በነገው የአንድ ጀምበር ችግኝ ተከላ በንቃት ለመሳተፍ ተዘጋጅተናል - የኢሉአባቦር ዞን ነዋሪዎች
*****************
የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን (ዶ/ር) ሀገራዊ ጥሪ በመቀበል በነገው ዕለት በሚካሄደው የአንድ ጀምበር የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር በንቃት ለመሳተፍ መዘጋጀታቸውን የኢሉአባቦር ዞን ነዋሪዎች ገለጹ።
የዞኑ ነዋሪዎች እንዳሉት፣ ባለፉት ተከታታይ ዓመታት በአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር በተከሏቸው ችግኞች በየአካባቢያቸው የተራቆቱ ስፍራዎች መልሰው አገግመዋል።
የአካባቢ ጥበቃ ሥራው ሥነ ምሕዳር እንዲያገግም፣ የአፈር ለምነት እንዲሻሻል እንዲሁም ምርትና ምርታማነት እንዲጨምር አስችሏል።
የተከሏቸውን ፍራፍሬ ለምግብነት በማዋል እና ለገበያ በማቅረብ ተጠቃሚ መሆን መጀመራቸውንም ነዋሪዎቹ ለኢቢሲ ተናግረዋል።
በዞን ደረጃ የነገውን የአንድ ጀምበር የችግኝ ተከላ ዕቅድ ለማሳካት የሚያስችል በቂ ቅድመ ዝግጅት ስለመደረጉ ተገልጿል።
አስቀድሞ በተለዩ 299 የችግኝ ተከላ ሳይቶች የጉድጓድ ቁፋሮ ተከናውኖ የሚተከሉ ችግኞችም ወደየስፍራው ተጓጉዘዋል ነው የተባለው።
በሚፍታህ አብዱልቃድር
#ethiopia #climateaction #greenlegacy #iluabbaborzone #greenethiopia #ebc

2 days ago