(ዘ-ሐበሻ ስፖርት) ፈረንሳያዊው ተከላካይ ኢብራሂማ ኮናቴ ወደ ስፔኑ ታላቅ ክለብ ሪያል ማድሪድ የሚያደርገው ዝውውር መገባደጃው ላይ መድረሱን ምንጮች አረጋገጡ። ባለፉት 48 ሰዓታት ውስጥ በተደረጉት የድርድር ሒደቶች ከፍተኛ መሻሻል የታየ ሲሆን፣ በቅርቡ 27ኛ ዓመት የልደት በዓሉን ያከበረው ኮናቴ በአራት ዓመት ኮንትራት እና በፊርማ ክፍያ ጉዳዮች ላይ ከስምምነት ለመድረስ ጥቂት ዝርዝር ጉዳዮች ብቻ ቀርተውታል።
የማድሪድ ኃላፊዎች በፓሪስ የተወለደውን ይህንን ተከላካይ ለማስፈረም ከወራት በፊት ጀምሮ ፍላጎት ያሳዩ ቢሆንም፣ የተጫዋቹ ቀዳሚ ምርጫ ግን በሊቨርፑል መቆየት ነበር። ይሁን እንጂ ከክለቡ ጋር አዲስ ኮንትራት ለመፈራረም ባለመቻሉ፣ እ.ኤ.አ. በ2021 ከሌይፕዚግ ተነስቶ ያቀናበትን አንፊልድን በነጻ ዝውውር ለመልቀቅ ተገዷል።
ኮናቴ ሊቨርፑልን እንደሚለቅ በተረጋገጠበት ወቅት ሪያል ማድሪድ ፈጣን ጥያቄ በማቅረብ ቀዳሚው ቢሆንም፣ ባየር ሙኒክን፣ ባርሴሎናን እና የሳውዲ ክለቦችን ጨምሮ ሌሎች በርካታ ክለቦች የተከላካዩን ፊርማ ለማግኘት ጥረት አድርገው እንደነበር ምንጮች ጠቁመዋል።
ይህ ዝውውር ዕውን የሚሆን ከሆነ፣ ኮናቴ በሳንቲያጎ በርናባው ከሚገኙት የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን አጋሮቹ ኪሊያን ምባፔ፣ ኦሬልየን ቹአሜኒ፣ ኤድዋርዶ ካማቪንጋ እና ፈርላንድ ሜንዲ ጋር ዳግም ይገናኛል። ተጫዋቹ በዓለማችን ትልቁን ክለብ ለመቀላቀል መቃረቡ እጅግ እንዳስደሰተው የተገለጸ ሲሆን፣ በቀጣዩ ሳምንት ከፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን ጋር ወደ ዓለም ዋንጫው ከማምራቱ በፊት የዝውውር ሒደቱ ሙሉ በሙሉ ተጠናቆ ማየት ይፈልጋል።

2 days ago