የንግድ ባንክ ሰራተኛዋን በአሰቃቂ ሁኔታ ገድሎ የተሰወረው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለ
#ethiopia | በሰንዳፋ በኬ ከተማ ነዋሪ እና በአሌልቱ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ ሰራተኛ የነበሩትን ወይዘሮ አዳነች ኩምሳን ህይወት ካለፈው ታህሳስ ወር ጀምሮ በአሰቃቂ ሁኔታ በመቅጠፍ ሲፈለግ የነበረው ተጠርጣሪ ፀጋዬ አሳልፈው በደብረ ብርሃን ከተማ ተያዘ።
ግለሰቡ ግድያውን የፈጸመው ታህሳስ 6 ቀን 2018 ዓ.ም ምሽት ላይ ከሟች ጋር በሆቴል ውስጥ ምግብ ሲመገቡ በተፈጠረ አለመግባባት መሆኑ ተገልጿል።
ሟች ተጠርጣሪውን ትታ በመሄዷ ምክንያት ተከትሏት በመሄድ መኪና ውስጥ ካስገባት በኋላ ጎማጣ ተብሎ በሚጠራው ስፍራ በሽጉጥ በመተኮስ ህይወቷ እንዲያልፍ ማድረጉ በፖሊስ የምርመራ መዝገብ ተመልክቷል።
ወንጀሉን ከፈጸመ በኋላ አስክሬኗን ጥሎ በመሰወሩ የሟች አካል በዱር አራዊት ተበልቶ ጭንቅላቷ ብቻ ሊገኝ ችሏል።
ተጠርጣሪው ግድያውን የፈጸመበትን መኪና እና መሳሪያ አሌልቱ ከተማ ውስጥ ጥሎ የተሰወረ ቢሆንም ፖሊስ በመኪናው ውስጥ ባገኘው የደም ዱካ እና በሽጉጡ አማካኝነት ክትትል ሲያደርግ ቆይቷል።
የፌዴራል ፖሊስ ከብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት እና ከሌሎች የፀጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት ባደረገው ኦፕሬሽን ግለሰቡን በቁጥጥር ስር ለማዋል ተችሏል።
ተጠርጣሪው በደብረ ብርሃን፣ በከሚሴ፣ በሸዋ ሮቢትና በአጣዬ ከተሞች ውስጥ የተለያዩ የሐሰት መታወቂያዎችን በመጠቀም እንደ ሰላማዊ ሰው ሲንቀሳቀስ እንደነበር ተደርሶበታል።
ፖሊስ በአሁኑ ወቅት በተጠርጣሪው ላይ ጥብቅ ምርመራ እያደረገ የሚገኝ ሲሆን ወንጀል ፈጽሞ ከህግ ማምለጥ እንደማይቻል አስታውቋል።
ለተጠርጣሪው መያዝ ትብብር ላደረጉ አካላትም ምስጋና ቀርቧል።
#justice #police #crime #federalpolice #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

5 months ago