የአሜሪካ የተወካዮች ምክር ቤት የትራምፕን የጦርነት ስልጣን ለመገደብ ድምፅ ሰጡ
የአሜሪካ የተወካዮች ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በኢራን ላይ ተጨማሪ የወታደራዊ እርምጃ እንዳይወስዱ የሚያግድ የውሳኔ ሃሳብ አሳልፈዋል፡፡
በየካቲት ወር የጀመረውን ጦርነት በአደባባይ በመቃወም አራት ሪፐብሊካኖች ከዲሞክራቶች ጋር ከተቀላቀሉ በኋላ፤ የውሳኔ ሃሳቡ በ2መቶ15 ለ 2መቶ8 ድምፅ ሊጸድቅ ችሏል።
ይህ የተወካዮች ምክር ቤት በትራምፕ የጦርነት ስልጣን ላይ ገደብ ለመጣል የሞከረው ለአራተኛ ጊዜ ሲሆን፤ ተቺዎች ፕሬዝዳንቱ የኮንግረሱን ፈቃድ ሳያገኙ እርምጃ እየወሰዱ ነው በማለት ይወቅሳሉ።
የምክር ቤቱ የውሳኔ ሃሳብ አሁንም በሪፐብሊካኖች በሚመራው የአሜሪካ ሴኔት መፅደቅ ይኖርበታል፤ይሁን እንጂ ሴኔቱ ቢቀበለው እንኳ እርምጃው በኢራን ላይ የሚሰነዘረውን ወታደራዊ እንቅስቃሴ ሙሉ በሙሉ ለመግታት መቻሉ አጠራጣሪ ነው፡፡
ውሳኔው ከዚህ ቀደም ሰባት ጊዜ ሳይሳካ ቀርቶ ባለፈው ግንቦት ወር ሴኔቱ መሰል የውሳኔ ሃሳብን ያራመደ ቢሆንም እስካሁን ሙሉ ድምፅ ለመስጠት ወደ መድረክ አላመጣውም።
እሮብ ዕለት የተካሄደው ድምፅ በትራምፕ እና ሪፐብሊካን ፓርቲ ውስጥ ያለውን ልዩነት የሚያሳይ የቅርብ ጊዜ ምልክት ነው ፡፡
ይህ የሆነው ደግሞ በኮንግረስ ውስጥ ባሉ ወግ አጥባቂዎች ተቃውሞ ምክንያት አስተዳደሩ ለፖለቲካ አጋሮቹ ሊመድበው የነበረውን የ1.8 ቢሊየን ዶላር "ፀረ-የጦር መሣሪያ ታጣቂነት" ፈንድ ዕቅዱን ለመሰረዝ በተገደደ በጥቂት ቀናት ውስጥ ነው።
በተወካዮች ምክር ቤት የሚገኙ ቶማስ ማሲ፣ ብሪያን ፊትዝፓትሪክ፣ ቶም ባሬት እና ዋረን ዴቪድሰን የተባሉ ሪፐብሊካኖች ከዲሞክራቶች ጋር በመተባበር ረቡዕ ዕለት የቀረበውን የውሳኔ ሃሳብ አሳልፈዋል፡፡
በተጨማሪም ከዚህ ቀደም መሰል እርምጃዎችን ተቃውመው የነበሩት የሜይን ግዛት ዲሞክራት ጃሬድ ጎልደን በዚህ ጊዜ ድጋፋቸውን ሰጥተዋል።
ከሚቺጋን የመጡት ሪፐብሊካን ቶም ባሬትበበኩላቸው "ጦርነት የሚያውጀው ኮንግረስ ብቻ ነው፤ ይህ ደግሞ በእርግጥ ልንጠብቀው የሚገባ ጉዳይ ነው" ብለዋል።
በዚህ ድምፅ አሰጣጥ ምክንያት ከትራምፕ ሊሰነዘርባቸው ስለሚችለው የአጸፋ እርምጃ ተጠይቀው ሲመልሱ፡ "ትክክል ነው ብዬ ላመንኩበት ነገር በህሊናዬ ነው ድምፅ የሰጠሁት እናም የሚመጣውን ማንኛውንም ነገር ለመቀበል ዝግጁ ነኝ" ብለዋል።
በተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ጉዳይ ኮሚቴ መሪ የሆኑት ዲሞክራቱ ግሬገሪ ሚክስ፣ የተሰጠውን ድምፅ "በፕሬዝዳንት ትራምፕ ህገ-ወጥ እና ከፍተኛ ኪሳራ እያስከተለ ባለው የኢራን ጦርነት ላይ የተሰነዘረ ጠንካራ የሁለቱ ፓርቲዎች ተግሳጽ እና ጦርነቱን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለማቆም የተነገደ የመጀመሪያው እርምጃ ነው" ሲሉ ገልጸውታል።
ሚክስ አክለውም ትራምፕ በሀገር ውስጥ የነዳጅ ዋጋ እንዲንር ከማድረጋቸው እና ለኢራን የኒውክሌር መርሃ ግብር ዲፕሎማሲያዊ መፍትሄ የመፈለጉን ሂደት ይበልጥ አስቸጋሪ ከማድረጋቸው ባለፈ የጦርነቱን የተቀመጡ ግቦች ማሳካት አልቻሉም ብለዋል።
የውሳኔ ሃሳቡን በጋራ ያዘጋጁት ሚክስ "የዚህ ውሳኔ መጽደቅ ትልቅ የማዕዘን ድንጋይ ነው ቁጥራቸው ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የመጣ ሪፐብሊካኖች በመካከለኛው ምስራቅ ሌላ ማብቂያ የሌለው ጦርነት የማይፈልጉትን የመራጮቻቸውን ድምፅ እየሰሙ ነው" ብለዋል።
ዩናይትድ ስቴትስ እና እስራኤል በየካቲት 28 በኢራን ላይ ጥቃት መሰንዘራቸው የሚታወቁ ሲሆን ኢራንም በእስራኤል እና በባህረ ሰላጤው ለሚገኙ የአሜሪካ አጋር ሀገራት ላይ ጥቃት በመሰንዘር ምላሽ የሰጠች ሲሆን ለአለም አቀፍ የመርከብ ትራንስፖርት ወሳኝ የውሃ መስመር የሆነውን የሆርሙዝ ወሽመጥ በውጤታማነት ዘግታለች።

2 months ago