በታክሲ መያዣ ተርሚናል ከኪስ ውስጥ ሞባይል የሰረቀው ተጠርጣሪ ፈጣን ችሎት ቀርቦ በእስራት ተቀጣ፡፡
የወንጀል ድርጊቱ የተፈፀመው ግንቦት 26 ቀን 2018 ዓ/ም በአራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 9 ልዩ ቦታው ቅድስት ሥላሴ የመገናኛ ታክሲ መያዣ ቦታ ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ነው፡፡
መትክል ሀብቱ የተባለው ተከሳሽ በተጠቀሰው ቦታ ላይ የታክሲ ትራንስፖርት አገልግሎት በመጠቀም ላይ ከነበሩ ግለሰብ ኪስ ውስጥ በመግባት የዋጋ ግምቱ 28 ሺህ ብር የሚያወጣ ሳምሰንግ ሞባይል ስልክ ሲሰርቅ በአካባቢው በነበሩ ትራንስፖርት ተጠቃሚዎችና በፖሊስ አባላት በቁጥጥር ስር ሊውል ችሏል፡፡
ተከሳሹ በቁጥጥር ስር ከዋለ በኋላ በአራዳ ክ/ከተማ ፖሊስ ዋና መምሪያ የአራት ኪሎ ፖሊስ መምሪያ ተገቢውን የሰውና የሰነድ ማስረጃ በማጠናቀርና መዝገቡን በማደራጀት ለዐ/ህግ አቅርቧል፡፡
የወንጀል ምርመራ መዝገቡን ሲከታተል የቆየው በፌደራሉ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ 3ኛ ወንጀል ፈጣን ችሎት ሰኔ 2 ቀን 2018 ዓ/ም ውሎው ተከሳሽን ያስተምራል፣ ሌሎች ወንጀል ፈፃሚዎችን ያስጠነቅቃል ሲል በ1 ዓመት ከ4 ወር እስራት እንዲቀጣ ወስኖበታል፡፡
ህብረተሰቡ ወንጀል ፈፃሚዎችን በቁጥጥር ስር በማዋል ጭምር ወንጀል ጠል መሆኑን እያስመስከረ መምጣቱ የሚያስመሰግን መሆኑን የገለፀው የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ መሰል ድርጊቶች ሲያጋጥሙም በአቅራቢያ ለሚገኝ ፖሊስ ማሳወቅ እንደሚገባም መልዕክቱን አስተላልፏል፡፡
Addis Ababa police

3 days ago