፈረመው ስምምነት የለውም የሚባለው እውነት ከሆነ፣ ማድሪድ አሁኑኑ እሱን የመሸጥ ግዴታ አለበት። ተጫዋቹን ኮንትራቱን ጨርሶ እንዲወጣ በማድረግ ከመቶ ሚሊዮን ዩሮ በላይ ማጣት አይቻልም፤ ግን ይህ የሚሆን ይመስለኛል። ይህ ይቅር የማይባል የአመራር ስህተት ነው" በማለት የክለቡን ቦርድ ክፉኛ ወቅሷል።
ማድሪዶች በዚህ የኮንትራት ውዝግብ ውስጥ እያሉ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊጉ ሀያል ክለብ አርሰናል ይህንን ውጥንቅጥ ለመጠቀም አድፍጦ እየጠበቀ ይገኛል። መድፈኞቹ ለብራዚላዊው ኮከብ እውነተኛ ፈላጊ ሆነው ብቅ ያሉ ሲሆን፣ የሚኬል አርቴታው ስብስብ ይህንን ፈጣን የክንፍ ተጫዋች ወደ ለንደን ለማምጣት ከፍተኛ ገንዘብ ለመክፈል ፈቃደኛ መሆኑን ከእንግሊዝ የሚወጡ መረጃዎች ያመለክታሉ።
ቪኒሽየስ አሁን ባለው ክለቡ ተገቢው ክብር እንዳልተሰጠው ከተሰማው፣ የፕሪሚየር ሊጉ ማራኪነት እና ሊቀርብለት የሚችለው ከፍተኛ የደሞዝ ጭማሪ ከስፔን ሊያባብለው የሚችልበት አቅም አለው። ይሁን እንጂ፣ ማድሪዶች አሁንም ቢሆን ቪኒሽየስን በአዲስ ኮንትራት እንደሚያስሩት ሙሉ በሙሉ በራስ መተማመን እንዳላቸው ተዘግቧል።
ይህንን የተወሳሰበ የዝውውር ሒደት ይበልጥ እንዲወሳሰብ የሚያደርገው ደግሞ ክለቡ አዲስ ተሰጥኦን ለማምጣት የሚያደርገው ጥረት፣ በተለይም የያን ዲዮማንዴ እምቅ ዝውውር ነው። አንዳንድ የስፖርት ተንታኞች እንደሚሉት፣ ወጣቱን ኮከብ ለማምጣት የሚደረገው ጥረት ማድሪድ ከቪኒሽየስ ውጪ ላለው ህይወት ቀድሞ እየተዘጋጀ መሆኑን የሚያሳይ የቅድመ-ጥንቃቄ እርምጃ ነው። ምንም እንኳን ይህ ግምት ቢኖርም፣ አዲሱ የሪያል ማድሪድ አሰልጣኝ ሆሴ ሞሪንሆ ብራዚላዊውን ኢንተርናሽናል የአዲሱ ፕሮጀክታቸው ቁልፍ አካል አድርገው ለማቆየት ቆርጠው መነሳታቸው ተነግሯል።

Comments