2 months ago
በአዲስ አበባ ስታዲየም :
የዊ ሻምፒዮንስ ( We Champions 2026 )
የስፖርት ፌስቲቫል እየተሰናዳ ነው
#ethiopia | የአርሰናል እግር ኳስ ክለብ ከ22 ዓመታት ረጅም የጥበቃ ጊዜ በኋላ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ዋንጫን ማሸነፉን አስመልክቶ፣ ይህንን ታሪካዊ ድል ለማክበር የተሰናዳውና በሀገራችን የመጀመሪያው ግዙፍ የስፖርት መድረክ የሆነው የዊ ሻምፒዮንስ 2026 ( We Champions 2026 ) የእግር ኳስ ፌስቲቫል በመጪው ግንቦት 29 ቀን 2018 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ስታዲየም በታላቅ ድምቀት እንደሚከናወን ተጠቁሟል።
በጎርደን ኢንተርቴይመንት አዘጋጅነት ለሚቀርበው ለዚህ ትልቅ ሁነት አዋሽ ባንክ በአፕክስ ኖብል ፕሮግራሙ አማካኝነት ዋነኛ ስፖንሰር በመሆን ድጋፍ እያደረገ ይገኛል።
ይህ ልዩ መርሃ ግብር የስፖርቱን ፍቅር፣ ታማኝነትን፣ ባህልን፣ መዝናኛንና ስፖርታዊ እሴቶችን በአንድ ላይ በማስተሳሰር ከ30 ሺህ በላይ የእግር ኳስ አፍቃሪያንን፣ የዓለም አቀፍ ስፖርት ተዋናዮችንና እውቅ ባለሙያዎችን በአንድ መድረክ ላይ የሚሰበስብ ሀገራዊ ፋይዳ ያለው የደስታ መግለጫ እንደሚሆን ይጠበቃል።
ዝግጅቱ ኢትዮጵያን በዓለም አቀፍ ደረጃ በበለጠ ለማስተዋወቅ መልካም አጋጣሚን የሚፈጥር ሲሆን፣ በዓለም ዙሪያ የሚገኙ የስፖርት መገናኛ ብዙኃንንና የዲጂታል ይዘት ፈጣሪዎችን ትኩረት በመሳብ የሀገሪቱን የቱሪዝም ፍሰት፣ የባህል ገጽታ እንዲሁም ትላልቅ ዓለም አቀፍ ኩነቶችን የማስተናገድ ብቃት በከፍተኛ ደረጃ እንደሚያሳድግ ታምኖበታል።
በዕለቱ ከሚታደሙት የክብር እንግዶች መካከል የቀድሞው የአርሰናልና የቱኒዥያ ብሔራዊ ቡድን ተከላካይ ራዲ ጃይዲ የሚገኝበት ሲሆን፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ተደራሽነትና ተፅዕኖ ካላቸው የእግር ኳስ ሚዲያ አንዱ የሆነው የኤኤፍቲቪ መስራቾችና ተወካዮችም በዝግጅቱ ላይ ለመሳተፍ ወደ አዲስ አበባ እንደሚመጡ መረጋገጡን በመግለጫው ላይ አስታውቀዋል።
ወደ ስታዲየም ለመግባት የሚያስችሉ የትኬት ሽያጮችን አስመልክቶ አዘጋጆቹ በሰጡት ማብራሪያ፣ መግቢያ ትኬቶችን ማግኘት የሚቻለው በአዋሽ ባንክ የአፕክስ ኖብል ፕሮግራም በኩል ብቻ መሆኑን ገልጸዋል።
የመዝናኛ ክፍሉን ይበልጥ ማራኪና ድምቅ ለማድረግ ከአስር በላይ ታዋቂና ወጣት የሙዚቃ አርቲስቶች የተጋበዙ ሲሆን፣ ከእነዚህም መካከል ታደለ ሮባ፣ ልጅ ሚካኤል (ፋፍ)፣ ሳሚ ዳን፣ አስማማው እሸቱ፣ ራሄል ጌቱ፣ ሮማን ማይክ፣ ዮሐንስ አፈወርቅ፣ ሚካ ያኖ፣ አማኑኤል የማነ፣ አዲስ ሙላት፣ እዩ ፀጋ እና ኩሉ ሱሌ ይገኙበታል።
የአዲስ አበባ ስታዲየም ከቀኑ 6:00 ሰዓት ጀምሮ ለታዳሚዎች ክፍት የሚሆን በመሆኑ፣ ተመልካቾች በጊዜ በመገኘት ቦታቸውን እንዲይዙ አዘጋጆቹ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።
#wechampions2026 #arsenal #awashbank #apexnoble #gordonentertainment #aftv #radhijaidi #footballfestival #ethiopiantourism #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

የአርሰናል የፕሪሚየር ሊግ ድል በአዲስ አበባ "WE CHAMPIONS 2026" ታሪካዊ ፌስቲቫል ሊካሄድ ነው
#fastmereja | አርሰናል ከ22 ዓመታት በኋላ ያነሳውን የፕሪሚየር ሊግ ዋንጫ ለማክበር ግንቦት 29/2018 በአዲስ አበባ ስታዲየም ታሪካዊ የእግር ኳስና የመዝናኛ ፌስቲቫል ይካሄዳል። በቫርደስ ኢንተርቴይመንት የተዘጋጀውና በአዋሽ ባንክ (አዋሽብር ፕሮ) ዋና ስፖንሰርነት የሚከናወነው ይህ ዝግጅት፣ ከ30 ሺህ በላይ ታዳሚዎችን እና ዓለም አቀፍ እንግዶችን በአንድ ላይ ያሰባስባል።
ዝግጅቱ የክለቡን ድል ከመዘከር ባለፈ፣ ኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ ዝግጅቶችን የማስተናገድ አቅሟን ለዓለም የምታሳይበት መድረክ እንደሚሆን ይጠበቃል። በስፍራውም ታዋቂ ድምፃውያን እና የስፖርት ቤተሰቦች ይታደማሉ።
በክስተቱ ላይ የቀድሞው የአርሰናል እና የኮትዲቯር ብሔራዊ ቡድን ተጫዋች ኢማኑኤል ኢቡዌ በልዩ እንግድነት ይገኛል። ከእርሱ በተጨማሪ በዓለም ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ ካላቸው የእግር ኳስ ሚዲያዎች አንዱ የሆነው AFTV ልዑካን ቡድን ወደ ኢትዮጵያ ይመጣል። በቡድኑ ውስጥ፡
ሊ ዳጅስ (Lee Judges) – አቅራቢ (ዩናይትድ ኪንግደም)
ሴሲል ጂ ቶማስ (Cecil Jee Thomas) – አቅራቢ (ዩናይትድ ኪንግደም)
ጀረሚ (Jeremy) – ዲጂታል ይዘት ፈጣሪ (ደቡብ አፍሪካ) ይገኙበታል።
በዚህ ዝግጀት ላይ ከ 10 በላይ የሆኑ እውቅ እና ወጣት ኢትዮጵያዊ ድምፃዊያን የሙዚቃ ስራቸው እንደሚያቀረቡ ተገልጾ ከነዚህም መካከል ታደለ ሮባ ፣ ልጅ ሚካኤል (ፋፍ) ፣ ሳሚ ዳን ፣ አስጌ ዴንዳሾ ፣ ራሄል ጌቱ ፣ ሮቤል ሚዲቅሳ ፣ ዮ ማሪዮስ ፣ ሚክ ዋን ፣ አማኑኤል የማነ ፣ አዲስ ሙላት እንዲሁም እውቁ የዳስሆል/የአፍሮቢትስ ሙዚቃ ተጫዋቹ ፍራንኪዬ ዲ እና ሌሎችም ድምፃዊያን የሙዚቃ ስራዎቻቸውን ያቀርባሉ::
የዝግጅቱ ብቸኛ የትኬት መሸጫ መድረክ "አዋሽብር ፕሮ" ነው። ደጋፊዎች ትኬታቸውን በሚከተሉት መንገዶች ማግኘት ይችላሉ፦
በአዋሽብር ፕሮ አፕሊኬሽን
በአዋሽ ባንክ ቅርንጫፎች (ከ1,000 በላይ ቅርንጫፎች)
በአዋሽ ብር ፕሮ ኤጀንቶች
በአዲስ አበባ ስታዲየም በተዘጋጁ ጊዜያዊ መሸጫ ጣቢያዎች (ከግንቦት 25 እስከ ግንቦት 29)
ከግዢው ጋር በተያያዘ፣ ትኬታቸውን በቅድሚያ ለሚገዙ ደጋፊዎች የ"WE CHAMPIONS 2026" ይፋዊ ማሊያ የማግኘት ዕድል ተመቻችቷል።

ዝነኛው AFTV (Arsenal Fan TV) ወደ ኢትዮጵያ ሊመጣ ነው!
#ethiopia | የዓለማችን ትልቁና ተፅዕኖ ፈጣሪው የክለብ ደጋፊዎች ሚዲያ AFTV፣ በኢትዮጵያ የሚገኘውን እጅግ በርካታ የአርሰናል ደጋፊ ማህበረሰብ ለመጎብኘትና ልዩ ዝግጅቶችን ለማድረግ ጉዞውን ወደ አዲስ አበባ ሊያደርግ መሆኑ ታውቋል።
ይህ ጉብኝት በኢትዮጵያ ስፖርታዊ ሚዲያና በደጋፊዎች መካከል አዲስ መነቃቃትን ይፈጥራል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን፣ የለንደኑ ክለብ በሀገራችን ያለውን ታላቅ ተወዳጅነት ለዓለም ይበልጥ የሚያሳይ ትልቅ አጋጣሚ ይሆናል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu
#aftv #arsenalfantv #arsenalethiopia #coyg #addisababa #gooners #ethiopiangooners #aftvinethiopia

Sponsored by
Surafel
Comments