(ዘ-ሐበሻ ዜና) በጅቡቲ የኢትዮጵያ አምባሳደር የሆኑት አምባሳደር ለገሰ ቱሉ፣ በሰሜን ኢትዮጵያ ለተፈጠረው አውዳሚ ጦርነት መቋጫ የሆነው የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት ትግበራን በተመለከተ፣ የህወሓት እሳቸው "ጽንፈኛ" ያሉት አመራሮች እያራመዱት ያለው ፖለቲካዊ ትርክት የትግራይን ህዝብ ፍላጎት የረሳ እና የሰላም ሂደቱን አደጋ ላይ የጣለ መሆኑን የሚያብራራ ትችት አወጡ። አምባሳደሩ "TPLF’s rhetoric and Ethiopia’s reality on the ground: When politics forgets people" (የህወሓት ፖለቲካዊ ትርክቶች እና የኢትዮጵያ ነባራዊ ሁኔታ፦ ፖለቲካ ህዝብን ሲረሳ" በሚል ርዕስ በኒው አፍሪካን መጽሔት ድረገጽ ላይ ዛሬ ባሳተሙት ጽሁፍ፣ ዘላቂ ሰላም ሊመጣ የሚችለው አካላት ከግል እና ከፓርቲ ፍላጎት ይልቅ የዜጎችን ደህንነት ሲያስቀድሙ ብቻ መሆኑን አስገንዝበዋል።
አምባሳደሩ በጽሁፋቸው እንዳስመዘገቡት ከጦርነቱ በኋላ እጅግ አሳሳቢ ከሆኑት ጉዳዮች አንዱ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮችን ወደ ቀዬአቸው የመመለስ ስራ ነው። የፌደራል መንግስት ተፈናቃዮች ያለምንም የፖለቲካ ቅድመ ሁኔታ እና መጓተት ወደ ቤታቸው ሊመለሱ ይገባል የሚል ጽኑ አቋም ቢኖረውም፣ ህወሓቶች ግን የሰብዓዊ እርዳታን እና የተፈናቃዮችን ጉዳይ ካልተፈቱ የፖለቲካ አጀንዳዎቻቸው ጋር በማያያዝ የህዝቡን ስቃይ ለፖለቲካ መደራደሪያነት እያዋሉት መሆኑን ኮንነዋል። ቤተሰቦች በፖለቲካዊ ዲስኩር ብቻ ህይወታቸውን መልሰው ሊገነቡ አይችሉም ያሉት አምባሳደሩ፣ በአከራካሪ ግዛቶች ዙሪያም የፌደራል መንግስት ጉዳዩ በህገ-መንግስታዊ ስርአቱ እና በሰላም ስምምነቱ መሰረት እንዲፈታ ጥረት ቢያደርግም፣ አመራሮቹ እነዚህን ተቋማዊ አሰራሮች ውድቅ በማድረግ እና የጊዜያዊ አስተዳደሩን ስልጣን ጥያቄ ውስጥ በማስገባት እንቅፋት እየፈጠሩ ይገኛሉ ብለዋል።
የፕሪቶሪያው ስምምነት ህገ-መንግስታዊ እና ዲሞክራሲያዊ አስተዳደርን ለመገንባት ምርጫ እንዲካሄድ ቢደነግግም፣ ህወሓቶች የፓርቲው የውስጥ ፖለቲካዊ ልዩነቶች እስኪፈቱ በሚል ሰበብ ምርጫን ላልተወሰነ ጊዜ እንዲራዘም እያደረጉ መሆኑ ተገልጿል። በተጨማሪም የፌደራል መንግስት፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች እና የብሄራዊ ምክክር ኮሚሽን ያቀረቡትን የሽምግልና እና የውይይት ጥሪዎች በተደጋጋሚ ውድቅ ማድረጋቸው የእርቅ እድሎችን እያጠበበው መምጣቱን አምባሳደር ለገሰ አስረድተዋል።
ተቋማትን እያፈረሱ እና የሽግግር ፍትህ ስርአቱን እየተቃወሙ በተመሳሳይ ጊዜ ፍትህ እንፈልጋለን ማለታቸውም ግልጽ የሆነ የተግባር ተቃርኖ መሆኑን አንስተዋል።
ዳግም ወታደራዊ ቅስቀሳ እና የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ስጋት
የሰላም ስምምነቱ ትጥቅ መፍታት፣ ከወታደራዊ መዋቅር መውጣት እና ወደ ሰላማዊ ህይወት መቀላቀልን (DDR) ቅድሚያ ቢሰጥም፣ አመራሮቹ ግን አሁንም ወታደራዊ ቅስቀሳ እያደረጉ፣ ከባድ የጦር መሳሪያዎችን እየደበቁ እና ወጣቶችን በግዴታ እየመለመሉ መሆኑ እጅግ አሳሳቢ መሆኑን አምባሳደሩ ገልጸዋል። ከዓመታት የጦርነት ስቃይ በኋላ ወጣቶች ወደ ትምህርት እና ስራ መመለስ ሲገባቸው ዳግም ለጦርነት መመልመላቸው ተቀባይነት የሌለው ተግባር ነው። ይህ ድርጊታቸው የአውሮፓ ህብረትን እና በሰላም አደናቃፊዎች ላይ የቪዛ ማዕቀብ የጣለችውን አሜሪካን ጨምሮ ዓለም አቀፍ አጋሮችን ጭምር በእጅጉ እንዳሳሰበ አምባሳደሩ አስታውሰዋል።
የትግራይ ህዝብ ከዚህ በላይ ጦርነት እና ስቃይ እንደማይገባው ያሳሰቡት አምባሳደር ለገሰ ቱሉ፣ የፕሪቶሪያው ስምምነት ወደ ዘላቂ ሰላም መሻገሪያ ጠንካራ መሰረት መሆኑን አውቆ ማክበር እንደሚገባ አጽንኦት ሰጥተዋል። ዳግም ወደ ጦርነት እና ወታደራዊ ፉክክር መግባት ትግራይን ብቻ ሳይሆን መላው ኢትዮጵያን አደጋ ላይ የሚጥል መሆኑን በማስጠንቀቅ፣ ፖለቲከኞች የጥቃት ፖለቲካን ትተው ለኢትዮጵያ ህዝብ ሲሉ የዲሞክራሲያዊ ውድድር ፖለቲካን ሊመርጡ እንደሚገባ ጥሪያቸውን አቅርበዋል።
በአምባሳደሩ ጽሁፍ ዙሪያ፣ ይህ መረጃ እስከቀረበበት ጊዜ ድረስ ከሕወሐት ወገን የተሰጠ ምላሽ የለም።

2 months ago