የተሽከርካሪ መስኮት በመስበር የስርቆት ወንጀል የፈጸመ ተከሳሽ በ7 ዓመት ከ9 ወር እስራት እንዲቀጣ ተወሰነበት፡፡
እንዳልካቸው ጣሰው የተባለው ተከሳሽ የወንጀል ድርጊቱን የፈፀመው መጋቢት 29 ቀን 2018 ዓ/ም ከቀኑ 7:00 ሠዓት በየካ ክ/ከተማ ወረዳ 1 ጨፌ ኳስ ሜዳ ከሚባል ስፍራ ነው፡፡
ተከሳሹ በተጠቀሰው ዕለትና ቦታ ንብረትነቱ የቅዱስ ጊዮርጊስ እግር ኳስ ክለብ የሆነውን የሠሌዳ ቁጥር ኮድ 2A-40-5-29 አ/አ ዶልፊን ተሽከርካሪ መንገድ ዳር ባቆሙበት ወቅት የተሽከርካሪያቸውን መስኮት በመስበር 4 የተለያዩ ሞዴል ያላቸውን ስማርት ሞባይል ስልኮችን ሰርቆ ይሰወራል።
የግል ተበዳዮች የወንጀሉን መፈፀም በየካ ክ/ከተማ ፖሊስ ዋና መምሪያ ለፈረንሳይ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ በማሳወቃቸው ፖሊስ ተጠርጣሪውን አፈላልጎ በመያዝ ባከናወነው የወንጀል ምርመራ ተግባር አራቱን ስልኮች በ25 ሺ ብር በመሸጥ በአካውንቱ እንዳስላከ በማረጋገጥ ብሩን በኤግዚቢትነት በመያዝ የምርመራ መዝገቡን ለአቃቤ ህግ በማቅረብ ክስ እንዲመሰረትም አድርጓል፡፡
የክስ ሂደቱን ሲከታተል የቆየው በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የካ ምድብ አንደኛ ወንጀል ችሎት ተከሳሽ እንዳልካቸው ጣሰው በፈፀመው የወንጀል ድርጊት ጥፋተኛ መሆኑን በማረጋገጡ በ7 ዓመት ከ9 ወር እስራት እንዲቀጣ ወስኖበታል።
ተሽከርካሪን ደህንነቱ ባልተጠበቀ ቦታ ማቆም ለመሰል ወንጀል ተጋላጭ የሚያደርግ መሆኑን ያስታወቀው የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አሽከርካሪዎች የወንጀል ሰለባ ከመሆናቸው በፊት ተገቢውን ጥንቃቄ ሊያደርጉ እንደሚገባም መልዕክቱን አስተላልፏል፡፡
Addis Ababa police

20 days ago