30 mins. ago
“ እንደ ሲቲ መሆን አንፈልግም “ የኮሞ ፕሬዝዳንት
የኮሞ ፕሬዝዳንት ሚርዋን ሱዋርሶ ክለባቸው እንደ ማንችስተር ሲቲ መሆን አይፈልግም በማለት ተናግረዋል።
ስለ ማንችስተር ሲቲ ክስ የተጠየቁት ፕሬዝዳንቱ “ እውነት ሆኖ ከተረጋገጠ በጣም አስከፊ ነገር ነው ” ብለዋል።
“ ፍትሀዊ በሆነ ስፖርት ስኬታማ ለመሆን ማጭበርበር ለምን እንዳሰቡ አልገባኝም “ሲሉ ጨምረው ተናግረዋል።
አክለውም “ ስኬታቸውን ተጠቅመው የሰሩትን ስህተት ማስተካከል አለባቸው ፤ እኛ በጭራሽ እንደነሱ መሆን አንፈልግም "ሲሉ ገልጸዋል።
@tikvahethsport kidusyoftahe

47 mins. ago
በአሽከርካሪዎች እና አሠሪዎች መካከል የሚፈጠሩ አለመግባባቶችን ለመፍታት የሚያግዝ የመግባቢያ ስምምነት ተፈረመ
በአሽከርካሪዎች እና አሠሪዎች መካከል የሚፈጠሩ አለመግባባቶችን ወደ ሕግ ከመውሰድ ይልቅ በሦስትዮሽ ውይይት በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት መፈረሙ ተገለጸ።
ስምምነቱን የኢትዮጵያ ትራንስፖርት አሠሪዎች ፌዴሬሽን እና የትራንስፖርት ሠራተኞች ፌዴሬሽን በጋራ የተፈራረሙት ሲሆን፣ የአሽከርካሪዎችን መብትና ጥቅም በማስከበር አላስፈላጊ ወጪና የጊዜ ብክነትን ለማስቀረት ያለመ እንደሆነ ተነግሯል።
የኢትዮጵያ ትራንስፖርት አሠሪዎች ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት አቶ ብርሃኔ ዘሩ ለአሐዱ ሬድዮ እንዳስታወቁት፣ ስምምነቱ የጡረታ አበልን፣ የሥራ ውልን እና ሕጋዊ ማዕቀፎችን በማጠናከር አስተማማኝ የሥራ ሁኔታን ለመፍጠር ያለመ ነው።
አሽከርካሪዎች የትራንስፖርት ዘርፉ ዋና አንቀሳቃሽ በመሆናቸው የመብት እና ጥቅም ጥያቄዎቻቸው ምላሽ ማግኘት እንዳለባቸው አቶ ብርሃኔ ገልጸዋል።
የአሽከርካሪዎች መብት እና የሥራ ዋስትና ካልተረጋገጠ የትራንስፖርት ዘርፉም ሆነ የሀገሪቱ ኢኮኖሚ ሊጎዳ እንደሚችል የተገለጸ ሲሆን፣ ከአጋር ድርጅቶች ጋር በመተባበር የሥራ ዋስትናቸውን የሚያሻሽሉ ተግባራት እየተከናወኑ ይገኛሉ ተብሏል።
በደረጄ መንግስቱ
#አሐዱ_ሬዲዮ_94 .3
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ

3 hours ago
ኬንያ የመጀመሪያው የኢቦላ በሽታ በሀገሯ መገኘቱን ማረጋገጫ ሰጠች
👉ከዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ መነሻውን አድርጎ የተጓዘው ታካሚም በናይሮቢ ህይወቱ አልፏል
ኬኒያ የመጀመሪያውን የኢቦላ ቫይረስ ተጠቂ ማረጋገጧን የጤና ሚኒስትሩ አደን ዱዋሌ አስታውቀዋል። ህይወቱ ያለፈው ኬኒያዊ ዜጋ ላለፉት ሰባት ዓመታት በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ኑሮውን ያደረገ ሲሆን፣ ወደ ኬኒያ ከመመለሱ ከአንድ ወር አስቀድሞ በህመም ተይዞ ነበር።
ታካሚው በጤና ተቋማት ህክምናን ከተከታተለ በኋላ በየብስ ትራንስፖርት ወደ ጎረቤት ሀገር ኡጋንዳ ተጉዟል። ከዚያም ከኡጋንዳ በጃምቦጀት አውሮፕላን ተሳፍሮ በአውሮፓውያኑ አቆጣጠር ጥቅምት 3 ቀን ከቀኑ 7 ሰአት ከ10 ደቂቃ ላይ ናይሮቢ ከሚገኘው ጆሞ ኬንያታ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ደርሷል።
በአውሮፕላን ማረፊያው የተለመደውን የህዝብ ጤና ምርመራ ካደረገ በኋላ፣ ዘመድ አዝማዶቹ እና ጓደኞቹ በቀጥታ ከኤርፖርት ወደ ናይሮቢ ሆስፒታል ወስደውት ወዲያውኑ በለይቶ ማቆያ እንዲገባ የተደረገ ሲሆን በሆስፒታል ቆይታው በ‘ቡንዲቡግዮ የኢቦላ ዝርያ መያዙ ተረጋግጦ ህይወቱ አልፏል።
የጤና ባለስልጣናት ወረርሽኙ እንዳይስፋፋ ለመከላከል ፈጣን እርምጃዎችን የወሰዱ ሲሆን ከሟቹ ጋር ንክኪ ነበራቸው የተባሉ የቤተሰብ አባላትና የጤና ሰራተኞችን ጨምሮ 28 ግለሰቦችን ለይተዋል።በኮንጎ፣ በኡጋንዳ እና በናይሮቢ የተደረገው የታካሚው የአውሮፕላን በረራ እንዲሁም ከቤተሰብ እና ከህክምና ባለሙያዎች ጋር የነበረው ንክኪ አሁን ላይ በመንግስት የክትትል ሰንሰለት ውስጥ ተካቷል።
ኢቦላ በበሽታው ከተያዘ ሰው ሰውነት ውስጥ ከሚወጡ ፈሳሾች ወይም በበሽታው ከተበከሉ ነገሮች ጋር ቀጥተኛ ንክኪ በሚፈጠርበት ወቅት የሚተላለፍ አደገኛ በሽታ በመሆኑ የጤና ባለስልጣናት የኢቦላን ስርጭት ለመቆጣጠር የተለዩትን ግለሰቦች በቅርበት እየተከታተሉ ይገኛሉ።
ትግስት ላቀው
#ዳጉ_ጆርናል Photo

4 hours ago
#uog
በ2019 ዓ.ም ጎንደር ዩኒቨርሲቲ አዲስ የተመደባችሁ የመጀመሪያ ዓመት መደበኛ ተማሪዎች እንዲሁም በ2018 ዓ.ም የሪሚዲያል ትምህርታችሁን ተከታትላችሁ ያለፋችሁ ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ቀናት ጥቅምት 04 እና 05/2019 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።
በተመሳሳይ በጎንደር ዩኒቨርሲቲ በድኅረ-ምረቃ ፕሮግራም ለመማር ያመለከታችሁ አዲስ ገቢ ተማሪዎች የመግቢያ ቀናት ጥቅምት 04 እና 05/2019 ዓ.ም መሆኑ ተገልጿል።
አዲስ ገቢ የመጀመሪያ ዲግሪ መደበኛ ተማሪዎች ለምዝገባ ልትይዟቸው የሚገቡ፦
● ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
● የ12ኛ ክፍል ሰርተፊኬት ዋናውና ኮፒው፣
● አራት 3x4 መጠን የሆኑ ጉርድ ፎቶግራፎች፣
● አንሶላ፣ ብርድ ልብስ፣ ትራስ ልብስ እና የስፖርት ልብስ።
የምዝገባ ቦታ፡-
● ለማኅበራዊ ሳይንስ መስክ መደበኛ አዲስ ገቢ ተማሪዎች በማራኪ ግቢ
● ለተፈጥሮ ሳይንስ መስክ መደበኛ አዲስ ገቢ ተማሪዎች በአጼ ቴዎድሮስ ግቢ
● ለድኅረ-ምረቃ ተማሪዎች በግቢው ረዳት ሬጅስትራር ጽ/ቤቶች
አዲስ ገቢ የመጀመሪያ ዲግሪ መደበኛ ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሰቲው ከመሔዳችሁ በፊት በኦንላይን (Registration.uog.edu.et) ምዝገባችሁን እንድትፈጸሙ ተብሏል። (የምዝገባ ሒደቱ ቅደም ተከተልን ከላይ ከተያያዘው ምስል ይመልከቱ።)
@tikvahuniversity

#dillauniversity
በ2019 ዓ.ም ዲላ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ ገቢ (Freshman) ተማሪዎች እንዲሁም በ2018 ዓ.ም የሪሚዲያል ትምህርታችሁን በዲላ ዩኒቨርሲቲ ተከታትላችሁ የማለፊያ ውጤት ያመጣችሁ ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ጥቅምት 05 እና 06/2019 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።
በተመሳሳይ በ2ኛ ዲግሪ (Masters) እና በ3ኛ ዲግሪ (PhD) ፕሮግራሞች ለመማር አመልክታችሁ ተቀባይነት ያገኛችሁ አዲስ ገቢ የድኅረ-ምረቃ መደበኛ ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ጥቅምት 05 እና 06/2019 ዓ.ም መሆኑ ተገልጿል።
በ2019 ዓ.ም ወደ ዲላ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ ገቢ የሪሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ጥቅምት 19 እና 20/2019 ዓ.ም መሆኑ ተመላክቷል።
አዲስ ገቢ ተማሪዎች ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦
● ከ9-12ኛ ክፍል የትምህርት ማስረጃዎች ዋናውና ኮፒው፣
● የ8ኛ ክፍል ፈተና ካርድ ዋናውና ኮፒው፣
● ስምንት 3x4 የሆነ ፎቶግራፎች፣
● አንሶላ፣ የትራስ ጨርቅ፣ ብርድ ልብስ እና የስፖርት ልብስ፣
● አንድ የሰነድ መያዣ ክላሰር።
የምዝገባ ቦታ፦
ኦዳያኣ ግቢ የሬጅስትራር ህንፃ ቁጥር 609 በአካል

10 hours ago
ከመካከለኛው ምስራቅ የሚላከው የጥሬ ነዳጅ መጠን በመጨመሩ የዓለም አቀፍ የነዳጅ ዋጋ ቀነሰ
ከመካከለኛው ምስራቅ የሚላከው የጥሬ ነዳጅ መጠን አሜሪካ እና እስራኤል በኢራን ላይ ጦርነት ከመክፈታቸው በፊት ከነበረበት ደረጃ በላይ መጨመሩን የሚያሳዩ ዘገባዎችን ተከትሎ፣ የዓለም አቀፍ የነዳጅ ዋጋ ቅናሽ ማሳየቱን ሮይተርስ ዘግቧል።
የብሬንት ጥሬ ነዳጅ የ1 በመቶ ቅናሽ በማሳየት በበርሜል 101.18 ዶላር የደረሰ ሲሆን፣ ከጥቂት ሰዓታት በፊት ደግሞ የአሜሪካው ዌስት ቴክሳስ ኢንተርሚዲየት ጥሬ ነዳጅ ዋጋ የ1.03 በመቶ ቅናሽ በማሳየት በበርሜል 90.12 ዶላር ሆኖ ነበር።
ቀደም ሲል እንደተዘገበው፣ ከቀጠናው የሚወጣው የጥሬ ነዳጅ ኤክስፖርት መጠን በሴፕቴምበር 24 እንዲሁም በሴፕቴምበር 27 እና 29 መካከል ከጦርነቱ በፊት ከነበረው መጠን በልጦ ተገኝቷል።ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ የጂ 7 ሀገራት ከድንገተኛ አደጋ ተጠባባቂ ቋታቸው 100 ሚሊዮን በርሜል ጥሬ ነዳጅ እና ዲዜል ለገበያ ለማቅረብ ተስማምተዋል።
የ KCM Trade ዋና ተነታኝ ቲም ዋተረር ለሮይተርስ እንደተናገሩት፣ “በባህረ ሰላጤው ቀጠና በሚገኙ የኃይል መሰረተ ልማቶች ላይ ተጨማሪ ጉዳት የመድረሱ ስጋት እስካሁን ያልተወገደ ቢሆንም፣ የሁለቱ ሁኔታዎች መጣመር የነዳጅ ዋጋን ለጊዜው ለማረጋጋት በቂ ነው” ብለዋል።
በሚኪያስ ጸሐዬ
#ዳጉ_ጆርናል

Sponsored by
Surafel
18 hours ago
ጥራትና ደህንነቱ ሳይጠበቅ የሚጓጓዝ ጥሬ ወተት ለከፍተኛ የጤና አደጋ የሚያጋልጥ መሆኑ ተገለፀ!
#fastmereja :- ጥራትና ደህንነቱ ሳይጠበቅ ከቦታ ቦታ የሚጓጓዝ ጥሬ ወተት ለከፍተኛ የጤና አደጋ የሚያጋልጥ በመሆኑ፣ የህብረተሰቡን ጤና ለመጠበቅ በትራንስፖርትና አያያዝ ሂደት ላይ ተገቢው ጥንቃቄ ሊደረግ እንደሚገባ ተገለፀ።
ወተት ከታለበ በኋላ ተገቢው የንፅህና እና የቅዝቃዜ ቁጥጥር (Cold Chain) ሳይደረግለት በሚጓጓዝበት ወቅት እንደ E. coli Salmonella እና Listeria ያሉ አደገኛ ባክቴሪያዎች በቀላሉ የሚራቡበት መንገድ እንደሚሆን ተመላክቷል።
በተለይም ወተቱ ከታለበበት ጊዜ ጀምሮ እስከ ተጠቃሚው ድረስ ከ 4°C በታች ባለው የቅዝቃዜ መጠን ካልተጠበቀ፣ በሙቀት ምክንያት ተህዋሲያኑ በፍጥነት በመራባት ለከባድ የሆድ ቁርጠት፣ ለተቅማጥ፣ ለትውከት፣ ለሳንባ ነቀርሳ እንዲሁም ለተለያዩ ህመሞች ሊዳርጉ እንደሚችሉ ተጠቁሟል።
ይህ የጤና አደጋ በተለይ በህፃናት፣ በነፍሰ ጡር እናቶች፣ በአረጋውያን እና የበሽታ መከላከል አቅማቸው ዝቅተኛ በሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች ላይ ከባድ ጉዳት የሚያደርስ ነው።
የወተት ደህንነትንና ጥራትን ለማረጋገጥ የሚከተሉት አበይት እርምጃዎች ሊወሰዱ እንደሚገባ ተመላክቷል፦
ወተትን ለማጓጓዝ ደረጃቸውን የጠበቁ የአሉሚኒየም ወይም የማይዝግ ብረት (Stainless steel) ዕቃዎችን መጠቀም እና የዕቃዎቹን ንፅህና በየጊዜው መጠበቅ፤ የማቀዝቀዣ ዘዴዎችን መጠቀም በትራንስፖርት ወቅት ወተቱ እንዳይበላሽ የቅዝቃዜ ሰንሰለቱን የጠበቁ የመጓጓዣ ዘዴዎችን (Refrigerated transport) መተግበር እንዲሁም ተጠቃሚዎች ጥሬ ወተትን ከመጠቀማቸው በፊት በደንብ አፍልተው የመጠቀም ልምድን ማዳበር እንደሚገባ ነዉ የተገለፀዉ።
በመሆኑም አምራቾች፣ አጓጓዦችና ነጋዴዎች የምግብ ደህንነት መመሪያዎችን በአግባቡ በመተግበርየህብረተሰቡን ጤና የመጠበቅ ሀላፊነታቸውን እንዲወጡ ጥሪ ቀርቧል።
ህብረተሰቡ ጥራትና ደህንነቱ ያልተረጋገጠ የወተት ምርት ሲያጋጥመው ወደ 8482 በነፃ በመደወል ጥቆማ መስጠት እንደሚችል ባለሥልጣኑ አስታውቋል።

23 hours ago
የእናንተ ጀማ ማልያ እናሰራ ብሎ ማውራት ከጀመረ ስንት ወር አልፎታል😭
እናንተ መወዛገብ አቁማቹ ወደ የኛ ስፖርት ዌር በመምጣት በፈለጋቹት ዲዛይን፣ ከለር እና ጥራት ማልያዎችን እንድታሰሩ እንጋብዛለን።
ደግሞ ከየኛ ስፖርት 25 ማልያ ለሚያዙ ቡድኖችች;-
⚡️25 ነፃ ፒፕስ
⚡️ነፃ የቡድን ባንዲራ
⚡️ነፃ የአመበል ባጅ መስጠት ጀምረናል::
ምን እሱ ብቻ⚡️
🚛በፈጣን ትራንስፖርትም ያላቹበት ከተማ እንልካለን።
📍አድራሻችን-> አዲስ አበባ -ደምበል ፣ አሚር ህንፃ ግራውንድ ላይ
📞ስልካችን- 0906230303
0944613334
0970970707
የኛ ስፖርት-ይቻላል!

1 day ago
ወደ ኬንያ የድንጋይ ከሰል ኤክስፖርት ለማድረግ ንግግር መጀመሩን ዮ ሆልዲንግ ገለጸ።
"ዮ ሆልዲንግ ንግድና ማኑፋክቸሪንግ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር"፣ በኢትዮጵያ ያለውን የድንጋይ ከሰል ሀብት በዘመናዊ ቴክኖሎጂ በማጣራት ለሀገር ውስጥ ኢንዱስትሪዎች የኃይል ግብዓት እያቀረበ መሆኑን ገልጿል።
የኩባንያው ባለቤትና ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ መኳንንት አለሙ እንደገለጹት፣ ኩባንያው በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ካማሺ ዞን ፏፏቴ ወረዳ በ2012 ዓ.ም የመጀመሪያውን የድንጋይ ከሰል ማጠቢያ ፋብሪካ (በሰዓት 150 ቶን የማምረት አቅም ያለው) አስጀምሮ፣ በ2017 ዓ.ም መጨረሻ ደግሞ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጋሞ ዞን ቦረዳ ወረዳ ሁለተኛውን ፋብሪካ (በሰዓት 250 ቶን የማምረት አቅም ያለው) አስገንብቷል።
በሁለቱ ፋብሪካዎች በጥምረት በሰዓት እስከ 400 ቶን የታጠበ ከሰል የማምረት አቅም ላይ ደርሷል።
ኩባንያው በአዲሱ በጀት ዓመት በሁለት ወራት ውስጥ ከ200,000 ቶን በላይ ድንጋይ ከሰል አጥቦ ያቀረበ ሲሆን፣ በዓመቱ ውስጥ ከ1.2 ሚሊዮን ቶን በላይ ለማዘጋጀት እየሰራ መሆኑን ገልጿል፤ በአጠቃላይ በሁለቱም ክልል ካሉ ፋብሪካዎች 1.7 ሚሊዮን ቶን ለማምረት አቅዷል።
በ2018 ዓ.ም በ6 ወራት ውስጥ ብቻ ከ450 ሺህ ቶን በላይ ማምረቱንም አክሏል።
"ዮ ሆልዲንግ" በሁለት ተጨማሪ አካባቢዎች ተጨማሪ ፋብሪካዎችን ለመገንባት በዝግጅት ላይ ሲሆን፣ በዚህ ዓመት መጨረሻ ወደ ኬንያ የድንጋይ ከሰል ኤክስፖርት ለማድረግ የሚያስችለውን ስምምነት ለማድረግ ከሚመለከታቸው ኩባንያዎች ጋር ንግግር መጀመሩን አቶ መኳንንት ገልጸዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መስከረም 25 ቀን 2019 ዓ.ም
@TikvahethMagazine

የኢትዮጵያ ከባድ ጭነት አሽከርካሪዎች ጅቡቲ ከገቡ በኋላ ደህንነታቸውን ለመከታተል የሚያስችል አዲስ ሥርዓት እንደዘረጋ ፌዴሬሽኑ አስታወቀ
ወደ ጂቡቲ የሚገቡ የኢትዮጵያ ከባድ ጭነት አሽከርካሪዎችን ደኅንነት እና የሚደርስባቸውን ችግር በቀላሉ ለመከታተል የሚያስችል አዲስ ሥርዓት መዘርጋቱን ያስታወቀው የኢትዮጵያ ትራንስፖርት አሠሪዎች ፌዴሬሽን ነው።
የፌዴሬሽኑ ፕሬዝዳንት አቶ ብርሃኔ ዘርዑ፣ "አሽከርካሪዎች የሀገር ድንበር ካለፉ በኋላ ለመቆጣጠር የሚያስችለው ይህ አሠራር የተዘረጋው ከጂቡቲ ትራንስፖርት ፌዴሬሽን ጋር በተደረገ ስምምነት ነው" ብለዋል።
አሠራሩን ወደ ሥራ ለማስገባት የሚያስችሉ የሰነድ ሥራዎች በመጠናቀቃቸው በቅርቡ አገልግሎት መስጠት ይጀምራል ተብሏል።
አዲሱ ሥርዓት የአሽከርካሪዎችን ደኅንነት እና የተሽከርካሪዎችን ሁኔታ ለማረጋገጥ እንደሚረዳ አቶ ብርሃኔ ጠቁመዋል።
አሠራሩን በተግባር ለሚያውሉ አካላት ለአንድ ወር ያህል ስልጠና እንደሚሰጥም ገልጸዋል።
ከዚህ ቀደም ይህ ሥርዓት ባለመኖሩ በተሽከርካሪዎች ላይ እንግልት መድረሱን አሰና በሀገሪቱ ኢኮኖሚ ላይ ጫና ፈጥሮ መቆየቱን ፕሬዝዳንቱ አብራርተዋል። አዲሱ አሠራር ተሽከርካሪዎች በተመደበላቸው ጊዜ አገልግሎት እንዲሰጡ እንደሚያደርግም ተገልጿል።
በተመስገን ተጋፋው

#haramayauniversity
በ2019 ዓ.ም የከፍተኛ ትምህርታችሁን በሐረማያ ዩኒቨርሲቲ እንድትከታተሉ የተመደባችሁ አዲስ የቅድመ-ምረቃ ፕሮግራም ተማሪዎች ሪፖርት ማድረጊያ ቀናት ከጥቅምት 05-08/2019 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።
የምዝገባ ቦታ፦
ሐረማያ በሚገኘው የዩኒቨርሲቲው ዋና ግቢ
ወደ ዩኒቨርሲቲው ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦
➻ የ8ኛ ክፍል ሰርቲፍኬት፣
➻ ከ9ኛ-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት፣
➻ የ12ኛ ክፍል ፈተና ሰርቲፍኬት ዋናውና ኮፒው፣
➻ 6 ፓስፖርት መጠን ፎቶግራፎች፣
➻ ብርድ ልብስ፣ አንሶላ፣ የትራስ ልብስ እና የስፖርት ልብስ።
ከላይ የተገለፁትን የትምህርት ማስረጃዎች እና ጉርድ ፎቶግራፍ ስካን በማድረግ በሶፍት ኮፒ መያዝ ይኖርባችኋል ተብሏል።

#hawassauniversity
በ2019 ዓ.ም በመደበኛ የዲግሪ ፕሮግራም ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ አዲስ የተመደባችሁ ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ጥቅምት 03 እና 04/2019 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።
የምዝገባ ቦታ፦
➻ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች በዋናው ግቢ
➻ የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች በቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት
ወደ ዩኒቨርሲቲው ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦
➻ የ12ኛ ክፍል ፈተና ውጤት ዋናውና ኮፒው፣
➻ ከ9ኛ-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
➻ አራት ጉርድ ፎቶግራፍ፣
➻ አንሶላ፣ ብርድ ልብስ እና ትራስ ጨርቅ፣
➻ የስፖርት ልብስ።

2 days ago
የኮቴ ክፍያ‼️
በተለያዩ አካባቢዎች የሚጠየቀው የአሽከርካሪዎች የኮቴ ክፍያ በ70% መቀነሱ ተገለጸ‼️
👉በ2019 የኮቴ ክፍያን ሙሉ በሙሉ ለማስቀረት ይሰራል ተብሏል
በትራንስፖርት እና ሎጀስቲክስ ሚኒስቴር እና በፌደሬሽኑ ቅንጅታዊ አሰራር በተከናወነ ሥራ አሽከርካሪዎች የሚጠየቁት አግባብነት የሌለው የኮቴ ክፍያ በ70% መቀነሱን የኢትዮጵያ ትራንስፖርት አሰሪዎች ፌደሬሽን አስታውቋል።
የፌደሬሽኑ ፕሬዘዳንት አቶ ብርሃኔ ዘሩ ለአሐዱ ሬድዮ እንደተናገሩት፤ ክፍያው በሀገሪቱ ሕግ የማይፈቀድ በመሆኑ ከክልሎች ጋር በተደረገ ውይይት እንዲቀንስ ተደርጓል።
በአማራ ክልል፣ በኦሮሚያ ክልል እና በጂቡቲ ኮሪደር የሚጠየቀው ክፍያ መቀነሱን ተናግረዋል።
የኮቴ ክፍያ አሁንም ባልቀረባቸው አካባቢዎች በ2019 የበጀት ዓመት ሙሉ ለሙሉ ለማስቀረት መንግሥት እና ፌደሬሽኑ በትኩረት እንደሚሠሩ አቶ ብርሃኔ ዘሩ ገልጸዋል።
@Yenetube Fikerassefa

Seledadotio

ላይቤሪያን የሚመጥን
የላይቤሪያ ብሔራዊ ቡድን × ዋናው የስፖርት ትጥቅ
ይፋዊ የስፖርት ትጥቅ አቅራቢ
ግጥሚያው ከመጀመሩ በፊት...
አንድ ሀገር ቀለሟን፣ ማንነቷን የምትለብስበት ያ ታላቅ ቅፅበት አለ!
በላይቤሪያ ብሔራዊ ቡድን የተጫዋቾች ልብስ መቀየሪያ ክፍል ግድግዳ ላይ የ'ዋናው'ን የስፖርት ትጥቆች ማየት ለኢትዮጵያም ታላቅ ኩራት ይሰጠናል።
ይሄ ነው ዋናው!
📸 የፎቶ ምንጭ፦ የላይቤሪያ ወንዶች ብሔራዊ ቡድን / LFA
https://web.facebook.com/s...

በተለያዩ አካባቢዎች የሚጠየቀው የአሽከርካሪዎች የኮቴ ክፍያ በ70% መቀነሱ ተገለጸ
👉በ2019 የኮቴ ክፍያን ሙሉ በሙሉ ለማስቀረት ይሰራል ተብሏል
በትራንስፖርት እና ሎጀስቲክስ ሚኒስቴር እና በፌደሬሽኑ ቅንጅታዊ አሰራር በተከናወነ ሥራ አሽከርካሪዎች የሚጠየቁት አግባብነት የሌለው የኮቴ ክፍያ በ70% መቀነሱን የኢትዮጵያ ትራንስፖርት አሰሪዎች ፌደሬሽን አስታውቋል።
የፌደሬሽኑ ፕሬዘዳንት አቶ ብርሃኔ ዘሩ ለአሐዱ ሬድዮ እንደተናገሩት፤ ክፍያው በሀገሪቱ ሕግ የማይፈቀድ በመሆኑ ከክልሎች ጋር በተደረገ ውይይት እንዲቀንስ ተደርጓል።
በአማራ ክልል፣ በኦሮሚያ ክልል እና በጂቡቲ ኮሪደር የሚጠየቀው ክፍያ መቀነሱን ተናግረዋል።
የኮቴ ክፍያ አሁንም ባልቀረባቸው አካባቢዎች በ2019 የበጀት ዓመት ሙሉ ለሙሉ ለማስቀረት መንግሥት እና ፌደሬሽኑ በትኩረት እንደሚሠሩ አቶ ብርሃኔ ዘሩ ገልጸዋል።
በህይወቴ ጌትነት

ከ30 ዓመት በላይ ያገለገሉ የጭነት ተሽከርካሪዎች ላይ ተጥሎ የነበረው ዕገዳ በጊዜያዊነት መነሳቱ ተገለጸ
ከ30 ዓመት በላይ አገልግሎት የሰጡ የጭነት ተሽከርካሪዎች ወደ ጅቡቲ እንዳይገቡ ተጥሎ የቆየው ዕገዳ በጊዜያዊነት መነሳቱን የኢትዮጵያ ትራንስፖርት አሰሪዎች ፌዴሬሽን አስታውቋል።
የትራንስፖርት እና ሎጀስቲክስ ሚኒስቴር ተሽከርካሪዎቹ ረጅም ጊዜ ያገለገሉ በመሆናቸው አገልግሎት እንዳይሰጡ ውሳኔ አሳልፎ እንደነበር ይታወሳል።
የፌዴሬሽኑ ፕሬዚዳንት አቶ ብርሃኔ ዘርዑ ለአሐዱ ሬድዮ እንዳስታወቁት መንግስት በተፈጥሮ ጋዝ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎችን የሚያበረታታ የፖሊሲ ለውጥ በማድረጉ ረጅም ዓመታት ያስቆጠሩ የጭነት ተሽከርካሪዎችን ለመቀነስ እየተሰራ ይገኛል።
ፌደሬሽኑ በብድር አዳዲስ የጭነት ተሽከርካሪዎችን ለማስገባት ጥረት እያደረገ በመሆኑ በቆዩት ላይ ተጥሎ የነበረው ዕገዳ በጊዜያዊነት ተነስቶ አገልግሎት እንዲሰጡ መደረጉን ገልጸዋል።
ረጅም ዓመታት አገልግሎት የሰጡ ተሽከርካሪዎችን ያለበቂ ዝግጅት ከዘርፉ ማስወጣት ተገቢ አለመሆኑን አቶ ብርሃኔ ጠቁመዋል።
አክለውም፤ ለውሳኔው ተግባራዊነት ምቹ ሁኔታ እንዲፈጠር ጥሪ አቅርበዋል።
በኢትዮጵያ በጥናት የተረጋገጠ መረጃ ባይኖርም ከ14 እስከ 15 ሺህ የሚገመቱ የጭነት ተሽከርካሪዎች እንደሚገኙ ይታመናል።

3 days ago
የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ የሂሳብ መዝገብ ለሌላቸው ግብር ከፋዮች የሽግግር መመሪያ ይፋ አደረገ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ በ2018 የበጀት ዓመት የግብር ማሳወቂያ ወቅት የሂሳብ መዝገብ ማቅረብ ላልቻሉ የደረጃ «ሀ» እና «ለ» ግብር ከፋዮች የሚያገለግል የማስተናገጃ መመሪያ ይፋ አደረገ። ቢሮው መስከረም 2019 ዓ.ም ባወጣው መመሪያ እንደገለጸው፣ ይህ አሰራር ለ2018 የግብር ዘመን ብቻ የሚሰራ ጊዜያዊ የሽግግር መፍትሔ ነው።
መመሪያው የተዘጋጀው በተሻሻለው የፌዴራል ገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር 1395/2017 እና በነባር አዋጆች መሰረት መዝገብ መያዝ ግዴታ ቢሆንም፣ ከግብር ከፋዮች በቀረቡ የሥራ ባህሪ ቅሬታዎች ምክንያት ነው። በዚህም መሰረት፡-
ከመንግስት ጋር ውል ያላቸው፡- የትምህርት ቤት መጋቢ እናቶች፣ የፅዳት፣ የቆሻሻ አሰባሰብ እና ገፀ-ምድር ማስዋብ ማህበራት ዓመታዊ የክፍያ ሰነድ በማቅረብ በደንብ ቁጥር 410/2009 ሠንጠረዥ «ሐ» መሠረት ግብራቸው ይሰላል። የሸገር ዳቦ አከፋፋዮች ተጨማሪ ንግድ ካላቸው፣ ተጨማሪው ስራ ብቻ ተለይቶ ግብር ይጣልበታል።
በትርፍ ህዳግ የሚስተናገዱ፡- የጫኝና አውራጅ፣ የኤሌክትሪክ ምሰሶ ቆፋሪዎች፣ የጥበቃ ማህበራት እና የታክሲ ታራ አስከባሪዎች የሂሳብ መዝገብ ባያቀርቡም ለዘርፉ በተቀመጠው የትርፍ ህዳግ መሰረት ግብራቸው ይወሰናል።
የሙያ ፈቃድ ያላቸው እና የኪራይ ገቢዎች፡- ጠበቆች፣ የኢንሹራንስ ወኪሎችና ገማቾች እንዲሁም መዝገብ የሌላቸው የንግድና መኖሪያ ኪራይ ገቢ ያላቸው አካላት 35 በመቶው እንደ ወጪ ተይዞላቸዋል፤ በቀረው 65 በመቶ ገቢያቸው ላይ ግብር ይከፍላሉ።
የትራንስፖርት ዘርፍ እና ያደጉ ግብር ከፋዮች፡- በትራንስፖርት የተሰማሩ ደረጃ «ሀ» ግብር ከፋዮች የ57 በመቶ የዋጋ ግሽበት ማስተካከያ ተደርጎላቸው በደረጃ «ለ» ቀመር የሚያሳውቁ ሲሆን፣ በአዲሱ አዋጅ ወደ ደረጃ «ሀ» ያደጉትም በደረጃ «ለ» አሰራር እንዲስተናገዱ ተወስኗል።
ይህ አሰራር ለ2018 የበጀት ዓመት ብቻ የሚያገለግል ሲሆን፣ ተጠቃሚዎች ለቀጣይ ዓመት መዝገብ ለመያዝ የቃል-መሐላ እንደሚፈፅሙና የሰነድ አለመያዝ አስተዳደራዊ ቅጣት እንደሚጣስባቸው ቢሮው አሳውቋል።

የአዲስ አበባ ከተማ ገቢዎች ቢሮ የሂሳብ መዝገብ የማይዙ ግብር ከፋዮች የሚስተናገዱበትን የአሰራር ስርዓትን የሚዘረጋ ማስተናገጃ መመሪያ ይፋ አደረገ።
• ይህ ሁሉን አቀፍ የማስተናገጃ አሰራር ተግባራዊ የሚሆነው ለ2018 የግብር ዘመን ብቻ ነው።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ በ2018 የበጀት ዓመት የግብር ማሳወቂያ ወቅት የሂሳብ መዝገብ የማቅረብ ግዴታቸውን መወጣት ላልቻሉ የተወሰኑ የንግድና አገልግሎት ዘርፎች የተዘጋጀውን ዝርዝር የማስተናገጃ የአሰራር ስርዓት ይፋ አፍርጓል።
ቢሮው መስከረም 2019 ዓ.ም ባወጣው የክንውን መመሪያ እንዳብራራው፣ በተሻሻለው የፌዴራል ገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር 1395/2017 እንዲሁም በነባሮቹ አዋጆች ቁጥር 979/2008 እና 983/2008 መሰረት የደረጃ «ሀ» እና «ለ» ግብር ከፋዮች የሂሳብ መዝገብና መግለጫ መያዝ ህጋዊ ግዴታቸው ቢሆንም፣ በርካታ ከፋዮች የስራ ባህሪያቸውን ጠቅሰው ቅሬታ በማቅረባቸው ፍትሃዊ የታክስ አሰባሰብን ለማረጋገጥ የመጨረሻ የሽግግር አሰራር ዘርግቷል።
በመመሪያው ላይ በዝርዝር እንደተቀመጠው፣ ስራዎችን ከመንግስት ጋር በተገባ ውል ብቻ የሚያከናውኑ እና የተለየ ድጋፍ የሚሹ ግብር ከፋዮች ማለትም:-
- በትምህርት ቤቶችና በምግብ ማዕከላት ውስጥ በምግብ አቅራቢነት የተደራጁ መጋቢ እናቶች፣
- በከተማ ፅዳትና ውበት፣
- በደረቅ ቆሻሻ አሰባሰብ እና በገፀ-ምድር ማስዋብ ላይ የተሰማሩ ማህበራት ከመንግስት ተቋማት የተከፈላቸውን ዓመታዊ ክፍያ የሚያሳይ ሰነድ ሲያቀርቡ፣ በደንብ ቁጥር 410/2009 ሠንጠረዥ «ሐ» መሠረት ግብራቸው ተሰልቶ እንዲከፍሉ ይደረጋል።
ከዚህም በተጨማሪ የሸገር ዳቦ የሚሸጡ ማህበራት በተጓዳኝ የሚያከናውኑት ተጨማሪ ንግድ መኖሩ በመስክ ምልከታ ከተረጋገጠ ተጨማሪው ስራ ብቻ ተለይቶ ግብር እንዲጣልበት ይደረጋል።
• የጫኝና አውራጅ፣
• የኢትዮጵያ መብራት ኃይል ኤሌክትሪክ ምሰሶ ጉድጓድ ቆፋሪዎች፣
• በጥበቃ ስራ የተደራጁ ማህበራት እንዲሁም የታክሲ ታራ አስከባሪዎች የሂሳብ መዝገብ መያዝ ሲኖርባቸው ያልያዙ ግብር ከፋዮች ለዘርፉ በተቀመጠው የትርፍ ህዳግ መሰረት ግብራቸው ይሰላል።
በሌላ በኩል፣ የንግድ ስራ ፈቃድ ሳይኖራቸው በሙያ ፈቃድ ብቻ አገልግሎት የሚሰጡ እንደ ጠበቆች፣ የኢንሹራንስ ወኪሎች፣ የኢንሹራንስ ጉዳት ገማቾች እና በአዋጁ የተዘረዘሩ ሌሎች 8ቱ ዘርፎች የሂሳብ መዝገብ ማቅረብ የሚጠበቅባቸው ቢሆንም፣ የገንዘብ ሚኒስቴር ወጪን በተመለከተ ዝርዝር መመሪያ እስካላወጣ ድረስ ቀደም ሲል በተጠኑ ጥናቶች መሰረት ከተገኘው አጠቃላይ ገቢ ላይ 35 በመቶው እንደ ወጪ እንዲያዝላቸው፣ ቀሪው 65 በመቶ ደግሞ ግብር የሚሰላበት የተጣራ ገቢ ሆኖ በሠንጠረዥ «ሐ» እንዲስተናገዱ ይደረጋል።
በግምት ግብር አዋሳኝ አዋጅ ቁጥር 138/2010 መሰረት የደረጃ «ሀ» የንግድና የመኖሪያ ኪራይ ገቢ ያላቸው አካላትም መዝገብ ካላቀረቡ በተመሳሳይ መልኩ 35 በመቶ ወጪ ተቀናሽ ተደርጎ በ65 በመቶ ገቢያቸው ላይ ግብሩ ይሰላል።
መመሪያው የትራንስፖርት ዘርፉን እና የአነስተኛ ግብር ከፋዮችን እድገት በተመለከተም ዝርዝር መፍትሔዎችን አስቀምጧል።
በትራንስፖርት ዘርፍ የተሰማሩ የደረጃ «ሀ» ግብር ከፋዮች በ2016 ወይም በ2017 የበጀት ዓመት የ57 በመቶ የዋጋ ግሽበት ማስተካከያ ተደርጎላቸው በደረጃ «ለ» ቀመር መሰረት ግብራቸውን እንዲያሳውቁ ይደረጋል።
በአዋጅ ቁጥር 979/2008 መሰረት በደረጃ «ለ» እና «ሐ» ስር ቆይተው በአዲሱ ማሻሻያ አዋጅ ቁጥር 1395/2017 ወደ ደረጃ «ሀ» ያደጉ ግብር ከፋዮችም የ2017 ዓመታዊ የንግድ ስራ ግብር እና የትርፍ ድርሻ ክፍያቸው ተወስዶ በደረጃ «ለ» አሰራር እንዲሰላ ተወስኗል።
በአዋጅ ቁጥር 1395/2017 አንቀጽ 23 አማራጭ አነስተኛ ግብር ለደረጃ «ሀ» ግብር ከፋዮች የተደነገገውም ከ2 ሚሊዮን ብር አማራጭ አነስተኛ ግብር 2.5 በመቶ ጋር ተነጻጽሮ የተሻለው ተወስዶ ግብር ይወሰናል።
ቢሮው በመሪሪያው ላይ እንዳመለከተው ፣ ይህ ሁሉን አቀፍ የማስተናገጃ አሰራር ተግባራዊ የሚሆነው ለ2018 የግብር ዘመን ብቻ ነው።
በዚህ እድል ተጠቃሚ የሚሆኑ ማናቸውም ግብር ከፋዮች ለቀጣዩ የበጀት ዓመት የሂሳብ መዝገብ ይዘው ለመቅረብ ህጋዊ የቃል-መሐላ እንዲፈፅሙ የሚደረግ ሲሆን፣ የሰነድ አለመያዝ አስተዳደራዊ ቅጣትም አብሮ ተግባራዊ እንደሚሆንባቸው ተመላክቷል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
መስከረም 23 ቀን 2019 ዓ/ም
@tikvahethiopia

ከትራምፕ ዛቻ በኋላ የቡድን 7 አገራት ከክምችታቸው 100 ሚሊዮን በርሜል ነዳጅ እና ናፍጣ ሊለቁ ነው
የቡድን ሰባት አገራት የዋጋ ንረት ያስከተለውን የአቅርቦት ችግርን ለማቃለል 100 ሚሊዮን በርሜል ነዳጅ እና ናፍጣ እንደሚለቅቁ አስታወቁ።
የቡድን ሰባት መሪዎች በሰጡት መግለጫ፣ ይህ በ20 ቀናት ውስጥ የሚለቀቀውን ነጭ ናፍጣ የሚያካትት ሲሆን "አስፈላጊ ከሆነ ተጨማሪ ናፍጣ ለመልቀቅ ውይይት ይደረጋል" ብለዋል።
አሜሪካን ጨምሮ የላቀ ምጣኔ ሃብት ያላቸው የቡድኑ አባል አገራት፣ እርምጃው ወዲያውኑ ተግባራዊ መሆን እንደሚጀምር እና ለአራት ወራት ያህል እንደሚቆይ ገልጸዋል።
የአሜሪካው ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ የአሜሪካን ነዳጅ ወደ ውጪ እንዳይላክ እገዳ እንደሚጥሉ ካስፈራሩ በኋላ በተላለፈው ውሳኔ መሠረትም በቡድን ሰባት አባል አገራት መካከል ኢነርጂን እና የኢነርጂ ውጤቶችን ወደ ውጪ መላክ የሚከለክል ምንም ዓይነት ገደብ አይኖርም ተብሏል።
ቡድን ሰባት አሜሪካ፣ ዩናይትድ ኪንግደም፣ ካናዳ፣ ጃፓን፣ ጀርመን፣ ጣልያን እና ፈረንሳይን የሚይዝ ሲሆን አውሮፓ ኅብረትም በስብሰባዎቹ ተወክሏል።
ትራምፕ ቀደም ብሎ የአውሮፓ አገራት ከክምችታቸው ነዳጅ ወደ ገበያ ለመልቀቅ ካልተስማሙ ከአሜሪካ ናፍጣ ወደ ውጪ እንዳይላክ እንደሚያግዱ አስጠንቅቀው ነበር።
ይህንን ተከትሎ የቡድን ሰባት አገራት ከነዳጅ ክምችታቸው ወደ ገበያ ለመልቀቅ መስማማታቸው በመጪው ወር ከሚካሄደው የአሜሪካ የአጋማሽ ዘመን ምርጫ አስቀድሞ ለአሜሪካ ሸማቾች የዋጋ ንረትን እንደሚያቃልል ተገልጿል።
ትራምፕ አርብ ዕለት በማኅበራዊ ሚዲያ ገጻቸው ባጋሩት ጽሑፍ " አውሮፓውያን ከነጭ ናፍጣ ክምችታቸው በብዛት ለመልቀቅ ተስማምተዋል፤ ሒደቱም ወዲያውኑ ይጀምራል" ብለዋል።
የግምጃ ቤት ኃላፊው ስኮት ቢሴንትም ቀደም ብለው በዋጋ ንረቱ "የአሜሪካ አርሶ አደሮች ፣ የከባድ መኪና አሽከርካሪዎች እና የንግድ ተቋማት ጫናውን መሸከም የለባቸውም" ሲሉ አሳስበው ነበር።
ትራምፕ በኋላ ላይ በዋይት ሃውስ በተናገሩበት ወቅት ግን "ነጭ ናፍጣ ወደ ውጭ የመላክ እገዳ ጠረጴዛ ላይ አልነበረም" ብለዋል።
ቡድን ሰባት ከክምችቱ ነዳጅ ለመልቀቅ ያሳለፈውን ውሳኔ በመጥቀስም ፤ "አውሮፓ ያደረገው በጣም ትልቅ ነገር ነው" ሲሉ ውሳኔውን አድንቀዋል።
"አውሮፓ ብዙ ነጭ ናፍጣ አለው፤ ለዓለም ትልቁን አስተዋፅኦ ያደረጋል፤ እኛም እንደዚያው" ያሉት ትራምፕ ከአሜሪካ ነዳጅ እንዳይላክ እንደማያግዱ አስታውቀዋል። " ማድረግ ያለብንን እናደርጋለን" ብለዋል።
ትራምፕ ነጭ ናፍጣ ወደ ውጭ እንዳይላክ እገዳ እንደሚጥሉ ያስታወቁት ባለፈው ሳምንት መጀመሪያ ላይ ሲሆን አስተዳደራቸው አውሮፓ ከክምችቱ እንዲለቅ ጫና ሲያደርግ ቆይቷል።
ውሳኔው የተላለፈበትን ስብሰባ የመሩት የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ፣ ኅብረቱ በዓለም አቀፍ የኢነርጂ ኤጀንሲ (አይኢኤ) ትብብር ሥር "እስከ 100 ሚሊዮን በርሜል" የሚደርስ ክምችት በአራት ወራት ውስጥ ለመልቀቅ መስማማቱን" ተናግረዋል።
ሆኖም የትኞቹ አገራት እንደሚለቅቁ እንዲሁም በምን ያህል ፍጥነት እንደሚለቅቁ እስካሁን ግልጽ አይደለም።
ነጭ ናፍጣ በተለይ በትራንስፖርት ኢንደስትሪው እና በግብርናው ዘርፍ በብዛት ጥቅም ላይ የሚውል ሲሆን የዋጋው ንረት ምግብን ጨምሮ በተለያዩ ወሳኝ ፍጆታዎች ላይ የዋጋ ጭማሪን አስከትሏል።
ግማሽ የሚሆነው የዩኬ ናፍጣ ከውጭ የሚገባ ሲሆን ከዚህ ውስጥ 31 በመቶ የሚሆነው ከአሜሪካ የሚላክ ነው።
በውሳኔው አሜሪካ ለመጣል ስታስፈራራ የነበረውን እገዳ ማስቀረት መቻሉም ዩኬን ጨምሮ ከውጪ በሚመጣ ነዳጅ ላይ ጥገኛ ለሆኑ አገራት እፎይታን የሚሰጥ ነው ተብሏል።
አሜሪካ በዓለማችን ከፍተኛው ነጭ ናፍጣ ከሚያቀርቡ አገራት መካከል አንዷ ናት። እንደ የአሜሪካ ኢነርጂ ኢንፎርሜሽን አስተዳደር መረጃ ከሆነ በአገር ውስጥ ያላት ማጣሪያ በየቀኑ ከአራት እስከ አምስት ሚሊዮን በርሜል ያመርታል።
ከዚህ ውስጥ 3.6 ሚሊዮኑን አሜሪካውያን የሚጠቀሙበት ሲሆን የነዳጅ አጣሪዎች በቀን ከ1.2 እስከ 1.5 ሚሊዮን በርሜል ናፍጣ ወደ ውጪ ይልካሉ። ይህም አሜሪካን በዓለም ገበያ ወሳኝ አቅራቢ አድርጓታል።
ዋነኛ የነዳጅ አምራች የሆነችው ሩሲያ በነዳጅ ማጣሪያዎቿ ላይ በዩክሬን የተፈፀመባትን ጥቃት ተከትሎ ነጭ ናፍጣን ወደ ውጭ እንዳይላክ አግዳለች። ይህም የአቅርቦት እጥረቱን አባብሶታል።
ነጭ ናፍጣ ከቤንዚን የበለጠ ለማጣራት አስቸጋሪ ቢሆንም ፣ በትራንስፖርት ኢንደስትሪው እና በግብርናው ዘርፍ ጥቅም ላይ ስለሚውል ፍላጎትን መቀነስ አስቸጋሪ ነው።
BBC

በውጭ ሀገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በ25 ኤምባሲዎች ባሉበት ሆነው የፓስፖርት አገልግሎት እንዲያገኙ የሚያስችል አሰራር መዘርጋቱ ተገለጸ
በውጭ ሀገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ባሉበት ሆነው የፓስፖርት አገልግሎት እንዲያገኙ በ25 ኤምባሲዎች በኩል ሥራ መጀመሩን የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት አስታውቋል።
ተገልጋዮች በአቅራቢያቸው በሚገኙ የኢትዮጵያ ኤምባሲዎች በመሄድ አገልግሎቱን ማግኘት እንደሚችሉ የተቋሙ የሕዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ አምቦ መቃሳ ለአሐዱ ሬድዮ ገልጸዋል።
ተቋሙ አገልግሎቱን በሀገር አቀፍ ደረጃ ይበልጥ ተደራሽ ለማድረግ የቅርንጫፍ ቢሮዎቹን ቁጥር ከ38 ወደ 40 ማሳደጉ ተገልጿል።
ከነባር ቅርንጫፎች በተጨማሪ በአዲስ አበባ አጣና ተራ እና ንፋስ ስልክ ክፍለ ከተሞች ተጨማሪ የፓስፖርት ቅርንጫፎች ተከፍተዋል።
በተያዘው የበጀት ዓመት በሁሉም የአንድ መሶብ ማዕከላት የፓስፖርት አሰጣጥ አገልግሎት ለማስጀመር ቅድመ ዝግጅት መጠናቀቁን አቶ አምቦ መቃሳ ተናግረዋል።

የሁለተኛው ትውልድ የአርበኝነት ጥሪ፣ የኢትዮጵያ የታሪክ አደራ፣ የባሕር በር ተፈጥሯዊ መብት እና የጠላቶች ሴራ ማምከኛ አንድነት
*****************
ኢትዮጵያ ከ130 ሚሊዮን በላይ ሕዝብ ያላት፣ በሕዝብ ብዛት ከአፍሪካ ሁለተኛ እንዲሁም በዓለም ላይ ካሉ የባሕር በር የሌላቸው ሀገራት መካከል ደግሞ ቀዳሚዋ ናት።
የሀገር ዕድገትና የሕዝብ ቁጥር መስፋፋት ከተፈጥሮ ሀብት አጠቃቀምና ከንግድ መስመሮች ጋር ቀጥተኛ ቁርኝት ያለው ሲሆን፣ ኢትዮጵያ ከቀይ ባሕርና ከኤደን ባሕረ ሰላጤ ጋር ያላት ቁርኝት ትናንት የተጀመረ ሳይሆን የረጅም ዘመናት የታሪክ እውነት ነው።
በአክሱም ሥልጣኔ ወቅት አዱሊስ በመባል ይታወቅ የነበረው የቀይ ባሕር ወደብ ለአክሱም ንግድ፣ የባሕር ኃይልና ከሩቅ ምስራቅ እስከ ሜዲትራኒያን ከነበሩት ዓለም አቀፍ ማህበረሰቦች ጋር ለመገናኘት ዋና በር ነበር።
ሆኖም በተለያዩ ታሪካዊ አጋጣሚዎች፣ ጂኦፖለቲካዊ ለውጦችና በ1980ዎቹ መጨረሻ በታዩ ፖለቲካዊ ክስተቶች ምክንያት ኢትዮጵያ የባሕር በሯን እንድታጣ ሆነች። ይህ የባሕር በር ማጣት የሀገራችንን የታሪክ ጉዞ፣ የንግድ መስመርና የደኅንነት መዋቅር በእጅጉ የጎዳ የታሪክ ጠባሳ መሆኑ የብዙዎች ስምምነት ነው።
በአሁኑ ወቅት የቀይ ባሕርና የኤደን ባሕረ ሰላጤ ቀጣና በዓለም አቀፍ የንግድና የደኅንነት መዋቅር ውስጥ እጅግ ወሳኝ ስትራቴጂካዊ ቦታ አላቸው።
የአሜሪካ፣ የቻይና፣ የአውሮፓ ሀገራትና የባሕረ ሰላጤው ሀገራት በዚህ ቀጣና ያላቸው የጦር ሰፈርና ወታደራዊ እንቅስቃሴ የቀጣናውን ከፍተኛ አስፈላጊነት ያሳያል።
በምስራቅ አፍሪካ ትልቋና የኃይል ማዕከል የሆነች ሀገራችን ኢትዮጵያ፣ በዚህ ወሳኝ የውኃ አካል ላይ ቀጥተኛ መግቢያና ተጽዕኖ እንዳይኖራት መደረጉ የቀጣናውን የኃይል ሚዛንና ዘላቂ ሰላም የሚፈታተን ነው።
የባሕር በር አለመኖር ለኢትዮጵያ በቀላሉ የሚታይ ሳይሆን በየቀኑ የሚከፈል ከፍተኛ የኢኮኖሚ ዋጋ ነው። ሀገራችን በየዓመቱ በቢሊዮን የሚቆጠሩ ዶላሮችን ወደብ ኪራይ ክፍያ ታወጣለች።
በዚህም የትራንስፖርትና የሎጂስቲክስ ወጪ ከፍተኛ በመሆኑ የኢትዮጵያ ምርቶች በዓለም አቀፍ ገበያ ተወዳዳሪ እንዳይሆኑ ያደርጋል፤ የጥሬ ዕቃዎች በፍጥነት አለመድረስና የወደብ መጨናነቅ የኢንዱስትሪ ፓርኮችንና የአምራች ዘርፉን ምርታማነት ይገድባል።
የባሕር በር ተፈጥሯዊ መብታችንን ለማረጋገጥ የምናደርገው ጉዞ እና የግብፅና የሻዕቢያን እኩይ ሴራ ማምከን፣ የዚህ ትውልድ የሁለተኛው ትውልድ አርበኝነት ዋነኛ አጀንዳ ነው።
ታሪካዊ ጠላቶቻችን ኢትዮጵያን ለማዳከም፣ በኢኮኖሚ አረንቋ ውስጥ ለማስቀረት እና የቀጣናው ሀይል ሆና እንዳትወጣ ሌሊትና ቀን በሴራ ሲደክሙ ይኖራሉ።
ይህንን የተደቀነብንን አደጋ ለማክሸፍ መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ውስጣዊ ልዩነቶቹን ወደ ጎን በመተው እንደ አንድ ልብ መካሪ፣ እንደ አንድ ቃል ተናጋሪ ሆኖ ከሀገሩ ጎን ሊቆም ይገባል።
የኢትዮጵያ የባሕር በር ጥያቄ ከጎረቤት ሀገራት ጋር የሚደረግ የጉልበት ወይም የኃይል አማራጭ ሳይሆን፣ በሕጋዊና ሰላማዊ መንገድ የጋራ እድገትን ማዕከል ያደረገ ነው።
ኢትዮጵያ ያላትን ሰፊ የሕዝብ ቁጥር፣ የታዳሽ ኃይል፣ የግብርና ምርቶችና የትራንስፖርት መሠረተ ልማት ከጎረቤት ሀገራት የወደብ ሀብት ጋር በማጣመር የጋራ ብልጽግናን መፍጠር ይቻላል።
በምስራቅ አፍሪካ በነፃ የንግድ ቀጣና እና በቀጣናዊ ትስስር በኩል የኢኮኖሚ ድንበሮችን በማጥበብ የወደብ አጠቃቀምን ማቃለል ይቻላል።
ለኢትዮጵያ የታሪክ አደራና የወደፊት ግዴታዋን ለማሳካት በሚደረገው ጉዞ ውስጥ የባሕር በር ማግኘት የሕልውና እና የልማት ጥያቄ ነው።
ይህ ጥያቄ በሰላማዊ ድርድር፣ በዲፕሎማሲያዊ ጥረት፣ በሕጋዊ መንገድና በጋራ እድገት መርህ ላይ ተመስርቶ የሚመለስ ሲሆን፣ በቀጣናው ያሉ ሀገራትም የኢትዮጵያን የባሕር በር ፍላጎት እንደ ስጋት ሳይሆን ለጋራ ልማትና ሰላም እንደታደለ ትልቅ ዕድል በመቁጠር በውይይት ላይ የተመሠረተ ዘላቂ መፍትሔ ማምጣት ይጠበቅባቸዋል።
እስከዚያው ግን ኢትዮጵያውያን የጠላቶቻቸውን ሴራ በማንቃት፣ በብሔራዊ ዓላማችን ዙሪያ በመሰለፍ የሁለተኛው ትውልድ አርበኝነት ግዴታችንን እንወጣለን።
#ትልቅ_ሀገር #ትልቅ_ሕዝብ #ታላቅ_ርዕይ
በአድማሱ አራጋው
#redseaaccess #ethiopiaseagate #redseageopolitics #hornofafrica #ethiopianunity

#jimmauniversity
ጅማ ዩኒቨርሲቲ በ2019 ዓ.ም ወደ ተቋሙ የተመደቡ የመጀመሪያ ዓመት (Freshman) ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ጥቅምት 04 እና 05/2019 ዓ.ም መሆኑን አሳውቋል።
የምዝገባ ቦታ፦
● የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች በቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት
● የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች በግብርና ኮሌጅ እና በቬተርናሪ ሕክምና ኮሌጅ
ለምዝገባ የሚያስፈልጉ
● የ12ኛ ክፍል ሰርተፊኬት ዋናውና ኮፒው
● የ12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው
● አራት ፓስፖርት መጠን ፎቶግራፍ
● የመኝታ አልባሳት እና የስፖርት ልብስ
ወደ ተቋሙ የተመደቡ የሪሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ በሌላ ማስታወቂያ ወደፊት ይገለጻል ተብሏል።

አዲስ ሕይወት ጄኔራል ሆስፒታል ለላንቃ እና ከንፈር መሰንጠቅ የሚሰጠውን ነፃ ህክምና ወደ ሙሉ ማዕቀፍ አሳደገ
አዲስ ሕይወት ጄኔራል ሆስፒታል ከዓለም አቀፉ 'ስማይል ትሬን' እና 'ሪስቶሪንግ ስማይል' ጋር በመተባበር የላንቃ እና የከንፈር መሰንጠቅ ችግር ላለባቸው ህፃናት ሲሰጥ የነበረውን ነፃ የቀዶ ጥገና አገልግሎት በማስፋት ሙሉ የሕክምና ማዕቀፍ መስጠት መጀመሩን አስታውቋል።
የዓለም የፈገግታ ቀንን አስመልክቶ ማዕከሉ ከቀዶ ሕክምናው በተጨማሪ የስነ-ምግብ፣ የአነጋገር ማስተካከያ፣ የጥርስ እና የአፍ ንፅህና እንዲሁም የስነ-ልቦና ድጋፍን ያካተተ ነፃ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን ገልጿል ።
የሆስፒታሉ ሜዲካል ዳይሬክተር ዶ/ር ሚካኤል ተስፋዬ ለብስራት ሬድዮ እንደተናገሩት፤ በተያዘው በጀት ዓመት ከ130 በላይ ለሚሆኑ ህፃናት የቀዶ ሕክምና እንዲሁም ለሌሎች በርካታ ህፃናት ተያያዥ የቴራፒ ህክምናዎችን ለመስጠት ታቅዷል።
ሪስቶሪንግ ስማይል' በበኩሉ በዘንድሮው ዓመት በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የሚገኙ 175 ህፃናትን ለይቶ ወደ ህክምና ለማምጣት እየሰራ መሆኑን የድርጅቱ ስራ አስኪያጅ አቶ ቢንያም መኮንን ለብስራት ሬድዮ ተናግረዋል።
የታካሚዎች እና የአጋዥ ቤተሰቦቻቸው ትራንስፖርት፣ ምግብ፣ ማረፊያ እና ሙሉ የሕክምና ወጪ በዓለም አቀፉ 'ስማይል ትሬን' ድርጅት ሙሉ በሙሉ የሚሸፈን መሆኑን የተናገሩት አቶ ቢኒያም፣ የላንቃ እና ከንፈር መሰንጠቅ ሙሉ በሙሉ በህክምና የሚስተካከል እንጂ እርግማን ባለመሆኑ፤ ህብረተሰቡ ችግሩ ያለባቸውን ህፃናት በመደበቅ ፈንታ ወደ ጤና ተቋማት በመውሰድ የነፃ ህክምናው ተጠቃሚ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል።
በሚኪያስ ፀሐዬ

10 ሺህ የቡና ሲኒዎች የተሰበሰቡበት ዝግጅት በአፍሪካ ድንቃ ድንቅ መዝገብ ሰፈረ
በኢትዮጵያ የቡና ታሪክና ባህልን ከቴክኖሎጂ ጋር በማቀናጀት 10 ሺህ ባህላዊ የቡና ሲኒዎች የተሰባሰቡበት ዝግጅት በአፍሪካ ድንቃ ድንቅ መዝገብ ማስፈሩ ተገለጸ።
ምስራቅ አፍሪካ ኢንተርቴመንት ከባህል እና ስፖርት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ያዘጋጀው ይህ መርሃ-ግብር፣ በልዩ ዲዛይን የተገነባ መሆኑ ተጠቅሷል።
በዝግጅቱ ላይ የተገኙት የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር የባህል እሴቶችና ሀገር በቀል እውቀቶች ልማት መሪ ሥራ አስፈጻሚ እስከዳር ግሩም እንዳስረዱት፣ የቡና ሥነ-ሥርዓት ለሽምግልና እና ለማኅበራዊ ግንኙነቶች የሚያገለግል ባህላዊ እሴት ነው።
ባህሉን በዓለም ደረጃ ለማስተዋወቅ እና የቱሪዝም አበርክቶውን ለማሳደግ በቀጣይ ተጨማሪ ሥራዎች እንደሚሠሩም ገልጸዋል።
የአፍሪካ ድንቃ ድንቅ መዝገብ ሥራ አስኪያጅ አሸናፊ ዓለሙ በበኩላቸው፣ ክንውኑ ሀገራዊ የቡና ከፍታን ከማሳየት ባለፈ ለአፍሪካ የባህልና ቱሪዝም ልማት ከፍተኛ ፋይዳ እንዳለው ተናግረዋል።
በአበረ ስሜነህ
#አሐዱ_ሬዲዮ_94

4 days ago
አዲሱ የድሬድዋ ከተማ ከንቲባ ማናቸው ?
የድሬዳዋ ከተማ ም/ ቤት አቶ አብዱላሂ አደምን የከተማዋ ከንቲባ በማድረግ ሾሟል። ለመሆኑ አዲሱ ከንቲባ ማናቸው ? ስለ ትምህርትና የስራ ጉዟቸውስ ምን ይታወቃል ?
በኤረር ከተማ ተወልደው ያደጉት አቶ አብዱላሂ የአንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በዚያው ኤረር እና በአዲስ አበባ አጠናቀዋል።
ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በሶሺዮሎጂና ሶሻል አንትሮፖሎጂ የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን አግኝተዋል። የማስተርስ ዲግሪያቸውን በቻይና በዓለምአቀፍ ግንኙነት መስክ አጠናቀዋል።
በስራ ዓለም ፦
- ከ2001 እስከ 2003 ዓ.ም. የኤረር ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ እና የኤረር ወረዳ ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ኃላፊ፣
- ከ2004 እስከ 2010 ዓ.ም ባለው ጊዜ በድሬዳዋ አስተዳደር የኢትዮጵያ ሶማሌ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢሶህዴፓ) ጽ/ቤት ዋና ኃላፊ፣
- ከ2011 ዓ.ም. ጀምሮ በሶማሊ ክልል በአደጋ ሥጋት ቢሮ፣ በከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ፣ በግብርና ቢሮና በትምህርት ቢሮ በአመራርነት ሰርተዋል።
ከንቲባ እስከሆኑበት እስከዛሬው ቀን ድረስ የሶማሊ ክልል ንግድና ትራንስፖርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ ሆነው አገልግለዋል።
የአማርኛ ፣ አፍ ሶማሊና የአፋን ኦሮሞ እንዲሁም የእንግሊዘኛ ቋንቋንዎችን አቀላጥፈው ይናገራሉ ተብሏል።
መስከረም 22 ቀን 2019 ዓ/ም
@tikvahethiopia አቶ ከድር ጁሀር የድሬዳዋ ከተማ ምክትል ከንቲባ ሆነው ተሾሙ። የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት አቶ ከድር ጁሀርን የአስተዳደሩ ምክትል ከንቲባ አድርጎ ሾሟል። ምክትል ከንቲባው በምክር ቤቱ ፊት ቃለ መሃላ ፈጽመዋል። አቶ ከድር ጁሀር ላለፉት ዓመታት ከተማዋን ከንቲባ ሆነው ሲመሩ ቆይተው በዛሬው ዕለት በአቶ አብዱላሂ አደን ተተክተዋል። መስከረም 22 ቀን 2019 ዓ/ም @tikvahethiopia

ሚሊዮኖችን ያስተሳሰረው የኢሬቻ በዓል እና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳው
*******************
የኢሬቻ በዓል ከጥልቅ መንፈሳዊ፣ ባህላዊ እና ማኅበራዊ ፋይዳው ባሻገር በሚሊዮኖችን በአንድነት አስተሳስሮ ከፍተኛ የኢኮኖሚ ንቅናቄ የሚፈጥር ሀገራዊ ሁነት ነው።
በየዓመቱ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ታዳሚዎችን የሚያስተናግደው ይህ ደማቅ በዓል፣ የኢትዮጵያን ማራኪ የብዝኃነት እሴት የሚያንጸባርቅ ከመሆኑም በላይ ለንግድ፣ ለሆቴል፣ ለትራንስፖርት እና ለቱሪዝም ዘርፎች ቀጥተኛ የኢኮኖሚ ማበልጸጊያ ጉልበት ሆኖ ያገለግላል።
በበዓሉ ዋዜማ እና በክብረ በዓሉ ዕለት የባህላዊ አልባሳት፣ ጌጣጌጦች እና የእጅ ጥበብ ምርቶች ገበያ ከፍተኛ ዕድገት ያሳያል።
የኢሬቻን ደማቅ ቀለማት የሚያንጸባርቁ አልባሳትን የሚያዘጋጁ ሸማኔዎች፣ ዲዛይነሮች፣ አነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ሰፊ የገበያ ዕድል ያገኛሉ።
በከተሞች የሚዘጋጁ ባዛሮች እና አውደ-ርዕዮች የሀገር ውስጥ ምርቶችን በስፋት በማስተዋወቅ የአምራቾችን እና የነጋዴዎችን ገቢ በከፍተኛ ደረጃ ያሳድጋሉ።
በአዲስ አበባ እና በቢሾፍቱ ከተሞች የሚገኙ ሆቴሎች፣ ሪዞርቶች፣ የእንግዳ ማረፊያዎች እና የኬተሪንግ ድርጅቶች የማስተናገድ አቅማቸው ሙሉ በሙሉ በመያዙ ምክንያት የሚሰበስቡት ገቢ በከፍተኛ ሁኔታ ይጨምራል።
ይህ ወቅታዊ የፍላጎት ዕድገት ለባለሀብቶች ከሚያስገኘው ትርፍ በላይ፣ ለበርካታ ዜጎች ጊዜያዊ እና ቋሚ የሥራ ዕድል በመፍጠር የማኅበረሰቡን የኑሮ ደረጃ ያሻሽላል።
በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ታዳሚዎች ከተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች እና ከውጭ ሀገር ወደ በዓሉ ቦታዎች በሚያደርጉት ጉዞ የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ዘርፉ ከፍተኛ ንቅናቄ ያሳያል።
የከተማ ውስጥ እና የረጅም ርቀት የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪዎች፣ ታክሲዎች እና የኪራይ ተሽከርካሪዎች ያለ እረፍት በመሥራት ከፍተኛ ገቢ ያገኛሉ።
ይህም ለትራንስፖርት ዘርፉ ሰፊ የገበያ ዕድል ከመፍጠሩ ባሻገር የሰዎች እና የንግድ ዕቃዎች እንቅስቃሴን በማፋጠን የኢኮኖሚውን የደም ሥር ያነቃቃል።
ከሁሉም በላይ ኢሬቻ ለኢትዮጵያ የቱሪዝም ኢንዱስትሪ እና ለገጽታ ግንባታ የሚጫወተው ሚና የጎላ ነው። በዓሉ የዳያስፖራ አባላትን እና የውጭ ሀገር ጎብኚዎችን በመሳብ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ ያስገኛል።
ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ደረጃ በብዝኃ-ባህል፣ በመቻቻል እና በሚሊዮኖች የሚታደሙባቸውን ሰላማዊ ሁነቶች በስኬት በማስተናገድ ረገድ ያላትን አቅም በተግባር የሚያስመሰክር ነው።
ኢሬቻ የባህል መገለጫ ብቻ ሳይሆን፣ ኢትዮጵያውያን በአንድነት ሲቆሙ የሚያመጡትን ዘርፈ-ብዙ የኢኮኖሚ እና የማኅበራዊ መስተጋብር ውጤት የሚያሳይ የጋራ አኩሪ ሀብታችን ነው።
በለሚ ታደሰ
#ትልቅ_ሀገር #ትልቅ_ሕዝብ #ታላቅ_ርዕይ
#ethiopia #irreechaa #culturaltourism #addisababa #bishoftu #diversity #culture

አሚጎስ እና አሸናፊ ግርማ ሶከር አካዳሚ የጋራ መግባቢያ ሰነድ ተፈራረሙ
#ethiopia | አሚጎስ እና በቀድሞ የኢትዮጵያ ታዋቂ የእግር ኳስ ተጫዋችና አሰልጣኝ አቶ አሸናፊ ግርማ የተቋቋመው አሸናፊ ግርማ ሶከር አካዳሚ፣ በጋራ ለመሥራት የሚያስችላቸውን የጋራ መግባቢያ ሰነድ ተፈራርመዋል።
ስምምነቱ በእግር ኳስ ዘርፍ ያሉ ተሳታፊዎችንና የኢትዮጵያ ዲያስፖራ ማኅበረሰብን አሚጎስ በሚሰጣቸው የቁጠባና የብድር አገልግሎቶች ተጠቃሚ ለማድረግ ያለመ የጋራ የሥራ ማዕቀፍን ያካትታል።
አቶ አሸናፊ ግርማ ነዋሪነቱን በካናዳ ካደረገ በኋላ በስሙ የተቋቋመውን ሶከር አካዳሚ በማስፋፋት፣ የእግር ኳስ ፍቅር ባላቸው ታዳጊዎች ላይ ትኩረት በማድረግ የአሰልጣኝነት ሙያውን ቀጥሏል።
በበኩሉ አሚጎስ ወጣቶችን በስፖርት ዘርፍ ለማበረታታት በእግር ኳስ መሣሪያዎች በመደገፍ ከ300 በላይ ታዳጊዎችን እያሰለጠነ መሆኑ ተገልጿል።
በሁለቱ ተቋማት መካከል በሚኖረው የጋራ የሥራ ትብብር የተለያዩ የስፖርትና የፋይናንስ አገልግሎቶችን በማገናኘት የዲያስፖራ ማኅበረሰቡ ከአሚጎስ የቁጠባና የብድር አገልግሎቶች ተጠቃሚ እንዲሆን ለማስቻል አሰልጣኝ አሸናፊ ግርማ በካናዳ የማስተባበር ሚና እንዲወጣ በስምምነቱ ተካቷል።
በፊርማ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ አሰልጣኝና የቀድሞ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ተጫዋች አቶ አሸናፊ ግርማ፣ አሚጎስ ይህንን ሥራ በጋራ እንዲሠሩ ዕድሉን በመስጠቱ ምስጋና አቅርበዋል።
አሰልጣኝ አሸናፊ ግርማ እንደገለጹት፣ ትብብሩ ኢትዮጵያን ናፍቀው በውጭ አገራት ለሚኖሩ የዲያስፖራ ማኅበረሰብ በሀገራቸው የቁጠባ፣ የብድርና የኢንቨስትመንት ዕድሎችን ለመጠቀም አማራጭ ይፈጥራል።
በፊርማ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ በማኅበር ወይም በግል ብድር መጠቀም ለሚፈልጉ ዲያስፖራዎች፣ እንዲሁም በተለያዩ የኢንቨስትመንት አማራጮች ለመሳተፍ ፍላጎት ላላቸው የአሚጎስ የፋይናንስ አገልግሎት አሰጣጥ መንገዶች ላይም ውይይት ተደርጓል።
በዚህም የሁለቱ ተቋማት ትብብር የስፖርት ልማትን ከዲያስፖራ ተሳትፎና ከፋይናንስ አገልግሎት ጋር በማጣመር ወጣቶችንና የዲያስፖራ ማኅበረሰቡን የሚያገናኝ የጋራ የሥራ ማዕቀፍ ለመፍጠር ያለመ መሆኑ ተገልጿል።
#amigos #ashenafigirma #sports #diaspora #finance #ethiopiansports #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

Comments